Telegram Web Link
Our hearts should be like our endometrium-s. Shedding off every time love goes... bleeding and squeezing out everything... all ready for a new one.

It is not that easy though, is it? Do you know with the number of times you ovulate the risk of developing ovarian ca increases?Do you know what I mean?
@coffeeandscribblings
የምትወዷቸው ቃላት ምንድን ናቸው? ስለትርጉማቸው አይደለም። ምላስ ላይ ስለመጣፈጣቸው እና ስለሚሰጧችሁ የሆነ ስሜት።


ሀቅ
ኢዮር
አክርማ
ቀለማት
ደርባባ
ማለዳ
አቦል
ውድድ
ሚያው
@coffeeandscibblings
Forwarded from አማዶን
መቼም ቢመዘምዙት ቢመዘምዙት የማያልቅ ነገር ሀዘን ነው። ብዙ ነገር አለ የሚያሳዝን። በተለይ ሆስፒታል ውስጥ። በተለይ ህፃናት ታመው። ገና አፍ ያልፈቱ ህፃናት በልብ ህመም ተኝተው።

* * *

Pediatrics በብዙ መንገድ የተለየ attachment ነበር።


✓ Clerk ለማድረግ ስትሄዱ የሚጠብቋችሁ ህፃናት ምናልባት ኦክስጅን ላይ ናቸው። ምናልባትም ከህመማቸው የተነሳ ሲያለቅሱ የዋሉ ናቸው። ገና ነጭ የለበሰ ሰው ሲያዩ የሚሸበሩ ወይም ስትነኳቸው ለመሸሽ የሚፍጨረጨሩ ናቸው ግን ቀስስ ብላችሁ ትግባባላችሁ። Sthetescope, Name tag ወይም እስክርቢቷችሁን ትሰጧቸዋላችሁ። ማስክ ቢኖርም አቀራረባችሁ በፈገግታ ነው። እና አልጋቸው ላይ ሆነው ፈገግ ይሉላችኋል። ሊጫወቱ ይፈልጋሉ።

ብዙ ጊዜ አዋቂ፣ ሲያመው ያቃስት ይሆናል። ጋብ ሲልለትና ሲሻለውም ግን ፊቱ አይፈካም። ራሱን ያዳምጣል። ኮስተር እንዳለ ነው። ጠያቂ “ተሻለህ ወይ?” ሲለው፣ “ያው ምንም አልል” ይላል። ህፃናትስ? እንዲህ ያለ ነገር አያውቁም። ከሁለት ሶስት ቀን በፊት ኦክስጅን ላይ ሆኖ ቁና ቁና ሲተነፍስ የነበረ ልጅ፣ ዛሬ ሲሻለው ward ሲሯሯጥ ታገኙታላችሁ። ለውጣቸውን መደበቅ አይችሉም።


✓ እናቶች። እያጠቡና እየተንከባከቡ፣ ቀንና ሌት እየባተቱ ልጆቻቸውን የሚያስታምሙ እናቶች ደሞ አሉ። የልጃቸውን ችግር በዝርዝር የሚናገሩ እንዳሉ ሆነው፣ አንዳንድ እናቶች ደሞ “ደህና ነው አሁን” ይሏችኋል። “መጀመሪያ ምን ሆኖ አመጣሽው?” ስትሏት “ትንሽ አለቀሰብኝና አመጣሁት፣ አሁን ግን ደህና ነው” ትላችኋለች። ልጇን እንዲያመው አትፈልግም። እና የልጁ ትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ እያለ እያየች፣ የምትለው “ይሻለዋል ከቅድም” ነው። አንጀት ይበላል ይሄ ይሄ። በመሃል እየጠየቃችኋት ደሞ “ጠዋት አካባቢ ግን የተወሰነ አስታውኮታል ግን ያው ምግብ አብዝቼበት መሰለኝ። ችግር የለውም አደል?” ብላ ‘ሁሉም ሰላም ነው’ የሚል ማረጋገጫ ትጠብቃለች። Unfortunately ሁሉም ነገሮች ሰላም ሊሆኑ አይችሉም። እንደ ቅዱስ ጳውሎስ አይነት ሆስፒታል ደሞ Most cases referred ናቸው። ቀላል ላይሆን ይችላል።


✓ ነፍስ ያለወቁ ህፃናት ‘እንዲህ ሆንን’ አይሉም። የሚያመጧቸው ወይ ሲነጫነጩ ነው፣ ወይ ምግብ እምቢ ሲሉ ነው፣ ወይ ትንፋሻቸው ሲፈጥን ነው... የትኛውም ሰው የሚያልፍበት የእድገት ሂደት ቢሆንም እንኳን የበለጠ ለሰው የምታዝኑበት ጊዜ ይህ እድሜ አስኪመስላችሁ ድረስ ይሰማችኋል። ምንም ባይደረግለት እንኳን ሲያወራ ይቀለዋል ሰው።

✓ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ከሚታከሙ ህፃናት መሃል በልብ ህመም የሚሰቃዩት ትንሽ አይደሉም። ያቺን በምታክል ትከሻ ላይ የሚጫነው ሸክም ከባድ ነው። እንደ ልብ መሆን በሚፈልጉበት እድሜ ልባቸው ስትለግም፣ ብስጭትም ጭምር ይይዛችኋል። “ይሄ ነገር fair አደለም። እነዚህ ልቦች ንፁህ ናቸው። እዛ ግን ህፃናትን የሚደፍሩ ክፉ ልቦች ሞልተዋል።” ተብሎ አቤቱታ አይቀርብ ነገር። ማንም ወላጅ፣ ይህ ህመም እንደ ወጀብ ቢመጣ ልጁን ለመከለል አይዳዳም ነበር ግን ያው...
ቢመዘምዙት ቢመዘምዙት አያልቅም ሀዘን፣ ግን “ልጄ ጡት ትንሽ እንደጠባ፣ ትንፋሽ ያጥረውና ያቆማል” ሲሏችሁ የተለየ ነው።


✓ አንዲት የ 12 አመት asthmatic patient ነበረችኝ። ከአባቷ እና ከታናሽ እህቷ ጋር በጦርነቱ ምክንያት ከወልድያ ተፈናቅለው የመጡ ነበሩ። ያረፉበት ቤት አንድ ክፍል ነው። ይህን ክፍል ከሌሎች 7 ሰዎች ጋር ይጋሩታል። 10 ሆነው በዚህች አራት በአራት ክፍል ሲኖሩ ‘በቂ አየር’ ብሎ መጠየቅ ቅብጠት ነው። እና እቺ ልጅ exacerbate አድርጐባት መጣች። እንባዋ ዱብ ዱብ እያለ ትተነፍሳለች። ተሽሏት በነጋታው የወጣች ቢሆንም ‘ልገልፀው የማልችለው የጥፋተኝነት ስሜት ግን ተሰምቶኛል’ ለማለት ያህል ብቻ ነው እዚህጋ የፃፍኳት። እናንተ አሁን የተሰማችሁን አይነት።


***

አንብባችሁ እዚህ ከደረሳችሁ፣ ለትዕግስታችሁ ራሳችሁን ሸልሙ። “6710” ላይ ላኩ አንድ መልዕክት። ለህፃናት የልብ ማዕከል ነው።


አማዶን



@amadonart
This is Brittany Howard. The song is one of Joni Mitchell's. It is a deep song and I think this is just an amazing performance.

It gave me goosebumps. 🙃 You will love it too.
አባ ይማሩኝ
ዶሮም ብር አወጣች፤ እኔም ስጋ አማረኝ።

ከ50 ሳንቲም፣ 1 ብር፣ ከ1 ብር 2 ብር እያለች እዚህ ደረሰች።
ቆንጅዬ፣ እኔ በ 1 ብር ሁለት ዶሮ በልቻለሁ። ነጫጭ ሻሽ ሻሽ የመሳሰሉ። በ77 ነው ሁለት ብር የገባው እኮ።
እሱ ነው የጠቀመኝ። እውነት።
(የጠዋት ማልጎምጎሞች፣ ለአላፊው ይሁን ለራስ ይሁን የሚወራው የማይታወቁ)
@coffeeandscribblings
ለአንድ ጊዜ ኑሮ ሀምሳ ጊዜ መሞት
ሊፈነዱ መድረስ ሳይፈነዱ መቅረት
ወደጥልቅ ጨለማ በሀይል መጎተት
ከሰፊ ብርኃን በክፋት መከስከስ
ሳይፈልጉ መሳም፣ ፈልገው አለመሳም
መበተን... መሰበር...
መፍራት፣ መጠራጠር፣ ማልቀስ
ጥርስ መንከስ
ለራሴ ያለሁት ራሴ ነኝ ማለት
መናፈቅ፣ መ.ና.ፈ.ቅ
የማያውቁትን ሰው... የማያውቁትን ሀገር... ማያውቁትን ቅጽበት
ዝም ብሎ መናፈቅ


መሳቅ
ተስፋ ማድረግ
ለመንገደኛ ሰው ዝም ብሎ መፈገግ
ህጻናትን መውደድ
ወደላይ እያዩ እንኳን ኖርህ ማለት
ሁሉንም ሰው አቅፎ ሳም ሳም ለማድረግ በጣሙን መፈለግ

አቤት... መኖር ማለት
@coffeeandscribblings
Forwarded from Sost Kilo
ደግሞ አንዳንድ ምሽት አለ ቀስተደመና የወጣበት የሚመስል።
@coffeeandscribblings
My friend and I talked about this:

If given a preview of life, like a movie with rating and all, how many of us would do it?
ግን ማን የማንንም preview ያምናል? የቢጫን ቢጫነት፣ የነጭን ነጭነት፣ የእንባን ጣፋጭነት እንዴት አድርገው ያሳያሉ? ጸሀይን ጀርባ አስቀጥቅጦ ንቃቃትን ማነቃቃትን ማን ያሳይኃል? ከእንቅልፍ ጠግቦ መነሳት... ከጓደኛ ጋር መሳሳቅ... ቆንጆ ፍርፍር በደንብ መብላት... ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ኋላ የሚመጣን እርፍ ማለት... በእናት እቅፍ ውስጥ መተኛት... የወተትን ነጭነት በእውነት ማን ያሳያል? ከአንገት መሳም... ቆንጆ ማየት... የባጥ የቆጥ እያወሩ ረዥም ሰአት መቆየት... የክራርን አንጀት መብላት... አስቴርዬን አወቀዬን አስቴር አወቀዬን... ልብን የሚያሞቅ ጨዋታ... የምትጣፍጥ ትንሽ ግጥም... ቡና ከጤናአዳም ጋር ተያይዘው ያለው ሽታ... እናም ሌላው ሁሉ ሁሉ ሌላው መኖርን ትንሽ የሚያቀል ትናንሹን ነገር ሁሉ... ማን እንዴት አድርጎ ያሳያል? ሊቀርብን? ሊቀርብኝ?
እንቢ በል። እንቢ ነው የምለው።
'እ ትወለጃለሽ?' ስባል ደጋግሜ ደ.ጋ.ግ.ሜ. ደጋግሜ አዎ እላለሁ።
@coffeeandscribblings
Whatever you do, read 'The book thief'.

And kiss that Saukrel.
እንዴት ነሽ?

እንደዚህ።

@coffeeandscribblings
Oh self! How beautiful! How close! @coffeeandscribblings
Can you help us by filling this form? It is very short but of great consequence to us. I thank you very much in advance.


Edit [4:44] Already got a response. Thank you very much responder. Hugs to you.
አባቴ፣ "ለምን ካፌ ትወጃለሽ?" ይለኛል።

ለሰዎች ድምጽ ነው። ለጣፋጭ ሙዚቃ ነው። ለቡና ነው።
@coffeeandscribblings
2025/07/07 12:43:26
Back to Top
HTML Embed Code: