እውነተኛ ክብርን ማግኘት ትፈልጋለህን? ክብርን ናቅ፤ ያን ጊዜም ትከብራለህ፡፡ ለምን እንደ ናቡከደነፆር ታስባለህ? እርሱ ክብርን መጨመር በፈለገ ጊዜ ከዕንጨትና ከድንጋይ የራሱን ምስል ሐውልት አቁሞአልና፤ ሕይወት በሌለው በዚህ ግዑዝ ነገር ሕይወት ላለው ለእርሱ ክብር የሚጨምርለት መስሎት ነበርና፡፡ [ነገር ግን ክብር ሳይኾን ውርደት አገኘው፡፡] እንግዲህ የስንፍናውን መጠን አለፍነት ታያለህን? እከብርበታለሁ ብሎ ባቆመው ነገር እንዴት የገዛ ራሱን እንደ ዘለፈበት ትመለከታለህን? በራሱና በገዛ ነፍሱ ንጽህና ሳይኾን ሕይወት በሌለው ነገር ላይ መደገፉ፣ በዚያ ረዳትነትም ክብርን ማግኘት ፈልጎ ሐውልቱን ማቆሙ፥ ከዚህ በላይ ምን ሞኝነት አለ? ራሱን ለማክበር ብሎ የገዛ ሕይወቱን እንደ ማስተካከል፥ በዕንጨት ላይ ዕንጨት እንደ መጨመር ያለ ምን ሞኝነት አለ? ይህ ማለት “አንድ ሰው ፈሊጥ ያውቃል የሚባለው ሰው በመኾኑ ሳይኾን የቤቱ ምንጣፍ ያማረ ስለ ኾነ፣ የቤቱ ደረጃም የተወደደ ስለ ኾነ ነው” እንደ ማለት ይቈጠራል፡፡ በእኛ ዘንድ በእኛ ዘመን ናቡከደነፆርን የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እርሱ ሐውልት እንዳቆመ አንዳንዶችም ስለ ለበሱት ልብስ፣ ስለ ገነቡት ቤት፣ ስላላቸው ፈረስ፣ ገንዘብ ስላደረጉት ሠረገላ፣ ወይም ስለ ቤታቸው አሠራር ክብር የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡ ከሰውነት አፍአ ወጥተው ይህን በመሰለ መጠን አለፍ ዕብደት ይያዛሉ፡፡ የራሳቸውን ሕይወት እንደ ማስተካከል ቁሳዊ ነገርን በመሰብሰብ ክብርን ይፈልጋሉ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስ ወንጌል፣ 4:20 በተረጎመበት ድርሳኑ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

❤139🙏21🕊6👍1
"እግዚአብሔር ከዓለም በፊት፣ እስከ ዘለዓለምም ድረስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ። እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ። እግዚአብሔር በመለኮቱ አለ።
ከጎሕና ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ።
ሰማያት ሳይዘረጉ የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
ከፀሐይና ከጨረቃ ከከዋክብትም በፊት። ከብርሃናትም መመላለስ በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
ከሚቀሳቀሱ እንስሳት በፊት፣ ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት፣ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
አዳምን በእርሱ አምሳልና እርአያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዙንም ሳያፈርስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።...."
(ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)

❤159🙏23👍3💯3🏆2
የእረፍቴን አሸኛኘት በዐይኔ በማየቴ ደስ ብሎኛል!
ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
ላይክ፣ ሼር፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ።
https://youtu.be/iMm5FPapg2w?si=ZvwmAo2r7DbcpYWo

YouTube
የእረፍቴን አሸኛኘት በዐይኔ በማየቴ ደስ ብሎኛል|| የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የምስጋና መርሐ ግብር ክፍል 3
#ተው_ማረኝና_ልሂድ_በእግሬ
#የሰሜን_ወሎ_ሀገረ_ስብከት_የማኅበራዊ_ሚዲያ_አማራጮችን_ይወዳጁ_ለሌሎችም_ያጋሩ፦
~ ቴሌግራም፡ https://www.tg-me.com/NWDnews
~ ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
~ ድረገጽ፡ https://eotc-nw.org
~ ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK
~ ቲክቶክ https://w…

❤47
"ለሰዎች የምትሰጠው ምንም ነገር ባይኖርህ ሞቅ ያለ ፈገግታ እና መልካም ቃልን ስጣቸው፣ ፍቅርን ስጣቸው፣ መልካምነትን ስጣቸው፣ የማበረታቻ ቃልን ስጣቸው፣ልብህን ስጣቸው..
ሰዎችን በማሳዘን ፈንታ ሁሌም ይህንን ብናደርግ ኢየሱስ በእኛ እንዳለ ያኔ ይታወቃል።
(አቡነ ሽኖዳ)

🙏138❤107😍10🕊6👍4👌1
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሰላም የቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቤተሰቦች ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ለአምስት ችግረኛ ተማሪዎች ለ2017 የትምህርት ዘመን የመማሪያ ቁሳቁስ ከዩኒፎርም (ከትምህርት ቤት የደንብ ልብስ) ጋር አሟልተን እንዲማሩ አድርገናል። ዘንድሮም ለ2018 የትምህርት ዘመን ለእነዚህ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት እንዲማሩ ለማድረግ የተለመደ ትብብራችሁን ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን። እስከዚህ ሰዓት ድረስ፦ ➛ ሁለት…
በጎ አድራጊ የቅዱስ ዮሐንስ ልጆች ይህንን ነገር እያያችሁልኝ አይደለም...
👍27❤11🙏6
#ጻድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት - #ነሐሴ_24
ነሐሴ ሃያ አራት በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለሃይማኖት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖሩ።
በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ። የሀገር መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል። ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶች ያደርጋቸዋል።
በዚያም ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ።
ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት ባያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደመኳንንቶቹ ሁሉ ላከ።
እግዚእ ኀረያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞራሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት። ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድን ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ።
የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዙእ ኀረያ እንደሆነች አገኛት እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው።
ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው የዜናው መሰማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው።
ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ይህ ቅዱሱ ተፀንሶ በታኀሣሦ ወር በሃያ አራት ተወለደ በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ ቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸውና ከጐረቤቶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው።
ለክርስትና ጥምቀትም በአስገቡት ጊዜ ፍሥሓ ጽዮን ብለው ሰየሙት። ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመነፈስ ቅዱስ ጸና።
ከዚህም በሗላ ዲቁና ይሾመው ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት በዚያንም ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ነበር። ወደ ጳጳሱም በአደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት። የዲቁና ሹመትንም ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
ጐልማሳ በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ። ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ የሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክነፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳጄ አትፍራ እንግዲህ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኀፀን መርጬ አከብሬሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኩሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ።
ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘብን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርኩዙን ይዞ በሌሊት ወጣ።
ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሔዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ። ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ ለጣፆት የሚሠውበትን ሁሉ ሻረ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንት እስከሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ።
ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሔዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው እርሱ ግን በደኀና ይመለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሠቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትንም ጦር ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው።
ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር።
ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኀነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስን በማመን ያጸናቸዋል።
ከዚህ በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ በገድል ተጸምዶ ወደሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደባሪያ ሲያገለግል ኖረ በአንድነት የሚኖሩ መነኰሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር።
በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በሗላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደሚኖር ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔዶ ከእርሱም የምንኲስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሔዶ ለአቡነ አረጋዊ አራተኛ ከሆነ ከአባ ዮሐኒ ዘንድ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ። ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ።
በዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ ከዚያም ግራርያ ወደ ሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበረ ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው።
ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኲሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስበርሳቸውም አይተዋወቁም እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ሰለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እነደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም።
በዚህም በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በሗላው በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ። በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣ ኖረ።

❤57
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።
መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።
አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳ በአባታችን ተክለሃይማኖት ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)

❤66🙏18
"እንግዲህ ከሀሜት፣ ከሀሰት ጓደኝነት፣ የጌታን ሥም በግብዝነት ከሚጠሩ፣ ምንም የማያውቁትን ከሚያታልሉ በመራቅ ለጥሩ ነገር እንቅና። ማንም ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው። ማንኛውም በመስቀል ላይ መከራ መቀበሉን የማያምን ዲያብሎስ ነው። ማንም የክርስቶስን ትምህርት ለራሱ እንደሚመቸው የሚያጣምም እና ትንሳኤና የመጨረሻ ፍርድ የለም የሚል ይህም የሰይጣን የበኩር ልጅ ነው።"
ቅዱስ ፖሊካርፐስ
ቅዱስ ፖሊካርፐስ
❤168🙏20🕊3
የነገሥታት ንጉሥ ፈጣሪን ወልደሽ፣
እንዴትስ መመሥገን ማርያም ይነስሽ፤
ዓለም ለማመሥገን እውነቱ ቢከብደው፣
እኛ ግን ስላንቺ ምንለው ብዙ ነው።
Share and Subscribe
https://youtu.be/5xIut9G890M?si=eObSKQRCJ8aOtlQX

የነገሥታት ንጉሥ ፈጣሪን ወልደሽ - በዘማሪ አቤል መክብብ
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
❤49🙏6
ሰላም የቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቤተሰቦች
ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ለአምስት ችግረኛ ተማሪዎች ለ2017 የትምህርት ዘመን የመማሪያ ቁሳቁስ ከዩኒፎርም (ከትምህርት ቤት የደንብ ልብስ) ጋር አሟልተን እንዲማሩ አድርገናል። ዘንድሮም ለ2018 የትምህርት ዘመን ለእነዚህ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት እንዲማሩ ለማድረግ የተለመደ ትብብራችሁን ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን።
እስከዚህ ሰዓት ድረስ፦
➛ 4 የቻናላችን ቤተሰቦች ተሣታፊ ሆነዋል
የመጨረሻ ቀናችን እስከ ሰኞ ነው መሣተፍ የሚችል በውስጥ መስመር @natansolo ማናገር ይችላል!

❤29🙏4
"እኔ ከእርሱ [ከባልንጀራዬ] ጋር ምንም ግንኙነት የለኝምና የሚል ደካማ መልስም አትስጠኝ፡፡ ምንም ግንኙነት የሌለን ከዲያብሎስ ጋር ብቻ ነው፡፡ ከሰዎች ኹሉ ጋር ግን በጣም ብዙ የምንጋራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም አንድ ዓይነት ባሕርይ (ሰው መኾንን) አለን፤ እኛ በምንኖርባት ምድር ይኖራሉ፤ እኛ የምንበላውን ምግብ ይበላሉ፤ አንድ ጌታ አለን፤ እኛ የተቀበልነውን ሕግ ተቀብለዋል፤ እኛ ወደ ተጠራነው መንግሥትም ተጠርተዋል፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም አንበል፡፡ እንዲህ ብሎ መናገር ሰይጣናዊ ንግግር ነውና፡፡ ዲያብሎሳዊና ኢ-ሰብአዊነት ነውና፡፡ ስለዚህ ለወንድማችን ያለንን ጥንቃቄ እናሳይ እንጂ እንደዚህ ዓይነት ቃላትን አንናገር፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት፣ 1፥32)
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት፣ 1፥32)
❤126🙏13💯5🕊4
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስምህ፡-
“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መንፈሳዊ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይገባል፡፡ ዋጋው የማይታወቅ ነጋዴ ገንዘቡን ሁሉ ሰጥቶ የተወዳጀው እውነተኛ ዕንቁ ደንጊያ አንተ ነህ፡፡ ይህንን የዕንቁ ደንጊያ በሰውነታችን ውስጥ ያበራ ዘንድ ደግሞ ዛሬ ለእኛ አድርግልን፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የተቀደሰው ስምህ የልባችን ደስታ የሰውነታችን ሽልማት ጌጥ ነው፡፡ …
አቤቱ ምድርንና ዓለሙን ሁሉ ዞርሁ ያለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር ጣፋጭ ስምን አላገኘሁም፡፡ በምድር ላይ የሚደረግ ረድኤትና ኃይል ሁሉ ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር አይሆንም፡፡ እግዚአብሔርን ያገለገሉ የሰው ወገኖች ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኵል ነው፡፡ የከበረና የተመረጠውን እጅ መንሻ ሁሉ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አልተቀበልንም፡፡ ሰማይና ምድር ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሁከት አልጸኑም፡፡…
የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከማር ከወለላና ከሦከር ይጥማል፡፡ ማርና ሦከር በሚበሉበት ጊዜ ይጠገባሉ፤ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን አይጠገብም፡፡ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምጠራ ጊዜ ከንፈሮቼ ማርን ያንጠባጥባሉ፡፡ ማር፣ ስኳርና እንጀራ ቢሆኑም እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእኔ ዘንድ ጣዕም የላቸውም፡፡ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሻለኛልና ከሰማይ በታች ካለ ፍጥረት ሁሉም ይበልጣልና፡፡
ቸርነትህ ብዙ ነው፤ አይነገርምም፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በሚያምንብህና በሚወድህ አፍ ሁሉ ስምህ የታወቀ ነው፡፡ በሕግ ከታወቁ ምስጋናዎች ሁሉ ከውስጣቸው የሚመስልህ የለም፡፡ የዓይኖቼ ብርሃንና የሥጋዬ ብርታት ከከበረው ስምህ ወገን ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እስከ ሕይወቴ መጨረሻ የከበረ ስምህን በአንደበቴ ዘወትር የተሾመ አድርገው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትያን ሰውነት ሁሉ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአንድነት ያከብራሉ፤ ያመሰግናሉ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ከኃጢአት ወገን የሚሆን የክፋት መንፈስን ሁሉ ከእኔ አስወግድ፡፡ መዳኛችን በሚሆን በዚህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ክርስቲያኖች ሁላችሁም ፈጽሞ ደስ ይበላችሁ፡፡
የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጣፋጭ ነው፤ በገነት ካለ ፍሬም ይልቅ ይጣፍጣል፡፡ አባታችን ዳዊት በአመሰገነበት በከበረ መዝሙር የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ስም ፈጽሞ እናመሰግናለን፤ እናከብራለን፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ብዙ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በእኔ ላይ አሳድር፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አንተን ደስ የማያሰኝህን ሓሳብ ሁሉ ከእኔ ታርቅ ዘንድ ወዳንተ እለምናለሁ፤ ከአንተም እሻለሁ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በጌትነትህ ከእኔ ጋር ቸርነትህን አድርግ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር አባትህ ጋራ ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሰግድልሃለን፡፡ አሜን!”
(ምንጭ፡ ግብረ ሕማማት)

❤126🙏11👍5💯1🏆1
"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡
እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡
ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወደ ኦሎምፒያስ ከላከው መልእክት የተቀነጨበ

❤190😍10🙏1
እግዚአብሔር ሲቀጣን
"አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ የተላኩ መልእክቶች፥ ገጽ 36)

❤201💯24🙏11🎉1👌1🕊1
፩
ተግሣጽ ገንዘብን የመውደድ ጣጣው
..ወዳጆቼ እለምናችኋለሁ፤ ከእርሱ እረኝነት ሥር ሆነን እንሰማራ እርሱን ከታዘዝን ድምፁንም ከሰማን ሌቦችን ከመከተል ከተመለስን እንድናለን፡፡ የእርሱ ድምፅ ምንድን ነው? “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ ልበ ንጹሐን ብፁዓን ናችሁ፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው” የሚሉት ናቸው፡፡ (ማቴ 5፥3፣ ማቴ. 8፥7) እነዚህን ፈጽመን ከተገኘን ከእረኛው ጥበቃ ሥር እንሆናለን፡፡ ተኵላውም በሩን አልፎ ወደ በረቱ ዘልቆ መግባት አይቻለውም፡፡ ወይም በእኛ ላይ ቢነሣ ለገዛ ጥፋቱ ይሆንበታል፡፡
ለእኛ ራሱን እስከ መስጠት ደርሶ የወደደን እረኛ አለን፡፡ እርሱ ብርቱ ነው፤ ይወደናልም፡፡ ስለዚህ ለመዳን እንቅፋት የሚሆንብን ምን አለ? እርሱን ላለመታዘዝ ካላመፅን በቀር፡፡ በእርሱ ላይ ዓመፅን ሊባል የሚቻለው እንዴት ነው? ጌታችን ምን እንደሚል ስሙ፡- “ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም" ይለናል፡፡ (ማቴ. 6፥24) ስለዚህ እግዚአብሔርን የምናገለግል ከሆነ ለገንዘብ ባሮች ልሆን አይገባንም።
ባለጸጋ ለመሆን ከመሻት በላይ እጅግ ጽኑ የሆነ ባርነት የለም፡፡ ለገንዘብ ባሪያ መሆን ደስታን አያመጣልንም በተቃራኒው ግን ጭንቀትንና ቅንዓትን፣ ተንኮልና ጥላቻን፣ በሐሰት መካሰስን፣ እጅግ ብዙ የሆነ የጽድቅ እንቅፋቶችን፤ ስንፍንና ዋልጌነትን፣ ስስትን፣ ስካርን ያመጣብናል፡፡ ገንዘብን መውደድ ከሰው ባርነት ነጻ የሆኑትን እንኳ ባሮች ያደርጋቸዋል። ባርነቱ በገንዘብ የሚገዙትን ሰዎች ዓይነት ባርነት አይደለም፤ ከዚህ በእጅጉ የከፋ ነው፡፡
ገንዘብን መውደድ ሰዎችን ባሮች ብቻ የሚያደርጋቸው አይደለም፤ ከእርሱ ለከፋና ጨካኝ ጌታ ለሆነ ለሥጋ ፈቃድ አሳልፎ የሚሰጥና ነፍስን ለክፉ ደዌ የሚዳርጋት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ባርነት እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን ሁሉ ያጠፋሉ፡፡ ከዚህ ባርነት ካልተላቀቁ በአገዛዙ ጨካኝ ነው፡፡ ይህ ዲያብሎስ የሚሠለጥንበት አገዛዝ ነው! ከዚህ በላይ የከፋ ባርነት ከቶ የለም፡፡ በዚህ ክፉ ባርነት ደስተኞች ከሆንንና በራሳችን ላይ የባርነቱን ሰንሰለት ካጠለቅን ድቅድቅ ከሆነው የእስረኞች ወኀኒ ቤት መታሰርን መርጠናል፤ ወደ ብርሃን መውጣትን አልፈቀድንም፤ ኀጢአት በእኛ ላይ እንዲሠለጥን አድርገናል፤ በደዌአችንም ደስተኞች ሆነናል ማለት ነው፡፡
እንዲህ ከሆንን ከቶ ነጻ መውጣት አይቻለንም፤ ነገር ግን በማዕድን ቁፋሮ ያለማቋረጥ የሚደክሙና የሚለፉ ስዎች አብዝተው እንዲደክሙ፤ እኛም እንዲሁ እንደክማለን ፍሬአችን ግን ጥፋት ይሆናል፡፡ በእውነት ከዚህ የከፋ ምን አለ? ሆኖም ከዚህ ጽኑ ባርነት ነጻ እንዲያወጣን ለማንም ሰው አንፈቅድም፤ ነገር ግን እንጨነቃለን፣ ደስታን አጥተን እንቅበዘበዛለን፡፡
ይቀጥላል....
(ዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ድርሳን ስድሳ ዮሐ. 9፥39 በተረጎመበት ድርሳኑ ገጽ 84-87 - ዲያቆን ሽመልስ መርጊያ እንደተረጎመው)

❤81🙏15💯6