Telegram Web Link
~መኖር ውስጥ አለመኖር

.....ፀሀይ መውጣቷን ማዬት በራሱ መኖር ነው....በመኖር ውስጥ አለመኖር አለ አይደል?ወዳጄ አንተ ግን አትፍረድ የጨለማ ትርጉም ይለያያልና ....ሻማውን ሆኜ የሰዎችን ጨለማ ማብራት እመኛለሁ እየኖርኩ ግን መሞት አልፈልግም ...እያለን አለመኖር ግን አይከብድም?

❤️ ከአላህ በታች #ብዕሬ ነች ጓደኛዬ💔💐
❤️❤️ግን እኮ በህይወታችን ፍጹም የሆነ ነገር የለም ከሁሉም የሚገርመኝ ሁሉም ነገር ጊዜያዊ መሆኑን አለመረዳታችን ነው።

አንዳንድ ሰዎች ወደ ህይወትህ ይመጡና ሻማ ሆነው ኖረው ብቻህን መኖር እንዳለብህ ብቻ አሳማሚ ትምርት ሰጥተውህ ይሄዳሉ💔😢

ከአላህ በታች #ብዕሬ ነች ጓደኛዬ💔🌹
❝በልቤ ያለህን ቦታ ማወቅ ተስኖሃል አይኔን እንጂ ልቤን ማየት አልቻልክም..😘
ስለ አንተ ስኖር እራሴን አጣሁት..ፍቅር መቀበል ላይ አይሰራም🥺ሁሌም መስጠት ነው ተግባሩ.. በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ የኔ ፍቅር አለ ህያው ፍቅር አይሞትም... ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ፍቅር ነው ስለዚህ ፍቅር ሲይዘን አላህን በልባችን እናስቀምጠዋለን።።❞❤️ላንተ ያለኝ ፍቅር ሁሌም #ህያው ነው⚘💍ኑርልኝ በደስታ💔🥺😘

⚘ብዕሬ…
ልብ ይበሉ‼️

በሽልማት ፕሮግራሙ ከመሳተፍዎ በፊት # በጥንቃቄ መመሪያዎችን ያንብቡ!
ለመሸለም እነዚህን መመሪያዎች በጥንቃቄ ይከተሉ።

1.መጀመርያ ከታች ባለው ማስፈንጠርያ መሠረት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ። (ወይም ከታች 👇 ''JOIN'' 👇የሚለውን ቁልፍ ተጭነው መቀላቀል ይኖርብዎታል)

https://www.tg-me.com/Zemzemofficial

2. በመቀጠል ይህንን መልዕክት ከ50 በላይ ለሆኑ ሰዎች በፍጥነት ሼር ( Forward) ያድርጉ፤
(ልብ ይበሉ! ብዙ ሰዎችን # add ባደረጉ ቁጥር የሽልማት ዕድልዎን ያሠፋሉ!)
አሏህ አክበር" ማሻ አሏህ " በቃሪዕ ኢምሩ(Imru)❤️
bin Tahir😘😘😘😍😍😍😍
ربي يحفظك ويزيدك علم⚘⚘
6:32

وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا لَعِبٌ وَلَهْوٌ ۖ وَلَلدَّارُ الْآخِرَةُ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَ ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

የቅርቢቱም ሕይወት ጨዋታና ላግጣ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር (ገነት) ለእነዚያ ለሚጠነቀቁት በጣም በላጭ ናት፡፡ አታውቁምን
ለውብ ቀን!
💚

ማጣት መሸነፍና መውደቅ ብዙ እውነትነት የሌላቸው ስሜቶች ናቸው።
የተመኘነውን የማናገኘው ጊዜው ስላልደረሰ አልያም የተሻለ ነገር ስለታሰበልን ወይም
ደግሞ ምኞታችን በመልካም መሰረት ላይ ስላልተመሰረተ ነው።
መሸነፍና መውደቅም እኛ የውሸት ማንነታችን ሲነካ የሚሰሙን ስሜቶች ናቸው።
እያንዳንዱ እንቅፋት መንገዳችንን አስተካክለን እንድንራመድ የሚያግዘን አጋጣሚ ነው።
እያንዳንዱ ስህተት ከዚህ የተሻለ ማሰብ እንደምንችል የሚያስታውሰን ቅጣት ነው።

ውብ ቀን!💚
✘ ጥላቻን በውስጥ መያዝ ማለት ውድ ንብረቶች ከተቀመጡበት ስፍራ ክብሪት ለኩሶ እንደመተው ነው።እሳቱ ውድ ንብረቶችን እንዳልነበሩ እንደሚያደርገው ጥላቻም ውስጣችን ያሉ መልካም ነገሮች በሙሉ ያወድምብናል።
በድርጊታቸው እንድትጠላቸው ሚያስገድዱህ ሰዎች ካሉ ይቅር ብለህ እርሳቸው።ልብህ ውስጥ ለጥላቻ ሚሆን ክፍት ቦታ ሊኖርህ አይገባም።

ይቅር በልና እርሳው♥️
@Astentn
ወዳጅነታችሁን ጠብቁ። ከወዳጆቻችሁ ጋር መልካም ጊዜ እያሳለፋችሁ ስለውዴታችሁ ንገሯቸው። ስህተታቸውን እለፏቸው። የሆነ ቀን እናንተ ወይም እነርሱ ላይመለሱ ይጓዛሉ። ሽታቸውም ይናፍቃችኋል። ያኔ ልባችሁ አንደበቱን ከፍቶ ስለነርሱ ይናገር ይሆናል፣ በምናልባት ናፍቆት ብዙ ርቀት ይጓዝም ይሆናል። እኛ የትናንት ትዝታ ነን። በቃ ነገም ትዝታ ብቻ ነን። ፈገግ በሉ፣ ይቅር በሉ። ህይወት አጭር ናት።

@Astentn
የኋላ ኋላ እንዳትጸጸት!
(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

የኋላ ኋላ እንዳትጸጸት ከሁሉ በፊት ራስህን መምራት ልመድ፡፡ አመራር የሚጀምረው ራስን ከመምራት መሆኑን አስታውስ፡፡ ሰዎች ከሚሰሩት ትልልቅ ስህተቶች አንዱ ራስን መምራት ሳያውቁ ቤተሰብን፣ ድርጅትንና አልፎም ሃገርን ወደመምራት ሲዘልቁ ነው፡፡

ካለማቋረጥ በእውቀት በማደግ፣ የራስን ሕይወት በማሻሻል፣ መሰረታዊ ዲሲፕሊኖችን በማዳበርና በመሳሰሉት አቅጣጫዎች ራሱን ያልመራ ሰው የኋላ ኋላ መጸጸቱ አይቀርም፡፡ ራስህን ካልመራህ የመጣ ነገርና ሁኔታ ሁሉ ይመራሃል፡፡ ለራስህ አቅጣጫን ካላስያዝህ ሌሎች ሰዎች ወይም ሁኔታዎች አቅጣጫን ቀይሰው ወደማትፈልገው ስፍራ ይወስዱሃል፡፡

ራስህን በማወቅ፣ ዓላማህን በመለየት፣ ደካማ ጎንህን በማሻሻል፣ ብርቱውን ጎንህን ደግሞ የበለጠ በማሳደግ ወደፊት የምትራመድ አይነት ሰው ካልሆንክ ባለህበት ከመርገጥ አልፈህ ወደኋላ መንሸራተትህ አይቀርም፡፡ ራስህን በመምራት እንዳትሻሻል ያደረጉህ እንቅፋቶች እንዳሉብህ ማሰብና ማሳበብ በኋላ ከመጸጸት አያድንህም፡፡
2025/06/27 18:56:46
Back to Top
HTML Embed Code: