Telegram Web Link
"በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤
ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ (ጽላተ) ኪዳን፤
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን።"
(ማኅሌተ ጽጌ- አባ ጽጌ ድንግል)

የሁለተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል
82😍5👍4
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤
​ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን፤
እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤
ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤
ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን፤
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን።

ትርጉም፦
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ኾነ። የዓለማት ፈጣሪ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን በለበሰበት የሕፃንነቱ ወራት እንደ ነዳያን ቤት ስንኳ የሌለው ስደተኛና መጻተኛ ኾኖ በሰዎች ዘንድ እንደምን ተናቀ እያልኹ የእናቱ ድንግል ማርያም ኀዘን ለእኔ የልቅሶ ዜማ ኾነብኝ።

(ሰቆቃወ ድንግል)
112🙏6
450 አበቦች ለዛሬ ለሁለተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ደርሶልናል እናመሠግናለን!

ለሦስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ የተፈጥሮ አበቦችን የምትተባበሩን በውስጥ አናግሩኝ

@natansolo
74🙏38
ወዳጄ ሆይ! ጥቅም የማይሰጥኽን ነገር አትፈልግ፡፡ ወደዚኽ ዓለም ስትመጣ ባዶ እጅህን ነው፡፡ ገንዘብ ይዘኽ አልመጣኽም፡፡ ክብርን ይዘኽ አልመጣኽም፡፡ ዶክተር፣ ፕሬዚዳንት፣ ኢንጂነር የሚሉ ማዕረጋትን ይዘኽ አልመጣኽም፡፡ ስለዚኽ አጥተኽ ከኾነ አታጉረምርም፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል” እንዳለ /ማቴ.19፡24/ ገንዘብ የብዙ ክፉ ነገሮች ምንጭ እንደኾነ አስተውል፡፡ እንግዲኽ ከዚኽ የጌታችን ንግግር ገንዘብ ስንት ነገርን እንደሚከለክል አስተዋልክን? ታድያ ገነት መንግሥተ ሰማያትን ከመግባት የሚከለክል ገንዘብ ከአንተ በመራቁ ደስ አይልህምን?

ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት የምትወስድ መንገድ ጠባብ ናት፡፡ ወደ ገሃነም የምታስገባ ገንዘብ ግን ትዕቢትንንና ትምክሕትን የተመላች ናት፡፡ ለዚኽም ነው ጠባቢቱን መንገድ እንዲያገኝ ጌታ ባለጸጋውን “ያለኽን ሽጥ” ያለው (ማቴ.19፥21)፡፡ እንዲኽ ከኾነ ታድያ ገንዘብን የምታሳድደው ስለምንድነው? እግዚአብሔር ለገንዘብ እንዳትገዛ ብሎ በዚያም የገሃነም እራት እንዳትኾን ብሎ ገንዘብን ከአንተ አራቀልኽ፡፡

እውነተኞች አባቶች ልጃቸው ከአንዲት ዘማ ሴት ጋር የማይገባ ሥራ ሲሠራ ባዩት ጊዜ ከርሷ ይለይ ዘንድ ይገሥፁታል፡፡ ርሱን ከርሷ መለየት ባይችሉ እንኳን ርሷን ያባርሯታል፡፡ ክቡር ልዑል የሚኾን እግዚአብሔርም ለእኛ በማሰብ፣ እኛን ከመውደዱ የተነሣ ገንዘብን (ሀብትን) ከእኛ እንዲርቅ ያደርጋል፡፡ ስለዚኽ እንዲኽ ስላጣን ብቻ ክፉ ነገር እንደደረሰብን አድርገን ልናስብ አይገባንም፤ ክፉ ኃጢአት ብቻ ነውና፡፡ ገንዘብ በራሱ መልካም አይደለም፡፡ መልካም የሚኾነው እግዚአብሔርን ደስ ስናሰኝበት ብቻ ነው፡፡

በማግኘት ውስጥ ከመኾን ይልቅ በማጣት ውስጥ ኾኖ እግዚአብሔርን ማገልገል ይበልጣል፡፡ ስለዚኽ ድካምን፣ መከራን፣ ማጣትን እንደ ክፉ ነገር በማየት አንጥላው፡፡

በእውነት ያለ ሐሰት ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር የክብር ክብር፣ ጌትነት የባሕርዩ በሚኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰጭነት በመንግሥተ ሰማያት ጸጋ ክብር እናገኛለንና ማጣትን አንጥላው፡፡ አሜን!!!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
128🙏23👍2
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡።

የኀዘን መግለጫ

"አድኅነኒ እግዚኦ እስለመ ኀልቀ ኄር አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቋልና።" መዝ. 11፥1

እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም!

ለዚህም ምስክሩ ታላቅ አረጋዊ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ፣ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ፣ የተጠቁት ወዳጅ ፣ የትውልድ አባት የሆኑት የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ነበሩ፡፡

ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች፡፡

ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

እግዚአብሔር አምሳክ ኢተዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ
ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
132🕊11🙏3👌1
2025/10/21 21:43:17
Back to Top
HTML Embed Code: