Telegram Web Link
Channel photo updated
❤️ አስገራሚ ታሪክ ❤️

አንዱ ሚስቱን ይመታታል፤ በአጋጣሚ ሊገድላት ሳያስብ በእጁ ትሞትበታለች። ጉዳዩ ይፋ ወጥቶ ዕዳ እንዳይኾንበት ምን
ማድረግ እንዳለበት ያስባል። አስቦ አሰላስሎ በስተመጨረሻም
አንድ ሀሳብ መጣለት። እርሱም ወደሰፈራቸው አዋቂ ነኝ ባይ ሰው
ጋር መሄድ ነበር። ታዲያ ይሄ አዋቂ ተብዬ ሰውም መፍትሄ
የሚለውን ሀሳብ እንዲህ ሲል ይመክረዋል፦
ደጅህ ላይ ተቀምጥና ቆንጆ ወጣት ሲያልፍ ካየህ "አንዳች
የምታግዘኝ ነገር አለ" በለውና ወደ ቤትህ አስገባው።ከዚያም
ግደለውና ከባለቤትህ እሬሳ ጋር አጠገብ ለአጠገብ አጋድመው።
የርሷን ቤተሰቦች ጥራና "ከዚህ ወጣት ጋር ሲያመነዝሩ ስመለከት
እራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ እርምጃ ስወስድባቸው በእጄ ሞቱ" ብለህ ንገራቸው አለው።
አባ ውራውም መላ ነው ተብሎ የተነገረውን ተቀብሎ ደጃፉ ላይ
ሄዶ ቁጭ ብሎ መጠባበቅ ይጀምራል። ብዙም ሳይቆይ አንድ
ወጣት በአጠገቡ ሲያልፍ ተመለከተና "ወንድም አንዴ
ላስቸግርህ? የሆነች ነገር እንድታግዘኝ ፈልጌህ ነበር" ብሎ
አስማምቶ ወደ ቤት ያስገባዋል። እንደተመከረውም ይገድለውና
ከሚስቱ ጀነዛ አጠገብ ያጋድመዋል።
የሚስቱ ቤተዘመዶች ሲመጡም በዝሙት ላይ አግኝቷቸው ራሱን
መቆጣጠር አቅቶት እርምጃ እንደወሰደባቸው ይነግራቸዋል።
እነርሱም ጥፋተኛ ሳያደርጉት ምክኒያቱን ይረዱትና ይተዉታል።
ይሄንን የማምለጫ ዘዴ ነግሮት የነበረው ሰውዬ ገዳዩ ከምን
እንደደረሰ ሊጠይቀው ቤቱ ይከሰታል። ገዳዩ ሰውዬም የመከረውን
እንዳደረገና እንደተሳካለት በኩራትና በምስጋና ይነግረዋል። እስኪ
የገደልከውን ልጅ አሳየኝ ብሎ አዋቂ ተብዬው ይጠይቀዋል።
ገዳዩ ወስዶ ሲያሳየውም
ለካስ የተገደለው የራሱ የአዋቂ ነኝ ባዩ ልጅ ኖሯል! በሳሉት
ቢለዋ
መቆረጥ ይሉሃል እንደዚህ ነው!
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ ዐ) እንዲህ ይላሉ፦
ለተንኮል ሰይፉን የሳለ እራሱ ይቆረጥበታል። ለወንድሙ ጉድጓድ
የቆፈረ ራሱ ይገባበታል። የሌሎችን ነውር አደባባይ የሚበትን
የራሱ ነውር አደባባይ ይታይበታል።

ከተመቻችሁ ለሌሎች ሼር አድርጉት!

https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
#أذكار_الصباح
((اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ)) (عشرَ مرَّاتٍ).
🍃🌻
#ሙሽሪትና_ሙሽራው
ነብዩ ሱለይማን (ዐለይሂ ሰላም) አንድ ጓደኛቸው ቤት ሠርግ ተጠርተው ለመሔድ ዝግጅት ላይ ሳሉ መለከል መውት መጣ‘ና የት ለመሔድ እንደተነሱ ሲጠይቃቸው ሠርግ እንደተጠሩ ነገሩት ።
ከዚያም መለከል መውት "እንዳትሄድ ዛሬ ማታ የዚህችን ሙሽሪት ነፍስ እንደወጣ እኔ ተዛዣለሁ" አላቸው ።
እሳቸውም ይህንን ሲሰሙ ጉዟቸውን ስረዛው ሰርጉን ከመሄድ ቀሩ ። ከዚያም በማግስቱ ነብዩላህ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ከሙሽሪት አባት ጋር ሲገናኙ ሰርጉን በመቅረታቸው በጣም ወቀሳቸው...እሳቸውም መልሥ አጥተው ዝም አሉ ።
እሳቸውም ሰርጉን ለመቅረት ምክኒያት የሆናቸውን መለከል መውትን ሲወቅሱት መልሱ እንዲህ ነበር
«አዎ በእርግጥ የሙሽሪትን ነፍስ እንዳወጣ ተዝዤ ነበር ፤ እናም ነፍሷን ለማውጣት ጉዞ ላይ ሳለሁ ድንገት ተመለሥ የሚል ትዕዛዝ ከላይ መጣልኝ‘ና ተመለስኩ ።»
መለከል መውት ትረካውን ይቀጥላል...
«ይህም ሊሆን የቻለው አንዲት አሮጊት እዛ ሠርግ ቤት ደጅ ላይ ቁጭ ብላ ሳለ የሙሽሪት አባት ያያት‘ና “ምን ፈልገሽ ነው ?˝ ሲላት እርቦኛል አለችው ።
ያን ጊዜ ነበር ለእርሱ ተብሎ የተዘጋጀውን ልዩ‘ና ጣፋጭ የሆነ ምግብ ሰውየው አንስቶ ለዚህች አሮጊት የሰጣት ። አሮጊቷም በልታ እንደጠገበች ለሙሽሪት አሏህ ዕድሜ እንዲሰጣት ዱዓ አድርጋ ወጣች ። አሏህም ዱዓዋን ተቀበላት‘ና እኔን ተመለስ አለኝ ።»
。。。。。。。。。。。。
ሸይኽ አልመጋሚሲ እንዲህ ይላሉ :-
ወፍ ውኃ ሲጠጣ በአጠገቡ አትለፉ ታስደነግጡታለችሁ‘ና ። በዚህም የአሏህን ውዴታ ፈልጉ...
የተረፋችሁን ምግብ ልትጥሉ ስታስቡ ሌሎች እንሰሳት ይበሉታል በሚል ኒያ ጣሉ ። በዚህም የአሏህን ውዴታ ፈልጉ...
。。。。。。。。。。。。
☞ እኔም ደግሞ ይህችን ጹሑፍ ሼር ለማድረግ ስታስቡ መልካም ነገር ነይቱ ።
ሼር 。。。
👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
              
አንድ ከአላህ መንገድ የራቀ ዱንያውን በአኺራው የገዛ ወጣት ነበር። ወጣቱ የሚኖረው አላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ከሚፈሩ ሰዎች መንደር ሲሎን ሰዉ ሁሉ እንዲስተካከል እንዲሁም የታላቅ ወንድሙን ፈለግ እንዲከተል ይመክሩታል። ይህ ልጅ ግን የሚሰማ አይደለም። ስለ ታላቅ ወንድሙ ካነሳን አይቀር የዚህ አስቸጋሪ ወጣት የ4አመት ታላቁ ነው። ቁርዓንን ከመጨረስም አልፎ በቃሉ ሃፍዟል። እንደ ዘመኑ ሃፊዞችም ሃፍዞ ከሃፈዘው ቁርዓን ተቃራኒ አይተገብርም። ባይሆን አላህ እንዲሸመድድ በወፈቀው ቃሉ ውስጥ ያሉትን ትዕዛዛቶች እንዲሁም ክልከላዎች በጥንቃቄ ያከናውናል።

ከእለታት አንድ ቀን ይህ አስቸጋሪ ወጣት ከዚያ አላህን ከሚፈራው ከታላቅ ወንድሙ ይማር ዘንድ አባት ሁለቱን ለጉዞ ያሰናዱ ጀመር። ለታላቅ ወንድሙ የጉዞውን አላማ በደንብ ያወጉት ሲሆን ለታናሽ ወንድሙ ግን አልነገሩትም። ታናሹ አስቸጋሪ ወንድም ይህን ጉዞ ባይቀበልም አባት እናት እንዲሁም ወንድሙ እንደምንም ብለው አሳምነውታል። እነሆ በጉዟቸው ቢያንስ የታላቅ ወንድሙን ባህሪ ይላበስ በማለት ከቤት ወጥተው መጓዝ ጀምረዋል።

ከቤት የተነሱት የሱብሂን ሰላት ሰግደው ሲሆን ከረጅም ጉዞ በኋላ ወደ ረፋድ አካባቢ የሆነ ጫካ ውስጥ ይገባሉ። ይሄና ታላቅ ወንድሙ የለመደውን #የዱሃ ሰላት ለመስገድ ውዱዕ ማድረግ ጀመረ። ታናሹም እኔ አሁን መስከድ ስለማልፈልግ ሽንቴን ሸንቼ መጣሁ በማለት ከወንድሙ ተለይቶ ይጓዛል። ይሄኔ አላህ ይህን ወጣት ሊያስተካክለው ይመስል አንድ አይቶት የማያውቀውን #ፍጡር ይልክበታል። ፍጡሩን ሲመለከቱት ያስፈራል። ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ነው።አብዛሃኛው የሰውነቱ ክፍል በፀጉር የተሸፈነ ሲሆን ከድፍን ጥቁርነቱ ጋር ተዳምሮ ላየው ሰው እጅክ ያስፈራል።

ወጣቱ ይህን አላስተዋለውም ነበር። ድንገት ይህ ፍጡር ከዛፍ ላይ በመዝለል ፊት ለፊቱ ድቅን አለበት። የሚያደርገውን አጣ ተርበተበት እየሮጠም ለማምለጥ ሞከረ። ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም። ምክንያቱም ይህ ፍጡር በጣም ፈጣን ስለነበር ዞሮ እፊት ለፊቱ ድቅን አለበት። አንዳንዴ ስንደነግጥ ለማያወራን ነገር እንደምናወራው ወጣቱም ለዚህ ፍጡር ያወራ ይመስል "አንተ ማን ነህ?" በማለት እየተርበደበደ የተቆራረጡ ሲቃ የተናነቃቸው ቃላቶቹን ሰነዘረ።

ዳሩ ግን እንስሳ መናገር አይችልምና የዚህ #አስፈሪ #ፍጡር ምላሽ ዝምታ ነበር። ላጩን እያንጠባጠበ ከቀጭ ወደ ግራ ይዟዟራል። አንዳንዴ አፋን በሃይል ይከፍተዋል። የሚያጉረመረም ድምፁ ከርቀት ለሰማው ልብ ይሰብራል። ወጣቱ የሚሆነው አጣ። መሬት ጠበበችበት። ይሄኔ ያኔ ከአላህ መንገድ ርቆ ሲከውናቸው የነበሩትን እኩይ ተግባሮች ማስታወስ ጀመረ። እያንዳንዱ ስራው እንደ መፅሐፍ ፊቱ ላይ ይገለጥ ጀመር። የሰፈሩ ሰው፣ እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድሙ ሲመክረው እንቢ ማለቱ ቆጨው። በውስጡም እንዲህ ሲል ተናዘዘ። 'አላህዬ !! ከዚህ ጭንቅ ገላግለኝ እንጂ ዳግም አንተን ላለማመፅ ቃል እገባለሁ"

ይህንን ንግግሩን ሳይጨርስ ታላቅ ወንድሙ ከሩቅ ትልቅ ዱላ ይዞ ወደ እንስሳው መሮጥ ጀመረ።ይህም ወጣት ወንድሙን እንዲመለስ ተማፀነው። ነገር ግን ያኛውም ጀግና ስለነበር በያዘው ዱላ አስፈሪውን ፍጡር ይነርተው ገባ። እንስሳ ቢጎዳ ሳይጎዳ አይተውም እንዲሉት አንድ ተሳክቶለት ያ አደገኛ ፍጡር ታላቅ ወንድሙን አንድ ግዜ በሃይል ነከሰው። ይሄኔ በታላቅ ወንድሙ መነከስ የተማረረው ወጣት እንስሳብጅውን በሃይል ባገኘው ዱላ ቀጥቅጦ ገደለው።

ወዲያውኑ አይኑ በእንባ እንደተሞላች ወደ ታላቅ ወንድሙ በመዞር ሲመለከተው ታላቅ ወንድሙ ጣቱን ወደ ሰማይ ቀስሮ እያጣጣረ ነው። ወንድሜ!! ወንድሜ!! እያለ ቢጮህም ማንም ሊደርስለት አልቻለም። ብዙ ደም ስለፈሰሰው ወደ ቀጣዩ አለም አኺራ ሸሃዳን ብሎ በሰላም ተሰናበት።

ይሄኔ ኑበር ያ ወጣት የወንድሙን ጀናዛ አጥቦ፣እራሱን ከዚህ በፊት ጀናዛ እንደነበር በማሰብ ንፁህ በሆነ መልኩ ገላውን ታጥቦ ወደ አላህ መንገድ ተመለሰ። ከዚያም በኋላ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየዞረ ኢልም በማካበት ሃገሪቱ ውስጥ አለ የተባለ ታዋቂ ዓሉም ለመባል በቃ።

ከዚህ አጭር ልብ-ወለድ የምንማረው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ማንኛውንም ሰው በፈለገው መንገድ ያቀናል። የፈለገውንም ያጠማል። እኛ ግን ጥሪ አድራሾች ሆነን ተሹመናል።

Share it to ur friends
👇Join our best channel👇
https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
ይህንን ድንቅ ታሪክ ያውቁ ኖሯል ???
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈
አላህ ( ሱ.ወ) ጅብሪል (ዐ.ሰ) ምን በፈጠረ ግዜ አሳምሮ ነበር
የፈጠረው::
600 ክንፎችን የቸረው ሲሆን የአንዱ ክንፍ
ርዝመት ከፀሐይ መውጫ እስክ ፀሐይ መግቢያ
ይደርሳል።
ጅብሪልም ይህን በተመለከተ ግዜ እንዲህ አለ ፡እንደኔ አሣምረክ
የፈጠርከው አለን ? ብሎ አላህን(ሡ.ወ)ን ጠየቀው
አላህም (ሡ.ወ) የለም አለው ።
ጅብሪልም በጣም በመደሠት 2 ረካዐ ሀረመ ለያንዳንዱ ረካዐ 20
ሺ ዐመት ፈጀበት ።
እንደጨረሠም አላህ(ሡ.ወ) ም የሚገባኝን መገዛት ተገዝተኸኛል
እንዳንተ የሚገዛኝም የለም ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን አካባቢ
ነብይ ይመጣል እኔ ዘንድ ውድ የሆነ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የሚባል
፡የሡ ዑመቶች ደካሞች ወንጀለኞች ናቸው፡፡
2 ረካዐ ይሠግዳሉ በመሠላቸትም ጭምር በአጭር ደቂቃ ከብዙ
ሀሣብ ጭንቅ ጭምር ጋር ይሰግዳሉ።
ነገር ግን በልቅናዬ በክብሬ ይሁንብኝ
የነሡ ሠላት እኔ ዘንድ ተወዳጅ ነች ።
ካንተ ሠላት የነሡ
ሠላት እኔ ዘንድ ተወዳጅ የሆነችው እነሡ በኔ ትዕዛዝ ነው
የሚሰግዱት አንተ ግን በሠጠሁህ ኒዕማ ተደሥተህ በፍላጎትህ
ነው ።
ጅብሪልም ለዚህ ኢባዳቸው ምን አዘጋጀህላቸው ? ሢልው
ጀነቱል መዕዋ አለው
ጅብሪልም ለማየት ፍቃድ ጠየቀ አላህ (ሡ.ወ)ም ፈቀደለት
በሙሉ ክንፎቹ መብረር ጀመረ።
1ክንፉ ሢዘረጋ 3 ሺ ዐመት ይቆርጣል እጥፍ ሢሆን እንደዛው።
በዚህ ሁኔታ 300 ዐመት በረረ ያም ሆኖ ደከመው አረፍ ብሎ
ስጁድ አድርጎ አላህ ሆይ ግማሿን ደረስኩ ወይስ ሩቧን ወይስ
ሲሶዋን ?? ብሎ ጠየቀ
አላህ(ሠ.ወ) ም 3000 ዐመት ብትበር የሠጠሁክን ያክል ሀይል
የሠጠሁክን ያክል ክንፍ እጥፍ ብሠጥህ አሁን የበረርከውን ያክል
ብትበር የሙሐመድን (ሠ.ዐ.ወ) ዑመት የሠጠሁትን ስጦታ አንድ
አስረኛውን አትደርስም !!!! አላሁ አክበር አላህ(ሡ.ወ) ምን ያክል
ስጦታ አዘጋጀልን ለ 2 ረካዐ ሡብሀነ አላህ።ትክክለኛ ሠጋጆች
አላህ ያድርገን።
አሚን
•════••• •••════
https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለበይክ አላሁመ ለበይክ...!🤲 መልካም ጁምዐ

JOIN👉 https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
جمعة مباركة 💚

اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَأَصْلِحْ ذَاتَ بَيْنِهِمْ

اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَنَا، اللَّهُمَّ ارْحَمْنَا ، اللَّهُمَّ ارْحَمْنَا، اللَّهُمَّ أَصْلِحْ بَالَنَا

اللَّهُمَّ إِنّا ظَلَمْنا أَنْفُسَنا ظُلْمًا كَثِيرًا وإِنَّهُ لا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلا أَنْتَ فَٱغْفِرْ لَنا ذُنُوبَنا وطَهِّرْ قُلُوبَنا واسْتُرْ عيوبَنا وأصلحْ أحوالَنا، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَنا وَارْحَمْنا وَتُبْ عَلَينا إِنَّكَ أَنْتَ التَّوَّابُ الْغَفُورُ، وارزُقنا حُسن الختام وتوبةً قبل الممَات

جمعة طيبة مباركة إن شاء الله

💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖

https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
#ጡባ ምን እንደሆነ ታቃላችሁ?

ጡባ በጀነት የሚገኝ የወርቅ ዛፍ ነው።
የጀነት ሰዎች ልብስም ከሱ ነው ሚሰራው።
ጥላው 100 አመት በፈጣን ፈረስ የሚጓዙበት ድረስ ነው።
ለማን እንደሆነ ታቃላችሁ?
እስቲግፋርን ለሚያበዙ ሰዎች
ነብያችን( ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ( ጡባ በመፅሀፉ ውስጥ ብዙ እስቲግፋር ለተገኘለት
ሰው ነው) ብለዋል።
አስተግፊሩላህ አለዚ ላ ኢላህ ኢላ ሁወ አልሀዩ አልቀዩም ወ አቱቡ
ኢለይህ።
ታድያ ለማያውቁ ብታሳውቁና በናንተ ሰበብ ብዙ ሙስሊሞችን
እስቲግፋር አብዝተው የጡባ ባለቤት ቢሆኑና እኛም የአጅሩ ተካፋይ
ብንሆን ምን ይመስላችኀል ።
አጅሩን ከፈለክ ለምታውቀው ሁሉ አስተላልፍ።
ለወዳጅዎም ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-1Vr67jA3DZU3ZGI0
2024/05/20 21:29:01
Back to Top
HTML Embed Code: