Telegram Web Link
48🙏7🕊4💯3
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo
66🙏16👍5😍4👌2💯1
“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ 65፥11

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ኃጥአታችን ያይደለ እንደቸርነቱ የንስሃ ጊዜ የፍሬ ጊዜ ሰጥቶናልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል፡፡ ምስጋናችንም ይህን የተወዳጅ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመተግበር እንግለፅ፡፡

“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22

መልካም አዲስ አመት!
95🙏14🏆1
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo
40🙏3👍1💯1🏆1
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?”

ተወዳጆች ሆይ! አዲስ ዓመት ሲመጣ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ልናስብባቸው ይገባናል፡፡ ይህን እያደረግንም ስለ ቀጣዩ ዓመት እናስብ፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ “ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፤ ዓመቶቻቸውም በችኰላ” አይባልብንም (መዝ.78፡3)፡፡ ዕለት ዕለት በዓልን እናድርግ ብዬ የገለጥኩላችሁም ይኸው ነው፡፡ የእኛ በዓል ዘወትር መኾን ይገባዋል፡፡ የክርስቲያኖች በዓል በዓመታትና በቀናት ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በሳምንት፣ በወር፣ በዓመት የሚከበሩ በዓላት እንዲኖሩ ማድረጓ ዘወትር ከዚሁ ልንርቅ እንደማይገባ ማሳሰቧ እንጂ ሌላ አይደለምና፡፡ ይህን በዓል በየዕለቱ ማድረግም ለኹሉም ይቻላል፤ ለድኻውም ለባለጸጋውም ይቻላል፡፡ በዓልን ለማድረግ (የጽድቅ ሥራን ሠርቶ ሐሴት ለማድረግ) የሚያስፈልገው ቅን ልቡና እንጂ ገንዘብ አይደለምና፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰማዕትነት አያምለጣችሁ ገጽ 13-19 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው)
82🙏14💯4
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እኅቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡

እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንኾናለን፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ- የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች ገጽ 27)
70🙏9
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ!

ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም።

ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም 11/2018 ዓ.ም በማረሚያ ቤት (በእስር) ከሚገኙ ወገኖች ጋር አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በጉባኤ እናከብራለን። በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ይዘን እንሄዳለንና እርስዎ ለጌታ ጥያቄ መልስ የሚሆንዎት ተግባር ላይ ከአንድ ሰው ጀምረው እስከፈቀዱ መጽሐፍ ቅዱስን ማበርከት ይችላሉ። እስከ ሰማኒያ ሰው ለመስጠት አስበናል የአንዱ ዋጋ 900 ብር ነው። ዓመቱን በዚህ የተቀደሰ ተግባር ይጀምሩና ነፍስዎን ያስባርኩ።

ይህን ስጦታ ልዩ የሚያደርገው ለማያውቁት ሰው ከእግዚአብሔር ብቻ የሚጠብቁትን በረከት ለመቀበል የሚደረግ ፍጹም ስጦታ በመሆኑና የሚሰጡት የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመሆኑ ነው።

ለዚህ በረከት ተሻሙ!
የንስሐ ዘመን ይሁንልን!

@natansolo

እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 10 የቻናላችን ቤተሰቦች 20,900 ብር አግኝተናል።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ23 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 57 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።

በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
34🙏11👍1
"እናንተ ደካሞች…"

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-“እናንተ ኃጢአት ሸክም የሆነችባችሁ፣ እናንተ ጭንቀት አላኖር አላስቀምጥ ያላችሁ፣ እናንተ ሐዘን የደቆሳችሁ፣ እናንተ ትእዛዛቴን በመተላለፍ ቅስማችሁን የተሰበራችሁ፣ እናንተ በሐፍረት ካባ ተከናንባችሁ የምትቆዝሙ፣ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ አበቃልኝ በቃኝ ብላችሁ ያንገሸገሻችሁ፣ እናንተ ለመናገር እንኳን ድፍረት ያጣችሁ… ምንም እንኳን ዝሙት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን ዋሽታችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን ሰርቃችሁ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን መናገር የማትችሉት ከባድ የምትሉት ኃጢአት ብትሠሩም፣ ምንም እንኳን “ከእንግዲህ ወዲህ በቃ እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም” ብትሉም የእኔ ፍቅር የእኔ ቸርነት ይህን ሁሉ ኃጢአታችሁን፣ ይህን ሁሉ ሸክማችሁን፣ ይህን ሁሉ ሐዘናችሁን፣ ይህን ሁሉ ከባድ የምትሉትን ነገራችሁን መደምሰስ የሚችል ነውና ኑ፡፡

ኑና ላሳርፋችሁ፤ ኑና ስለ እናንተ የቆሰለውን እጄ ተደገፉ፤ ኑና ፍቅሬን ቅመሱ፤ ኑና ቸርነቴን አጣጥሙ፤ ኑና ሸክማችሁን ሁሉ በእኔ ላይ አራግፉ፡፡ ብቻ እናንተ ፈቅዳችሁ ኑ እንጂ ከእኔ አቅም በላይ የሆነ ሸክም የለባችሁምና አትስጉ፡፡

ኑና ሥርየተ ኃጢአትን ልስጣችሁ፤ ኑና ዕረፍተ ነፍስን ሰጥቼ ላሳርፋችሁ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንኳ እንደ አመዳይ አነጻላችኋለሁ፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ አጠራላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ ኃጢአታችሁን እየቆጠራችሁ ከምትቆዝሙ ቀና በሉና ወደ እኔ ኑ፡፡ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ልጆቼ ወደ እኔ ቅረቡ፡፡ እኔም ልቅረባችሁ፡፡ “ቀንበሬን ተሸከሙ” ስላችሁ በሩቁ አትፍሩኝ፡፡ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፡፡ ደግሞም ይህ ቀንበር አንገታችሁን ለማለዘብ (ለመላጥ) ሳይሆን በቀጭኒቱ መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትሉ እኔ ወዳዘጋጀሁላችሁ ርስት መንግሥት የምታደርስ ናትና በሩቁ አትፍሯት፡፡

ስለዚህ እናንተ ደካሞች፣ እናንተ ዓቅመ ቢሶች፣ እናንተ ከእኔ ውጪ ምንም ማድረግ የማትችሉ በገዛ ደሜም የገዛኋችሁ ልጆቼ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ማዳን ብቻ ሳይሆን አሳርፋችኋለሁ፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
116🙏23👍1🏆1
አሮጌውን ሰው አስወግዱ

“ከእንግዲኽ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥራ ይሽር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋል" /ሮሜ.6፥6/ የሚለውን የሐዋርያው ቃል ሳስብና የእኛን ሕይወት ስመለከተው ምን ያኽልም ከዚያ እንደራቅን ሳስብ ውስጤ ይቃትታል፡፡ ዐይኔ በእንባ ይመላል፡፡ ምንም እንኳን በጥምቀት አዲሱን ሰብእናችን ብንለብሰውም እኛ ግን ወደ ቀደመ አሮጌ ሰብእናችን ወደ አሕዛባዊውም ኑሮ ተመልሰናልና፡፡ አማናዊውን መና ትተን በግብጽ እንበላው የነበረውን ዓሣ፣ ዱባና ሽንኩርት እናስባለንና /ዘኁ.11፥5/፡፡ አንድ ሳምንት እንኳን ሳይሞላን በየጊዜው ጥለነው ወደመጣን ትፋታችን እንመለሳለንና፡፡ በአዲሱ ሰዋችን ላይ የኃጢአት ሕንፃ እየገነባን እመለከታለሁና አለቅሳለሁ፡፡ የዘፈን፣ የስካር፣ ጣዖትን የመውደድ ሕንፃ በመገንባት አዲሱን ሰዋችን እያበላሸነው ነውና አነባለሁ፡፡ አሮጌውና ውራጁ ሊጠፋ ሲገባው በየጊዜው ስናድሰው እየተመለከትኩ አለቅሳለሁ፡፡

ፍቁራን ሆይ! ሽማግሌዎችን አይታችኋልን? አዎ! ሽማግሌ ቆዳው የተሸበሸበ ነው፤ ድምጹ ይቆራረጣል፤ መጋጥሞቹ በሪህና በቁርጥማት የሚሰቃዩ ናቸው፤ ብዙውን ጊዜ የሚናገረውን ስለማያውቅ ይዘባርቃል፤ ይረሳል፤ ዓይኑ በሞራ የተጋረደ ነው፤ ደም ግባት የለውም፤ ጉልበቱ የተዳከመ ነው፡፡ የአሮጌ ሰው ነፍስም እንዲኽ የተጐሳቆለች ናት፡፡ የአዲሱ ሰው ነፍስ ግን ወጣትን ትመስላለች፡፡ ወጣት ደም ግባት አለው፤ ርሷም ውብ ነች፡፡ ወጣት ኹል ጊዜ ዝግጁ ነው፤ ርሷም የሚመጣባትን ፈተና ለመዋጋት ዘወትር ዝግጁ ናት፡፡

የአሮጌው ሰው ነፍስ እንዲኽ ዓቅም ስለሌላት በቀላሉ ትወድቃለች፡፡ መዝሙረኛው “ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ" እንዳለ የአሮጌ ሰው ነፍስ ኃጢአት እንዳሻው ወደ ፊትና ወደ ኋላ ስለሚያወዛውዛት ኹል ጊዜ ለአደጋ የተጋለጠች ናት /መዝ.1፥4/፡፡

በዕድሜ የሸመገሉ ሰዎች አስቀድመን ከተናገርነው በተጫማሪ ብዙውን ጊዜ ጤና ስለሌላቸው ያስላቸዋል፤ ዓቅም ስሌላቸው አክታቸውን እንኳን መትፋት ይሳናቸዋል፤ በብዙ ጥረትም በእጃቸው ይጠርጉታል፡፡ ያነጫንጫቸዋል፤ ትንሽ ነገር ያበሳጫቸዋል፤ ትንፋሽ ያጥራቸዋል፡፡ ከእኛ መካከል ምናልባት እንዲኽ በጠና የታመመ ሰው ካለ እነዚኽን ምልክቶች በቀላሉ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚኽ ኹሉ በሥጋ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ወዮ! ወዮ! የአሮጌው ሰው ነፍስ እንደምን ከዚኽ የባሰች ትኾን?

በሉቃስ ወንጌል ላይ የምናገኘው የጠፋው ልጅ እንዲኽ ኾኖ ታሞ የገረጣ የከሳ ልጅ ነበር፡፡ ሲወስንና ሲጸጸት ግን ወድያው እንደ ቀድሞ ወጣት ኾነ፡፡ “ተነሥቼም ወደ አባቴ እሔዳለሁ” ባለ ጊዜ አሮጌው ሰውነቱ እየከሰመለት... እየጠፋለት... አዲሱ ሰውነቱ ደግሞ እየፋፋለት... መጣ /ሉቃ.15፥17/፡፡ በሐሳቡና በቃሉ ላይ ተግባር እየጨመረበት ሲመጣ ደግሞ የበለጠ እየወፈረ... እያገገመ… መጣ፡፡ “ተነሥቼ ወደ አባቴ እሔዳለሁ፡፡ አባቴ አንተንም ፈጣሪዬንም በደልኩ፡፡ ከእንግዲኽ ወዲኽ ልጅህ ልባል አይገባኝም፡፡ ከባሮችህ እንደ አንዱ ቁጥረኝ እንጂ እለዋለኁ" ብሎ እዚያ የቆየ አይደለም፤ ፈጥኖ ድሮ የሔደበትን መንገድ እየተወ ወደ ቤቱ ተመለሰ እንጂ፡፡
ይቀጥላል....

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች ገጽ 66-69 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)
79🙏12🕊7
ሁለቱን ሐሳቦች ተረዷቸውና ተጠንቀቋቸው አንደኛው "አንተ ቅዱስ ነህ" የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "መቼም ቢሆን ልትድን አትችልም" የሚለው ነው፡፡

ሁለቱም ሐሳቦች ከጠላት ናቸው፤ በትዕቢትና ተስፋ በመቁረጥ የተሞሉ እውነት የሌላቸው ናቸው፡፡

አንተ ግን ለራስህ ይህን በለው "እኔ ታላቅ ኃጢአተኛ ነኝ ስራዬ በፊቴ ነው ግን አምላክ መሐሪ ነው! ሰዎችንም በጣም ይወዳል፤ ስለዚህ ኃጢአቴን ይቅር ይለኛል፡፡"

አባ ስልዋኖስ ዘአምድ
89🙏22🕊3👍1

አሮጌውን ሰው አስወግዱ


ተወዳጆች ሆይ! ከአባታችን ቤት ብዙ ርቀን በአሕዛብ ሀገር ገብተን ቢኾንም ፀሐይዋ ገና አልጠለቀችምና አኹንኑ ወስነን እንመለስ፡፡ የመንገዱን ርዝማኔ እየታሰበን በዚያ የምንዘገይ አንኹን፡፡ እኛ ፈቃደኞች ከኾንን የሔድንበት መንገድ ለመመለስ ከቀድሞ ይልቅ ቀላል ደግሞ የፈጠነ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የሔድንበትን የእንግድነት ሀገር ወስኖ መልቀቅ ብቻ ነው፡፡ ስለዚኸ ከሔድንበት የኃጢአት ሀገር ተመልሰን ከአባታችን ከጽድቅ ቤት እንግባ፡፡ አባታችን እኛን ለመቀበል ፍሪዳውን አርዶ (ቅዱስ ሥጋዉን ክቡር ደሙን አዘጋጅቶ) ቤቱንም አሰናድቶ እየጠበቀን ነውና ከዚያ የኃጢአት ሀገር ፈጥነን እንውጣ፡፡ ጤናን ከማጣት የተነሣ የገረጣውን ሰውነታችን በእንግድነት ሀገር ሳይሞት ፈጥነን እንመለሰው፡፡

ተወዳጆች ሆይ! ሓኪሞች አንድ የታመመን ሰው “ከአልጋህ ተነሥና ተመላለስ" ሲሉት መዠመርያ እንደሚፈራ ወደ አባታችን ቤት መመለሱን የምንፈራ አንኹን፡፡ ይኸ ከአልጋ የሚነሣ ታማሚ የሚያበረታቱት ሐኪሞችና ቤተሰቦች በዙርያው እንዳሉ ኹሉ ከእኛ ጋርም መንፈስ ቅዱስና እልፍ አእላፍ ወትእልፊት ቅዱሳን መላእክት አሉ፡፡ ታማሚው አንዴ ከተነሣ በኋላ ዓቅምና ብርታት እያገኘ እንደሚሔድ ኹሉ እኛም አንድ ቀንና ኹለት ቀን መመለስን ስንዠምር በሦስተኛው ቀን የበለጠ እየበረታንና እየፈጠንን እንሔዳለን፡፡ የበለጠ በመጣን ቁጥር የአባታችንን ቤት አሻግረን እናያታለን፤ ጉልበትም እናገኛለን፡፡ የተዘጋጀልንን ድግስ በሩቅ ስናይም የበለጠ ብርታት እየተሰማን እንመጣለን፡፡

የጠፋው ልጅ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ስላባከነው ገንዘብ አባቱ አንዳች ስንኳ የጠየቀው አይደለም፡፡ አንዲት የወቀሳ ቃል ስንኳ አልሰነዘረበትም፡፡ ፊቱን አላጠቆረበትም፡፡ ከዚያ ይልቅ አዘነለት፤ ፈጥኖም አንገቱን አቅፎ ሳመው እንጂ፡፡ ባሮቹን ፈጥነው ያማረውን ልብስ እንዲያለብሱት፣ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ እንዲያስገቡለት አዘዛቸው እንጂ፡፡ ማለፊያውን ፍሪዳ አምጥተው እንዲያርዱለት አዘዛቸው እንጂ። ፍቁራን ሆይ! አባታችንም እንዲኽ አዘጋጅቶ እየጠበቀን ነውና እንመለስ፡፡ በእንግድነት ሀገር ስለምን እየተራብን እንቆያለን? አባታችን እኮ ለገዛ ልጁ ስንኳ ያልራራለት ይልቁንም ስለኹላችን ቤዛነት ለሕማም ለሞት አሳልፎ የሰጠው አፍቃሪያችን ነው /ሮሜ.8፥32/! እንዲኽ አሮጌው ሰብእናችንን አውልቀን ስንመለስ'ማ አባታችን እንዴት በእጅጉ አይደሰት?! እንኳንስ ርሱ የሰማይ መላእክትም በእኛ መመለስ ምክንያት ሐሴት ያደርጋሉ፡፡

ስለዚኽ እንምጣና የተጨማደደውን አሮጌ ሰውነታችንን እናድሰው፡፡ እንምጣና በበሽታ የተጠቃው አሮጌ ሰውነታችንን አውልቀን በሽታን የመቋቋም ዓቅም ያለው አዲሱን ሰውነታችን እንልበስ፡፡ እንምጣና ለይስሙላ ሳይኾን ለእውነት በሚኾኑ የጽድቅና የቅድስና ልብስ እናጊጥ፡፡ እንምጣና አክሊልን እንደለበሰ ሙሽራ በጌጥ ሽልማትም እንዳጌጠች ሙሽሪት የመዳንን ልብስ እንልበስ /ኢሳ.61፥10/፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች ገጽ 66-69 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)
76🙏15👍2👌1🏆1
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚ እስረኞች እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ! ጌታችን ዳግመኛ በመጣ ጊዜ በቀኝና በግራ ለሚያቆማቸው ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ ታስሬ ጠይቃችኹኛል?” ማቴዎስ 25፥36 የሚል ነው። መቼም ጌታ ለታሰሩት የምናደርገውን ለእርሱ እንደሆነ ቆጥሮ እንጂ በእርሱ ይሄ የለበትም። ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልስ የሚሆን ተግባር አለ በመስከረም 11/2018…
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36

እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 13 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,500 ብር አግኝተናል።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።

በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
28👍3
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36

እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 13 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,500 ብር አግኝተናል።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።

በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
30👍3
መልካም አድርግና እርሳው!

ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ።
መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።

መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን!
መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።

እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
129🙏15👍4🤩1
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት

“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36

እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 14 የቻናላችን ቤተሰቦች 25,800 ብር አግኝተናል።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ28 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 52 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።

በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
52👍2
2025/10/21 10:23:42
Back to Top
HTML Embed Code: