Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
+++++(ዘለሰኛ-ክበር ተመስገን )+++++
(ዘማሪቀሲስ +ዳዊት ፋንታዬ
(ግጥምና ዜማ +ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
ክበር ተመስገን ጌታችን ለዚህ ያደረሰከን
ሰላምን ስጣት ለምድሪቱ
አላስተኛ አለን ሁከቱ
የዘንድሮስ ጠብ ክፋቱ
ወንዱ ከወንዱ ሴት ከሴቱ
ምነው ወዳጄ ምነው
ይፍቱኝ አባቴ በጠዋቱ
ወጥቶ ቀሪ ነው ሰው ከንቱ
ይፍቱኝ ሳይል የበረረ
እንደታሰረ በዘያው ቀረ
ምነው ወዳጄ ምነው
ቅዳሴ ቅኔ ማኅሌቱ
አቤት ማመሩ አይ ውበቱ
ሥራውም ቀሏል ከትላንቱ
ተከፋፍለዋል ካህናቱ
ምነው ወዳጄ ምነው
ተጣልቻለሁ ከአባቶቼ
የጾሙን መብዛት ጠልቼ
አርባ ቀን ጾመን በነበር
ምነው ማማቱ ቢቀር
ምነው ወዳጄ ምነው
ወንድሜ ሲሄድ ሸኘሁት
መናፈቁን ግን ፈራሁት
የርሱ ሳይበቃኝ ደግሞ እኅቴ
ተኩላ መጣች ከቤቴ
ምነው ወዳጄ ምነው
(ዘማሪቀሲስ +ዳዊት ፋንታዬ
(ግጥምና ዜማ +ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
ክበር ተመስገን ጌታችን ለዚህ ያደረሰከን
ሰላምን ስጣት ለምድሪቱ
አላስተኛ አለን ሁከቱ
የዘንድሮስ ጠብ ክፋቱ
ወንዱ ከወንዱ ሴት ከሴቱ
ምነው ወዳጄ ምነው
ይፍቱኝ አባቴ በጠዋቱ
ወጥቶ ቀሪ ነው ሰው ከንቱ
ይፍቱኝ ሳይል የበረረ
እንደታሰረ በዘያው ቀረ
ምነው ወዳጄ ምነው
ቅዳሴ ቅኔ ማኅሌቱ
አቤት ማመሩ አይ ውበቱ
ሥራውም ቀሏል ከትላንቱ
ተከፋፍለዋል ካህናቱ
ምነው ወዳጄ ምነው
ተጣልቻለሁ ከአባቶቼ
የጾሙን መብዛት ጠልቼ
አርባ ቀን ጾመን በነበር
ምነው ማማቱ ቢቀር
ምነው ወዳጄ ምነው
ወንድሜ ሲሄድ ሸኘሁት
መናፈቁን ግን ፈራሁት
የርሱ ሳይበቃኝ ደግሞ እኅቴ
ተኩላ መጣች ከቤቴ
ምነው ወዳጄ ምነው
+ ተራ የማይደርሰው ተጠማቂ +
"ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው ሰውዬውም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡ ብሎ መለሰለት" ዮሐ.5:5-7
ይህንን ጥያቄና መልስ ሳይ በሽተኛውን ማናገር ያምረኝና እንዲህ በል ይለኛል :-
አንተ በሽተኛ ግድ የለህም የተጠየቅከውን መልስ:: እመነኝ ጠያቂህ ተራ ጠያቂ አይደለም::
የሚጠይቅህ ሲያደርቁህ እንደኖሩት አሰልቺ ጠያቂዎች አይደለም:: ጥያቄውም የሌሎችን ሰዎች ዓይነት ጥያቄ አይደለም:: ከፊትህ የቆመው የመጠመቂያውን ውኃ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሞላውን ውኃ የፈጠረ ነው::
"ወደ መጠመቂያው የሚያኖረኝ ሰው የለኝም" አልክን? የተጠየቅከውን መልስ እንጂ!
ወደ መጠመቂያው መግባት ትወድዳለህን? ብሎ ማን ጠየቀህ? ተው እንጂ! የጠየቀህ ማን እንደሆነ ባታውቅ እንኩዋን ጥያቄውን በደንብ ስማ::
ሰው የለኝም አትበለው : ስለመጠመቂያው ወረፋ አትንገረው : ስንት ሰው ቀድሞህ እንደዳነ አትቁጠርለት:: የጠየቀህ ግልፅ ጥያቄ ነው::
ልትድን ትወዳለህን?
እግዚአብሔር ፊት ስለ ችግርህ ክብደት ለምን ታወራለህ? ምን እንደሌለህማ እሱም ያውቃል:: አዎን እድን ዘንድ በለው:: ችግርህን ትተህ የምትፈልገውን ንገረው:: የችግርህ መወሳሰብና ሥር መስደድ ለእሱ የሚከብድ አይደለምና መዳን እንደምትሻ ብቻ በእምነት ንገረው የሚል ተግሣፅ በበሽተኛው በኩል ወደ እኛ ደረሰ::
🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌
መጻጉዕ (በሽተኛው) ቤተ ሳይዳ ከመጣ 38 ዓመት ሆነው:: ዳዊትና ሰሎሞን 40 40 ዓመት ነግሠው እንኳን ብዙ የምሬት ቅኔ ተቀኝተዋል:: ይህ ሰው አልጋ ላይ ሆኖ አርባ ዓመት ሊሞላው ሲል ምንኛ ተንገሽግሾ ይሆን?
ልብ በሉ ጌታችን በቤተልሔም ሲወለድ ይህ በሽተኛ በአልጋው ላይ ነበረ:: እረኞች ከብዙ መላእክት ጋር ሲዘምሩ እሱ የአንድን መልአክ መውረድና ውኃውን ማናወጥ እየጠበቀ ስድስተኛ ዓመቱን ደፍኖ ነበር:: ጌታችን የሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ደርሶ ወደ መጠመቂያው ሥፍራ ሲመጣም ይህ ሰው አልጋው ላይ ነው:: መጠመቂያዋን 38 ዓመት በተስፋ ሲጠብቅ ቆይቶ ሳይጠመቅባት ቀረ::
ጌታ ሆይ የማይደርሰኝን ወረፋ ከመጠበቅ አድነኝ:: እንድፈወስበት ባልፈቀድክበት ሥፍራ ዕድሜዬን እንዳልጨርስ ጠብቀኝ::
ወደ ሐዲስ ኪዳንዋ ቤተ ሳይዳ ወደ ቤተክርስቲያን ከመጣሁ ብዙ ዘመን አስቆጠርኩኝ:: ግን እስካሁንም ድረስ ከኃጢአት አልጋ ላይ አልወረድሁም:: መነሣት እፈልጋለሁ ግን አቃተኝ:: ልቤ እንጂ እግሬ ጸንቶ መቆም አልቻለም::
ፈረቃ የሌለብህን የሕይወት ውኃ አንተን ሊጠጡ ሲመጡ በዓይኔ እየተቀበልኩ ብዙዎች ጠጥተውህ ሲድኑ በዓይኔ እየሸኘሁ አልጋዬ ላይ ቀረሁ::
እኔ እንደተኛሁ ስንቱ ቀድሞኝ እንደዳነ ባየህልኝ:: ከእኔ በኁዋላ መጥተውስ ከእኔ በፊት ስንቶች ዳኑ?
ስንቱ ከኃጢአት አልጋ በንስሓ ተነሥቶ ያንተን ሥጋና ደም ተቀብሎ ተፈወሰ?
የቤተ ሳይዳው ሐኪም ሆይ ወደ አንጋፋው በሽተኛህ ወደ ጽኑዕ ሕመምተኛህ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ይሆን? ያን ሕመምተኛ "ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበረ" አውቀህ ያናገርከው ሆይ እኔን የምታናግረኝ መቼ ይሆን? እኔስ ብዙ ዘመን እንደሆነኝ አታውቅምን? ሰው የለኝም : ልብ የለኝም : ኃይል የለኝም : አቅም የለኝም ብዬ ብሶቴን የምነግርህ መቼ ይሆን?
"ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ" ዮሐ.5:8-9
አንተ ተነሥ ብለኸው የማይነሣ ማን ነው? እንኳንስ ከአልጋ ከመቃብርም ተነሥ ያልከው ይነሣ የለምን?
ግዴለህም እኔንም ተነሥ በለኝ:: ተነሥ ኃይልን ልበስ ያልከኝ እንደሆነ እንኳንስ "ሸክሜም ቀሊል ነው" ያልከው አንተ ያዘዝከኝ የራሴን ሸክም ቀርቶ የወንድሜን ሸክምም ተሸክሜ የአንተን ሕግ እፈጽማለሁ:: (ገላ. 6:2)
🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌
"ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ... ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፡ አለው" ይላል::
በሽተኛው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ እንደሔደ ሳነብ አንድ ነገር ልቤን አስጨነቀው:: ይህ ሰውዬ 38 ዓመት ሙሉ የኖረው በቤተ ሳይዳ ነው:: ክርስቶስ ድንገት ፈውሶት ሒድ ሲለው እሺ ብሎ ከዚያ መጠመቂያ ሥፍራ ከወጣ በኁዋላ ወዴት ሔደ?
የሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛው ሆይ እውነት ወዴት ሔድህ? ከመጠመቂያው መውጣትህን ሰምተን አድንቀናል:: ከዚያስ ወዴት ሔድክ? ዙሪያ ገባው አልተለወጠብህም? መንገድስ አልጠፋብህም?
ወደ ዘመዶች ቤት ሔድክ እንዳልል "ሰው የለኝም" ስትል ሰምቼሃለሁ::
አልጋህንስ የት አደረስካት? መቼም ሰባብረህ እንደማትጥላት የታወቀ ነው:: አልጋ ለታመመ ብቻ ሳይሆን ለጤነኛም ያስፈልጋልና አራት እግር እያላት ጥላህ ያልሔደችውን ዘመድህን መቼም በክብር ማስቀመጥህ አይቀርም::
ለማንኛውም እዚያው ምዕራፍ ላይ ኢየሱስ ይህንን በሽተኛ ዳግም በመቅደስ አገኘው ይላል:: ዮሐ. 5:14 ጌታ ከመጠመቂያ ቦታ አድኖ ያስነሣውን ሰው በመቅደስ ቆሞ አገኘው:: ይህ በሽተኛ እግሩ ሲጸናለት የሔደው ወደ ፈጣሪ ደጅ መሆኑ ያስመሰግነዋል::
ጌታ በመጠጥ ቤት ቢያገኘው ኖሮ ያሳዝን ነበር:: እግርህን ያጸናሁልህ ለዚህ ነው ወይ ብሎ ባዘነበት ነበር:: አሁን ግን ያዳነው ጌታ በመቅደስ አግኝቶት "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" አለው::
ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ክርስቶስ አንተንስ አላዳነህም? "ኸረ እኔ ሽባ ሆኜ አላውቅም:: ማንም እኔን ከአልጋ አላስነሣኝም ትለኝ እንደሆን እመነኝ ክርስቶስ እንደ አንተ ያዳነውስ የለም:: እርሱ እኔና አንተን ተነሡ ብሎ ያስነሣን ከ38 ሳይሆን ከዘላለም የሲኦልና የኃጢአት አልጋ ነው::
እኛን የፈወሰን አልጋችንን አሸክሞ ሳይሆን እሱ ራሱ እኛን ከነአልጋችን ተሸክሞን ነው:: ካላመንከኝ ነቢዩ ኢሳይያስን ጠይቀው "እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ" ሲልህ ትሰማዋለህ:: ኢሳ. 53:12 የእኛን በደል ተሸክሞ ጀርባው ምን ያህል እንደ ቆሰለ ባየህ:: ይህንስ ጀርባዬን ታያለህ የተባለውን ሙሴን ብትጠይቀው ሳይሻል አይቀርም::
ያዳነህ አምላክ አንተንስ የት ነው የሚያገኝህ? እንደዚህ ሰውዬ መቅደስ ያገኝህ ይሆን?
የትም ቢያገኝህ ግን ቃሉ አንድ ነው "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" ከሠላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት የሚብስ ምን ሊመጣ ነው? ካልክስ እሱን ከማየት ይሠውረኝ ብትል ይሻልሃል::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 10 2014 ዓ.ም.
ባሕር ዳር ኢትዮጵያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

+++ ለምን ትመታኛለህ?+++
ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ የአይሁድ ፋሲካ ለሦስት ጊዜ ተከብሯል፡፡ የመጀመሪያው ፋሲካ ጌታችን ቤተ መቅደሱን ያጸዳበትና በቤተ መቅደስ ሲሸጡ ሲለውጡ የነበሩትን ያስወጣበት ሲሆን በመጨረሻው ፋሲካም ሰሞን እንዲሁ ለሁለተኛ ጊዜ ቤተ መቅደሱን አንጽቶ ከፋሲካው ማግስት ተሰቅሏል፡፡ በሁለቱ ፋሲካዎች መካከል በነበረው ፋሲካ ደግሞ ጌታችን ወደ ቤተ ሳይዳ መጣ፡፡
ቤተ ሳይዳ የመጠመቂያው ስፍራ ስም ሲሆን ከአጠገቡ ደግሞ በጎች በር ነበር፡፡ (የበጎች በር በአሁኑ ሰዓት የቅዱስ እስጢፋኖስ (ሊወግሩት ያወጡበት) በር እና የአንበሳ በር ተብሎም ይጠራል) እንደሚታወቀው ዘመነ ኦሪት በግ መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት ነበር፡፡ ስለዚህ በዚያ በር መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ በጎች የሚገቡበት ነበር፡፡ በጎቹ ነውር እንደሌለባቸው ማለትም ቀንዳቸው እንዳልከረረ ፣ ጥፍራቸው እንዳልዘረዘረ፣ ጠጉራቸው እንዳላረረ እያገላበጡ የሚጠኑበት ፣ የአንድ ዓመት ተባዕት/ወንድ/ መሆናቸው የሚታይበት ሥፍራ ነው፡፡ ይህን መስፈርት አሟልተው ያለፉ በጎች ለመሥዋዕትነት ሲቀርቡ ለዚህ ብቁ ያልሆኑትን ግን ለይተው ፣ በአለንጋ እየገረፉ ያስወጡአቸዋል፡፡
በቤተ ሳይዳ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያዪቱ ወርዶ ውኃውን አንዳንድ ጊዜ ያናውጥ ነበር፡፡ ይህ መልአክ ‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ፣ በበሽታም ላይ ሁሉ የተሾመ› የስሙም ትርጓሜ ‹እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው› ማለት የሆነ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነበር፡፡መልአኩ ውኆችን ለመቀደስ ፣ ጸሎትን ከሰው ወደ ፈጣሪ ለማድረስ ወደ ውኃው ይወርድ ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ውኃ በራሱ ማዳን ባይቻለውም ቅዱሳን መላእክት የነኩት እንደሆነ በረከትና ፈውስ እንደሚሠጥ የሚያስረዳን ነው፡፡ ውኃው ከተነዋወጠ በኋላ ግን መዳን የሚቻለውመጀመሪያ መግባት ሲቻል ነበር፡፡ በዚህ የጠበል ሥፍራ በነበሩ አምስት መመላለሻዎች ‹በሽተኞች ፣ አንካሶች ፣ ዕውሮችና እግራቸው የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡በተለይ ደግሞ አንካሶች ፣ ዕውሮችና እግራቸው የሰለለ ሰዎች በቁጥር የሚበዙት ከሌላው በሽተኛ በተለየ እነሱ የውኃውን መንቀሳቀስ አይተው ለመግባት እንዳይችሉ ወይ ዓይናቸው ማየት አይችልም ፤ ያም ባይሆን መንቀሳቀስ ያቅታቸዋል፡፡ ገብተውም እንኳን ቢሆን ድንገትከእነሱ ቀድሞ የገባ ሰው ካለ እነሱ ስለማይፈወሱ ከውኃው መልሶ የሚያወጣቸውም ሰው ያስፈልጋቸዋል፡፡ አለዚያ ገብተውም አውጪ አጥተውሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም በእንዲህ ዓይነት ችግር ለባሰ ነገር የተዳረገም ሊኖር ይችላል፡፡
ከእነሱ ቀድሞ የሚድነው እንግዲህ ሁለት ዓይነት ሰው ነው፡፡ አንደኛው በሽታው ለመንቀሳቀስ የማያግደው ሆኖ እያለ የእነሱ ይብሳል ብሎ ሳያዝን የሚገባ ነው፡፡ መቼም ሰው እንኳን ቀድሞ የገባ ሰው ብቻ በሚድንበት ሥፍራ ቀርቶ ፤ በማንኛውም ሰዓት ቢገባ በሚዳንበት የጠበልሥፍራ ‹ከእኔ በሽታ የእገሌ ይብሳል ፤ እስቲ ቅድሚያ ልስጠው› ሲል ብዙ ጊዜ አይታይም፡፡ ስለዚህ እነዚህን ደካሞች ቀድሞ የሚገባ በሽተኛ ብዙ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ወደ መጠመቂያው ሊወረውሩት የሚጠባበቁ ዘመዶች ያሉት ፣ አለዚያም ዘመድ የሚያፈራበት ገንዘብ ያለው በሽተኛ ደግሞ ሌላው ቀድሞ ወደ መጠመቂያው የሚገባ ነው፡፡
በዚህ ሥፍራ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል የተኛ በሽተኛ (በግእዙ መጻጉዕ) ነበር፡፡ እንግዲህ ሠላሳ ስምንት ዓመት ማለት የጉልምስና ዕድሜ ነው፡፡መጻጉዕ የመጣው በዐሥር ዓመቱ ነው እንኳን ብንል አሁን አርባ ስምንት ዓመቱ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጌታችን በኋላ ‹የሚብስ እንዳይደርስብህ ደግመህ ኃጢአትን አትሥራ › ብሎ ስለተናገረ ከመታመሙ በፊት ለዚህ ጽኑ ደዌ የሚዳርግ ኃጢአት ለመሥራት የሚችልበት ዕድሜ ላይ ደርሶአልማለት ነው፡፡ መቼም ክፉ ደግ በማያውቅበት ሕጻንነቱ በድሎ ‹‹የልጅነቱ መተላለፍ ታስቦበት›› ታመመ ብሎ መናገር ይከብዳል፡፡ ብቻይህ ሰው የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ ያህል በአልጋ ላይ ሆኖ በቤተ ሳይዳ ተኝቶአል፡፡ ጠበል ሊጠመቅ ሲጠባበቅ በጸጉሩ ሽበት ፣ በግንባሩ ምልክት አውጥቶአል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ግርግም ውስጥ ሲወለድም ይህ በሽተኛ በዚሁ መጠመቂያ ስፍራ ነበረ:: ድንግል ማርያም የወለደችውን ሕጻን በበረት ውስጥ ስታስተኛው ይህ በሽተኛ አልጋው ላይ ከተኛ ስድስት ዓመት ደፍኖ ነበር::
ከሁሉ የሚያሳዝነውደግሞ ይህ ሰው አልጋው ላይ ሆኖ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲፈወሱ መመልከቱ ነው፡፡ ከእሱ በኋላ መጥተው ከእሱ በፊት ድነው የሚሔዱ ሰዎችን ማየት እንዴት ይከብደው ይሆን? እንደሱ ብዙ ዘመን የቆዩት ሲድኑ ሲያይ ተስፋው ሊለመልም ይችላል፡፡ በመጡ በአጭር ጊዜ ዘመደ ብዙ በመሆናቸው ብቻ የሚድኑ ሰዎችን ሲያይ ግን ልቡ በኀዘን ይሰበራል፡፡ ዓመቱ በረዘመ ቁጥር ተስፋ ቆርጦ ቤተ ሳይዳን ቤቴ ብሎ ከመኖር በስተቀር ምንም የሚታየው ነገር አይኖርም፡፡ እግዚአብሔርን በመከራው ውስጥ ተስፋ እያደረገ ይጽናናል አንዳንል ደግሞ እንደ ጻድቁ ኢዮብ ወይም እንደ በሽተኛው አልዓዛር ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበረው ቢሆን ኖሮ መቼ ለዚህ በሽታ የሚዳርገው ኃጢአትይሠራ ነበር? ስለዚህ በቃለ እግዚአብሔር ይጽናናል ማለትም ያስቸግራል፡፡ያም ሆነ ይህ ይህ ሰው እጅግ ተሰቃይቶ ነበር፡፡
ጌታችን የዚህን ሰው ችግር ብቻ ሳይሆን ብዙ ዘመን እንደዚህ እንደነበረ ያወቀው ማንም ሳነግረው ነበር፡፡ በሽታውን ከነመንሥኤው አስቀድሞ ያውቃልና ወደዚህ የብዙ ዓመታት በሽተኛ መጣና ‹ልትድን ትወዳለህን?› አለው፡፡ ጌታችን የሚፈልገው ይህንን ሰው መፈወስ እንጂ የራሱን ማንነት ማሳየት ስላልነበረ ‹ላድንህ ትወዳለህን?› አላለውም፡፡ በዚያ ላይ ይህ ሰው የጌታን ማንነት አያውቅም፡፡ ጌታችን ‹ስታምኑብኝ ብቻ ነው የምፈውሳችሁ›የሚል አምላክ አይደለም ፣ ለሁሉ ፀሐይን የሚያወጣ ፣ ለሁሉ ዝናምን የሚያዘንም አምላክ ይህንን ሰውም ለመፈወስ እስኪያምነውም አልጠበቀም፡፡
ይህ በሽተኛ‹ልትድን ትወዳለህን?› ሲባል የሠጠው መልስ እጅግ የሚያስገርም ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሽታ አመል ያጠፋል፡፡ በሽታው በቆየ ቁጥር ደግሞ መራር ያደርጋል፡፡ ሰዎች በበሽታ ሲፈተኑ በሰው በፈጣሪም ላይ ብዙ የምሬት ንግግር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ጌታችን ‹ልትድን ትወዳለህን?›ብሎ ሲጠይቀው ‹ታዲያ መዳን ባልፈልግ ጠበል ቦታ ምን አስቀመጠኝ? እያየኸኝ አይደል... › ወዘተ ብሎ ብዙ ያለፈ ንግግር ሊናገር ይችል ነበር፡፡ ይህ ሰው ግን ምንም የምሬት እና የቁጣ ቃል አልተናገረም፡፡ ጌታችንም ሲያናግረው በጨዋ ሰው ደንብ ‹ጌታ ሆይ..›ብሎ ነው የመለሰለት፡፡ በዚህ ሁኔታው ትሑት ሊባል ይችላል፡፡
ነገር ግን የመለሰው የተጠየቀውን አይደለም፡፡ ጥያቄው ‹ልትድን ትወዳለህን?› የሚል ከሆነ መልሱ ‹አዎ መዳን እወዳለሁ› አለዚያም ‹አይ አልፈልግም› ብቻ መሆን ነበረበት፡፡ እሱ ግን ‹ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።› እንግዲህ የጌታችንን ማንነት ባይረዳውም ጌታችን በወቅቱ የሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበርና ‹ምናልባት ወደ መጠመቂያው ሊጨምረኝ አስቦ ይሆናል ያም ባይሆን ግን ከተከተሉት ሰዎች አንዱን አደራ ሊልልኝ ይሆናል› ብሎ አስቦ ነበር፡፡ ‹ሰው የለኝም› ብሎ የሠላሳ ስምንት ዓመታት ብሶቱን ተናገረ፡፡

‹ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል› ብሎ እያየ የቀደሙትን ሰዎች አስታወሰ፡፡
ጌታችን ‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ› አለው፡፡ ባላሰበው ባልጠበቀው መንገድ ፈወሰው፡፡ ይህ ሰው ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ ሲጠባበቃት የነበረችውን የቤተ ሳይዳ ጠበል ሳያገኝ ፣ በመልአኩ መውረድ ሳይሆን በመላእክት ፈጣሪ ቃል ተፈወሰ፡፡ ገባሬ መላእክት ክርስቶስ ራሱ መጥቶ አዳነው፡፡ ይህ ሰው እግዚአብሔር በዚህች ጠበል ካልሆነ በቀር በሌላ በምንም መንገድ ያድናል ብሎ አስቦም አልሞም አያውቅም ነበር፡፡ ለመዳን የሚያስፈልገው ምንድን ነው ተብሎ ቢጠየቅ የሚመልሰው ‹ወደ ውኃው የሚጨምር ሰው እና የቤተ ሳይዳ ውኃ› ብሎ ነበር፡፡ ጌታችን መጻጉዕ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ተስፋ ያደረጋትን ጠበል ወይም ደግሞ ወደ ጠበሉ የሚጨምሩትን ሰዎች ሳይጠቀም ፈወሰው፡፡ እግዚአብሔር ያለ ጠበልም እንደሚያድን ማመን ካልቻልን እምነታችን ሙሉ አይደለም፡፡ ይህ ሰው ወደ ውኃው ገብቶ ቢድን ኖሮ‹ጌታዬ አዳነኝ› ከማለት ይልቅ ‹‹መዳን ይነሰኝ? ሠላሳ ስምንት ዓመት እኮ ነው የጠበቅኩት...›› እያለ ልፋቱን ያወራርድ ነበርእንጂ ፈጣሪውን አያመሰግንም ነበር፡፡
ጌታችን ጠበል ቦታ ያገኘውን ያለ ጠበል ፈወሰው ሲባል መቼም ጠበል መጠመቅ የማይወዱ ወይም በጠበል የማያምኑ ሰዎች ደስ ሊላቸው ይችላል፡፡‹‹እኛስ ምን አልን ጌታ እኮ ይህን በሽተኛ ጠበል ቦታ አግኝቶ እንኳን የፈወሰው ያለ ጠበል ነው›› ብለው ባቀበልናቸው በትር ሊመቱንይፈልጉ ይሆናል፡፡ ሆኖም እዚሁ ዮሐንስ ወንጌል በዘጠነኛው ምዕራፍ ላይ ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ጠበል በሌለበት ሥፍራ አግኝቶትእኛ እመት (እምነት) የምንለውን አፈር በምራቁ ለውሶ ከቀባው በኋላ ‹ሒድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ› ብሎ ልኮታል፡፡ ጠበል ምንምየማያስፈልግ ቢሆን ኖሮ ዓይነ ስውሩን ሰው ወደ ወንዝ ወርደህ ተጠመቅ ብሎ አይልከውም ነበር፡፡ ዛሬ ለታመሙ ሰዎች ጠበል ሒዱ ብለን ስንመክር ክርስትና ያልገባን ፣ ክርስቶስን የማናውቅ የሚመስለው ይኖራል፡፡ አሁን ባየነው ታሪክ ውስጥ ግን ለበሽተኛው ‹ጠበል ሔደህ ተጠመቅ› ብሎ የመከረው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ መፈወስ የሚቻለው ክርስቶስ ጠበል ተጠመቅ ብሎ ከተናገረ ፤ የታመመን መፈወስ የማንችለው እኛ ኃጢአተኞቹ ከንፈር ከመምጠጥ ይልቅ ሔደህ ተጠመቅ ብንል ምን አጥፍተናል? ጌታችን ሲያደርግ ያየነውን ነው፡፡እኔን ምሰሉ ብሎ የለ እንዴ? (ዮሐ. 9፡7)
በእነዚህ ሁለት ታሪኮች ግን ጌታችን ሲፈልግ በጠበል ሲፈልግ ያለ ጠበል ፤ ሲሻው በምክንያት ሲሻው ያለ ምክንያት፡፡ ሲፈልግ በጠበል ሲፈልግበህክምና ፤ ሲፈልግ በቃሉ ሲፈልግ በዝምታ ፣ ሲፈልግ በቅዱሳን መላእክቱ ሲፈልግ ያለ ቅዱሳን መላእክቱ ማዳን እንደሚቻለው እንረዳለን፡፡
ጌታችን ለመጻጉዕ ‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ› ብሎ ሲነግረው ወዲውኑ ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሔደ፡፡ እዚህ ላይ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳደረገው የበሽተኛውን እምነት እናደንቃለን፡፡ ራሱን መሸከም የማይችለው ይህ በሽተኛ ተነሣና አልጋህን ተሸከም ሲባልአልሳቀም፡፡ ‹እንዴት አድርጌ ነው ደግሞ አልጋ የምሸከመው› ብሎ አልጠየቀም፡፡ በፍጹም እምነት ተነሣና ተሸክሞ ሔደ፡፡ የሠላሳ ስምንት ዓመት ጓደኛውን ፣ ሰው ሳይኖረው አብራው ኖረችውን ፣ የተሸከመችውን ባለ ውለታው የሆነችዋን አልጋ ተሸክማት አለው - ተሸክሞ ሔደ፡፡
አንድ ሰው እንኳን ለሠላሳ ስምንትዓመታት ይቅርና ለሠላሳ ስምንት ቀናት እንኳን ቢታመም እንደተሻለው ተነሥቶ አልጋ አይሸከመምም፡፡ እስከሚያገግም ድረስ በደንብ መንቀሳቀስአይችልም፡፡ ራሱን ያዞረዋል ፣ ደክመዋል፡፡ የቀረ ሕመም አያጣውም፡፡ መጻጉዕ ግን የተፈወሰው ያለ ቀሪ በሽታ (ያለ ተረፈ ደዌ)ነበር፡፡ ስለዚህ ወዲያው ተነሥቶ አልጋውን እንዲሸከም ነገረው፡፡ መምህር ኤስድሮስ እንዳሉት ያንን የብረት አልጋ ተሸክሞ እየሔደ የጌታን ጽንዐ ተአምራት አሳየ፡፡ ጌታችንም ከዛ በሽታ ያዳነው በነጻ መሆኑን በሚያሳይ ሁኔታ ያችን አንዲት ንብረቱንም ተሸክመህ ሒድ አለው፡፡
መጻጉዕ የተሸከመችህን አልጋ ተሸከምተባለ፡፡ አግዚአብሔር የተሸከሙንን እንድንሸከም የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡ ውለታ ሳንረሳ የተሸከሙንን ወላጆቻችንን የተሸከመችንንቤተ ክርስቲያንን ፣ የተሸከመችንን ሀገራችንን እንድንሸከም ይፈልጋል፡፡ በአንዱ ሊቅ ደግሞ ‹ዓለም እንደዚህ ናት ፤ እናት ዓለምአልጋ መጻጉዕን እንደተሸከምኩህ ተሸከመኝ አለችው› ብለው ተቀኝተዋል፡፡ ( ዝክረ ሊቃውንት 2 )
እዚህ ላይ ጌታችን ቤተ ሳይዳ ከመጣ አይቀር ሁሉንም በሽተኛ መፈወስ ሲችል ለምን አንዱን ብቻ ፈውሶ ሔደ? ብለን ማሰባችን አይቀርም፡፡ የበለጠ የሚያሳዝነው ደግሞ ሊቃውንቱእንደጻፉት የቤተ ሳይዳው መጠመቂያ ፈውስ ከዚያ በኋላ ብዙም አልቆየም፡፡ የመልአኩም መውረድ ቆሞአል፡፡ ከዚያ በኋላ በሰባ ዓመተ ምሕረትም ኢየሩሳሌም መቅደስዋ ፈርሶአል ተመሰቃቅላለች፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስም የዮሐንስ ወንጌልን ሲጽፍ ‹‹ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።... ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።... ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆንነበር።›› ብሎ በኃላፊ ኃላፊ ግሥ /past perfect tense/ ነበር፡፡
ታዲያ ጌታችን እንዲህ መሆኑን እያወቀ ምነው መጻጉዕን ብቻ ፈውሶት ሔደ? ቢባል የፈወሰው እሱን ብቻ አይደለም፡፡እሱን በሥጋ ቢፈውሰውም ተአምራቱን አይተው በማመናቸው በነፍሳቸው የተፈወሱ ይበዛሉ፡፡ ‹ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት እየፈወሰ› እንዲሉ አበው በዚያ ሥፍራ በሥጋ ታመው በነፍሳቸው አምነው የዳኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ የጌታችንና የእርሱ አካል የሆነች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ሥራዋ ነፍስን መፈወስ እንጂ ሥጋዊ በሽታን መፈወስ ብቻ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው እንጂ ጌታችን ሰው ሆኖ ይህችን ምድር በእግሩ ሲረግጥ በሽታ እንዳይኖር ያደርግ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ‹በመስቀል ላይ በቆሰልኸው ቁስል ከኃጢአቴቁስል አድነኝ› ብሎ እንደጸለየ እኛም የዘወትር ልመናችን ለሚከፋው ለነፍሳችን በሽታ ነው፡፡
የጌታችን መምጣት ዋነኛ ዓላማ ለነፍስ ድኅነት ነው:: ይህ ማለት ግን ለሥጋ አልመጣም ማለት አይደለም:: ጌታችን ‹‹ኃጢአተኞችን ለንስሐ ልጠራ መጣሁ እንጂ ጻድቃን ልጠራ አልመጣሁም›› ‹‹ከእስራኤል ቤት በቀር ለአሕዛብ አልተላክሁም›› ሲል ለጻድቃን አይገደኝም ፣ ለአሕዛብ አላስብም ማለቱ እንዳልነበር ሁሉ ለነፍስ ድኅነት ቅድሚያ ሠጥቶአል ማለት ለሥጋ አይገደውም ማለት አይደለም፡፡
በመጻጉዕ ታሪክ ውስጥ ብዙ ቀሪ ነጥቦች ቢኖሩም ሁለት ነገሮችን ብቻ እናንሣና ይህችን አጭር ጽሑፍ እንግታ፡፡ ይህ ሰው ተፈውሶ አልጋውን ተሸክሞ ሲሔድ ሰንበት ለሰው ድኅነትእንደተፈጠረች ያልተረዱ አይሁድ በቁጣ ነደዱ፡፡ ‹‹ሰንበት ነው አልጋህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም›› አሉት፡፡ ልብ አድርጉ ይህሰው በቤተ ሳይዳ ሠላሳ ስምንት ዓመታት ሙሉ ሲማቅቅ እንደኖረ የሰውን ገመና አዋቂ ነን ባዮቹ አይሁድ ይቅሩና ቤተ ሳይዳን የረገጠሰው ሁሉ ያውቃል፡፡ ላለፉት ሠላሳ ስምንት ዓመታት ወደዚያች የመጠመቂያ ስፍራ ሲሔዱ ያም ባይሆን በጎች ታጥበው ተመርጠው ወደሚገቡበትወደ በጎች በር ሲያልፉ ይህን በሽተኛ በአልጋው ተጣብቆ ሳዩት አይቀሩም፡፡ አሁን ግን ከአልጋው ተነሥቶ የተሸከመችውን

አልጋ ተሸክሞበአደባባይ ሲያዩት የጠየቁትን ጥያቄ ተመልከቱ፡፡ ‹‹እንኳን ለዚህ አበቃህ ፤ ዛሬ መልአክ ወረደ ማለት ነው?›› ‹‹እሰይ ልፋትህን ቆጠረልህ!›› ያለው የለም፡፡ የተናገሩት አንድ ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ ‹‹ሰንበት ነው አልጋህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም›› የሚልብቻ!! በአይሁድ ዓይን ድኖ ሠላሳ ስምንት ዓመት የተኛበትን አልጋ ከመሸከሙይልቅ ሰንበት ማፍረሱ የሚያስደንቅ ትልቅ ዜና ነው፡፡
መጻጉዕ ‹ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸከም አለኝ› አላቸው፡፡ እስቲ በደንብ አስተውሉ፡፡ እነዚህ ሰዎችይህን በሽተኛ ፈጽሞ አያውቁትም ነበር እንበል፡፡ እንደዛ ከሆነ ‹ያዳነኝ ሰው› ሲላቸው ‹ከምንድን ነው የምትድነው? ምን ሆነህነበር? ከየት ነው የመጣኸው?› ይሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ መዳኑን ማየት አልፈለጉም እንጂ ማን እንደሆነ ጠንቅቀውያውቁታል፡፡ ከዚያም ‹‹ያዳነኝ ያ ሰው አልጋህን ተሸከም አለኝ›› ሲላቸው ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ያለህ ሰው ማን ነው?››ብለው ጠየቁት፡፡ እስቲ ጥያቄና መልሱ ውስጥ ያለውን ሽሽት እንመልከት፡፡ ‹‹ያዳነኝ ሰው አልጋህን ተሸከም አለኝ›› ለሚለው መልስተከታዩ ጥያቄ ‹ማን ነው ያዳነህ?› የሚል ነበር፡፡ እነሱ ግን የጌታንየማዳን ሥራ ላለመስማት ጆሮአቸውን ደፍነው ስለነበር ‹አልጋህን ተሸከም ያለህ ማን ነው?› አሉ፡፡ የማዳኑን ሥራ እያዩ ከማመንይልቅ መከራከር ፣ ከማድነቅ ይልቅ የትችት ሰበብ መፈለግ እንግዲህጌታን የሰቀሉ የአይሁድ ጠባይ ነው፡፡
የመጨረሻው ነገር መጻጉዕ ከዚህ በኋላወደ አይሁድ ሄዶ ጌታን መክሰሱና ለጌታ ሞት የመማከራቸው ምክንያት መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሰው ‹የሚብስ እንዳይገጥምህ ደግመህ ኃጢአትንአትሥራ› ብሎ ጌታ ቢያሳስበውም አልሰማም፡፡ ጌታ በተያዘበት በምሴተ ሐሙስ ለሊቀ ካህናቱ አግዞ ጌታችንን በጥፊ መታው፡፡ ጌታችንም‹‹ክፉ ተናግሬ እንደሆነ ስለ ክፉ መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ?›› አለው፡፡ (ዮሐ.18፡23) ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ከማለት በቀር ክፉቃል ተናግሬህ ከሆነ መስክርብኝ ፤ የተናገርኩህ መልካም ሆኖ ሳለ ስለምን ትመታኛለህ›› ማለቱ ነበር፡፡ ጌታችን በማግሥቱ ያ ሁሉጅራፍና ግርፋት ሲደርስበት አንድም ጊዜ ‹‹ለምን ትመታኛለህ›› ብሎ አልተናገረም፡፡ የመጻጉዕ ጥፊ ይህን ያህል ዘልቆ የተሰማውለምንድር ነው?
የመጀመሪያው ምክንያት ከቤተ ሳይዳ ከበጎች በር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጌታችን የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው፡፡ በበጎች በር አልፎ የመጣውንጹሐ ባሕርይ እንደሆነ ለማስረዳት ነበር፡፡ ለዚህም ንጽሕናው ዋነኛው ምስክር ፈውስን የሠጠው ይህ በሽተኛ ነበር፡፡ እሱ ግን መታው፡፡‹‹በቤተ ሳይዳ ክፉ ቃል ተናግሬህ ከነበር መስክርብኝ› ማለቱ ‹ነውርየሌለብኝ ፣ ለመሥዋዕት የተዘጋጀሁ በግ ነኝ ለምን ትመታኛለህ?› ማለቱ ነበር፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሮማውያን ግርፋት በላይለጌታ ዘልቆ የሚሰማው ባዳነው ሰው መመታቱ ስለሆነ ነው፡፡ ውድ አንባቢያን መጻጉዕ ከሠላሳ ስምንት ዓመት በሽታ ብቻ ዳነ ፣ እኛግን የዳንነው ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በሽታ ነበር፡፡ ጌታችን እኛን ያስነሣን ከሲኦል አልጋ ነው፡፡ ከሌላው ሰው ይልቅእግዚአብሔር የእኛ ዱላ ይሰማዋል፡፡ ይህም ዱላ ኃጢአታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር ዛሬም ድረስ ለእያንዳንዳችን ይጠይቃል፡፡ ‹‹ለምን ትመታኛለህ?››
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
[email protected]
መጋቢት 2003 አቡዳቢ

+ ያልተናገረችው አህያ +
ነቢዩ በለዓም በአህያ ላይ ተጭኖ ሲሔድ አህያው የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፡፡ በለዓም ተናድዶ መታት፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አህያይቱ ድጋሚ መልአኩን አየች፡፡ ከበለዓም በታችም ተኛች፡፡ በለዓም ተበሳጭቶ አህያይቱን በበትሩ ደበደባት፡፡
እግዚአብሔርም የአህያይቱን አፍ ከፈተ ፦ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው፡፡ በለዓምም አህያይቱን ፦ ስላላገጥሽብኝ ነው ሰይፍ በእጄ ቢኖር ኖሮ እገድልሽ ነበር አላት፡፡ አህያይቱም በለዓምን ፦ ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት’’ /ዘኁ 22፡27-30/
ይህንን ታሪክ ባነበብሁ ቁጥር ሁልጊዜም የሚያስደንቀኝ የአህያይቱ መናገር ሳይሆን የበለዓም መልስ መሥጠት ነው፡፡
እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ በለዓም መልስ የሠጠው ከሎሌዎቹ ለአንዱ አይደለም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‘ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን ዕብደት አገደ’ /2ጴጥ 2፡16/ እንዳለው አህያ ስትናገር ታይቶ ተሰምቶ አያውቅም፡፡
መንገድ ላይ እየሔድህ ከሰፈርህ ውሾች አንዱ ‘እንዴት አደርህ?’ ቢልህ እግዚአብሔር ይመስገን ትላለህ? እርግጠኛ ነኝ ራስህን ስተህ ልትወድቅ ትችላለህ፡፡ ከተረጋጋህ በኋላም አእምሮህ ተነክቶ ‘ውሻው ተናገረ እኮ’ እያልክ ትኖራለህ፡፡
በለዓም ግን ተናግራ የማታውቀው አህያ አፍ አውጥታ ስትናገር ሲያይ ትንሽ ደንገጥ እንኳን አላለም፡፡ ሌላ ቀን ሲያናግራት እንደኖረ ሰው ኮስተር ብሎ መመላለስ ጀመረ፡፡ አህያዋ አብረው ስለኖሩበት ዘመን የሥራ ልምድዋና የሥራ አፈጻጸምዋ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ ብላ ስትነግረው በለዓም ሠራተኛውን እንደሚያናግር አለቃ ተረጋግቶ ያለ ምንም መደንገጥ ራሱን እየነቀነቀ ከሰማ በኋላ ፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም ብሎ ግምገማዋን ተቀብሎ ኂሱን ዋጠ፡፡
የበለዓምን ነገር እንተወውና የተናጋሪዋ አህያውንም ነገር እንርሳውና አንዲት መናገር ሲኖርባት ያልተናገረች አህያ ነገር ግን የበለጠ ይቆጫል፡፡
ይህች አህያ በሆሳዕና ዕለት ጌታችን የተጫነባት አህያ ናት፡፡ ይህች አህያ እንደ በለዓም አህያ ጌታዋ በበትሩ የሚደበድባት ሳይሆን ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብሎ ከነ ልጅዋ ያስፈታት አህያ ናት፡፡ የእርስዋ ጌታ በተኛችበት በበትር የሚቀጠቅጣት ሳትሆን እግርዋ መሬት እንዳይረግጥ ጌታዋ ያስነጠፈላት አህያ ናት፡፡
የእርስዋ ጌታ እንደ በለዓም መልአክ መንገድ የሚዘጋበት ሳይሆን መላእክት በፊቱ እየሰገዱ እንደ ሻሽ የሚነጠፉለት ነው፡፡ የበለዓምን አህያ አንደበት የከፈተ ጌታ ምነው የዚህችን አህያ አንደበት በከፈተው ኖሮ! ስንት ነገር በተናገረች ነበር?
የሆሳዕናዋ አህያ አንደበትዋ ቢከፈት እንደ በለዓም አህያ ጌታዋን ከማማረር ይልቅ ከሕዝቡ ጋር አብራ ትዘምር ነበር፡፡ እንደ በለዓም አህያ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ በማለት ፋንታ ‘ከብዙ ዘመን ጀምሮ ሰው ሲቀመጥብኝ የኖርሁ አህያ ነበርሁ፡፡ በውኑ ንጉሥን እሸከም ዘንድ ልማዴ ነበርን?’ ብላ ታመሰግን ነበር፡፡
ጌታ ሆይ እኛስ ስንት በለዓሞችን ተሸክመን ኖርን? ስንት በለዓሞች በተሸከምናቸው በታግስናቸው ልክ በማመስገን ፈንታ በበትር ደበደቡን? በብሶት በምሬት አፍ አውጥተን ስንናገር እንኳን ትንሽ አይደንቃቸውም፡፡
አንተው መጥተህ ገላግለን፡፡ ለምስጋና ቢስ በለዓሞች ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብለህ እንዲፈቱን ንገራቸው፡፡ አንተው ዙፋንህ አድርገን፡፡ አንተን መሸከም አይከብደንም፡፡ አንተን የያዝን እንደሆን መንገዳችን በዝማሬ የተሞላ ይሆናል፡፡ የሚንቁን ሁሉ አንተን ብለው ያከብሩናል፡፡ ምንም እንኳን አንተን ሊይዝህ የሚችል ባይኖርም በደስታ እንሸከምሃለን፡፡
ራስህ እንዲህ ብለሃልና ፦
‘እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ
እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ
ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና
ለነፍሳችሁም ዕረፍትን ታገኛላችሁ
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና’ /ማቴ 11፡28/
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 17 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
(መጋቢት 12 ቅዱስ ሚካኤል በለዓምን የተቋቋመበት መታሰቢያ ነው)

+ የመጽሐፍ ዮሴፍ +
ዮሴፍ ግብፅ ወርዶ ፣ የግብፅን ንጉሥ የፈርኦንን ሕልም ፈትቶ ፣ ሀገረ ገዢ ሆኖ ነበር፡፡ ግብፅን ከረሃብ ከማዳንም አልፎ የዓለም የእህል ጎተራ እንድትሆን አድርጓት ነበረ፡፡ ይህንን የዮሴፍን ውለታ ያልዘነጋው የግብፅ ንጉሥ ፈርኦን ለዮሴፍና በቁጥር ሰባ ለነበሩት የዮሴፍ ዘመዶች የክብር ማረፊያ ሠጥቶ እንደ ሀገራቸው ተስፋፍተው እየተዋለዱ በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው፡፡ በፈርኦን ላይ ፈርኦን ፣ በትውልድ ላይ ትውልድ ሲተካ ግን ድንገት ‘ዮሴፍን የማያውቅ ፈርኦን ተነሣ’ (ዘጸ. 1፡8)
ከዚያ በኋላ የሆነውን ምኑን ልንገራችሁ? ፳ኤል ልጆቻቸውን ከሲሚንቶ ጋር ለውሰው ፒራሚድ እስኪሠሩ ድረስ የወረደባቸው መከራ ምኑ ይነገራል? ለዚህ ሁሉ መከራ መነሻው ግን ‘ዮሴፍ ደግሞ ማን ነው?’ የሚል ትውልድ መምጣቱ ነው፡፡
‘ዮሴፍን የማያውቅ ፈርኦን ተነሣ’ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ያስጠቀሰኝ የመጽሐፍም ዮሴፍ አለ ለካ የሚያሰኝ የሰሞኑ አንድ ገጠመኝ ነው፡፡ ከዐሠርት ዓመታት በላይ ከገበያ ጠፍቶ የቆየውን ውድ መጽሐፍ ‘ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት’ እኮ ታተመ!’ የሚል ዜና የነገርናቸው ሰዎች ሁሉ ብዙም አለመደነቃቸውን ሳይ ለካ የመጽሐፍም ዮሴፍ አለ? ብዬ እንድተክዝና ይህንን የመጽሐፍ ዮሴፍ ለማስተዋወቅ ብእሬን እንዳነሣ ግድ ሆነብኝ፡፡
‘ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት’ የሚለውን [በወቅቱ በሚጠራበት ስም] የዲያቆን አንዱዓለም ዳግማዊ መጽሐፍ ውለታ እንዴት ልንገራችሁ? ይህ መጽሐፍ የአዲሱ ትውልድ የነገረ ማርያም ሥነ ጽሑፍ የተወለደበት እጅግ አንገብጋቢ (critical) ሥራ መሆኑን ለመግለጽ ቃላት ሊያጥረኝ ይችላል፡፡ ስለተጻፈበት ዘመን ሁኔታ ብቻ ላስታውስ፡፡
ያ ጊዜ መንፈሳዊ ኮሌጆች በእንግዳ ትምህርቶች ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ የወደቁ በሚያስመስል ሁኔታ ላይ ነበርን፡፡ ‘ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ የገባ ሰው ጤነኛ ሆኖ አይወጣም’ የሚል ድምዳሜ ላይ እስኪደረስ ድረስ ብዙዎች ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ነን እያሉ ከኦርቶዶክሳዊ መንገድ የወጣ ትምህርት ያስተምሩ ነበረ፡፡ በቅርቡ ያረፉት ባለቅኔው መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒን የመሳሰሉ ሊቃውንት ሳይቀር ‘የሀገር ውስጥ ቦንኬ ማምረቻ’ ብለው መንፈሳዊ ኮሌጁን እስኪያማርሩ ድረስ የተደረሰበትና ቤተ ክርስቲያን በራስዋ በጀት ጠላት እንዴት ታፈራለች የሚባልበት ዘመን ነበረ፡፡ (ቦንኬ ልጆች ሳለን የብዙ ውዝግብ ምክንያት የነበረ ፈረንጅ ፓስተር ስም ነው) ያ ጊዜ የአብነት ትምህርት ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርት ጋር እንደ እሳትና ጭድ ተደርጎ የሚቆጠርበት ፣ ቀሚስ ለባሹ ነጠላ ለባሹን በንቀት ፣ ነጠላ ለባሹ ቀሚስ ለባሹን በጥርጣሬ የሚያይበት ወቅት ነበር፡፡
በዚያን ወቅት ራሳቸው ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ስላልመጣላቸው መንፈሳዊ ኮሌጅ የገቡና መመረቂያ ጽሑፋቸውን ሳይቀር በሰው የሚያሠሩ አንዳንድ ድኩማን ተማሪዎች ‘traditional’ በሚል በጉባኤ ቤት ያለፉ ሊቃውንትን የማሸማቀቂያ ቃል ነባሩን የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥልቅ ነገረ ሃይማኖት ሳይረዱ የሚያናንቁ ወጣቶች የተነሡበት ጊዜ ነበር፡፡ ‘Salvation, redemption, Christology’ የሚሉ ቃላትን ከማዘውተራቸው ውጪ የጠለቀ theological እውቀት ሳይኖራቸው በትዕቢት የተወጠሩ ሰዎች የመንፈሳዊ ኮሌጅን ገጽታና ምንነት የሸፈኑበት ዘመን ነበረ፡፡
በተለይ ነገረ ማርያምን ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ አቅጣጫ መስማት እንደ ሶምሶን እንቆቅልሽ ‘ከበላተኛ መብል ወጣ ፣ ከሚያፈራውም ጥፍጥ ወጣ’ (እምአፈ በላዒ ወጽአ መብልዕ ፤ ወእምአፈ ግሩም ወጽአ ጥዑም)ን የሚያስጠቅስ ክስተት ነበር፡፡ የጉባኤ ቤት ትምህርትና ቴዎሎጂን ማዋሐድም ዘይትና ውኃን የማዋሐድ ያህል ከባድ እንደሆነ ተደምድሞ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ሆነው ሁለት ዓይነት ጎራዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት እየሆነ በመምጣቱ በወቅቱ ገና ልጆች ለነበርነው ግራ የሚያጋባና የቱን መስመር ልከተል የሚያሰኝ መንታ መንገድ ነበረ፡፡
በዚህን ወቅት ነው የዲያቆን አንዱ ዓለም ዳግማዊ ዓይነት ዘይትና ውኃን ያዋሐዱ ፣ ቴዎሎጂን ከአብነት ትምህርት ፣ እንግሊዝኛን ከግእዝ ፣ ፋዘር ጆሲን ከመምህር ደጉ ዓለም ፣ ነገረ ክርስቶስን ከነገረ ማርያም ፣ የሰባኪ ቀሚስን ከልብሰ ተክህኖ ያስታረቁ ልጆች ከዚያው ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አብራክ ተወልደው ብቅ ብቅ ሲሉ አይተን ልባችን ማረፍ ጀመረ፡፡ የዲያቆን አንዱዓለም ዳግማዊ ዓይነቶቹ ከመንገድ ሲያልፉ ውዳሴ ማርያም ዜማ ሲደርስ በፍርሃት ቆመው ሰአሊለነ ቅድስት እስኪባል የሚጨርሱ ፣ በወጣትነታቸው የአንደበታቸው ላህይ የቀደምት መምህራን የሆነ ፣ ትሕትናቸው የሊቃውንት የሆነላቸውን ‘በማር ላይ ቅቤ’ የሆኑ ጥንቅቅ ያሉ ሰባኪያንን ቆመው ሲያገለግሉ ማየት በዚያን ወቅት ለብዙዎቻችን ተስፋና መነሻ ነበረ፡፡
ይህ በሆነበት ሁኔታ በተሐድሶ (የጲጥፋራ ሚስት) የሐሰት ክስ ምክንያት በግፍ የታሰረውን ነገረ ማርያም (ዮሴፍን) ከእስር ቤት ያስፈታ የብዙዎቻችን እውነተኛ የሕልም ፍቺ ፣ የወላዲተ አምላክን ፍቅር ለተራብን ሁሉ ምግብ የሆነ ‘ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት’ የተሰኘ መጽሐፍ ታተመ፡፡
ይህ መጽሐፍ የነገረ ማርያም (Mariology) ድንቅ ምሁራዊ ጥናት ከመሆኑ ባሻገር ውዳሴ ማርያም ትርጓሜን ከቤተ ክርስቲያን ቀደምት አበው ሥነ ጽሑፍ (Patristic Litrature) ጋር ያጣመረ አባ ጊዮርጊስን ከቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፣ ቅዱስ ያሬድን ከዮስጦስ ሰማዕት ፣ አባ ህርያቆስን ከቅዱስ ጄሮም ጋር ለምስክር የጠራ ቴዎሎጂ ከአብነት ትምህርት ጋር ሲጣመር እንዴት ያለ ውበት እንዳለውና ለክህደት የሚዳርጋቸው በአግባቡ ያልተማሩና ያላነበቡትን ሰዎች ብቻ እንደሆነ በተግባር ያስመሰከረ ፣ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን ያስከበረ እጅግ እጅግ ውብ ሥራ ነበረ፡፡
በዛሬው መጠሪያቸው የመጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዶ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ ‘ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት’ መጽሐፍ ያለ ምንም ማጋነን ይሄ ትውልድ ተሳልሞ ሊያነበው የሚገባ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ ጸሐፊውን ለPHD ያበቃ እኛን ደግሞ ለጥልቅ ንባብ ያነቃ ታሪካዊ መጽሐፍ ነው፡፡ ምንም እንኳን በጸሐፊያን ዘንድ የተሻሉ ሥራዎችን አይቶ እንዳላየ የመሆን በሽታ (Silent conspiracy) የጸናበት ዘመን ቢሆንም በመጽሐፉ የተጠቀማችሁ ጸሐፍት ሁሉ ስለዚህ መጽሐፍ ውለታ ዝም ልትሉ አይገባም::
መጽሐፉ ከገበያ ጠፍቶ አሁን ሲታተም ‘ዮሴፍን የማያውቅ ፈርኦን ተነሣ’ እንዲል ብዙ ሰው የዚህን መጽሐፍ ምንነት አልተረዳም፡፡ ወዳጄ ይህ መጽሐፍ ትናንት ባይኖር የዛሬዎቹ እነ ‘የብርሃን እናት’ ጨርሶ ባልኖሩም ነበረ፡፡ በእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ቤት ሊኖር የሚገባና በማንበብህ የምትኮራበት ውድ መጽሐፍ መሆኑን ስታነቡት ታምኑኛላችሁ፡፡ መጽሐፉን በይፋ ግንቦት ላይ እስክንመርቀው ድረስ ‘ይህን መጽሐፍ ብላ’ ብዬ ስናገር እንደ ሕዝቅኤል ‘በላሁት ጣፈጠኝ’ እንደምትሉ በመተማመን ነው፡፡ አሁን በገበያ ላይ ያለው ውስን ኮፒ ሳያልቅ እጃችሁ አስገቡ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 13 2015 ዓ.ም.

+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡
ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ
‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7
እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡
ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡
‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31
የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24
አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]
ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18
ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡
የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 18 2012 ዓ ም

➳➺ ለንስኃ የሚቀሰቅስ ዶሮ ⬅
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡
"ሕማማት" ከተሰኘው ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ 2ኛው ምዕራፍ ላይ የተወሰደ!

+++ የኒቆዲሞስ ክርስትና +++
ኒቆዲሞስ የሚለው ስም በዮሐንስ ወንጌል ብቻ ከተጻፉ ስሞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የዚህን ሰው ስም ባነሣበት ሥፍራ ሁሉ ‹አስቀድሞ በሌሊት የመጣው› የምትል ቅጽል ያስቀድማል፡፡ ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ ነው፡፡ በሀብቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ባለጸጋ ፣ በሹመቱ የአይሁድ ሸንጎ /synagogue/ አባል ፣ በትምህርቱ ደግሞ ጌታችን ራሱ እንደመሰከረለት ‹የእስራኤል መምህር› የሆነና አዋቂ ነው፡፡ የአይሁድ አለቃ ፣ የእስራኤል መምህር ኒቆዲሞስ ጌታችን ራሱ ለብቻቸው በቃል ምልልስ እያናገረ ጥያቄያቸውን እየመለሰ ካስተማራቸው ጥቂት ዕድለኛ ሰዎች አንዱም ነው፡፡ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅነት ያገኘንበትን ምሥጢረ ጥምቀት በጥልቀት እና በዝርዝር የተማረው የመጀመሪያው ሰውም ኒቆዲሞስ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችን ጥምቀትን በተግባር ሲመሠርት የዓይን ምስክር እንደነበረ ሁሉ ጥምቀት በትምህርት ስትመሠረት ደግሞ የዓይን ምስክሩ ኒቆዲሞስ ነው፡፡
በትምህርቱ መካከልም ባቀረበው ጥያቄ ‹ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ስለ መወለድ› ጌታችን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረው ሲሆን አላምን ብሎ ‹እንዴት ሊሆን ይችላል?› ብሎ ሲከራከር ደግሞ ገሥጾታል፡፡ ዛሬም ድረስ ኒቆዲሞስ መልስ ከተሠጣቸው በኋላ የሚነታረኩ ተከራካሪዎች ምሳሌ ሆኖ በሊቃውንት ይጠቀሳል፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያምን የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት በሙሉ ልብ በመቀበሏ በምናመሰግናት ጊዜም ‹እንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠሪ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ ቃሉን የተቀበልሽ› እያልን መሆኑ ይህን እውነታ ያጎላዋል፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ ክርስትና ከመጣበት መንገድ ጀምረን በዮሐንስ ወንጌል ስንከተለው ቀስ በቀስ እያደገ የመጣ የመንፈሳዊነት ደረጃን እናገኛለን፡፡ የኒቆዲሞስ ክርስትና እንደ ወጣኒ (ጀማሪ) እንደ ማዕከላዊና እንደ ፍጹም በሦስት ደረጃዎች ላይ የሚታይ ሕይወት ሆኖ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንደሚከተለው እንመልከተው፡፡
ወጣኒው (ጀማሪው) ኒቆዲሞስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ ያደረገውን ተአምር ተመልክተው ብዙ ሰዎች በስሙ አምነው ነበር፡፡ ያ ወቅት ጌታችን በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ውኃን ወይን ያደረገበትና ፣ በቤተ መቅደስ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ገሥጾ ያስወጣበት ነበር፡፡ ይህንን ምልክት ተከትለው ካመኑበት ብዙ ሰዎች አንዱ ታዲያ ኒቆዲሞስ ነበር፡፡ ይህ ሰው በጌታችን ቢያምንም ባመነበት ወቅት እምነቱን በልቡ ብቻ ይዞ አቆይቶ ነበር፡፡ ከዚያም በአሳቻ ሰዓት በማታ ወደ ጌታችን መጣና ‹መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን› አለው፡፡ ኒቆዲሞስ ጌታችንን እግዚአብሔር በረድኤቱ ተአምራትን እንዲያደርጉ ከሚያስችላቸው ጻድቃን እና ነቢያት ለይቶ አላየውም ነበር፡፡ ንግግሩም ከእርሱ ጋር ምልክቱን አይተው አምነው ከነበሩት ሰዎች ቁጥር መሆኑን በሚያሳይ መንገድ ‹እናውቃለን› የሚል የብዙዎች ወኪልነት ንግግር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር እንግዲህ አምላካችን በዝርዝር ያስተማረው፡፡
ኒቆዲሞስን እንዲህ በሌሊት ያስመጣው ምንድር ነበር? ክርስቶስን በቀን በአደባባይ ሊያናግረው አይችልም ነበር? እሱ እንደሆነ በሔደበት መንገድ የሚለቀቅለት የአይሁድ አለቃ ነውና ጌታችንን ለማግኘት ሰዎች አገዱኝ ሊል አይችልም፡፡ ይህ እንግዲህ የኒቆዲሞስ የመጀመሪያው የክርስትና ደረጃ ነበር፡፡ እሱ አምላካችንን ስላደረገው ተአምር ሊያደንቀው ፈልጓል ‹እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው› ብሎ አመስግኖታል ፤ ሊከተለው ግን አልፈለገም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከጌታችን ጋር ሆኖ ሰዎች እንዲያዩት አልፈለገም፡፡ የጌታ ተከታይ ፣ ደቀመዝሙር ሆኖ መታሰብ አልፈለገም ፣ ጉዳዩ ክብሩን የሚነካበት መሰለው፡፡ የተማረ ነውና ‹ገና ይማራል እንዴ› ብለው እንዳይንቁት ለክብሩ ሳሳ ፣ በዚያ ላይ ደግሞ ጌታችን በአይሁድ ሹማምንት ዓይን የተናቀ ነበር፡፡ እርሱ ‹ግንበኞች እንደናቁት ድንጋይ› ነበር፡፡ ‹‹የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።›› ይላል ነቢዩ፡፡ /ኢሳ. ፶፫፥፫/ ታዲያ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ መታየት በዚያን ወቅት የሚያስከብር ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ ፈራ ተባ እያለ በጨለማ መጣ፡፡
ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚመጣ ሰው አንዱ ፈተናው ይኼ ነው፡፡ ክርስትናችን በሰዎች ፊት የታወቀ እንዲሆን ፈቃደኞች የማንሆን ብዙዎች ነን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሰው ተብሎ ላለመታየት የሚሸሹ ብዙዎች ናቸው፡፡ ማዕተብ ማድረግ ፣ በቤተ ክርስቲያን አጠገብ ሲያልፉ መሳለም ፣ በአበው ትውፊት ጽዋዕ መጠጣት ወዘተ ማድረግ የሚከብዳቸው የሚጨነቁና የሚያፍሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሚሠሩበት መሥሪያ ቤት አካባቢ ስለ ሃይማኖታቸው ባይታወቅ የሚመርጡ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔዳቸው ባይሰማ ደስ የሚላቸው ኒቆዲሞሶች ብዙኃን ናቸው፡፡
የኒቆዲሞስ ችግር በክርስትናው ማፈሩ ብቻ አልነበረም፡፡ ክርስትና የሚያመጣበትን መዘዝ መፍራቱም ጭምር ነው፡፡ አይሁድ ‹‹እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኩራብ ይውጣ›› የሚል ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ (ዮሐ. ፱፥፳፪) በዚህ ሕግ ምክንያት በጌታችን አምነው እንኳን ስለ እርሱ ለመመስከር የሚፈሩ ብዙዎች ነበሩ፡፡ ‹‹ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።›› (ዮሐ. ፲፪፥፵፪)
ኒቆዲሞስ ወደ ጌታ መጥቶ መማሩ እንዲታወቅ ያልፈለገውም ለዚህ ነበር፡፡ ለክርስትናው ምንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ለማድነቅ እንጂ መከራን ለመቀበል አልተዘጋጀም፡፡ ይህ ዓይነቱ ችግር ሌላው የክርስቲያናዊ ሕይወት ፈተና ነው፡፡ ሐዋርያው የክርስትናችንን ዓላማ ሲገልጥ ‹‹ስለ እርሱ ደግሞ መከራን ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፡፡›› ብሏል፡፡ (ፊል. ፩፥፳፱) ብዙዎቻችን ክርስትናችንን እንፈልገዋለን ፤ ሆኖም በክርስትናችን ምክንያት ቅንጣት መከራ እንኳን እንዲነካን አንፈልግም፡፡ በእግዚአብሔር በማመን ውስጥ ፈተናም አለ፡፡ ራሳችንን በእውነት ክርስቲያን ነኝ ብለን ለመጠየቅ ብንፈልግ አብረን መጠየቅ ያለብን በእውነት መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ወይ ማለት ጋር ነው፡፡ በእግዚአብሔር በማመናችን ምክንያት ምን የከፈልነው ዋጋ አለ? ለእርሱ ብለን የተውነው ነገር ምንድን ነው? ለእሱስ ብለን ያጣነው ነገር ይኖር ይሆን? ምንም ነገር ከሌለ ክርስትናችን ገና ያልጠነከረ ነው ማለት ነው፡፡
ማዕከላዊው ኒቆዲሞስ
ፈሪሳዊያንና የካህናት አለቆች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘውት እንዲመጡ ሎሌዎች ላኩአቸው፡፡ እነዚህ ሎሌዎች ጌታችንን ይዘው እንዲመጡ ቢላኩም በጌታችን ጣዕመ ትምህርት ተደንቀው ተመስጠው ሲማሩ ውለው ባዶ እጃቸውን ተመለሱ፡፡ አይሁድ ‹ያላመጣችሁት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም›› ብለው መለሱ፡፡ ይህን ጊዜ አይሁድ ተቆጥተው ሎሌዎቹን ‹‹እናንተ ደግሞ ሳታችሁ? ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእርሱ ያመነ ሰው የለም፡፡ ሕዝቡም ያመነበት ሕግ የማያውቅ ርጉም ስለሆነ ነው›› ብለው ገሠጹአቸው፡፡ እናንተ ያመናችሁት ባለማወቃችሁ ነው ፤

ከእኛ ከአዋቂዎቹ ማን በእሱ አመነ? ብለው ሊያሸማቅቋቸው ሞከሩ፡፡
ይህን ሁሉ ሲሆን የማታው ተማሪ የአይሁድ መምህር ኒቆዲሞስ እዚያ ቆሞ ነበር፡፡ ከአለቆች መካከል በጌታ ያመነ የለም ሲባል እየሰማ ነው፡፡ አሁን ክርስትናው ልትፈተን ነው፡፡ ደፍሮ እኔ አምኜአለሁ ብሎ መናገር ባይችልም ፈራ ተባ እያለ እንዲህ አለ ‹‹ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው።›› እነሱ በተናገሩት ብቻ ለምን ትፈርዳላችሁ? እሱን ሳትሰሙ መፍረድ ተገቢ ነው ወይ? ማለቱ ነበር፡፡ አይሁድ እንደ ሎሌዎቹ ሁሉ ኒቆዲሞስን ማቃለል እንዳይችሉ የተከበረ መምህር ሆነባቸው፡፡ ስለዚህ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።›› ጌታችን ከገሊላ ናዝሬት መምጣቱን በመጥቀስ መሲህ ከገሊላ አይነሣም ብለው ሊያስተባብሉ ሞከሩ፡፡ ይህ ግራ መጋባት በሐዋርያው ናትናኤልም የታየ ነበር እርሱ ‹‹ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?›› ብሎ የጠየቀው መሲሁ ከይሁዳ ቤተ ልሔም እንደሚነሣ የተነገረውን ትንቢት በማየት ነበር፡፡ ጌታችን የተወለደው ከቤተ ልሔም ነው ያደገው ግን በገሊላ ናዝሬት በመሆኑ ነው ይኼ ሁሉ ውዥንብር፡፡ ኒቆዲሞስ ክርስትናውን በሌሊት ፈርቶ ጀመረ፡፡ አሁን ሙሉ በሙሉ ክርስቲያን ነኝ ብሎ መመስከርና መግለጥ ባይችልም ቢያንስ አይሁድ ከአለቆች ማን በእርሱ አመነ? ብለው ሲዘብቱ ቢያንስ ድምፁን ለማሰማት ሞከረ፡፡ በጥያቄ አስጨንቆም በዚያች ዕለት ስብሰባውን በተነው፡፡
ፍጹማዊው ኒቆዲሞስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል መከራ ዓለምን የማዳን ሥራውን ፈጸመ፡፡ በዚህ የመከራ ወቅት በዋለበት የዋሉ ባደረበት ያደሩ ደቀ መዛሙርቱ ከዮሐንስ በቀር በፍርሃት ተበተኑ፡፡ ነፍሱን ከሥጋው ተለይቶ ከመስቀሉ ሲወርድም አንድም ሐዋርያ አብሮት አልነበረም፡፡ በዚህ ወቅት ኒቆዲሞስ እንደ ቀድሞው ሌሊት እስኪሆን አልጠበቀም፡፡ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ ከአርማትያው ዮሴፍ ጋር ሆነው የጌታችንን ሥጋ ወሰዱ፡፡ እንደ አይሁድ የአገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት፡፡ ሲገንዙት እያለቀሱ ነበር ‹‹ሞትከኑ መንሥኤሆሙ ለሙታን ፤ ደከምከኑ መጽንኤሆሙ ለድኩማን›› ‹‹ሙታንን የምታስነሣ ሆይ ሞትክን? ደካሞችን የምታጸናቸው ሆይ ደከምክን?›› እያሉ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጌታችን በመለኮቱ ሕያው እንደመሆኑ አነጋገራቸው፡፡ በነገራቸው መሠረት ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት…›› የሚለውን በኪዳን ወቅት የምናደርሰውን ዓለም አቀፋዊ ጸሎት እያደረሱ ገነዙት፡፡
ኒቆዲሞስ ሲፈራ ፣ ቀስ እያለ ሲናገር የነበረውን ክርስትናውን በአደባባይ ገለጠ፡፡ ‹‹ልቡ ለጻድቅ ውኩል ከመ አንበሳ›› ‹‹ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ሳይፈራ ይኖራል ›› እንዲል ጠቢቡ በጌታ የደረሰ መከራ ቢደርስብኝ ሳይል ሥጋውን ተሸክሞ ገነዘ፡፡ ከምኩራብ ያስወጡኛል ብሎ የፈራው ኒቆዲሞስ ቤተ ክርስቲያን እንዳለች ስለተረዳ በድፍረት ክርስትናውን መሰከረ፡፡ ከሦስቱ የኒቆዲሞስ ክርስትና ደረጃዎች እኛ በየትኛው ላይ ነን? ስለ ሃይማኖታችንስ በየትኛው ደረጃ እንመሰክራለን፡፡ በጨለማ ነው? ፈራ ተባ እያልን ነው ? ወይንስ ያለ ፍርሃት?
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 2006 ዓ ም

"በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ"
(ሽራፊ ሃሳብ 1 ከኒቆዲሞስ ምንባብ)
ኒቆዲሞስ በውድቅት ሌሊት ወደ ጌታችን መጣ። ሌሊት እንግዲህ በቂ ብርሃን የሌለበት ፣ እንቅፋት የሚበዛበት ፣ ጭልም የሚልበት ፣ ግራ ቀኝ ቢያዩ ሰው የሚታጣበት ፣ ማጅራት ከሚመቱ ወንበዴዎች በቀር በመንገድ ሌላ ሰው የማያጋጥምበት ፣ ብርድና ቆፈን ሰውነትን የሚያስጨንቅበት ሰዓት ነው። ይህ የአይሁድ መምህር በሌሊት የመጣበት ምክንያቱ ብዙ ሲሆን ለእምነት ማነስ ማሳያ የሚሆን ሰው ነው።
ዛሬ ደግሞ ለአፍታ ኒቆዲሞስን "በሌሊት ወደ ኢየሱስ በመምጣቱ" በጥቂቱ እናመስግነው። ብዙ እግሮች ወደ ኃጢአት በሚሮጡባት ሌሊት ወደ ክርስቶስ የሮጠውን ይህንን ሰው እስቲ እናድንቀው! ይህንን የሌሊት ግርማ ሳይበግረው ወደ ኢየሱስ የተጓዘ የጨለማ ተጓዥ ፣ ይህንን ሰዓታት ቋሚ ፣ ይህንን ማሕሌት ቋሚ በጥቂቱ ብናመሰግነው ምን አለ? ከጌታ ፊት ቆሞ ቅኔ የተመራውን ፣ ስለ ልደት እየተናገረ ስለ ጥምቀት የሚያመሰጥረውን የፈጣሪን ቅኔ ተቀብሎ ሊያዜም ከጀመረ በኋላ መቀበል ሲያቅተው ጌታችን "አንተ የአይሁድ መምህር ስትሆን ይህንን አታውቅምን?" ብሎ የገሠፀውን ኒቆዲሞስን እስቲ ዛሬ በበጎነቱ አርኣያ እናድርገው።
በሕይወታችን ውስጥ የተስፋ ብርሃን ጭልም ባለብን ጊዜ ፣ እንቅፋት በበዛብን ወቅት ፣ ግራ ቀኝ አይተን ሰው ባጣንበትና ብቸኝነት በዋጠን ሰዓት ፣ ክፉ ከማድረግ በማይመለሱ ጨካኞች በተከበብን ሰዓት እኛስ ወዴት እንሔዳለን?
ሕይወቱ "ሌሊት" የሆነበት ሰው ሁሉ ወደ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ቢሔድ እንደሚሻለው ከኒቆዲሞስ የተሻለ ምሳሌ የለም። ሕይወቱ የጨለመ ባይሆን እንኳን ልቡ የጨለመበት ፣ በኃጢአት ጠል የጠቆረ ፣ በበደል ብርድ ቆፈን እጅ እግሩ የታሰረ ከእኛ መካከል ስንት አለ?
እመነኝ ፣ ተስፋ ቆርጠህ ቁጭ ብለህ እስከሚነጋልህ ብትጠብቅ አይነጋም። ይልቅ ተነሥና "በሌሊት ወደ ክርስቶስ ሒድ" እርሱ ተስፋ ለቆረጠው ማንነትህ ዳግመኛ መወለድ እንዳለም ይነግርልሃል። ኒቆዲሞስ ጌታችንን ሊያየው ሔዶ ራሱ ታይቶ እንደመጣ አንተም ወደ እርሱ የቀረብህ እንደሆነ ራስህን ታያለህ።
በ"ሌሊት" ውስጥ ለሚኖር ሰው ነግቶ ፀሐይ ትወጣልኛለች ብሎ ከሚጠባበቅ ይልቅ በሌሊት እንደ ኒቆዲሞስ ተነሥቶ ወደ ጽድቅ ፀሐይ ወደ ክርስቶስ ቢሔድ ይሻለዋል። ወደ እርሱ ለሚሔድ ሰው ሌሊቱ ይነጋል ፣ ክርስቶስ ያለበት ሌሊት ከቀን ይልቅ ብሩሕ ነው ፣ እውነተኛው ብርሃን ያለበት ጨለማም ጨለማ አይደለም። ስለ እርሱ "ጨለማም በአንተ ዘንድ አይጨልምም" ተብሎ ተጽፎአልና።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 16 2010
ኒቆዲሞስ
ናይሮቢ ፣ ኬንያ

+ በርባን ይፈታልን +
ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈትቶ በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡
ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)
ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው መውደድ ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን ጌታችን ነበር፡፡
ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን?
ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡
በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል!
‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ
ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ
እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት
የሞቱን መድኃኒት …››
ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡
(ሕማማት ከሚለው መጽሐፍ ለመድኃኔ ዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ የተወሰደ)

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው
እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት
ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር
እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"
ልብ አድርጉ :-
ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል
ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::
ይህንንም እናስታውስ
ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::
ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-
"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ ም
Translated from Mighty arrows publications