እንደዚህ ብዙ ሳነብ ይደብረኛል። አዳም እንዲህ ቃላቱን እየደለቀ ሲያስጨፍራቸው፣ እኔ ምንድን ነኝ እላለሁ። አዳም አባቴ ይሆናል፣ ግን እቀናበታለሁ።
ደግሞ ሰማዩ እንዲህ አገልጋዬ ይመስል ፊቴ ሲነጠፍና አረንጓዴዎች የተለያየ ጥላቸውን ሲያጠሉ ይበልጥ እሸማቀቃለሁ። ከዚህ ድንቢጥ በምን በልጬ፣ ከአዳምስ በምን አንሳለሁ? በፈጣሪ አምሳል ተሰራሁ የተባልሁት ደግሞ እኔስ እንድፈጥር አይደለም ወይ?
ተፈጥሮ ያሸማቅቃል፤ ግዙፍ ነው። እንደአዳም ያለ ደራሲ ያሸማቅቃል። ከአማልክቱ ጋር ትከሻ እየተመታታ ይስቅ ይመስል።
@coffeeandscribblings

የሰፈሬ ልጆች መጎልመስ ያስበረግገኛል። ክረምት ሲመጣ ከቁመቴ አጥረው ይራገጡት የነበረው ኳስ፣ <<ከአሁን በኋላ ብታስገቡ ዋ>> የምላቸው፣ አመድ አመድ መስለው ሲጯጯኹ የነበረው ቀርቶ... ትናንሽ ጺሞቻቸውን እየጎተቱ የስልክ እንጨት እና ግንብ ተደግፈው እያልጎመጎሙ ያወራሉ። ስልክ አላቸው። ሰላም ስላቸው የድምጻቸው መጎርነን ይገርመኛል። <<ኧረ ልለፍበት>> ከማለት <<እንዴት ናችሁ?>> ለማለት መብቃቴ ይገርመኛል። ይመስገን ነው ብቻ።
@coffeeandscribblings
@coffeeandscribblings
እንዲያው ለጨዋታ እንዲያው ለነገሩ
ልብ የሚሰጥ ወዳጅ አለ ወይ በሀገሩ
Fikreaddis the underrated. I know she is 'rated' well even now but she needs more 'rat'ing.
As Helen said,
ባደግኹ ቁጥር እያደገችብኝ መጣች።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@coffeeandscribblings
ልብ የሚሰጥ ወዳጅ አለ ወይ በሀገሩ
Fikreaddis the underrated. I know she is 'rated' well even now but she needs more 'rat'ing.
As Helen said,
ባደግኹ ቁጥር እያደገችብኝ መጣች።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@coffeeandscribblings
ህይወትማ በጊዜ የፍጥኝ የተያዘች እስረኛ ናት። ግን እንደዚህ ባሉ ቅጽበቶች፣ ለትንሽ ጊዜ ነጻ ትወጣለች። ነገ የሚሆነው አይታወቅምና ዛሬን፣ አሁንን ነጻ እናውጣት።
የዛሬን... የአሁንን አትሂጂ። እንደዚሁ እንዳለሽው ሆነሽ ከፊቴ ቁጭ በይ። በኋላ ይቆጨናል።
(Fayaz Hashmi- Aaj jane ki zid na karo- ውርስ ትርጉም)
@coffeeandscribblings
የዛሬን... የአሁንን አትሂጂ። እንደዚሁ እንዳለሽው ሆነሽ ከፊቴ ቁጭ በይ። በኋላ ይቆጨናል።
(Fayaz Hashmi- Aaj jane ki zid na karo- ውርስ ትርጉም)
@coffeeandscribblings
Forwarded from አማዶን
28|10
አልፏል አልፏል
መከራዬ
ና ግደለኝ
ደስ’ታዬ።
በቃ በቃ
ጭንቀት ወዲያ
ይህንን ቀን
ያለ አላማ።
ልብ መምታት
ሰለቸኸኝ
ፍርሃት ሆይ
ሰለቸኸኝ
ባር ባር ማለት
ሰለቸኸኝ...
የእሮብ ሰንበት ሆኖልኛል
የጀርባ ዋና አምሮኛል።
ለአላርም ድምፅ
ሁለት ሞት
ለእንቅልፍ ማጣት
ሁለት ሞት
ለትኩረትም ሁለት ሞት
እመኛለሁ። እመኛለሁ።
ዛሬ እረፍት ሆኖልኛል
የጀርባ ዋና አምሮኛል።
(ከፈተና መልስ 😁)
አልፏል አልፏል
መከራዬ
ና ግደለኝ
ደስ’ታዬ።
በቃ በቃ
ጭንቀት ወዲያ
ይህንን ቀን
ያለ አላማ።
ልብ መምታት
ሰለቸኸኝ
ፍርሃት ሆይ
ሰለቸኸኝ
ባር ባር ማለት
ሰለቸኸኝ...
የእሮብ ሰንበት ሆኖልኛል
የጀርባ ዋና አምሮኛል።
ለአላርም ድምፅ
ሁለት ሞት
ለእንቅልፍ ማጣት
ሁለት ሞት
ለትኩረትም ሁለት ሞት
እመኛለሁ። እመኛለሁ።
ዛሬ እረፍት ሆኖልኛል
የጀርባ ዋና አምሮኛል።
(ከፈተና መልስ 😁)
የዚህ ሰው (የፍቅረ ማርቆስ ደስታ) መጻሕፍት እንደአሊ ሆይ አላሊ ሆይ ናቸው ለእኔ። በልጅነቴ ካርለት፣ ከሎ፣ ጎይቲ ምናምን አይኔ ውስጥ የተሳሉ ነበሩ። በአእምሮዬ ቁልጭ ብሎ የተቀመጠ ሀመር አለ። ሳድግ አንደኛ የማደርገው ሀመር መሄድ ነው እል ነበር። (አራተኛ ክፍል ሆኜ) አለመሄዴ ይገርመኛል።
ብቻ... ይሄ ሰው <ረ>ዎቹን እንደአስፋልት እየጠቀለለ ከመዓዛ ጋር ያወራው ነገር ሁሉ አፍ ውስጥ ማር ማር ይላል። እንደልጅ ያደርጋል።
ሰው መሆን የሚገርም ነገር ነው። አሁን አይኔን ስጨፍን የመጽሐፉ ሽፋን ከነአጻጻፉ እና ሽታው ይመጣብኛል።
@coffeeandscribblings
ብቻ... ይሄ ሰው <ረ>ዎቹን እንደአስፋልት እየጠቀለለ ከመዓዛ ጋር ያወራው ነገር ሁሉ አፍ ውስጥ ማር ማር ይላል። እንደልጅ ያደርጋል።
ሰው መሆን የሚገርም ነገር ነው። አሁን አይኔን ስጨፍን የመጽሐፉ ሽፋን ከነአጻጻፉ እና ሽታው ይመጣብኛል።
@coffeeandscribblings
አዳም አዳም አዳም
ሔዋን ረታ ነው መሆን የምፈልገው እለዋለሁ ለጓደኛዬ።
ለደቂቃዎች ያህል አዳምና የአዳም ስራዎች ከምድረ ገጽ ቢጠፉ የሀገራችን ስነጽሁፍ የኋልዮሽ ምን ያህል እንደሚፈረጥጥ አስበው እለዋለሁ ደግሜ።
አዳም ታላቄ ባይሆን... የእኔ እኩያ ቢሆን ቅናት አንገብግቦ ይደፋኝ ነበር። እንደትንኳሽ።
ቃላትንና አማርኛን እኛ ድኩማኖቹ ቢሳካልን ብለን ስናሽኮረምማቸው ስንውል... አዳም እርቃናቸውን አልጋው ውስጥ ያስገባቸው ይመስለኛል።
ሁሉ የሚወደው ነገር አልወድም። አዳምን ግን ዘረ አዳም ሁሉ ቢወደው እንኳ ውድድድድድድድድድድድድድድድድድድድ አደርገዋለሁ።
እንግዲህ እንኳን ተወለደ። ብዕሩ አይንጠፍ። ክንዱን ቁርጥማት አይንካው።
ዝም ብሎ አምስት የአዳም ወሬዎች
1. የምወደው የአዳም መጽሐፍ መረቅ ነው።
2. አዳም ስለቅቅል ሲጽፍ አንብቤ አንድ ቀን በቅቅል ጉምዥት ልሞት። መጽሐፉን መሳም ቀረኝ።
3. አዳም ረታ ሰው መውደድ ርዕዮተ አለማዊ መሆን ነው ይላል። ሶሻሊስት እንደምትሆን... ተኮላን ስትወድ ተኮሊስት ትሆናለህ ይላል። ደስ አይልም? ማር ማር አይልም? የወደድኋቸውን ሁሉ እያሰብሁ ራሴን ጎፈሬ አበጥሬ ጠብመንጃ ይዤ ምናምን አስባለሁ። ትልቅ ነገር ያደርገዋል መዋደድን።
4. መጀመሪያ የአዳም ረታን ያነበብኹት ማህሌትን ነው። አባቴ ከመስሪያ ቤታቸው ላይብረሪ ለክረምት ንባብ ተውሶልኝ። ድጋሚ ባለፈው ሳነበው አፌ ውስጥ እንባ አቀረርሁ። የአይን እንባ ማቅረር ምን ይገርማል? አፌ ውስጥ አይኔ ውስጥ የሌለ እንባዬ ተሰማኝ።
5. አዳምን እንዳታገናኙኝ።

አንተን ሳስብ ሆዴ ውስጥ ዝናብ እየዘነበ ይመስለኛል። ወላ ትልቁ አንጀቴ ላይ ትንሹ አንጀቴ እና ጉበቴ ደመና አጥልለው እየዘነቡ ይመስል።
ማታ ለብቻዬ ስቀመጥ እንደከሰረ ነጋዴ ሸቀጡን ከምሮ እንደሚተክዝ አስብኃለሁ። ዝም ብዬ ወድጄህ አስልቼ እንደተለየሁህ ማሰብ ያሳፍረኛል። አረጀሁ ማለት ነው።
እዚህ ታች ሆዴ ውስጥ ነህ። ቅብር አደረግኹኽ።
ውጬህ ክፉ ጊዜ ሲያልፍ ብተፋህስ? ያዋጣል?
@coffeeandscribblings
ማታ ለብቻዬ ስቀመጥ እንደከሰረ ነጋዴ ሸቀጡን ከምሮ እንደሚተክዝ አስብኃለሁ። ዝም ብዬ ወድጄህ አስልቼ እንደተለየሁህ ማሰብ ያሳፍረኛል። አረጀሁ ማለት ነው።
እዚህ ታች ሆዴ ውስጥ ነህ። ቅብር አደረግኹኽ።
ውጬህ ክፉ ጊዜ ሲያልፍ ብተፋህስ? ያዋጣል?
@coffeeandscribblings
How foolish I am, I saw life, I saw the earth
I saw
Everything
Except my own eyes
Pablo Neruda
አዳም ረታ እንደጠቀሰው
@coffeeandscribblings
I saw
Everything
Except my own eyes
Pablo Neruda
አዳም ረታ እንደጠቀሰው
@coffeeandscribblings
Coffee and Scribblings
There is something about Russian literature which stirs something in my heart and in many others I dare say. They are weirdly humane and not just in the good ways but in the unpleasant and almost cruel aspects of the human heart. Russian authors examine…
Are you reading these? I just finished reading the crucible and it was such a good read.