"እኔ ከእርሱ [ከባልንጀራዬ] ጋር ምንም ግንኙነት የለኝምና የሚል ደካማ መልስም አትስጠኝ፡፡ ምንም ግንኙነት የሌለን ከዲያብሎስ ጋር ብቻ ነው፡፡ ከሰዎች ኹሉ ጋር ግን በጣም ብዙ የምንጋራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም አንድ ዓይነት ባሕርይ (ሰው መኾንን) አለን፤ እኛ በምንኖርባት ምድር ይኖራሉ፤ እኛ የምንበላውን ምግብ ይበላሉ፤ አንድ ጌታ አለን፤ እኛ የተቀበልነውን ሕግ ተቀብለዋል፤ እኛ ወደ ተጠራነው መንግሥትም ተጠርተዋል፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም አንበል፡፡ እንዲህ ብሎ መናገር ሰይጣናዊ ንግግር ነውና፡፡ ዲያብሎሳዊና ኢ-ሰብአዊነት ነውና፡፡ ስለዚህ ለወንድማችን ያለንን ጥንቃቄ እናሳይ እንጂ እንደዚህ ዓይነት ቃላትን አንናገር፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት፣ 1፥32)
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት፣ 1፥32)
❤126🙏13💯5🕊4
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስምህ፡-
“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መንፈሳዊ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይገባል፡፡ ዋጋው የማይታወቅ ነጋዴ ገንዘቡን ሁሉ ሰጥቶ የተወዳጀው እውነተኛ ዕንቁ ደንጊያ አንተ ነህ፡፡ ይህንን የዕንቁ ደንጊያ በሰውነታችን ውስጥ ያበራ ዘንድ ደግሞ ዛሬ ለእኛ አድርግልን፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የተቀደሰው ስምህ የልባችን ደስታ የሰውነታችን ሽልማት ጌጥ ነው፡፡ …
አቤቱ ምድርንና ዓለሙን ሁሉ ዞርሁ ያለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር ጣፋጭ ስምን አላገኘሁም፡፡ በምድር ላይ የሚደረግ ረድኤትና ኃይል ሁሉ ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር አይሆንም፡፡ እግዚአብሔርን ያገለገሉ የሰው ወገኖች ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኵል ነው፡፡ የከበረና የተመረጠውን እጅ መንሻ ሁሉ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አልተቀበልንም፡፡ ሰማይና ምድር ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሁከት አልጸኑም፡፡…
የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከማር ከወለላና ከሦከር ይጥማል፡፡ ማርና ሦከር በሚበሉበት ጊዜ ይጠገባሉ፤ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን አይጠገብም፡፡ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምጠራ ጊዜ ከንፈሮቼ ማርን ያንጠባጥባሉ፡፡ ማር፣ ስኳርና እንጀራ ቢሆኑም እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእኔ ዘንድ ጣዕም የላቸውም፡፡ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሻለኛልና ከሰማይ በታች ካለ ፍጥረት ሁሉም ይበልጣልና፡፡
ቸርነትህ ብዙ ነው፤ አይነገርምም፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በሚያምንብህና በሚወድህ አፍ ሁሉ ስምህ የታወቀ ነው፡፡ በሕግ ከታወቁ ምስጋናዎች ሁሉ ከውስጣቸው የሚመስልህ የለም፡፡ የዓይኖቼ ብርሃንና የሥጋዬ ብርታት ከከበረው ስምህ ወገን ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እስከ ሕይወቴ መጨረሻ የከበረ ስምህን በአንደበቴ ዘወትር የተሾመ አድርገው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትያን ሰውነት ሁሉ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአንድነት ያከብራሉ፤ ያመሰግናሉ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ከኃጢአት ወገን የሚሆን የክፋት መንፈስን ሁሉ ከእኔ አስወግድ፡፡ መዳኛችን በሚሆን በዚህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ክርስቲያኖች ሁላችሁም ፈጽሞ ደስ ይበላችሁ፡፡
የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጣፋጭ ነው፤ በገነት ካለ ፍሬም ይልቅ ይጣፍጣል፡፡ አባታችን ዳዊት በአመሰገነበት በከበረ መዝሙር የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ስም ፈጽሞ እናመሰግናለን፤ እናከብራለን፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ብዙ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በእኔ ላይ አሳድር፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አንተን ደስ የማያሰኝህን ሓሳብ ሁሉ ከእኔ ታርቅ ዘንድ ወዳንተ እለምናለሁ፤ ከአንተም እሻለሁ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በጌትነትህ ከእኔ ጋር ቸርነትህን አድርግ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር አባትህ ጋራ ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሰግድልሃለን፡፡ አሜን!”
(ምንጭ፡ ግብረ ሕማማት)

❤126🙏11👍5💯1🏆1
"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡
እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡
ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወደ ኦሎምፒያስ ከላከው መልእክት የተቀነጨበ

❤190😍10🙏1
እግዚአብሔር ሲቀጣን
"አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ የተላኩ መልእክቶች፥ ገጽ 36)

❤201💯24🙏11🎉1👌1🕊1
፩
ተግሣጽ ገንዘብን የመውደድ ጣጣው
..ወዳጆቼ እለምናችኋለሁ፤ ከእርሱ እረኝነት ሥር ሆነን እንሰማራ እርሱን ከታዘዝን ድምፁንም ከሰማን ሌቦችን ከመከተል ከተመለስን እንድናለን፡፡ የእርሱ ድምፅ ምንድን ነው? “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ ልበ ንጹሐን ብፁዓን ናችሁ፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው” የሚሉት ናቸው፡፡ (ማቴ 5፥3፣ ማቴ. 8፥7) እነዚህን ፈጽመን ከተገኘን ከእረኛው ጥበቃ ሥር እንሆናለን፡፡ ተኵላውም በሩን አልፎ ወደ በረቱ ዘልቆ መግባት አይቻለውም፡፡ ወይም በእኛ ላይ ቢነሣ ለገዛ ጥፋቱ ይሆንበታል፡፡
ለእኛ ራሱን እስከ መስጠት ደርሶ የወደደን እረኛ አለን፡፡ እርሱ ብርቱ ነው፤ ይወደናልም፡፡ ስለዚህ ለመዳን እንቅፋት የሚሆንብን ምን አለ? እርሱን ላለመታዘዝ ካላመፅን በቀር፡፡ በእርሱ ላይ ዓመፅን ሊባል የሚቻለው እንዴት ነው? ጌታችን ምን እንደሚል ስሙ፡- “ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም" ይለናል፡፡ (ማቴ. 6፥24) ስለዚህ እግዚአብሔርን የምናገለግል ከሆነ ለገንዘብ ባሮች ልሆን አይገባንም።
ባለጸጋ ለመሆን ከመሻት በላይ እጅግ ጽኑ የሆነ ባርነት የለም፡፡ ለገንዘብ ባሪያ መሆን ደስታን አያመጣልንም በተቃራኒው ግን ጭንቀትንና ቅንዓትን፣ ተንኮልና ጥላቻን፣ በሐሰት መካሰስን፣ እጅግ ብዙ የሆነ የጽድቅ እንቅፋቶችን፤ ስንፍንና ዋልጌነትን፣ ስስትን፣ ስካርን ያመጣብናል፡፡ ገንዘብን መውደድ ከሰው ባርነት ነጻ የሆኑትን እንኳ ባሮች ያደርጋቸዋል። ባርነቱ በገንዘብ የሚገዙትን ሰዎች ዓይነት ባርነት አይደለም፤ ከዚህ በእጅጉ የከፋ ነው፡፡
ገንዘብን መውደድ ሰዎችን ባሮች ብቻ የሚያደርጋቸው አይደለም፤ ከእርሱ ለከፋና ጨካኝ ጌታ ለሆነ ለሥጋ ፈቃድ አሳልፎ የሚሰጥና ነፍስን ለክፉ ደዌ የሚዳርጋት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ባርነት እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን ሁሉ ያጠፋሉ፡፡ ከዚህ ባርነት ካልተላቀቁ በአገዛዙ ጨካኝ ነው፡፡ ይህ ዲያብሎስ የሚሠለጥንበት አገዛዝ ነው! ከዚህ በላይ የከፋ ባርነት ከቶ የለም፡፡ በዚህ ክፉ ባርነት ደስተኞች ከሆንንና በራሳችን ላይ የባርነቱን ሰንሰለት ካጠለቅን ድቅድቅ ከሆነው የእስረኞች ወኀኒ ቤት መታሰርን መርጠናል፤ ወደ ብርሃን መውጣትን አልፈቀድንም፤ ኀጢአት በእኛ ላይ እንዲሠለጥን አድርገናል፤ በደዌአችንም ደስተኞች ሆነናል ማለት ነው፡፡
እንዲህ ከሆንን ከቶ ነጻ መውጣት አይቻለንም፤ ነገር ግን በማዕድን ቁፋሮ ያለማቋረጥ የሚደክሙና የሚለፉ ስዎች አብዝተው እንዲደክሙ፤ እኛም እንዲሁ እንደክማለን ፍሬአችን ግን ጥፋት ይሆናል፡፡ በእውነት ከዚህ የከፋ ምን አለ? ሆኖም ከዚህ ጽኑ ባርነት ነጻ እንዲያወጣን ለማንም ሰው አንፈቅድም፤ ነገር ግን እንጨነቃለን፣ ደስታን አጥተን እንቅበዘበዛለን፡፡
ይቀጥላል....
(ዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ድርሳን ስድሳ ዮሐ. 9፥39 በተረጎመበት ድርሳኑ ገጽ 84-87 - ዲያቆን ሽመልስ መርጊያ እንደተረጎመው)

❤81🙏15💯6
፪
ተግሣጽ ገንዘብን የመውደድ ጣጣው
...ባለጻጋ ለመሆን ከመሻት በላይ አእምሮን ማጣት የለም ወይም ከዚህ በላይግራ የሚያጋባ ሕይወት ከቶ የለም፤ ከዚህም በላይ ዕብደት የለም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ባርነት ራሳችንን ነጻ ለማውጣት ልንፈቅድ ይገባል፡፡
ምንድን ነው? ወደዚህ ዓለም መምጣታችሁ ለዚህ ነውን? ሰው ሆናችሁ መፈጠራችሁ ወርቅን ታከማቹ ዘንድ ነውን? ነገር ግን እናንተን በአርአያውና በአምሳሉ መፍጠሩ ይህን ትፈጽሙ ዘንድ አልነበረም፤ ይልቁኑ እርሱን ደስ ታሰኙትና የሚመጣውን ዓለም ወርሳችሁ ከመላእክት ማኅበር ትቀላቀሉ ዘንድ ነው፡፡
ስለ ምን ታዲያ ከዚህ ኅብረትና እጅግ ከሚያዋርድ ምናምንቴ ከሆነ ፍቅረ ንዋይ ራሳችሁን ማራቅ እንዴት ተሣናችሁ? መንፈሳዊውን ልደት እንደ አንተ የፈጸመ፤ በራብ ሲማቅቅ እያየኸው አንተ ጠግበህ በቊንጣ ትታመማለህ፤ ወንድምህ ተራቁቶ አንተ በልብስ ላይ ልብስን ታከማቻለህ፡፡ እንዲሞቅህም በአንዱ ላይ አንዱን ትደርባለህ፡፡ ነገር ግን የደሃውን ከልብስ የተራቆተ ሰውነት ከማልበስ በላይ ምን በጎ ነገር አለ? እንዲያ አድርጋችሁ እንደሆነ ድሆች ብልን እንዴት አድርገው አራግፈው ማስወግድ እንደሚቻሉ ያውቁበታልና የማይጠፋ ሰማያዊ ልብስ አድርገው በሰማያት ያቆዩላችኋል፤ ከጭንቅ ሁሉ ይታደጓችኋል፤ የሚመጣውን ዓለም ሕይወት እንድትወርሱ ያበቁአችኋል፡፡ ስለዚህ ልብሶችህ በብል ተበልተው እንዳይጠፉ ከፈለግህ ለድሃው ወገንህ ስጣቸው፡፡
ከምድራዊው መዝገብህ ይልቅ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እጅግ የከበረና ማንም ከማይቀርበው ብርሃን ውስጥ እንደሚኖር ልብ በል። ይህ ሰውነት ልብሶቻችን እንዳይጠፉ አድርጎ ማቆየት ብቻ አይደለም በእነርሱ ምትክ ብርሃንን እንድንጎናጸፍ ያደርገናል፡፡ ብዙን ጊዜ ከመዝገብህ ጋር ልብሶችህ በመሠረቃቸው ያልተጠበቀ ጉዳት ይደርስብሃል፤ በደኅንነት የተጠበቀው ሰማያዊ ስፍራ ግን ሞት እንኳ የሚደርስበት አይደለም፡፡ ለዚያ ሰማያዊ መዝገብ በር ወይም ቊልፍ ወይም ትጉሃን የሆኑ ጠባቂዎች አያስፈልጉትም ወይም ይህንን የመሰለ ጥበቃ አያስፈልገውም፡፡ በዚያ ሀብታችን ሁሉ ከወንበዴዎች የራቀና ከጠባቂው እግር ሥር ያለ ነው በሰማያዊው ስፍራ ያለው መዝገባችን የሚጠበቀው እንዲህ ነው፡፡

❤64🙏8
Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የእርዳታ ጥሪ
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቄት ወረዳ የሚገኘዉ ቆላ መቄት መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስር የምትገኘዉ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ማሰሪያ እርዳታ ታደርጉልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
ለመካነ ሕይወት ወይራ በር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
➛ ንግድ ባንክ - 1000701102208
➛ አቢሲኒያ ባንክ - 227712295
ለበለጠ መረጃ
➛ 0986113837
➛ 0928768186

❤39💔7
ግብዣ ከዲያቆን አቤል ካሳሁን
ስለምንወደው ሐዋርያ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ለመማማር፣ እርሱን ለመዘከር “ቅዱስ ጳውሎስ” መጽሐፉን ለመመረቅ እሑድ ጳጉሜን 02/2017 ዓም ከ7:00 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ስብከተ ወንጌል አዳራሽ እንድንገናኝ በአክብሮት ጋብዟል።
➛ መገኘት የምትችሉ በሰዓቱ ተገኙ
➛ መግቢያ: ቅዱስ ጳውሎስን መውደድ ብቻ!

❤92
፫ (የመጨረሻ)
ተግሣጽ ገንዘብን የመውደድ ጣጣው
....ይህን መዝገብ ዋጋ የሚያሳጡ ኀጢአቶች በዚያ በሰማያዊ ሥፍራ ዘንድ አይደሉም፡፡ ይህን ለእናንተ ከመናገር አልቆጠብም፤ እኛን ከመስማት ግን እንቢ ብላችኋል፡፡ ቃሉንም ከመፈጸም ተመልሳችኋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ነፍሳችሁ በምድራዊ ፈቃድ ተይዛና ከእርሱ ጋር ተጣብቃ በመገኘቷ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ ስለ ኃጢአታችሁ እናንተ ላይ ከመፍረድ ይጠብቀኝ፤ ምክንያቱም ሁላችሁም በዚህ በማይድን ሕመም ተይዛችሁ አያችኋለውና፡፡ በባለጸግነታቸው የስከሩ እነርሱ ቃሌን ለመስማት የማይፈቅዱ ናቸው፡፡ በድህነት የሚኖሩት ግን እኔ የማስተማራቸውን ማስተዋል ይቻላቸዋል፡፡
አንዱ “ይህን እንዴት በድሆች ሊፈጽሙት ይቻላቸዋል? ወርቅ የላቸውም፤ የሚሰጡት ልብስ እንኳ የላቸውምና?'' ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ድሆች ይህ ምድራዊው ሀብት ላይኖራቸው ይችላል፤ ነገር ግን ቊራሽ እንጀራና ቀዝቃዛ ውኃ አይጠፋቸውም፤ ሕመምተኞችን ለመጠየቅ ለምነው ሁለት ዲናር ቢያገኙ አንዱን ሊሰጡ ይችላሉ፤ ሕመምተኛው ጋር ሄደው ለማጽናናት ሁለት እግር አላቸው፤ በሕመም አልጋ ላይ የወደቀውን ለማጽናናት አንደበት አላቸው፤ ባለጠጎቹ ግን እንግዶችን ለመቀበል ቤት አላቸው፤ ከደሃው ይህንና ይህን የመሰሉ ነገሮችን እንዲሁም ብዙ ሺህ ታለንት ወርቅ አንጠብቅም፤ እነዚህን ከባለጠጋው እንጠብቃለን እንጂ፡፡
ነገር ግን አንድ ሰው ደሃ ሆኖ ከሌላው ሰው ደጅ ቢጠናና በልመና ያገኘውን መልሶ ምጽዋት አድርጎ ቢሰጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን አልቀበልህም አይለውም፡፡ ብዙ ካላቸው ጥቂቱን ከሰጡት ይልቅ ይህ ሰው በምጽዋት ያገኘውን በመስጠቱ የበለጠ ዋጋ ያገኛል፡፡
ከዚህ ካለነው ጌታችን በሥጋ በተመላለሰባቸው ወራት ተወልደን ከእርሱ ጋር ተነጋግረንና ማዕድ ተካፍለን ብንሆን ኖሮ ብለው የሚመኙ ብዙዎች አይደሉምን? ይህን ግን እነሆ አሁንም ልንፈጽመው ይቻለናል፡፡ እኛ ከእርሱ ጋር በማዕድ ከመካፈልና ግብዣን ከማድረግ ባለፈ ወደ እኛ እንዲመጣ በመጋበዝ ታላቅ የሆነ በረከትን ልንቀበል እንችላለን፡፡
ከጌታችን ጋር በማዕድ የተካፈሉ ይሁዳና እርሱን የመሰሉ ብዙዎች ጠፍተዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ከእነዚህ (በጌታ ጊዜ ተወልደን ቢሆን ኖሮ ከሚሉት) አንዱ እርሱን በቤቱ ቢቀበለው፣ ከማዕዱ ቢያካፍለውና ከጣራውም በታች ቢያሳድረው ታላቅ በረከትን ያገኛል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰውን ጌታችን፡-“እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና" ይለዋል። (ማቴ 25፥34)
ይህን ቃል ሰምተን ወደ መንግሥቱ ለመግባትና የኀጢአት ሥርየትን ለማግኘት እንዲሁም ከምናስበውና ከቃላት በላይ ከሆነ በረከቶቹ ተካፋይ እንድንሆን ከልብስ የተራቆቱትን ድሆችን እናልብስ፣ እንግዶችን እንቀበል፣ የተራበውን እናብላ፣ የተጠማውን እናጠጣ፣ ሕመምተኞችን እንጠይቅ፣ በእስር ያሉትን እንጎብኛቸው፡፡ እነዚህን ፈጽመን ከተገኘን የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን የበቃን እንሆናለን፡፡

❤69🙏13👍2
#የምንለወጠው_ምን_ስናደርግ_ነው?
በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደ በረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰ'ሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም !
“እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ ፈጽመው ሊወገዱ እንደ ማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡
በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡
እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ አምስቱ የንስሐ መንገዶች - ገጽ 69-70 )

❤134🙏20💯2🏆2🕊1
አንቺ ሴት ሆይ! በምንዝር ጌጥ እንግዶችን ደስ ማሰኘትና በእነርሱ ዘንድ መመስገንን ትፈልጊያለሽን? ይህ በእርግጥ ጭምት የሆነች ሴት ጠባይ አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ እኔ እንዳስተማርኩሽ በማድረግ እንግዶቹ አብዝተው እንዲወዱሽ ማድረግ ትችያለሽ፡፡
በጭምትነትሽም ያመሰግኑሻል፡፡ ሰውነቷን በውጫዊ ጌጦች የምታስጌጥ ሴት ጥሩ ሥነ ምግባር ባለውና በጻድቅ ሰው ዘንድ የምትወደድ አይደለችም፡፡ በሴሰኛና አመንዝራ ሰው ዘንድ ግን ልትፈቀር ትችላለች፡፡ ይህም መወደድ በንጽሕና የቀረበ መውደድ ሳይሆን በእርሷ ምክንያት በዝሙት ጦር በመነደፉ የመጣ ነው፡፡ ራሷን በመልካም ሥነ ምግባር ያስጌጠች ከሆነች ግን በአንድም ሆነ በሌላ ለእርሷ የሚቀርበው ምስጋና የሚያስነቅፋት አይሆንም፡፡ እርሷን በማመስገናቸው አይጎዱም ምክንያቱም ሰማያዊ ጥበብን ከእርሷ ተምረዋልና፡፡ እንደዚህች ያለች ሴት በሰዎች ዘንድ የከበረች ናት! በእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ዋጋን ይጠብቃታል፡፡
ስለዚህ ያለ ፍርሀት ለመኖርና ከማያልፈው ዓለም በረከት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ርኅራኄ ተካፋይ ለመሆን እንድንበቃ ራሳችንን እንዲህ እናስጊጥ፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ዮሐንስ ወንጌልን በተረጎመበት ድርሳኑ ቅጽ 2 ገጽ 118 - በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤173🙏22👌1
ተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ከማሳዘን ውጪ ምንም ይኹን ምን [አንፍራ፡፡] ሠለስቱ ደቂቅ የሚንበለበል እሳት በፊታቸው ቢያዩም ናቁት፤ ኃጢአትንም ብቻ ፈሩ፡፡ በእሳቱ ቢቃጠሉ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር እንደሌለ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባይገኝባቸው ግን እጅግ የከፋ ጉስቁልና እንደሚያገኛቸው ያውቃሉና፡፡ ምንም ሳንቀጣ ብንቀርም እንኳን እጅግ ትልቁ ቅጣት ግን ኃጢአት መሥራት ነው፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም ያህል ቅጣት ቢያገኘንም እጅግ ትልቁ ክብርና ጸጥታ ግን በተጋድሎና በምግባር ሕይወት መኖር ነው፡፡
እግዚአብሔር ራሱ፡- “በደላችሁ በእናንተና በእኔ መካከል አልለየችምን?” ብሎ እንደ ተናገረ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል (ኢሳ.59፡2)፡፡ ቅጣት ግን “እግዚኦ አምላክነ ሰላመ ሀበነ እስመ ኵሎ ወሀብከነ - አቤቱ አምላካችን ኹሉን ሰጥተኸናልና ሰላምን ስጠን” እንደ ተባለ ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል (ኢሳ.26፡12)፡፡
እንበልና አንድ ሰው ቁስል ወጣበት፡፡ የሚያስፈራው የትኛው ነው - የሚሰፋው ቁስል ወይስ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ቢላ? ብረቱ ወይስ እጅግ እየባሰበት ያለው ቁስል? ኃጢአት የሚሰፋ ቁስል (Gangrene) ነው፤ ቅጣት ደግሞ የቀዶ ጥገናው ሐኪም ቢላ ነው፡፡ ያልፈረጠ የሚሰፋ ቁስል ያለው ሰው ሕመሙ እንዳለበትና ለወደፊቱም የማያፈርጠው ከኾነ ሥቃዩ እየባሰበት እንደሚኼድ ኹሉ፥ ቅጣት ያላገኘው ኃጢአተኛ ሰውም ከሰዎች ኹሉ ይልቅ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፤ ለወደፊቱ ጭራሽ ቅጣትና መከራ የማያገኘው ከኾነ ደግሞ ከአሁኑ ይልቅ እጅግ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፡፡ የጣፊያ ወይም የሆድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ መብል ቢበሉ፣ ቀዝቃዛ መጠጦችን ቢጠጡ፣ የተለያዩ ዓይነት ጣፋጭና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው መብሎችንም ቢወስዱ ይህ ድሎት ሕመማቸው እንደሚጨምረውና እንደ ሕክምናው ሕግ ራሳቸውን ከመብሉም ከመጠጡም በመጠኑ ቢወስዱ ግን የመዳን ተስፋ ሊኖራቸው እንደሚችል ኹሉ፥ በክፋት ዓዘቅት የሚኖሩ ሰዎችም ቅጣት ካገኛቸው በጎ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከክፋታቸው ጋር አብረው ዝንጋዔንና ድሎትን የሚጨምሩበት ከኾነ ግን ሆዳቸውን ከሚያማቸው ሰዎች በላይ እጅግ ጐስቋሎች ሰዎች ናቸው - ደዌ ዘነፍስ ከደዌ ዘሥጋ ይልቅ የከፋ ነውና፡፡
ተመሳሳይ ኃጢአት እያላቸው አንዳንዶቹ በማጣትና በብዙ ሕመም ሲሠቃዩ፣ ሌሎቹ ግን እስኪበቃቸው ድረስ እየጠጡና እየተስገበገቡ የሚበሉ እየተመቻቸውም በደስታ የሚኖሩ ሰዎችን ብትመለከት እነዚያ መከራ የሚቀበሉት የተሻሉ እንደ ኾኑ አስተውል፡፡ በእነዚህ መከራዎች የተወገደላቸው የፈንጠዝያ ሕይወት እሳት ብቻ ሳይኾን ሊመጣ ወዳለው ፍርድና አስፈሪ ዙፋን ሲኼዱም ከቀላል ዕረፍት ጋር አይደለምና፤ ስለኾነም እዚያ ሲኼዱ ከኃጢአታቸው የሚበዛውን በዚህ ዓለም ባገኛቸው ሥቃይ አስወግደው ነው፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 34-35)

❤79🙏7👍2
እንደ ሞተ ሰው ሁን
ከወንድሞች አንዱ ወደ አባ መቃርዮስ መጥቶ "እባክህ ለሕይወቴ የሚሆን መመርያ ስጠኝ" አለው። አባ መቃርዮስም ያንን ወንድም "ወደ መቃብር ሒድና በሙታን ላይ ክፉ ነገር አድርግባቸው" ብሎ ላከው። ሰውየውም በሙታን ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመሳደብ የተላከውን ፈጽሞ መጣ። አባ መቃርዮስም "ምን አሉህ?" ሲል ጠየቀው። ያም ወንድም "ምንም አላሉኝም" ብሎ መለሰ። "በነጋታው ተመልሰህ ናና አመስግናቸው" አለው። በነጋታው ያ ወንድም ወደ መቃብሩ ሥፍራ ተጉዞ ሙታኑን "ሐዋርያት ፣ ቅዱሳን ፣ ጻድቃን" እያለ አመሰገናቸውና ተመለሰ። መቃርዮስም "ምን መለሱልህ?" አለው። "ምንም" አለ። መቃርዮስም "ስትሰድባቸውና በድንጋይ ስትመታቸው ፣ ስታመሰግናቸውና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድኅነትን ከፈለግክ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አለው። (በበረሓው ጉያ ውስጥ ገጽ 38)
ወዳጄ ሆይ! የታላቁን አባት ምክር ልብ አልክን? የሚሰድቡህንና ድንጋይ የሚወረውሩብህን እንዴት ማለፍ እንደሚገባህ ተማርክን? የሚያመሰግኑህንና የሚያወድሱህን እንዴት መቀበል እንዳለብህ አስተዋልክን?
መቼስ በምድር ላይ ስትሆን ቀልብህን የሚቀሙህ ብዙ ሰዳቢዎች አሉብህ፤ የሚያስጎነብሱህም ብዙ ድንጋይ ወርዋሪዎችም አሉብህ፡፡ አንዱ ድህነትህን እያነሣ ያሸማቅቅኻል፤ ሀብት የሌለህና ገንዘብ መቁጠር ያልቻልከው የማትረባ ስለሆንክ ብቻ እንደኾነ በማሳሰብ ያሣንስሃል፤ አንዱ ደግሞ በምግባርህ የሞትህ እንደሆንክ እየጮኸ ይነግርሃል፡፡ ሃይማኖትህና ኢትዮጵያዊነትህ ለድህነትህ አስተዋጽዖ እንዳደረገና ማንነትህ ራሱ የተዋረደ እንደሆነ በመንገር ተፈጥሮህን ንቀህ 'አርተፊሻል' እንድትሆን ፣ 'ኦሪጅናልነትህን' አርክሰህ 'ፌክ' እንድትሆን ይሰብክሃል፡፡ አለኝ የምትለውን ጸጋ በማንሣትም ባዕለ ጸጋ መሆንህን እስክታማርር ድረስ የሚያንቋሽሹህንስ አስታወስክ? ያለህን ጸጋ በመያዝህ የሚሰድቡህ ጸጋና ሀብት ማለት በእነርሱ ሚዛን ላይ የሚቀመጥ ብቻ እንደሆነ በመንገር አዕምሮህን የሚያሳምሙህ ትዝ አሉህ? ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ልምከርህ… ሃይማኖትህ እና ኢትዮጵያዊነትህ ላይ እንድታምጽ ለሚገፋፉህ ለቁስ አካላውያን ዘለፋ እንደሞተ ሰው ሁን!
በዘር ገመድ ተብትበው ከወንድምህ ጋር የሚያናቁሩህ፣ ሃይማኖትና ሰብአዊነትን ሳይቀር በዘረኝነት ሰፌድ የሚያበጥሩ ድንጋይ ወርዋሪዎችን እንዴት ይሆ ያለፍካቸው? ማበጠሪያቸው አንጓሎህ ወሬያቸው በአእምሮህ ላይ ቤት ሠራ? ወይስ እንደ ሞተ ሰው ንቀህ ዝም ብለሃቸው በማንነትህ ዓለም ውስጥ ሥራህን አበረታህ? 'ይሄ ነገር እኮ እውነት ሳይሆን አይቀርም' ብለህ ፣ የእነርሱንም ሰፌድ ተውሰህ ወንድሞችህንና እኅቶችህን አበጠርክ? ወይስ ለእነርሱ አሉባልታ ራስህን ገድለህ በብልኃት መነንክ? ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ልንገርህ… ለዘረኞች ድንጋይ እንደሞተ ሰው ሁን!
ያለህበት ሕይወት ሞኝነት እንደሆነ የሚነግሩህስ ትዝ ብለውህ ይሆን? ጾምህን የሚያንቋሽሹ ፣ ሱባኤህን የሚረብሹ ፣ ጸበል መጠጣትህን የሚነቅፉ ፣ እምነት መቀባትህን የሚያንሻፍፉ ፣ እግዚአብሔር በሞተ ነገር ላይ ታሪክ እንደሚሠራ ስትነግራቸው የሚስቁ ፣ በሰማይ ሕይወት አለ ስትላቸው በሙት አእምሮአቸው የሚሳለቁ ፣ 'ይልቅ ዓለምህን ቅጭ… ጊዜህን ተጠቀምበት' የሚሉህ ዓለማውያንና እውቀታውያን ማንነትህን ለማርከስ ማንነታቸውን ለማንገሥ የሚወረውሩት ጥቁር ድንጋይ አቁስሎህ ይሆን? ወዳጄ ሆይ ታላቁ አባት እንዲህ ይልሃል… ለሥጋውያንና ለስሌታውያን እንደሞተ ሰው ሁን!
ሥራህን እንዳትሠራ… ያመንክበትን እንዳትናገር በፖለቲካ መረብ የሚያጠምዱህስ ደግሞ…. አገልግሎትህን እየፈጸምክ፣ ዕቅበተ እምነትን እየከወንክ ድንገት የፓርቲ አባል ሲያደርጉህ? ሰማያዊ የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራህን ድንገት ባላሰብከው ሁኔታ ሽብር ሲያደርጉብህ? ለማታውቃቸው ለነ እገሌ አጋር ሲያደርጉህ… ብቻ እነዚህም ሥጋህን እንጂ ነፍስህን መግደል አይችሉምና እንደሞተ ሰው ዝም ብለሃቸው ከንቱ ዘለፋቸውን ናቀው!
ደግሞስ ገና ብዙ ልትሠራ የምትችለውን ገና በልዑልነትህ ንጉሥ ብለውህ ፣ ገና በወጣኒነትህ ጻድቅ አድርገውህ ፣ ገና በተማሪነትህ ረቡኒ ብለውህ ፣ ዳዴህን ሳትጨርስ የአትሌትነት ማዕረግን ሰጥተውህ ፣ ልብስ ቀደህ እንኳን የማትሰፋውን ቀዶ ጠጋኝ ሐኪም አድርገውህ ፣ በዲያቢሎስ መዝሙር…
'ከፍ ከፍ በጣሙን ከፍ ከፍ
ኋላ ስትወድቅ አጥንትህ እንዳይተርፍ'
ዘይቤ የሚጨቁኑህን፤ ሰቅለውህ በአፍጢምህ የሚደፉህን አድርባዮችና ሕሊና ቢሶች እንዴት አልፈሃቸው ይሆን? ለእነርሱ ወሬ መንኩሰህ እንደሞተ ሰው ተቀበርክን?
ወዳጄ ሆይ! እንደሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ትዳር አለህ፤ እንደሞተ ሰው ሆነህ የማትገድለው ሕይወት አለህ ፣ እንደሞተ ሰው ሆነህ የምታጠነክረው ወዳጅነት አለህ፤ እንደሞተ ሰው ሆነህ የምትሠራው እልፍ ሥራ አለህ … ስለዚህ ወፎቹ በሰማይ ይብረሩ አንተም ሥራህን ቀጥል፤ አናትህ ላይ ጎጆ እንዳይሠሩብህ ወፎቹን ከልክል… አንተ ሰው ነህ እንጂ ዛፍ አይደለህምና!
ወዳጄ ሆይ ግን ልብ በል!
እንደ ሞተ ሰው ሁን እንጂ ሙት ሁን አልተባልክም፤ እንደሞተ ሰው ሆነህ በግብርህ ሕያው ሁን እንጂ ሙት አትሁን፡፡
በዚህች የቅዠት ዓለም በቁሙ የሞተ ሰው በወሬ ሕያው ነው፤ በቁሙ ሕያው የሆነ ግን በወሬ እንደ ሞተ ሰው ነው፡፡
ሐዋርያው እንዳለው አንተም ለዚህች ዓለም ሙትባት… ይህች ዓለምም በአንተ ዘንድ የሞተች ትሁን፡፡
እንደሞተ ሰው ሁን!!!
(ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን)

❤132👌5💯4🙏3🏆3😍2🕊1
ሰላም ተወዳጆች ለአንዲት በጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለምትገኝ ዝርጋ ማርያም እየተባለች ለምትጠራ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድስት (መጻሕፍት፣ ልብሰ ተክህኖ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ ጧፍ፣ ሻማ....) ያስፈልጋልና ወደጆቼ አለን በሉኝ።
@natansolo
@natansolo
❤80🙏8👍1
#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?
#ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡
#ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡
#ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

❤104🙏15🏆1
ሰላም ተወዳጆች፣
በቻናላችን በቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "አዲሱ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" የሚለውን እጅግ መሳጭ የሆነውን የቅዱሱን ትምህርቶች ከነገ ጀምሮ በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል።
ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ቻናላችንን እናስተዋወቅ እንጋበዝ፣ እናጋራ...
https://www.tg-me.com/beteafework

❤41