Forwarded from አማዶን
“ሁሉ ነገር እርጋታ እና ጥበብ ይጠይቃል። በተለይ ቡና!”
እትዬ ምናለሽኝ ናቸው እንደዚህ የሚሉት። እትዬ ምናለሽኝ ቡና ማፍላት ይወዳሉ። ቆንጆ ቡና ያፈላሉ። ከየት እንደሚያገኙት ገና ባይደረስበትም ደሞ አሪፍ እጣን ያጨሳሉ። እጣኑ ግን የሱዳን ነው ይላሉ የሰፈር ሰዎች። ግን አምናለሁ ሱዳን እንዲህ አትራቀቅም። ደርባባ ናቸው ምናለሽኝ። ዘርፈፍ ብለው ከተቀመጡ ከቀሚሳቸው ጋር፥ ከዚያ ረከቦት ላይ የሚያነሳቸው የለም። ሰው ጠጥቶ የሚረካ አይመስላቸውም።
“ጠጡ እንጂ!” ይላሉ። “ገና አራተኛው ነው” ይላሉ።
እንግዲህ እትዬ ቡና ለማፍላት የሚቀመጡት የበዓል ቀን ወይም ደስ ደስ ባላቸው ሰንበት ነው። የሚያፈሉ ቀን ግን ቤተሰቡ (ባለቤታቸው፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቸው) ገና በጠዋት እንዲያውቁ ይሆናል። መጀመሪያ ለቤት ሰራተኛቸው ለእንጉ ይነግሯታል። “ዛሬ ቡና የማፈላ ነኝ። ማንም እንዳይረብሸኝ እ?” ይላሉ። እንጉ ከዚያ በኋላ እየተወረወረች በየክፍሉ እየገባች ይህን መልዕክት ታደርሳለች። “ቡና አፈላለሁ ብለዋል” “ቡና አፈላለሁ ብለዋል” “እትየ ያፈላሉ ዛሬ”...
ቤቱ ትርምስምሱ ይወጣል። እቃ እዛ ጋር ይወድቃል። እንዷ የልጅ ልጃቸው ታለቅሳለች። እንደገና ትሪ ይመስላል የሆነ ነገር፣ እሱም ይወድቃል። የባኞ ቤት ፍለሽ ሿሿሿ! ይላል። ፍልስልስ ይላል እንዳለ።
“አንቺ እንጉ! እንጉ!” ይላሉ እትዬ።
“አቤት እትየ”
“አላልኩሽም ማንም እንዳይረብሸኝ?!
አላልኩሽም ማንም እንዳይረብሸኝ?!”
እንዲህ ይበሉ እንጂ እሳቸው በሚያፈሉ ቀን ሳይደፈርስ አይጠራም። ተንኳኩቶ፣ ተንጓጉቶ ነው በኋላ አየሩ በሰላም የሚተነፍሰው።
ረከቦቱ ይሰናዳል። ሲኒዎቹ በወግ በወግ ሆነው ይደረደራሉ። ነጭ ስስ ጨርቅ ይለብሳሉ። አንድ አንገታም ጀበና በቀኝ በኩል ይሆናል። እሳቱ በግራ በኩል፣ ማጨሻው ፊት ለፊት ይቀመጣሉ። በጨርቅ ያበጠ ዱካ አለ ወዲህ ደሞ። የቤተሰቡ አባላት ሳሎን ውስጥ።
ከዚያ ጥለቱ ሰማያዊ የሆነ ነጭ ቀሚስ ለብሰው እየተንጐራደዱ የሚመጡት እትዬ ምናለሽኝ ናቸው። ፍስስ እያሉ ይራመዳሉ። አደገኛ ጥላ አላቸው ደሞ። ግርማ ሞገስ የምንለው ይህን ነው። በመቀጠል ይቀመጣሉ ዱካው ላይ።
እጣኑን ነ ስ ነ ስ ነ ስ... ጭስስስስ...
“ማነሽ እንጉ ማራገቢያውን አምጪልኝ። የቡና ቁርሱስ?”
ቡናው ይቆላል። ሿ ሿ ሿ... ችስስ...
የሚቆላው ቡና ሽታ በአየር ላይ...
አንደኛ ቡና ይወጣል። በጥቁርና በቡኒ መሃል ያለ፣ ጡንቻ ያለው ቡና ይባላል?
ከጀበናው ሸረረር እያለ ይወርዳል። “ነፋስ አታዩም። ዝናብ አታዩም።” እኚህ ባዶ ሲኒዎች ግን በቡና ይሞላሉ።
“ነይ ስጪያቸው እንጉ”
እንጉ እየተጠዳደፈች ስኒዎቹን ስትቀበል “አይ! አይ!” ሲሉ ይበሳጫሉ እትዬ።
“ቀስስ በይ እንጂ። ሁሉ ነገር እርጋታና ጥበብ ይጠይቃል። በተለይ ቡና!”
“በተለይ ቡና!”
@amadonart
@coffeeandscribblings
ሎዛ ናት የሀሳቡ ባለቤት።

The art, inspiration and lessons behind animated movies... 😢😢😢
These three are awesome.
These three are awesome.
በዚህች ጉድ በምታኽል ምድር ላይ አንድ የራሴ ቦታ እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር። ነጥብም ብትሆን... ትንሽዬ ክብም ብትሆን... ሰውም ብትሆን... ግን የኔ የምላት። አንቺን አገኘሁሽ። ለዚያውም ባለአራት ግድግዳ። ለዚያውም ጠባብ ክፍል። (ልጋራሽ ብሎ ሰው ቢመጣ እንኳ ጭንቅ ጭንቅ ብሎት እንዲወጣ የምታደርግ።)
ስደክም ውዬ ወደአንቺ መጥቼ በሬን ስዘጋ የምወደው ሰው ያቀፈኝ ይመስለኝ ነበር። 'ሀይ!!!' ብዬ መጮህ ያሰኘኛል። ትዝ ይልሻል ያንን የፋርስ ግጥም ግንባርሽ ላይ የለጠፍሁልሽ?
Agar firadus bar ruye zameen ast
O hameen ast hameen ast hameen ast
እውነት ገነት በምድር ላይ ካለ ይህ ነው ይህ ነው ይህ ነው።
ስወድሽ። ጠረንሽን ስወደው። (የእኔ ጠረን አይደለም። እኔ የአንቺን ይዤው ስለምወጣ ነው።)ነጭ ቀለምሽን ስወደው። መኃል ላይ ያልሆነ አምፖልሽን ስወደው። በጥግ ጣርያሽ በኩል ያለውን ተነቅሎ የተሰካ በዚያም የተነሳ አበጥ ያለ ችፑድ ስወደው። ግጥም የማይለው በርሽ ሲዘጋ የሚያወጣውን ድሞጽ ስወደው። እንደእኔ ትመስኛለሽ። ፍጹም ያልሆንሽ። ብስምሽ። ብትስሚኝ። ብንተቃቀፍ።
ግን አጨናንቄሽ ነበር አይደል? እናቴ፣ ''አቤት ይሄ ክፍል አፍ ቢኖረው ይጮህ... እግር ቢኖረው ይሮጥ ነበር።'' ትላለች። ''ሴት እኮ ናት።" ልላት እያልሁ አፌን ይዛለሁ። ግድግዳሽን በቢጫ ወረቀቶች ሞላሁት። 'መዝ 31፥17' 'Namak' 'Day 65 of stay at home' 'Help a girl go to school' ምናምን ምናምን። እንደዚያ ስላደረግሁ ደበረሽ? በመካከልሽ ጠረጴዛ አቁሜ ከአራት እግሩ አንዱ እስኪንሻፈፍ በደብተሮች እና በመጻህፍት ስለሞላኹት ከፋሽ? ወለልሽን በወረቀቶች ስለሞላሁት ከፋሽ? አልጋውን ስላላለበስሁ ከፋሽ? አውቃለሁ አይደብርሽም። አውቃለሁ አይከፋሽም። የጠቀሙኝ መስሏቸው ወረቀቶቹን ሲሰበስቡት፣ ጠረጴዛውን ሲያስተነፍሱት፣ አልጋውን ሲያለባብሱት ግራ እንደሚገባኝ እንደሚጨንቀኝ ሆድ እንደሚብሰኝ አይተሻል። በምዝርቅርቁ ውስጥ እንደተናበብን አንቺ ካልገባሽ ማን ይገባዋል? በዚህች ትልቅ ምድር ያገኘሁሽ ትንሽዬ የኔ ቦታ አይደለሽ? አፍ ቢኖርሽ ትጮኺ ነበር? አይመስለኝም። አራቱ ግድግዳዎችሽ ቢያወሩ ምን ይሉ ነበር? ይህች ልጅ እዚህ ክፍል እየገባች ምንድን ነው የምትሰራው? ሲሉሽ ትነግሪያቸው ነበር? እንዳትነግሪያቸው። ቀንተውብሽ እስኪያፈርሱሽ እኔንም አፈር እስኪበላኝ ዝምምም በያቸው።
ስወድሽ። ስትናፍቂኝ።
ክፉ ጊዜ ለይቶን የሌላ ሆነሽ አይሻለሁ። እቀናለሁ? አልቀናም። ከነቢጫ ወረቀቶችሽ ከነጠረንሽ ከነቀለምሽ ከነሙቀትሽ ውስጤ ትኖሪያለሽ። ከአዕማዱ አንዷ ሆነሽ... እወድሻለሁ።
ሚያዝያ 27/2013

👍1
People who hate coffee, capitalists, extremists, taxi drivers making us overpay, shopkeepers hiding the oil, people who don't like reading, readers who think fictions are just lies and waste of time, guys catcalling, the guy who was going to beat me up for calling out his catcalling, all misogynists, law enforcers choosing being right than being kind, people who make me wait, people who choose violence... I love you. You keep me going. @coffeeandscribblings
Helen brought yet another marvel to our lives. Helen (and I) invite you all to check out the YouTube channel: Jubilee
Hello,
Besides being an awful channel manager, I am also a reproductive health advocate. We recently started a podcast on Sexual and reproductive health and rights topics. (I believe in podcasts turns out).
Here is our channel:
@tankua
Please follow us. Please let us know what you think.
Thank you

የሚወደኝ እና 'የከተማው መናኝ' የሚለውን መጽሐፍ የሚገዛልኝ ሰው እፈልጋለሁ።
ማጥናት ሲገባኝ የመጽሐፉን ምርቃት በባላገሩ ቲቪ አያለሁ።
ሞት እንዴት ክፉ ነው?
ጀማነሽ የምትባለው መልካም ሴት እና የኤልያስ መልካ የቤት ሰራተኛ እና ረዳት ቀረበች። ስታወራ እንባዬን አስመጣችብኝ።