Telegram Web Link
ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ | ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ
በግዮን ሆቴል እስከ ሚያዚያ 13

የመግቢያ ትኬትዎን ግዮን ሆቴል በር ላይ ያገኙታል።
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
አቤቱ አንተን የሚመስል ማነው?

“መኑ ይመስለከ፡ እምነ አማልክት እግዚኦ፡ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ፡ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኀይለከ፡ ወአድኀንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ ሖርከ ውስተ ሲኦል፡ ወአዕረገ ጼዋ፡ እምህየ ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኀከነ፡፡ በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ፡ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል፡ ቡሩክ አንተ እግዚኦ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ፡፡” (ሥርዓተ ቅዳሴ)

አቤቱ ፈጣሪያችን፡ መድኀኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፤ “አማልክት” ከተባሉ፡ አማልክት ከሆኑባቸው ከእነ ዜውስ፡ ከእነ አርጤምስ አንተን የሚያህል፡ አንተን የሚተካከል ማነው? አማልክት ከሆኑብን ከአምሮት፤ ከስስት አንተን አንተን የሚተካከል እውነተኛውን ደስታ መስጠት የሚችል ማነው? እኒህ ሁሉ አማልክት ሕዝብህን ከክፉው እና ከክፋት ማዳን አይችሉምና፤ ሕዝብህን ከክፉ በማዳንም ድንቅን አላደረጉምና፤ እንዲያውም ሕዝብህን ወደ ሞት ይወስዳሉና፡፡

አንተ ግን በከበረች ኀይልህ፡ እኛን ልታከብር፡ እኛ ከገባንበት ደይን (ሲኦል) ለማውጣት፡ ወደ ሲኦል ሄድኽ፡፡ እኛን ለመፈለግ በፍቅርህ ብዛት ወደ ምድር መጣህ፡፡ ፍቅርህ እውነተኛ ናትና “ወደ ምድር መጣሁላቸው፤ እሱ ይብቃቸው” ብለህ ፍቅርህን ሳትቆጥር፤ በደላችን ከምድር በታች (ሲኦል) ወስዳናለችና፡ እዚያም ሄድኽ፡፡ ክቡር እና ልዑል ለሆነ አባትህ ምርኮን ማረክህ፤ እኛን ወደ እርሱ አቀረብከን፡፡ እኛን ከከፋችው ቦታ አወጣኸን፡፡ ለዘለዓለም የሚሆን ነጻነትን (ጸጋን) ዳግመኛ ሰጠኸን፡፡ ጥንት የሰጠኸንን ነጻነት አንተን ላለመውደድ፤ ሕግህንም ላለማድረግ በጥመት ተጠቅመንበት ነበርና፡፡ አሁን ግን ወደን፡ ፈቅደን ለአንተ እንድንገዛ ከሰይጣን ባርነት፤ ያንተን ወደምትመስል ነጻነት መለስከን፡፡ ታዲያ እኛ ምን ብለን፡ ምን አድርገን እንመልስልህ? “የቡሩክ አብ ልጁ፡ ቡሩክ ወልድ” ብለን እናመስግንህ እንጂ፡፡ “እኛን ክፉ ከተባለው ሁሉ ጠብቀን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ “እኛን ከራሳችንም ጠብቀን፤ አድነን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ አንተ መጥተህ (ሰው ሆነህ) አድነኸናልና፡፡ አሁንም በመምህራን ትምህርት፤ በካህናት መሥዋዕት፤ በምዕመናን ጸሎት መጥተህ ታድነናለኽና፡፡ አቤቱ ከአማልክት አንተን የሚመስል ማነው? አቤቱ ማረን!

በቴሌግራም እንገናኝ - http://www.tg-me.com/Micah_Mikias
በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡
ቅዱስ አውጉስጢን
".......እግዚአብሔርን ቃል ወደ ምድር ይወርድ ዘንድ ከድንግል ማርያም ሰው ይሆን ዘንድ በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ በበረት ውስጥ ይጣል ዘንድ ከሴት ልጅ ጡቶች ወተትን ይጠጣ ዘንድ ምን አተጋው? ለእኛ ለጠፋናው አይደለምን?"

ሃይማኖተ አበው ንባብና ትርጓሜው፤ ዘቅዱስ እለእስክንድሮስ ፲፮÷፪
2024/06/01 14:35:33
Back to Top
HTML Embed Code: