Telegram Web Link
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel
 
For Photography lovers  join us
           👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography

Hawassa University 🏢

Order now 📸 @Juliiian
አዲስ የጎሀው
እንሆ ጀመረ 👇👇👇
....የሀዘኔ መጨረሻ....

....ክፍል 1 .....

☺️☺️😍😍☺️☺️

.....ሰላም እባላለሁ ታሪኬን ላካፍላችሁ ያኔ 17 አመቴ ነበር የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ :: የምኖረው ከእናት አባቴ እንዲሁም ከወንድሜ ጋር ነበር፡፡ አባቴ የኮንስትራክሽን ባለሙያ ነበር፡፡ እናቴ የህክምና መስጫ ተቋም ውስጥ ዳይሬክተር ነበረች፡፡ ያው ዶክተር ማለት ነው፡፡ እሁድ እሁድ ከእንቅልፌ የምነሳው 4 ሰዐት ነበር ፡፡ በ1እሁድ ቀን ግን የተነሳሁት 2 ሰዐት ነበር፡፡ ምክንያቱም አቤል ቤተ ክርስቲያን እንሂድ ስላለኝ፡፡

......አቤል የ 7 አወት ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡ አቤልን በጣም እወደዋለው፡እናም መኝታ ክፍሌ ገብቶ "ሰሊ ሰሊ ተነሺ" አለኝ አይኔን እያሻሸሁኝ "በጌታ ተወኝ" አልኩት፡፡"ተነሺ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ በናትሽ" አለኝ፡ ትንሽ ከተግደረደርኩኝ በኀላ "እሺ" አልኩት፡፡ ደስ ብሎት ከአልጋዬ ሊወርድ ሲል "ግን" ብዬ እጁን ያዝኩት ፡፡ዞር ብሎ "ምን" አለኝ እየተቅለሰለስኩኝ "ያው የሳምንት ብር ተሰቶሀላ"አልኩት"፡፡እናትና አባታችን የሳምንት ብለው እሁድ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ ብር ይሰጡናል፡፡ አቤልም ድምፁን ቀነስ አድርጎ "አው"አለኝ፡፡ "እሺ የተሰጠህን ብር ግማሹን ትሰጠኛለህ"አልኩት "አልሰጥሽም" ሲለኝ ተመልሼ ተኛው::
...ትንሽ ከቆየ በኀላ ባዘነ ድምፅ "እሺ "አለኝ፡፡ ከዛ ተነስቼ ተጣጥቤ ሄድን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ሲያልቅ ትንሽ ቁጭ አልን፡፡ በድንገት የሆነ ልጅ መጣና እጄን ያዘኝ፡፡ዞር ብዬ በግርምት "አቤት" አልኩት ከዛ "ይቅርታ ከሰው ጋር ተመሳስለሽብኝ ነው" አለኝ፡፡ እኔም"እሺ ምንም ችግር የለውም "ብዬ ዞር አልኩኝ፡፡ ድጋሚ መጥና...........



ክፍል 2 እንዲለቀቅ like . Share ❤️በማረግ ተባበሩን....


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
.....የሀዘኔ መጨረሻ.....

😌😌😍😍😌😌

.....ክፍል 2....
.
........ድጋሚ መጣና.."ይቅርታ ስንት ሰዐት ነው"አለኝ፡፡ የሚገርመው እጁ ላይ ትልቅ ሰዐት አለ፡፡ እጅ ላይ ያለውን ሰዐት እየተመለከትኩት "ያንተ አይሰራም" አልኩት፡፡ ደንግጦ እጁን አየው፡፡ ...ትንሽ ካፈጠጠበት በኀላ "አው አይሰራም" አለኝ፡፡

.....ከዛ ስልኬን አውጥቼ ልነግረው ስል"እንደውም ተይው "ብሎኝ ሄደ፡፡ በጣም ገርሞኝ ፈገግ አልኩኝ፡፡

.....ከዛም እኔና አቤል ወደ ቤት ተመለስን፡፡ እቤት እንደገባን ቤዚ እና ሙሌ ይጨቃጨቃሉ፡፡ ቤዛ እናቴ ናት እኛ ቤዚ ነው የምንላት፡፡ሙሌ ደግሞ አባታችን ነው፡፡.....እኔና አቤል በሩን ከፍተን ገባን..ቤዚ"አይሆንም ምን ሆነካል" አለችው ሙሌ ደግሞ ድምፁን እያቅለሰለሰ "ችግር የለውም የኔ ንግስት" አላት፡፡ከዛ አጅዋን ራስዋ ላይ አድርጋ ዞር ስትልእኛን አየችን፡፡ከዛጠ"ውይ መጣችሁ እንዴ" አለችን፡፡ ሙሌ እኛን እንዳየ በፍጥነት ከቤት ወጣ፡፡ "ቤዚ ምን ሆናችሁ ነው" አልኩዋት እሱዋም ሳቅ እያለች "አይ ምንም አልሆንም " አለቺኝ፡፡ ውሸትዋን እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ አቤል በጣም አዝኗል እኔም ደንግጫለው ሁለታችንም እንደዛ ሲሆኑ አይተናቸው ስለማናውቅ በጣም አዝነናል፡፡ቤዚ"አቤሌ ዛሬ አልደከመህማ" አለችው እሱም በአዎንታ አንገቱን ነቀነቀ፡፡ አቤል ቅዳሴ ላይ ስለሚደክመው ቁጭ ይል ነበር ለዛ ነው የጠየቀችው፡፡ ከዛ ቁርስ በላን አቤል ጓደኛው ቤት ለመጫወት ሄደ፡፡ እኔም ክፍሌ ውስጥ ሙዚቃ እየሰማሁኝ ነበር.....

......ወደ 8 ሰዐት አካባቢ ሙሌ ከአንድ ሰውዬ ጋር
ወደ ቤት መጡ፡፡ እኛም ምሳችንን አብረናቸው በላን ከዛ ሙሌ ለሰውዬው " እንግዲ ቤቱ ይሄ ነው"አለው፡፡ቤዚም ተመነጫጭቃ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ሙሌም በእፍረት ድምፅ "ጠዋት ራሴን አመመኝ ስትል ነበር ለዛ ነው ይቅርታ አድርግላት" አለው ሰውዬውም "ኧረ ችግር የለውም" አለው፡፡በችኮላ ድምፅ "አሁን ተስማምተናል በል ካርታውን ስጠኝ "አለው፡፡ ሙሌም "በሚገባ " ብሎ ወደ መኝታ ክፍሉ ሄደ፡፡ እኔና ሰውዬው ብቻችንን ቀረን.....


ክፍል 3 እንዲለቀቅ like ማረግ አትርሱ...❤️

••●◉Join us share
Forwarded from Julian Pictures 📸
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel
 
For Photography lovers 
join us
           👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography



Order now 📸 @Juliiian
አዲስ የጎሀው
.....የሀዘኔ መጨረሻ.....

😌😌😍😍😌😌

....ክፍል 3.....
.......እኔና ሰውዬው ብቻችንን ቀረን.....ስለደበረኝ ተነስቼ ወደ መኝታ ክፍሌ ሄድኩኝ እየሄድኩኝ እያለ ሙሌ እና ቤዚ ሲጨቃጨቁ ሰማኀቸው፡፡ በር ስር ተደብቄ ማዳመጥ ጀመርኩኝ፡፡ ቤዚ"ምን ሆነሀል እንዴት የልጆቼ ማረፊያ የሆነውን ቤት ታሲዛለሀህ" አለችው ፡፡ሙሌም "ምን ሆነሻል ትልቅ ትርፍ እኮ ነው የማገኘው" አላት፡፡ "ያንተ ትርፍ ብር ይቅርብኝ ነገ እንኳን ብሞት ልጆቼን ያለ ቤት ለላስቀራቸው አልፈልግም ስለዚህ አልስማማም" አለችው፡፡ እዛው በር ስር ቆሜ አንድ ነገር ታወሰኝ..... ከ 1 ወር በፊት ሙሌ እራት ልጋብዛቹ ብሎን ወጥተን ነበር፡፡ እራታችንን እየበላን ሙሌ "አንድ የምነግራቹ ነገር አለ " አለን ፡፡እኛም"እሺ ንገረን" አልነው፡፡"አንድ ኘሮጀክት አለ እና ይህን ኘሮደክት ከ 2 ጓደኞቼ ጋር ነው የምንሰራው" አለን፡፡ ቤዚ " የምን ኘሮጀክት" አለችው፡፡እሱም " 5 ፎቆች አሉ እነሱን መገንባት ነው " አላት፡፡እሷም " እሺ ጥሩ ነዋ " አለችው፡፡ ከዛ እራታችንን መብላት ቀጠልን፡፡ በድንገት ሙሌ "ቤዚ" አላት "ወዬ አለችው " ግን ብር ያስፈልገኛል " አላት፡፡እሷም " እና ባንክ አለልሀ አይደል " አለችው፡፡ "እሱማ አይበቃም " አላት፡፡ " እና ምን " አለችው፡፡ ያው አበዳሪ አግኝቻለው፡፡ ኮስተር ብላ " በቃ እቤት እናወራለን " አለችው፡፡ወድያው የሙሌ ጓደኛ መጣና ሰላምታ ሰጠን፡፡ እነሱም ድጋሚ ዕርሱን አላነሱትም፡፡ .......

......በድንገት የነ ቤዚ ክፍል ተከፈተ በፍጥነት ከበሩ ራቅ ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ሙሌ የቤቱን ካርታ ይዞ ነበር " ሙሌ እንጣላለን ቶሎ ብለህ ካርታውን አስቀምጠው" አለችው፡፡ "ቤዛ ሌላ አማራጭ የለኝም" ብሏት ሄደ፡፡ ለሰውዬው ካርታውን ሰጠው ሰውዬውም ካርታውን እየተቀበለ "እንግዲህ በተባባልነው ጊዜ ብሩን ትሰጠኛለህ እኔም ካርታውን እሰጥሀለው" አለው በድንገት ቤዚ መጣችና" ይቅርታ የኔ ወንድም እኔ አልተስማማሁም ስለዚህ ካርታውን ስጠኝ"አለችው፡፡ሰውዬውም"ከባልሽ ጋር ተስማምቻለው እሱ የኔ ጉዳይ አይደለም" ብሎት ሄደ፡፡

.....ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቤዚ ሰላምዋን አጣች ፡፡ደም ግፊት ስኳር ምናምን የሚባሉ በሽታዎች እየተፈራረቁ በሰውነትዋ ተጫወቱባት፡፡ ህመምዋም እየጠና ሄደ፡፡ውሎዋችን ከቤት ወደ ሀኪም ቤት ሆነ፡፡ አቤል በጣም ተጨንቋል እኔም እንደዛው፡፡ በቤታችን ሰላም ጠፋ ጭቅጭቅና ኩርፊያ ቤታችንን አንኳኩተው ከገቡ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ እንደድሮው መሆን አልቻልንም፡፡ አቤልም ትምህርቱ ላይ ደክሟል፡፡ ይህንን ስታይ እናታችን ይበልጥ ተጨነቀች ሙሌም " ቤዚ ዝም ብለሽ አትጨነቂ"ይላታል፡፡"እንደዚ የሆንኩት በአንተ ምክንያት ነው " ብላ ታለቅሳለች፡

.......በአንድ የተረገመች አርብ ቀን..............
.....የሀዘኔ መጨረሻ.....

ክፍል 4

......በአንድ የምታስጠላ አርብ
የተባለች ቀን እኔና አቤል ወደ ትምህርት ቤት ልንሄድ እየተዘገጃጀን ነው። መስቴ ምግብ እያዘጋጀች ነው ማስቴ እውነተኛ ስሟ መስታወት ነው እኛ ግን ማስቴ ነው የምንላት ቤዚ ማስቴን ጠራቻት እሷም ሄደች ከትንሽ ደቂቃ በኀላ ተመልሳ መጥታ "ሰሊ እናትሽ እየጠራችሽ ነው" አለችኝ:: እኔም በድንጋጤ "ምነው አመማት እንዴ "አልኳት በዝግታ "እስቲ ሂጂና እያት" አለችኝ::

.......እኔም በፍጥነት ሄድኩኝ የቤዚ ክፍል ስገባ ቤዚ ጠቋቁራ ነበር "ምነው ቤዚ አመመሽ እነዴ" አልኳት ::"ሰሊ ዛሬ አንድ ነገር እነግርሻለው" አለችኝ::" ምን አልኳት" አልጋዋ ላይ እንድቀመጥ ጋበዘችኝ እኔም ተቀመጥኩኝ "ልጄ አባትሽን በጣም እወደዋለው እሱ ግን እኔን ሳይሰማኝ ቤቱን አስይዞታል ስራውም የተሳካለት አይመስለኝም ምን እንደማደርግ አላውቅም" እንባዋ ከአይኖቿ እንደጉድ ወረዱ እኔም ማልቀሴን ቀጥያለሁ "እና የኔ ልጅ ወንድምሽን እንዳይከፋው መቼም ቢሆን በጥሩ እና በመልካም ምግባር አንፀሽ አሳድገው አደራ የኔ ልጅ" አለችኝ:: ምንም ማለት ስላልቻልኩኝ እጄን አፌ ላይ ለጥፌ ማልቀስ ጀመርኩኝ " ወድያው አቤል ጠራኝ ቤዚም "አደራ የኔ ልጅ ለዚህ ቃል ግቢልኝ" አለችኝ እኔ ግን ዝም ብዬ ማልቀሴን ቀጠልኩኝ ወድያው አቤል በሩን ከፍቶ ገባ እኔም ቤዚም በፍጥነት እንባችንን ጠራረግን አቤል ግን እያለቀስን እንደነበር ሳይገባው አልቀረም ቤዚ ምንም ማለት አልቻለችም ቃላቶች ሲተናነቅዋት ዞር ብዬ" አቤል ሂድና ከመኝታ ቤቴ በርሳዬን አምጣልኝ "አልኩት::

.......እሱም ሄደ እሱ ከክፍሉ መውጣቱን እንዳረጋገጥኩኝ" ቤዚ በናትሽ ዛሬ ትምህርት ቤት አልሂድ እዚ ከአንቺ ጋር ልዋል" አልኳት:: እሷም እየተኮሳተረች "እሱማ አይሆንም እኔ እኮ ደህና ነኝ በይ አሁን ወንድምሽን አታስጠብቂው "አለችን "ቤዚ ግን" ስላት ፀጉሬን እየነካካችኝ እኔና አቤልን እነደምትወደን ነገረችኝ እኔም እንደምወዳት ነግሬያት ከክፍሉ ልወጣ ስል "ሰሊ "አለችኝ እኔም ዞር አልኩኝ "አቤልን አደራ እሺ የኔ ልጅ እንዳላዝንብሽ "አለችኝ ተንደርድሬ አቀፍኳች መሄድ አልፈለኩም ግን በግድ እንድሄድ አደረገች.....

ክፍል5 እንዲለቀቅ like ማድረግ አትርሱ
የሀዘኔ መጨረሻ....

....ክፍል 5....

......በግድ እንድሄድ አደረገች...... እኔም እሺ ብዬ ሄድኩኝ፡፡ ክፍል ውስጥ እያለሁ አንዴ ልቤ ይፈራል አንዴ በጣም ይጨነቃል ፡፡ብቻ መማር አይበለው እንደነገሩ ሆኜ የመለቀቂያ ሰዐታችን ደረሰ፡፡እኔም አቤልን ይዤ እየተጣደፍኩኝ ወደ ቤት ሄድን፡፡ እቤት እንደደረስን የግቢው በር ክፍት ነበር፡፡ቶሎ ብዬ ገባሁኝ ፡፡ማስቴ" እነዚህን የመሰሉ ልጆች ለማን ጥለሽ" እያለች ታለቅሳለች፡፡ ቦርሳዬን መሬት ላይ ጣልኩት እንባዬ ከአይኔ ላይ ድብ ድብ አለ፡፡ ልቤ እንደመትረይስ መታች፡፡ እግሮቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ አፌ ተርበደበደ ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላወኩም ነበር፡፡

.......ቶሎ ብዬ ወደ ቤዚ መኝታ ክፍል ሄድኩኝ፡፡ ፊትዋ በነጭ ነጠላ ተሸፍኖ ነበር፡፡ በዛ ሰዐት በድን ሆንኩኝ፡፡ ጎረቤቶቻችን ክፍሉ ውስጥ ነበሩ ከክፍሉ ሊያሶጡኝ ሞከሩ፡፡እኔም " ለምን ታሶጡኛላችሁ ቤዚን ልያት እንጂ " አልኳቸው፡፡እጄን ለቀውኝ ማልቀስ ጀመሩ፡፡ ቤዚ ሞታ ነበር ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡የምር ማመን አልፈለኩኝም ነበር ግን ቤዚ ጠዋት አቤልን አደራ ብላኝ ነበር ይህን ሳስታውስ ተንበርክኬ ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ ቤዚን ይዣት "ቤዚ እናቴ አልኳት"ግን ምንም መልስ የለም ነበር፡፡ በዛ ሰዐት " አቤት ሰሊ" እንድትለኝ በጣም ፈልጌ ነበር፡፡ ግን እሷ ዝም ነበር ያለችው፡፡ ወድያው አቤል መጣ፡፡"እማ " አላት "ቤዚ አሁንም ዝም አለች፡፡ አቤል ሳያስበው እንባዎቹ ወረድ፡፡ እኔና አቤል ተቃቅፈን ተላቀስን፡፡ ወዲያው ሙሌ መጣ፡፡ ሲያየን በጣም ደነገጠ ፡፡ ማልቀስም ጀመረ"ወይኔ ፍቅሬ ...ወይኔ ምነው ጨከንሽ እኛን ለማን ጥለሽ"እያለ ማልቀሱን ቀጠለ፡፡ ጎረቤቶቻችን ቶሎ አሶጡን፡፡ውጪ ላይ ተንበርክከን ሶስታችንም ተቃቅፈን እየጮህን ማልቀስ ያዝን ፡፡ ሁላችንም በጣም አዝነን ነበር፡፡ብዙ ካለቀስን በሁዋላ ልቤ ላይ ትልቅ ቁስል ያለ ይመስል ተንገበገብኩኝ፡፡የሚገርመው አቤልን ሳየው ቤዚ የነገረችኝ ነገር ትዝ እያለኝ እንባዬ ሳላስበው እንደጉድ ይወርዳል ።ሙሌም አልቻለም የሚገርመው እንደዚህ አይተነው አናውቅም ነበር ። እያየን አንገቱን ደፍቶ ያነባል ያው ቤዚም ከሁለት ቀን በኀላ ተቀበረች የቀብሩ ቀን በጣም ያስጠላ ነበር ማስታወስ እራሱ አልፈልግም እኔ በዛ ሰዐት የእናቴ እቅፍ እፈልገው ነበር ። ትንፋሽ ባይኖራት እንኳን ብታቅፈኝ ብዬ ተመኘው ። ህይወታችን በሙሉ ተቀየረ ቤዚ በጣም ነበር የምትናፍቀን ሙሌም እራሱን ጥሎል ። በዚህ ሁኔታ ቀናት ወራት ተቆጠሩ ።

........ሰኞ ቀን ወደ 4 ሰዐት አካባቢ ፖሊሶች ቤታችን መጥተው ሙሌን ይዘውት ሄዱ እኛም ተከትለናቸው ሄድን ፖሊስ ጣቢያ እንደደረስን ሙሌን የሆነ ክፍል ውስጥ አስገቡት። እኔና አቤልም ወደ መርማሪው ክፍል ገብተን ምን እንደተፈጠረ ጠየቅን ።መርማሪውም" ልጆች ከናንተ ከፍ የሚል ሰው የለም" አለን "አው የለም ለምንድን ነው አባታችንን ያሰራቹት" አልኩት እሱም በረዥሙ ተነፈሰና "አባትችሁ ወንጀል ሰርቷል.... ልጆች አለን" ጉጉት ይሁን ፍርሀት አላውቅም ግን መልሱን ለመስማት በሚፈልግ ስሜት ሆነን ሁለታችንም በእኩል ድምፅ ምን አልነው። ይህን ለኛ መናገር አልፈለገም ግን ግድ ስለሆነበት መሰለኝ "አባታችሁ ባለቤት የሌላቸውን ፎቆች ሲሰራ ተገኝቷል ለዛ ነው "አለን ወድያው ሁሉም ነገር ትዝ አለኝ ። ያ እራት የጋበዘን ቀን የነገረን ነገር ፤ ቤታችን መጥቶ የቤት ካርታውን የወሰደው ሰውዬ ፤ ያ የቤዚና የውሌ ጭቅጭቅ ትዝ እያለኝ ጭንቅላቴን ሊያፈነዳው.........

ክፍል 6 እንዲለቀቅ like ማድረግ አትርሱ
....የሀዘኔ መጨረሻ.....

ክፍል 6

........ሊያፈነዳው ደረሰ፡፡ ወድያው እራሴን ሳትኩኝ ፡፡ አፋፍሰውኝ ስታፍ አስገቡኝ ስነቃ አቤል እጄን ይዞኝ ያለቅሳል። መርማሪው ቆሞ እጁን አፉ ላይ ደቅኖ በግርምት ያየናል፡፡ ሌሎችም ሁለት ፖሊሶች ነበሩ፡፡ መንቃቴን ሲያዩ "አይዞሽ ተረጋጊ ተረጋጊ" አሉኝ። አቤል እያለቀሰ "ሰሊ አንቺም እንደነሱ አትተይኝ እባክሽ" አለኝ ::እነሱን ያለው ቤዚን እና ሙሌን ነው እያለቀስኩኝ አይኖቹን በስስት እየተመለከትኩኝ "እንዴት ወንድሜ እንዴት እንደዚ አደርጋለው" አልኩት:: እቅፍ አደረገኝና "እህቴ በጣም እወድሻለው "አለኝ እቅፍ አድርጌ እኔም አልኩት ...

ትንሽ ከተረጋጋሁኝ በኀላ ወደ ቤት ሄድን ፡፡ ማስቴ በጣም ጨንቋት ነበር ቤቱን ለማን ጥዬ እሄዳለው ብላ ነው እንጂ መምጣት ፈልጋ ነበር፡፡ ልክ እንደደረስን "ሰሊ ምንድን ነው" አለችኝ ሁሉንም ነገር ነገርኳት እጇን አፏ ላይ አድርጋ በግርምት እኔን ማየት ጀመረች ፡፡ እኔም "በቃ አሁን ትንሽ ልረፍ "ብያት ወደ ክፍሌ ሄድኩኝ፡፡

ክፍሌ ገብቼ አልጋዬ ላይ ጋደም ልል ስል አቤል "ሰሊ" አለኝ::እኔም የሚነግረኝን ለመስማት ውስጥ ባለ ስሜት "ወዬ" አልኩት:: በስስትና በፍርሀት ያየኝ ጀመረ ፡፡ምን ሆንክብኝ አልኩት ፡፡እሱ ግን ዝም ብሎ እያየኝ ነበር ፡፡እጁን ጉትት አድርጌ እቅፍ አድርጌው ፀጉሩን እያሻሸሁኝ" አይዞህ ወንድሜ እኔ አለሁልህ ምንም እንድትሆን መቼም ቢሆን አልፈቅድም" አልኩት:: ሁለታችንም ተቃቅፈን ትንሽ ተኛን፡፡ስንነሳ ማስቴ ምግብ ሰራርታ ነበር እሱን በላልተን ወደ ሙሌ ጋር ሄድን:: ግን መግባት አትችሉም ተባልን መርማሪው በጣም ስላሳዘንነው ከሙያ ስነምግባሩ ውጪ ሆኖ ሙሌን አሳየን ፡፡ሁለታችንም ሙሌን ስናየው በጣም ደስ አለን ሙሌም እያለቀሰ "ልጆቼ ይቅር በሉኝ "አለን ፡፡"አባ ሁሉን ነገር ካንተ መስማት እፈልንለው" አልኩት:: እሱም ሁሉንም ነገር ነገረን ይቅር በሉኝ አለን "እያለቀስኩኝ አባታችን ነህ እኮ እንዴት ይቅርታ አናረግልህ አንተ ፈልገህ አይደለም እንደዚህ የሆነው ሁሉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ነው ከልባችን ይቅር ብለንሀል" አልኩት::እኔንም አቤልንም እቅፍ አደረገን:: ገና የአባቴን እቅፍ ሳልጠግበው መርማሪው"በቃ ሰዐት አልቋል" ብሎ ሙሌን ይዞት ሄደ ፡፡እኛም ወደቤት ተመለስን ከሁለት ቀን በኀላ ሙሌ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ዳኛውም የ13 ዐመት ፅኑ እስራት ፈረደበት፡፡

......አቤል "አባቴን አትውሰድብኝ እባካችሁ" እያለ ያለቅሳል እኔ ምንም ማድረግ አልቻልኩም:: አቤል እንደዛ ሆኖ ሳየው የቤዚ ቃል በአእምሮዬ ላይ ድቅን ይሉብኝ ነበር፡፡ተቀምጬ አይኔን እንኳን ለማርገብገብ ሳልደፍር አለቀስኩኝ ፡፡ፖሊሶቹም ሙሌን ወሰድት ፡፡ማስቴ አቤልን ያዘችው ፡፡ሙሌ "አይዟቹ ልጆቼ" ሲል ይሰማኛል ነገር ግን አንገቴን ለማዞር እንኳን አቅሙ አልነበረኝም ነበር፡፡ ሁሉም ከሄድ በኀላ ማስቴ በሉ ወደቤት እንሂድ አለችን አቤል እያለቀሰ አባቴን ጥዬው አልሄድም አላት:: እሷም በሀዘን ተውጣ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ድንገት ሳይታሰብ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንባዬን እየጠራረኩኝ "በቃ እንሂድ አልኳቸው" አቤል "አልሄድም አለኝ" ተኮሰታትሬ "አይ እንግዲ" ብዬ እጅን እየጎተትኩኝ ከፖሊስ ጣቢያ ወጣን፡፡ እኔ የአቤልን እጅ ይዤ በፍጥነት እየተራመድኩኝ ነው ማስቴ ከኀላችን እየሮጠች ትከተለናለች፡፡ አቤልም ማስቴም "ሰሊ ሰሊ ...."ብለው ይጠሩኛል እኔ ግን ዝም ብዬ መንገዴን ቀጥያለው በድንገት.............

ክፍል 7እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
Channel photo updated
☺️☺️😍😍☺️☺️

.......የሀዘኔ መጨረሻ.......

ክፍል 7

..........መንገዴን ቀጥያለው ... በድንገት ቆም ብዬ "አቤት" አልኳቸው ማስቴ "ምን ሆነሻል ልጁን ልትገይው ነው እንዴ" ብላ እጄን ከአቤል እጅ ላይ አስለቅቃ አቤልን ያዘችው ፡፡ ተንበርክኬ "ውይ አቤልዬ ይቅርታ "አልኩት:: መንገዳችንንም ቀጠልን እቤት እንደደረስን 2 ፖሊሶች እና አንድ ቀን ቤታችን መቶ የቤቱን ካርታ የወሰደውሰውዬ መጡ፡፡በሩን የከፈትኩላቸው እኔ ነበርኩኝ:: "አቤት" አልኳቸው:: ሰውዬው በኩራት "አባትሽ ብሬን በጊዜው ስላልከፈለኝ አሁን ቤቱን አወርሰዋለው" አለኝ::

በመንግስት ደረጃ አራጣ አበዳሪ መሆን ያስቀጣል ግን ለምን ፖሊሶቹ ለምን እንደመጡ አልገባኝም ስገምት በገንዘብ ገዝቷቸው ነው መሰለኝ ::

ከዛ ብዬ ላወራ ስል አንደኛው ፖሊስ ቤቱን" በ 1 ሳምንት ልቀቁ አለበለዛ የማይሆን ነገር ይፈጠራል" አለኝ ፡፡ ከዛ ሶስቱም ሄድ በሩን ዘግቼ በርስር ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ ወድያው አቤል መጣ:: መምጣቱን ሳይ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንባዬን ጠራረኩኝ" አቤልዬ አልኩት"፡፡ "ሰሊ ምነው አለኝ ""ምንም አልሆንኩም አልኩት" "ሰሊ ቤተክርስቲያን እንሂድ "አለኝ ::እኔም እሺ አልኩት ወድያው ለባብሰን ወደ ቤተክርስቲያን ሄድን ፡፡አቤል ለመሳለም ሄደ እኔም ተንበርክኬ "ምን አጠፋን ምን ለምን እንደዚ ታደርጋለህ "እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩኝ ፡፡ አቤል እየሮጠ መጣና "እህቴ እባክሽ ተነሺ" አለኝ፡፡ እኔም ቶሎ ብዬ ተነስቼ ወደ መቀመጫ ቦታው ሄደን ተቀመጥን አቤል "እህቴ እባክሽ እንደዚህ አትሁኚ" ብሎ እቅፍ አደረገኝ:: ማልቀሴን ማቆም አልቻልኩም አታልቅሺ አለኝ ሳቅ እያልኩኝ እንባዬን እንደመጠራረግ አድርጌ "ይኜው ካሁን በኀላ አላለቅስም" አልኩት....

ትንሽ ቁጭ እንዳልን ያ እንዲየውም አንድ ቀን መጥቶ እጄን የያዘኝና ሰዐት የጠየቀኝ ልጅ አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ ፡፡ ብዙም አላስተዋልኩትም ነበር ፡፡ "ሰላም" አለኝ ፡፡ እኔም ዞር ብዬ "አቤት "አልኩት ሳየው ደነገጥኩኝ "ስምሽ ሰላም ነው እንዴ" አለኝ "አው ምነው" አልኩት ፡፡ አይ ምንም ብሎ "እኔ ደግሞ ብሩክ እባላለው" ብሎ እጁን ለሰላምታ ሲዘረጋ አቤልን በል ተነስ አሁን እንሂድ አልኩት፡፡ አቤልም ተነሳ የአቤል ትከሻ ላይ እጄን ጣል አድርጌ ዞር ስል ብሩክ እጁን እንደዘረጋ ነው፡፡" መጨባበጡ አስፈላጊ አይመስለኝም ስለዚህ እጁህን ሰብስበው" ብዬ አቤልን ይዤ ሄድኩኝ፡፡ቀናት እንደጉድ እየፈጠኑ ቤቱን ልቀቁ የተባልንበት ቀን ደረሰ፡፡ ሙሌን ለማግኘት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄድኩኝ፡፡

ናፍቆታችንን ከተወጣን በኀላ ስለ ቤቱ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፡፡ በጣም ደነገጠጠ ከዛ እራሱን ሳተ በመሀከላችን የብረት አጥር ስለነበረ ልይዘው አልቻልኩም ፡፡ "ወይኔ አባቴ" እያልኩኝ መጮህ ጀመርኩኝ ፡፡ ወድያው ፖሊሶቹ አንስተው ወሰድት፡፡ ወደ አንድ ክፍል ነበረ ያስገቡት ተከትያቸው ገባሁኝ ሊያሶጡኝ ሞከሩ አልወጣም አልኳቸው ጉልበት መጠቀም ጀመሩ ወድያው ሙሌ ነቃ ፡፡ ከእጃቸው እራሴን ፈንጥቄ አውጥቼ ሙሌን አቀፍኩት ፡፡" አባ እኔ አልችልም አንተንም ቤዚንም አጥቼ መኖር አልችልም" አልኩት፡፡ በትኩረት እያየኝ "ልጄ እናትሽ ......

ክፍል 8 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ..

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
የሀዘኔ መጨረሻ......


ክፍል 8

......."ልጄ እናትሽ.....የምትለኝን አልሰማሁም ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂው እኔ ነኝ እባክሽ ይቅር በይኝ "አለኝ፡፡ በስስት እየተመለከትኩት "የኔ አባት ምንም አላጠፋህም እኮ" አልኩት:: ወድያው ትንፋሹ መቆራረጥ ጀመረ፡፡" አባ" ብዬ ፊቱን ደባበስኩት ፡፡ አባቴ ጨክኖ የዛን ቀን ወደማይመለስበት ጥሎን ሄደ፡፡ ላብድ ደረስኩኝ እግዛብሄር ምን አድርጌው ይህንን ሁሉ ስቃይ እንዳመጣብኝ ማወቅ ፈለኩኝ ፡፡ ወድያው እራሴን ሳትኩኝ ፡፡

ከነቃሁኝ በኀላ ለመጠንከር ወሰንኩኝ፡፡ የወንድሜ ሀላፊነት አለብኝና ጠንካራ ለመሆን ለራሴ ቃል ገባሁኝ፡፡ ሙሌ ተቀበረ ቤታችንም ሀዘን ላይ ስለነበርን ለ1 ሳምንት ተጨማሪ ጊዜ ሰጡን ፡፡ ሳምንቱም አለቀ ያ ሰውዬ መጥቶ ከቤቱ አሶጣን ፡፡ እንደቀልድ ከተወለድንበት ያ ብዙ ደስታ ካየንበት ቤት ወጣን ፡፡ ስንወጣ የቤዚን እና የሙሌን ፎቶ ብቻ ይዘን ነበር የወጣነው ፡፡ ማስቴ ማልቀስ ጀመረች "በቃ አይዟቹ እኔ አንድ የማውቃት ዘመዴ አለች እሷ ጋር እንሄዳለን" ብላ ይዛን ሄደች፡፡ እዛ ስንደርስ ቤቱ 1 ክፍል ነበር ማስቴ ዘመዴ ያለችው አክስትዋን ነበር በጣም ደግ ናት፡፡ ምግብ ሰጥታን አሳደረችን፡፡ግን እንደዚህ ሊቀጥል እንደማይችል ገባኝ በንጋታው ስራ ለመፈለግ ሄድኩኝ ፡፡ ቀኑን በሙሉ ስዞር ዋልኩኝ ግን ስራ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ አቤልም ተጨነቀብኝ ለኔ ከባድ የህይወት ደረጃ ላይ የደረስኩኝ ያህል ተሰማኝ፡፡

ይህንን ያየች የማስቴ አክስት በጣም አሳዘንናት "በሉ አሁን አንድ ቦታ እንሂድ "አለችን ማስቴም "የት ነው የምንሄደው "አለቻት ፡፡ "አንድ ልብስ የማጥብላት ሴት አለች እና ሰራተኛ ትፈልጋለች፡፡ ደግሞ እነሱም ማረፊያ ያገኛሉ" አለቻት ፡፡ ማስቴ ሳቅ እያለች "አይ አክስቴ ሰሊ እኮ ምንም ስራ መስራት አትችልም "አለቻት ከተቀመጥኩበት ተነስቼ "ችግር የለውም ማስቴ 2 ቀን ሰው ካሳየኝ ሁሉንም ነገር ማድረግ አያቅተኝም" አልኳት ፡፡እሷም" ሰሊ ይሄ ስራ እኮ ላንቺ አይገባሽም" አለችኝ፡፡ኮስተር ብዬ አቤልን እየተመለከትኩት " አቤል አንዴ ውጣ "አልኩት እሱም እየተነጫነጨ ወጣ፡፡ እሱ እንደወጣ የማስቴን እጅ ይዣት "ማስቴ እኔ እኮ ትንሽ ልጅ አይደለሁም ወንድሜን ማስተዳደር ያለብኝ ትልቅ ሴት ነኝ፡፡ "አልኳት አይኗ ውስጥ እንባዎች ተጠራቀሙ "ማስቴ አንቺ እኮ ቤተሰቤ ነሽ ለዛ አይደል እስከዛሬ ያልተለየሽን "ስላት "እንዴት እተዋችኀለው" አለችኝ" እኮ አሁን ዕድል ሲመጣልኝ ፍቀዲና ሸኚኛ" አልኳት እቅፍ አደረገችኝ "ግን ሰሊ እራስሽንም ወንድምሽንም መጠበቅ አለብሽ እሺ" አለችኝ ማስቴ ወደ አክስቷ ዞር አለችና "ግን ሁሉን ነገር እስክትለምደው አብሬያት እሆናለው" አለቻት አክስቷም "ችግር የለውም ሴትየዋን ስለምግባባት እናስፈቅዳታለን" አለቻት፡፡ ትንሽ ቁጭ ካልን በኀላ ወደ ሴትየዋ ቤት ሄድን ፡፡ ቤቱ በጣም ትልቅ ነበር ፡፡ አንኳኳን.....

ክፍል 9 እንዲቀጥል ❤️ ማድረግ አትርሱ...

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
..የሀዘኔ መጨረሻ .....

ክፍል 9

.....አንኳኳን.... የግቢውን በር የከፈተልን የጥበቃ ሰራተኛው ነበር፡፡ ከማስቴ አክስት ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኀላ ወደ ውስጥ ገባን ወድያው የቤቱ ባለቤት መጣች ፡፡ የማስቴን አክስት በግርምት እየተመለከተቻት ''እንዴት ዛሬ መጣሽ አለቻትጠ'' የማስቴ አክስትም የመጣችበትን ጉዳይ ነገረቻት፡፡ ከዛ ወደ ውጪ እንነጋገር አለቻት፡፡ ካወሩ በኀላ ተመልሰው መጡ፡፡ ሴትየዋ እጄን እንደመጨበጥ አያለች "ኤልሳ እባላለው "አለችኝ ፡፡ እኔም እራሴንና አቤልን አስተዋወቅኩዋት፡፡ ''ዘነቡ ሁሉንም ነገር ነግራኛለች አይዟቹ አሺ" አለችን፡፡ እኔም እሺ አልኳትና እጄን የአቤል ትከሻ ላይ ጣል አደረኩት፡፡ ዘነቡ ማለት የማስቴ አክስት ናት፡፡

ትንሽ ቁጭ ካልን በኀላ ዘነቡ በይ ማስቴ ተነሺ እንሂድ" አለቻት፡፡ ማስቴም "እንዴ አክስቴ ግን እኮ"ብላ ልታወራ ስትል ወ/ሮ ኤልሳ "መስታወት ሁሉን ነገር ዘነቡ ነግራኛለች አይዞሽ እኔ አለው "አለቻት፡፡ ማስቴ በሀሳቡ ባትስማማም ግን ምንም ማድረግ ስላልቻለች እኔንና አቤልን ተሰናብታ ከአክስቷ ጋር ሄደች፡፡ወ/ሮ እስከግቢው በር ድረስ ሸኘቻቸው፡፡ ወደ እኛ ጋር መጥታ እኔና አቤል የምንናልፍበትን ክፍል አሳየችን ፡፡ በመቀጠል የስራ ድርሻዬን መዘርዘር ጀመረች፡፡

"ጠዋት ከእንቅልፍሽ 12 ሰዐት ትነሻለሽ ከብርቄ ጋር ቁርስ ትሰሪያለሽ " ብርቄ ማለት እነሱ ቤት የምትሰራ የቤት ሰራተኛ ናት፡፡ ከዛ ብላ ትዕዛዝዋን ቀጠለች፡፡ "ልጄን መኝታ ክፍሉ ሄደሽ ትቀሰቅሺዋለሽ እሱ ከመኝታ ክፍሉ እንደወጣ ክፍሉን በደንብ ታፀጃለሽ፡፡ በመቀጠል እኛ ቁርስ ልንበላ ወደ ማዕድ ቤት ስንሄድ የኔና የባለቤቴን መኝታ ክፍል ታፀጃለሽ፡፡እሱን እንደጨረሽ ከብርቄ ጋር ሆናችሁ እቃውን አጣጥባቹ ቤቱን በደንብ አስተካክላቹ እንደጨረሳቹ ምግባቹን ትበሉና አንቺ ከዘበኛው ጋር ገበያ ሄደሽ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ገዛዝተሽ ትመጫለሽ፡፡ እዚህ ቤት ምሳ ብዙም አይደለንም ብሩኬ ት/ቤት ይዞ ይሄዳል ባለቤቴ ደግሞ ውጪ ነው የሚበላው ስለዚህ ምሳ ሰዐት ላይ ብዙም ስራ አይበዛብሽም" አለችኝ ብሩኬ ያለችው ልጆን ነው፡፡

" ከሰዐት በኀላ ብዙም ስራ የለም ግቢውን ታፀዳጃለሽ ከዛ 11 ሰዐት አካባቢ ብርቄን የሚታገዝ ነገር ካለ ታግዢያትና እረፍት ታረጊያለሽ ከዛ እራትሽን በላልተሽ ትተኛለሽ" አለችኝ፡፡ እኔም በእሺ ስሜት አንገቴን ነቀነቅኩላት፡፡ "በይ እሺ ለዛሬ ከብርቄ ጋር ሁኚ " ብላ የኩሽናውን በር አሳየችኝ እሺ ብዬ ልሄድ ስል "ሰላም" አለችኝ እኔም ዞር ብዬ "አቤት" አልኳት "እንግዲ.........

ክፍል 10 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ
....የሀዘኔ መጨረሻ .......

ክፍል 10

......ዞር ብዬ "አቤት" አልኳት "እንግዲህ.....ደሞዝሽ 1500 ብር ነው፡፡ ወንድምሽን እኔ አስተምረዋለው አታስቢ" አለችኝ፡፡ የማደርገው ግራ እንደገባኝ "እሺ" ብያት ሄድኩኝ ፡፡ ግን በቀን ውስጥ የምሰራውን ስራ ሳስበው በጣም እንደሚከብደኝ ተረዳሁኝ፡፡ ግን ለአቤል ብዬ መስራት አለብኝ አልኩና እራሴን አፅናናሁኝ፡፡

ሰዐቱ 12:30 ይሆናል ወ/ሮ ኤልሳ እኔንና አበራ ወደ ገበያ ላከችን፡፡ እኛም ሄድን ግን ታክሲ አጥተን ስለነበር ከምሽቱ 3 ሰዐት ነበር የተመለስነው የግቢውን ቀር ከፍተን እንደገባን ወ/ሮ ኤልሳ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ "ለምንድን ነው በዚህ ሰዐት የመጣችሁት አንደኛችሁን አታድሩም ነበር" አለችን፡፡ አበራም " ታክሲ አጥተን ነው እኮ እሜቴ" አላት፡፡አበራ ማለት የቤቱ ዘበኛ ነው፡፡ እኔ ግን አንገቴን ዘቅዝቄ ዝምታን መረጥኩኝ ወ/ሮ ኤልሳ እየተኮሳተረች "በይ አሁን ወደውስጥ ገብተሽ እራትሽን በልተሽ ተኚ ነገ ብዙ ስራ ይጠብቅሻል" አለችኝ ፡፡እኔም አንገቴን እ! ዳቀረቀርኩኝ "እሺ" ብያት ገባሁኝ፡፡ ቀጥታ ወደ መኝታ ክፍሌ ነበር የገባሁት የእውነት ቀዛ ሰዐት ማልቀስ ፈልጌ ነበር፡፡ ግን ፊትለፊቴ አቤል ተኝቶ ሳየው እና የቤዚ ቃል ትዝ ሲለኝ አቤልዬን እቅፍ አድርጌው ተኛው፡፡

በለሊት ብርቄ መጥታ ቀሰቀሰችኝ እኔም ተነስቼ ምግብ ቀመስራት አገዝኳት ...ከዛ የወ/ሮ ኤልሳን ልጅ ለመቀስቀስ ወደ መኝታ ክፍሉ ሄድኩኝ ፡፡ ..ስገባ በጣም ደነገጥኩኝ ያ እንዳውም ሁለት ጊዜ ቤተክርስቲያን አግኝቼው ሊያዋራኝ ፈልጎ ጥዬው የሄድኩት ልጅ ነበር፡፡ በፍጥነት ከክፍሉ ወጣሁኝ በሩ ጋር ቆሜ ተገረምኩኝ፡፡ በፍጥነት ወደ መክታ ክፍሌ ሄጄ ሻርፕ ኮፍያ ያለው ሹራብ ምናምን አድርጌ ተመልሼ ብሩክን ለመቀስቀስ ወደ ክፍሉ አመራሁኝ፡፡ ቀሰቀስኩት መነሳቱን እንዳረጋገጥኩኝ ከክፍሉ ልወጣ ስል .... እጄን ያዘኝ እኔም የለበስኩትን ሻርፕ አስተካክዬ ወደሱ ዞርኩኝ "አቤት " አልኩት እሱም ማነሽ አለኝ ፡፡ ፊቴን እየሸፋፈንኩኝ "አዲስዋ የቤት ሰራተኛ ነኝ" አልኩት፡፡ እጄን ለቀቀኝና እጁን በቀሽም ስሜት ፀጉሩ ላይ ጣል አድርጎት "ይቅርታ ማም ነግራኝ ነበር ፡፡ በጣም ይቅርታ " አለኝ፡፡ እኔም " እሺ" ብዬው ብዬ ከክፍሉ ወጣሁኝ ፡፡ ከክፍሉ እንደወጣሁኝ ተሰምቶኝ የማያውቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡

በመቀጠል ትላንት ወ/ሮ ኤልሳ ስትዘረዝርልኝ የነቀረውን ስራ ወስራት ጀመርኩኝ፡፡ ወደ ምግብ መመገቢያው ክፍል ልገባ ስል ብሩክ እንደሚያውቀኝ ትዝ ሲለኝ ወደ ውስጥ መግባት ደበረኝ፡፡ ውጪ ቁጭ አልኩኝ ፡፡ አቤል ከእንቅልፉ ተነስቆ ዩኒፎርሙን ለብሶ ወደኔ መጣ ፡፡ "የኔ ቆንጆ በጣም አምሮብሀል" ብዬ እቅፍ አደረኩት፡፡ ወድያው ብርቄ መጣችና ወ/ሮ ኤልሳ እየጠራቺኝ መሆኑን ነገረችኝ ፡፡ መሄድ አልፈለኩም ነበር ግን ግድ ስለሆነ አቤልን ይዤው ወደ ምግብ መመገቢያው ክፍል አመራሁ፡፡ ልክ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁኝ ወ/ሮ ኤልሳ "ውይ መጣቹ ኑ ልጄንና ባለቤቴን ተዋወቁዋቸው " አለችን ፡፡ እኔም ወደ ጠረቤዛው ቀረብ አልኩኝ ብሩክም እኛን ለማየት ዞር አለ .........


ክፍል 11 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ .....
....የሀዘኔ መጨረሻ......

ክፍል 11

.....ብሩክም እኛን ለማየት ዞር አለ ....ሲያየን በጣም ደነገጠ የሱ ሲገርመኝ የወ/ሮ ኤልሳም ባለቤት በትኩረትና በትዝብት ይመለከቱን ጀመር፡፡ ...... ትንሽ ከተፋጠጥን በኀላ የወ/ሮ ኤልሳን ባለቤት አጠገቡ ሄዴ እጄን ለሰላምታ ዘርግቼ " ሰላም እባላለው "አልኳቸው እሳቸውም እጄን ለመጨበጥ እየተጣደፉ "ሰላም እንዴት ነሽ " አሉኝ፡፡ እኔም "ደህና " አልኳቸው ፡፡ አቤልን "ና የኔ ልጅ " ብለው አገላብጠው ሳሙት፡፡ ዞር አልኩኝና እጄን እንደመዘርጋት እያልኩኝ ብሩክን " ሰላም እባላለው አልኩት"እሱም እጄን ይዞኝ በሀሳብ ነጎደ ቶሎ ብዬ እጄን ከእጁ ላይ መነጨቅኩት

የወ/ሮ ኤልሳ ባለቤትም "እኔ ሄኖክ " እባላለሁኝ አሉን፡፡ እኔም ፈገግ ብዬ አቤልን ይዤ ልወጣ ስል አቶ ሄኖክ "ይቅርታ ሰላም " አሉኝ እኔም ሊያዙኝ መስሎኝ ዞር ብዬ "አቤት " አልኳቸው ፡፡ " ባልሳሳት የኮንስትራክሽን ባለሞያው የሙሉጌታ ልጆች ናችሁ አይደል " አሉን፡፡ ይህን ስሰማ አባቴ ትዝ ብሎኝ ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ አቤልም አለቀሰ ከትንሽ ደቂቃዎች በኀላ እንባዬን እየጠራረኩኝ በኩራት "አዎ" አልኳቸው፡፡ አቶ ሄኖክም " ስለ ሙሉጌታ ሁሉንም ነገር ሰምቻለው እንደውም ላፈላልጋቹ ነበር "አሉን፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ወደ አቶ
ሄኖክ ዞር እያለች " ለምንድን ነው ልታፈላልጋቸው የነበረው ውዴ " አለቻቸው ፡፡ " የአባታቸው አደራ አለብኝ " ብለው ፈገግ አሉ፡፡ ብሩክ አሁንም ደንግጦ አፉን ከፍቶ እየተመለከተን ነው ፡፡ እኔም ባላየ ባላወቀ ማለቴን ቀጥያለው፡፡ ቁርስ አብረናቸው እንጅንበላ አቶ ሄኖክ ጋበዙን፡፡ እኔና አቤልም አሻፈረን አልን ፡፡

ኮስተር ሲሉብን አብረናቸው መመገብ ጀመርን፡፡ የተቀመጥኩት ከብሩክ ፊት ለፊት ነበር፡፡በጣም ጨነቀኝ ብሩክም ቁርሱን ትቶ እኔን በዝምታ ማየቱን ቀጥሎል፡፡ እያየኝ መሆኑን ለማወቅ ቀና ስል አይን ለአይን እንገጣጠማለን በፍጥነት አይኔን ከአይኖቹ ነጥዬ ምግቡነ መመልከት እጀምራለው፡፡ ከትንሽ ደቂቃዎች በኀላ ወ/ሮ ኤልሳ ብሩክን "በላ የኔ ልጅ እንዳይረፍድብህ ሂድ" አለችው ፡፡ እሱም እኔ ላይ እያፈጠጠ ማም ዛሬ ክላስ አልሄድም" አላት፡፡ ከመቀመጫዋ ተነስታ የብሩክን ጭንቅላት እየነካካች በድንጋጤ "ምነው ልጄ አመመክ እንዴ " አለችው ፡፡ አይኑን ሰበር አድርጎ " አይ ትንሽ ስለደበረኝ ነው " አላት፡፡ አቶ ሄኖክም " በቃ ተይው ውዴ ዛሬ እረፍት ያድርግ "አሏት፡፡ "እሺ በቃ" ብላ ተቀመጠች፡፡

ወድያው አቶ ሄኖክ ከመመገቢያ ክፍሉ ወጡ፡፡ እኔም እቃውን ለማነሳሳት ተነሳሁኝ፡፡ አቶ ሄኖክ ብቅ ብለው "ሰላም እሱን ተይውና አንዴ ነይ እፈልግሻለው " አሉኝ፡፡ እኔም " እሺ" ብዬ ሄድኩኝ፡፡

ከብሩክ አጠገብ ያለ ክፍል ውስጥ አስገብተውኝ...........

ክፍል 12 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ
..........የሀዘኔ መጨረሻ......

ክፍል 12

........ክፍል ውስጥ አስገብተውኝ ....." እኔ የአባትሽ ጓደኛ ነኝአይዞሽ እኔ አለሁላቹ አባትሽ እንድንከባከባቹ ቃል አስገብቶኝ ነበር ስለዚህ አብራቹ እዚ ከኛ ጋር ትኖራላችሁ፡፡ ደግሞ ትምህርትሽን እንዳቋረጥሽ ማታ ኤልሲ ነግራኛለች እና አሁን ትቀጢዋለሽ ብሩኬ የሚማርበት ት/ቤት ትገቢያለሽ " አሉኝ ፡፡ እውነት ለመናገር አቶ ሄኖክ እንደዛ ሲሉኝ በቃላት ልገልፃቸው የማልችለው ስሜት ተሰማኝ፡፡ ትንሽ ከቆየሁ በኀላ ቀና ብዬ " እና ለምን ለአባቴ ለቅሶ እቤት መጥተው አላፅናኑንም " አልኳቸው ፡፡ አቶ ሄኖክም " የኔ ስራ ፊልድ ነው እና ብዙ ጊዜ እዚህ ሀገር አልገኝም ለዛነው እና ለናትሽም ለቅሶ ጊዜ አልመጣሁም እና ይቅርታ አድርጊልኝ " አሉኝ፡፡ ፊት ለፊት የሚገኘው ወንበር ላይ ቁጭ ብለው በሀዘን ተውጠው "አባትሽ እስር ቤት አስጠረቶኝ ነበር....አው ከማረፉ ከ 2 ቀን በፊት አስቀድሞ የኔ ውድ ጓደኛ መሞቱ ታውቆት ነው መሰለኝ " ልጆቼን አደራ ....አደራ ሲለኝ ነበር ፡፡ ከዛ እኔ በንጋታው ወደ ሌላ ሀገር ለስራ ሄድኩኝ ፡፡ መሞቱን የሰማሁት እራሱ እዚህ ከመጣሁኝ በኀላ ነው " አሉኝ ፡፡ ሳላስበው እንባዬ ድብ ድብ አሉ፡፡


ከተቀመጡበት ተነስተው አጠገቤ ቁጭ አሉ ደረታቸው ላይ ለጥፈውኝ "እኔ እንደ አባትሽ ልሆንልሽ አልችል ይሆናል ግን እንደ አባትሽ እይኝ ምክንያቱም እኔ እንደ ልጄ ነው የማይሽ " አሉኝ፡፡ እቅፍ አደረግኳቸው፡፡

ወደ ማዕድ ቤት ተመለስን ብሩክ አቤልን ጉልበቱ ላይ አስቀምጦ ስልኩን ሰጥቶት ጌም እያጫወተው ነበር፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ደግሞ ቡና እየጠጣች ነበር ፡፡ አቶ ሄኖክ ወ/ሮ ኤልሳን " ውዴ አንዴ ነይ "አሉዋት፡፡ተነስታ ሄደች፡፡

አቤልም ት/ቤት ስለረፈደበት የብሩክ ሹፌር ወደ ት/ቤት ይዞት ሄደ፡፡ በፍጥነት ተነስቼ ቁርስ የበላንበትን እቃዎች ላነሳሳ ስል ብርቄ መጥታ " ተይው እኔ አነሳሳዋለው ጋሼ ምንም እንዳትሰራ ብለውኛል " ብላ እጄ ላይ ያለውን ሰሀን ተቀበለችኝ ፡፡ እኔም እሺ አልኳት፡፡ ማዕድ ቤቱና ሳሎን ቤቱ ብዙም አይራራቅም፡፡ ብሩክ ሳሎን ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ እያየኝ ነበር፡፡ ከዛ በአይኖቹ ነይ አለኝ፡፡ እኔም ሄጄ ሶፋው ላይ ቁጭ አልኩኝ፡፡

ሁለታችንም መነጋገር ፈልገናል ግን ፈርተናል የተቀመጥኩት ፊት ለፊቱ ስለነበር በጣም ጨነቀኝ የሆነ እንከን ያለብኝ ይመስል ተርበተበትኩኝ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኀላ "አስታወስሽኝ " አለኝ፡፡ እኔም በአዏንታ አንገቴን ነቀነቅኩለት፡፡ የሆነ እንግዳ ስሜት ተሰማኝ ፡፡

ወድያው ወ/ሮ ኤልሳ እየተፍለቀለቀች መጣች፡፡ "ሰላም" አለችኝ ከመቀመጫዬ ተነስቼ "አቤት " አልኳት፡፡ ፈገግ እያለች " ነይ" አለችኝ፡፡ አቶ ሄኖክ ወደ ብሩክ ጠጋ ብለው ትከሻውን መታ መታ እያደረጉ " ሰላምን ተንከባከባት እሷ ማለን ......" ብለው ጀመሩለት፡፡ እኔና ወ/ሮ ኤልሳ ወደ ላይኛው ክፍል ሄድን፡፡ ይመስለኛል ..........

ክፍል 13 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ
..የሀዘኔ መጨረሻ......

ክፍል 13

ሄድን፡፡ ይመስለኛል ........አቶ ሄኖክ እና ወ/ሮ ኤልሳ ስለ ህይወታችን ነበር ሲያወሩ የነበረው፡፡ እኔና ወ/ሮ ኤልሳ አቶ ሄኖክ አስገብተውኝ ወደነበረው ክፍል አስገባችኝ ፡፡ ቅድም ደንግጬ ስለነበር የክፍሉን ውበት አላየሁትም ነበር ግን አሁን ሳደው በጣም ያምራል፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ፍልቅልቅ እያለች " የምታርፊበት ክፍል ይሄ ነው የወንድምሽም ክፍል ከጎንሽ ያለው ክፍል ነው ማለቴ በስተግራ ያለው< ብላ በእጅዋ ጠቆመችልኝ፡፡ ወድያው ከክፍሉ ወጣች፡፡ ተመልሳ መጥታ "የብሩኬ ክፍል በቀኝ በኩል ያለው ነው የሚቸግርሽ ነገር ካለ ጠይቂው" ብላኝ ሄደች፡፡ በጣም ደስ አለኝ ፈጣሪ ከላይ ሆኖ እንዳየኝ ተሰማኝ፡፡

በሩን ዘጋ አድርጌ አልጋው ላይ ጋደም አልኩኝ፡፡ ትንሽ የሰላም እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ከክፍሉ ልወጣ ስል ብርቄ ሻንጣዬን ይዛልኝ መጣች፡፡ ቶሎ ብዬ ከሻንጣው ውስጥ የቤዚን እና የሙሌን ፎቶ አውጥቼ በፈገግታ መመልከት ጀመርኩኝ፡፡ ወደላይ ቀና ብዬ" ፈጣሪዬ እንደዛ እንዳላዘንኩኝ አሁን ደስታው በተራው ተፈራረቀብኝ ተመስገን" አልኩት፡፡ ምግብ ክፍሌ ድረስ መጣልኝ እሱን በልቼ ሰሀኑን ለመመለስ ወደ ኩሽና አመራሁ ሳላስበው ከብሩክ ጋር ተጋጭተን ወደቅኩኝ " ውይ አላየሁሽም ነበር በጣም ይቅርታ "ብሎ አነሳኝ፡፡ እኔም ቆፍጠን ብዬ "ምንም አይደል " አልኩት፡፡ መንገዴንም ቀጠልኩኝ፡፡ እጄን ያዘኝ ዞር አልኩኝ፡፡ አይኖቹ በጣም ያምራሉ አፈጠጥኩባቸው "ስለ ቤተሰቦችሽ ስለ ሁሉም ነገር ዳድ ነግሮኛል አይዞሽ" አለኝ፡፡ አይኔን ከአይኖቹ መንጭቄ "አመሰግናለው " አልኩት፡፡ ፊልም አብረን እንድናይ ጋበዘኝ እኔም ትንሽ ከተግደረደርኩኝ በኀላ ግብዣውን ተቀበልኩኝ፡፡

ወደ ኩሽና ሄዶ ቺብስ ይዞ መጣ መብራቱን አጠፋፍተን ማየት ጀመርን፡፡ አጠገብ ለአጠገብ ነበር የተቀመጥነው እውነት ለመናገር ፊልሙን አየው ማለት አይቻልም እሱም ያየ አይመስለኝም፡፡ሁለታችንም እየሰረቅን ስንተያይ በልባችን ደግሞ ስናወራ ነበር፡፡ ፊልሙ አለቀ አቤልም ከት/ቤት ተመልሶ መጣ ፡፡ አቶ ሄኖክ እና ወ/ሮ ኤልሳ ያደረጉልንን ሲመለከት በጣም ደስ አለው፡፡ እሱ ስለተደሰተ የኔ ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡አቤል እና ብሩክ በጣም ተግባብተዋል አብረው ጌም ኳስ መጫወት ነው ስራቸው፡፡


በንደዚ አይነት ሁኔታ ለ3 ወር ኖርን፡፡ በአንድ እሁድ ቀን የጥቁር ልብሴን እንዳወልቀው አቶ ሄኖክና ወ/ሮ ኤልሳ ኮስተር ብለው ነገሩኝ፡፡ እኔም ሀዘኔን ለመግታች ወስኜ ጥቁር ልብሴን አወለቅኩኝ ፡፡ እናትና አባቴንም ያገኘሁኝ ያህል ተሰማኝ፡፡

አቶ ሄኖክ ስራቸው ፊልድ ነው እና ብዙም ጊዜ እቤት አይገኙም እኔና ብሩክም ከ3 ወር በፊት እንደነበርነው አይደለንም በጣም ተግባብተናል፡፡ ት/ት ቤታችንም አንድ ላይ ስለሆነ ተለያይተን አናውቅም፡፡ ብሩክ 12 ክፍል ሲሆን እኔ ደግሞ 11 ነኝ ስለዚህም በጣም ተግባብተናል፡፡

የት/ት አመት ግማሽ ላይ ደረስን፡፡ እናም እረፍት ወጣን፡፡ አቶ ሄኖክ እንደ ሁል ጊዜው ፊልድ ላይ ናቸው፡፡

እረፍት ከወጣን ከ 2 ቀን በኀላ የወ/ሮ ኤልሳ ወንድም ከጠዋቱ 3 ሰዐት አካባቢ መጣ.........

ክፍል 14 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ
የሀዘኔ መጨረሻ....
☺️☺️😍😍☺️☺️

ክፍል 14

.......3 ሰዐት አካባቢ የወ/ሮ ኤልሳ ወንድም መጣ፡፡ እናም ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ "ይልማ እባላለው" አለኝ፡፡ እኔም የውሸት ፈገግታ ፊቴ ላይ ጣል እያደረግኩኝ "እኔ ደግሞ ሰላም እባላለው" አልኩት፡፡ ሲጀመር ይልማን ቀልቤ አሎደደውም ይሄን ደግሞ ብሩኬ አውቋል፡፡ ግን ግድ ስለሆነብኝ ቁጭ አልኩኝ ከትንሽ ቆይታዎች በኀላ ይጨንቀኝ ጀመር፡፡ ይልማ በሚያስጠላው ፊቱ ፈገግ ሲልብኝ የምሰራው ስራ አለ ብዬ ተነስቼ ወደክፍሌ ሄድኩኝ፡፡ ብሩኬም ተከትሎኝ መጣ፡፡ " ሰሊ አጎት ተብዬውን አልወደድሽውማ" አለኝ ፡፡ በአዎንታ አንገቴን ነቀነቅኩለት፡፡ በፈገግታ እያየኝ ግንባሬን ስሞኝ ወጣ፡፡ ወዱያው አቤል መጣና video game መጫወት ጀመርን፡፡

ከዛን ቀን ጀምሮ ይልማ እቤት ይመላለስ ጀመር፡፡ በቀን2 3 ጊዜ መምጣት ጀመረ፡፡ እኔም በራስ መተማመኔ እየተመናመነ ሄደ፡፡ ጭራሽ ወደ ክፍሌ እየወጣ በኩራት "ሰላም እንዴት ነሽ" ይል ጀመረ፡፡ እኔም እየተሳቀቅኩኝ "ደና" እለዋለው፡፡ የኔና የብሩክ ክፍል አጠገብ ለአጠገብ ስለነበረ ድምፅ ያሰማል ብሩክ የይልማን ድምፅ ሲሰማ ወድያው ይመጣል፡፡ ይልማ ብሩክ መምጣቱን ሲመለከት በፍጥነት ይሄዳል፡፡ ብሩክም ይልማ እንደማይመቸው ሁኔታዏች ያሳብቃሉ፡፡ ብዙን ጊዜ የማሳልፈው ክፍሌ ነው፡፡

ቅዳሜ ቀን ጠዋት አካባቢ ነበር ....አቤልና ብሩኬ ሳይክል ለመንዳት ወጥተው ነበር፡፡

ይልማም እንደ ሁል ጊዜው በጠዋት ነው የመጣው፡፡ ይልማ እንደመጣ ወ/ሮ ኤልሳ ብርቄን ጠርታት ወደገበያ ሄድ፡፡ በቤቱ ውስጥ የነበርነው እኔና ይልማ ብቻ ነበርን፡፡ከክፍሌ እንደወጣሁኝ ይልማን አገኘሁት፡፡ እየተርበትበትኩኝ ሰላም አልኩት፡፡ እሱም ሰላምታ ሰጠኝ፡፡ ቶሎ ብዬ ወደ ታች ወረድኩኝ፡፡ ታች ስወርድ ማንም አልነበረም፡፡ እሱም ተከትሎኝ መጣ፡፡ በፍርሀት "ማንም የለም እንዴ" አልኩት፡፡ እሱም እየተጠጋኝና እየሳቀ "አ.....ው ማንም የለም" አለኝ፡፡ ፈርቻለው ግን ፍርሀቴ እንዲታወቅብኝ አልፈለኩም ነበር፡፡ ፈገግ ብዬ "እሺ" አልኩትና እየሮጥኩኝ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ ክፍሌንም ቆለፍኩት፡፡

ከ5 ደቂቃ በኀላ የክፍሌ በር ተንኳኳ፡፡ በድንጋጤ "ማነው" አልኩኝ፡፡ "ይልማ ነኝ ክፈቺልኝ" አለኝ፡፡ እየተንቀጠቀጥኩኝ ሆዴን አሞኛል ልተኛ ነው" ስለው በቁጣ ስሜት "ክፈቺ ብዬሻለው አለበለዚያ በሩን እሰብረዋለው" አለኝ፡፡ በጣም ፈራሁ መልስም አልሰጠሁትም ፡፡ በሩን ለመክፈት ትግል ጀመረ የማደርገው ጠፍቶኝ አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩኝ፡፡ ከብዙ ትግል በኀላ ክፍሌን ሰብሮት ገባ፡፡ በአን እጁ ቢራ በአንዱ ደግሞ ቢላ ይዞ ነበር ፈገግ እያለ "... ዛሬ .....ብቻችንን ተገናኘን አይደል ቆንጂዬ .....አለን፡፡ ከክፍሉ ለመውጣት ስሞክር ገፍትሮ አልጋው ላይ ጣለኝ፡፡ መጮህ ጀመርኩኝ ፡፡ እየታገለ ሱሪዬን በያዘው ቢላ መቆራረጥ ጀመረ፡፡ እያለቀስኩኝ ተወኝ አልኩት እሱ ግን ጭራሽ የያዘውን ቢራ እላዬ ላይ ማፍሰስ ጀመረ..........

ክፍል 15 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ


Any comments inbox @Juliiian
የጥቁር ህዝቦች ድል...!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት እየተወረሩ በነበረበት ጊዜ ሁሉም የአፍሪካ ህዝቦች እንደ ባሪያ በሚቆጠሩበት ሰዓት በጣሊያን ተወረረች።

በየካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ም ጣሊያን ኢትዮጵያን ወረረች የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት አጤ ሚኒሊክ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለቤተሰቡ , ለሀይማኖቱ እና ለሀገሩ ሲል መሳሪያውን ይዞ እንዲመጣ እና የማይመጣ ካለ ከእርሳቸው ጋር የመጨረሻው እንደሆነ በማርያም ስም እየማሉ ተናገሩ።

የወቅቱ የአጤ ሚኒሊክ ባለቤት የነበሩት እቴጌ ጣይቱ ሴትነቴን ሳይሉ ሀገራቸው ተደፍራ ዝም እንደማይሉ ተናገሩ።

የአጤ ሚኒሊክን ጥሪ የሰማው በሀገሩ ጉዳይ የማይደራደረው የኢትዮጵያ ህዝብም በ1888 የካቲት 21 ወደ አድዋ ተራራ ለመሄድ ቢያስብም በዝናቡ ምክንያት ይህን ማድረግ ስላልቻለ ክንዱን ሳይተራስ የካቲት 22 1888 ዓ.ም ወደ አድዋ ተራራ ማምራት ጀምሮ ለሊቱን ሙሉ ተጉዞ የካቲት 23 አድዋ ተራራ ደረሰ።

የንጋት ጮራ እንፈነጠቀ ኢትዮጵያ በጀነራል አሉላ እየተመራች የአድዋ ጦርነት ተጀመረ ምድር ድብልቅልቅ አለች ጦርነቱም ቀጥሎ ንጋት 4 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ድል ማድረጓ ተሰማ ፤ ንጋት 5 ሰዓት ኢትዮጵያ የጣሊያንን ወታደሮች ሙሉ ለሙሉ መማረኳ ተሰማ።

አድዋ በዛሬው እለት ለ126ኛ ጊዜ የአጤ ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በደማቅ ሁኔታ በመላው ኢትዮጵያዊያን ይከበራል።

- ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ

ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤

- ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ

መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ፤

- የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው

ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው

ለአድዋ ከተገጠሙ ግጥሞች ዋነኞቹ ናቸው።

ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
ክፍል 15

.....የያዘው ቢራ እላዬ ላይ ማፍሰስ ጀመረ..... እኔም መጮኄንና ማልቀሴን ቀጥያለው ፡፡ ያደረኩትን ሱሪ ሙሉ ለሙሉ አወለቀው፡፡ ወንድነቱን እና ጉልበቱን ተጠቅሞ ሊደፍረኝ ሞከረ፡፡በድንገት ዞር ስል ብሩክ ክፍሌ በር ላይ ቆሟል፡፡ አይኖቹ እንባ አቅርረው በንዴት ደርቆ ቆሞል፡፡ እያለቀስኩኝ "ብሩክ አድነኝ! አድነኝ" አልኩት፡፡ ቶሎ ብሎ ይልማን ከላዬ ላይ አነሳው በቦክስም ደጋግሞ መታው ይልማም ሰነዘረበት እዛው ድብድ ጀመሩ፡፡ እኔም ቶሎ ብዬ ሱሪ ለበስኩኝ፡፡ ለብሼ ዞር ስል ብሩክን አስተኝቶ አየመታው ነበር፡፡ በድንጋጤ በቢራ ጠርሙሱ አንገቱን መታሁት፡፡ እራሱን ስቶ ወደቀ፡፡ ጠርሙሱን መሬት ላይ ጥዬው ማልቀስ ጀመረኩኝ፡፡ብሩኬም አቅፎኝ ያባብለኝ ጀመር፡፡ ወድያው አቤል መጣ.. ብሩኬም በፍጥነት ወደታች እንዲወርድ ጠየቀው እሱም ደንግጦ በፍጥነት ወረደ፡፡ "ብሩኬ ሊደፍረኝ ነበር እኮ .......ሊያበላሸኝ " እያልኩኝ ማልቀሴን ቀጠልኩኝ ደረቱ ላይ አስተኝቶኝ ማባበሉን ቀጠለ፡፡

ከትንሽ ደቂቃ በኀላ ወ/ሮ ኤልሳ መጣች፡፡ ወንድሟ ደም በደም ሆኖ መሬት ላይ ስታየው አበደች የምትይዘው የምትጨብጠው ነገር ጠፋት፡፡ ዞር ስትል ብሩኬም ፊቱ ደምቷል፡፡ "ምን ሆነው ነው ማነው እንደዚ ያደረጋቸው ወይኔ ኤልሳ!"ብላ ማልቀስ ያዘች፡፡ ወዲያውኑ ታክሲ ጠርታ ወደ ሀኪም ቤት ይልማንም ብሩኬንም ይዛቸው ሄደኝ፡፡ እኔም ለብሩኬ ብዬ አብሬያቸው ሄድኩኝ፡፡

ሆስፒታል እንደደረስን ይልማ ነቃ፡፡ እኔ እንደዚ እንዳደረኩትና ብሩክም እንዲመታው እንዳደረኩኝ ነገራት፡፡ የዛን ቀን የወይዘሮ ኤልሳ አይኖች በጣም ያስፈሩ ነበር፡፡ ተኮሰታትራ "በይ እቤት ሄደሽ ጠብቂኝ "አለችኝ፡፡ ብሩኬም "ይኘው የኔም ቁስል ስለታሸገልኝ ከሷ ጋር አብሬ እሄዳለው" አላት፡፡ እኔና ብሩኬ ወደቤት ሄድን፡፡ ከ 2 ሰዐታት በኀላ ወ/ሮ ኤልሳ መጣች፡፡ ወገብዋን ይዛ "አንቺ የማትረቢ ማን ስለሆንሽ ነው ወንድሜን እንደዛ ያደረግሽው ሁሉን ነገር ስናሟላልሽ ምነው ወጥ ረገጥሽ" አለችኝ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ "ይኘውልሽ" ብዬ ወሬ ልጀምር ስል "በቃሽ ያ ወንድምሽን ይዘሽልኝ ከቤቴ ውልቅ በይ" አለችኝ፡፡ እንባዏቼ ወረድ የምናገረው ነገር ጠፋኝ ደርቄ ቀረሁኝ፡፡ "በያ ቶሎ በይ ከቤቴ ውጪ" አለችኝ፡፡ ይሄን ሁሉ ስትናገረኝ ብሩኬ ክፍሉ እቃ ሊያመጣ ሄዶ ነበር፡፡

አቤልን ጠርቼው ልብሳችንን መሰብሰብ ጀመርን፡፡ ከቤት ልንወጣ ስንል ብሩኬ ወዴት ነው አለኝ፡፡ ወ/ሮ ኤልሳም ሁሉንም ነገር ነገረችው፡፡ እጄን ይዞኝ "ማም እነሱ ከዚ ከሄድ እኔም እዚህ አልኖርም" አላት፡፡ "ብሩኬ አንተ እዚህ ነገር ውስጥ አትግባ ወደክፍልህ ሂድ" አለችው፡፡ "ማም አትፈልጊኝም!" አላት፡፡"እንዴት ነው የማልፈልግ" አለችው፡፡"እንግዲያውስ እኔ እዚህ ቤት እንድቆይ እነሱም እዚህ መሆን አለባቸው" አላት፡፡ "አይሆንም እነሱ እዚህ ቤት አንድም ቀን አያድሩም" አለችው፡፡ ከብሩክ እጅ ላይ እጄን መንጭቄ አቤልን ይዤ ከሳሎን ወጣን፡፡ ብሩክም ተከትሎን ወጣ፡፡ " አንዴ ላናግርሽ " አለኝ እኔም "እሺ አልኩት፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ በመስታወት እያየችን ነበር፡፡ ብሩክ ወደ ጓሮ ሄደን እንድናወራ ጋበዘኝ፡፡ ወደ ጓሮ ሄድን፡፡ "ምንድን ነው ብሩክ" አልኩት፡፡ "የትም አትሄዱም እዚሁ ትኖራላችሁ" አለኝ፡፡ ፈገግ እያልኩኝ "አይሆንም ከዚህ በኀላ እንድናስቸግራቹ አንፈልግም " ብዬ ጥዬው ልሄድ ስል እጄን ጎትቶ ከንፈሬን ሳመኝ..........

ክፍል 16 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ

CONTACT US💐....
ክፍል 16

.........እጄን ጎትቶ ከንፈሬን ሳመኝ ...... በጣም ደስ አለኝ፡፡ ምንም ማለት አልቻልኩም ደርቄ ቀረሁኝ፡፡ ፀጉሬን እየነካካ " ሰላሜ በጣም አፈቅርሻለው" አለኝ፡፡ "ግን እኮ..." ስለው አፌን በእጆቹ አረነው በድጋሚም ሳመኝ፡፡ "...ተቀበይኛለሽ" አለን፡፡ በአእምሮዬ ብዙ ሀሳቦች ተመላለሱ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ ጠፋኝ፡፡ ትንሽ ካሰብኩኝ በኀላ "አይ ብሩክ የማይሆን ነገር ነው " አልኩትና መንገዴን ቀጠልኩኝ፡፡

ድምፁን ጮክ አድርጎ" ትዝ ይልሻል ያኔ የመጀመሪያ የተገናኘንበት ቀን አንቺ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ያየሽኝ እኔ ግን ሁሌም አይሽ ነበር!፡፡ ት/ት ቤት ስትሄጂ የትም ስትሄጂ አይሽ ነበር፡፡ ምክንያቱም በጣም አፈቅርሽ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁ ሆቴል ውስጥ ነበር፡፡ ከቤተሰቦችሽ ጋር እራት ስትበይ ነበር፡፡ እኔም ከነ ማም ጋር እራት እየበላሁ ነበር የዛን ቀን ነበር ያየሁሽ ......ልቤን የሰረቅሽው የዛን ቀን ነው፡፡ እስከዛሬ ስንቴ ልነግርሽ ወስኜ እየፈራሁ ትቼዋለው ከአሁን በኀላ ግን አልችል በቃ የኔ ብቻ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው" አለኝ፡፡ ምንም ማለት አልቻልኩም ደርቄ ቀረሁ፡፡ እንባዎቼ ወረድ ጠጋ እያለኝ እንባዬን በእጆቹ ጠረገልኝ፡፡ "ሰላሜ ላገባሽ እፈልጋለው በጣም ነው የማፈቅርሽ" አለኝ ፡፡ እንደዚህ ሲለኝ በጣም ደስ አለኝ ተጠመጠምኩበት እጁንም ያዝኩት "ሰሊ እናንተ እዚህ ቤት ከሌላቹ እኔም አልኖርም ስለዚህ አብሬያቹ ነው የምሄደው" አለኝ፡፡ "አይሆንም ....." ስለው፡፡ "ግድ የለውም ሰላሜ ከአንቺ ጋር እንደምንም ሆኜ ነው መኖር የምፈልገው "አለኝ፡፡ የብሩኬ ሀሳብ ጥሩ እንዳልሆነ ገባኝ ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም በሱ ሀሳብ ተስማማሁኝ፡፡

እጄን ይዞ ወደ ሳሎን ሄደ፡፡ " ማም እነሰላም እዚህ ይኖራሉ ካልኖሩ እኔም እዚህ ቤት አልኖርም "አላት፡፡ ነገር ግን ዝም አለችው እኔም አንገቴን አቀርቅሬ መልሷን እጠብቃለው ግን ዝም አለች፡፡ ብሩኬ ወደ ክፍሉ ይዞኝ ሄደና ልብሱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ " በይ ሰላሜ እንሂድ "አለኝ፡፡ እውነት ለመናገር ብሩኬ ለኛ ብሎ ከቤት እንዲወጣ አልፈለኩም ነበር ነገር ግን ብሩኬ ከገገመ ገገመ ነው ስለዚህ ስለዚህ ዝም አልኩት፡፡

የግቢውን በር ሊከፍተው ሲል "ብሩክ ከዚ ግቢ እንዳትወጣ ከወጣህ ግን ....." ስትለው "ማም እንደማትፈልጊኝ አውቄያለው እሄዳለው " ብሎ በሩን ከፈተው እየሮጠች መጥታ አቀፈችው " እንዴት አልፈልግህም አንድ ልጄ ነህ እኮ አትወደኝም እንዴ " ብላ እንባዋን አነባች ቦርሳውን ጣል አድርጎ "ማም በጣም ነው የምወድሽ ግን ሰላምንና አቤልን ብቻቸውን መተው አልችልም ፡፡ ዞር ብላ በሚያስጠላ አስተያየት አየችኝ፡፡ እኔም አንገቴን አቀረቀርኩኝ፡፡ እንባዋን እየጠራረገች እና እየገለማመጠችኝ "እሺ ልጄ እዚህ ይኑሩ አንተን ማጣት አልችልም እሺ እዚህ እንዲኖሩ ፈቅጃለው " አለችው፡፡ከዛ የብሩኬን ቦርሳ ይዛው ወደቤት ገባች፡፡ ብሩኬም የኔና የአቤልን ሻንጣ ይዞ ወደቤት ገባ፡፡እኔ እዛ ቤት መቆየት አልፈለኩም ግን አቤልን አሰብኩት .... ብሩኬም እጄን ይዞ ወደቤት አስገባኝ......

ክፍል 17 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ
2024/05/15 11:27:51
Back to Top
HTML Embed Code: