Telegram Web Link
በፍርስራሽ ለተከበበውን የአራት ኪሎ መንገድ ጀርባዬን ሰጥቼ ሽቅብ ወደ ስድስት ኪሎ walk እያደረግኹ ነበር።

ድንገት ገንዘብ ሚንስቴር ጋር ስደርስ "ሶፊ! እኔ አላምንም ፤ አንተ ነህ? " የሚል ውብ የሴት ድምፅ አባነነኝ። (እኔ ለመሆኔ እኔም እርግጠኛ አልነበርኹም ።)

ፊቷን ጥቂት ትኩር ብዬ አየኹት በሜካፕ እና በረዥም ዊግ ብትደበቅም ለየዋት " ሐመልማል ?! " እቅፍ አደረግኋት ። እየተያየን ደግመን ደጋግመን ተቃቀፍን...ሰው ምን ብሎን ይሆን ? እኛ ምን ገዶን ! ናፍቆታችንን አንገት ለአንገት ተቃቅፈን አስታገስን ።

የታምራት ዘፈን ትዝ አለኝ...

"እኛን ነው ማየት ስትመጪ እርሱ ብሎት
ለጉድ ተናንቀን በእምባ አንገት ለአንገት
ሰው አያግደን..."

ከብዙ ድብልቅልቅ ስሜት ጋር...አቀፍኋት።

ቸኩላ ነበር...ሰዓቷን አየችው..."ሶፊዬ ዛሬ በጊዜ ከጨርስኹ እደውላለኹ ካልኾነ ሰሞኑን ጊዜ አመቻችተን እንገናኛለን " አለች።

በእሺታ ፊቴን ወዘወዝኹ...

እጆቻችን ተያይዘዋል...የግራ እጄን ከፍ አድርጋ የቀለበት ጣቴን አየችው..."አገባህ እንዴ ሶፊዬ?" አለች እንደመደንገጥ እየቃጣት።

ሁለት ፀጉር አብቅዬ ማግባቴ እንዴት አስገረማት ስል በውጤ እያሰብኹ። "አዎ አንቺስ ?" አልኋት ።

እንዳላገባች በጥልቅ ሐዘን ነግራኝ ስልክ ከተለዋወጥን በኋላ ተሰናብታኝ ሄደች።

ሐ መ ል ማ ል !

በአይነ ስጋ ከተያየን 10 አመት ይሆነናል።ባህር ማዶ መሄዷን እንኳን ሳትነግረኝ ነበር የሄደችው ፤ መሄዷን እንደ ሩቅ ሰው ከሰው ሰማሁ ። "አንድ እለት ደውላ ለስንብት ስለከበደኝ ነበር ዝም ብዬህ የሄድሁት ። " አለቺኝ ከዚያ ወዲያ ትኑር ትሙት አላውቅም። ከሰውም አልሰማሁም ።

ወይ ሐመልማል !

እወዳት ነበር ፍቅርን የማውቀው በእርሷ ነው።ምንም ባልነበረኝ ጊዜ ነው እሷም ትወደኝ የነበረው ። እኔ ስለ ራሴ ተስፋ በቆረጥኹበት ወቅት እንኳን ተስፋ ልትሆነኝ "አንተ ትልቅ ሰው ትሆናለህ ታገስ ፤ ይሄ ቀን ያልፋል " እያለች ታበረታኝ ነበር ። በሞላበት የምትፈስ አልነበረቺም የኔ ሐመልማል ፤ በጎደለበት የምትሞላ ደግ ሰብ ነበረች ሐመልማሌ !




ይቺን ሐመልማል ነው ዛሬ በድንገት ያየኋት ?






የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
በዝምታ አብረሃት ልትቀመጥ የምትችል አይነት ሰው ናት። የዝምታን ውበት ታውቀዋለች ። የዝምታን ውቅያኖስ ፤ በንግግር ማዕበል አታደፈርስም ።ይልቁንም ከስክነቱ ጋር አብራ ሰክና ፤ አርምሞን ታጸናለች። አብረሃት ቁጭ ብለህ እንድታስብ እድሉን የምትሰጥ አይነት ሰው ነች ።ያሻህን ጊዜ ውሰድ ትጠብቅሃለች። የፀጋዬን ስንኝ እየቋጠረች የምትጠብቅ ይመስለኛል...

"ከሰው መንጋ እንገንጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።"


...ንግግሯ የሚናፈቅ አይነት ሰው ብትሆንም ወሬዬ አማረልኝ ብላ አትዘላብድም ። " አዋቂ ነች " ለመባልም በሁሉ ነገር ላይ አስተያየት አትሠጥም ፤ የምታውቀውን ብቻ ትናገራለች እርሱንም ከተጠየቀች። (ስንቱ አዋቂ ለመባል አለማወቁን ሲገልጥ እያየች በአርምሞ ሳትታዘበዘው አትቀርም ።)

she is someone you can have comfortable silence with...is it beautiful?



ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻዬን ገልጬ ስለ እኔ እና ስ'ላንቺ እንዲህ ፃፍኹ ፡


"አጋጣሚ አይደለም እግዚያብሔር ነው ያገናኘን። "
" ስማ ቢል ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው ፡ ከዛሬ ጀምሮ የእራት ሰአት ላይ መፅሀፍ ስታነብ እንዳናይ "
.....

ይህን ያሉት በአንድ ወቅት ከፎርብስ መፅሄት ጋር ኢንተርቪው አድርገው የነበሩት የቢልጌትስ አባት ናቸው ።
ሚስተር William H. Gates ይህን በተመለከተ ሲናገሩ .....
ቢልጌትስ ከልጅነቱ ጀምሮ አንባቢ ነበር በዚህ ነገሩ ደስተኞች ብንሆንም ፡ ለማንበብ ካለው ፍቅር የተነሳ የእራት ሰአት ላይ እንኳን ንባቡን አያቆምም ። ስለዚህ እኔና እናቱ ፡ በእራት ሰአት ወቅት ምንም አይነት መፅሀፍ ይዞ ወደገበታ እንዳይቀርብ ህግ እስከማውጣት ደርሰን ነበር ብለዋል ።
.......

የማይክሮሶፍት መስራች የሆነውን የቢሊየነሩ የቢልጌትስ የንባብ ልማድ የጀመረው ያኔ ነበር ። ይህ ልማዱ አሁንም ቀጥሎ ፡ ቢልጌትስ በሳምንት አንድ መፅሀፍ ፡ በአመት ከሀምሳ መፅሀፍት በላይ ያነባል ።
በቤቱ ውስጥ ባስገነባው ግዙፍ ቤተመጻህፍት ውስጥም ፡ ሊዮናርዶ ዳቬንቺ በእጁ የጻፈውን Codex Leicester" የተባለ በ 30.8 ሚሊዮን ዶላር የገዛውን መፅሀፍ ጨምሮ ፡ ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ መፅሀፍት ይገኛሉ ።
.......
የቴስላና ስፔስ ኤክስ መስራች ፡ የትዊተር ባለቤት የሆነው ኤለን መስክም ንባብን በተመለከተ ያለው ልማድ ተመሳሳይ ነው ። ኤለን መስክ ተማሪ እያለ በቀን አስር ሰአት ያነብ ነበር ። አሁንም ጎበዝ አንባቢ ከሚባሉ ሰወች መሀከል አንዱ ነው ።

የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግም በሳምንት አንድ መፅሀፍ ያነባል ። እንደውም በአንድ ወቅት ፡ " አንድ መፅሀፍ በአንድ ሳምንት " የሚል ቻሌንጅ በፌስቡክ ገፁ ጀምሮ ፡ ሰወች እንዲያነቡ ያበረታታ ነበር ።
......
ወደእኛ ሀገር ስናመጣው ደግሞ ፡ አደለም መፅሀፍ በፌስቡክ ላይ እንኳን ትንሽ ረዘም ያለ ፅሁፍ ስናይ ፡ የሚያዞረን ብዙ ነን ፡ ሆኖም ንባብ ያልኖርክበትን ፡ የማታውቀውን አዲስ ነገር በየእለቱ የሚያሳውቅ ነገር ነውና ፡ በዚህ በመፅሀፍት ቀን የንባብ ልምዳችንን ለማዳበር ብንሞክር እንላለን ። በነገራችን ላይ በአለም ፡ ብዙ መፅሀፍትን በማንበብ ህንዶች ቀዳሚ ናቸው ፡
.......
የንባብ ልምዳችንን ለማሻሻል የሚረዱ ጥቂት ነጥቦች 📚

* ወደ ቤተመፅሀፍት መሄድ ወይም የተመረጡ ዌብሳይቶችን ጆይን በማድረግ በኢንተርኔት የንባብ ልምድን ማዳበር

* በየቀኑ ምን ያህል ሰአት እንዳነበቡ ለማወቅ ንባብ ሲጀምሩ ሰአትን መመዝገብ ( ይህ ነገር ፡ የራሳችንን ሰአት ለማሻሻልና ፡ በየጊዜው ረዘም ያለ ሰአት ለማንበብ ይረዳናል )

* መፅሀፍቶችን በቤት ውስጥ በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ በቅርብ ቦታዎች ላይ ማስቀመጥ ።

* ከመተኛትዎ በፊት የተወሰኑ ገጾችን የማንበብ ልማድ ማዳበር ፡

* ረጅም ሰአት በትራንስፖርት ስንጓዝ ፡ መፅሀፍ ይዘን ለማንበብ መሞከር ወይም የተቀረፁ በኦዲዮ የተዘጋጁ መፅሀፎችን ማዳመጥ ፡ የንባብ ልምዳችንን ለማሻሻል የሚረዱን ነገሮች ናቸው ።

እንጠቀምበት 📚




Wasihune @via Facebook 🦋
📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
" ስማ ቢል ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው ፡ ከዛሬ ጀምሮ የእራት ሰአት ላይ መፅሀፍ ስታነብ እንዳናይ " ..... ይህን ያሉት በአንድ ወቅት ከፎርብስ መፅሄት ጋር ኢንተርቪው አድርገው የነበሩት የቢልጌትስ አባት ናቸው ። ሚስተር William H. Gates ይህን በተመለከተ ሲናገሩ ..... ቢልጌትስ ከልጅነቱ ጀምሮ አንባቢ ነበር በዚህ ነገሩ ደስተኞች ብንሆንም ፡ ለማንበብ ካለው ፍቅር የተነሳ የእራት…
እና ዛሬ የመፅሐፍ ቀን ነበር አሉ...

በዚህ አጋጣሚ ያነበባችሁትን ሌላው ሰው ሊያነበው ይገባል የምትሉትን መፅሐፍ comment ላይ አስቀምጡ...

እኔ ያን ያህል የንባብ ዝንባሌ የለኝም ግን ማንበብ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ አውቃለው።ቢሆንም አንባቢ አይደለሁም ። ካነበብኹት ጥቂት መፅሐፍት ውስጥ እናንተ ብታነቡት ብዬ የማስበው...

1. "ሀዲስ" ከበአሉ ግርማ (ለኔ የምንግዜም ምርጥ ደራሲ።)
2."ራስ" ከፍሬዘር (በሳቅ የሚገል መፅሐፍ ነው።)
3."ዙቤይዳ" ከአሌክስ አብርሃም
...ተመልሳ እንደማትመጣ ልቡ ያቃዋል…ብቻ ልፋ ቢለው እንደሆነም ይረዳዋል…ቀኑን ሙሉ ሲያማትር ቢውልም አንዳች አዲስ ነገር እንደማይፈጠር ከእሱ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም…ማንም!

…ግን እራሱን መሟገት አይፈልግም…ባትመጣም ትመጣለች ማለትን ይመርጣል…እራሱንም መሸወድ፣ ከራሱ ጋር ፀብ እንደሆነ ቅንጣት ታህል አይጠፋውም…ግን "አትመጣም" ከሚለው የእውነት ጩኽት ይልቅ "ትመጣለች" የሚለው ሹክሹክታ ለእሱ ሰላም አለው።

…ከሰላም በላይ ደሞ ምን አለ?



  ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
ለማይኾን ሰው አይሆኑ ሆኜ ደክሞኝ ነው እንጂ ላንቺ የምኾነው ይሄን ብቻ አልነበረም... !

...ቃላቶቼን ለማይገባቸው ሰዎች አባክኛቸው ነው ፤ አንቺ ጋር ስደርስ ቃላት አልባ የሆንኹት...ተናግሬ እንዳልተናገርኹ ያደረገኝ ሰው ስላለ ነው ፤ ለቃሌ የሳሳሁት...እንጂማ ላንቺ የምነግርሽ ይሄን ብቻ አልነበረም።ብዙ የማወጋሽ ነገር ነበረኝ።

...ደካማ ጎኔን የነገርኹት ሰው በድክመቴ ስለተጠቀመበት ነው ፤ ብርቱ ፣ ፍፁም ፣ የማልረታ ሰው እንደሆንሁ የማስመስለው እንጂ ደካማ ፍጥረት እንደሆንኹ እንደ እንስት እያነባው እነግርሽ ነበር።

...ካንቺ በፊት "እወድሻለሁ" ያልኋት ሴት መወደዷን ስታውቅ "እጠላሻለሁ" ያልኋት ያህል ስለሸሸችኝ ነው እንደምወድሽ የማልነግርሽ እንጂ...



ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
በረከት በላይነህ በደጃፍ ፖድካስት ነጻ ትምህርት (Lecture) እየሰጠ አይደል እንዴ ?

በረከት ከኪነጥበብ ሰውነቱ ባሻገር የብዙ እውቀት ባለቤት ሆኗል። እውቀቱ ደግሞ የዋዛ አይደለም። በእያንዳንዱ የንግግሩ ውርወራ ውስጥ የዳበረ እና ትጋትን የተሞላ የንባብ ሥርዓት ( Discipline ) ውስጥ እንደታሸ ሚያመለክት እውቀት ነው ያለው ። በራሱ ምርምር ጂኦ ፖለቲክሱን ፣ የተፈጥሮ ሀብቶች ሁኔታን ሚተነትንበት ፣ ሚያነጽርበት መንገድ በጣም ነው ደስ ሚለው። በዚህ ውይይት ብቻ ሳይገታ በመጽሐፎችም በሌሎች ቪድዮዎችም እየመጣ እንዲህ ቢያስደምመን ደስታዬ ነው።


Dawit Tesfaye ! 🙏🏾


It's an amazing podcast.
ዛሬ ያነበብኹት ምርጥ አባባል ፡

"ፈጣሪ ሲወድህ ፤ ሰው ነው የሚሰጥህ።"

አንቺን ሰጠኝ 💙


(ሲንግሎች ይሄን አንብበው ፡ "ሶፊ ደግሞ ሁሉንም ከሷ ጋር አታገናኝብና...ጥሩ ትመጣ ትመጣ ና 😒"

ይሉ ይሆናል። ይበሉ ! ስንት ዘመን ሲንጉላር (singular) ሆኜ እንደኖርኹ እነርሱ መች ያውቃሉ።
ባለፈው ከስራ እንደወጣው እቃ ልገዛ ወደ ፒያሳ ጎራ አልኹ...የምፈልገው ቤት ጋር ስደርስ ቆምኹ...ቤቱ የለም ፤ በቤቱ ፋንታ ፍርስራሽ ጠበቀኝ ፤ የአድራሻ ለውጥ ማድረጋቸውን የሚገልፅ ፅሁፍ ተንጠልጥሏል። በራሴ ተበሳጨው "ፒያሳ ፈርሷል" እያሉኝ ለማረጋገጥ ይሁን ለምን እንደመጣው አልውቅም ። ካላየው ስለማላምን ይሆን ? አረፍ የሚባልበት ካፌ እንኳ አላስቀሩም ። ፒያሳ ማረፊያ ቦታ የላትም ፤ ደግሞም ያለረፍት እየተቆፈረች ነው...ልሂድ ቢሉም አይቻልም። መጓጓዣም ሆነ መንገድ የለም ።

...ወደ ቤቴ መሄድ ፈለግኹ...ሰማዩ ጠቁሯል። ዝናቡ መጣው እያለ እየፎከረ ነው። አማራጭ ስላልነበረኝ ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ በእግሬ ተያያዝኹት ። ደክሞኛል...መሄድ ሳይሆን ጥቅልል ብሎ መተኛት ነበር ያማረኝ ።ሄድኹ ፤ ብዙ ስሄድ ተበሳጨው፤ስበሳጭ... ይሄን መንገድ ለመስራት ሃሳብ ያመጣውን ሰው ረገምኹ። ሃሳቡን ተቀብሎ መቆፈር የጀመረውን ሰው ረገምኹ...ሀገሬንም ረገምሁ፣ የተወለድኹበትንም ቀን ረገምኹት።

...አራት ኪሎ ጋር ስደርስ እዛም ታክሲ የለም...ባሶቹ ከመሙላት አልፈው ሰው እያንጠባጠቡ ያልፋሉ...ባስ አይሞከርም። ሜትር ታክሲ በስልኬ ጠርቼ ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ አካባቢ ከወዲያ ወዲህ እያልኹ ጠበቅኹ።የመጣም፤የደወለም የለም። እየፎከረ የነበረው ዝናብ በጥቂት በጥቂቱ ማንጠባጠብ ዠምሯል ። ሰው'ው ይተራመሳል። ከግራ ከቀኝ መንገዱ በዶዘር ይታረሳል። የእግረኛውም የመኪናውም መንገድ አንድ ላይ ነው ። የረባ ጃኬት አለበስኹም...በርዶኛል...ደክሞኛል...ግን አማራጭ ስለሌለኝ በእግሬ መሄድ ዠመርኹ...ካፊያው ቀስ ብሎ ወደ ዶፍ ዝናብ ተለወጠ...መንገድ ዳር የነበሩት ቤቶች፣ካፌዎች፣የንግድ ሱቆች ለኮሪደር ልማት ፈርሷል...ከፒያሳ-መገናኛ እየተቆፈረ ነው...በዶፍ ዝናብ ውስጥ እየተራገምኹ መረማመዴን ተያያዝሁት...የለስኹት ሸራ ጫማ የቻለውን ያህል ውሃ አስገብቷል ።(መብራት ነው የቀረው)...ያልበሰበሰ የሰውነት ክፍል የለኝም።

...ስልኬ ጮኽ በረጠበው እጄ፤ስልኬን ዝናብ እንዳይነካው አጎንብሼ ስሙን አነበብኹት እና ክው ብዬ ደነገጥኹ ! ክው አድርጎ ያስደነገጠኝ የደዋዩ ማንነት ሳይሆን Data እስካሁን አለማጥፋቴን ሳይ ነው። የተደወለው በቴሌግራም ነዉ ። Clare ናት የደወለቺው ።

Clare አሜሪካዊት ናት። አንድ አሜሪካ የሚገኝ ጓደኛዬን አዲስ አበባ ኑሮ እጅግ እንደተወደደ በደወለልኝ ቁጥር ስለምነግረው ፤ ብር መላኩ ሲሰለቸው አንድ ስራ አገኘልኝ። ስራው ማዳመጥ ነው።አሁን የኔ ጆሮ የውጪ ምንዛሬ እንደሚያመጣ ማን ሰው ያምናል?
Clare የ28 አመት ጎልማሳ ናት ፤ ጎልማሳ ያሰኛት እድሜዋ ሳይሆን ነገረ ስራዋ ነው። አረ እንደውም አዛውት ናት። ገና ህይወትን በቅጡ ሳታጣጥመው መኖር የደከማት ናት። በወጣት ጉልበቷ አልሮጠችበትም ፤ ቁጭ ብላ ታማርርበታለች። የትም መሄድ አትፈልግም...ሁሉንም ያየች ይመስል ሁሉም ነገር አስጠልቷታል ። ትገርመኛለች ሰው ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት እንዴት ያማራል ? የምትኖርበት ቅንጡ አፓርታማ፣የምትነዳው መኪና፣የምትሰራው ስራ፣ስኬቷ ሰላምን አላመጣላትም ።የምትፈልገው ነገር ግራ ገብቷት ፤ የምትፈልገውን እየፈለገች ነው።

ጓደኛዬ ሲያስቀጥረኝ ስራው የሚጠይቀው መስፈርት "A good listener" መሆን ነው። ገርሞኝ ነበር እዛ ሀገር የሚያዳምጥ የለም ማለት ነው ? አንድም ደስ ብሎኝ ነበር ። ስራ በዶላር በመቀጠሬ...Clare ታወራለች ያለማቋረጥ...የምትደውልልኝ ድባቴ ውስጥ ስትገባ ነው...ከምታወራኝ አብዛኛው ምሬት ነው። በቤተሰቧ ፣ በጓደኞቿ የደረሰባት በደል (አንዳንዴ እኔ ምናገባኝ ! ልላት አስብና መክፈሏ ትዝ ሲለኝ ዝም እላለሁ። ለካ እርቦኝ ጆሮዬን ሸጨዋለሁ ።) ድባቴ ውስጥ ስትገባ Clare ታወራለች ! እየጠጣች... ! አንዳንዴ በ Video ነው የምታወራኝ ። ቅንጡ ሶፋ ላይ በድብርት ተኮራምታ ስለልጅነቷ ታወራለች...የዛኔ ጆሮዬን ብቻ አይደለም...ፊቴንም ትገዛዋለች፤በምትነግረኝ ነገር ያዘንኹ ለመምሰል እየጣርኹ ...የረገበ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እሰማታለሁ።
Clare አንድ እለት ቆንጆ ስልክ ላከቺልኝ።ከዛም በቪዲዮ ኮል ደውላ ቤቴን በጥራት ብታየው ጊዜ ልቧ በሐዘን ተነካ። ልታወራኝ የነበረውን ነገር ርግፍ አድርጋ ትታ..."i want you to tell me about yourself...your child hood...." በተሰባበረ ኢንጊሊዘኛ አወራት ዠመር። የዛኔ ይመስለኛል ኢንግሊዘኛዬን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማችው ።የዛኔ ይመስለኛል ያወራችውን ልሰማት እንደማልችል የጠረጠረችው...።

ለClare አላነሳሁላትም ጠርቶ ሲጨርስ ዳታዬን አጠፋኹ። ከአራት ኪሎ፣ግንፍሌ፣ቀበና እንዳለፍኹ ወደቤቴ የሚወስደውን ቅያስ ያዝኹ።ቤቴ ስገባ ።መብራት ጠፍቷል።ውሀም የለም።እራትም አልሰራሁም።እጅግ ተበሳጭቼ።ልብሴን ቀያይሬ ጋደም አልኹና ዳታዬን አበራኹ።Clare ደወለች።

Clare: What's wrong Sofi...i have been calling you the whole day...?

Sofi: Come on Clare anything could happen,i live in Ethiopia...no electricity...no water...no food

ልላት አሰብኹና የሀገሬን ገፅታ እንዳላጎድፍ ብዬ

"I was at work the whole day" አልኋት።በባዶ ሆዴ ምሬቷን እንዳልሰማ እየተመኘው ጆሮዬን አዋስኋት። "ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው።"





የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
ሌላ ጥኹፍ አዘጋጅቼ ነበር ግን ማናጀሬን ሳስነብበው ተደነቀ (ማናጀር የለኝም ሳክስ ነው።) እና "ይሄ ጥኹፍ በመጥሐፍህ የምታወጣው እንጂ እንዲህ ቀለል አድርገህ የምትለቀው አይደለም።" አለኝ ።

...ነገር ግን አወጣሁ አወረድኹ እና እናንተን ወዳጆቼን ላስነብብ ወደድኹ ፤ ከዛም ካነበባችሁት በኋላ አጠፋዋለኹ። type አድርጌ ነገ እለቀዋለኹ።

ሰላም እደሩ ።


አክባሪያችኹ።
©ሶፊ
📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ
ሌላ ጥኹፍ አዘጋጅቼ ነበር ግን ማናጀሬን ሳስነብበው ተደነቀ (ማናጀር የለኝም ሳክስ ነው።) እና "ይሄ ጥኹፍ በመጥሐፍህ የምታወጣው እንጂ እንዲህ ቀለል አድርገህ የምትለቀው አይደለም።" አለኝ ። ...ነገር ግን አወጣሁ አወረድኹ እና እናንተን ወዳጆቼን ላስነብብ ወደድኹ ፤ ከዛም ካነበባችሁት በኋላ አጠፋዋለኹ። type አድርጌ ነገ እለቀዋለኹ። ሰላም እደሩ ። አክባሪያችኹ። ©ሶፊ
እነሆ ያልኳችሁ ድርሰት...የዘገየውት ሐሳቡን የተሻለ አድርጌ እንደ አዲስ ስለፃፍኹት ነው።

አንብቡት እና ከሦስት ቀን በኋላ ይጠፋል።


መልካም ንባብ።
©ሶፊ
አንዱ እብድ ቲክቶከር የተወሰነ ተከታይ ያገኛል፤ በመሠደብ viral ይሆናል አንድ ቀን live ገባና እንዲህ አለ አሉ : መንገድ ላይ እያያችሁኝ ለምን ዝም ብላችሁ ታልፉኛላችሁ ሻሂ እንኳን አትጋብዙኝም ?

ምን ለማለት ነው አንብባችሁ ለምን ዝም ትላላችሁ ? አንድ ኮመንት እንኳን አጥፉልኝም? 😒
እንዲህ የምትሉት ወይም የሚላችኹ ሰው ይስጣችሁ።
Guys is there any doctor?

Hospital መሄድ ስለፈራው ነው ። ለምን ? ምርመራ ተደረገልህም ፤ አልተደረገልህም የሚያዙልህ መድሀኒት አይለያይም 🙄 (በጥናት ያረጋገጥኹት ነው። እንዴት? 6 ሰዎች አንድ ጤና ጣቢያ ላኩ...5 ቱ typhus and typhoid አለባችሁ ተብለዋል ። ይሄ ጥናት ምንን ያሳያል ? ብዬ ብጠይቀው አንዱን ዶክተር ጥናትህ ልክ ሊሆን ይችላል ። የተሳሳሳቱት ዶክተሮቹ ሳይሆን ሰዎቹ የእውነት ስለታመሙ ነው አለኝ። ይህስ ምን ማለት ነው ? ኢትዮጵያ ውስጥ ከስድስት ሰው አንዱ ብቻ ነው ጤነኛ ማለት አይደለምን ? ሆ እኔ አላልኩም !)

ብቻ ከመታመም በላይ ሐኪም ቤት መሄድ እፈራለሁ። እና ምን ለማለት ነው እዛ ሄጄ ከሚጫወቱብኝ እናንተ እንዲሁ ህመሜን ብትገምቱልኝ ይሻለኛል። ቤት ለቤት ህክምና እንደማለት ነው 😁

ዋና የህመሜ ምልክት ፡ በልቼ ልክ ስጨርስ ይርበኛል።



N.B ማንኛውንም ግምት አልንቅም።




ህመምተኛችኹ።
©ሶፊ
አንዳንዴ የከፋኝ ቀን ቤተክርስቲያን ሄጄ :

... ድንገት በመንገድ ሳልፍ አስቀይመውኝ ከህይወቴ ያላሶጣዋቸው ሰዎች ፤ ከንሰሀ አባቶቻቸው ጋር ስመለከት ሄጄ : " እኔ ላይ ያደረከውን ተናዘዝክ ?" ብዬ መጠየቅ ወይም "አባ ያደረገኝን ሰሙ ፤ እንዲህ ይደረጋል ነውር አይደል ? አዩልኝ አይደል የሰራኝን ሥራ ?" ብዬ ለእግዚአብሔር ማቃጠር ያምረኛል ።


ዛሬ ምንድነው የጠጣውት?
©ሶፊ
So ልጅቷን እኛ መስሪያ ቤት ነው የማውቃት (this kinda storytelling ከticktock ነው ያየኹት። grammatically wrong ነው አይደል ?ደግሞ አብዛኛዎቹ ብዙ view አላቸው...ምን ያህል ወረኛ ብንሆን ነው በእመቤቴ ! ስራ የለንም እንዴ? )

እና ወደ ወሬዬ ሾመለሾ áˆáŒ…ቡ እኛ መስሪያ ቤት አዲስ ገቢ ናት።ከቢሮአችን ጎን ነው ቢርዋ...በውበቷ ብዙ ሰው ስለሚያሸረግድላት...በቅርጿ ሴቶችም ሳይቀሩ መነጋገሪያ ስላደረጓት...እጅግ ጣሪያ የነካ መኮፈስ...መንጠባረር...መመፃደቅ...ይስተዋልባታል።

...አንድ ቀን እኛ ቢሮ ለጉዳይ መጥታ ፈገግ ብላ ሰላም አለቺኝ...ከደማቅ ፈገግታ ጋር አፀፋውን መለስኹ።
...ከዛ ሌላ ጊዜ በመንገድ ስንገናኝ ሰላም መባባል የለብንም ? በሁለተኛው ቀን ፊት ለፊት ስንገናኝ ከመተላለፋችን በፊት ሰላም ልበላት አልበላት እያልኹ ሳመነታ "ሰላም ነህ ?" አለቺኝ በዛ ድምጿ...አፀፋዋን መለስኹ።

ከዛ በቀጣዩ ቀናቶች ፊት ለፊት ስንገጣጠም አንዴ ሰላም ትለኛለች ሌላ ጊዜ ትዘጋኛለች ። ብቻዬን "ሰላም ነው?" እያልኹ አልፋለሁ። አሁን አሁን እሷን ሳይ መሳቀቅ ጀመርኹ ሰላም ልበላት ወይስ አልበላት?

ቆይ ማነኝ ብላ ነው የምታስበው?
የእርሷ ሰላምታ ቀኔን የሚያበራው ፤ ምሽቴን የሚያደምቀው መሰላት ?


ምናባቷ ነው የምታወዛግበኝ ፤ ስንት ሰው ሳቀብኝ ብቻዬን " ሰላም ነው? " እያልኹ እያለፍኹ !




ሰላም ነው?
©ሶፊ
ከመሸ አንድ ነገር ታወሰኝ...

እኔ ዩንቨርስቲ የተመደብኹት ለአዲስ አበባ ቀረብ ያለ ቦታ ነበር...ዮንቨርስቲው ገና አዲስ የተመሠረተ በመሆኑ ገና infrastructure አልተሟላለትም...እና እኔ ደግሞ ከቤተሰብ ስርቅ የመጀመሪያዬ ነበር ። network እንኳን internet ለመጠቀም ቀርቶ ከቤተሰብ ጋር ለማውራት እራሱ አስቸጋሪ ነበር፤ ውስን ቦታሆች ላይ ብቻ ይሰራል። እጅግ ተጨንቄ ነበር ከቤተሰብ ስርቅ የመጀመሪያዬ ነው። ቤተሰብ የጠቀመኝ መስሎት እንኳን ከሰፈር ልርቅ ቀርቶ ሰፈር ውስጥ እንድጫወት ራሱ አይፈቀድልኝም ፤ ትምህርት ቤት ከዛ ቤት ነኝ ሌላ ቦታ ከሄድኹ ከቤተሰብ ጋር ነው ( ይሄ ትልቅ በደል አይደል ? ገና ለገና ይበላሻል ብለው ስለሚሰጉ Independent እንድንሆን እድሉን አይሰጡንም። ከዛ ቶሎ ራሳችንን እንድንችል ይፈልጋሉ ። እጅን ጥፍር አድርጎ አስሮ ተመገብ እንደማለት አይሆንም?) ።
ዩንቨርስቲ እያለኹ የመጀመሪያው አመት ላይ ትምህርቱ ያስጨንቅ ነበር።ገና ለገና እባረራለሁ የሚል ስጋት ስላየለብኝ በጭንቀት የተገዝኹበት ጊዜያት ብዙ ነበሩ ። እናም ስተክዝ ጊዜ ሄጄ የምቀመጥበት ከዶርማችን ፊት ለፊት አንዲት ስፍራ ነበረች ። ለካ ያቺ ስፍራ ለትካዜ ሁነኛ ስፍራ ኑራለች ፤ ሌሎች ወዳጆችንም ሠበሠበች ። እዛች ስፍራ ላይ ትላንትን በትዝታ ቃኘንባት ፣ በተለያየ ስፍራ ብናድግም የኾነ የሚያመሳስለን ነገር እንደነበር አስተዋልን ልዩነትን አጣጣምነው ፣ ነጋችንን ተነበይነው...እዛች ስፍራ ላይ በትካዜ ቁጭ ብለን ዛሬንና ነገን በተስፋ ድልድይ አያያዝነው ። ያቺ ልዩ ስፍራ ደስታችንን አስተናግዳለች ፣ ሐዘንን አስታግሳለለች ፣ ብቻ መብሠልሠልን ገትታለች...ብዙ ብዙ ነገር አይታለች። ታዲያ በሀይሉ ያቺን ስፍራ " ብሶት አደባባይ " ብሎ ሰየማት ።

ከጊቢ ወጥቼ ሐዘን በጎበኘኝ ጊዜ ያቺ ስፍራ ትውስ ትለኛለች ።


አሁን ላይ ለእኔ ያቺ ስፍራ እናንተ ናችሁ...! የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ።




ብሶት አደባባይ
©ሶፊ
"What Kind of Person Are You?"

Me???

I am different. I am imaginative.
I am far more than I have ever revealed
People know me as someone strong
But I'm fragile inside.

I'm someone who doesn't show my vulnerable side
Not because I don't have anyone
It's because I don't want them to stop relying on me

I am someone who smiles at small things
But I am also someone who gets hurt very often
I'm a shoulder to cry on for many people
But I'm also the one who has no shoulder to cry and to rely on.

I'm someone who forgives very fast
But I'm also someone who can't forget everything that's said.
I'm someone who adores sunlight
Yet, I'm also someone who discovers solace in the darkness of night.

I'm someone who has never been asked, "Are you okay?"
Yet, I'm also someone who will respond with, "I'm okay, I'm fine, nothing changed"


~Unknown source
"እወድሻለሁ እንኳን ብሎኝ አያውቅም " ብለሽ ማማረርሽን ሰማሁ...

እውነት እንደዛ ነው የምታስቢው?


ባልወድሽ ነው ከስርሽ የማልጠፋው?


ባልወድሽ ነው አስሬ ስምሽን የምጠራው?


ባልድሽማ...እስክትረሽኝ ነበር ከእይታሽ የምጠፋው...እኔ እንደዛ ነኝ የማልፈለግበት ስፍራ የምቆይ አይነት ሰው አይደለውም።


አየሽ ስስቴ ቃላት ሲደጋገም አቅሙን ያጣል...እንደቀላል ነገር "እወድሻለሁ" ይባላል?

በእኔ ቤት ይሄ ውድ የሆነ ቃል መለኮታዊ ሀይሉን አጥቶ ተርታ ቃል እንዳይሆንብኝ...መጠንቀቄ ነበር።

እንጂ...



እ ወ ድ ሻ ለ ሁ።


እንደውም ነይ...
ከዚህ ህይወት ፤ ከዚህ አለም ይዤሽ ልጥፋ !







ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
2024/05/19 19:32:07
Back to Top
HTML Embed Code: