"በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤
ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ (ጽላተ) ኪዳን፤
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን።"
(ማኅሌተ ጽጌ- አባ ጽጌ ድንግል)
የሁለተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል

❤82😍5👍3
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤
ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን፤
እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤
ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤
ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን፤
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን።
ትርጉም፦
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ኾነ። የዓለማት ፈጣሪ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን በለበሰበት የሕፃንነቱ ወራት እንደ ነዳያን ቤት ስንኳ የሌለው ስደተኛና መጻተኛ ኾኖ በሰዎች ዘንድ እንደምን ተናቀ እያልኹ የእናቱ ድንግል ማርያም ኀዘን ለእኔ የልቅሶ ዜማ ኾነብኝ።
(ሰቆቃወ ድንግል)

❤110🙏6
450 አበቦች ለዛሬ ለሁለተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ደርሶልናል እናመሠግናለን!
ለሦስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ የተፈጥሮ አበቦችን የምትተባበሩን በውስጥ አናግሩኝ
@natansolo

❤72🙏38
❤31🙏7
ወዳጄ ሆይ! ጥቅም የማይሰጥኽን ነገር አትፈልግ፡፡ ወደዚኽ ዓለም ስትመጣ ባዶ እጅህን ነው፡፡ ገንዘብ ይዘኽ አልመጣኽም፡፡ ክብርን ይዘኽ አልመጣኽም፡፡ ዶክተር፣ ፕሬዚዳንት፣ ኢንጂነር የሚሉ ማዕረጋትን ይዘኽ አልመጣኽም፡፡ ስለዚኽ አጥተኽ ከኾነ አታጉረምርም፡፡
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል” እንዳለ /ማቴ.19፡24/ ገንዘብ የብዙ ክፉ ነገሮች ምንጭ እንደኾነ አስተውል፡፡ እንግዲኽ ከዚኽ የጌታችን ንግግር ገንዘብ ስንት ነገርን እንደሚከለክል አስተዋልክን? ታድያ ገነት መንግሥተ ሰማያትን ከመግባት የሚከለክል ገንዘብ ከአንተ በመራቁ ደስ አይልህምን?
ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት የምትወስድ መንገድ ጠባብ ናት፡፡ ወደ ገሃነም የምታስገባ ገንዘብ ግን ትዕቢትንንና ትምክሕትን የተመላች ናት፡፡ ለዚኽም ነው ጠባቢቱን መንገድ እንዲያገኝ ጌታ ባለጸጋውን “ያለኽን ሽጥ” ያለው (ማቴ.19፥21)፡፡ እንዲኽ ከኾነ ታድያ ገንዘብን የምታሳድደው ስለምንድነው? እግዚአብሔር ለገንዘብ እንዳትገዛ ብሎ በዚያም የገሃነም እራት እንዳትኾን ብሎ ገንዘብን ከአንተ አራቀልኽ፡፡
እውነተኞች አባቶች ልጃቸው ከአንዲት ዘማ ሴት ጋር የማይገባ ሥራ ሲሠራ ባዩት ጊዜ ከርሷ ይለይ ዘንድ ይገሥፁታል፡፡ ርሱን ከርሷ መለየት ባይችሉ እንኳን ርሷን ያባርሯታል፡፡ ክቡር ልዑል የሚኾን እግዚአብሔርም ለእኛ በማሰብ፣ እኛን ከመውደዱ የተነሣ ገንዘብን (ሀብትን) ከእኛ እንዲርቅ ያደርጋል፡፡ ስለዚኽ እንዲኽ ስላጣን ብቻ ክፉ ነገር እንደደረሰብን አድርገን ልናስብ አይገባንም፤ ክፉ ኃጢአት ብቻ ነውና፡፡ ገንዘብ በራሱ መልካም አይደለም፡፡ መልካም የሚኾነው እግዚአብሔርን ደስ ስናሰኝበት ብቻ ነው፡፡
በማግኘት ውስጥ ከመኾን ይልቅ በማጣት ውስጥ ኾኖ እግዚአብሔርን ማገልገል ይበልጣል፡፡ ስለዚኽ ድካምን፣ መከራን፣ ማጣትን እንደ ክፉ ነገር በማየት አንጥላው፡፡
በእውነት ያለ ሐሰት ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር የክብር ክብር፣ ጌትነት የባሕርዩ በሚኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰጭነት በመንግሥተ ሰማያት ጸጋ ክብር እናገኛለንና ማጣትን አንጥላው፡፡ አሜን!!!
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

❤121🙏23👍1
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡።
የኀዘን መግለጫ
"አድኅነኒ እግዚኦ እስለመ ኀልቀ ኄር አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቋልና።" መዝ. 11፥1
እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም!
ለዚህም ምስክሩ ታላቅ አረጋዊ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ፣ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ፣ የተጠቁት ወዳጅ ፣ የትውልድ አባት የሆኑት የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ነበሩ፡፡
ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች፡፡
ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
እግዚአብሔር አምሳክ ኢተዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ
ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

❤122🕊11🙏3👌1
ለግንዛቤ ያህል፦
የቤተክርስቲያናችን ዓርማና ትርጉም
የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ በ2007 ዓ.ም አሻሽሎ ያወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለምትጠቀምበት ስለዚኹ ዓርማ አንቀጽ ፬ ላይ ደንግጓል፡፡
በዓርማው በነጭ መደብ ላይ የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ ክበብ ይዞ የሚታየው ትርጉሙ፡- የምሕረት፣ የደስታና የነፃነት ዘመን የኾነውን ዘመነ ሥጋዌን መሠረት አድርጎ ነገረ ድኅነትን፣ነገረ መስቀልን፣ ነገረ ማርያምን፣ ተልእኮ መላእክትንና ክብረ ቅዱሳንን የሚሰብክ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የዓርማው መሐል ቅዱስ መጽሐፍ ኾኖ “ነዋ ወንጌል መንግሥት” የሚል ጽሕፈት በበላዩ ያለበት መኾኑ፥ የቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖት ቀኖና እና የተቀደሰ ትውፊት በቅዱስ መጽሐፍ ትምህርት ላይ የተመሠረተ መኾኑን የሚያመለክት ነው፡፡
ዓርማው፥ ክርስቶስን በተዋሕዶ አንድ አካል፣ አንድ ባሕርይ ብላ የምታምነው፤ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ በኹሉም ያለች፣ አንዲትና ቅድስት የኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሉዓላዊ ክብር መገለጫና መለያ ነው፡፡
አንቀጽ ፬
የቤተ ክርስቲያን ዓርማ
፩. የዓርማው ቅርጽና ይዘት፡-
፩.፩. መደቡ ነጭ፤
፩.፪. ዙሪያው የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ፤
፩.፫. ከላይ ከአናቱ አክሊል፤ ከታች ከግርጌው መሐል ለመሐል ወጥቶ አናቱ ከአክሊሉ ሥር የደረሰና መስቀል ያለበት አርዌ ብርት፤
፩.፬. በግራ ኹኖ በቀኝ እጁ አርዌ ብርት፤ በግራ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ፤ በቀኝ ኹኖ በግራ እጁ አርዌ ብርት በቀኝ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ፤
፩.፭. ከአርዌ ብርቱ ሥር “ነዋ ወንጌለ መንግሥት” ተብሎ የተጻፈበት ቅዱስ መጽሐፍ፤
፩.፮. ከቅዱስ መጽሐፍ ሥር መስቀለኛ የ”ጸ” ፊደል ቅርፅን የሚመስል፤ ኹለቱ ጫፎቹ ከመደቡ ወደ ውጭ የወጣ ሰበን፤
፩.፯. የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ በተገናኙበት የዓለም ምስል፤ ያለበት ይኾናል፡፡
፪. የዓርማው ትርጉም፡-
ሀ/ መደቡ ነጭ መኾኑ፦ ዘመነ ሥጋዌ የምሕረት፣ የደስታና የነፃነት ዘመን መኾኑን ያመለክታል፤ (ዮሐ.፳፥፲፪፤ የሐዋ. ሥራ ፩፥፲)
ለ/ የዓርማው ዙሪያ በወይን ዛላና በስንዴ ዘለላ የተከበበ መኾኑ፦ ምእመናን በቅዱስ ቊርባን አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን፣ ስርየተ ኃጢአትን፣ የዘለዓለም ሕይወትን የሚያገኙ መኾናቸውን ይገልጻል፤ (ዮሐ. ፮፥ ፶፫-፶፰፤ ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱፤ መዝ. ፬፥፯)
ሐ/ በዓርማው መሐል ቀጥ ብሎ የቆመ የዓርዌ ብርት ምስል በበላዩ ላይ መስቀል፣ ከዚያም ከፍ ብሎ አክሊለ ክህነት አለው፤ የዚኽ ትርጉም፦ ሕዝበ እስራኤል ዓርዌ ብርቱን ባዩ ጊዜ ከእባብ መርዝ እንደ ዳኑ ኹሉ መስቀል ላይ በተሰቀለ በጌታችን በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ኹሉ በዲያቢሎስ ምክንያት ከመጣባቸው ፍዳ ኃጢአት የሚድኑ መኾናቸውን፤ መስቀሉ፦ የቤተ ክርስቲያን የድኅነት ዓርማ መኾኑን፤ (ዘኍ. ፳፩፥፰፤ ዮሐ. ፫፥፲፬)
መ/ አክሊል፦ ቅዱሳን በሰማያዊ መንግሥት የሚቀዳጁትን አክሊለ ክብር እና ማኅተመ ጽድቅን ያመለከታል፤ (ዘጸ. ፴፱፥፴፤ ፩ ተሰ. ፪፥፲፱፤ ፪ጢሞ. ፬፥፰፤ ፩ጴጥ. ፭፥፲፬፤ ራእይ ፪፥፲፤ ፬፥፲፬)
ሠ/ ኹለት መላእክት የዘንባባ ዝንጣፊና ዓርዌ ብርቱን ይዘው ይታያሉ፤ ይህም ዘንባባ፦ በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ መንፈሳዊ ደስታንና ድኅነተ ነፍስን ያመለክታል፤ ቅዱሳን መላእክት የቤተ ክርስቲያን ጠባቂዎችና የመልካም ዜና አብሣሪዎች መኾናቸውን ያሳያል፤ ዓርዌ ብርቱን ይዘው መቆማቸው፥ ነገረ መስቀሉን አምኖና ሃይማኖቱን አጽንቶ ይዞ የሚኖር የዘለዓለም ድኅነትን የሚያገኝ መኾኑን ያመለክታል፤ (መዝ. ፺፥፲፩፤ ሉቃ. ፲፫፥፮-፱፤ ዕብ. ፩፥፲፬)
ረ/ የዓርማው መሐል ቅዱስ መጽሐፍ ኹኖ፥ “ነዋ ወንጌለ መንግሥት” የሚል ጽሑፍ በበላዩ አለበት፤ የዚኽ ትርጉም፦ የቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖት፣ ቀኖና እና ትውፊት በቅዱስ መጽሐፍ ትምህርት ላይ የተመሠረተ መኾኑን ያመለክታል፡፡ (ማቴ. ፳፬፥፲፬)
ሰ/ ከቅዱስ መጽሐፉ ግርጌ የሚታየው ሰበን፥ ቅድስት ድንግል ማርያም ስታርግ ለቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ የሰጠችውን ሰበን የሚገልጽ ሲኾን፤ ትርጉሙ፦ የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤንና ዕርገትን እንደዚኹም የምእመናን እናት መኾኗን የሚያመለክት ነው፡፡ (ዮሐ.፲፱፥፳፯)
ሸ/ የስንዴው ዛላና የወይኑ ዘለላ በተገናኙበት ላይ የሚታየው ክብ ነገር፥ ዓለምን የሚወክል ኾኖ ዓለም በክርስቶስ መዳኑን ያመለክታል፡፡ (ዮሐ. ፫፥፲፯)

❤35🙏3👍2