ወደ 600,000 የሚጠጋ ብር ይቀራል።

ያልተሳተፍን ተሳትፎአችን ይቀጥል!

ለጓደኛችን የአቅማችንን ድጋፍ ማድረጉን እንቀጥል።

Samson Yishak Beyene
CBE: 1000139965691
Awash Bank: 013201172039000

Birhane Beyene Mideksa (his Mom)
CBE: 1000549927681
Awash Bank: 01347903970500

Thank you in advance for your kind concern and donation!

GoFundMe: (14k USD on GofundMe) https://gofund.me/693af59f
ስለ እናቶች ልናዘጋጅ የነበረው የስዕል ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል!
@debolteam
Page 101 : የሬዚደንቱ ዲያሪ ገፅ 33

"ወንድሞቼ ሆይ ስለታናሾቹ የማይጨነቅ የሆነ የቀደመን ስግብግብ ትዉልድማ
አለ ። የዚህኛዉን ትዉልድ ህይወት እያጨለመ ያለ ። ራስ ወዳድ ከመሆናቸዉ የተነሳ የራሳቸዉን ህይወት ያቅል እንጅ ከታች ላለዉ ትዉልድ እጣ ፈንታ የማይጨነቁ ድኩማን!
.
በነሱ ጊዜ ጠቅላላ ሀኪምነት ክብር ነበር። አራከሱት!…እጅህን አስረዉታል
እና…ወደፊትም ስፔሻሊስት ስትሆን እነሱ ሰብ ስፔሻሊስት ይሆናሉና አያስተምሩህም፣
እጅህ ይተሳሰር ዘንድ ፈርደውብሀልና …"
(ከ 2ዓመት በፊት የተፃፈ)
.
ዛሬስ
ትላልቅ ሲኒየሮች ከፊት መምጣታቸው ታሪካችንን ይቀይረው ይሆን?
አብረን የምናየው ይሆናል!

ለውጡን ያፅናልን ። አንድነታችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ይጠንክር!

@debolteam
"ልጄን"
PAGE 102 : የሬዚደንቱ ዲያሪ
.
ወደ ምርመራ ክፍሌ 1 እናት ገባች...

ገና ከመቀመጧ የቀሉ አይኗቿ በጣም እንዳለቀሰች ያሳብቃሉ አሁንም እምባ አቅረዎል...

የለበሰችው ሙሉ ጥቁር ልብስ ÷ ጠየም ካለ የቆዳዎ ቀለም ጋ ተዳመሮ አንዳንች የሀዘን ስሜት ይፈጥራል...

ምነው እናቴ?*ምን ሆነሽ ነው? ስል ግራ በመጋባት ጥያቄየን አቀረብኩ... ሁኔታዎ ያልተለመደ ነበር እና...የህመሟን ሁኔታ ለመረዳት ጓጉቼ...

አስፖልቱ....አስ...ፓልቱ አለች በተቆራረጠ ድምፅ...

ወደ ሆስፒታላችን ስትገባ ያቋረጠቸውን ከባ/ዳር ÷ አዴት ÷ አ/አ መስመር...

አስፖልቱ...ልጄን...

አስፖልቱ...ልጄን...
ልጄን አስታውሶኝ ነው...አለች እንባዎቿ ዱብ ዱብ ማለት እየጀመሩ...

ከወራቶች በፊት በነበረ ግጭት ከሆስፒታላችን ፊት ለፊት አስፓልቱ ላይ የሞቱ ልጆች ነበሩ እና... ሁኔታው ወዴት እየኸደ እንደሆን ስለገባኝ በሀዘኔታ ተክዤ ዝም አልኩኝ...

እናታችን ግን ቀጠሉ...
"ስልኬን አስጭኜ እመለሳለሁ ብሎ ÷ መመኪያየ ብቸኛ ልጄ እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ" ብለው ማልቀስ ቀጠሉ...

ሐኪም ነኝ : ታዲያ ይሄ እንዴት አድርጓ ቢታከም ከእናትየዎ አዕምሮ ይጠፋል...ፍትህስ ወዴት አለች?

@debolteam
#EMA ስለ ጤና መድን
.
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ለጤና ባለሙያው የተጠናከረ የጤና ኢንሹራንስ ስርዓት እንዲኖር ለመስራት ከሚሹ ሁሉ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው፡፡

ባለፉት ቀናት ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ሐኪሞች ሁሉም የአቅሙን ለማድረግ ሲረባረብ ተመልክተናል፡፡ በእውነት ፍጹም ኢትዮጵያዊ በጎነት የታየበት የአቅምን ብቻ ሳይሆን ያለውን የሰጠም ሰው ተመልክተናል፡፡

ይሁንና የነዚህን ሁለት ውድ ሃኪሞቻችንን ህይወት ከመታደግ በተጨማሪ በቀጣይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መሰረታዊ በሚባል ሁኔታ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በሚያስችል ልክ መሰራት እንዳለበት ከታች ጀምሮ እሰከ እውቅ ፕሮፌሰሮች ድረስ ሃሳብ ሲሰነዘርበት በሐኪም ፔጅ ለመመልከት ችለናል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ከግል ተነሳሽነት በመነሳት ልዩ ልዩ ሃሳቦች በማምጣት እየተጉ ላሉ ተቋማትና ግለሰቦች ያለንን አድናቆት ሳንገልጽ አናልፍም፡፡ የግል ምልከታን በጽሁፍ ከመግለጽ በተጨማሪ ተቋማዊ በማድረግ ለመስራት መሞከሩ ደግሞ አፈጻጸሙን ለማፋጠን ሁነኛ መንገድ በመሆኑ ይህም የሚደነቅ መነሳሳት ነው፡፡

እኛም ጥሪ ከቀረበላቸው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መካከል ልዩ ልዩ የፕሪምየም አማራጮች ይዞ ከመጣ አንድ የኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር የተሻለ መቀራረብ በመፍጠርና ልዩ ልዩ ስብሰባዎች በማካሄድ ለሕክምና ባለሙያው የተሻለ ፕሪሚየም በሚያስገኙ ዝርዝሮች ዙሪያ ድርድር በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡

በመጨረሻም ይህንን ሃሳብ በነጻነት እንዲንሸራሸር የሚዲያ ሃላፊነቱን እየተወጣ ለሚገኘው ሃኪም ፔጅ፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የድርሻቸውን ከመወጣት በተጨማሪ ልዩልዩ ሃሳቦችን በማቅረብ ብዙ አካላትን ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ አስተያየት ለሰጣችሁ ባለሙያዎች በሙሉ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር አባላት ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡

@debolteam
ማብሪያ ማጥፊያ!
.
በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል።

በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል።

ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።

መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።
ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።

ብዙ ጊዜ የኛ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው።

እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለፈጣሪ ይሁንና እንደዚህ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን ሁሉ በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋልና ቀኑን ፈታ እያላችሁ ዎሉ🙏

Via @Behailu beljige
Thank You Dr.Mezgebu for sharing!

@debolteam
📣 📣 Call from NADAN

Are you a passionate mental health professional or organization driven to make a real difference?

☀️ Are you a psychiatrist, psychologist, social worker, mental health specialist, counselor, or a Company/Organization with a shared mission?
🤝 We invite you to work with us!

NADAN INITIATIVES, a leader in innovative psychosocial development and mental health solutions, is building a groundbreaking community wellness program in Ethiopia's Amhara Region. This program tackles the deep-seated psychological wounds and psychosocial challenges caused by recent conflicts and socioeconomic constraints.

👌This program will provide essential resources and support to individuals and communities before crisis strikes.

🤝 Ready to join?Click here to register: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdHUre0xZNeh8g_hexVAoH7K0chF5Vv6_fptvN2zPBi2Tpq-Q/viewform?usp=sf_link

For more info
📞+251927958822

@debolteam
5.2 Million Birr #update
.
5,268,124 ብር ($18,121 ጨምሮ ) በእናንተ ትብብር ለዶ/ር ቤተል ሕክምና ተሰብስቧል።

ለ6 ወራት በሕንድ ሕክምናዋን እንደምትከታተልና 2 የአጥንት መቅኔ የሚለግሱ ሰዎች አብረው ስለሚሄዱ ድጋፋችሁ ይቀጥል...

Bethel Germamo Ganebo
CBE 1000105102384

https://gofund.me/0e1735fd

@debolteam
"ዛሬ ግንቦት ልደታ ስራ አጥ የሆንኩበት ቀን ነው" ፕሮፌሰር ወንድማገኝ

አገራችን እንቁየ ሐኪሞቿን እያጣች ትገኛለች ። ዛሬም ፕሮፌሰር ወንድማገኝ ከባ/ዳር ዪኒቨርስቲ መልቀቁን አሳውቋል ። እንዲህም ብሏል....

"ለሞያዊ ማንነቴ ትልቁን መሰረት የጣለው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲን ፤ የ 14 ዓመት ቤቴን ትናንት መሰናበት ነበረብኝ፡፡ ለመወሰን ከባድ ነበር ግን መሆን ነበረበት፤ አዎ መልቀቂያየን ሳስገባ የሆነ የአካሌ ክፍል ያጣሁ ሁኖ ነው የተሰማኝ፤ አለቀስኩም፡፡ ዩኒቨርሲቲው እና የህክማና ኮሌጁ የሞራል ኮንፓሴ፤ የነጻነቴ ምንጭ፤ ዞሮ መግቢያየ ፤ የስራ ገበታየ፤ በየቦታው አንጠልጥያቸው የምዞር መጠርያየ ነበሩ፡፡ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ፤ ዛሬ ከቋሚ ስራተኝነት ብለቅም ማስተማሬን እና የምርምር ስራዎቼን እንድቀጥል መድረኩን እንደምታመቻቹልኝ ሙሉ እምነት አለኝ ። ለሁሉም ነገር መጀመርያ አለው እንደሚሉት፤ ዛሬ ግንቦት ልደታ ስራ አጥ የሆንኩበት ቀን ነው ማለት ነው..."
ፕሮፌሰር ወንድማገኝ

ምቹ የስራ ቦታ ለሀኪሞቻችን!
@debolteam
Debol Surgery 4th Edition 2012e.c.pdf
12.6 MB
5th edition of Debol Bedside Oriented Surgery!

Medicine is an ever changing science. It has been almost 4 years since the 4th edition of Debol Bedside Oriented Surgery got released.

Debol team (@debolteam) would like to give the original file for a team interested in preparing the 5th edition with higher quality than it was.

If you have built a strong & dedicated team for this amazing task, please contact us ASAP.

Put ur finger print on #DEBOL SURGERY!

@debolteam

Medicine's Creativity Hub!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎙Podcast by Dr.Kaleab for DELT Yemariamwork General Hospital

Dr.Kaleab
Nigussie
🔥Senior graphic designer
🔥Medical intern
🔥BSc in Health informatics
🔥MSc in computer science
🔥Narrator

@debolteam
Medicine's creativity Hub!

Think outside the box!
Under construction!
.
Tropical Obstetrics & Gynecology || BCOG
.
https://www.youtube.com/@BCOG927
.
@debolteam
Anyone with a slightly used DP15 ULTRASOUND for sale...
📞Call me with this number 0922263841

@debolteam
2024/05/16 20:17:32
Back to Top
HTML Embed Code: