ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?

በወጣትነት ወራት ስለ አባል ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ፆታ የሚኖር ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች የመራብያ አካላቸውን በመነካካት ጾታዊ ስሜት እንዲሰማቸውና የስሜት እርካታ እንዲያገኙ ሆን ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ሴጋ ወይም ማስተርቤሽን በመባል ይታወቃል።
የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለ ግለ ወሲብ በዝርዝር ማብራራት ሳይሆን ማስተርቤሽን የተባለውን የዝሙት ኃጢአት የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው ተወዳጆች ሆይ እያወራን ያለነው ከወንድ ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ የማታውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሷን በራሷ ለማርካት ማስተርቤሽን ስለፈጸመች ሴት ወይም የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሱን በራሱ ለማርካት ማስተርቤሽን ስለፈጸመ ወንድ ነው።

እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳያደርጉ ለእንደዚህ አይነት የዝሙት ተግባር በመጋለጣቸው ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከወንዱ ጋር በምንጣፍ አንድ አልሆንኩም ነገር ግን ማስተርቤሽን ፈጽሜለሁኝ ድንግል ልባል እችላለሁ?

እና ለድንግላን የሚፈጸመውን ሥርዓተ ተክሊልስ ለእኔ ሊፈጸምልኝ ይችላልን?
የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ነው።

ይሄ ጥያቄ በራሱ ተገቢነት የሌለው ትሕትና በማጣት ዲያብሎስ እየፈተነን መሆኑ ማስረጃ ነው። አንድ ኦርቶዶክስ ከማንኛውም የዝሙት ተግባር እርቆ ከኖረ በኋላ ተክሊል ሊፈጸምለት ሲል አረኸ አይገባኝም በማለት ራሱን ዝቅ ያደርጋል።

ከዚህ በተቃራኒው ራስን በራስ የማርካት የዝሙት ኃጢአት የኖረ ሰው ተክሊል ይገባሃል ቢባል እንኳን አረኸ እኔ አይገባኝም ብሎ በተሰበረ ልብ ሊርቅ ሲገባው በማስተርቤሽን ኃጢአት የዝሙትን ተግባር ሲፈጽም ከኖረ በኋላ ተክሊል ይገኛል ብሎ መጠየቅ ልባችን በፈጸምነው ኃጢአት አለመሰበሩን ማረጋገጫ ነው።


አንዲት ሴት ራሷን የዝሙትን የኃጢአት እርካታ የመራቢያ አካሏን በመነካካት አያረካች ከኖረች በኋላ እንዴት ባለ ድፍረት ነው ተክሊል ይገባኛል ብላ የምትጠይቀው?

ይቺ ሴት ከወንድ የምታገኘውን የሩካቤ ሥጋ ግንኘነት ከራሷ እያገኘች ከሆነ ከጋብቻ ውጭ ከወንድ ጋር ዝሙት ከሰሩት ሴቶች በምን ትለያለች?


ምንም ከወንድ ጋር በምንጣፍ አንድ ባትሆንም በኅሊና ወንድ በማሰብ አልፋ በፍቃዷ አፈ ማኅፀኗን እየነካካች የዝሙትን ተግባር ስለፈጸመች ድንግል ተብላም አትጠራም።

በሉቃስ ወንጌል ላይ የሚገኝ አንድ ታሪክ አለ።
ይህ ሕያው ታሪክ ከአባቱ ተለይቶ የኮበለለው ልጅ ሕይወትን ያሳስበናል። ይህ ልጅ ከአባቱ ለመለየት መወሰኑ ስህተት መሆኑ ገብቶታል።
ስለዚህም የሰራውን ስህተት ለማረም ሲነሳ ወደ አባቱ ለመመለስም ሲወስን እንዲህ ብሎ ነው ያሰበው "ተነስቼ ወደ አባቴ እሄዳለሁና አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።" የሉቃስ ወንጌል 15፥18-19


ይሄ ልጅ በአባቱ ላይ ማመጹ ኃጢአት መስራቱ ፈጽሞ እንደጸጸተው የምንረዳው "ወደፊትም ልጅህ ልባል አአይገባኝም" በሚለው ንግግሩ ነው።
ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ ስለመብቱ እያሰበ አልነበረም በልጅነት ክብር ለመጠራት እንደማይገባው ወደ አባቱ ቤት የተመለሰው በአባቱ ቤት ከሚሰሩት ሙያተኞች መካከል እንደ አንዱ ሆኖ በባርነት ለማገልገል ነበር።
ማስተርቤሽን ሲፈጽም የኖረም ሰው ኃጢአቱን አምኖ ሲመለስ ድንግል ልባል የድንግልና ሥርዓትም ሊፈጸምልኝ አይገባም በሚል በተሰበረ መንፈስ ነው እንጂ በይገባኛል የሚል የትዕቢት ሐሳበ በልቡ የያዘ መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።


ከዚህም በተጨማሪ ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ከፈጸሙ በኋላ
"በአካል ተቃራኒ ጾታ ጋር ግንኙነት አላደረኩም ተክሊል መፈጸም ይፈቀድልኛል?"
የሚል ጥያቄ በአእምሯቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው።

ምክንያቱም ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅቡረ ዝሙት እየፈጸምን ያሳስበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው።
እንዲህ አይነት አስተሳሰብ "የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል።
ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈታ የኮበለለች ሴት ናት።

ከሄደችም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾት እና ክብር ነው።
አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ማለትም ኃጢአት ሰርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀየምኩት ስለ በደሉ ያለቅስ ነበር።

እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተሰነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን?"
"ተክሊል ይገባኛል?"
እያለ ያወጣውና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ" አንተን ብቻ በድልሁ በፊትህም ክፋትን አደረኩ መዝ 51፥4
ማለት ኃጥአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ አዳምን መስሎታልና የቤተ ፈት ፍቃድ ልማድ አላገኘውም ይባላል።

በመጨረሻ ከማስተርቤሽን እና ይህንን ከመሰሉ የዝሙት ርኩሰት መንገዶች የምታመልጠው በተቀደሰው ጋብቻ አማካኝነት ነው። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ፦ ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱም ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት። 1ኛ ወደ ቆሮንጦስ 7፥2 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዝሙትን ጠንቅ ብሎ ነው የጠራው በወጣትነት ወራታችን ከዲያብሎስ ከሚወረወሩ ፈላጻ ለመመከት ጋሻ መሆኑን ከገጸ ንባቡ እንረዳለን። በእውነት ከሴጋ የኃጢአት ዓለም ወጥተን በተቀደሰ ጋብቻ ለመኖር ማሰባችን የሚመሰገን መንፈሳዊ ውሳኔ ቢሆንም ጋብቻችንን ግን በትህትና በተሰበረ ልብ ልንፈጽም መዘጋጀት ይኖርብናል።
አንዳንድ ሰዎች ማስተርቤሽን ሲፈጽሙ ከኖሩ በኋላ የንስሐ አባቴ ፈቅደውልኛል በማለት ተክሊል ለመፈጸም ሲዳፈሩ ይታያል።
እነዚህ ሰዎች ስለ ማስተርቤሽን በጥልቀት ለንስሐ አባታቸው ሳይናገሩ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆናቸውን ብቻ አጉልተው በማምታታት በማድበስበስ ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ተክሊል ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ለምዓት ካልሆነ የበረከት መንገድ አለመሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነውና መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
ተወዳጆች ሆይ ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንደዚህ ያለው "የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን ጠብቀኝ ያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ" መዝሙር 19፥13
ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ስለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፈጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ አድርገን አይገባኝም😔 ልንል ያስፈልጋል።

በቀጣይ ክፍል በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
የሚለውን ጥያቄ እንመለከታለን
የዛሬው ጥያቄ የተመለሰላችሁ👍 በማድረግ ግለጹ

🙏እስከዛው ይሄንን ለወዳጅዎ ለጓደኞችዎ ለሴት እኅቶች ያጋሩት🙏

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_spiritual_question
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
ዓቢይ ፆም @eotc_books_by_pdf.docx
68.7 KB
📚⛪️የዓቢይ ፆም📚⛪️

በዚህ pdf #የዓብይ_ፆም የእያንዳንዱን
ሳምንት በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡትን ፦

➪ ምስባክ
➪ መልዕክታት
➪ የሐዋርያት ሥራ
➩ ወንጌል ይዟል

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_spiritual_question
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
በጾም_ወቅት_ንስሐ_መግባት_ይቻላል⁉️
@eotc_books_by_pdf
🎧⛪️በጾም ወቅት ንስሐ መግባት ይቻላል?🎧⛪️

👉 ንስሐ የዕድሜ ገደብ አለው?
👉 ንስሐ ከገባን በኋላ ግዴታ መቁረብ አለብን?
👉 ንስሐ ገብቼ ኃጢአት ብሰራስ?
መልሱን ከድምፅ ቅጂው ያገኙታል #ሼር ለወዳጅዎ

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_spiritual_question
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
😭አሳዛኝ ዜና😭

ውድ ✞የኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ📚 ቻናል ቤተሰቦች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
በረከታቸው አትለየን።

ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ  ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ የካቲት ፳፯ ቀን  ፳፻፲፬ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ውሳኔ አሳልፏል

ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን አሜን 🙏😭
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ለሁሉም ባለ ማዕተብ ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
📚⛪️አንድሮሜዳ 1📚⛪️

ይህ መጽሐፍ ስለ ህዋ ስለ ከዋክብት ስለ ተለያዩ ፍጥረታት ያስቃኘናል የተለያዩ ምንጮች ከኢ/ኦ/ተ/ቤተ/ክ የብራና መጽሐፍት😇📜😇

ጸሐፊ ፦ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
አንድሮሜዳ ፩ @eotc_books_by_pdf.pdf
33.7 MB
📚⛪️አንድሮሜዳ ፩📚⛪️

ከብራና የተገኙ የስነ ከዋክብት ዕውቀት ማግኘት ከፈለጉ ይህን በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተጻፈውን መጽሐፍ ያንብቡ

ጸሐፊ ፦ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
አንድሮሜዳ ፪ @eotc_books_by_pdf.pdf
38 MB
📚⛪️አንድሮሜዳ ፪📚⛪️

ከብራና የተገኙ የስነ ከዋክብት ዕውቀት ማግኘት ከፈለጉ ይህን በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተጻፈውን መጽሐፍ ያንብቡ

ጸሐፊ ፦ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
አንድሮሜዳ ፫ @eotc_books_by_pdf.pdf
66.2 MB
📚⛪️አንድሮሜዳ ፫📚⛪️

ከብራና የተገኙ የስነ ከዋክብት ዕውቀት ማግኘት ከፈለጉ ይህን በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተጻፈውን መጽሐፍ ያንብቡ

ጸሐፊ ፦ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት @eotc_books_by_pdf.docx
4.9 MB
📚⛪️መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት📚⛪️

በዚህ መጽሐፍ ቤተክርስቲያን የምታከናውናቸውን ሥርዓት በሙሉ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው ከ40+ ዓበይት ርዕስ አሉት
ሁላችሁም ኦርቶዶክስ የሆናችሁ አንብቡት።

ጸሐፊ ፦ ቀሲስ ዶክተር ዘበነ ለማ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና በእንተ እግዝእትነ ማርያም።

በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት የኃጥያት ማሠሪያ ይፍታችሁ ሲል ፲፪ [12] ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና ፲፪ [12] ደግሞ በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላል። ካህናትና ምዕመናን በሙሉ በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህንኑ ፲፪ [12] ጊዜ እንላለን።

➥እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት፦ አቤቱ ክርሰቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርሰቶስ ማረን ማለት ነው።

➥አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሌሊቱ 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሠራነው ኃጥያት ለሃያአራቱ ፳፬ [24ቱ] ሰዓት ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ነው።

ሌላው አሥራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት ፦

➥፩ኛ. በስመ ሥላሴ ነው። በእያንዳንዱ ፊደል

አ ብ ወ
ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

➥፪ኛ. የድኃነታችን ምክንያት በሆነችው በእመቤታችን ስም ፊደል

ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

➥አቆጣጠሩም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደታች ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት [በትንሿ] ጣት ወደላይ ነው።

➥ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን።

➥ መሐል ጣት ወደላይ ፦ ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን

➥ በቀለበት ጣት ወደታች ስንቆጥር፦ ለፍርድ መምጣቱን

በትንሿ ጣት ወደላይ ስንወጣ፦ ደግሞ ሁላችንን በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።
➥ በእንተ እግዝእትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ፦ ከትንሽ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደላይ ይፈፀማል። ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳየን ምስጢር ነው።

ምን
ከመጽሐፈ አሚን ወሥርዓት የተወሰደ በመምህር ዘበነ ለማ የተፃፈ ገፅ 238
ሙሉ መጽሐፉ ከላይ በpdf ተቀምጧል
ትምህርቱን ለሌሎች እናካፍል ‼️

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtu.be/9qI5JqH6QhE?sub_confirmation=1
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf_Group
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
Forwarded from DISK 15K+
🙏 በእግዚአብሔር ስም ሼር አድርጉት
እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ
ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ
😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱
📚በእመጓ መጽሐፍ እንደተጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተሰቅሎ ደሙ ተቀድቶበት ዓለም የተረጨበት ቅዱሱ ጽዋ የሚገኝበት #እመጓ_ዑራኤልን እንጎበኛለን።
እግር መንገዳችን የምንሳለማቸው ገዳማት

⛪️👇🏾👇🏾👇🏾⛪️
👉🏽አርባሐራ መድሃኔአለም
👉🏽ዘብር_ገብርኤል
👉🏽ሽብሻቦ_ማርያም
👉🏽አቡነ_ዘርአብሩክ
➦3 ገዳማትን ጨምሮ😱

💰የጉዞ ዋጋ 1000 መስተንግዶን ጨምሮ

📆የጉዞ ቀን እሮብ ግንቦት 24-27

🚐መነሻ ቦታ📍
👉🏽ፒያሳ ፣ መገናኛ ፣ ላምበረት እና ጣፎ
ያሉን ቦታ ውስን ስለሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ

📞📞
+251913162292
+251910455701
+251933527673
+251946055434

ማኅበረ እመጓ ኡራኤል ወአቡነ መልከ ፄዴቅ ዘሚዳ
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 9 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
2024/05/04 13:57:02
Back to Top
HTML Embed Code: