Forwarded from JEHOVAH JIREH (ያህዌ ይርዔ)
ሰላም ኦርቶዶክሳውያን ዛሬ ሉካንዳ አካባቢ በምትገኘው ልደታ ቤተክርስቲያን በነበረው ችግር ወንድማችን #የሰ_ት_ቤታችን_አባል_ሚኪያስ_ተሾመ በቦታው በነበሩ እና በታጠቁ ሲቢሎች የተያዘ ሲሆን ወዴት እንደተወሰደም ማወቅ አልተቻልም ስለዚህ እባካቹ ሁላቹም ኦርቶዶክሳውያን ይሄንን መልክት ሼር በማድረግ ለወንድማችን ድምጽ እንሁን።
መሰረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት
የካቲት 5 እስኪደርስ..............? ጅል አትሁኑ!‼️‼️‼️‼️

የካቲት 5ን ሁሉም በጉጉት እየጠበቀ ነው ። የአባቶችን ፊሽካ ሚጠብቅ መስቀል የታጠቀ የአንበሳ መንጋ ተሰናድቷል ። በዚህ መሐል ያሉ 5 ቀናት የፀሎት እና የምዕላ ግዜ ተብለዋል ። ከፀሎቱ እና ከምዕላው ጎን በዚህ 5 ቀን ስልኮቻችንን ብቻ በመጠቀም ምን እንስራ ሚለው ደግሞ የአንድ ብልጥ ክርስትያን ሐሳብ መሆን አለበት ።

በመጀመርያ መደረግ ያለበት ነገር መስጂዶችን በጥብቅ መጠበቅ ነው ። በተለይ ደግሞ በአማራ ክልል ያሉ መስጂዶችን በዐይነ ቁራኛ መጠበቅ የክርስትያኖች ግዴታ ነው ። መንግሥት እየመጣ ያለው ማዕበል ስለሚያስፈራው "እሾህን በእሾህ" በማለት ሙስሊም ወንድሞችን ነካክቶ እንዲነሱ ማድረጉ ማይቀር ነው ። ይሄ እንዳይፈጠር ግዴታ መስጂዶችን ከቤተክርስትያን እኩል መጠበቅ ግድ ነው ። ስህተት እንኳ ቢፈጠር ሙስሊም ወንድሞች ሁኔታውን እንዲገነዘቡ እና በመንግሥት ሴራ በቀላሉ እንዳይሸወዱ ሁሉም ክርስትያን ከጎኑ ላሉት ሙስሊም ወንድሞች ማስረዳት አለበት ።

ሌላው...........

Fana TV Youtube ላይ 1.2 ሚሊየን Subscriber ሲኖረው Exact ባይሆንም ወደ 56% ሰብስክራይበሩ ኦርቶዶክስ ክርስትያን ነው ተብሎ ይገመታል ።

Etv 1.2 ሚሊየን ሰብስክራይበር ሲኖው ወደ 52% ኦርቶዶክስ ክርስትያን ነው ተብሎ ይገመታል ።

Ethio Telecom 60 million ቋሚ ደንበኛ ሲኖረው ከዛ ውስጥ ወደ 51% ኦርቶዶክስ ክርስትያን ነው ተብሎ ይገመታል ።

ስልካችሁን አንስታችሁ ቀጥ ብላችሁ Youtube በመግባት በ2 ደቂቃ ስራ ብቻ Fana እና Etvን Unsubscribe በማድረግ የካቲት 5 ሰልፉ ሲደረግ ሊከሰቱ የሚችሉ የመንግሥት ፕሮፓጋንዳዎችን ከጨዋታ ውጭ ማድረግና የመንግሥትን ድምፅ ማፈን ይቻላል ።

በዓመት ወደ 100 billion ገቢ ለመንግሥት ሚያስገባው Ethiotelecom ወደ 51% ደንበኛው የሆነው ኦርቶዶክሳዊ ህዝብ ደንበኝነቱን አቋርጦ ወደ Safaricom ቢሄድ በትንሹ መንግሥት ወደ 50 billion ብር ያጣል ።

Youtube ከገባችሁ በኋላ እግረ መንገዳችሁን የቤተክርስቲያኒቱ ድምፅ የሆነውን EOTC youtube channal suscribe ማድረግ ደግሞ በሰልፉ ወቅት የሚዲያ የበላይነቱ ሙሉ በሙሉ በኦርቶዶክሳዊያን ቁጥጥር ስር ያስገባዋል ።

በዚህ ዘመቻ ላይ የሙስሊም ወንድሞች ትብብር ከተጨመረበት ደግሞ የካቲት 5 ኦርቶዶክሳዊያን ሳይሆኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት ይሆናሉ ሰልፍ ሚወጡት ።

ይሄ ሁሉ ስራ እንግዲህ ከበዛ 30 ደቂቃ ቢወስድ ነው  ። ነገር ግን መንግሥት ላይ ሚያደርሰው ተፅእኖ ቀላል አደለም ።  የሚደረገው ሰልፍ ላይም Positive ተፅእኖ ይኖረዋል ።

ከሰልፉ በኋላ ደግሞ ብዙ ብዙ ሚደረግ አለ ። ከተባበርን ቤተክርስትያን የለበሰችው ጥቁር ጨርቅ በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ ከቤተክርስትያን ገፈን ቤተ መንግሥቱ እንዲለብሰው ማድረግ እንችላለን።

ከ fb መንደር ያገኘሁት ነው ይጠቅመናል ብዬ አስባለሁ
በአሁኑ ሰዓት TELEGRAM መስራት አቋም ያለ proxy ወይም VPN በስተቀር

አልሰራ ላላቸው እንዲደርስ- ይሄን ሊንክ ተጠቀሙ

https://www.tg-me.com/proxy?server=cheha-ba-jan-khod-door-az-rokh-janan-khod-kardam.sbs&port=443&secret=7vQ1mpsyX_HR5QhN8OD3U3ttc24uY29t
ሁላቼሁም vpn ከፕሌይ ስቶር አውርዱ። ከላይ የላክንላችሁን አማራጮች ተጠቀሙ። በተጨማሪም ኢንተርኔት ከተዘጋ በሳፋሪኮም ሲም ኢንተርኔት ማጌኘት ትችላላችሁ።
271ሺ ደርሰናል
ግማሽ ሚልየን መድረስ አለብን

በመንግስት መገናኛ ብዙኅን ድምጿ እንዳይሰማ የታፈነችውን ቤተክርስቲያናችን ድምጽ እናጉላ
ላልሰሙት አሰሙ!

የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
ከመከላከያ ባለማዕተቦች የተላከ…!

"…ዘመዴ ምንም አትስጉ። እኛም ተዘጋጅተናል። ሃገር ወዳድ ሙስሊም ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችንም ከእኛው ጋር ናቸው። አትስጉ። የኦሮሞ አመራሮቹ ለአቢይ እና ሽመልስ አግዘው ወደ እርምጃ ገብተው ወደ ሕዝብ ከተኮሱ እኛም ተዘጋጅተናል። ይሄን ጻፈው ዘመዴ።

"…በዚህ ሰልፍ ለሚፀኑ የሚመጣውን መጠነኛ ርምጃ እንዳስፈላጊነቱ ለመመለስ እነሱ በመረጡት ቋንቋ መንቀሳቀስና ንፁሐን ለጥቃት እንዳይመቻቹ ማድረግ ይቻላል። እኛ ሃይማኖታችን ላይ ሰነፍ ብንሆንም ሃይማኖታችንን እንጠላለን፣ እንዲህ በጋጠወጥ መልኩ ስትደፈር፣ ሕዝብ በአደባባይ ሲረሸን እስከመጨረሻው ዝም እንላለን ማለት አይደለም። ባይሆን የመሳሪያ አሰላለፋቸውንና አሁን በወጣቱ እየተለቀቀ ያለውን ሽብር የሚያከሽፍ፣ ለሚተኮሰው ምላሻችን ሞት ብቻ እንዳይሆን ነው የምንመክረው።

"…ለኃይል መልስ ከተዋሕዶ ሕግና ሥርዓት በተጨማሪ ሰልፍ ዲፌንስ ካላደረግን በሁለት ቀናት ውስጥ የሚገባው ወይ ኮማንድ ፓስቱን የሚይዘው እስካሁን ከመረጃ ውጭ የነበረና በጦርነቱ ምክንያት ስልካቸው የተሰበሰበ ጀማሪ ኮማንዶወች ናቸው። እነሱ ደግሞ የሃይማኖት አክራሪነትን ነው ትሬኒንግ ሲወስዱ የቆዩት። ትምህርቱ ሰፊ ነው እና አርሚው ቴሬሪዝም ፎርስ በሚል ተልእኮ ነው የሚመጡት ስለሚሆነው ምንም መረጃ የላቸውም።

"…ዘመዴ ካስታወስክ በ2009 ዓም ጅንካ የተላኩት ከሶማሊያ ጫካዎች ለሥስት ዓመታት ምንም ነገር ያልሰሙ ነበሩ። እና አሁንም በተለይ በአዲስ አበባ እነሱ እንዳሰቡት ከፈቀድንላቸው እና ሚዛኑን ካለወጥነው በቀር በሰዋዊ እሳቤ መስዋእት ማብዛት ብቻ ነው የሚሆነው። በሳይንስ ለሚመጡት ሳይንሳቸውን ከገለበጥነው። ከእምነታችን ጥንካሬ ጋር እናሸንፋለን። አልያ ግን በሽብር ሰልጣኞች መጀመርያ ዋርካውን፣ ቀጥለህ ስሩን ያኔ ቅርንጫፍና ቅጠሉ … ይቀጥላል…
አረ ምንድን ነዉ ያዞሩብን ጎበዝ ፤ ፈዘናል እኮ ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ እኮ ቤተ ክርስቲያናችሁን በንቃት ጠብቁ ብሏል ፤ ላይክና ሼር አድርጉ ነዉ እንዴ ያለዉ!በአስቸኳይ ጠቅላይ ቤተ ክኅነት ያሉ የቢሮ ኃላፊዎች ወደ 54ቱ አህጉረ ስብከቶች ይመደቡና አድባራቱን ስብሰባ ጠርተዉ ይወያዩ፤ የአድባራት አስተዳዳሪዎችም አቅጣጫ ይሰጣቸዉና ለጸሎትና ለምኅላ ለቅዳሴ የሚመጣዉን ሕዝብ በየአጥቢያዉ ያወያዩ ፡ እንዴዴዴዴዴዴ ምንድን ነዉ የሚጠበቀዉ!
የመወያያ አጀንዳዎቻችን በኋላ የሚቀየሩ ቢሆኑም ፡
1. በቤተ ክርስቲያናችን ጥበቃ ጉዳይ
2. በቅርስ ምዝገባ
3. በአጥቢያዉ ነዋሪ የሰበካ ጉባኤ ምዝገባ እና ዓመታዊ ክፍያ
4. ንስሐ አባት የሌለዉ እንዲይዝ ያለዉ እንዲያጸና
5. ሁሉም ንስሐ እንዲገባ እና ሥጋ ወደሙ እንዲቀበል
ጎበዝ ለዚህ ነዉ ክርስቶስ ነዉጡን ያስነሳዉ ፤ እንንቃ እንዘጋጅ ይህን ካደረግን በኋላ በኩራት የሚመጣዉን ሞት እየዘመርን እየሳቅን እንቀበላለን !
ከዚህ ዉጪ የጅል ሞት ይባላል ፤ ገዳዮች እያመቻቹ ነዉ ፤ እኛ ደግሞ ለመሞት ተጣጥበን እንመቻች !
ሄሎ አይሰማም !?

@cherstianawiwetat
ብፁዕነታቸው ላይ ጥርጣሬ ያደረብን ቀን መጥፊያችን ነው!!
እየተፈለገ ያለውም ይሄ ነው‼️

"እንዲህ አድርጉህ የመንፈስ ልጆቼ " እስኪሉህ ድረስ ጆሮህን ስለምንም አታውሰው!!

እርሳቸው ላይ ያለው ፍፁም ነውና "

የአባታችን በረከት ይደርብን 🙏✝️🥰

#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያሪክ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን

#አጀንዳዬን_አልቀይርም

👉 እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ
በኦርቶዶክሳውያን ተጋድሎ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ዐቢይ አሕመድ ሦስቱን የሕገ ወጥ ቡድን መሪዎች ይቅርታ ጠይቁ ብሎ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ልኳቸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ተአማኒነት ለማግኘት የኦሮሚያ ብልጽግና እርቁን አልቀበልም አለ፤ ክፍፍል ተፈጠረ ብሎ ለማስወራት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
ያም ሆነ ይህ ትናንት ይቅርታ ጠይቆ እንደካደው ግለሰብ ሌላ ድራማ ላለመሠራቱ ዋስትና የለም። ነቅተን እንከታተል።
እኔ ግን ዛሬም ጥያቄ አለኝ !

¶ ትናንትና አባ ንዋይን የተቀበለ ማኅበረ ከለባት ዛሬ ምን ተገኘ ?
¶ ትናንት እንዲያ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የነበረ ዛሬ የጨመተው ለምን ነው ?
¶ ትናንት አይዞሽ ቤተክርስቲያን ያላሉ "ዓርብ ያልነበሩ ምነው ለትንሣኤ እሁድ ተሰበሰቡ " ?
¶ ትናንት የወጡበት ምክንያት ምን ነበር ? ዛሬስ በምን ተስማምተው ነው የመጡበት ?
¶ ትናንት አንድ ሰው ነው የሚመራው ጉባኤ ያሉት "ቅዱስ ሲኖዶስ" ዛሬም እኮ ያ ነው ምነው ታዲያ ?
¶ መቼም ቤተክርስቲያን (ቅዱስ ሲኖዶስ) አውግዞ ነበር ስለዚህ ቆቡም መስቀሉም የመያዝ መብት ገና አልሰጠችም ታዲያ #አቶ ከመቼ ጀምሮ ነው መስቀል የሚይዘው ?
¶ እኒህ ተገተልትለው የወጡት 25ቱ ሰዎችስ ይቅርታ አይሉም ?
¶ የፈሰሰው ደም እንዴት ሊሆን ነው ? እንደ ዘካርያስ ወልደ በራክዩ በመቅደሱ እንደ ቃየል በሰማይ ሲከስ ይኖራል !

ለማንኛውም ግር ብሎ ወጥቶ ግር ተብሎ መግባት ነውር ነው ይህቺ ቤተክርስቲያን ናት ወዳጄ !

ቸር እንሰንብት !
የነአቡነ ሳዊሮስ ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት አግኝቷል። የቋንቋ ጥያቄውም ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት አግኝቷል። የበጀት ጉዳይ መንግስት ሳይቀር involve አርጎ ኦዲት እንዲደረግ ተስማምተዋል። እነሱ የሾሟቸው ጳጳሳትም በህጉ መሰረት requirement የሚያሟሉት officially እንደሚሾሙም ተስማምተዋል። የኦሮምኛ ቋንቋ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች በብዛት እንደሚከፈቱ ተስማምተዋል። ቆይ እሺ አሁን ጥያቄው ምንድን ነው? ስምምነቱን መስበር ለምን አስፈለገ?::
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው (ገላ.5፡22-24)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ክርስቶስን የሚመስሉ፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው (ዘፍ.1፡26)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዘዙን ከማድረግ በላይ፥ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው፡፡ ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ፣ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እነርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡

#ትንሿ_ቤተ_ክርስቲያን፣ ገጽ 507-508

join

#cherstianawiwetat
ካህን ታፍኖ ታሥሮ ዝም የሚል ሲኖዶስን መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል ብለን አናስብም፤ አንጠብቅምም።
አባቶቻችን እውነት በመምህሩ መታሠር እጃችሁ ከሌለበት የታሠሩት የጉባኤ መምህር ናቸውና ዝምታችሁን አስወግዱ። ካልሆነ ግን እናንተን የሚተቹትን እየመረጣችሁ የምታሣሥሩ እናንተ ናችሁ።
በርግጥ የተወሰኑ አባቶች በጨለማው ሲኖዶስ ውስጥ ሆነው የሚሠሩትን ሥራ እያየን ነው። ጊዜ እንጠብቅ ብለን እንጂ ሀሉንም እንገልጠዋለን።
መንፈስ ቅዱስ የሚመራችሁ ከሆነ ኪህናችሁን አስፈቱ፤ ካህኑን የሚያሣሥር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው አካል የለምና ዝምታችሁን ስበሩ።
ትናንት በምእመን የተጀመረው እሥራት ዛሬ ካህን ላይ ደርሷል። ቀጣዩ ተራ የእናንተው ነው። የሚያዋጣው ከምትመሩት ምእመን ጋር መሆን ነው።
የምእመናን ጅረት አይቋረጥም፤ ፖለቲካ ግን ነገ ይጠፋል።

ድምፀ ተዋሕዶ
https://www.tg-me.com/onesinod
የኔ ልጅ እባክህ ላስቸግርህ እርዳኝ(መለኩሴው ጫት ከምሸጥበት መደብ ፊት ቆመው
አይ አባ እኛም እኮ ቸግሮናል ኑሮ ውድ ነው(ወደ ኪሴ እየገባሁ
አይደለም ልጄ እኔኮ ብር ፈልጌ አይደለም(ሰው እንዳይሰማ በሹክሹክታ እያወሩ
እሺ ምን ፈልገው ነው አባቴ መንገድ ልጠቁሞት?
አረ በፍፁም!!እኔማ ከዝች ከጫቷ ቆንጠር አድርገህ እንድትሰጠኝ ብዬ ነበር(በመሸማቀቅ አይናቸውን ስብር አድርገው
የተቀመጥኩበት ወንበር የሰመጠ ያህል ተሰማኝ ጥያቄያቸውን ተከትሎ አፌን ከፍቼ አይኔን አጉረጥርጬ ቅንድቤን ሰቅዬ አየኋቸው።ምናልባት ይህን ቃል የሠማሁት አጠገቤ ካለ የጫት ደንበኛዬ እንዲሆን በማሰብ
አከባቢዬን ቃኘሁት ግን ሁሉም ተርዚናውን አጭቆ አፉን የሚያላውስ የለም የተናገሩት እኚ መለኩሴ ናቸው?ጆሮዬ ነው?ግራ በመጋባት ደርቄ ስቀር..
የኔ ልጅ አልሰማከኝም?እባክህ ሱስ ሆኖብኝ ነው ሰው ሳያይ ቀስ ብለህ ስጠኝ
ተነስቼ መሮጥ ፈለኩኝ፣አልያም በአስማት ከዛ ቦታ
የሚሰልበኝን ተአምር ባገኝ ብዬ ተመኘሁ ግን እኚ በነጭ ቆብና በጥቁር ካባ ያሸበረቁ ለሠማይና ለምድር የከበዱ
መልዐክ የሚመስሉ መለኩሴ አሁንም ከፊቴ ፊትለፊቴ ቆመው በልምምጥ እያዩኝ ነው
አባ ይቅርታ እኔ ለእርሶ አልሸጥም
እንዴ ለምን እኔ ሰው አይደለሁ?
አይ እርሶ የእግዜር ሰው ኖት ሌላ ቦታ ይሂዱ
ብታቅማ አንተም የእግዜር ልጅ ነህ ግን ደሞ ሱስ ነው የምልከው ልጅ አጥቼ ብቸገር እንጂ ..
እኚ መለኩሴ ለምን አይሄዱም?ደግሞስ እውነት ብሰጣቸው እዚ አደባባይ ላይ ይቀበሉኛል?የሚሆነውን ለማየት እጄ እየተንቀጠቀጠ አንድ እስር ጫት በፔስታል አድርጌ እየፈራሁ ወደ መለኩሴው እጄን ስዘረጋ
ጎሽ የኔ ልጅ በል እንካ ሂሳብክን(በደስታ እየተፍለቀለቁ
እኔ የእርሶን ብር አልፈልግም ሂዱልኝ ከዚ ቦታ ሁለተኛ እኔ ጋር እንዳይመጡ(እኚ መለኩሴ ዛሬ ምነው ሚስማር ካልዘነበ መብረቅ ካልወረደ አሉሳ?ንዴቴ አናቴ ላይ ወጥቶ
አንባረቅኩባቸው
የማየው የምሰማው ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ እውነት ግን ለምን ተናደድኩ?እኚ ሰው ቆብ ያድርጉ እጂ እንደኔ ሰው አደሉ?ደሞስ እኔ ማን ሆኜ ነው ምወቅሳቸው? ምናልባትም አንዱ የቸገረው ዱርዬ ጫት መቃም ፈልጎ የፈጠረው ድራማ ቢሆንስ?(ጭንቅላቴን በጥያቄ ወጥሬ ያልተሸጠ ጫቴን እያስተካከልኩ መልሶ የሚጥል ድንጋጤ ወረረኝ...ያኚ ጫት ካልሰጠከኝ እያሉ ሲነታረኩኝ የነበሩት መለኩሴ ለጫት ሲንገበገቡ መስቀላቸውን የጫት
መሸጫዬ ላይ ጥለውት ሄደዋል!!
ድንጋጤ ቅፅበታዊ ሲሆን ፍርሀት ትከሻ ሲወዘውዝ የገጠመኝ በዚህ ቀን ነበር ፍርሀት የማያውቀኝ ሰውዬ እየተርበተበትኩ መስቀሉን አንስቼ ያኚ መዘዘኛ መለኩሴ ወደሄዱበት አቅጣጫ ከነፍኩ..ደርሼባቸው በእጄ የያዝኩትን መስቀል እስክሰጣቸው ልቤ ቆሟል ከኋላ አውሬ የሚያባርረኝ ያህል እየተሰባበርኩ ከሩቁ አባ መቋሚያቸውን እያስቀደሙ ሲራመዱ አየኋቸው ግን
እንደ እብድ ብጮኽ አባ አይሰሙም የምርቃና ሰአታቸው ደርሷል.
አባ..አባቴ..ይቁሙ..(አጠገባቸው ደርሼ ትንፋሼ
እየተቆራረጠ ጠራኋቸው
አባ የቤ/ክኑ በር ላይ ደርሰው እየተሳለሙ ጥሪዬን ሰምተው
በድንጋጤ ዞር አሉ
አቤት ምን አጣህ ምን ፈለክ?(በቁጣ ግንባራቸውን ቋጥረው እያዩኝ
አረ እኔ መስቀሎትን ጥለው.(በፍርሀት እያየኋቸው
በል ና እዚህ ጥሩ አይደለም ውስጥ እቀበልሀለው
እኚ ሰው ዛሬ ለምን አይተውኝም?ገብቼ ደሞ እንቃም ሊሉ ነው?ደሞስ ጫቱን ወደ ቤ/ክ ይዘው ሲገቡ አያፍሩም?በዛ ሁሉ ድካም ውስጥ ይሄ ሀሳብ አእምሮዬ ላይ ሲያቃጭል ዘገነነኝ።ግን አማራጭ ስለሌለኝ ተከትያቸው ቤ/ክኑን አልፈን እስከ ቤታቸው አደረስኳቸው።
ና እስቲ አረፍ በል ቆንጆ ምሳ አለ
አረ አባ መስቀሉን ይቀበሉኝ እኔ ለዚ ቦታ አልገባም ልሂድ...
ግድ የለም አትፍራ..(አባ ፈጠን ብለው በሰሀን እንጀራ በምስር ወጥ ይዘው መጡ...
እኚ ሰውዬ ግራ እያጋቡኝ ነው ውስጤ ብዙ ጥያቄ አለ ይሄን የመሠለ የመመረጥ ህይወት ትተው አለማዊ ነገር መመኘታቸው እያስገረመኝ...
ቆይ አባ ጫት መቃም ሀጥያት አይደለም እንዴ? (በጥርጣሬ ጠየኳቸው
አረ በፍፁም ሀጥያት አይደለም!ይኸው አንተ ትቅም የለም እንዴ?
እኔማ ሀጥያተኛ ነኝ ሁሌም ስራዬ ይህ ነው እርሶ ግን ..
ጎሽ የኔ ልጅ ተባረክ አየህ አሁን ትልቅ ቁም ነገር አወራክ ሰው ከፈጣሪ እንዳይታረቅ የሚያደርገው ዋናው ነገር ሀጥያት ሰልጥኖበት ሳለ ሀጥያተኛ ነኝ ብሎ አለማመኑ ነው ሰው ሁሉ ሀጥያተኛ ነው ግን ደሞ መርሳት የሌለብህ እግዚአብሔርም መሀሪ መሆኑን ነው።(አባ እያወሩኝ ከሰል ማንደጃቸው ላይ የገዙትን ጫት እያስቀመጡ
ታድያ ሀጥያት ከሆነ ለምን እኔ ጋር መጥተው ገዙ?ደሞስ ለምን ያቃጥሉታል?(ጋዝ አርከፍክፈው የሚያቃጥሉትን ጫት ሲንቦገቦግ በድንጋጤ እያየሁ..
አየህ ወጣትነት ማለት እንደዚህ እሳት ነው የያዘውን የቀረበውን ሁሉ ይፈጃል።ይህ እሳት ንፋሱ ወዳለበት አቅጣጫ እንደሚነድ ሁሉ ወጣትነትም አለም ባነፈሰችው ባራገበችው የሀጥያት አየር እንድንገፋ ያደርገናል።ይህ እሳት እንዲነድ ጋዝና ወረቀት ጨምሬበታለሁ ያለዚያ እንዲህ አይነድም ነበር ወጣትነትም ከልክ በላይ ሰውን
እንዲያነድ እና እንዲያጠፋ በጋዙ ቦታ ጫት ሱስ ዝሙት የመሣሠሉትን ሰይጣን ይጨምርብናል ያኔ እንደዚ እሳት በአለም ላይ እንነዳለን።
ቅድም ጫት ስጠኝ ስልክ ድንጋጤክን አስተውያለሁ..አንተ እኔ እንዳልገዛ እንዳልቅም እየከለከልከኝ እንዴት ለራስህ መሆን ያቅትሀል?እኔም አንተም በእግዜር አምሳል የተሠራን ክቡር ፍጥረታት ነን ለኔ ያልተገባ ሀጥያት እንዴት ላንተ ይገባል?ጫት ማለት ለጊዜያዊ መነቃቃት እና ደስታ ለስጋችን የምንጠቀመው እፅ ነው ይሄን ተከትሎ ደሞ መጠጥ ስካር ዝሙት የሚባል ሀጥያት ይመጣል።አንተ ይህን ጫት ቤ/ክ ይዤ ስገባ የጨነቀክ የእግዚአብሔር ቤት ስለሆነ አደል? በምድር ላይ ግን ሰውን የሚያክል የእ/ ር ቤተመቅደስ የለም!እና የእግዜር ቤተመቅደስን በጫት በሱስ ታረክሳለህ?ሱስ ማለት እግዜር የሠጠኝ ደስታ ሰላም አቅም አንሶብኛልና ሌላ ተጨማሪ ነገር ያስፈልገኛል ብሎ መልፋት ከፈጣሪ መጣላት በስራው መጠራጠር ነው! ስለዚህ የመዳን ቀን ዛሬ ነውና ከፈጣሪህ ታረቅ አምላካችን ሀጥያትን እንጂ ሀጥያተኛን አይጠላም ከሴሰኞች ጋር አትተባበሩ1ቆሮ5-9እንዳለ መፅሐፍ ለሀጥያት ለሱስ
አትተባበር።
ቅድም እንደዛ ሲነድ የነበረው እሳት አሁን አመድ ሆኗል! ሰው እንዲ ነው..ወጣትነት ማያልፍ ይመስላል ግን እንደዚ አመድ መክሰማችን አይቀርም።''ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን
ትወልዳለች"ያዕ1፥15 ስለዚህ የሞት ሞት እንዳትሞት የስጋ ምኞትህን ለፈጣሪ አስገዛ።
እኔም ሱሰኛ ነኝ ግን የፆም የፀሎት የስግደት ነው።ቅድም መስቀሌን ጥዬው ሳይሆን አንተ ተከትለከኝ እንድትመጣ ስለፈለኩ ነው ጥዬው የመጣሁት።አንዳንዴ ሰወች ወደ ቤ/ክ መምጣት ሲደክሙ ቤ/ክ ወደ ህዝቡ መሄድ አለባት እኔ የቤ/ክ አንድ አካል ስለሆንኩ አንተን ፈልጌ መጣሁ ታድያ ተሳክቶልኛል?
በትክክል አባ!ሁለተኛ እዚ ሀጥያት ውስጥ አልገባም እንደኔ ያሉትንም ለማምጣት ቃል እገባለሁ ይቅር በሉኝ አባቴ(እንባ ተናንቆኝ እግራቸው ስር እየወደቅኩ
እግዚአብሔር ይቅር ይበልክ በል ተነስ
አባ በፈገግታ ተሞልተው አነሱኝ እኔም የማትጠገብ ምስር እና የማይጠፋ ምክር ተመክሬ ቡራኬ
ተቀብዬ ልቤን ለፍቅሩ አስገዝቼ ወደቤቴ
ተመለስኩ።

✍️chaቻ

@cherstianawiwetat
ግድያው እንደቀጠለ ነው

ለቤተክርስቲያን ምቹ ጊዜ ነው 🤬🤬🤬

የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ተገደሉ

ይሄ ግፍ የተፈጸመው በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።ለጊዜው ማንንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ አካላት ተገደሉ::

ግድያው የተፈፀመው ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ ነበረ፥ ሟቾቹ አንድ መሪጌታና ዲያቆንን ጨምሮ አምስት የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ታውቋል።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ይታወሳል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።

ምንጭ ፦ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
**በሙዚቃ እና በድግስ የሚከብር ፈጣሪ የለንም።”

ህዝበ ክርስቲያን ሆይ በዳንኪራ ሐይማኖታዊ በዓላቶቻችንን መዘባበቻ ከማድረግ እንቆጠብ🙏🙏🙏

ቅበላ እና ፍሰካን እየጠበቁ በኦርቶዶክስ በዓላት ላይ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጁ አካላትን እቃወማለሁ‼️
2024/05/21 04:46:34
Back to Top
HTML Embed Code: