Telegram Web Link
በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ሃዋሳ ዲስትሪክ እና በስሩ የሚገኙ የቅርንጫፍ ሰራተኞች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ።
**************
ማዕድ ማጋራት መተሳሰብን፣አንድነትንና መደጋገፍን የሚያጠናክር ተግባር እንደሆነ በማሰብ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ቅርንጫፎች እና ዲስትሪክት ጽ/ቤት ሰራተኞች ከሲ/ብ/ክ/መ ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመሆን በማእከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ለሚገኙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋሩ።
በወረዳው ለሚገኙ አረጋዊያን፣ አቅመ ደካማዎችንና ጓዳቸው ለጎደለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዱቄት፣ ዘይት እና የሽንኩርት ድጋፍ አድርገዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ደንበኞች ከ50 ሺ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እንዳያወጡ ባንኩ ያረገው መክፈል ስላቃተው ሳይሆን በአገር ውስጥ በሚወጡ ሕግና እና ደንቦች መመራት ስላለበት መሆኑን አቶ አቤ ገለጹ።
*************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ይህንን የተናገሩት ሰሞኑን ከአዲስ ዋልታ ሚዲያ “ነፃ ሃሳብ” ጋር ባደረጉት ቆይታ ሲሆን ባንኩ የሚተዳደረው በሃገሪቷ ሕግና ደንብ መሰረት ሲሆን ብሄራዊ ባንክ ያፀደቀው የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ገደብ ሁሉም ባንኮች በጋራ በመነጋገር በባንኮች ማሕበር አማካኝነት ባቀረቡት ሓሳብ መሰረት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ለተለያዩ ችግሮች በቀላሉ የተጋለጠ መሆኑን የተናገሩት አቶ አቤ ደንበኞች የተለያዩ የዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን በመጠቀም የመገበያየት ልምዳቸውን ሊያዳብሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ኮንሰርት፣ ባዛር ሲያዘጋጁ
ፊልም/ቲያትር ሲያቀርቡ
የሚታይ የሚጎበኝ ሲኖርዎት
የመግቢያውን ትኬት
እኛ እንሽጥልዎት!
**********
በሲቢኢ ብር መተግበሪያ የትኬት ሽያጭ አገልግሎት
በቀላሉ ሚሊዮኖች ጋር ይደርሳሉ!

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
International Competitive #Bid (Re-Bid)
==========
Commercial Bank of Ethiopia invites interested and qualified bidders to participate on an International Competitive Bid (Bid No. 127/2023/24) for the supply of the under-listed items:

1. Wholesale Lending and Credit risk Management Solution
2. Loan Collection, Recovery and acquired asset Management Solution

Interested bidders can get the full information on our website using the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/CBE_Rebid_e7dff7d67d.pdf
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የሚስተናገድ አንድ ደንበኛ ባንኩን ከ70 እስከ 100 ብር ወጪ ያስወጣዋል ተባለ።
*************************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከሰሞኑ ከአዲስ ዋልታ ሚዲያ “ነፃ ሃሳብ” ጋር ባደረጉት ቆይታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕብረተሰቡን የባንክ አገልግሎት ለማስለመድ ለረጅም ዓመታት በርካታ አገልግሎቶችን በነፃ ሲሰጥ ቆይቷል ብለዋል፡፡

ባንኩ በየዓመቱ ለቴክኖሎጂ ማዘመኛ 3 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቋሚ ንብረቶች ግዥ 2 ቢሊዮን ብር እንደሚያወጣ የገለፁት አቶ አቤ፣ ይህን በየጊዜው እየናረ የሚመጣውን ወጪ በተወሰነ ደረጃ መጋራት የሚያስችለውን ስርዓት ለመዘርጋት ባንኩ በአንዳንድ አገልግሎቶቹ ላይ መጠነኛ ክፍያ ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል፡፡

አንድ ደንበኛ በባንኩ ቅርንጫፍ አገልግሎት ሲያገኝ ከ70 እስከ 100 ብር ድረስ ወጪ እንደሚያስወጣ የተናገሩት አቶ አቤ፣ ነገር ግን ባንኩ አሁንም በነፃ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንዳሉ እና ደንበኞች በቅርንጫፍ ከ1000 ብር በላይ ሲያወጡ የሚያስከፍለው ክፍያም ከ5 እስከ 10 ብር ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በቴሌግራም በተካሄደው 2ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር የአሸናፊዎች ዝርዝር፡፡

በዛሬው እለት (ሚያዝያ 29፣ 2016) ከምሽቱ 2፡30 በፌስቡክ ገፃችን (https://www.facebook.com/combanketh) በሚካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ይሳተፉ፣ ይሸለሙ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን በተመለከተ ለሚመለከተው አካል ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ፡፡
************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከሰሞኑ ከአዲስ ዋልታ ሚዲያ “ነፃ ሃሳብ” ጋር ባደረጉት ቆይታ ከእገታና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ጋር ተያይዞ የሚተላለፉ ገንዘቦችን አስቀድሞ ሊያውቅበት የሚችልበት መንገድ እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

አቶ አቤ እንዳሉት መሰል የገንዘብ ዝውውሮች ሲከናወኑ ለባንኩ መረጃ እስካልደረሰው ድረስ ህጋዊ ግብይይት እንደተፈፀመ የሚገመት ሲሆን፣ ነገር ግን የተፈፀመው የገንዘብ ዝውውር ለህገወጥ ተግባር መሆኑን ባንኩ ጥቆማ ከደረሰው ሂሳቡን ከማገድ ጀምሮ አስፈላጊውን ዝርዝር መረጃ ለሚመለከተው የህግ አካል ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
New job vacancy loading...
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በህገወጥ መንገድ የተወሰደበትን ገንዘብ ለማስመለስ በመደበኛው አሠራር የማይቻል በመሆኑ የወሳጆችን ምስል ለማውጣት መገደዱ ተገለፀ፡፡
*************

ይህን የገለፁት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ‘ነፃ ሀሳብ’ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቆይታ ነው፡፡

አቶ አቤ ባንኩ ገንዘቡን የወሰዱበትን ግለሰቦች ማወቅ እንደማይችል ይነገር እንደነበር ገልፀው፣ ነገር ግን ባንኩ ገንዘቡን የወሰዱትን በሚገባ እንደሚያውቅ ገልፆ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በርካታ ገንዘብ ያስመለሰ ሲሆን፣ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ግለሰቦች ፎቶ ለማውጣት እንደተገደደ ገልፀዋል፡፡
ለባለራዕይ ሴቶች...

የሴቶች ቁጠባ ሂሳብ
==========

ከመደበኛው ቁጠባ ሒሳብ የተሻለ ወለድ እና ሌሎችንም ተጨማሪ ጥቅሞች በሚያስገኘው
የሴቶች ቁጠባ ሂሳብ ቆጥቢ፤
ህልምሽን እውን ታደርጊያለሽ!

#CBE #women #saving #bankinethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ቁጥጥር ስርዓቱን ይበልጥ ማጠናከሩ ተገለፀ፡፡
*********
ይህን የገለፁት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ‘ነፃ ሀሳብ’ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቆይታ ነው፡፡

አቶ አቤ የባንኩ የሲስተም ቁጥጥር ስርዓት ከውጭ የሚመጣ ጥቃትን መከላከል፣ የትልልቅ ገንዘብ ዝውውሮችን ምንነት መለየት እና የአገልግሎት መቋረጥ ክትትል ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በባንኩ በቅርቡ ተከስቶ የነበረው ያለአግባብ የተፈፀመ የገንዘብ ዝውውር አይነት ችግር ከዚህ በፊት ገጥሞ ስላልነበር ከባንኩ የሲስተም ቁጥጥር ትኩረት ውጪ ሊሆን እንደቻለ አቶ አቤ ገልፀው፣ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ ተመሳሳይ ችግርን ፈጥኖ መለየት የሚያስችል የ24 ሰዓት የሲስተም ቁጥጥር ሥራ መተግበሩን ተናግረዋል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለሠራተኞች ደረጃውን የጠበቀ የደንብ ልብስ ማሰፋቱ ተገለፀ፡፡
**********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ‘ነፃ ሀሳብ’ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ባንኩ ዘንድሮ ተግባራዊ ላደረገው የአለባበስ ስርዓት ደረጃውን የጠበቀ የደንብ ልብስ ለሠራተኞች አሰፍቷል፡፡

በባንኩ የተተገበረው የደንብ ልብስ አለባበስ ስርዓት አዲስ እንደመሆኑ አንፃር ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የገለፁት አቶ አቤ፣ በቀጣይ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች እና ቢሮዎች ወጥነት ያለው የአለባብስ ስርዓት ለመተግበር ይሠራል ብለዋል፡፡
Vacancy
=======
Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following position:

1. Junior Mechanic

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website ( https://vacancy.cbe.com.et ) from May 09 – 15, 2024.

For requirements and other detail information, please refer to the attached document.
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/junior_mechanic_867c22f6d2.pdf
CBE Vacancy Site User Guideline.pdf
1.5 MB
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ማመልከቻ ድረ-ገፅ (https://vacancy.cbe.com.et ) ክፍት የሥራ ቦታዎች ለማመልከት የሚረዳ መመሪያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ‘ነፃ ሀሳብ’ ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቆይታ ብድር ሳይመለስ ሲቀር ባንኩ የሚከተለውን አሠራር በተመለከተ የተናገሩት
በኑር ስትመሩ
በሀላል ፈለግ ወደ ስኬት ታመራላችሁ!
****
ለእሴትዎ ተጠንቅቀን የሸሪዓ መርሆዎችን አክብረን
እንደ ፍላጎታችሁ ልናገለግላችሁ ዛሬም ተዘጋጅተናል

ሲቢኢ ኑር የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
#ሲቢኢ ኑር #ኑር #ሀላል# ስኬት https://www.youtube.com/watch?v=YRZBEXuxjIY
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሪፎርም የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ትስስርን ለማጠናከር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩ ተገለፀ፡፡
************************

ይህ የተገለፀው አይ - ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር እና ከናይሮቢ ሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ገበያ ጋር በመተባባር አዘጋጅተውት ከግንቦት 1 እስከ 2፣ 2016 በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው ሰባተኛው ዓመታዊ የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብን ታሳቢ ያደረገ የፋይናንስ ሪፎርም እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ማሞ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ እድገት እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረው፣ አጠቃላይ የፋይናንስ ተቋማት ቁጥር 121 መድረሱን፣ የተቋማቱ ጠቅላላ ሀብት 3 ነጥብ 4 ትሪሊየን ብር መድረሱን፣ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ብር እንዲሁም የብድር መጠን 2 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር መድረሱን እንደማሳያ አቅርበዋል፡፡ ።

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሪፎርም ብዙ መልካም እድሎች የያዘ በመሆኑ የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ትስስርን ለማጠናከር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን አቶ ማሞ ጨምረው ገልጸዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበርንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በወወከል በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልእክት የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ቤት ከመጣታቸው በፊት ትኩረት ለደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አንስተዋል ፡፡

የውጭ ባንኮቹ ወደ ሀገር ቤት ከመግባታቸው በፊት በውስን ዘርፎች እና ትርፍ ላይ ብቻ ሳያተኩሩ ተደራሽነት በሌለባቸው አካባቢዎች በመዝለቅ ለህብረተስቡ አገልገሎት መስጠታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባ ነው አቶ አቤ ያሳሰቡት፡፡

አቶ አቤ ይህንን ማድረግ ካልተቻለ ግን በሃገሪቱ ባሉ ባንኮች ያሉ ውስን የዘርፉ የተማረ የሰው ሃይል ሊያሳጣ እንደሚችል፣ በስራ ላይ ያሉ ደካማ ባንኮችም የመዋጥ አደጋ ሊደረስባቸው እንደሚችል እንዲሁም ዘርፉ ከህብረተሰብ አገልጋይነት ይለቅ ትርፍ ላይ ብቻ ያተኮረ እንዳይሆን ያሰጋል ብለዋል ፡፡

የአይካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚና የምስራቅ አፍሪካ ዓመታዊ የፋይናንስ ጉባዔ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ገመቹ ዋቅቶላ፤ ጉባዔው በዘርፉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና ትብብርን ለማጠናከር ዕድል እየፈጠረ ነው ብለዋል።

በጉባዔው ላይ ከምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ ከ450 በላይ የፋይናንስ ዘርፉ ባለሙያዎች እና መሪዎች፤ ፖሊሲ አውጭዎችና አማካሪዎች፤ የመንግስትና የግል ተቋማት፤ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችና ተወካዮች፤ የኢኮኖሚ ተንታኞችና ተመራማሪዎች እየተሳተፉ ነዉ።

ሰባተኛው የምስራቅ አፍሪካ ዓመታዊ የፋይናንስ ጉባዔ የዘርፉን ውጤታማነትና ትብብርን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ዛሬም ቀጥሎ ይውላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከወልቂጤ ከተማ ጨዋታ ያደርጋል፡፡
**********
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ቡድን እና ወልቂጤ ከተማ ዛሬ ግንቦት 2፣ 2016 ምሽት 12፡00 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን በ47 ነጥብ እየመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚጫወት ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ5ኛው ሳምንት መርሃ ግብር ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 0 ያሸነፈው ሲሆን፣ ወልቂጤ ከተማ ከ24ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ጨዋታዎች በፊት በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

መልካም እድል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን!
2024/05/28 20:02:06
Back to Top
HTML Embed Code: