Telegram Web Link
ዛሬ ያነበብኹት ምርጥ አባባል ፡

"ፈጣሪ ሲወድህ ፤ ሰው ነው የሚሰጥህ።"

አንቺን ሰጠኝ 💙


(ሲንግሎች ይሄን አንብበው ፡ "ሶፊ ደግሞ ሁሉንም ከሷ ጋር አታገናኝብና...ጥሩ ትመጣ ትመጣ ና 😒"

ይሉ ይሆናል። ይበሉ ! ስንት ዘመን ሲንጉላር (singular) ሆኜ እንደኖርኹ እነርሱ መች ያውቃሉ።
ባለፈው ከስራ እንደወጣው እቃ ልገዛ ወደ ፒያሳ ጎራ አልኹ...የምፈልገው ቤት ጋር ስደርስ ቆምኹ...ቤቱ የለም ፤ በቤቱ ፋንታ ፍርስራሽ ጠበቀኝ ፤ የአድራሻ ለውጥ ማድረጋቸውን የሚገልፅ ፅሁፍ ተንጠልጥሏል። በራሴ ተበሳጨው "ፒያሳ ፈርሷል" እያሉኝ ለማረጋገጥ ይሁን ለምን እንደመጣው አልውቅም ። ካላየው ስለማላምን ይሆን ? አረፍ የሚባልበት ካፌ እንኳ አላስቀሩም ። ፒያሳ ማረፊያ ቦታ የላትም ፤ ደግሞም ያለረፍት እየተቆፈረች ነው...ልሂድ ቢሉም አይቻልም። መጓጓዣም ሆነ መንገድ የለም ።

...ወደ ቤቴ መሄድ ፈለግኹ...ሰማዩ ጠቁሯል። ዝናቡ መጣው እያለ እየፎከረ ነው። አማራጭ ስላልነበረኝ ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ በእግሬ ተያያዝኹት ። ደክሞኛል...መሄድ ሳይሆን ጥቅልል ብሎ መተኛት ነበር ያማረኝ ።ሄድኹ ፤ ብዙ ስሄድ ተበሳጨው፤ስበሳጭ... ይሄን መንገድ ለመስራት ሃሳብ ያመጣውን ሰው ረገምኹ። ሃሳቡን ተቀብሎ መቆፈር የጀመረውን ሰው ረገምኹ...ሀገሬንም ረገምሁ፣ የተወለድኹበትንም ቀን ረገምኹት።

...አራት ኪሎ ጋር ስደርስ እዛም ታክሲ የለም...ባሶቹ ከመሙላት አልፈው ሰው እያንጠባጠቡ ያልፋሉ...ባስ አይሞከርም። ሜትር ታክሲ በስልኬ ጠርቼ ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ አካባቢ ከወዲያ ወዲህ እያልኹ ጠበቅኹ።የመጣም፤የደወለም የለም። እየፎከረ የነበረው ዝናብ በጥቂት በጥቂቱ ማንጠባጠብ ዠምሯል ። ሰው'ው ይተራመሳል። ከግራ ከቀኝ መንገዱ በዶዘር ይታረሳል። የእግረኛውም የመኪናውም መንገድ አንድ ላይ ነው ። የረባ ጃኬት አለበስኹም...በርዶኛል...ደክሞኛል...ግን አማራጭ ስለሌለኝ በእግሬ መሄድ ዠመርኹ...ካፊያው ቀስ ብሎ ወደ ዶፍ ዝናብ ተለወጠ...መንገድ ዳር የነበሩት ቤቶች፣ካፌዎች፣የንግድ ሱቆች ለኮሪደር ልማት ፈርሷል...ከፒያሳ-መገናኛ እየተቆፈረ ነው...በዶፍ ዝናብ ውስጥ እየተራገምኹ መረማመዴን ተያያዝሁት...የለስኹት ሸራ ጫማ የቻለውን ያህል ውሃ አስገብቷል ።(መብራት ነው የቀረው)...ያልበሰበሰ የሰውነት ክፍል የለኝም።

...ስልኬ ጮኽ በረጠበው እጄ፤ስልኬን ዝናብ እንዳይነካው አጎንብሼ ስሙን አነበብኹት እና ክው ብዬ ደነገጥኹ ! ክው አድርጎ ያስደነገጠኝ የደዋዩ ማንነት ሳይሆን Data እስካሁን አለማጥፋቴን ሳይ ነው። የተደወለው በቴሌግራም ነዉ ። Clare ናት የደወለቺው ።

Clare አሜሪካዊት ናት። አንድ አሜሪካ የሚገኝ ጓደኛዬን አዲስ አበባ ኑሮ እጅግ እንደተወደደ በደወለልኝ ቁጥር ስለምነግረው ፤ ብር መላኩ ሲሰለቸው አንድ ስራ አገኘልኝ። ስራው ማዳመጥ ነው።አሁን የኔ ጆሮ የውጪ ምንዛሬ እንደሚያመጣ ማን ሰው ያምናል?
Clare የ28 አመት ጎልማሳ ናት ፤ ጎልማሳ ያሰኛት እድሜዋ ሳይሆን ነገረ ስራዋ ነው። አረ እንደውም አዛውት ናት። ገና ህይወትን በቅጡ ሳታጣጥመው መኖር የደከማት ናት። በወጣት ጉልበቷ አልሮጠችበትም ፤ ቁጭ ብላ ታማርርበታለች። የትም መሄድ አትፈልግም...ሁሉንም ያየች ይመስል ሁሉም ነገር አስጠልቷታል ። ትገርመኛለች ሰው ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት እንዴት ያማራል ? የምትኖርበት ቅንጡ አፓርታማ፣የምትነዳው መኪና፣የምትሰራው ስራ፣ስኬቷ ሰላምን አላመጣላትም ።የምትፈልገው ነገር ግራ ገብቷት ፤ የምትፈልገውን እየፈለገች ነው።

ጓደኛዬ ሲያስቀጥረኝ ስራው የሚጠይቀው መስፈርት "A good listener" መሆን ነው። ገርሞኝ ነበር እዛ ሀገር የሚያዳምጥ የለም ማለት ነው ? አንድም ደስ ብሎኝ ነበር ። ስራ በዶላር በመቀጠሬ...Clare ታወራለች ያለማቋረጥ...የምትደውልልኝ ድባቴ ውስጥ ስትገባ ነው...ከምታወራኝ አብዛኛው ምሬት ነው። በቤተሰቧ ፣ በጓደኞቿ የደረሰባት በደል (አንዳንዴ እኔ ምናገባኝ ! ልላት አስብና መክፈሏ ትዝ ሲለኝ ዝም እላለሁ። ለካ እርቦኝ ጆሮዬን ሸጨዋለሁ ።) ድባቴ ውስጥ ስትገባ Clare ታወራለች ! እየጠጣች... ! አንዳንዴ በ Video ነው የምታወራኝ ። ቅንጡ ሶፋ ላይ በድብርት ተኮራምታ ስለልጅነቷ ታወራለች...የዛኔ ጆሮዬን ብቻ አይደለም...ፊቴንም ትገዛዋለች፤በምትነግረኝ ነገር ያዘንኹ ለመምሰል እየጣርኹ ...የረገበ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እሰማታለሁ።
Clare አንድ እለት ቆንጆ ስልክ ላከቺልኝ።ከዛም በቪዲዮ ኮል ደውላ ቤቴን በጥራት ብታየው ጊዜ ልቧ በሐዘን ተነካ። ልታወራኝ የነበረውን ነገር ርግፍ አድርጋ ትታ..."i want you to tell me about yourself...your child hood...." በተሰባበረ ኢንጊሊዘኛ አወራት ዠመር። የዛኔ ይመስለኛል ኢንግሊዘኛዬን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማችው ።የዛኔ ይመስለኛል ያወራችውን ልሰማት እንደማልችል የጠረጠረችው...።

ለClare አላነሳሁላትም ጠርቶ ሲጨርስ ዳታዬን አጠፋኹ። ከአራት ኪሎ፣ግንፍሌ፣ቀበና እንዳለፍኹ ወደቤቴ የሚወስደውን ቅያስ ያዝኹ።ቤቴ ስገባ ።መብራት ጠፍቷል።ውሀም የለም።እራትም አልሰራሁም።እጅግ ተበሳጭቼ።ልብሴን ቀያይሬ ጋደም አልኹና ዳታዬን አበራኹ።Clare ደወለች።

Clare: What's wrong Sofi...i have been calling you the whole day...?

Sofi: Come on Clare anything could happen,i live in Ethiopia...no electricity...no water...no food

ልላት አሰብኹና የሀገሬን ገፅታ እንዳላጎድፍ ብዬ

"I was at work the whole day" አልኋት።በባዶ ሆዴ ምሬቷን እንዳልሰማ እየተመኘው ጆሮዬን አዋስኋት። "ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው።"





የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
ሌላ ጥኹፍ አዘጋጅቼ ነበር ግን ማናጀሬን ሳስነብበው ተደነቀ (ማናጀር የለኝም ሳክስ ነው።) እና "ይሄ ጥኹፍ በመጥሐፍህ የምታወጣው እንጂ እንዲህ ቀለል አድርገህ የምትለቀው አይደለም።" አለኝ ።

...ነገር ግን አወጣሁ አወረድኹ እና እናንተን ወዳጆቼን ላስነብብ ወደድኹ ፤ ከዛም ካነበባችሁት በኋላ አጠፋዋለኹ። type አድርጌ ነገ እለቀዋለኹ።

ሰላም እደሩ ።


አክባሪያችኹ።
©ሶፊ
አንዱ እብድ ቲክቶከር የተወሰነ ተከታይ ያገኛል፤ በመሠደብ viral ይሆናል አንድ ቀን live ገባና እንዲህ አለ አሉ : መንገድ ላይ እያያችሁኝ ለምን ዝም ብላችሁ ታልፉኛላችሁ ሻሂ እንኳን አትጋብዙኝም ?

ምን ለማለት ነው አንብባችሁ ለምን ዝም ትላላችሁ ? አንድ ኮመንት እንኳን አጥፉልኝም? 😒
እንዲህ የምትሉት ወይም የሚላችኹ ሰው ይስጣችሁ።
Guys is there any doctor?

Hospital መሄድ ስለፈራው ነው ። ለምን ? ምርመራ ተደረገልህም ፤ አልተደረገልህም የሚያዙልህ መድሀኒት አይለያይም 🙄 (በጥናት ያረጋገጥኹት ነው። እንዴት? 6 ሰዎች አንድ ጤና ጣቢያ ላኩ...5 ቱ typhus and typhoid አለባችሁ ተብለዋል ። ይሄ ጥናት ምንን ያሳያል ? ብዬ ብጠይቀው አንዱን ዶክተር ጥናትህ ልክ ሊሆን ይችላል ። የተሳሳሳቱት ዶክተሮቹ ሳይሆን ሰዎቹ የእውነት ስለታመሙ ነው አለኝ። ይህስ ምን ማለት ነው ? ኢትዮጵያ ውስጥ ከስድስት ሰው አንዱ ብቻ ነው ጤነኛ ማለት አይደለምን ? ሆ እኔ አላልኩም !)

ብቻ ከመታመም በላይ ሐኪም ቤት መሄድ እፈራለሁ። እና ምን ለማለት ነው እዛ ሄጄ ከሚጫወቱብኝ እናንተ እንዲሁ ህመሜን ብትገምቱልኝ ይሻለኛል። ቤት ለቤት ህክምና እንደማለት ነው 😁

ዋና የህመሜ ምልክት ፡ በልቼ ልክ ስጨርስ ይርበኛል።



N.B ማንኛውንም ግምት አልንቅም።




ህመምተኛችኹ።
©ሶፊ
አንዳንዴ የከፋኝ ቀን ቤተክርስቲያን ሄጄ :

... ድንገት በመንገድ ሳልፍ አስቀይመውኝ ከህይወቴ ያላሶጣዋቸው ሰዎች ፤ ከንሰሀ አባቶቻቸው ጋር ስመለከት ሄጄ : " እኔ ላይ ያደረከውን ተናዘዝክ ?" ብዬ መጠየቅ ወይም "አባ ያደረገኝን ሰሙ ፤ እንዲህ ይደረጋል ነውር አይደል ? አዩልኝ አይደል የሰራኝን ሥራ ?" ብዬ ለእግዚአብሔር ማቃጠር ያምረኛል ።


ዛሬ ምንድነው የጠጣውት?
©ሶፊ
So ልጅቷን እኛ መስሪያ ቤት ነው የማውቃት (this kinda storytelling ከticktock ነው ያየኹት። grammatically wrong ነው አይደል ?ደግሞ አብዛኛዎቹ ብዙ view አላቸው...ምን ያህል ወረኛ ብንሆን ነው በእመቤቴ ! ስራ የለንም እንዴ? )

እና ወደ ወሬዬ ስመለስ ልጅቷ እኛ መስሪያ ቤት አዲስ ገቢ ናት።ከቢሮአችን ጎን ነው ቢርዋ...በውበቷ ብዙ ሰው ስለሚያሸረግድላት...በቅርጿ ሴቶችም ሳይቀሩ መነጋገሪያ ስላደረጓት...እጅግ ጣሪያ የነካ መኮፈስ...መንጠባረር...መመፃደቅ...ይስተዋልባታል።

...አንድ ቀን እኛ ቢሮ ለጉዳይ መጥታ ፈገግ ብላ ሰላም አለቺኝ...ከደማቅ ፈገግታ ጋር አፀፋውን መለስኹ።
...ከዛ ሌላ ጊዜ በመንገድ ስንገናኝ ሰላም መባባል የለብንም ? በሁለተኛው ቀን ፊት ለፊት ስንገናኝ ከመተላለፋችን በፊት ሰላም ልበላት አልበላት እያልኹ ሳመነታ "ሰላም ነህ ?" አለቺኝ በዛ ድምጿ...አፀፋዋን መለስኹ።

ከዛ በቀጣዩ ቀናቶች ፊት ለፊት ስንገጣጠም አንዴ ሰላም ትለኛለች ሌላ ጊዜ ትዘጋኛለች ። ብቻዬን "ሰላም ነው?" እያልኹ አልፋለሁ። አሁን አሁን እሷን ሳይ መሳቀቅ ጀመርኹ ሰላም ልበላት ወይስ አልበላት?

ቆይ ማነኝ ብላ ነው የምታስበው?
የእርሷ ሰላምታ ቀኔን የሚያበራው ፤ ምሽቴን የሚያደምቀው መሰላት ?


ምናባቷ ነው የምታወዛግበኝ ፤ ስንት ሰው ሳቀብኝ ብቻዬን " ሰላም ነው? " እያልኹ እያለፍኹ !




ሰላም ነው?
©ሶፊ
ከመሸ አንድ ነገር ታወሰኝ...

እኔ ዩንቨርስቲ የተመደብኹት ለአዲስ አበባ ቀረብ ያለ ቦታ ነበር...ዮንቨርስቲው ገና አዲስ የተመሠረተ በመሆኑ ገና infrastructure አልተሟላለትም...እና እኔ ደግሞ ከቤተሰብ ስርቅ የመጀመሪያዬ ነበር ። network እንኳን internet ለመጠቀም ቀርቶ ከቤተሰብ ጋር ለማውራት እራሱ አስቸጋሪ ነበር፤ ውስን ቦታሆች ላይ ብቻ ይሰራል። እጅግ ተጨንቄ ነበር ከቤተሰብ ስርቅ የመጀመሪያዬ ነው። ቤተሰብ የጠቀመኝ መስሎት እንኳን ከሰፈር ልርቅ ቀርቶ ሰፈር ውስጥ እንድጫወት ራሱ አይፈቀድልኝም ፤ ትምህርት ቤት ከዛ ቤት ነኝ ሌላ ቦታ ከሄድኹ ከቤተሰብ ጋር ነው ( ይሄ ትልቅ በደል አይደል ? ገና ለገና ይበላሻል ብለው ስለሚሰጉ Independent እንድንሆን እድሉን አይሰጡንም። ከዛ ቶሎ ራሳችንን እንድንችል ይፈልጋሉ ። እጅን ጥፍር አድርጎ አስሮ ተመገብ እንደማለት አይሆንም?) ።
ዩንቨርስቲ እያለኹ የመጀመሪያው አመት ላይ ትምህርቱ ያስጨንቅ ነበር።ገና ለገና እባረራለሁ የሚል ስጋት ስላየለብኝ በጭንቀት የተገዝኹበት ጊዜያት ብዙ ነበሩ ። እናም ስተክዝ ጊዜ ሄጄ የምቀመጥበት ከዶርማችን ፊት ለፊት አንዲት ስፍራ ነበረች ። ለካ ያቺ ስፍራ ለትካዜ ሁነኛ ስፍራ ኑራለች ፤ ሌሎች ወዳጆችንም ሠበሠበች ። እዛች ስፍራ ላይ ትላንትን በትዝታ ቃኘንባት ፣ በተለያየ ስፍራ ብናድግም የኾነ የሚያመሳስለን ነገር እንደነበር አስተዋልን ልዩነትን አጣጣምነው ፣ ነጋችንን ተነበይነው...እዛች ስፍራ ላይ በትካዜ ቁጭ ብለን ዛሬንና ነገን በተስፋ ድልድይ አያያዝነው ። ያቺ ልዩ ስፍራ ደስታችንን አስተናግዳለች ፣ ሐዘንን አስታግሳለለች ፣ ብቻ መብሠልሠልን ገትታለች...ብዙ ብዙ ነገር አይታለች። ታዲያ በሀይሉ ያቺን ስፍራ " ብሶት አደባባይ " ብሎ ሰየማት ።

ከጊቢ ወጥቼ ሐዘን በጎበኘኝ ጊዜ ያቺ ስፍራ ትውስ ትለኛለች ።


አሁን ላይ ለእኔ ያቺ ስፍራ እናንተ ናችሁ...! የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ።




ብሶት አደባባይ
©ሶፊ
"What Kind of Person Are You?"

Me???

I am different. I am imaginative.
I am far more than I have ever revealed
People know me as someone strong
But I'm fragile inside.

I'm someone who doesn't show my vulnerable side
Not because I don't have anyone
It's because I don't want them to stop relying on me

I am someone who smiles at small things
But I am also someone who gets hurt very often
I'm a shoulder to cry on for many people
But I'm also the one who has no shoulder to cry and to rely on.

I'm someone who forgives very fast
But I'm also someone who can't forget everything that's said.
I'm someone who adores sunlight
Yet, I'm also someone who discovers solace in the darkness of night.

I'm someone who has never been asked, "Are you okay?"
Yet, I'm also someone who will respond with, "I'm okay, I'm fine, nothing changed"


~Unknown source
"እወድሻለሁ እንኳን ብሎኝ አያውቅም " ብለሽ ማማረርሽን ሰማሁ...

እውነት እንደዛ ነው የምታስቢው?


ባልወድሽ ነው ከስርሽ የማልጠፋው?


ባልወድሽ ነው አስሬ ስምሽን የምጠራው?


ባልድሽማ...እስክትረሽኝ ነበር ከእይታሽ የምጠፋው...እኔ እንደዛ ነኝ የማልፈለግበት ስፍራ የምቆይ አይነት ሰው አይደለውም።


አየሽ ስስቴ ቃላት ሲደጋገም አቅሙን ያጣል...እንደቀላል ነገር "እወድሻለሁ" ይባላል?

በእኔ ቤት ይሄ ውድ የሆነ ቃል መለኮታዊ ሀይሉን አጥቶ ተርታ ቃል እንዳይሆንብኝ...መጠንቀቄ ነበር።

እንጂ...



እ ወ ድ ሻ ለ ሁ።


እንደውም ነይ...
ከዚህ ህይወት ፤ ከዚህ አለም ይዤሽ ልጥፋ !







ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
ለሚንቃት ወንድ ነፍሷን መበደል...
ለኩራተኛው እራሷን መግደል...
የዘመናችን ሴትነት አይደል...?

የሚወዳትን መች ትወድና...
ትሳለቃለች ፍቅርን በትና...

ከፍቅር ሸሽታ ፍቅርን ፍለጋ...
ትባክናለች ከማይሆን ሰው ጋ...




-Mahiru 🫡
"ሰበቡ ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር
ባላየሁ ባልወደድኩህ ምን ነበር...
ኡኡኡ
ምቀኛው ብዙ ነው እንዳፈር ለሳሱለትማ ነገር
ባላየሁ ባልወደድኩህ ምን ነበር...
ኡኡኡ"

"ሰማሀት?" አለቺኝ አንዳች የምስራች እንደተበሰረ ሰው በደስታ እየተፍነከነከች።
"ማንን?" አልኳት ካቀረቀርኩበት አሳዛኝ የፌስ ቡክ ወሬ ቀና እያልኩኝ።
"ሚካያን ነዋ!" አለች እንዳኮረፈ ሰው ከንፈሯን ጣል አድርጋ።
"እእ..." ብዬ መከፈቱን እንኳን ያላስተዋልኩትን ሙዚቃ ለማዳመጥ ጆሮዬን ጣል አደረኩ። በሚማርክ ድምፅ የተዜመ፤ በስሱ የተከፈተ ሙዚቃ ወደ ጆሮዬ ፈሰሰ...
ላንተ ስል
ሲያቀብጠኝ ወድጄ
ሰስቼህ እንደ ስለት ልጄ
ላንተ ስል
ለሊትና ቀን ቀን
ክፉውን አያለኹ ሰቀቀን...

ሰማዋት በማለት አይነት ወደ እሷ አቅጣጫ ዞሬ ፈገግ አልኩኝ።
"ሰማሀት አይደል ?" ብላ እሷም ፈገገች።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙዚቃ መስማት እርግፍ አድርጌ እንደተውኩ ታውቃለች።እሷ ስትጋብዘኝ ግን በድሮ ሙዚቃ አልጨክንም በተለይ...በእዮብ፣በጂጂ እና በሚካያ።
"አዎ ሰምቻታለሁ" አልኳት።
ፈገግታዋ ሳይቀዘቅዝ (ማግኘትና ማጣት የማያደበዝዘው ፈገግታ፤መውጣትና መውረድ ሳቋን አያሸንፉትም፤ ሁሌ ስትስቅ ነው የማውቃት...ሞልቶላት ግን አይደለም።)
"ታውቃለህ ስላንተ እንደዚህ ነው የማስበው..." አለቺኝ።
"እንዴት?"አልኳት ለመስማት ጓጉቼ አቀማመጤን እያመቻቸው።
"በስስት..." አለችና ትንሽ አሰብ አድርጋ ቀጠለች። "እኔ ወንፊት ነበርኩ ሁሉንም ለሰው የማወራ እኔ ጋር የማስቀረው ምንም ነገር የሌለኝ።ወንፊት እንኳን ከቀዳዳው የገዘፈውን ነገር ለራሱ ያስቀራል።እውነት ነው የምልህ ሰው የማያውቀው፤ያላወራኹት ደስ የሚል ነገር እንዲኖረኝ ስመኝ ነው የኖርኩት...ያ አንተ ነህ።ለሰው ያላወራሁ በስስት የያዝኩህ፣የምጠነቀቅልህ...ያ የተመኘውት ሰው አንተ ነህ።" አለቺኝ በፈገግታ እየተመለከተቺኝ።
ፈገግታዋ ከጥርሴ አለፈ ፤ ወደ ውስጤ ሰርፆ በሐሴት ሞላኝ።
ሶሻል ሚዲያው የነጠቀኝን ትኩረት አስመልሼ ዙሪያ ገባውን ቃኘውት...ምሳ ልንበላ የተቀመጥንበት ቤት ደጋግሜ የመጣሁበት ቢሆንም ዛሬ እንደ አዲስ አምሮ ታየኝ።



ይሄን አንብቦ... "Oh Sofi is in love." የሚል አይጠፋም።
እኔ ግን እላለኹ እነሆ ይሄ ድርሰት ምሳ ሊበሉ ከፊቴ የተቀመጡ ጥንዶችን ንግግር በምናብ ተስሎ ተፃፈ።



ከተቀደደው ማስታወሻ
18/02/2015
©ሶፊ
ቅንድም አንዱ በውስጥ መስመር መጥቶ " ቻናሉን ይዘህ ከምትተኛበት ለምን ህብረተሰቡን የሚያነቃ ነገር አትፅፍበትም " አለኝ ። (ማንም እየተነሳ ላንቃችኹ እያለን እኮ ተቸገርን። መጀመሪያ በደንብ ተኝተዋል ወይ የሚለው መጠናት የለበትም ? መቼ በወጉ ተኝተን ነው?)

"ቆይ አሁን ልተኛ ነው ስነቃ እፅፍላቸዋለሁ " ብዬው ነበር ሳልፅፍላችኹ ረሳሁት።

አሁንም እንቅልፌ መጣ በቃ የሚያነቃ ነገር ሳልፅፎላችሁ ልተኛ ነው።




እንደውም ለመንቃት መጀመሪያ በርትተን እንተኛ።
©ሶፊ
base (1).apk
31.1 MB
English book pdf የምታገኙበት App ነው።


Share ማንበብን እናበረታታ !
©ሶፊ
"ናፍቀሺኛል...

ቲሽ ! ናፍቀሺኛል ብቻ ናፍቆቴን አይገልፀውም። ቃለ አጋኖ ልጨምርበት ይሆን ? እርሱም በቂ አይደለም ።

በጣም ናፍቀሺኛል ብላትስ? ግን በጣም ብቻም አይደለም። ታዲያ ምን ይሻላል ?


የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
...ተስፋ መቁረጥ አያውቀኝም !…ያው እንደ ሰው ይከፋኝ አዝን እና እተክዝ ይሆናል…ነገር ግን በጭረሽ ተስፋ አልቆርጥም…እራሴን ከፍታው ላይ ብቻ ነው ማየት እምፈልገው…🤍


 
✍🏽 ፊሊሞን 🍷
2024/06/02 01:05:55
Back to Top
HTML Embed Code: