ገንዘባችሁን በድኾች ቀኝ እጅ የምታስቀምጡ ከኾነ ሐሜተኛ አያገኘውም፤ ቀናተኛ አያየውም፤ ሌባ አይሰርቀውም፤ ቀማኛ አይነጥቀውም፤ የቤት ውስጥ ሠራተኛ ደብቆ አይወስደውም፤ ማንም ይኹን ማን ሊያገኘው በማይችል ቦታ የተቀመጠ ነውና፡፡
በሌላ መልኩ ከቤት ውስጥ ብታስቀምጡት ግን ሌባም፣ ቀማኛም፣ ቀናተኛም፣ ሐሜተኛም፣ የቤት ውስጥ ሠራተኛም፣ ሌላም ሰው አግኝቶ ሊወስድባችሁ ይችላል፡፡ በጽኑ በርና ቁልፍ ስለ ዘጋነው ከውጭ ቀማኞች ሊተርፍ ይችል ይኾናል፤ ከቤት ውስጥ ቀማኞች ግን ላይተርፍ ይችላል፡፡ ይህ እንዲህ እንደሚኾን በብዙ ሰዎች ዘንድ ስለምናየው የታወቀ የተረዳ ነውና፡፡
እንግዲህ ገንዘባችንን በድኾች እጅ ስናስቀምጥ የገንዘባችን ጌቶች መኾናችንን ታያላችሁን? በድኾች እጅ ማስቀመጣችን ግን በአስተማማኝ ቦታ እንዲቀመጥልን ብቻ አይደለም፤ የብዙ ብዙ ትርፍና ወለድም ስላለው እንጂ፡፡ ምን ማለት ነው? ገንዘባችንን ለሰዎች ብናበድራቸው ምናልባት አንድ ፐርሰንት ትርፍ እናገኝ ይኾናል፡፡ በድኾች አማካኝነት ለእግዚአብሔር ብናበድረው ግን የምናገኘው ትርፍ መቶ ጊዜ መቶ እንጂ አንድ ፐርሰንት ብቻ አይደለም፡፡
እኽል በለም መሬት ብንዘራውና መልካም ምርት ሰጠ ቢባል ቢበዛ የዘራነውን ዐሥር ወይም ኹለት ዕጥፍ ነው፡፡ በድኾች እጅ አማካኝነት በመንግሥተ ሰማያት ብንዘራው ግን መቶ ዕጥፍ ትርፍ ከማግኘታችንም በላይ ማርጀት መፍጀት የሌለውን የዘለዓለምን ሕይወት እናገኛለን፡፡ ገበሬዎች በዚህ ምድር ላይ ዘርተው ምርት ለማግኘት ብዙ ውጣ ውረድ አለው፡፡ በድኾች አማካኝነት በመንግሥተ ሰማያት ለመዝራት ግን ማረሻ አያስፈልግም፤ በሬ አያስፈልግም፤ ወይም ሌላ ይህን የመሰለ ድካም አይጠይቅም፡፡ ከዚህም በላይ የዘራነው እኽል ዋግ አያገኘውም፤ የዝናብ እጥረት አያገኘውም፤ በረዶ አያገኘውም፤ ድርቅ አያገኘውም፤ አንበጣ አያገኘውም፤ ጎርፍ አያገኘውም፤ ገበሬውን (እኛን) ሥጋት ውስጥ ሊጥሉ የሚችሉ ምንም ነገሮች የሉም፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚዘራ ሰብል ከእነዚህ አደጋዎች ኹሉ ነጻ ነውና፡፡ ስለዚህ ይህን ምርት ለማግኘት ድካም የለውም፤ ሥጋት የለውም፤ መጥፎ አጋጣሚ የለውም፡፡ ከዚህ ይልቅ ምርቱ ከዘራነው በላይ ብዙ የብዙም ብዙ ከመኾኑ የተነሣ እስከ ዛሬ ድረስ የሰው ዓይን ያላየው፣ የሰው ጆሮ ያልሰማው፣ የሰው ልብም ያላሰበው ነው፡፡
ወዮ! ይህን ምርት ለማግኘት እንደ መፍጨርጨር ከመታየቱ የሚጠፋ ጥቂት ምርትን ለማግኘት መድከም እንደ ምን ያለ ስንፍና ነው? ሌቦችስ ይቅርና የሌቦች አለቃ ዲያብሎስ በማያገኘው ሥፍራ ገንዘብን እንደማስቀመጥ ሌቦች ሰርቀው በሚያገኙት ቦታ ማስቀመጥ እንደምን ያለ ዐላዋቂነት ነው? እንግዲህ ይህን በማድረጋችን ሊደረግልን የሚችል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው? ይህን ላለማድረጋችን ዘወትር የምናቀርበው ምክንያት ድኽነታችንን ነው፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የቱንም ያህል ድኾች ብንኾን ከዚያች ታዋቂዋና የነበራትን ኹለት ሳንቲም ከሰጠችው ድኻ በላይ ድኾች እንኾናለንን?
እንኪያስ ይህቺን ድኻ እንምሰላት፤ ይህቺን ድኻ አብነት አድርገን ገንዘባችንን የት ማስቀመጥ እንዳለብን እንወቅ እንረዳም፡፡ ይህቺ ድኻ ያገኘችውን በጎ ነገር እናገኝ ዘንድ ፈቃዷንም አሁን ገንዘብ እናድርግ፡፡ እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና በአባቶቻችን ካህናት ጸሎት፣ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነትና ሰውን መውደድ ርስቱንና መንግሥቱን እንድናገኝ ይርዳን፡፡
ለእርሱም ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ኃይልና ክብር ይኹን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

❤68🙏14👍1
Forwarded from የወልድያ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
በምስረታ ላይ ለሚገኘው የደብር ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ/ን ሰንበት ትምህርት ቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ተደረገ።
ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም
በወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ-ክህነት ዋና ጸሐፊና የሰ/ት/ቤት ክፍል ተጠሪ መ/ር ቡሩክ ተስፋዬ አሳሳቢነት፣ በወንድም ሰሎሞን አያሌው አሰተባባሪነት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወዳጆችን በቴሌግራም ቻናሉ በማስተባበር እስከ 7000 ብር ድረስ ወጭ የተደረገበት የ2000 እትም መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ስጦታውን የተረከቡት የሰ/ት/ቤቱ ሰብሳቢ ዲ/ን ኤርምያስ ከዚህ በፊት የተደረገላቸውን ድጋፍ አስታውሰው አሁንም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ወደፊትም በምስረታ ሂደት ላይ እንደመሆናቸው አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንዳይለያቸው አሳስበዋል።
አንድነታችንን አንተው!

❤26💯4🙏3
የወልድያ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
በምስረታ ላይ ለሚገኘው የደብር ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ/ን ሰንበት ትምህርት ቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ተደረገ። ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም በወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ-ክህነት ዋና ጸሐፊና የሰ/ት/ቤት ክፍል ተጠሪ መ/ር ቡሩክ ተስፋዬ አሳሳቢነት፣ በወንድም ሰሎሞን አያሌው አሰተባባሪነት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወዳጆችን በቴሌግራም ቻናሉ በማስተባበር እስከ 7000 ብር ድረስ ወጭ የተደረገበት…
በቻናላችን አማካኝነት በማሰባሰብ አዲስ ለተመሠረተው ሰንበት ት/ቤት ማጠናከሪያ የሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ አድርገናል።
❤17🙏4
እግዚአብሔር ሰዎችን ኹሉ ሲፈጥራቸው በመንፈሳዊ ማንነታቸው እኩል አድርጎ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ እያንዳንዱ ሰው በጎም ኾነ ክፉ ግብር ለመሥራት እኩል ዝንባሌ አለው፡፡ እግዚአብሔርን ለመታዘዝም ኾነ ላለመታዘዝ እኩል የመምረጥ ዕድል አለው፡፡ ከዚህ ውጪ በኾነ ነገር ግን ሰው ኹሉ እኩል አይደለም፡፡ አንዳንዱ እጅግ አስተዋይ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደከም ያለ ነው፡፡ አንዳንዱ በሰውነቱ ብርቱና ጤናማ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደካማና ሕመም የሚበዛበት ነው፡፡ አንዳንዱ ሰው መልከ መልካምና ማራኪ ነው፤ ሌላው ደግሞ አይደለም፡፡
ይህ ኹሉ ቢኾንም ግን በኾነ ነገር ስጦታው ያለው ሰው ስጦታው የሌለውን ሌላውን ሰው ሊንቀው አይገባም፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታን የሰጠን አንዳችን አንዳችንን እንድንጠቅም ነውና፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ከሌላው ወንድማችን የምንፈልገው ጥቅም እንዲኖር ያደረገው በመካከላችን መጠላላትና መለያየት እንዳይኖር ነው፤ እንድንፋቀርና አንድ እንድንኾን አስቦ ነውና፡፡
ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና ዐዋቂ፥ ብርቱም ቢኾን በዚህ ቅር አይበልህ፡፡ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ከወንድምህ አስተዋይነትና ዐዋቂነት ብርታትም ትጠቀማለህና፡፡ በዚህ ብቻ ሳታቆምም ራስህን፡- “ስጦታዬ ምንድን ነው? ወንድሜን እኅቴን በምን ልጠቅም እችላለሁ?” ብለህ ጠይቅ፡፡ ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ፥ እንደ መለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን፥ በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ሌላውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

❤132🙏17
ዓለማችን በብዙ ችግሮች የተሞላች ናት፡፡ ኹላችንም በየግላችን በሕይወታችን ብዙ ችግሮች አሉብን፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እንደ መጀመሪያ መፍትሔ አድርገን የምንወስደውም የችግራችን አፍአዊ ምልክቱን ነው፡፡ መፍታት የምንፈልገውና የምንደክመውም ይህንኑን ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው የሚኖርበት ቤት ባይኖረው ቤት ለመሥራት ያስባል፤ ያለው ቤት አነስተኛ ከኾነም ከዚህ የተሻለና ሰፋ ያለ ቤት መሥራት ይፈልጋል፡፡ የሚበላው ምግብ መናኛ ከኾነ የተሻለ ገቢ አግኝቶ የተሻለ ምግብ መብላትን ይፈልጋል፡፡ አንዱ ከሌላው ባልንጀራው ጋር ቢጣላም ኹለታቸውም ይቈጣሉ፡፡ "አንተ ነህ፤ አንተ ነህ እንጂ" እየተባባሉ ራሳቸውን ለመከላከልና ጥፋተኛ ላለመባል ይለፋሉ፡፡
ይህ ኹሉ ግን ክርስቲያናዊ መንገድ አይደለም፡፡ እንደ ክርስትና ችግሮች ኹሉ የሚወገዱት ነፍስን በመለወጥ ነውና፡፡ አንድ ሰው በሚኖርበት ቤት አነስተኛነትና በሚበላው የምግብ ዓይነት እርካታም ደስታም የማይሰማው ከኾነ ብዙ ገንዘብ ቢያገኝም አይረካም፤ አይደሰትምም፡፡ ምክንያቱም ብዙ ገንዘብ ሲያገኝ አሁንም ሌላ ምኞት ይኖሯልና፡፡ ከመጀመሪያው ይልቅ የተሻለ የሚለውን ቤትም ምግብም ቢያገኝም እንኳን አሁን ሌላ ከዚህ የተሻለ ቤትና ምግብ ይፈልጋልና፡፡
ስለዚህ እውነተኛ እርካታና ደስታ ውስጥን በመለወጥ እንጂ የችግሮች ምልክቶች የኾኑ አፍአዊ ነገሮችን ገንዘብ በማድረግ የሚገኝ አይደለም፡፡ ውስጣችንን ስንመለከት፣ ነፍሳችንን ስንለውጣትና ንጽህት ስናደርጋት በዚህ ምድር የምንኖረው ኑሮ አያሳስበንም፡፡ የዕለት መጠለያና ምግብ ካገኘን በቃን ማለት ይቻለናል፡፡ ስግብግብነታችን ወደ ምስጋና ይቀየራል፡፡
ከባልንጀራው ጋር የተጣላው ሰውም እንደዚሁ ወደ ውስጡ ቢመለከት ጠላቱን መውደድ እንዳለበት ይገነዘባል፡፡ የዚህን ጊዜም ከቁጣው በስተጀርባ ያለው ስሜት ኹሉ እንደ ጢስ ተንኖ እንደ ትቢያ በንኖ ይጠፋል፡፡ ከባልንጀራው ጋር መታረቅም እጅግ ቀላል ይኾንለታል፡፡
ስለዚህ ዋናው ችግራችንን ለማከም እንጂ ምልክቱን ለማስታገሥ አንድከም፡፡

❤76🙏12👍2
✟ የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች፤
✟ የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች፤
✟ የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል፤
✟ የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች፤
✟ የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም፤
✟ የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች፤
✟ የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች፤
✟ የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች፤
✟ የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤
"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

❤135🙏20💯10
"አማንያን የመንፈስና የሥነ ልቡና ሰላም ከማጣታቸውም በላይ አካላቸው ለሞትና ለጉዳት፤ ሃብታቸው ለዝርፊያና ለውድመት እየተዳረገ ነው፡፡ ይኽም ሁሉ ሆኖ ፍትሕን እያገኙ አይደለም፤ አብያተ ክርስቲያናትም በምእመናን ፍልሰት እየተዘጉም እየተቃጠሉም ነው፡፡
ከዚህም ሌላ የሌለን ነገር እንዳለ አስመስሎ ከየአቅጣጫው የሚወረወረው የባዕዳን ስም የማጥፋት ዘመቻ፣ የቤተ ክርስቲያኗን እምነት ከመንቀፍና ከማብጠልጠል በላይ አልፎ የቅዱሳንን ቅዱስ ሥዕል በአደባባይ እስከ መቅደድ ተደርሶአል፤ በቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ላይ በዓላማ የተነሡ አካላት የላኳቸው እንዳሉ በሚመስል መልኩ በስመ ተሐድሶ የሚደረገው እንቅስቃሴ የኛው መለያ የሆነውን ንዋየ ቅድሳትና ልብሰ ተክህኖ፣ መዝሙርና ሥርዓተ አምልኮ በመጠቀም ቤተ ክርስቲያናችንን በአደባባይ እየተዳፈረ ይገኛል፡፡
ይህ አላስፈላጊ ተግባር የሀገሪቱን ዜጎች በእኩልነት የሚያስተዳድረውን ሕገ መንግሥት በቀጥታ የሚፃረር ድርጊት ነው፤ ሆኖም በሕግ የሚጠይቅና የሚያስቆም አካል አልተገኘም፤ እኛም ዝምታን የመረጥን መስለናል፡፡ ነገር ግን መፍትሔው ዝምታ ሳይሆን በሕግ አግባብ ነገሩን ለመፍታት መንቀሳቀስ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡ "
(አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መግለጫ በከፊል የተወሰደ)

❤65👍11🙏10
❤109🙏4💯3
#ጥቅምት_13
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ጥቅምት አስራ ሦስት በዚችም ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ መታሰቢያው እንደሆነ ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል።
ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሔዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና።
ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት
ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ።
በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ።
ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል።
ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጐመ። በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ።
አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው። ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው።
የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚያደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም።
የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም። ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት።
ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው።
ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሃድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።
የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ
ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም። መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ።
ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት። ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንዳመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት።
ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ።
ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።

❤37👍2🏆1
የከበረ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋር መልኳ ይለወዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ። ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደ ናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የእመቤታችን አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ።
ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ሠሪ አስመጥቶ ለከበረ ዮሐንስ የወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስንም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምትና_ግንቦት)

❤52🙏7