Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል አሳክቷል፡፡
**********

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ድል አሳክቷል፡፡


እስከ እረፍት ምንም ጎል ባላስተናገደው በዚህ ጨዋታ፣ ከእረፍት መልስ ተጭኖ የተጫወተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ83ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል አሸናፊ ሆኗል፡፡

በድሉ የኢትዮያ ንግድ ባንክ በ56 ነጥብ ከተከታዩ መቻል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ማሳደግ የቻለ ሲሆን፣ ወደ ዋንጫው ይበልጥ እየቀረበ ይገኛል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ባለው አቋም የአራት ሳምንት መርሀ ግብሮች ብቻ በቀሩት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 ውድድር ዘመን ቀሪ ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒዮን መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ይጠበቃል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ከከፍተኛው ሊግ ፕሪሚየር ሊጉን በተቀላቀለ የመጀመሪያው ዓመት ዋንጫ በማንሳት ከሀዋሳ ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር ቀጥሎ ሶስተኛው ቡድን በመሆን ታሪክ ያስመዘግባል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ ደጋፊዎች በስታዲየም ተገኝተው ለቡድኑ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
2ኛው የኢትዮጵያ የሸሪዓ አማካሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደ፡፡
**************
የኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር 2ኛውን የሸሪዓ አማካሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2016 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዶል፡፡

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ የሼሪአ አማካሪዎች፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተግኝተዋል፡፡

በ2ኛው የኢትዮጵያ የሸሪዓ አማካሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ “የወለድ ነጻ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ - አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ተስፋዎች” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ቀጣይነት ያለው አስተማማኝ እድገት የሚያመጣ እንዲሆን አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚያስችሉ አበይት ነጥቦች ተነስተዋል፡፡

“የሸሪዓ አማካሪዎች ሚና ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ውስጥ” በሚል ርዕስ በባለሙያ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፣ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች የሸሪአ አማካሪ ቦርድ አባላትን ሰይመው የሚሰጡት አገልግሎት ለሀገር ዘላቂ የሆነ ልማት ለማምጣት፣ ሁሉንም ማኅበረሰብ ተደራሽ ያደረገ የባንክ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል ዓላማን ያነገበ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የሸሪአ ግቦቸን ለማወቅ እና ለመተግበርም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብን እንደሚጠይቅ ባለሙያው አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በበኩላቸው “የወለድ ነፃ አገልግሎት ባለፉት 10 ዓመታት ያሳለፋቸው እድገት አና ፈተናዎች ምንድናቸው“ በሚል ርዕስ የውውይት ሀሳብ በጉባኤው አቅርበዋል፡፡

አቶ ኑሪ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሕግ ማዕቀፍ ተሰርቶለት ወለድ በመሸሽ ከባንክ ርቀው ለነበሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ የዘረፉ ዋናው ስኬት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከወለድ ነፃ አገልግሎት ለሚሠጡ ተቋማት እውቀት ያለው የሰው ኃይል በብዛት ማግኘት አለመቻሉ እና በሀገር ውስጥ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችል የትምህርት ተቋም አለመኖሩ ዋናው ተግዳሮት መሆኑን አቶ ኑሪ አብራርተዋል፡፡

በዓመታዊው የሸሪዓ አማካሪዎች ጉባኤ የዘርፉ ሙሁራን እና የሥራ ኃላፊዎች ባቀረቧቸው ሌሎች የመወያያ ሀሳቦች መነሻነትም ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቆዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
የጉዞጎ መተግበሪያን ይጠቀሙ !
****
የጉዞጎ መተግበሪያን ተጠቅመው የበረራ ትኬትዎን ይቁረጡ!
ክፍያውን በሞባይል ባንኪንግ ይፈፅሙ!

#cbe #GuzoGo #mobilebanking

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
International Competitive #Bid
==========
Commercial Bank of Ethiopia invites interested and qualified bidders for International Competitive Bid No. 133/2023/24 for the supply of Retail credit Process Digitalization Solution.

Interested bidders can get the full information on CBE website using the following link:

https://combanketh.et/cbeapi/uploads/retail_credit_process_digitalization_solution_18d36d8c1b.pdf
2024/05/28 12:26:31
Back to Top
HTML Embed Code: