​​#ሕዳር_ሚካኤል !

#እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን !

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12)
(አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE
ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡)

ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡

በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት
አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡

ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም
የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡

ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር
#ጾመ_ነቢያት_ (#የገና_ጾም_)
የ2015 ዓ.ም. የገና (የነቢያት) ጾም፤
#ጾሙ_ኅዳር_15_ይጀምራል_!!
#Share

፠ ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡
፠ ኅዳር 15 ቀን ተጀምሮ እስከ ልደት ዋዜማ ለአርባ ሦስት ቀናት የሚጾም ጾም ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡
፠ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡
እነርሱም፤
† ፩. #ጾመ_አዳም_፤ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡

† ፪. #ጾመ_ነቢያት_፤ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::

† ፫. #ጾመ_ሐዋርያት_፤ ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡
† ፬. #ጾመ_ማርያም_፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡

† ፭. #ጾመ_ፊልጶስ_፤ ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

† ፮. #ጾመ_ስብከት_፤ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

† ፯. #ጾመ_ልደት_፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡

   ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡
ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

💚  •✥@bemaledanek •✥•💚
💛  •✥@bemaledanek •✥•💛
💖 •✥•@bemaledanek •✥• 💖
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
3•  ቅዱስ ቁርባን ክፍል - ፭ የቀጠለ..             ✞ አንድ አድርገን ከራሳችን ጋር ✞    "ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።"                      …
3•  ቅዱስ ቁርባን

ክፍል - ፮

           3.2•  ቅዱስ ቁርባን ለምን እንውሰድ ?

                      3.2.2•  በዲያቢሎስ ላይ

                    ✞ የልዑል ኃይል ይጸልልሻል

ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ አባቶች እግዚአብሔር አንድም በመፍጠር አባታችን ነው ይላሉ፡፡ ከክብሩ እንድንወርስ፣ ርስቱን እንድናስተዳድር፣ መልኩን እንድንመስል አድርጎ መፍጠሩ በእርግጥም ስለ አባትነቱ ይናገራል፡፡

ልጆቹ እንድንሆነው ፈቅዶ አስገኝቶናል፡፡ አምላክ ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ ከፈጠረ በኋላ ይባርካቸዋል፡፡ "ብዙ ተባዙ በምድርም ሙሉ" ሲል ባሕሪያቸው ውስጥ የመዋለድን ሥርዓት ይጽፍባቸዋል፡፡ በዚህ መንገድ አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔር ልጅ ሆነው የተፈጠሩበት ጥበብ እኛንም ልጆቹ ሊያደርገን በዘራችን ውስጥ በቡራኬ ተቀመጠ፡፡ ታዲያ "ውለዱ ክበዱ" ከማለቱ በፊት ባረካቸው የሚለው ይቀድማል፡፡ ይሄ የራሱ ምክንያት አለው፡፡

ስለ ቤተሰብ አንድነት ስንጨዋወት፥ አዳም በዲያቢሎስ ቃል ተሸውዶ ካስገኘው ፈቃድ ሲለይ የአምላኩ ፈቃድ ከሰጡትና ከሚሰጡትም ነገሮች አብሮ እንደተለየ አውስተን ነበር፡፡ ለምሳሌ ቀዳማውያኑ አባትና እናታችን ከገነት ተባርረው ነው የወለዱን፡፡ የአቤልና የቃየን ወላጆች ሰማያዊነትን ተገፈው ምድራዊ ሆነዋል፡፡ ከባረካቸው ከመለኮት ፍጹም ሕግ ተፋልሰዋል፤ ለመረጡት የሥጋ ሕግ ተላልፈዋል፡፡ እንግዲህ ልጆቻቸውም ለዚህ የሥጋ ሥርዓት የሚገዙ ይሆናሉ፡፡ በፈቃዱ ሆነን የምንዋለድበት የዘር ጽሕፈታችን በክፉው ድምፅ ተበላሽቷል፡፡ ከባሕሪያችን የተቆራኘ አሳች ምክር በፍጥረት የአምላክ ልጅ የምንሆንበትን የጸጋ ሥልጣን አስነጥቆናል፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድና ባርኮት ከምንወልድበት ሥርዓት በመውጣት፥ በራሳችን (በሥጋ) ፈቃድ ወደምንዋለድበት ሥርዓት ሄደናል፡፡

በዚህ ሁኔታ ቀጥለን ሳለ ነው ከወደ ቤተልሔም አንድ ብሥራት የተደመጠው፡፡ ከጠፋንበት የሚፈልግ፣ ወደ ወጣንበት የሚመልስ፣  ያጣነውን የሚሰጥ የምሥራች ቃል ለድንግል ማርያም ጆሮ ተሰማ፡፡ መልአኩ እንዲህ አላት፦

      "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።"

                                                        (የሉቃስ ወንጌል 1፥35)

ተመስገን! የምንወልደው ልጅ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን አጥቶት ነበር፡፡ እስከ መድኃኒቱ መወለድ ድረስ የወላጆቻችን ልጆች ብቻ ነበርን፡፡ በሌላ አባባል ምድርን ልንሞላ የምንባዛው ካለ እግዚአብሔር ቡራኬ ነበር፡፡ አሁን የቀደመው ተለውጦአል፤ ከእኛ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ የሚሆንበትን የባሕሪይ አለኝታ በዳዊት ከተማ አግኝተናል፡፡ እንዴት?

"አምላክ ሰው ሆነ" ብለን የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ ብለን በተዋሕዶ የምናምነው፤ "ሰውም አምላክ ሆነ" በሚለው ውስጥ ከእግዚአብሔር ተዋሕደን እንኖር ዘንድ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር እንደምንዋሐድ ስናምን ደግሞ በድንግል ማርያም የተገለጸው ኪዳን በእኛም ውስጥ ይገለጻል ብለን እንቀበላለን፡፡ ዮሐንስ ይህንን ጉዳይ ያስረዳናል፦

      "ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።"

                                                       (የዮሐንስ ወንጌል 1፥13)


እመቤቲቱ "እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" ስትል የእግዚአብሔርን [የባሕሪይ] ልጅ እንደወለደቺው፥ "እንደ ቃሉ አድርጉ" ስትል ደግሞ በእርሷ የተከናወነውን ታላቅ ሥራ በመቀበል እኛም የእግዚአብሔርን [የጸጋ] ልጅ እንድንወልድ ታስተምረናለች፡፡ ማርያም "ይሄ እንዴት ይሆናል?" ስትል ከመጠየቋ አስቀድሞ አንድ ነገር ሲመሰከርላት እንሰማለን፡፡ "መልአኩ ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ" ብሎአታል፡፡

የርእሳችን ዋና ሀሳብ ይኸው ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በምድር ከመወለዱ በፊት ወላጁ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረች፡፡ በሰማይ ዘንድም ብናየው ሥጋ የሆነው ቃል አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ ነው፡፡ ስለዚህ ከመውለድ በፊት፥ ከአምላክ ጋር መሆን መቅደም የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ ነው ማለት ነው፡፡

ታዲያ ብዙዎች የሚስቱበት ቦታ እዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ የመውለዱ ቦታ ላይ ነው፡፡ ምእመናን በዕውቀት ተረድተውት በእምነት ተቀብለውት ይሁን አይሁን፥ በወለዱ ጊዜ ልጆቻቸውን ክርስትና ያስነሳሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ወስደው በሥጋ ፈቃድ የወለዷቸው ልጆች በመንፈስም ፈቃድ እንዲወለዱ በ40 እና በ80 ቀን ያስጠምቋቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆንበትን የስም ሥልጣን እንደተቀበሉ የሚያረጋግጥ የክርስትና ስምና ሰነድ ይዘው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ መልካም!

ነገር ግን እኚሁ እናትና አባት ከመውለዳቸው አስቀድሞ ከጌታ ጋር እንደሆኑ የሚያስረግጥ የሕይወት ተክለ ቁመና የላቸውም (የራስን ቤተሰብ ያስቧል!)፡፡ ራሳቸውም ሲወለዱ ከእግዚአብሔር ጋር ካልኖሩ ወላጆች ተወልደው፤ በኑሮ መስመር በየፊናቸው ቆይተው፤ ወደ ትዳር ጊዜም ሲመጡ የኖሩበትን ልማድ ቀጥለው፤ ሃይማኖታዊ ዝግጅትና የእምነት መንፈስ ተረስቶ፥ ጋብቻቸው በፍሬ መድመቅ እንዳለበት በወሰኑበት ወቅት ላይ ልጅ ይወልዳሉ፡፡

ከጌታ ጋር ሳይሆን ከንግድ ጋራ፣ ከትምህርት ጋራ፣ ከሥጋ ዕውቀት ጋራ ቆይተን የወለድነው ልጅም፤ ከወላጆች ዘንድ መካፈል የነበረበትን መንፈሳዊ ቡራኬ አጥቶ ትናንሽ ልብሶችንና መታቀፊያ አግኝቶ ወደ ዓለም ይመጣል፡፡

እግዚአብሔርን ባጣ ኑሮ ውስጥ ያስገኘኘው ልጅ እንዲሁ እግዚአብሔርን እንደሚያጣ ሳይገባን፤ ከጌታ ጋር ሳንከርም የልዑል ኃይል እንደማይጸልልብንና መንፈስ ቅዱስም በኛ እንደማይመጣ ሳንረዳ የወለድናቸው ልጆች፤ መፍዘዝ፣ መደንገዝ፣ መጨነቅ፣ መታመም፣ እንቅልፍ ማጣት ወይም አብዝቶ መተኛት፣ መነጫነጭ በትንሽ ትልቁ ማልቀስ፣ መልፈስፈስ የማይለያቸው ግራ ግብት ያሉ ልጆች ሆነው ተወለዱ፡፡ ቁጭ በሉ ሲባሉ የሚነሡ፣ ተነሡ ሲባሉ የሚሄዱ፣ ሂዱ ሲባሉ የሚቀመጡ፣ ማስተዋልና የቤተሰብ ፍቅር የራቃቸው፣ ለመንፈሳዊ ዕውቀትና እውነት ፍላጎት የሌላቸው ሕፃናት ይዘው የሚሰቃዩ እናትና አባት በየሰፈሩና በየቤቱ በጣም ብዙ ናቸው፡፡

መንፈስ ቅዱስ በእርግጥ ልጆችን ክርስትና ባስነሳናቸው ጊዜ ይጎበኛቸዋል፡፡ ከጌታ ጋር ኖርንም አልኖርንም የእግዚአብሔር አባትነት አንድም በምሕረት ነውና፥ ቃልኪዳኑን አይተውም፡፡ እርሱን በአንደበት የወደደ በሕይወት የከዳ ሕይወትን ብንኖርንም ልጆቻችንን ልጁ የሚያደርግበትን የኪዳኑን ተስፋ አይከለክለንም፡፡ ችግሩ ልጆቻችን የክርስትና መታወቂያ አውጥተው ክርስቲያን የመሆናቸው ጉዳይ ላይ አይደለም፡፡ ችግሩ ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ባልኖርበት ጊዜ ውስጥ የዲያቢሎስ መንፈስ አብሮን ኖሮ፥ በልጆቻችንም ላይ ይኖር ዘንድ አብሮአቸው የመወለዱ ጉዳይ ላይ ነው (የተሰመረበት ተደጋግሞ ይነበብማ)፡፡
ቃየን አባትና እናቱ ከእግዚአብሔር ተለይተው የወለዱት ልጅ ነው፡፡ በኋላም ታሪኩ እንደሚተርከው በቅናት ተነሳስቶ ወንድሙን በሜዳ የገደለ ኃጢአት በደጁ ያደባችበት ሰው ነው፡፡ አዳም ከተከለከለው የዛፍ ፍሬ ሲበላ 'እነሆ ክፉውንና ደጉን ያውቅ ዘንድ ሆነ' ሲል አምላክ ተናግሮ ነበር፡፡ በአዳም ባሕሪይ ውስጥ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ዕውቀቶች ይዞታ አግኝተው ተቀምጠዋል፡፡ ይሄም በባሕሪይ ውስጥ የተገኘ ልዩነት በወለዳቸው ሁለቱ ልጆች ላይ በተጨባጭ ሲገለጥ እናያለን፡፡ ደጉ ዕውቀት በክፉው እንዲጠፋ ተፈርዶበታል፡፡ መልካሙ አቤል ሞቷል፡፡ እነሆ የቃየን ዘር በምድር ቀረ፤ ክፉውን ዕውቀት የገለጠው የነፍሰ ገዳዩ ዘር! ነፍሰ ገዳይን በተመለከተ ጌታ ሲናገር ፦

     "እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።"

                                                       (የዮሐንስ ወንጌል 8፥44)

ዘፍጥረት ምዕ.4 እንደሚነግረን የመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ቃየን ነበረ /አበው ከግብሩ ተነሥተው የቃየንን የስም ትርጉም ሲፈቱ በኩረ ቀታልያን ይሉታል/፡፡ ይሄን የምንለው ክስተቱን በሥጋ የተረክነው እንደሆነ ነው፡፡ በሥጋ የምናየው ቃየንን ነው፡፡ ከቃየን ውስጥ ያለውን ገዳይ መንፈስ ለማየት የጌታ ዓይኖች ያስፈልጋሉ፡፡ ከሥጋ ባሻገር ያለውን ለመመልከት በክርስቶስ መነጽር መመልከት ያሻል፡፡ የአቤል ደም እንዲፈስ የኃጢአት ኃይልና ግፊት የነበረው፥ የሰውን ሥጋ ተከናንቦ የተቀመጠው የቃየንን መንፈስ "ዲያቢሎስ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ" ሲል ጌታ ገልጦታል፡፡ አባቶችም ቃየን ወንድሙን የገደለበትን ታሪክ ባሰፈሩበት የትርጓሜ መጽሐፋቸው ላይ የመግደሉን ምክር ሹክ ያለው ሰይጣን ስለመሆኑና ሲያልፍም በሰውና በቁራ አምሳል በመገለጽ፥ ሰውየው ቁራውን ድንጋይ ወርውሮ ሲገድለው እንዳሳየው አስፍረዋል፡፡ (ኦሪት ዘልደት አንድምታ)

መጽሐፍ ቃየን ወንድሙን የገደለበት ፍርድ ከተቀበለ በኋላ አስከትሎ እንዲህ ሆነ ይላል ፦

    "ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፤ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ። ቃየንም ሚስቱን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፥ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖሕ አላት። ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ፤ ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ፤ ሜኤልም ማቱሣኤልን ወለደ፤ ማቱሣኤልም ላሜሕን ወለደ.. "

                                                (ኦሪት ዘፍጥረት 4፥16-18)

ቤተሰቦቹ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥተው የወለዱት ቃየን፥ እርሱም የራሱን ዓመፃ ጨምሮ ከእግዚአብሔር ፊት በመለየት ወለደ፡፡ በዚህ ዓመፃ በተጣባው ልደት ውስጥ የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ይገኛል ማለት መቼም ድፍረትም ጭምር ነው፡፡ ይልቅስ በአንጻሩ የኃጢአት መሠረትና መነሻ የሆነው የዲያቢሎስ መንፈስ በቃየን ዘር ውስጥ ዘልቆ ቁራኛ በመሆን ከማኅፀን ጀምሮ ልክፍት በመሆን የቁጥጥር አድማሱን ያጠነክራል፡፡

መናፍስት አብረው ይወለዳሉ ማለት በወላጆች ላይ አስቀድመው የነበሩ መንፈሶች የዘር ሐረግ ውስጥ ዘልቀው በመዋረስ፤ የሚወለዱት ልጆች ላይ ልክፍት በመሆን ከማኅፀን ሳለ ተዋሕደው የሰብአዊውን ሰው ማንነት በመጋራት፤ ሳጥን ውስጥ እንደ ተቀመጠ አንዳች ዕቃ ወይንም ጓንት እንዳጠለቀ እጅ ሆነው ግለሰቡን ይዳበላሉ ማለት ነው፡፡

በተለይም የዛር መናፍስት (በዘር ውስጥ የሚወራረሱ መንፈሶች) የቤተሰብን የኋላ ትከሻ በመቆጣጠር፤ በቀጣይነት በሚመጡት ትውልዶች ላይ ከእናትና ከአባት ውስጥ ሆነው ወደ ልጆች በመሻገር በባሕሪይ ውስጥ ገብተው፥ ተመሳስለው ያድጋሉ፡፡ አብረው ስለሚያድጉ መናፍስት ወንጌል ሲጠቁም፦

       "አባቱንም። ይህ ከያዘው ስንት ዘመን ነው? ብሎ ጠየቀው። እርሱም። ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው"

                                                     (የማርቆስ ወንጌል 9፥21)


ከቅድመ አያትና ከዛም በላይ ባለ የቤተሰብ ሰንሰለት ውስጥ ከጣዖት መናፍስት ጋር ቁርኝት ያላቸው ሰዎች በልጆቻቸው ላይ መንፈሶቹ እየተወራረሱ አብረው በመወለድ፤ ጠባይን፣ ጊዜን፣ ዕድልንና የኑሮ ገጽታን ተዋሕደው ይኖራሉ፡፡

የመናፍስት በዘር ትውልድ ውስጥ የመተላለፍ እውነታ እንዴት ነው ስንል፦

1ኛ•  አንድ ቤተሰብ በተለያዩ የባዕድ አምልኮቶች ውስጥ በመገኘት እንደ ጨሌ፣ አቴቴ፣ አዳል ሞቲ፣ ወሰን ገፊ፣ ወሰን ገላ፣ ውቃቢ፣ አዳኝ ወርቁ፣ አውሊያ፣ ታዬ ከራማ፣ አርሜት፣ ደማሜት፣ ራሔሎ፣ ሐጎስ፣ የአሩሲዋ እመቤት፣ አመቺሳ፣ ጠቋርና ወዘተ.. ተብለው በተለያየ መጠሪያ ለተሾሙ መንፈሶች ከባሕል፣ ከዘልማድ ወግና ከሥጋዊ ጥቅም ጋር የተያያዘ መናፍስታዊ ግብሮችን ሲገብር የቆየ ከሆነ፤ ከቤተሰቡ የዘር ትውልድ በሚገኙ ልጆች ሁሉ መንፈሶቹ እየተወራረሱ ልክፍት በመሆን አብረው ይወለዳሉ፡፡ ከእነዚህ መናፍስት ጋር ግንኙነት የነበረው የትውልድ ዘር፤ ባዕድ አምልኮቱን ቢያቆምም፣ ጨሌውን ቢጥልም፣ አንካሴውን ቢሰብርም፣ ጀበናና ልብሱን ቢጥልም፣ የመናፍስቱን ንብረቶች ቢያቃጥልም፣ ግብሩን ቢያስቀርም፣ በሞት ከዚህ ዓለም ቢለይም መንፈሶቹ እስካልተነቃባቸው ድረስ ልጆች ላይ አብረው ከመወለድ አያቆሙም፡፡

2ኛ• በመተት፣ በዓይነጥላ፣ በቡዳና በሌሎችም የተለያዩ መናፍስት የታሠረ ቤተሰብ ከሆነ፤ እንደ መስተፋቅር፣ መስተባርር፣ ዕፀ ፋሪስ፣ አረማዊ መፍትሔ ሥራይ እና ሌሎችም በርካታ የመናፍስት የአሠራር ድጋፎች ላይ በመሳተፍ የቆየ ቤተሰብ ከሆነ፤ ዛር የሚያነግሥ ቤተሰብ ባይሆን እንኳ፥ ዛሩ የተመለከበት ቤት አሊያም አካባቢ ውስጥ የሚኖር ከሆነ፤ የሌሎች ሰዎች መንፈስ በማየት፣ በመንካት፣ በምግብና በመጠጥ ተዋርሶ ወደ ቤተሰቡ የመጣ ከሆነ፤ በዓይን የማይታየው መንፈስ ገና በጽንስ ላይ ያለ ልጅን ለመያዝ ምንም አያግደውም፡፡ እነዚህኞቹ እንደ ግብር ፈላጊዎቹ ተሿሚ የዛር መናፍስት ረጅም የትውልድ ሐረግን አቆራርጠው ላይመጡ ይችላሉ፡፡ ከወላጆች ወደ ልጆች፥ ከሌሎች ሰዎች ወደ ልጆች ግን ይሻገራሉ፡፡

"ዘመናዊ" የተባለው የዛሬው ትውልድ ሊረዳው ያልቻለው ትልቁ የችግር መጀመሪያችን ይሄ ነው፡፡ ከተወለድንባት ዕለት ጀምሮ አብሮ የተገኘ ሌላ ክፉ ፍጡር እንዳለ ለመገንዘብ እንዳንችል ሥጋዊ ዕውቀትና የቁስ ሕይወት ከለላ ሆኖብናል፡፡ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሰዉ በነዚህ ውርስ መናፍስት አረንቋ ሥር ተይዞ ይገኛል፡፡ ቀደም ሲል በነበረው የማኅበረሰብ ልማድ በተለያየ ባሕላዊ ምክንያቶች የተሸፈነ የባዕድ አምልኮት ሥርዓት ነበር (አለም!)፡፡ በሰፊውና በጥልቀት የቁጥር መረጃዎችን ዋቢ ያደረገ ጥናት ቢደረግ፤ የጣዖት መናፍስት ትስስር በሕብረተሰባችን መካከል ሰርጎ እንደገባ የሚያመላክት እጅግ አስደንጋጭ የሆነ አዕዛዊ ማስረጃ እናገኝ ነበር፡፡

እዚህ ጋር ምእመናን ግር የሚያሰኛቸው አንድ ጥያቄ ሊኖር ይችላል፡፡ ቤተሰቦች ከእግዚአብሔር ጋር ሳይኖሩ በመቆየታቸው ምክንያትነት በተቃራኒው የሚኖረው የዲያብሎስ መንፈስ በተጠመቀ ልጃቸው ላይ እንዴት ሊዋረስ እንደተቻለው ጥያቄ ሊሆንባቸው ይችላል፡፡
በ40 እና በ80 ቀን ተጠምቀን መንፈሳዊ ልጅነትን በማየ ጥምቀት አግኝተን፤ ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን በመውሰድ በሰማያዊ ማኅተም ታትመን ሳለ፤ ክፉ መናፍስት በምን ሥልጣናቸው ከዘር ወደ ዘር (ከአባት ከእናት) ሊዋረሱ ይችላሉ? የሚለው ጥያቄ ብዙዎች ዘንድ ያለ ነው፡፡ በእርግጥም ዳግማዊው አዳም ክርስቶስ በመስቀል ባንቀላፋ ጊዜ ከጎኑ የወጣቺው ሴቲቱ ቤተክርስቲያን ዳግማዊት ሔዋን ሆና ከጌታ ጋር በምትፈጽመው ረቂቅ ጋብቻ ምእመናንን ዳግም ወልዳ ከማይጠፋው ዘር ትቀላቅላቸዋለች፡፡ ዳግም የመወለድ ሕግም አንድም ያስፈለገው፤ በመጀመሪያይቱ ሔዋን ፊት የቆመው እባብ የሰውን ልጅ በልቶ፤ በሕይወቱ፣ በዕውቀቱ፣ በትውልዱና በባሕሪይው እየገባ የራሱ ያደርገው የነበረበትን ውድቀት ለመሻር ነው፡፡ በአጭር አነጋገር ዲያቢሎስ በዘራችን እየዘለቀ እያጠፋ የመጣበትን የሥጋ አወላለድ ለመለወጥ ነው፡፡

ችግሩ እኛ ነን፡፡ ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ የድኅነት ሥራ በሙሉ ክብሩና እውነቱ አላስተናገድነውም፡፡ ባሕል፣ ልምድ፣ የይስሙላ፣ የግዴታ ውዴታ አደረግነው፡፡ የትኛው ወላጅ ነው በእውን ልጄ ከእግዚአብሔር አብራክ ይወለድልኛል በሚል የዋህ እምነት ክርስትና የሚያስነሣው?..ግዴለም ይቅር፤ ጌታ ገር ነውና፥ አለማመናችንን እየረዳ ልጆቻችንን ከመንፈሱ ይወልዳቸዋል፡፡ መናፍስቱ ግን በዘር መወራረሳቸውን እንዳያቆሙ ያደረጋቸውን ምክንያቶች ግን እኛ አላስወገድንም፡፡ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲወለድ ከጌታ ጋር አልቆየንም፡፡ ማለትም፦

☞  ከመውለዳችን በፊት ንስሐ አልገባንም፤ በቅዱስ ቁርባን አልተቀደስንም፡፡ ስለዚህ በኛ ውስጥ ያሉት መንፈሶች ለምን ይሽሹ?

☞  በቤተሰብ ታሪክ ሲመለክ፣ ሲገበርለት የቆየውን ባዕድ አምልኮት አልተላቀቅንም፣ አልሰበርንም፣ አልጣልንም፣ አላስቆምንም፣ አልተዋጋንም፡፡ ስለዚህ ዘሬ ናቸው ብሎ በኩራት ዙፋኑን አስፍቶ የተቀመጠው የጣዖት መንፈስ ለምን ይራቅ?

☞  ስለምንወልደው ልጅ አልጸለይንም፣ ሱባዔ አልጠየቅንም፣ ምንም መንፈሳዊ ቅደመ ዝግጅት አላደረግንም፡፡ ጨርቃ ጨረቁን፣ አልጋውን፣ የቤት ዕቃውን እንጂ የሃይማኖት ቀልብ አልገዛንም፡፡ የምንወልደው ልጅ ነፍስ ያለው የሰው ፍጡር እንደሆነ ዘንግተን ለሥጋ ለሥጋው ብቻ የሚያስፈልገውን ነው አሟልተን የምንጠብቀው፡፡ ስለዚህ "ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" የሚለው የሐዲስ ኪዳን ቃልኪዳን እንዴት አድርጎ ወደኛ ይድረስ?


( አማኞች ሁሉ ሊረዱት የሚገባ እጅግ አስፈላጊ ትምህርት ነበረ! ታነቡት ይሁን? .. ማንበብ የራሱ ድካምና መሻት ይጠይቃልና እርሱን ታደርጉ ይሁን? .. እኔንጃ! አብዛኛው የዚህ ዘመን ሰው ልፋት የማትጠይቅ መዳንን ይወዳታል፡፡ ብቻም ሳይሆን ያመመውን የግል ችግር ለሚፈውስ መረጃ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ካልሆነ ማንበብ የማይታሰብ ነው፡፡ ሦስት ገጽ የማይሞላ ጽሑፍ ረዘመ የምትሉኝ አላችሁ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳ ከማለት የተሻለ ምንም አይባልለትም፡፡ ግን ደግሜ ደጋግሜ፥ ደግሜ ደጋግሜ እንደምለው ነው፡፡ በጎቹ ድምፁን ይሰሙታል፡፡ ከእግዚአብሔር የሆነው፥ የእግዚአብሔርን በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ይቀበላል፡፡ ለምን እንዲህ እንደምላችሁ ሕያው አምላክ ያውቀዋል፡፡ ዕውቀት ከእምነት የተጣመረለት አማኝ የሚያደርገውን ስላየሁና ስለማውቅ ነው በማንበብ ዕውቀት ያዙ የምለው! ነገሩ አሁንም ጉዳዩ የታወቀ ነው፤ የእረኛው በግ ያልሆነ መልካሙን ጥሪ በምንም ውትወታና ጩኸት አይሰማም!)


ለማንኛውም የሚያነቡ ስለሚያነቡ ይቀጥላል. . .
#ጸባዖት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
3•  ቅዱስ ቁርባን ክፍል - ፮            3.2•  ቅዱስ ቁርባን ለምን እንውሰድ ?                       3.2.2•  በዲያቢሎስ ላይ                     ✞ የልዑል ኃይል ይጸልልሻል ✞ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ አባቶች እግዚአብሔር አንድም በመፍጠር አባታችን ነው ይላሉ፡፡ ከክብሩ እንድንወርስ፣ ርስቱን እንድናስተዳድር፣ መልኩን እንድንመስል አድርጎ መፍጠሩ…
3•  ቅዱስ ቁርባን

   ከክፍል - ፮ የቀጠለ..

ወደ ጀመርነው ሀሳባችን እንመለስ፡፡ መልአኩ ለድንግል ማርያም "ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው" ብሎ አላበቃም፡፡ እንዴት እንደምትወልድ ጭምር ይነግራታል፡፡ ከተለመደው የሥጋ ፈቃድ ውጪ የምትጸንስበትን ጥበብ ያሳውቃታል፡፡ "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" አላት፡፡

እዚህ ጋር በደንብ እናስተውል፡፡ "ከአንቺ የሚወለደው" ከሚለው በፊት የተጻፈው "መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል" የሚለው ነው፡፡ መድኃኒታችን ከመጸነሱ አስቀድሞ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእመቤታችን ላይ መጥቶአል፥ የልዑልም ኃይል ጸልሎአት አርፎአል፡፡ 'መጸለል' የሚለው ቃል አውዳዊ ፍቺው 'መጋረድ፣ መከለል፣ መጠበቅ' የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ረቂቅ የእግዚአብሔር ልጅ በምድራዊው ዓለም በግዙፍ ሥጋ ከመገለጡ አስቀድሞ የድንግሊቱን ውሳጣዊ ሕይወት ከኃጢአት ጠብቆ ማደሪያ ሲያደርገው፥ ውጪያዊ ሰውነቷን ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ጋርዶታል፡፡

መንፈስ ቅዱስ በድንግል ማርያም እሳተ ክበብ ሆኖ እንደ መጋረጃ ሲከድናት፥ ቃል ሥጋ የመሆኑ ጥበብ ሚሥጢር ሆነ፡፡ የመለኮት ባሕሪይ የሰውነትን ባሕሪይ በተዋሕዶ ገንዘብ ማድረጉ 'ሚሥጥረ ሥጋዌ' የተባለው፥ ይህ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ በፍጡራን ልዕልና ለመመርመርና ለመታወቅ ባለመቻሉ ነው፡፡ የልዑል ኃይል በብላቴናይቱ ላይ ከጸለለ በኋላ፥ ከዓለም የእውቅና መረጃ ርቆ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ ለመሆኑ የወልደ እግዚአብሔር በሥጋ መገለጥ ስለምን ሚሥጢር ሆነ?

      "ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።"

                                              (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፥8-9)

ዲያቢሎስ ወደነአዳም በእባብ ሥጋ ተደብቆ በመሄድ በኃጢአት እንደጣላቸው ባለፉት ክፍሎች በተደጋጋሚ አውስተናል፡፡ በአካላዊ ሥጋ ተሰውሮ፥ ለባሕሪይዋ ሐሰትን የሚያማክራት የክፋት መንፈስ ስለመሆኑ ሔዋኒቱ ብታውቅ ኖሮ፥ ምክሩን እንደማትቀበል መቼም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይሄ በሥጋ ጀርባ ተከልሎ የማጥፋት የዲያብሎስ ስልት በዘራችን ተቆራኝቶ፥ ሰዎች ሁሉ በተጨባጭ ለምናየውና ለምንሰማው እየታለልን ከቅድስና መራቅ ዕጣችን ሆነ፡፡

አባቶች ክርስቶስ በሥጋ ሚሥጢርነት ለምን እንደተገለጠ ሲያስረዱ "ሰይጣን ባሳተበት መንገድ ሄዶ ራሱን አሳተው" ይላሉ፡፡ የማይታይና የማይዳሰስ ስውር መንፈስ በሥጋ ተሸፍኖ ከዓመፃው እንዳካፈለን፥ ከሁሉ የተሰወረ እግዚአብሔር ቃል ሥጋ ሆኖ ከቅድስናው አካፈለን፡፡ ሳናውቀው ካጠፋን ጠላት እውቅና በመጥፋት፥ በባሕሪያችን ያስቀመጠውን ጥፋት አጠፋበት፡፡

ዲያቢሎስ ዓለምን በመላ ለመቆጣጠር፥ የታላላቅ ሥልጣኔዎች መሪና አድራጊ እየሆነ፣ የነገሥታትን ሕይወት ከመሠረቱ እየያዘ፣ አምልኮተ እግዚአብሔር ያልተቋረጠባቸውን የቃልኪዳን ሰዎችና ቦታዎች በትኩረት እየተፈታተነ፣ ሰውን ሁሉ ከሕግ በታች ለማድረግ ኃይል ጨምሮ እየሮጠ ባለበት ጊዜ፤ በመጀመሪያ ከእርሱ ዕይታ ርቃ ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ወላጆቿ ሐና እና ኢያቄም ቅዱሳን የነበሩ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ላይ ኑሮአቸውን የገነቡ፣ የእግዚአብሔርን እውነትና የተስፋ ኃይል በዘመናቸው የያዙ፣ የወለዷትን አንዲቱ ልጃቸውን ከሦስት ዓመቷ ጀምሮ ለቤተመቅደስ አሳልፈው የሰጡ መሆኑ፥ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን ከመነሻው ጀምሮ ለታላቅ ሥራ እንደመረጣት ያሳያል፡፡ (መዝሙረ ዳዊት 87፥5)

ይህ በእንዲህ እያለ ዲያቢሎስ ዓለምን ሸብቦ ለመያዝ ሌት ተቀን ሲከንፍ፥ ዓለም ውስጥ ያለቺው ማርያም ከዓለም ውጪ ሆና፤ እርሱን ከሚወክለው፣ ከሚስበው፣ ከሚመራውና ከሚያስፈጽመው ኃጢአት በሁለንተናዋ ተጠብቃ፤ በፍጹም የንጽሕና ኑሮ ብትመላለስ፥ እግዚአብሔር አብ አካላዊ ቃሉ ከእርሷ ሥጋ ይነሳ ዘንድ ወደዳት፡፡ እነሆም፥ ሕያው እግዚአብሔር ከዓለም ክፉ ዕውቀትና ኃይል ርቃ፥ ተሰውራ በቆየች ሴት በኩል ከዓለም ርቆ፥ ከሥጋ ዕውቀት ተሰውሮ ተወለደ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 1፥10)

መድኃኒታችን ከዲያቢሎስ ሚሥጢር ሆኖ በሥጋ በመወለድ፥ ዓላማና ሥራውን እንዳያውቅበት በልዑል ኃይል ጋረደው፡፡ ይሄ ከክፉ መናፍስት ዕይታ ርቆ የተወለደበት ጥበብ እኛንም እንዲወልደን ደግሞ ቃልኪዳኑን አንድም በሥጋና ደሙ ሰጠን፡፡ እንግዲህ "ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና" የሚያሰኘው ይሄ ነው፡፡

ሆኖሞ እኛ ከመወለድ አንስቶ በእግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጠብቀን እንዳንወለድ እናቶቻችን ቅዱስ ቁርባን እየወሰዱ አልጸነሱንም፡፡ ስለዚህ በቤተሰብ የኋላ ታሪክ ውስጥ የተለያየ ባዕድ አምልኮ ሲደረግለት የቆየው የግብር መንፈስ፥ በደም ትስስራችን በኩል እያቆራረጠ መጥቶ አብሮን ተጸንሶ አብሮን ተወልዶ አብሮን ያድጋል፡፡ "የዛር መንፈስ" ማለት ከስያሜው በቀላሉ እንደምንገነዘበው፤ በዘር ሐረግ ዘልቆ የሚያልፍ የርኩስ መንፈስ ስም መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ፥ ሥልጡን ዘመናችን ይሄን ከግንዛቤው ሳጥን በማውጣቱ ምክንያት ትውልዱ ከማኅፀን ጀምሮ እየተለከፈ ተወልዶ፥ በዕድሜው ሁሉ አልሰምርለት ያለ ከርታታ ሆኖ ይኸው ይሰቃያል፡፡

በነዚህ የዘር መናፍስት ተይዞ መወለዱ ጣጣው ይሄ ብቻ አይደለም፡፡ እናትና አባት የአምልኮተ እግዚአብሔር አኗኗርን ባልመሠረቱበት ኑሮ፥ ያለ ቅዱስ ቁርባን መቀደስ የሚወልዱት ልጅ፤ ከዘራቸው ሲወራረድ በመጣው መንፈስ ተጠቂ ሆኖ ያድጋል፡፡ ይኸው ልጅ፥ እያደገና እየጎለመሰ በሚመጣበት የተፈጥሮ ዑደት ውስጥ አብሮ የተወለደው የዛር መንፈስ ሌሎች የመናፍስት አይነቶችን እየሳበ በማምጣት አሊያ እንዲገቡ ጥሪ በማድረግ፤ ግለሰቡን የርኩሳን መናፍስት ዋሻ ያደርገዋል፡፡

በሐዲስ ኪዳን ግን፥ የመልአኩ ቃል "የልዑል ኃይል ይልልሻል" ካለ በኋላ "ስለዚህ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" ሲል ነበረ የተናገረው፡፡ ይሄ ንግግር የተቀደሰ ልጅ ወላጅ መሆንን ለሚፈልጉ ሁሉ ቢደገም እንዲህ ሊጻፍ ይችላል፦ "የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲያድርባችሁ፥ የምትወልዱት ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል"፡፡

የገብርኤል መልእክት ለሰው ልጆች ባሕሪይ ሁሉ የተላከ ብሥራት መሆኑን እኛ ሳናስተውል፤ "በቅዱስ ቁርባን ኃይል በኩል ተጸልሎ የተወለደ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል" የሚለው የኛ የጸጋ ልጅነት ስጦታ ሳይገባን፤ ካለ ሥጋና ደሙ የሚጸነሰው ልጅ ላይ የዛር መንፈስ ጸልሎበት፥ የሚወለደው የዲያቢሎስ ልጅ እየሆነ፤ ትውልዳችን ባልተረዳው መንፈሳዊ ባላጋራ ዘመኑን ተነጥቆ፥ እንደ የተናጠልም እንደ የጋራም እየተጨነቅን የክፉ ትንቢት መግለጫዎች ለመሆን ተገድደናል፡፡

ሁላችን በአጽንዖት እንድናስተውል የሚገባው፥ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጸንሰን ካልተወለድን፥ በመንፈስ ርኩስ ኃይል እንወለድ ዘንድ ያለው ዕድል ቀሪ አማራጭ ሆኖ እንደሚጠብቀን ነው፡፡ ዓለም ሦስተኛ ምርጫ የላትም ከብርሃን ካልሆንን ጨለማ ውስጥ ነን፡፡ ክፉውን ካልተቃወምን በመልካሙ አንመላለስም፡፡ ለፍቅር አንገዛም ስንል በጥላቻ የሚገዛን አለ፡፡
አንባቢ ተረድተኸኛል?.. በኃጢአተ አዳም ጀምሮ በተለያዩ ዘመናት ላይ ተጨማሪ ኃጢአቶችን በማስፈጸም ፥ ሕገ ኦሪትን በማስጣስና ጽድቅን ከሰው ባሕሪይ በማሸሽ፤ ብዙ ነፍሳትን ሰብስቦ እየዋጠ እባቡ ፋፍቶ ዘንዶ መሆን ችሎአል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ የዚህን ከይሲ ክፋት ሊያስወግድ በሥጋ የተገለጠ መሢሕ ሲሆን በመስቀሉ ኃይል የጥፋቱን ሥራ ከሰዎች ላይ ጠርቆ አስወግዶ፤ ለኃጢአቶች ሁሉ መፍለቂያ የሆነቺውን የአዳምን በደል በመካስ ከታሰርንበት እንድንፈታ አድርጎናል፡፡ ዳሩ ግን ሰዎች ከተጣባቸው ክፉ ዘር ተላቅቀው እንደገና አዲስ ፍጥረት የሚሆኑበትን ኪዳን ሊያምኑበትና ሊቀበሉት አልፈቀዱም፡፡ ስለዚህ በመድኃኒታችን ሰይፍ ለሞት የታረደቺው የአውሬው ራስ ተፈውሳ ልትገለጽ ተቻላት፡፡ ኃጢአተ አዳም እንደገና ልትተገበር በቃች፡፡ እስቲ ወደ ሀገራችን እንምጣ..

ከታሪክ ማኅደራችን እንደተቀመጠው ሀገራችን ኢትዮጲያ ይፋዊ በሆነ መልኩ በሐዲስ ኪዳን አምና ወደ ክርስትናው የመጣቺው በ328ዓ.ም በአክሱም ዘመነ መንግሥት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ መዳንን ማምጣት ያልቻለው የብሉዩ ሕግ በሐዲሱ ተፈጽሞ፥ ኢትዮጲያም ከዚህ በእግዚአብሔር ልጅ መምጣት ምክንያት ከተገለጠው ብርሃን ተካፋይ መሆን ችላለች፡፡ በሌላ አገላለጽ የክፋት መናፍስት አገዛዝ ተሽሮ፥ በክርስቶስ ስሙ ያመነቺውና የተቀበለቺው ሀገራችን የዘንዶውን ራስ የምትቀጠቅጥበትን የሃይማኖት መዶሻ (የተዋሕዶ ዶግማ) ተቀብላለች፡፡ ሥርዓተ መንግሥቷን፣ መተዳደሪያ ሰነዷን፣ ባሕሏን፣ አኗኗሯን፣ ዕውቀቶቿን፣ .. ሁሉ በክርስትናው መንፈስ እንዲቃኙ በመትጋት ሁለንተናዊ ማንነቷን ሐዲስ አድርጋ መንቀሳቀስ ጀምራለች፡፡ ጽድቅና ኩነኔ የማኅበረሰብ ብያኔዎች ማጥሊያዎች ሆኑ፡፡ ትክክልና ስሕተት በቅድስና ሚዛን እንዲለኩ መሥፈሪያ ተሰጣቸው፡፡ መንፈሳዊ እውነቶች የፖለቲካ መዋቅሩን እንዲመሩ ተደረገ፡፡ "ቀድሞ የነበረው አውሬ አሁን የለም" ማለቱን ያስታውሷል፡፡

"የለም" ሲባል ደብዛው ጠፍቷል በሚል እሳቦት እንዳይተረጎም ለአንባቢ አሳስባለሁ፡፡ ሰይጣን የማይኖርበት ጊዜ የለም፡፡ በሌላ አነጋገር በማይቻል ሁኔታም ይሁን የሚቻለውን ያህል ከመሥራት አያርፍም፡፡ ከክርስቶስ መሰቀል በኋላ እውነትን የማሳደዱ አዋጅ እንዳልቆመ ልብ እንላለን፡፡ መቃብሩ ላይ ጠባቂዎችን በመሾም የትንሣኤውን ምስክርነት እንዲያሳብሉ በአይሁዳውያኑ በኩል ሲጠነስስ መገኘቱ ላነሳነው ጭብጥ ምሳሌ ነው፡፡ ከትንሣኤውም በኋላ የጌታን ደቀመዛሙርት ሲያንከራትትና ሲያስገድል የሚታየውም ለዚህ ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጲያው ጉዳይ ስንመለስ፥ ክርስትናው ወደ ሀገሪቱ በመግባቱና ሀገሪቱም ሥር ነቀል በሚያሰኝ ለውጥ በእውነት ወንጌል በመጠመቋ ዲያቢሎስ ይፋዊ ሥራውን ከመከወን ተወግዶ ነበር፡፡ ሆኖም በውስጥ መስመር እውነት እንዳይስፋፋ ሲሸርብ፥ በአንጻሩ ይመለኩ የነበሩ ባዕድ አምልኮቶች እንዲስፋፉ ሲደክም ቆይቷል፡፡ ምእመናንን በተለያየ መልኩ ሲፈትንና ሲያሳሳት መክረሙ የታሪክ ክስተቶችን በማጥናት በቀላሉ ማወቅ ይቻላል፡፡ ዘመን መጥቶለት ዓላማው ሙሉ ለሙሉ ግቡን እስኪመታለት ድረስ ድምፅ አጥፍቶ በጥንቃቄ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡

እነሆ፥ ሲያልመው የኖረውም አልቀረ ይፋ የሚወጣበት ጊዜ ደረሰለት፡፡ ከአንድ ሺሕ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ ሀገረ እግዚአብሔር በሚል ቅጽል ስትጠራ በኖረች ምድር ላይ "እግዜር የለም" የሚል አብዮተኛ ትውልድ ተነሣ፡፡ ሃይማኖትን ከሚክድና መንፈሳዊ ዓለምን ከሚንድ ወገን የተማሩ "ምሁሮች" የ60'ዎቹን ዘመን አብዮት አቀጣጠሉ፡፡ "ሶሻሊዝም ይለምልም፥ ፊውዳሊዝም ይወድም" ሲሉ በየአደባባዩ ጮኹ፡፡ እግዜር መረጠኝ የሚለው የንጉሣዊያኑ ሥርዓትና አስተዳደር፥ ሀገሪቱን ለድንቁርና ብሎም ለድህነት እንዳጋለጣት ደረስንበት አሉ፡፡ ስለዚህ በማርኪሲዝም ቁሳዊ ዓለምን በሚያበረታታ ርዕዮት ችግራችንን "እንቀርፋለን" በማለት፥ ቀደም ሲል ሀገሪቱ ለሺሕ ዓመታት ስትመራበት የነበረውን ሥርዓት እያከታተሉ ማጥፋትን ሥራቸው አደረጉ፡፡ ጥፋትና ልማት የሚለዩበትን አፍታ ሳይወስዱ፥ በነበረው ታሪክ ላይ እንደወረደ ዓመፁ፡፡ ወልደው ያሳደጓቸውን አባቶች፣ ዕሴቶች፣ ሕብረተሰባዊ ደንቦች፣ መንፈሳዊ መርሆች ለታሪክ እንኳ እንዳይቀመጡ አንድ ጊዜ ዘመቱባቸው፡፡ አንባቢ አሁን ምን ገባህ?.. "አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ.." የሚልህ አልገባህም?

ኃጢአተ አዳም "እንደ አምላክ በመሆን ከንቱ ምኞት" የተፈጸመች ኃጢአት ናት፡፡ ምክሩንም ያቀበለው ቀድሞ "አምላክ እኔ ነኝ" ሲል ያመፀው እባብ ነበር፡፡ የሰው ልጅ እንደ አምላክ እሆናለሁ ሲል አምላክ የለምንም እየተናገራት እንደሆነ ያስተውሏል፡፡ የኛዎቹ፥ የ1960'ዎቹ አብዮተኞች "አምላክ የለም" በሚል የማርኪሲዚም እባብ-ፍልስፍና የተደነፉ ሶሻሊስቶች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ የክሕደቱን ፍልስፍና ካጠኑት በኋላ እንደ ማሳያ የሆነላቸውን የሶቪየት ሕብረትን "ብልጽግና" ሲያዩ የማርኪሲዝሙ ሕብረተሰባዊነት ጥበብ ሰጪ፥ ፖለቲካዊ ሥርዓትም አድርጎ ለመጠቀም የሚያጓጓ ሆነባቸው፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥6) አላመነቱም! "ኢትዮጲያዊ" ማኒፌሶቶአቸውን ከቀዱት የሶሻሊዝሙ ዕውቀት ላይ በማስደገፍ በ1968 የሀገሪቱ ሥልጣን ላይ ወጡ፡፡ ከዛፉ ፍሬ የገመጡለት የዛ ጊዜው ዘንዶም እየተጎተተ መጥቶ ወንበራቸው ላይ ተደላደለ፡፡

ዘንዶው ፖለቲካዊ ኃይልን ከእጁ እንዳስገባ ሲያይም፥ በሐዲስ ኪዳን መነሻዎቹ ዓመታት ክርስትናን በይፋ ሲያሳድዱ እንደነበሩት ሮማውያን ነገሥታት፥ መንፈሳዊነትን ለማጥፋት ብቀላ ባለበት እልህ ሠራዊት ያስከትት ጀመር፡፡ በእርግጥም ከ50 ዓመታት ወዲህ የሆነብንንና የተነሣውን ትውልድ እናውቃለን፡፡

መድኃኒታችን ከግምጃ ቤት አጠገብ በመቅደስ ሆኖ ያስተምራል፤ አይሁዳውያኑ ይሰሙታል፡፡ በሚናገራቸውም ግር እየተሰኙ ይጠይቁታል፥ እርሱም ይመልሳል፡፡ የሚናገራቸውንም እየሰሙ ከአይሁዳውያኑ ውስጥ የሚያምኑበት ሰዎች እየበዙ መጡ፡፡ እርሱም እንደ እውነትነቱ ከባርነት ነጻ የሚያወጣው መሢሕ እንደሆነ ይገልጽላቸዋል፡፡ ይሄን ጊዜ ያመኑቱ ሳይቀሩ ቁጣ ይጀምራሉ፡፡ "እኛ የአብርሃም ዘር ሳለን እንደባሪያዎች አርነት ላውጣችሁ ትላለህን?" አሉት፡፡ እርሱም መልሶ የኃጢአት ባሪያዎች እንደሆኑና በእርሱ ካልሆነ ከዚህ ባርነት ነጻ ሆነው የእግዚአብሔርን ልጅነት እንደማያገኙ ዕንቅጩን ይነግራቸዋል፡፡ እነርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆኑ ሲነግሩትና በንግግሩም ሊገድሉት እንደሚፈልጉ ባስተዋላቸው ጊዜ የሚከተለውን ይላቸዋል፦

        "እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና። ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው። እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ።"

                                                  (የዮሐንስ ወንጌል 8፥42-44)

ሰዎቹ የእግዚአብሔር ልጅ ነን ቢሉም አባታቸው ሌላ ነበር፡፡ ዲያቢሎስ! ይሄ የሐሰት አባት የነርሱም አባት ሲሆናቸው በዘርነት አብሯቸው ያለ ጭምር ስለመሆኑ እንገነዘባለን፡፡ ከዝሙት አልተወለድንም ቢሉም፥ ባልተሠረየ ኃጢአት ውስጥ የሚዋለዱበት ሥጋዊ ሥርዓት ለክፉው መዋረስ የተመቸ ነበር፡፡
የዛሬው የዘመን ትውልዶች የ60'ዎቹ ትውልዶች ልጆች ነን፡፡ በግልጽ ቋንቋ አምላክ የለም ሲሉ አዲስ ርዕዮት ያመጡት ሰዎች አባቶቻችን ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የለም የተባለበት ጊዜ ፍሬዎች ነን፡፡ ነን አይደለንም?

አባቶች በእውነተኛ ሰማያዊ ሞገስና ጸጋ ያቆዩትን ቃልኪዳን፤ በፍጹም መሥዋዕትነትና ተጋድሎ ያስረከቡትን የእምነት ስጦታ፤ አክብረውና ጠብቀው ያቆዩት የተስፋና የመገለጥ በረከት፤ ሐሰትን በአንድ ኅብረት ተቃውመውና አውግዘው መልካሙን ያቆዩበት የእውነት ክብር፤ አንዱ ለአንዱ ድክመቱ በታየበት ቦታ ላይ ለድጋፍና ለመተባበር የተከፈተው ስብዕና፤ አንደበታቸውንና ምግባራቸውን ከመንፈሳዊ ጉድለትና ሙላት አንጻር እየመዘኑ የእግዚአብሔርን የረድኤት እጆች የያዙበትን ዘመን፤ ባለጊዜዎች ተነሡና "ይውደም" አሉት፡፡

ከዚህ የይውደም የፍልስፍናው አምባ የተነሣው አፍራሽነታችን፥ አጥፊነቱን በቀጥታ ለቀጣዩ ትውልድ በሚያስተላልፍበት ጊዜ፥ ይውደም ያልንበት የቃል እርግማን በእያንዳንዳችን ልብና ቤት ውስጥ ዘልቆ ሲገባ፤ በመጀመሪያው ውድመት አንድ ሲል ውስጣችንን ከእግዚአብሔር እውነት ለይቶ አወደመው፡፡ ውስጣችን በሚወድምበት ጊዜ፤ የትናንት ማንነቶቻችን ተስማምተውን መቆየት አቃታቸውና ወዳስጠጓቸው ልቦች ሄደው ተሸሸጉ፡፡

ከኮሚኒስቱ ዘመን ርዕዮት ወዲህ በመጣንባቸው የሕይወት ምዕራፎች ውስጥ፤ ያዋጡናል ብለን የተከተልናቸው ሀገራዊ አስተሳሰቦች፣ ትክክል ናቸው ብለን የተቀበልናቸው የሕብረተሰብ ፖሊሲዎች፣ ይሻሉናል ብለን የሰበሰብናቸው የፍልስፍና ዕውቀቶች፤ የአባቶችን የእምነት ፍቅርና ኃይል እንደ ባሕላዊ ጎታች ሥርዓት ተመልክቶ ከመናቁም በተጨማሪ፤ የራሱን የታሪክ ዘውግና እውነት በእንግዳ አመለካከት በማጉደፍ በዓለም ፊት ማንነቱን ያዋረደ፣ ነገሥታትን ያንቋሸሸ፣ ጳጳሳትን ያሳደደ፣ ሃይማኖታዊ አሻራዎችን ያወደመ፤ አረማዊ ጠባይ በሀገር አቀፍ ሰፊ ሽፋን የተንጸባረቀበት ጊዜ ነበረ፡፡

      "ሥርዓቱንም ከአባቶቻቸውም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን፥ ያጸናላቸውንም ምስክሩን ናቁ፤ ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፥ ምናምንቴዎችም ሆኑ፥ እግዚአብሔርም እንደ እነርሱ እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብን ተከተሉ።"

                                        (መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 17፥15
)

በዘመኑ ከነበረው የፖለቲካ ቅዠት-ወለድ ሀሳብ ጋር ተጣምረው፤ ጊዜን ከትውልድ ፍጥነትና ለውጥ ጋር ለማስኬድ ያደረግናቸው ጥረቶች የእግዚአብሔርን መሪነት አፍርሰንና እንዲሁም ክደን ስለተጓዝንባቸው፤ ስመ መለኮት በሌለበት ቦታ ላይ የጀመረነው ባልተጨበጠ የመመሪያ አጀንዳ የናወዘ ግስጋሴ የታሪክ ከፍታዎችን እንዳልነበሩ ያህል ደምስሶ ለመጣል ቀላል ሆኖለታል፡፡ ቀደምቶቻችን ደምና ዋጋ ከፍለው ባቆዩት መንፈሳዊ ቀለም ላይ የፍልስፍና እርሾ ቀይጠን ስንደባልቅ፤ በግማሽ ሕሊናችን አማኞች በቀረው ግማሽ ሕሊናችን አፈንጋጮች በመሆን፤ በቀደመው የእምነት ትውልድ ተሸንፎ የነበረው የዲያብሎስ ሠራዊት በኛ ዘመን ላይ ለጥፋት ቁጥጥር እንዲያንሰራራ ምቹ አጋጣሚ ስላገኘ፤ ቀጥሎ የተተካውን ባለተራ ትውልድ በጥቁር ሥልጣን ጨፍልቆ በመግዛት፤ በአስተሳሰብ ጨለምተኝነት ሃይማኖታዊ እውነታዎችን የሚንቅ፣ ባሕላዊ ሥነ ምግባራትን የሚጠየፍ፣ ማኅበረሰባዊ ዕሴቶችን የሚያሸማቅቅ፣ የእምነት ታሪኮቹንና የአባቶቹን የተጋድሎ መሥዋዕትነት የሚያጥላላ፣ በዘርና በጎሳ ልዩነት የሚነቃቀፍ፣ ሥጋዊ እሳቦቶችንና መሻቶቹን የሕይወቱ ብቸኛ እቅድ የሚያደርግ፣ አርቆ የማስተዋልን የሥነ ልቦና አቅም የተነጠቀና በተለያዩ ዘመን አመጣሽ የለውጥ እስራቶች የተጠፈነገ፥ የርኩሰት ዳፍንት እንደ ወረርሺን ያጠቃው ትውልድ ተከተለ፡፡
 
አሁን ያለውን ትውልድ ያስገኘው ትውልድ፤ በየግል በየግል ስናየው፥ ከሞላ ጎደል በንጽጽሮሽ መልኩ የተሻለ እርሱን ባስገኙት ቤተሰቦች ሞራላዊና ሥነ ምግባራዊ አጥር የተከለለ ስለነበረ፤ ከማኅበረሰቡ ባሕል ሲወጣ ቢንገዳገድም፤ አኗኗሩን ርኩሳን መናፍስት ቢያበላሹትም፤ ፈሪሐ አምላክ ያላቸው ስለነበሩ ቢያንስ በሀገራዊ ደረጃ የትውልድ መጥመምን አላስተናገዱም፡፡ ግን ታዲያ ትዳር መሥርተው አብዛኛዎቹ ልጅ ሲወልዱ እንደዛው በተንገዳገዱበት የሕይወት ልክ ሆነውና የሰማይ አምላክን ጸጋ አርቀው በአንጻሩ የዘመንን ምርቃና ይዘው ከነበረ፥ የተወለደውም ከልጅነቱ በአመልና በሱስ ግንፍልተኝነት የመረቀነ፤ የአስተዳደግ ሕጉም የተንገዳገደ እንዲሆን ይገደዳል፡፡ የዛሬ የወጣቱ ትውልድ ወላጆች በወጣትነት ዘመናቸው ቃማዊች የነበሩ፣ ጠጪዎች የነበሩ፣ የፖለቲካ ግፈኞች የነበሩ፣ በዝሙት የወደቁ፣ የጣዖትና የባዕድ አምልኮት ግብር የሚገብሩ "የነበሩ" ሲሆን፤ ንስሐ ሳይገቡና ቅዱስ ቁርባን ሳይቀበሉ ከፊሉ ልባቸው መለስ ባለጊዜም ይሁን እዛው ውስጥ በቆዩበት ጊዜ የሚወልዱት ልጅ፥ የእነርሱን "የነበሩ" ታሪክ ገጽታውን አዘምኖ እንዲቀጥል፤ ገና ከማለዳው በመናፍስቱ የውርስ ኃይል ተይዞ መኖር መጀመር ዕድሉ ሆኖ፥ ከቅድስና የሚዋልል ቢሆን በእውነት የሚጠብቅ ነው፡፡

አዎ.. ኃጢአት በንስሐ ባልተሠረየበትና ከጌታ ጋር መኖር እንድንችል ቅዱስ ቁርባን ባልተወሰደበት ሁኔታ የተወለድን ትውልዶች ነንና እኛም ዘራችንን ዘሩ ካደረገው ከአባታችን ከዲያቢሎስ ስለመሆናችን ሕይወታችን ማረጋገጫ የማያስፈለገው መታያ ይሆናል፡፡ በሥጋ የአኗኗር ውጥረት መካከል በጠበበ የማስተዋል መስመር ላይ ወድቀን፤ የቅርብ ቅርቡን ብቻ እያየን ጊዜያችንን በትምህርትና በሥራ ብቻ አጥረን ይዘነው፤ ውስጣችን መቼ እንደታመመ እንኳ መረጃውን አጥተን ቀስ በቀስ በመጀመሪያ ከውስጥ ቀጥሎም በውጪ ገጽታችን እየተበላን መጣን፡፡ እየተበላን መጣንና ወደ ኋላችን ዞረን የመጣንበትን አቅጣጫ ቆመን የምናስተውልበትን አእምሮና ጊዜ አጥተን፤ ከባሰ ወደ ባሰ፣ ከጨነቀ ወደ ጨነቀ፣ ግራ ከተጋባ ወደ ተስፋ የቆረጠ የሕይወት እርከን እየተሸጋገርን ዕለቶቻችን ለማሳለፍ ብቻ የምንኖር ሆንን፡፡

እንግዲህ ስንወለድ ጀምሮ በመናፍስት ተጋቦት ውስጥ ሆነን ከነፍስና ከሥጋችን ተጨማሪ አጥፊ ኃይልን ከማኅፀን ወርሰን ስለተወለድን፤ እግዚአብሔር የፈጠረልን ንጹሕ ሕሊናና ልቦና ላይ አብሮ የተወለደው ክፉ መንፈስ የአሉታዊ ሀሳቦችና ምሪቶች ምንጭ ሆኖ፤ በሥጋዊ ዕውቀት ብቻ የምንሄድበት የኑሮአችን ጓዳና ተስማሚ ምሽግ ሠርቶለት ብዙ ጥፋትና ኪሣራ እያደረሰ፤ የዘመን ክፉ እንዲፈጥን የጋራ እርግማንን ለሕይወታችን አሰልጥኖ የመቅሠፍት ትውልዶች አድርጎናል፡፡ በእርግጥ ክፉ መናፍስት በዘራችን ውስጥ እየተዳበሉ አብረው በመወለድ ያጠፉን ነበር፥ ግና ክርስቶስ ልጆቹ እንድንሆን በመሥዋዕትነት ኪዳን ቃልኪዳን ሰጥቶ ከጥፋት ታደገን፥ ዳሩ ግን በጥፋት ዘመን ላይ የደረስነው የአሁን ጊዜ ትውልዶች ከተሰጠን ኪዳን አፈንግጠን ስንወጣ መናፍስቱ እንደገና በቤተሰባችን ሐረግ ውስጥ ዘልቀው ገቡ፤ እነሆም መናፍስት አብረው እንደሚወለዱ በሐዲስ ኪዳን ዘመን ስንሰማ ግርምት ሆኖብን እናደንቃለን፡፡ ቃሉ ምን አለ? "..አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።"


ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባዖት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
✞ ቅዱስ ቁርባን - የሕይወት እንጀራ ✞

(እነሆ የዘመቻችን የመጨረሻ ምዕራፍ)

እውቀት ንጋት ናት ጨለማን ታበራለች! ስለዚህ .. ጊዜ ወስዳችሁ አንብቡ!
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
3•  ቅዱስ ቁርባን    ከክፍል - ፮ የቀጠለ.. ወደ ጀመርነው ሀሳባችን እንመለስ፡፡ መልአኩ ለድንግል ማርያም "ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው" ብሎ አላበቃም፡፡ እንዴት እንደምትወልድ ጭምር ይነግራታል፡፡ ከተለመደው የሥጋ ፈቃድ ውጪ የምትጸንስበትን ጥበብ ያሳውቃታል፡፡ "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል"…
3•  ቅዱስ ቁርባን

   ከክፍል - ፮ የቀጠለ..

ወደ ጀመርነው ሀሳባችን እንመለስ፡፡ መልአኩ ለድንግል ማርያም "ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው" ብሎ አላበቃም፡፡ እንዴት እንደምትወልድ ጭምር ይነግራታል፡፡ ከተለመደው የሥጋ ፈቃድ ውጪ የምትጸንስበትን ጥበብ ያሳውቃታል፡፡ "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" አላት፡፡

እዚህ ጋር በደንብ እናስተውል፡፡ "ከአንቺ የሚወለደው" ከሚለው በፊት የተጻፈው "መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል" የሚለው ነው፡፡ መድኃኒታችን ከመጸነሱ አስቀድሞ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእመቤታችን ላይ መጥቶአል፥ የልዑልም ኃይል ጸልሎአት አርፎአል፡፡ 'መጸለል' የሚለው ቃል አውዳዊ ፍቺው 'መጋረድ፣ መከለል፣ መጠበቅ' የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ረቂቅ የእግዚአብሔር ልጅ በምድራዊው ዓለም በግዙፍ ሥጋ ከመገለጡ አስቀድሞ የድንግሊቱን ውሳጣዊ ሕይወት ከኃጢአት ጠብቆ ማደሪያ ሲያደርገው፥ ውጪያዊ ሰውነቷን ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ጋርዶታል፡፡

መንፈስ ቅዱስ በድንግል ማርያም እሳተ ክበብ ሆኖ እንደ መጋረጃ ሲከድናት፥ ቃል ሥጋ የመሆኑ ጥበብ ሚሥጢር ሆነ፡፡ የመለኮት ባሕሪይ የሰውነትን ባሕሪይ በተዋሕዶ ገንዘብ ማድረጉ 'ሚሥጥረ ሥጋዌ' የተባለው፥ ይህ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ በፍጡራን ልዕልና ለመመርመርና ለመታወቅ ባለመቻሉ ነው፡፡ የልዑል ኃይል በብላቴናይቱ ላይ ከጸለለ በኋላ፥ ከዓለም የእውቅና መረጃ ርቆ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ ለመሆኑ የወልደ እግዚአብሔር በሥጋ መገለጥ ስለምን ሚሥጢር ሆነ?

      "ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።"

                                              (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፥8-9)

ዲያቢሎስ ወደነአዳም በእባብ ሥጋ ተደብቆ በመሄድ በኃጢአት እንደጣላቸው ባለፉት ክፍሎች በተደጋጋሚ አውስተናል፡፡ በአካላዊ ሥጋ ተሰውሮ፥ ለባሕሪይዋ ሐሰትን የሚያማክራት የክፋት መንፈስ ስለመሆኑ ሔዋኒቱ ብታውቅ ኖሮ፥ ምክሩን እንደማትቀበል መቼም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይሄ በሥጋ ጀርባ ተከልሎ የማጥፋት የዲያብሎስ ስልት በዘራችን ተቆራኝቶ፥ ሰዎች ሁሉ በተጨባጭ ለምናየውና ለምንሰማው እየታለልን ከቅድስና መራቅ ዕጣችን ሆነ፡፡

አባቶች ክርስቶስ በሥጋ ሚሥጢርነት ለምን እንደተገለጠ ሲያስረዱ "ሰይጣን ባሳተበት መንገድ ሄዶ ራሱን አሳተው" ይላሉ፡፡ የማይታይና የማይዳሰስ ስውር መንፈስ በሥጋ ተሸፍኖ ከዓመፃው እንዳካፈለን፥ ከሁሉ የተሰወረ እግዚአብሔር ቃል ሥጋ ሆኖ ከቅድስናው አካፈለን፡፡ ሳናውቀው ካጠፋን ጠላት እውቅና በመጥፋት፥ በባሕሪያችን ያስቀመጠውን ጥፋት አጠፋበት፡፡

ዲያቢሎስ ዓለምን በመላ ለመቆጣጠር፥ የታላላቅ ሥልጣኔዎች መሪና አድራጊ እየሆነ፣ የነገሥታትን ሕይወት ከመሠረቱ እየያዘ፣ አምልኮተ እግዚአብሔር ያልተቋረጠባቸውን የቃልኪዳን ሰዎችና ቦታዎች በትኩረት እየተፈታተነ፣ ሰውን ሁሉ ከሕግ በታች ለማድረግ ኃይል ጨምሮ እየሮጠ ባለበት ጊዜ፤ በመጀመሪያ ከእርሱ ዕይታ ርቃ ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ወላጆቿ ሐና እና ኢያቄም ቅዱሳን የነበሩ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ላይ ኑሮአቸውን የገነቡ፣ የእግዚአብሔርን እውነትና የተስፋ ኃይል በዘመናቸው የያዙ፣ የወለዷትን አንዲቱ ልጃቸውን ከሦስት ዓመቷ ጀምሮ ለቤተመቅደስ አሳልፈው የሰጡ መሆኑ፥ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን ከመነሻው ጀምሮ ለታላቅ ሥራ እንደመረጣት ያሳያል፡፡ (መዝሙረ ዳዊት 87፥5)

ይህ በእንዲህ እያለ ዲያቢሎስ ዓለምን ሸብቦ ለመያዝ ሌት ተቀን ሲከንፍ፥ ዓለም ውስጥ ያለቺው ማርያም ከዓለም ውጪ ሆና፤ እርሱን ከሚወክለው፣ ከሚስበው፣ ከሚመራውና ከሚያስፈጽመው ኃጢአት በሁለንተናዋ ተጠብቃ፤ በፍጹም የንጽሕና ኑሮ ብትመላለስ፥ እግዚአብሔር አብ አካላዊ ቃሉ ከእርሷ ሥጋ ይነሳ ዘንድ ወደዳት፡፡ እነሆም፥ ሕያው እግዚአብሔር ከዓለም ክፉ ዕውቀትና ኃይል ርቃ፥ ተሰውራ በቆየች ሴት በኩል ከዓለም ርቆ፥ ከሥጋ ዕውቀት ተሰውሮ ተወለደ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 1፥10)

መድኃኒታችን ከዲያቢሎስ ሚሥጢር ሆኖ በሥጋ በመወለድ፥ ዓላማና ሥራውን እንዳያውቅበት በልዑል ኃይል ጋረደው፡፡ ይሄ ከክፉ መናፍስት ዕይታ ርቆ የተወለደበት ጥበብ እኛንም እንዲወልደን ደግሞ ቃልኪዳኑን አንድም በሥጋና ደሙ ሰጠን፡፡ እንግዲህ "ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና" የሚያሰኘው ይሄ ነው፡፡

ሆኖሞ እኛ ከመወለድ አንስቶ በእግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጠብቀን እንዳንወለድ እናቶቻችን ቅዱስ ቁርባን እየወሰዱ አልጸነሱንም፡፡ ስለዚህ በቤተሰብ የኋላ ታሪክ ውስጥ የተለያየ ባዕድ አምልኮ ሲደረግለት የቆየው የግብር መንፈስ፥ በደም ትስስራችን በኩል እያቆራረጠ መጥቶ አብሮን ተጸንሶ አብሮን ተወልዶ አብሮን ያድጋል፡፡ "የዛር መንፈስ" ማለት ከስያሜው በቀላሉ እንደምንገነዘበው፤ በዘር ሐረግ ዘልቆ የሚያልፍ የርኩስ መንፈስ ስም መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ፥ ሥልጡን ዘመናችን ይሄን ከግንዛቤው ሳጥን በማውጣቱ ምክንያት ትውልዱ ከማኅፀን ጀምሮ እየተለከፈ ተወልዶ፥ በዕድሜው ሁሉ አልሰምርለት ያለ ከርታታ ሆኖ ይኸው ይሰቃያል፡፡

በነዚህ የዘር መናፍስት ተይዞ መወለዱ ጣጣው ይሄ ብቻ አይደለም፡፡ እናትና አባት የአምልኮተ እግዚአብሔር አኗኗርን ባልመሠረቱበት ኑሮ፥ ያለ ቅዱስ ቁርባን መቀደስ የሚወልዱት ልጅ፤ ከዘራቸው ሲወራረድ በመጣው መንፈስ ተጠቂ ሆኖ ያድጋል፡፡ ይኸው ልጅ፥ እያደገና እየጎለመሰ በሚመጣበት የተፈጥሮ ዑደት ውስጥ አብሮ የተወለደው የዛር መንፈስ ሌሎች የመናፍስት አይነቶችን እየሳበ በማምጣት አሊያ እንዲገቡ ጥሪ በማድረግ፤ ግለሰቡን የርኩሳን መናፍስት ዋሻ ያደርገዋል፡፡

በሐዲስ ኪዳን ግን፥ የመልአኩ ቃል "የልዑል ኃይል ይልልሻል" ካለ በኋላ "ስለዚህ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" ሲል ነበረ የተናገረው፡፡ ይሄ ንግግር የተቀደሰ ልጅ ወላጅ መሆንን ለሚፈልጉ ሁሉ ቢደገም እንዲህ ሊጻፍ ይችላል፦ "የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲያድርባችሁ፥ የምትወልዱት ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል"፡፡

የገብርኤል መልእክት ለሰው ልጆች ባሕሪይ ሁሉ የተላከ ብሥራት መሆኑን እኛ ሳናስተውል፤ "በቅዱስ ቁርባን ኃይል በኩል ተጸልሎ የተወለደ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል" የሚለው የኛ የጸጋ ልጅነት ስጦታ ሳይገባን፤ ካለ ሥጋና ደሙ የሚጸነሰው ልጅ ላይ የዛር መንፈስ ጸልሎበት፥ የሚወለደው የዲያቢሎስ ልጅ እየሆነ፤ ትውልዳችን ባልተረዳው መንፈሳዊ ባላጋራ ዘመኑን ተነጥቆ፥ እንደ የተናጠልም እንደ የጋራም እየተጨነቅን የክፉ ትንቢት መግለጫዎች ለመሆን ተገድደናል፡፡

ሁላችን በአጽንዖት እንድናስተውል የሚገባው፥ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጸንሰን ካልተወለድን፥ በመንፈስ ርኩስ ኃይል እንወለድ ዘንድ ያለው ዕድል ቀሪ አማራጭ ሆኖ እንደሚጠብቀን ነው፡፡ ዓለም ሦስተኛ ምርጫ የላትም ከብርሃን ካልሆንን ጨለማ ውስጥ ነን፡፡ ክፉውን ካልተቃወምን በመልካሙ አንመላለስም፡፡ ለፍቅር አንገዛም ስንል በጥላቻ የሚገዛን አለ፡፡
ሕፃናት ሲወለዱ አስቀድሞ በቤተሰቦቻቸው ላይ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲኖር የተሠራ ምንም የእምነት ሥራ ከሌለ፥ ክፉው መንፈስ ስለተወለደው ልጅ መረጃ አግኝቶ አብሮት ይወለዳል፡፡ ከማለዳው ጀምሮም ከማኅፀን ሳለ ይቆራኘዋል፡፡

ሕፃናቱ ሲወለዱ የሚታዩን ለሥጋ ዓይኖቻችን ብቻ እየመሰሉን፤ በስውር የሕይወታችን ዘመን ውስጥ ሥር ሰደው የቆዩት መናፍስት እንደኛ እንደሚያዯቸው እየዘነጋን የወለድናቸው ልጆች አድገው አሁን ላይ ሱሰኛ፣ ድብርተኛ፣ ፌዘኛ፣ ዳንኪረኛ፣ ዓመፀኛ፣ ነውረኛ፣ ዘረኛ፣ ተሳዳቢ፣ ተደባዳቢና ደም አፍሳሽ በመሆን የሀገርና የሕብረተሰብ ጠንቅ ሲሆኑ የነገሩ ምንጭ በውል አይገባንም፡፡

ጌታችን ከመወለዱ አስቀድሞ ወደ ወላጁ ድንግል ማርያም መንፈስ ቅዱስ መጥቶ አድሯል፡፡ እንዲሁ ልጆች ሲወለዱ መንፈስ ቅዱስ አብሮአቸው እንዲኖር እናቶች አስቀድመው በጽንሰት ጊዜ በተደጋጋሚ ቅዱስ ቁርባን መውሰድ አለባቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በጸለለባት እናቱ ሚሥጢር ሆኖ የተወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ከክፉው ዓለም ተጋርዶ በተወለደ ጊዜ፥ የመወለዱን ነገር ሲሰማ ዲያቢሎስ በዘመኑ ነግሦ በነበረው በሄሮድስ ልቦና ውስጥ ሆኖ ነበረ የደነጠው፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ.፪)

ሰብአ ሰገል የኮከቡን ምሪት ተከትለው ሄሮድስ ጋር በደረሱ ጊዜ "የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ልንሰግድለት መጥተናል" በማለት ሲናገሩ ንጉሡ ሰምቶ ታወከ፡፡ የታወከው ሄሮድስ በሥጋ ብቻ ሳይሆን፥ ውስጡ ያለው በዘውድ ንግሥና አብሮ የነገሠው ክፉ መንፈሱ ጭምር ነው፡፡ ንጉሥ የሚሆን ብላቴና ባልጠበቀው ጊዜና መንገድ እንደተወለደ ሲሰማ ታወከ፡፡ ወንበሩን የሚቀናቀነውና ዙፋን የሚነጥቀው መሰለው፡፡ ስለዚህ ስለተወለደው ሕፃን መረጃ ለሰጡት ሰብአ ሰገል "ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።"

"ሕፃኑን በጥንቃቄ መርምሩ" የሚለው መረጃ የመፈለግ ጥያቄ በሄሮድስነት የተገለጠ የክፉ መንፈስ ሀሳብ ነው፡፡ ከእውቅናው ውጪ የተወለደውን ጌታ ከውስጥ ሆኖ ሊያየው ስለማይችል፥ ከውጪ በመሆን ወደ ውስጥ ያለውን መረጃ በጥንቃቄ ለመረዳት ሰብአ ሰገልን ሰላይ አድርጎ ቤተልሔም ሰደዳቸው፡፡ ሰብአ ሰገልም ወደ ክርስቶስ ደርሰው ወድቀውም በመስገድ አምልኮትን ሰጥተው መሥዋዕታቸውን ካቀረቡ በኋላ፤ ሰማይ ተከፍቶ በሕልም የሄሮድስን ማንነት መመልከት ስለቻሉ መንገድ ቀይረው በሌላ አቅጣጫ ሄዱ፡፡ መረጃ አጥተው የተጨነቁት ሄሮድስና መንፈሱ፥ የተወለደውን ንጉሥ ዘመን ከሰብአ ሰገል አስቀድመው ተገንዝበው ስለነበረ፤ በክፉው መንፈስ ፈቃድ በሄሮድስ ትእዛዝ አስፈጻሚነት ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ የቤተልሔም ሕፃናት እንዲገደሉ ተደረገ፡፡

እንግዲህ በዚህ መንገድ ፈተናው ሲጀምር፤፥ የመድኃኒታችን የውስጥ እውነት ሚሥጢር የሆነበት ጠላት፥ በእያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፉ ላይ እየመጣ ውስጡን ለማንበብ በብዙ ቢጥርም አልተሳካለትም፡፡ ጌታ በየሄደበት አውራጃ "ማነህ? ከወዴት ነህ? ማን ሥልጣን ሰጠህ?" እያለ፥ በየሰዉ አንደበት ቃል እየሆነ፥ መረጃ ለማግኘት ብዙ ቢሞክርም አልቻለም፡፡ መምህራን በተለምዶ ሲያስተምሩ "ኢየሱስ ሰው ነው ወይስ አምላክ?" እያለ ሰይጣን ይወዛገብ ነበር የሚሉት ይሄንን ነው፡፡

እናቶች የሚፈልጉት የተባረከ ፍሬ እንዲሰጣቸው፤ ድንግል ማርያም ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደተቀበለቺው፤ መጀመርያ ከመጸነሳቸው አስቀድሞ፥ ሰማይ ተከፍቶ ኃይል እንዲቀበሉ ቅዱስ ቁርባን እየጸለዩ ይወስዳሉ፡፡ ከጸነሱም በኋላ፥ የልዑል ኃይል ልጃቸውን እንዲጠብቅላቸው እየተማጸኑ ቅዱስ ቁርባን ይወስዳሉ፡፡ ክፉ መንፈስና የእርግማን ኃይል አብሮ እንዳይወለድ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲወለድ፤ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልጋል፡፡

አንባቢ፥ ያለ ክርስቶስ ሥጋና ደም የተወለደው ሁሉ የሥጋ ልጅ ብቻ ነው፡፡ የሥጋ መልክ እንደ 'ፎቶግራፍ' ነው፡፡ ሕይወቱ በእግዚአብሔር ኃይልና ጥበቃ በኩል የሚጻፍበት መዝገብ የለውም፡፡ ጌታችን "ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም" አለን፡፡ አሁን እኛ ሕይወት አለን ወይ? የወለድናቸውስ ልጆቻችን ሕይወት አላቸው?

በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለተባረከ ትውልድ ፍሬ የሚያስፈልገን የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ አንዲት እናት ጸንሳ ካለች፤ የክርስቶስን ሥጋና ደም እየወሰደች እስከ መውለጃዋ ጊዜ ድረስ ትቀደሳለች፡፡ እርሷ ስትቀደስ ልጇም አብሮ ይቀደሳል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀን ጀምሮ ይባርከዋል፡፡ የሚጦርህ ልጅ የሚወለደው በዚህ መንገድ ነው፡፡ የሚያጠፋህ ልጅ የሚወለደው ደግሞ ከክርስቶስ ስትርቅ ነው፡፡

አንድ እናት ከጸነሰች በኋላ ከቅዱስ ቁርባኑ እንድትርቅ የሚናገሩ ሰዎች (በተለይ አገልጋዮች) ካሉ እጅግ በጣም ትልቅ ስሕተት እየሠሩ ነው፡፡ ለምን እንደዚህ ይላሉ? መንፈስ ቅዱስ እንዳይባርከው? በቤተሰብ ውስጥ ስፍራ ይዞ የቆየው ጠላት እንዲይይዘው? ለምንድን ነው? ..በዚህ አይነት የዘልማድ ንግግር ዲያቢሎስ እየተመካ፥ ትውልዱ ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት ግዙፍ ነው፡፡ የተባረከና ከክፉ የተጠበቀ ትውልድ ለማግኘት በቃ የግድ ነው፥ የክርስቶስ ሥጋና ደም ያስፈልጋል፡፡

ከጽንሰት ጀምሮ እናት ሆነ ብላ የተባረከ ልጅ እንዲሰጣት ወደ ውስጥ ክርስቶስን እየተቀበለች፥ ከውጭ በጸሎት ውኃው፣ በወይራ ዘይቱ፣ በእምነቱ እየዳበሰች፤ በየቀኑ በጸሎትና በአምልኮት እየባረከች ስትቆይ፤ በዚህ ሁኔታ ኃይል ያለው ልጅ ይወለዳል፡፡ ይሄ ኃይሉ እግዚአብሔር ይሆናል፡፡ ይሄንን ትተን የወለድናቸውን ትውልዶች ስናይ፥ ሁለ ገብ ውደቀታቸውን በቀላሉ ለማገናዘብ አንቸገርም፡፡

ለዚህ ምሳሌ የምናደርጋት በመጽሐፈ ሳሙኤል ላይ ያለቺውን ሐናን ነው፡፡ ቤተመቅደስ ሄዳ እየጸለየች የወለደቺው ልጅ እስከ መጨረሻው ድረስ የእግዚአብሔርን ቅባት ይዞ የሚመላለስ ታላቅ አገልጋይ ሆኖ ዘመኑን ጨርሶዋል፡፡ እርሷ ከውስጥም ከውጪም የባረከቺው ልጅ ሆኖ ስለተገኘ ነው፡፡ በቅድስናው ስፍራ ላይ የበላችውና በዛ በመሥዋዕቱ ቦታ ላይ የቆየችበት ፍሬ ሳሙኤልን አስገኘ፡፡ ሳሙኤል እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚሰማው ኑሮ፣ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ በረከትና ትዳር ከልጅ ፍሬ ጋር እንዲሰጣችሁ፥ እንግዲያው ከሰማያዊው ማዕድ ተካፈሉ፡፡

ያለ ቅዱስ ቁርባን ተወልደንና እየኖርን ቆይተን ከሆነም፥ ጊዜው አልፈረደም፡፡ በተለያየ መንገድ አስቀድመው ገብተው የነበሩትም ይሁኑ አዳዲስ የሚመጡ ክፉ መናፍስት፤ የሕይወት ገጻችንን እንዳያነቡ፣ ስለ ተሰጠን ጸጋ እንዳይገነዘቡ፣ በዕድላችን ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ የምንደበቅባቸው በልዑል ኃይል ተጸልለን ስንኖር ነው፡፡ ቅዱስ ቁርባን ስንወስድ! ዲያቢሎስ አዳምን በሥጋ ተደብቆ እንዳሳተው፥ እኛም በዳግማዊው አዳም ሥጋ ተደብቀን የዲያቢሎስን ሥራ እናፈርሳለን፡፡

ቅዱስ ቁርባንን ሕይወቱ አድርጎ የሚኖር አማኝ፤ በአካሉም ይሁን በዙሪያው ያሉት መናፍስት ራእዩን ሊያውቁት፣ ጸጋውን ሊለዩትና ውስጡን ሊያነቡት አይችሉም፡፡ ነገር ግን ብዙዎቻችን የሥጋና ደሙ መቀደስ ስለሌለን፤ ከኛ በላይ ውስጣችንንና ጸጋችንን ዓይነጥላ ያውቀዋል፡፡ የተሰጠንን ዐይቶ፥ እንዳንደርስበት ይፋለመናል፡፡ አካሄዳችንን ቀድሞ ተገንዝቦ እንዳናገኘው መንገዱን ዘግቶታል፡፡ እና ምን ይሻለናል?

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባዖት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
+ ሐሙሶች ሁሉ እግር ያጥባሉ +
+ ሐሙሶች ሁሉ እግር ያጥባሉ +

   በሰሞነ ሕማማት ሳምንት በልዩ ታሪካዊ ሥርዓትና መንፈሳዊ ዳራ የሚከበረው በ'ሕጽበተ እግር' እና በሌሎች ተጨማሪ አምስት ስያሜዎች የሚጠራው ዕለተ ሐሙስ ካለፈ እነሆ ሰባት ቀናት ሆነ፡፡

   "አሁን የትንሣኤውን ክብረ በዓል አክብረን ወደ ዳግማዊ ትንሣኤው በምንሻገርበት ጊዜ ላይ ምን ነክቶህ ወደ ሕማማተ ሐሙስ ትመልሰናለህ?" የሚል ጥያቄ ታነሡልኝ ይሆናል፡፡ እኔም ጌታ በማንኛውም ጊዜ ያደረጋቸው እያንዳንዱ ሥራዎችና የተናገራቸው ቃላት በዓመት አንዴ ታስበው የሚውሉ የዝክር በዓላት ብቻ አለመሆናቸውን እነግራችኋለሁ፡፡

   ጊዜ በረጅም ቆጠራ ነጉዶ ከእውነት መነሻ ቦታ ሲርቅ፤ ክስተት መጀመሪያ ከተነሣበት አኳኋን በዘመናቶች መደራረብ ምክንያት ሲደበዝዝ፤ የድርጊት ስሜትና ዓለማ ከተፈጸመበት ቅጽበት ጀምሮ ወደፊት በተጓዘ መጠነ ልክ ሲረሣና ትዝታው በአሳብ አሊያ በቃል ብቻ ሲቀር፤ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በምድር የነበረው ክርስቶስና እና ዛሬ በስሙ የተጠራነው ክርስቶሳውያን መንገድ ተለያይተን በግራና በቀኝ ተነጣጠልን፡፡

   ለዚህም መነጣጠል ሁነኛ ማሳያ የሚሆነን ባለፈው ሳምንት ዐውደ በዓሉ የተከበረለት 'ጸሎተ ሐሙስ' ነው፡፡ በዚህም ዕለተ ቀን እንደምታውቁት ጌታና ሐዋሪያቱ የመጨረሻዋን ማዕድ እየተካፈሉ ሳለ ክርስቶስ ከመካከላቸው "ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።" (የዮሐንስ ወንጌል 13፥5)
   
   እንዲህ ያለውን መላእክትን ያስደነገጠ ታላቅ ትሕትና ወንጌል ሆኖ ትናንት የተጻፈው፤ ሁልጊዜ ትሕትናን በነባራዊነት እንኖረው ዘንድ ነው፡፡ ዘወትር በሰዎች ፊት ዝቅታን ጠባያችን እናደርገው ዘንድ ነው፡፡ በየዕለቱ ከታናናሾቻችንም ፊት አገልጋይ መሆንን እንመርጥ ዘንድ ነው፡፡

   ጌታ ነገ(ስቅለተ ዓርብ) በጎልጎታ ምድር እንደሚሞት አውቆ ዛሬን(የነጻነት ሐሙስን) ግን ከደቀመዛሙርቱ ሥር ተንበርክኮ እግር ሊያጥብ አጎነበሰ፡፡ እኛም ከመንፈስ ቅዱስ አብራክ በቤተክርስቲያን ማኅፀን የተወለድን አምሳያ ልጆቹ ስንሆን፤ ነገዎችን እየሞትን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ዛሬዎችን በርኅራኄና በገርነት እንድናሳልፋቸው 'የሚስጢር ቀን 'የተሰኘው ያ.. የክርስቶስ ሐሙስ ለዛሬዎቹ ክርስቲያን ሐሙሶች አጽንዖት ይሰጣል፡፡

   ነገር ግን እንደተገለጸው ከአምላካችን መንገድ በብዙ ኪሎሜትሮች ልዩነት የራቅን በስሙ ያመንን የድርጊት አረማውያን ነንና፤ በሰሞነ ሕማማት ሐሙስ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ዝቅ ማለት ትልቅነት እንደሆነ የሚናገሩ ቃላትን፣ ትምህርቶችንና ምስሎችን በማሕበራዊ ሚዲያ ስናመላልስ ውለን፤ ከቀኑ የማታ ክፍለ ጊዜ ጀምሮ ትሕትናን ከባሕሪያችን መዝገበ ፍለጋ ፍቀን እናጠፋለን፡፡

   ክርስቶስ ሕማማትን እየጠበቅን በሁሉ ፊት ራስን አገልጋይ እንድናደርግ ቢፈልግ ኖሮ በቃሉ ላይ "ይህንን ሥራዬን በየዓመቱ መታሰቢያ አድርጉ" ብሉ ያዝዝ ነበረ፡፡ በደቀመዛሙርቱ በኩል የዕለት ጸሎትን 'አባታችን ሆይ በሉ' ሲል ያስተማረን ጌታ፤ በደቀመዛሙርቱ በኩል የዕለት ትሕትናንም እንዲህ በማለት አስተምሮናል፤ "እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 13፥14-17)

   ይህንንም የጌታችንን ትእዛዝ የተቀበልን እንደሆነ፤ ከትንሣኤ በፊትም፣ በሰሞነ ሕማማትም፣ ከትንሣኤ በኋላም ያሉት ሐሙሶቻችን ሁሉ እግር ያጥባሉ፡፡ በቻልንበት የቸርነት ቀናት ሁሉ ላይ ልብሳቸው የቆሸሸ፣ ሰውነታቸው ያደፈ፣ በመንገድ ዳር የወደቁ ወገኖቻችንን ለማጠብ ጎንበስ ማለትን ብናውቅበትና ብናደርገው ብፁዓን እንሆናለን፡፡

   ከውልደት በኋላ ተጠምቀን መስቀል በአንገታችን ማሰር ክርስቲያን አያስብለንም፡፡ ሲሆን ጥምቀታችንና ማኅተባችን በስማችን የተከፈተ የክርስትናን ሰነድ እንጂ ክርስትናን አይወክሉም፡፡ ክርስቲያን እንባል ዘንድ የሚገባው፤ እንደ ክርስትና አባታችን ክርስቶስ ባለን የሕይወት ዘመን ሁሉ ላይ የዋህነትን ጠመኔ፤ ሌሎችን በእውነተኛ አቅም ከልብ ማገልገል ፊደል አድርገን እርሱን በመከተል፤ የቃል ምግባርን ሃይማኖታዊ ሰነዳችን ላይ ስንጽፍ ነው፡፡

   ስለዚህ አሁን ጀምሩ፡፡ ከተቀመጣችሁበት ብድግ በሉና ከወገናዊነት ፍቅር የመነጨ ጽድቅን መኖር ጀምሩ፡፡ ቤታችሁ ውስጥ ያለ አልባስ ይዛችሁ በአቅራቢያችሁ ወዳለ ነዳይ ሄዳችሁ ስጡ፡፡ እግር ማጠብ ባዶ እግርን ማልበስ ጭምር ነው፡፡ ከምትቀያይሩት ጫማ አንዱን አንሡና ስጡ፡፡ እግር ማጠብ ባዶ እግር እሾህ እንዳይወጋው መከላከል ጭምር ነው፡፡ ሌላም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ ምንም ማድረግ ለማይችሉት ወገኖች አድርጉላቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን፤ በዓመት አንዴ የሚመጣውን ሐሙስ ለማሰብ ብቻ የጌታን ሕጽበተ እግር ስዕሎችና ተያያዥ ፎቶዎችን በማሕበራዊ ሚዲያ እየለጠፉ፥ በዕለተ ቀኑ ቤተክርስቲያን ሄዶ መምጣት ብቻውን የእምነት አቁማዳን አይሞላም፡፡ እንደውም እነዚህ ወቅት እየጠበቁ አንዴ የሚከናወኑ ልምዶች በማይቋረጥ የቅድስና ምግባር ካልተደገፉ እንደ ማስታወሻ ሐውልት በመልእክታቸው ክርስቶስ ሞቷልና አልተነሣም የሚሉ ናቸው፡፡ 'እንዴ ምን ማለትህ ነው? "እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 14፥19) የሚለውን ሕያው ቃል እኮ እናምናለን' ካላችሁኝ ዘንዳ፤ ሕያው ክርስቶስ መታሰቢያን ሳይሆን የጽድቅ ሥራን ይመርጣልና፤ እናንተ ውስጥ ሕያው ሆኖ እግር ማጠቡን በመቀጠል ከነፍስ-ባሕሪይ የሚፈልቅ ድንቅ ትሕትናን በሥጋ እንዲገልጥባችሁ፤ በሐሙሶች ሁሉ ላይ እግር ለማጠብ በዝቅታ ተመላለሱ፡፡

"ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 14፥15)
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
...ብቻ..የኔ..ጌታ 😭


""አንተ ነህ የኔ አባት የልቤን አዋቂ
ሁሌም.. የማትለየኝ..ሕይወቴን ጠባቂ
ከልቤ የነገስክ ገዝተህኝ በዋጋ
ለኔ ስትል ቆሰለክ..እጅህምተ.ወጋ
ያንድ ሌሊት ግርፊያ የጅራፍ እሩምታ
ምራቅ ሲተፋብክ ጥፊ ስትመታ

...ብቻ የኔ ጌታ፣😭

..ይህ አልበቃ ብሎህ በዛ ባደባባይ
ቃልህን ጠብቀህ ቀራኒዮ ስትታይ,
ስለፍቅር..ስትል..ስለኔ..ተሰቅለህ ያሳየህኝ እውነተኛ ፍቅር.አንተ ነክ የኔ አባት ሌላው
ሁሉ  ይቅር!!

..ብቻ..የኔ.ጌታ😭

አይገርምም..!!ቀይ አበባ አይደለም የተከፈለልኝ
ቀይ ደም አፍስሶ ነው
በሕይወት ያቆመኝ

..ብቻ..የኔ..ጌታ😭

...አንተ ነክ የመንገዴ መሪ ህይወት መሰረቴ
ቃል ኪዳን የወንከኝ የገነት መብራቴ!
...ለእውነተኛው ዳኛ ቃሉን ለማያስቀር
ሆነክ ለተገኘህ ሳታረፍድ በሰአቱ
ላንተ ነው የኔ ቀን ሌላው ሁሉ ከንቱ!!😭

...ብቻ..የኔ.ጌታ!!😭


,✍️hiyab)
🔔  ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች  🔔

🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ
የብዙ ዘማሪያንን መዝሙሮችን አዘጋጅተናል
በመቀላቀል የፈለጉትን መርጠው ያድምጡ‼️

🔔➯ የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔔➯ የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
🔔➯ የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
🔔➯ የቀዳሜጸጋ መዝሙር
🔔➯ የኪነጥበብ መዝሙር
🔔➯ የቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
🔔➯ የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
🔔➯ የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
🔔➯ የዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
🔔➯ የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
🔔➯ የዘማሪት አቦነሽ አድነው
🔔➯ የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
🔔➯ የዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ


በቻናላችን ላይ የእነዚህን ድንቅ ዝማሬ እና ሌላ
ብዙ መዝሙሮችን ያገኙበታል ይ🀄️🀄️ሉን።
➲ @Orthodox_mezemur

መዝሙሮቹን ለማግኘት ከስር
OPEN የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወቅታዊ መልዕክት ለምዕመና
*
***

የደብረ ኤልያስ ብሔረ ብፁዓን መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳምን በተመለከተ በበርካታ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችና የመገናኛ አውታሮች ልዩ ልዩ ዘገባዎች እየተላለፉ ይገኛሉ።

ይህን ተከትሎም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ገዳማት አስተዳደር  መምሪያ ከሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ጋር በመገናኘት ተፈጸመ የተባለውን ችግር በተመለከተ በዝርዝር  የማጣራት ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም በማዕከል ደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛል።

ስለሆነም ዝርዝር ሁኔታው በሚገባ ተጣርቶ የተደረሰበት የማጣራት ውጤት  እውነታውን በሚገባ በሚያሳይ መልኩ በቤተክርስቲያናችን ማዕከላዊ አስተዳደር የሚገለጽ ይሆናል።

በሌላ በኩል በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ግንቦት ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ምሽት ላይ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ደረሰ ተብሎ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች የተገለጸውን ጥቃት በተመለከተ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸች በሀገረ ስብከቱ በኩል ተጣርቶ በሚቀርቀው መረጃ መሰረት ጉዳዩን  በህግ አግባብ  የምትከታተሐው መሆኑን ትገልጻለች።

ልዑል እግዚአብሔር የሟች ወገኖቻችንን ነፍስ በአብርሃም፣
በይስሐቅና በያዕቆብ ዘንድ እንዲያኖርልንም የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ ነው።

        የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
           መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት

ምንጭ: EOTC PR
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
3•  ቅዱስ ቁርባን    ከክፍል - ፮ የቀጠለ.. ወደ ጀመርነው ሀሳባችን እንመለስ፡፡ መልአኩ ለድንግል ማርያም "ደስ ይበልሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው" ብሎ አላበቃም፡፡ እንዴት እንደምትወልድ ጭምር ይነግራታል፡፡ ከተለመደው የሥጋ ፈቃድ ውጪ የምትጸንስበትን ጥበብ ያሳውቃታል፡፡ "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል"…
3•  ቅዱስ ቁርባን

  ክፍል - ፯

       3.3•  የመናፍስት ውጊያ በቅዱስ ቁርባን ላይ

ውድቀትን በባሕሪዩ የተጣባት ክፉ መንፈስ "አምላክ እኔ ነኝ" ሲል ዋሽቷል፡፡ እንደ ፈጣሪ መሆን ተስፋ አልቆርጥ ያለ ምኞቱ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ወዳስገኛቸው እያመለከተ "የእኔ ናቸው" ማለትን ከጥንት ጀምሯታል፡፡ የሰውን ልጅ ጭምር!

ሰውነት ቤተመቅደስነት እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ ዲያቢሎስ በዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ ነው መመለክ የሚፈልገው፡፡ የሰውን ልጅ መግዛት፣ መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ልክ እንደ አምላክ "ይሄን ይሄን አትንኩ" የሚላቸውን ትእዛዛት ያሰቀምጣል፡፡ እርሱ እንደፈቀደው እንዴት መኖር እንዲገባን ደንብና ሥርዓት የሚያሳዩ ሕግጋት ያረቃል፡፡ ከእግዚአብሔር በተቃራኒ የሚሠራ መንፈስ እንደሆነ ሲታወቅ፥ ሕግ አድርጎ የሚያስቀምጣቸው ትእዛዛቱ የእግዚአብሔርን እንደሚጻረሩ እንዲሁ ለመገመት አይከብድም፡፡ ጽድቅን የሚጠሩና በጽድቅ የሚያኖሩ ማንኛቸውንም ነገራት አትንኩ ይላል፡፡

ይሄ የክፋት ኃይል አዳምን ካሳተ በኋላ ዓለምን በመላ በራሱ መስመርና ዓላማ ለመምራት ያለመታከት ሲደክም ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ተሳክቶለትም የምድር ማዕዘናት ጽድቅን በሚቃወሙ፣ በሥጋ ድክመት ላይ በሚመኩ ሥርዓቶች እንዲተዳደሩ አስገድዷል፡፡ ከዚህም የተነሳ በምድራችን የአስተሳሰብና የኑሮ ሚዛን ቅዱስ የሆኑት ከብደው፥ ርኩሳኑ በእጅጉ ቀልለውና በዝተው ይገኛሉ፡፡

ለዚህ በቂ ማሳያ አድርገን የምንናነሳው ርእሳችንን፥ የአዲስ ኪዳኑን አማናዊ ቃልኪዳን፥ የመድኃኒታችንን ሥጋና ደም ነው፡፡

[በተለይ] ባለንበት በዚህ ዘመን፥ ቅዱስ ቁርባን ሲባል የሚጠራው የኪዳኑ ስጦታ ከሰዎች ሕይወት በእጅጉ የራቀ ጉዳይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ከታዳጊነት እስከ መካከለኛው የዕድሜ እርከን ያሉ ብዙ አማንያን፥ ከሰማያዊው ማዕድ መካፈል ካቆሙ ሰነባብተዋል፡፡ ቅዱስ ቁርባን በእርጅና ጊዜ የሚወሰድ ልምዳዊ ድርጊት ወደ መሆን ከመጣ ቆየት ብሏል፡፡ ሕፃናት እስከ ዐሥራ መጀመሪያዎቹ ይቆርባሉ፤ ከዛ ሥጋና ደሙ የጠፋ እስኪመሰል ከቁርባን ጠፍተው ያድጋሉ፡፡
 
በመሆኑ ብዙው ሰው፥ "አንቱ በመቁረቢያ ዕድሜዎት እንዲህ ያደርጋሉ እንዴ?" እስከሚባልበት የጊዜ ማምሻ ድረስ ሕይወት እንደመራው፥ ኑሮ እየጣለው፥ እርሱም ሌላውን እየጣለ፥ የነፍስ እውነትን ረስቶ ይቆይና፤ የዕድሜ በረከት አግኝቶ ለሽበት ሲደርስ ቅዱስ ቁርባን ይቀበላል፡፡ ለዚህ ካልታደለም በዛው ጥቁር ጸጉር ሳለ፥ ጥቁር ኃጢአትና ጨለማ ዘመን ወርሶት፥ "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ እኔ በእርሱ እኖራለሁ እርሱም በእኔ ይኖራል" ያለውን፥ የክርስቶስን ወዳጅነት በወጣትነቱ ሳያገኘው ወደ መቃብር ይሸኛል፡፡

ለመሆኑ ይሄ የሆነው ለምንድነው? ስለ ቅዱስ ቁርባን ስንማር የቆየነው ቃል ምንድን ነው? በውስጣችን ተቀርጾ ያለው መንፈሳዊ ትምህርት ምን አይነት ነው? እንዴት ነው ክርስትናን የተረዳነው? የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት እንዴት ነው የምንመለከታቸው? ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ ሞትን ድል ነሥቶ የዘላለም ሕይወት ሰጠን የሚለውን የድኅነት አገላለጽ እንዴት ነው የተገነዘብነው?

ክርስቲያኖች ነን ስንል መቼም በክርስቶስ አምነን ነው፡፡ በክርስቶስ ስናምን፥ የተናገራቸውን የታመኑ ቃላት እናምናለን ማለት ይሆናል፡፡ እንግዲያው "እንካችሁ፥ ብሉ ይሄ ሥጋዬ ነው፤ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ኃጢአት የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይሄ ነው" ያለውን ቃል እንዴት ነው ያመንነው?

"ሰው ዓለሙን ሁሉ አትርፎ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?" የሚለው ንግግር የቅዱስ ቁርባን ልክ ይዞ ቢነገር "ክርስቲያን ነገርን ሁሉ አድርጎ የክርስቶስን ሥጋና ደም ካልተቀበለ ምን ይበጀዋል?" ሊባል ይችላል፡፡ ይህም ማለት እንኳን ዓለማዊ፥ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ሁሉ ምእመናን አድርገው፥ ከሥጋና ደሙ ጋር ባወቀ ካልተገናኙ ትልቁን ዋጋ አጥተውታል ማለት ነው፡፡ አስተምህሮቱ "የሚሥጢራት ሁሉ ፍጻሜ ቅዱስ ቁርባን ነው" እያለ የሚያውጀው ለዚህ ነው፡፡

ታዲያ ምንድነው የምናስበው? ምንድነው ከውስጣችን ቆይቶ ለዘመናት የገዛን አመለካከት? ስለ ዘላለም ሕይወት ያለን መንፈሳዊ እይታ ርቀቱ እስከየት ይጠልቃል? ስለ መቁረብ ስናስብ ምንድነው ወደ ጭንቅላታችን አስቀድሞ የሚመጣው?
  
ብዙ ክርስቲያኖች ለቅዳሴ ይቆማሉ፡፡ የሚቆርቡት ግን ከሕፃናትና ከአዛውንት ውጪ ከእጅ ጣቶች የማይበልጡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይሄም ነገር የተለመደ ከመሆን አልፎ አሁን ያልተለመደው የወጣቶች ከሕይወት እንጀራ መቁረስ ሆኗል፡፡ ለምንድነው ነው እንደዚህ የሆነው? ለምንድነው ወጣቶች ከክርስቶስ ሥጋና ደም የማይቀበሉት? ለምንድነው መምህራን ስለዚህ ነገር አበክረው የማያሳስቡት? የሚያሳስቡትንስ፥ አማኙ ሕብረተሰብ የማይሰማቸው ለምንድነው?

ሥርዓተ ቅዳሴ ያለ ቅዱስ ቁርባን መሥዋዕት ቅዳሴ ይባል ዘንድ አይችልም፡፡ ዝርዝር ትንታኔ ውስጥም ሳንገባ ከስያሜው ብንጀምር "ቅዳሴ" የሚለው ቃል የሚጠቁመው አንድን ነገር የመቀደስ ሂደት ነው፡፡ ያ በምስጋና፣ በአምልኮትና በኅብረት ጸሎት የሚቀደሰው ነገር ሕብሥተ ስንዴው እና ሕብሥተ ወይኑ ነው፡፡ የተቀደሰው ማዕድ ከዛ በእምነት የሚወስዱትን ሁሉ ይቀድሳቸዋል፡፡ ከቤተልሔም እስከ ቀራኒዮ የሚገሰግሰው ቅዳሴ፥ ዋነኛ አንድምታው ይሄ ነው፡፡

ቅዳሴ የአዲስ ኪዳን ቃልኪዳን የሚፈጽምበት ሰማያዊ ሥርዓት ነው መባሉ በክርስቶስ ሥጋና ደም ምክንያት ነው፡፡ ያለ ቅዱስ ቁርባን ቅዳሴ የለም፡፡ በዚህ መሠረት ቅዳሴ አስቀድሰን ከተቀደሰው ምግብና መጠጥ የማንሳተፍ ሰዎች፥ ምን ቀድሰንና በምን ተቀድሰን እንደተመለስን ያልታወቀበት ቆይታ አድርገን ነው የመጣነው ማለት ነው፡፡

ሱታፌ ቅዳሴ ኖሮ ከቅዱስ ቁርባን አለመቀበል አግባብ እንዳልሆነ የቤተክርስቲያን አያሌ ሥርዓተ መጽሐፍት በግልጽ ይደነግጋሉ፡፡ ሌላውን እንተወውና ራሱ ቅዳሴ ከቅዱስ ቁርባን [በፍትሐ ነገሥት ከተዘረዘሩ በቂ ምክንያቶች ውጪ] ሥጋና ደሙን አለመቀበል የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ስለመሆኑ ገና በመግቢያው ክፍል ላይ ያስጠነቅቃል፦

        "በቅዳሴ ጊዜ የሚገኙ ምእመናን፥ መጽሐፍተ ቅዱሳትን ባይሰሙ፣ ቅዳሴ እስኪፈጸም ድረስ ባይታገሡና ከቁርባንም ባይቀበሉ ከቤተክርስቲያን ይሰደዱ፤ ሕገ እግዚአብሔርን አፍርሰዋልና"

                                                        መጽሐፈ ቅዳሴ

የቅዳሴ ብቻ ሳይሆን የንስሐም አድራሻ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ "በአዲሱ አቁማዳ አዲሱ ወይን ሊሞላ ይገባል" የሚለውን የጌታ ትእዛዝ ይዛ፥ ቤተክርስቲያን ማንኛውም ግለሰብ ሥጋና ደሙን ከመቀበሉ በፊት ንስሐ እንዲገባ ታዝዛለች፡፡ በመሆኑ ቅዳሴ ያስቀደሰ ሰው መቁረብ እንዲገባው ሁሉ፥ ንስሐውን የጨረሰ አማኝም ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ምርጫው አይደለም፡፡ የውዴታ ግዴታው ነው፡፡ ጸድቶ የተቀመጠ ብርጭቆ ለታጠበለት አገልግሎት ካልዋለ፥ ቆሽሾ ከተቀመጠው ብርጭቆ ከመታጠቡ ባሻገር አልተለየም፡፡ ንስሐ የገባም አንድ ሰው፥ ከእግዚአብሔር መንግሥተ ማዕድ ተካፍሎ የዘላለም ሕይወትን የቃልኪዳን ማኅተም በሰውነቱ እስካልያዘ ድረስ የንስሐውን አገልግሎት ከግብ አላደረሰም፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 6፥51)
እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ እንኪያስ ለምንድነው ምእመናን ከቅዱስ ቁርባን የተለዩት? ከክርስቶስ ማዕድ መካፈል ያቃተቸው ክርስቲያኖች ስለምን በርካታ ሆኑ? አዲስ ኪዳንን የምሕረት ዘመን ያሰኘው የመዳን ዋስትናችን የመስቀሉ መሥዋዕት ሆኖ እያለ ብዙዎች ከእርሱ ለምን ራቁ? የተዋሕዶ ሃይማኖት አንዱ ዓምድ (ዶግማ) የበጉ ሥጋና ደም ነው መባሉ በአማኞች ሕይወት ላይ ለምን በተጨባጭ አልተተረጎመም?.. ?

የነዚህና መሰል ጥያቄዎች ቀጥተኛ መልስ በመነሻ አንቀጻችን ላይ የተጻፈው ይሆናል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ያለማቋረጥ የሚጥረው ዲያቢሎስ፥ አትንኩት ብሎ በዐዋጅ እንዲከለከሉ ካደረጋቸው ገደቦች መካከል መቀደስ (ቀ ጠብቆ ይነበብ) በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል፡፡

ስናስታውስ፥ በመጀመሪያ በእኛ በእግዚአብሔር መካከል "አትብሉ"ን አሰበልቶ ከፈቃዱ ነጥሎን ነበር፡፡ አሁንም ይሄው አካሄዱ ይዘቱን ሳይለውጥ ቀጠለና "ብሉ" የተባለውን አትብሉ አስደርጎ ፈቃዱን እንዳንኖር እየተዋጋን ይገኛል፡፡ የተከለከልነውን አስፈቅዶ፥ የተፈቀደልንን ከልክሎናል፡፡

አንባቢ የምለውን ተመልከት፥ በነገሩ ላይ ጌታ ማስተዋልን ይስጥህ! ክፉው መንፈስ እንደ ፍላጎቱ በሰውነታችን ላይ ፈላጭ ቆራጭ እንዲሆን እኛነታችንን ከመንፈስ ቅዱስ መለያየት ያስፈልገዋል፡፡ በቃ ቅዱስ ቁርባን ላይ ከተለያየ አቅጣጫ የተከፈተው አጠቃላይ ዘመቻ ከዚህ የጠላት ፍላጎት ይመነጫል፡፡ ከእግዚአብሔር በራቅን ልክ እርሱ ወደኛ የሚጠጋበት ርቀት ያጥርለታልና፥ ከአምላክ ጋር የሚያስተባብረንን የኪዳኑን ጸጋ እንዳናገኘው ባገኘውና በሆነለት መንገድ ሁሉ እየተጠቀመ ያሸሸናል፡፡ እንዴት? 

                         3.3.1.  በኃጢአት በኩል

ኃጢአት በሰውና በአምላክ መካከል ያለ የዓመፅ ግድግዳ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር እንዳንሆን የሚፈልገው መንፈስ፥ ኃጢአትን በማስተዋወቅ፣ በማስፈጸምና በመምራት ከመለኮት ንጽሕና ይለያየናል፡፡ ብቻ ሳይሆን፥ ኃጢአት ከሕይወታችን ሳይወጣ እንዲቆይ በማጽናት ቅድሰና እንዳያገኘን ነቅቶ ይጠብቃል፡፡

የመድኃኒታችን ሥጋና ደም ስለ ኃጢአት ሥርየት የተሠዋ ዘላለማዊ መሥዋዕት እንደሆነ በክፍል ፫ አይተናል፡፡ እነሆም ዲያቢሎስ በኃጢአት ረግረግ ተውጠን እንድንያዝ ሲወድ፥ ኃጢአትን ከሥር መሠረቱ ነቅሎ የሚጥለውን ቅዱስ ቁርባን በእጅጉ ይጠላዋል፤ ይፈራዋል፡፡ ይሄንን ፍራቻውንም ባላጋራ ሆኖ ላደረበት አስተሳሰባችን ለማጋባት የሚከተሉትን ሁለት ዋና ዋና ስልቶች አቀናጅቶ ይተገብራል፡፡ እንመልከታቸው፡፡

                      1•  ከኃጢአት የመላቀቅ ፍራቻ

"እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ለሥጋና ደሙ የበቃሁ አይደለሁም፤.. " የሚሉ ዓይነት ምላሾች፥ ቅዱስ ቁርባን ለምን እንደማይወስዱ ከተጠየቁ ብዙ ምእመናን ዘንድ ይነገራሉ፡፡ እነዚህ ንግግሮች በአብዛኛው ሰማያዊውን አምኃ ከማክበርና ከመፍራት የተነሱ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ በእርግጥስ፥ ከኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ አካል የሚያካፍለን ክቡር ሥጋና ክቡር ደም እንደምን ያለ የክብር ጥግ፣ እንዴት ያለ የፍርሃት መጨረሻ ቢቸረው (ቸ ጠብቆ ይነበብ) ይመጥነው ይሁን?

ነገር ግን መላእክት፣ ቅዱሳን እና ቀደም ሲል እምነታቸውን በየዋህነትና በፍቅር ሲኖሯት የነበሩት ሁሉ ለቅዱሱ መሥዋዕት የሰጡት የክብር ፍራቻ፥ ለዛሬዎቹ እኛ፥ ከኃጢአት ሳይርቁ የመኖር ፍራቻን የምናለባብስበት መጋረጃ ሆኖ ነው እያገለገለ ያለው፡፡ የአብዛኞቻችን "ለክርስቶስ ሥጋና ደም አልገባም" (ገ ጠብቆ ይነበብ) ከምትለዋ የትሕትና ንግግር ጀርባ፥ ኃጢአትን የለመደ ሽሽግ ማንነት አለ፡፡

በሥጋዊቷ ዓለም ስንኖር ክፋቶች ክፉነታቸው እንዳይገለጥልን፥
ቢገለጥልንም ከክፋቶች እንዳንመለስ ማድረግ የክፉ መናፍስት ቀንደኛ ሥራ ነው፡፡ ይኸውም ከእግዚአብሔር የሆነ ቅዱስ ዕውቀት በማሳጣትና ኃጢአትን ተላምደን እንድንኖር ሁለንተናችንን በማጠር የሚከውኑት ይሆናል፡፡ ስለ ኃጢአትና የኃጢአት ራስ ዲያቢሎስ ደገኛ ትምህርት ካለማግኘታችን ጋር ተያይዞ፥ ዓለም በዘመናት ሂደት ሰብስባ ባጠራቀመቺው የአስተሳሰብ ሥርዓት እንድንቀረጽ እየሆነ ከልጅነታችን እናድጋለን፡፡

ይሄ አስተዳደጋችን ደግሞ፤ ጠባይን፣ ፍላጎትን፣ ውሳኔንና ዓላማን ሁሉ በተጽዕኖ የሚነካ፥ ከሕይወታችን ጋር ተጋብቶ ያለ የማንነት መገለጫችን ይሆናል፡፡ ክፉው ለዚህ አስተዳደጋችን ነው እንግዲህ ኃጢአትን በተለያየ ዕውቀት በኩል ለአመለካከታችን በመመገብ፥ ዓመፃዎችን ከለጋነት የሚያለማምደን፡፡ [ወጣቶች፥] ኋላችሁን አስቡት እስኪ፡፡ እስከ አሁናችሁ ድረስ ያወቃችኋቸውና የለመዳችኋቸው ነገራት ምንድን ናቸው? ለጽድቅ ያላቸው ቅርበት ለኃጢአት ያላቸው ርቅትስ ምን ይመስላል?..

ምእመናን ከኃጢአት ጋር ተዛምደው የኖሩባቸው የዕድሜ ቆይታዎች ወደ ተቀደሰው መብል እንዳይመጡ የሚጠልፉ ዕንቅፋቶች ናቸው፡፡ ትናንትናችን ተሳስሮት የቆየው የልምድ ኑሮ ለውጥን አፍኖ የሚይዝ የክፉ መንፈስ ጥምጣም ነው፡፡ ለረጅም ጊዜያት ከውስጣችን ሲገነባ የቆየን ካብ ማፍረስ ራሱን የቻለ ጣር አለበት፡፡ ለምሳሌ ሐሜት ዕለት ተዕለታችን የሆነብን ሰዎች ከቅዱስ ቁርባን በኋላ ያሉት ቀኖቻችንን ምን እንደሚያወሩ ከወዲሁ ስለምናውቅ "የበቃሁ አይደለሁም" በሚል ቋንቋ ሸፍነን "ልምዴን የምተው አይደለሁም" የምትል የውስጠታችንን መልእክት እንተነፍሳለን፡፡ ዝሙት፣ ስካር፣ ዳንኪራ፣ ጉቦ፣ ውሸት፣ ስርቆት፣ ትዕቢት፣ ምቀኝነት፣.. ምሳሌ እንደጠቀስነው እንደ ሐሜቱ ናቸው፡፡ እነዚህና ሌሎችም "ለቁርባን አልገባም" እያልን እሽሩሩ የምንላቸው፣ የዲያብሎስ መንፈስ በምሽግነት የተደበቀባቸው፣ እንድላቀቃቸው በጽድቅ ቀናዒነት ያልጨከንባቸው፣ ከዘወትር ደቂቃዎቻችን መካከል ቦታ ያገኙ ኃጢአቶቻችን፥ የአዲስ ኪዳኑ ታላቅ መሥዋዕት ከሕይወታችን እንዲቋረጥ ለአጥፊው መንፈስ በብዙ አግዘዋል፡፡

                     2•   ከኃጢአት ያለመላቀቅ  ፍራቻ

ቅዱስ ቁርባንን የተመለከቱ እንደ ማኅበረሰብ ደንቦች ሲዛመቱ ከምንሰማቸው ወጎች መካከል "ቁርባን ዓለም በቃኝ ላለ ሰው ነው፣ ከተቆረበ በኋላ ኃጢአትን መሥራት ያልተላቀቀ ይቀሠፋል" የሚሉት ዝነኛ ሆነው ከጫፍ ጫፍ ተዳርሰዋል፡፡ ያሳዝናል!

ወገኖቼ፥ ክርስቶስ የሚያፈቅር እንጂ የሚቀሥፍ፣ የሚያከብር እንጂ የሚያዋርድ፣ የሚያነሳ እንጂ የሚጥል፣ የሚያቅፍ እንጂ የሚገፋ በጭራሽ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም፤ ወደፊትም አይሆንም፡፡ እንኳን ሰዎችን "ሥጋና ደሜን ከወሰዳችሁ በኋላ ኃጢአት ሠራችሁ" ብሎ ሊያጠፋ ይቅርና፥ የጠፉ ሰዎችን ሲያይ የሚያለቅስ የዋህ አባታችን እንደሆነ የሰቀለቺውን ኢየሩሳሌም ባየ ጊዜ እንባውን አፍስሶ ገርነቱን ገልጧል፡፡ "በቅዱስ ቁርባን ምክንያት" መቅሠፍት ይመጣል የሚሉ መነሻቸው ያልታወቁ ድምፆች፥ ዲያቢሎስ የነዛቸው ተንኮሎች እንደሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡

አዎ፤ የጌታን ሥጋና ደም ሳይገባን (ገ ላልቶም ጠብቆም ይነበብ) መውሰድ አይፈቅድም (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፥27)፡፡ ይሄ የሕግ ድንበር የተሰመረው ግን በመሢሑ በሥጋ መምጣት ያላመኑ፣ አምነውም በስሙ ያልተጠመቁ፣ የመስቀሉን ፍቅር ያልተቀበሉ፣ የቅዱስ ቁርባንን ሚሥጢር ያልተማሩ፣ መንፈሳዊ ኃይልን ለመፈታተን የሚቀበሉ፣ ለሌላ ድብቅ ተልዕኮና አጀንዳ የቀረቡ፣ ከመቁረብ በፊት ንስሐ ያልወሰዱ ሲኖሩ ለማረም ተፈልጎ እንጂ ክርስቲያኖችን ለማስፈራራት ታስቦ አይደለም፡፡ እንደውም ክርስቲያን ከክርስቶስ እንጀራና ጽዋ የማይካፈል ከሆነ ነው ዕዳ ያለበት፡፡
አንድ አማኝ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለበት ጊዜ በኋላ ኃጢአት ቢያስተው ይቀሠፋል የሚባለው ሙሉ ለሙሉ ሐሰት ነው፡፡ እንዲህ ቢሆንማ፥ እኔን ጨምሮ ስንት ሰው እስካሁን ተቀሥፎ አልቆ ነበረ፡፡ "እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን" ከምንልበት የቅዳሴያችን የኅብረት ተማጽኖ በተቃራኒ የተሰለፈ፥ ዲያቢሎስ የሚያራግበው የወሬ ነፋስ ነው ይሄ፡፡

ሐዋሪያው ጴጥሮስ ሊቀ ካህኑ ኢየሱስ ራሱ ባርኮ ባቀበለው ሥጋና ደሙ ስለመቀደሱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የመከራዋ ለሊት ስትደርስ፥ ማታቸው ስትመጣ፥ የጨለማ ሥልጣናቸውን አግኝተው ክርስቶስን ያሰሩ ጉልበተኞች "አንተም ከእርሱ ጋር ነህ" ቢሉት ከአንድም ሦስቴ "ኸረ አላውቀውም" ሲል ካደ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 18፥25 ፤ የሉቃስ ወንጌል 22፥58) ሥጋውን በልቶ፥ ደሙን ጠጥቶ አላውቀውም? እንዴት ነው ነገሩ?

ከተቆረበ በኋላ ስሕተት ሊኖር እንደሚችልና ጴጥሮስና ሐዋሪያቱ እነሆ በታሪካቸው አስተማሩ፡፡ አስቀድመው ሲከተሉት፣ ድንቅ ሥራውን ሲያዩ፣ ቃሉን ሲሰሙ የቆዩት ሥጋና ደሙን ከተቀበሉ በኋላ እንደማያውቁት ሆነው ጥለውት ሸሹ፡፡ ወደነበሩበት ሊመለሱ አፈገፈጉ፡፡ ሕብረተሰባችን መካከል ዛሬ እንደሚመላለሰው ወሬ ቢሆን፥ ሐዋሪያቱ መቀሠፍ ነበረባቸው፡፡

ነገር ግን ጴጥሮስ ሥጋና ደሙን ወስዶ ስለፈጸመው ጥፋት ንስሐ ገባ እንጂ አልተቀሠፈም፡፡ (የሉቃስ ወንጌል 22፥62) እንደውም ሦስት ጊዜ ደጋግሞ ከድቶ የነበረውን ስምዖን፥ በደልን ፈጽሞ የሚረሳው ጌታ ከትንሣኤው በኋላ ሲያገኘው "ትወደኛለህን?" አለው፡፡ ከዚህ በፊት በአስቸጋሪው ወቅት "አላውቀውም" ሲል የነበረው አገልጋይ፥ እዚህ ከንስሐ በኋላ ቋንቋው ተቀይሮ ሦስቴ "እንድወድህስ አንተ ታውቃለህ" ይለው ጀመረ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 21፥15-17) ፍቅሩንም ሕይወቱንም አሳልፎ ሰጠው፡፡ ወንጌል የሚያውቀው እውነት እንግዲህ ይሄ ነው፡፡

ዛሬ አንዳንድ የንስሐ አባቶች፣ አገልጋይ ነን የሚሉ ሰዎችና ማኅበረሰብ ወጣቱን ከማስተማር ይልቅ ያርቁታል፡፡ "ወዮውልሽ" አይነት ማስፈራሪያዎች ከዛም ከዚህም ይወረወራሉ፡፡ ጫት ሲበላ ተው ትቀሠፋለህ የሚል እምብዛም የለም፡፡ መጠጥ ሲጠጣ ተው ትጠፋለህ የሚል ትንሽ ነው፡፡ ሥጋና ደሙን ልውሰድ ሲል ግን ብዙዎች ያንጎራጉራሉ፡፡ ለምን? ለምን ከሥጋና ደሙን ወጣቶችን እናርቃለን?

ወጣቶች እወቁ! ቅዱስ ቁርባንን ለመውሰድ የተቀመጠ የዕድሜ ገደብ የለም፡፡ "ወጣት ከሆንክ ስለምታጠፋ አትቁረብ" የሚሉት፤ ስለ አምልኮት ሕይወትና የክፉ መናፍስት ጥልቅ ሥራ በተግባር ያልተገነዘቡ፥ በልምድ አካሄድ የሃይማኖትን ጎዳና የጀመሩ ሰዎች እንጂ ቤተክርስቲያን አይደለችም፡፡ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቀድሳ ሥጋና ደሙን አዘጋጅታ ጠቦቶቿን ከእረኛቸው ሥጋ የማካፈል አደራዋን ዘወትር ትወጣለች እንጂ ዕድሜውን ቆጥራ "አንተ አትቁረብ" የምትለው አንድም ወጣት የለም፡፡

ሲሆንማ፥ ይልቁኑ ሥጋና ደም ለማን በጣም ያስፈልጋል ካላችሁኝ ለወጣቱና ለጎልማሳው ነው ያስፈልጋል የምለው፡፡ ምክንያቱም ስሜታዊነት የሚወጣበት፣ ጉልበት የሚጠነክርበት፣ ብዙ ሥራ የሚሠራበት፣ ትዳር የሚመሠረትበትና እንደ አገርም አምራች ዜጋ የሚኮንበት የዕድሜ ክልል ስለሆነ፥ በዚህ የጉብዝና ጊዜ ነው እግዚአብሔር አብሮ መገኘት ያለበት፡፡ ስሜታዊነትን ወደ መንፈሳዊ ኃይል እንዲቀይረው፣ ጉልበታችን በመናፍስት እንዳይደክም አሊያ ለክፋት እንዳይውል፣ ሥራችን እንዲባረክ፣ ትዳራችን እንዲሰምር፣ የአገር ፍቅር ከታሪክ ቁጭት ጋር ያለው የተቀደሰ ዜጋ እንዲኖር ሥጋና ደሙ መቅረብ የነበረበት ለወጣቶች ነበረ፡፡ አልሆነም! ተገላበጠና ወጣቶች ከቅዱስ ቁርባን ሲርቁ ይኸው ነገራችንም ከብዙ እውነቶች ተገላብጦ ቁጭ አለ፡፡

#ጸባዖት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
2024/06/08 05:17:51
Back to Top
HTML Embed Code: