Telegram Web Link
Professor Nigusie Tebeje - ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ

የቮልስዋገን ታሪካቸው እና ከነ ክብራቸው እንዘክራለን

ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ በ1965 በቀድሞው አፄ ሀይለስላሴ ዩኒቨርስቲ በሲቪል ኢንጅነሪንግ ትምህርት ብቸኛው የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ የነበሩ እና ሜዳልያውንም ከኤፄ ሀይለስላሴ እጅ የተቀበሉ ኢንጅነር ነበሩ በመቀጠልም ወደ አሜሪካ ሀገር በማቅናት ማስትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማእረግ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፣ በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሲቪል ምህንድስና ለ3 አመት ሌክቸር አስተማሪ በመሆን እና በቀጣይም ከ1975-1991 ረጅም አመት የትምህርት ክፍሉ ከፍተኛ ዲን በመሆን አገልግለዋል። ይህ ብቻ አይደለም በአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ግብዣ እየቀረበላቸው እውቀታቸውን ያለ ስስት አካፍለዋል ።

አንድ የዘርፍ ባለሙያ ብቁ የሚያደርገውንም ምርምር ያሳኩ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ 8 ድንቅ መፀሀፍትን አሳትመዋል፣ እነዚህ CENG ተብለው በአብዛኛው የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች በሪፈረንስም ሆነ በዋና መፀሀፍትነት በትምህርት ጊዜ ተጠቅመንበታል እጅግ በጣም ቆንጆ የምህንድስናን እውቀት በቀላሉ የሚያስረዱ ሀገር በቀል መፀሀፍት ናቸው።

Part 1
11👍2
ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ የሲቪል ምህንድስና የተማሪዎቸወም ሆነ አጠቃላይ ሀገራዊ ማህበር መስራች(Founding Fathers) ጭምር ናቸው፣ አሁንም ድረስ ይህ ማህበር በጥንካሬ ያገለግላል ብዙ ተማሪዎች በዚህ ማህበር አይናቸውን ከፍተውበታል መሸጋገሪያ ድልድይም ሆኗቸዋል እና ለዚህ ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል። በተማሪም የ United States High Buildings Council, International Bridge and Structural Engineers Association, African Network Scientific Technology Institute መስራች ናቸው

ከዚህ በተጨማሪም ፕሮፌሰር ንጉሴ አዲስ አበባ ውስጥ እና በሌሎች ክልል ከተሞች ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በምህንድስና ጥበባቸው መርተዋል ለአብነት ያህልም ንብ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ አዳማ ስታድየም፣ መቀሌ ስታድየም፣ ራማዳ ሆቴል፣ ማሪዬት ሆቴል እና እጅግ በጣም ብዙ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መርተዋል አስፈፅመዋል።

ባለ ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑት ንጉሴ ተበጀ በአለም አቀፍ ደረጃ በስትራክቸር ኢንጅነሪን በአሜሪካ እና በአፍረካ ትልቅ ዋንጫ እና የተለያየ ሽልማት ባለቤት ናቸው።

እኝህ ፕሮፌሰር በአዲስ አበባ የትምህርት ዘመናቸው አብራቸው የማትለይ ቡርትካናማ ቀለም ያላት ቮልስዋገን ላለፊት 40 አመት በላይ ያሽከረክሩ ነበር ይህችም ቮልስ እጅግ በጣም ንፁህ ይዞታ ላይ የምትገኝ ከታሪካቸው ጋር ታሪክን ያሳለፈች ቮልስ ነች፣ በእውነት ለስራቸው እና ላበረከቱት አስተዋፅኦ ልናከብራቸው ይገባል።

ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ ባለትዳር እና የ4 ልጆች አባት ነበሩ፣ በተወለዱ በ76 እድሚያቸው ባደረባቸው ህመም ሲታከሙ ቆይተው ከ2 አመት በፊት በህይወት ተለይተዋል። ስራቸው እና አስተዋፇቸው ዘላለም ሲወደስ ይውላል እናመሰግናለን።

© ድሮም ዘንድሮም

@deromzenderom
11👍2
ባሳለፍነው ሳምንት ያካፈልናችሁ አዲስ ወደ ኤሌክትሪክ የተቀየረ ቮልስዋገን መኪና ታሪክ ነበር። የዚህ ፈጠራ ባለቤት የሆነውን ግለሰብ በስልክ አውርተን ከናንተ የተነሱ ጥያቄዎችን አቅርበንለት ነበር

ጥያቄ 1) ምን ያህል ቻርጅ ያደርጋል? ምን ያህል ብር ያወጣል?

መልስ 1) ምንም አይነት ብር ቻርች ለማድረግ አይወጣም፣ ምንም አይነት የቻርጅ ሶኬት የለውም፣ ቻርጅ የሚያደርገው ጎማው በሚፈጥረው መካኒካል ኢነርጂ ወደ ኤሌትሪክ ኢነርጂ በመቀየር ባትሪ ላይ ቻርች ያጠራቅማል → ከዛ ኤሌትሪካል ሞተር ያንቀሳቅሳል፣ የ35 ደቂቃ መንዳት ለ8 ሰአት ያህል መኪናው መገልገል እንዲያስችል ያደርገዋል፣ በሚገርም ሁኔታ 220v~ ስለሚያመነጭ መብራት በሚጠፋ ጊዜ ስቶቭ እና ሌሎች የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ሳይቆራረጥ ማመንጨት ይችላል

ጥያቄ 2) ምን ያህል ወጪ አወጣህ?
መልስ 2) ከ320,000 ብር በላይ አውጥቻለሁ፣ ከዛም ባነሰ ዋጋ እስከ 150,000 ብር የኤሌትሪክ አዲስ ጥሩ ጉልበት ያለው ሞተር ከቀረጥ ነፃ ማምጣት ይቻላል ብዙ ሰውም ተጠቃሚ መሆን ይችላል።

ጥያቄ 3) የፈጠራ ስራ ነው ማለት ይቻላል?
መልስ 3) የፈጠራ የሚያደርገው ስራዎች አሉ እነሱንም በፈጠራ ስራ ምዝገባ ላይ ይገኛሉ ከቆይታ በሗላ ሰዎች ይሄንን ነገር ከፍለው ማስቀየር እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።

@deromzenderom
👍8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በቪትስ መኪና 90 ሲሄድ እስክስታ ለሚመታው ጀለስ

በ120/130 በቮልስ እንደሚኬድ አሳዩት please 😁

@deromzenderom
🥰74😁1
ስለ ነጩ ኮምቢ ቀስ ብለን እናወራለን አረንጓዴው ቢትል እንዴት እዛ ላይ ወጣ 🤔😂

@deromzenderom
😁6🤣3👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዲዛየር በጣም ከርካሽ እቃ ከመመረቱ የተነሳ እንደ ፊኛ ይንሳፈፋል 😂🙆‍♂

ጎርፍ ውስጥ ቢያልፍ አስቡት 🪽🪶

ፍልውሀ አካባቢ ጎርፍ ነሀሴ 17/2015
😁2
ላለፉት ብዙ አመት መኪኖችን ፅድት አድርጎ በማደስ ምርጥ ስራ የሚሰራው ወንድማችን ሄኖክ የእጅ ስራ ነው👌

ለም ሆቴል በሄኒ መኪና የማያውቀው የለም

እናመሰግናለን ለአገልግሎትህ Henock Lemhotel 🏆

@deromzenderom
👍32
ከእለታት በእሁድ ቀን thank you @city_cruise_ for inviting us

More photos coming soon

@deromzenderom
12
2025/07/08 18:07:08
Back to Top
HTML Embed Code: