Telegram Web Link
#ትሕትና

ልቡ አብዝቶ የጸለየውን ያህል በዚህ መጠን ልብ ትሑት ይሆናል፡፡ ትሑት ቢሆን እንጂ ትሑት ካልሆነ የሚለምን፣ የሚማልድ የለም፡፡ ፈጣሪ ጽኑ፣ ክቡር፣ ትሑት፣ ኅዙን፣ ልቡና የጸለየውን ጸሎት አልቀበልም አይልምና፡፡

ልቡናም በመከራ ትሑት ካልሆነ ትዕቢትን መተው አይቻለውም፡፡ ትሕትና መከራን ያርቃልና፤ ሰው ትሑት በሆነ ጊዜ ይቅርታን ያገኛል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር እንደተሰጠችው ያውቃል፡፡ ያድነኛል ብሎ በማመን ዕውቀት ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ሰው ረድኤተ እግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠችው ያወቀ እንደሆነ ያድነኛል ብሎ ያምናል፡፡ የድኅነት መገኛ እንደሆነች፣ የሃይማኖት መገኛ እንደሆነች፣ ከመከራ ማዕበል ሞገድ ከውስጧ  የሚያድን ወደብ እንደሆነች፣ በመከራ ድንቁርና ላሉ ዕውቀታቸው እንደሆነች፣ የድኩማን መጠጊያ በመከራ ጊዜ የሚያርፉባት ክንፍ እንደሆነች፣ በጽኑ ደዌ ጊዜ የሚድኑባት ረድኤት እንደሆነች፣ በጭንቅ ጊዜ የሚያርፉባት የሕይወት ተክል እንደሆነች፣ በጠላት ፊት የተቃጣ ፍላጻ እንሆነች ያውቃል፡፡

(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ-ገጽ 31)
111😍9🙏6👍3💯1
ጠቃሚ ምክር ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ባልንጀራህን ልትገሥጽ ብትፈልግ፣ ልትመክር ብትሻ፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ልታደርግ ብትፈቅድ ይህን ያለ ቍጣና ከስሜታዊነት ወጥተህ አድርገው፡፡ የሚገሥጽ፣ የሚመክር ሰው ባለ መድኃኒት ነውና፡፡ ነገር ግን ለራሱ ባለ መድኃኒትን የሚሻ ከኾነ ሌላውን ሰው እንደ ምን መፈወስ ይቻለዋል? ራሱ ቁስለኛ ኾኖ ሳለ ሌላውን ለመፈወስ ከመኼዱ በፊት የራሱን ቁስል የማያሽረው ለምንድን ነው? ባለ መድኃኒት ሌላ ሰውን ለማዳን በሚኼድበት መጀመሪያ የራሱን እጅ ያቆስላልን? የሌላውን ዐይን ለማዳን የሚኼድ ባለ መድኃኒት አስቀድሞ የራሱን ዐይን ያሳውራልን? እንዲህ ከማድርግ እግዚአብሔር ይጠብ ቀን፡፡

ስለዚህ አንተ ሰው! ሌላውን ከመገሠጽህና ከመምከርህ በፊት የራስህ ዐይኖች አጥርተው የሚያዩና ንጹሃን ይኹኑ፡፡ ሕሊናህን አታቆሽሸው፡፡ እንዲህ ከኾነ ግን ሌላውን ማንጻት እንደ ምን ይቻልሃል? በቍጣ ውስጥ መኾንና ከቍጣ ንጹህ መኾን የሚሰጡት ውስጣዊ ሰላም በጭራሽ የሚነጻጸር አይደለም፡፡ እንዲህ ከኾነ ታዲያ ሰላም የሚሰጥህን ጌታ [ነፍስህን] አስቀድመህ ከዙፋኑ ላይ ጥለህና ከጭቃው ጋር ለውሰኸው ስታበቃ፡ ከእርሱ እርዳታን የምትሻው እንዴት ብለህ ነው? ዳኞች የዳኝነት ሥራቸውን ሊያከናውኑ ሲፈልጉ አስቀድመው ካባቸውን ደርው ከፍርድ ዙፋናቸው ላይ እንደሚቀመጡ አላየህንምን? አንተም ነፍስህን የዳኝነት ልብስን አልብሰሃት በተገቢው ቦታዋ ልታስቀምጣት ይገባሃል፡፡ እርሱም የማስተዋል ልብስ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 62-63)
78🙏14👍1
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው ለተለያዩ አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶች ምደባ አከናውኗል።

በዚህ መሠረት፦

ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ የኢሉባቡር ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮምያ ብሔረሰብ ዞን ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ።

ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ

ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና የሆሮጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ በሁለተኛ ቀን የጉባኤው ውሎው ወስኗል።
🙏3715🕊7🏆1
"ዓይኖቻችን ለብርሃን ሲጋለጡ ዙሪያውን ማየት እንደሚችሉ ኹሉ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያተኮረች ነፍስም የማይጠፋ ብርሃኑን ታገኛለች፡፡ ይህም ከልብ የመነጨ ጸሎት ነው እንጂ ተራ ወይም ለተወሰኑ ጊዜ የሚቆይ አይደለም:: በቀናችን እና በሌሊታችን ውስጥ የሚዘራ ጸሎት ነው፤ ከእግዚአብሔር ጋርም ቀጣይነት ያለው ወዳጅነት ይፈጥራል፡፡

ችግረኞችን በመንከባከብ፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ወይም በልግስና የምንሠራም ብንሆን እንኳ ሁልጊዜም አምላክን በአእምሯችን ልንይዘውና ልናስታውሰው ይገባል። የእግዚአብሔር ፍቅር እንደ ማጣፈጫ ጨው ኾኖ ይሠራል፤ ለድርጊታችን ጣዕምን ይጨምራል፡፡ እንግዲያውስ ሕይወታችንን ኹሉ ለእርሱ ስናቀርብ ከቆየን፣ የድካማችንን ፍሬ፣ ለዘለአለም ወደ እኛ የሚጎርፈውን ልንቀበል የተገባን እንሆናለን፡፡

ጸሎት በእግዚአብሔር እና በሰው ልጅ መካከል አስታራቂ ኾኖ ያገለግላል። ጸሎት ነፍስን ወደ ሰማያዊ ከፍታ ከፍ ያደርጋታል፤ እዚያም እግዚአብሔርን በቃላት ሊገለጽ በማይችል ሙቀት ውስጥ ትታቀፋለች። የተራበ ሕፃን የእናቱን ወተት እንደሚመኝ፣ ነፍስም መለኮታዊ ምግብን ትሻለች፤ የተቀደሰ ስእለትዋን በመፈጸም፣ ከሚታዩ ወይም ሊታሰቡ ከሚችሉ ሀብቶች ኹሉ የሚበልጡ ስጦታዎችን ትቀበላለች፡፡

ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ነው፤ ለነፍስ ደስታን ያመጣል፡፡ ይሁን እንጂ ጸሎት በቃላት ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ እወቁ፡፡ የእግዚአብሔር ጥልቅ ናፍቆት ነው፤ በቃላት ሊገለጽ የማይችል የአምልኮ መንገድ ነው፤ ከመለኮታዊ ጥበብ የተገኘ እንጂ ከሰው ጥረት አይደለም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በአግባብ ለመጸለይ ቃላትን መምረጥ ባልቻልን ጊዜ፣ መንፈስ ራሱ በቃላት ይረዳናል እንዳለ ኹሉ፡፡ (ሮሜ ፰፥ ፳፮)

አምላክ ለአንድ ሰው እንዲህ ዓይነቱን ጸሎት ስጦታ ከሰጠው፣ የማይጠፋ ሀብትን፣ መንፈስን የሚያረካ ሰማያዊ ምግብ አብሮ ይሰጠዋል፡፡ ማንም ይህ መለኮታዊ ምግብ ያጋጠመው፣ በነፍሱ ውስጥ ዘላለማዊ ነበልባል ይቀጣጥላል፤ በመሆኑም ጌታን ለዘላለም ይናፍቃል፡፡

በዚህ መንገድ ላይ ለመጓዝ፣ ውስጣዊ ማንነትህን በትህትና በማስጌጥ ጀምር። በፊትህ ብርሃንም ይብራ፡፡ በታማኝነት እና በሞገስ በተጌጡ መልካም ስራዎች አስጊጥው፡፡ ጌታህንም ወደዚህ ግርማ ሞገስ ወዳለው መኖሪያ ቤት እንኳን ደህና መጣህ ብለህ ወደ ነፍስህ መቅደስ ጋብዘው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)
73🙏8👌1
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል፦

አንዳንድ ቀን ድኾችን ስትረዱ አያለሁ፡፡ ነገር ግን በጣም አዝንባችኋለሁ፡፡ ምክንያቱም "እከሌ ይኼን ያህል ብር ሰጠ" ለመባል ብቻ ስለምትመጸውቱ፡፡

ታዲያ ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን አለ? ለምንድነው ደካማውና ሟቹ እኔ እንዳመሰግናችሁ የምትፈልጉት? ባለጸጋው እግዚአብሔርን ትታችሁ ከድኻው ከእኔ ምስጋናን የምትሹት ለምንድን ነው? የዘለዓለም ሕይወት የምሰጠው እኔ ነኝን? እንዴት ነው የምታስቡት? እግዚአብሔር ድኻ ነውን? ታዲያ እርሱ እንደማያመሰግናችሁ አድርጋችሁ በመቍጠር እኔ በደለኛው እንዳመሰግናችሁ የምትጠብቁት ለምንድን ነው?

(አምስቱ የንስሐ መንገዶች - ገጽ 80)
126🙏18💯9👌5👍4
የንስሐ መንገዶች

አምስት የንስሐ መንገዶች አሉ። የተለያዩ ቢሆኑም ቅሉ ሁሉም የሚያደርሱት ግን ርስት መንግሥተ ሰማያት ነው። እነርሱስ ምን ምን ናቸው ? ያልከኝ እንደሆነ እንዲህ ብየ እመልስልሃለሁ፦

የመጀመሪያው መንገድ "የራስን ኃጢአት ማመን፣ መጥላትና ማውገዝ ነው።

ይኽውም ልዑል ቃል ኢሳይያስ "እንድትጸድቅ መጀመሪያ ኃጢአትህን ተናገር እንዳለው" (ኢሳ 43 ፥26 )፤ ክቡር ዳዊትም "በደሌን አልሸፈንኩም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውኽልኝ" ብሎ እንደተናገረ መዝ. 31፥5 ስለዚህ አንተም ስለ ሠራኽው ኃጢአት እራስህን ውቀሰው። በዚህ እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ታደርገዋለህና። ይህ ብቻ ሳይሆን ስለ ኃጢአቱ እራሱን የሚወቅስና ኃጢአቱን የሚኮንን ሰው በተመሳሳይ ኃጢአት በቀላሉ አይወድቅምና። ስለዚህ በጌታ የፍርድ ዙፋን የሚወቅስህ እንዳይኖር ዛሬ እውነተኛ ወቃሽ በኾነው ሕሊናህን አንቅተህ በራስህ ላይ ወቃሽና ከሳሽ አድርገህ ሹመው። ይህ አንዱና ደገኛው መንገድ ነው ።

ሁለተኛው የንስሐ መንገድ ደግሞ የወገኖቻችንን በደል ይቅር ማለትና በበደሉህ ላይ ቅሬታና ቂም አለመያዝ ነው።

እንዲህ ስናደርግ "ለሰወች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተንም ደግሞ ይቅር ይላችኋል" እንዲል እኛ በጌታችን ላይ ያደረግነውን በደል ይቅር እንባላለንና። ማቴ. 6፥14

ሦስተኛውን የንስሐ መንገድ መንበረ ጸባዖት የደርስ በትጋትና በጥልቅ ስሜት የሚደረግ "ከልብ የመነጨ ጸሎት ነው"

ጨካኙ ዳኛ እንዲርፈድላት ያደረገችው ያቺ መበለት እንዴት እንዲፈርድላት እንዳደረችው አታያትም? ( ሉቃ 18፥3) አንተ ግን ሩኅሩኅና መሐሪ የኾነ ጌታ ነው ያለህ። እርሷ በጠላቶቿ ላይ እንዲፈርድላት ነው የጠየቀችው፤ አንተ ግን እምትጠይቀው ስለራስህ ድኅነት ነው።

አራተኛ መንገድ አለ እርሱም "ምጽትዋ ነው " ይህም እጅግ በጣም ታላቅ የኾነ ኃጢአትን የሚስተርይ ኃይል አለውና።

ናቡከደነጾር ኃጢትን ንቅስ ጥቅስ አርድጎ ወደ ክኅደት ሁሉ በገባ ጊዜ እንዲህ ብሎታልና፦ "ንጉሥ ሆይ ! ምክሬ ደስ ያሰኝህ ኃጢአትህም ለጽድቅ በደልህን ለድኾች በመመጽወት አስቀር" (ዳን. 3፥27 ) ይህ ቸርነትና ሰውን መውደድስ ምንስ ይስተካከለዋል? እንዴት ያልከኝ እንደሆነ ስፍር ቁጥር የሌለውን ኃጢአት ከሥራ በኋላ ከዚያ ኹሉ በደል በኋላ እንደርሱ ለሆኑ ሰወች ርኅራኄን ቢያደርግ ከተገዳደረውና ከተጣላው አምላክ ጋር መታረቅ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታልና ።

አምስተኛው መንገድ "እንዲሁም ትሕትናና እራስን ማዋረድ ኃጢአትን ያደክማል"

ይህንንም ቀራጩ ያረጋግጥልናል ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ለማንሳት እንኳንስ እስኪፈራ ድረስ በታላቅ ትሕትና ራሱን ባዶ ባደረገ ጊዜ "ጻድቅ ሆኖ ሄደ ተብሏልና ።(ሉቃ 18፥13) ስለዚህም ምንም ምግባር ቢኖርህም እንኳን በደልህን ከመናር በቀር በጎ ምግባርህን አታስበው። ያን ጊዜ እግዚአብሔር የበደል ሸምክህን ያራግፍልሃል።

ስለዚህ እነዚህን መንገደኞች ተመላለስባቸው እንጅ ሰነፍ አትኹን።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 78-80)
107👍10🙏6😍4
#ሰናይ_ውሳኔ

ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የአራተኛ ቀን ውሎ በተለያዩ አህጉረ ስብከቶች የተለያዩ ክብረ በዓላት፣ የዐውደ ምሕረት፣ የቅኔ ማኅሌትም አገልግሎቶች ላይ ከትውፊቱ የወጡ፣ ከቤተክርስቲያኗ ሥርዐትና ቀኖና በእጅጉ የራቁ የበዓላት አከባበር ገጽታዎች እየታዩ መምጣታቸው ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡

በቅኔ ማኅሌት ውስጥ የከበሮ አመታት፣ የምስጋና ከማኅሌት አፈጻጸም ጀምሮ በበዓላት ዑደት በሚፈጸምበት ጊዜ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የሚለብሷው አልባሳት ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና ከሆኑት ከቀሳውስት፣ ዲያቆናት ካህናት ልብሶች ጋር የመመሳሰል ሁኔታዎች እያደጉ መጥተዋል፡፡ በዓላት ዑደታትም የምስጋና አፈጻጸም ላይ እየታዩ ያሉ አንዳንድ አዳዲስ ክስተቶች መታረም የሚገባቸው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በጥንታዊውና ታካሪዊው በአጫብር ዜማ ስም አዳዲስ እንቅስቃሴዎችም እያደጉ መጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በሥርዐተ ዑደት፣ በዓላት አከባበር ጊዜውና ሰዓቱ ባልጠበቀ ሁኔታ ጸበል መርጨት፣ በቀኖና አገልግሎቱን እንዲፈጽሙ ከተሰየሙ ቀሳውስት ውጭ ማዕጠንት ያልተፈቀደላቸው የማዕጠንት አገልግሎትን ባልተገባ ቦታና ጊዜ የመፈጸም፣ ትላልቅ በዓላት በሚፈጸሙ ጊዜ በዐውደ ምሕረቱ የመርሐ ግብር አያያዝ ላይ ብዙ አላስፈላጊ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ናቸው፡፡ እነዚህ መታረም አስፈላጊ ሆኗል፤ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ቀኖና ያላት፣ በየዘመኑም አባቶች በቅዱስ ሲኖዶስ እየወሰኑ አገልግሎት የሚፈጸምበት ሥርዐት ሲደነግጉ የቆዩ በመሆኑ፤ መታረም ስለሚገባቸው ጉዳይ ምልዓተ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቷል፡፡

ይህንንም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሊቃውንትንና ባለሙያዎችን ያካተተ ኮሚቴ በአጭር ጊዜ ተዋቅሮ አስቸኳይ ጥናት ተደርጎ ለትምህርትም፣ ለውሳኔም አመቺ በሚሆን መንገድ ለግንቦት ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ጸድቆ የሥራ መመሪያ እንዲሆን፣ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

(EOTC TV)
94🙏8👍4
ለሦስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ለማኅሌት አገልግሎት የተዘጋጀ አበባ ነው!

ተናፋቂዋ ወርኀ ጽጌን ልንጨርስ ሁለት ሳምንታት ቀርተውናል።

እናም ለቀጣዩ ለአራተኛ ሳምንት የተፈጥሮ አበባ ገዝቶ የሚሰጠን (የሚያግዘን) እንፈልጋለንና እኔ አለሁ በሉን!

@natansolo ያናግሩን
80🙏25
ተናፋቂዋ ወርኀ ጽጌን ልንጨርስ ሁለት ሳምንታት ቀርተውናል።

እናም ለቀጣዩ ለአራተኛ ሳምንት የተፈጥሮ አበባ ገዝቶ የሚሰጠን (የሚያግዘን) እንፈልጋለንና እኔ አለሁ በሉን!

@natansolo ያናግሩን
56🙏13
አንዳንድ ሰው ነሐስን ቀጥቅጦ እጅግ ውብ ቅርጽ እንዲኖረው፣ በላዩ ላይም የተለያየ ዓይነት ሐረግ በማውጣት የማሳመር ችሎታ አለው፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ጥቃቅን ዕንጨቶችን አገጣጥሞ በመሥራት ማንም ሰው ሊሰብረው የማይችል ውብ ጠረጴዛ የመሥራት ችሎታ አለው፡፡ ሦስተኛው ሰው እጅግ ውብ የኾነ ክር የመፍተል ችሎታ አለው፡፡ አራተኛው ሰው ደግሞ ይህን የመሸመን ችሎታ አለው፡፡ አምስተኛው ሰው ድንጋይ በድንጋይ ላይ በማኖር ቤት የመገንባት ችሎታ አለው፡፡ ስድስተኛው ሰው ደግሞ በተገነባው ቤት ላይ ጣሪያ የመክደን ችሎታ አለው፡፡ እዚህ ልንዘረዝራቸው የማንችላቸውና እነርሱን ለመማር ብዙ ዓመታትን የሚፈጁ ሌሎች ሙያዎችም አሉ፡፡

ባለጸጎች ሊኖራቸው የሚገባ ችሎታስ ምንድን ነው? ነሐስ መቀጥቀጥ፣ ወይም ዕንጨቶችን መገጣጠም፣ ወይም ቤቶችን መሥራት የሚችሉበት ሙያ አያስፈልጋቸውም፡፡ እነርሱ ሊማሩት የሚገባው ሙያ ሀብታቸውን እንደ ምን ሊጠቀሙበትና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችንም እንዴት ሊጠቅሙ እንደሚገባ ነው፡፡ አንድ እደ ጥበበኛ “ይህን መማር’ማ ቀላል ነው” ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከኹሉም ይልቅ እጅግ ከባዱ ሙያ ይኼ ነው፡፡ ይህን ማወቅ ከፈለጋችሁም ስንት ባለጸጎች ይህን ማድረግ እንዳቃታቸውና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመጡት እጅግ ጥቂቶች እንደ ኾኑ ተመልከቱ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች መጽሐፍ)
48👍1💯1
2025/10/26 22:08:51
Back to Top
HTML Embed Code: