Telegram Web Link
እዚህ ላይ እንኳን ደንግጠው ነው እንጂ እርሱ የጠቀሳቸው እነ ቅዱስ ሄሬኔዎስና ቅዱስ አግናጥዮስ መልስ የሰጡት ታዲያ ለማን ነበር? ብለው መጠየቅ ይችሉ ነበር:: ዶሲቲስቶችና ግኖስቲኮች ሙሉ በሙሉ የፓስተሮቹን ሃሳብም ባይሆን ቁርባን ላይ ተቃዋሚዎች ነበሩ:: የምሕረት መልአክ ቀሳፊ መልአክ ሆኖባቸው ግን ትንሽ እንኳን አልታገሉም:: ግን ዶሲቲስቶችና ግኖስቲኮች ተጠቃሽ ክርስቲያኖች ስላልሆኑ ሁለት ወገን አልነበረም ቢል ዲያቆን ምሕረት ልክ ነው::

“So you are saying” አለ ፓስተሩ:: የJordan Peterson እና የCathy Newmanን አስቂኝ ቃለ መጠይቅ ከሰማሁ ወዲህ ክርክር ላይ “So you are saying” ብሎ ተከራካሪው አፍ ውስጥ ቃላት ለመክተት የሚሞክር ሰው የራሱን ቀብር ጡሩምባ እየነፋ ይመስለኛል::

ፓስተሩ “እሺ ሉተርስ?” አለ:: (ኸረ ባልወልድህም አደርስሃለሁ ተው በሰው ፊት አታዋርደኝ:: ሉተር እንኳን ቁርባንን ተቃውሞአል በልልኝ [በሆዱ ያለ ይመስለኛል])

ምሕረት ወይ ፍንክች የሉተርን መፍቀሬ ቁርባን የሆነ “I would rather drink pure blood with the pope than mere wine with the radicals” የሚል ንግግር ሊጠቅስበት ጀመረ:: (በዚህ ጉዳይ ሉተርና ሚካኤል የሚል ያልታተመ መጽሐፍና ያልተለቀቀ የYoutube video ስላለ ሁለቱንም በቅርብ እዚሁ ላይ Link አደርጋለሁ) “ነገሩ የመጣው ገና 500 ዓመት ከሆናቸው ከራዲካል ሪፎርመሮች ነው” ብሎ የሉተርን ባላንጦች ጠቀሰበት::
@diyakonhenokhaile
ፓስተሩ “ጊዜው ምን ያደርጋል” አለ:: ስለ ታሪክ እየተወራ ጊዜው ምን ያደርጋል ከሚል ሰው ይሰውራችሁ::

“ከታሪክ አንጻር ክርስትና ጌታ ለሐዋርያት የሠጠው እምነት ነው ብለህ ካመንህ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች የምታምነውን እንደሚያምኑ የሚያሳይ ነገር ልታገኝ ይገባሃል” አለው::

ፓስተሩ “ወዳጄ እመነኝ በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ሁሉ ክርስቶስ ‘የራሱን ሥጋ’ በልቶአል ብለው አላመኑም” ብሎ ነገሩን ridiculous ሊያደርገው ሞከረ:: ይህን ስሰማ ትዝ ያለኝ “ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል?” ብለው አይሁድ የተከራከሩት ክርክር ነው:: ዮሐንስ 6:52
ጌታ ሥጋዬ እነሆ እያለ የለም ሥጋህ አይደለም ብሎ ክርክር እንዴት ያለ ነው::

ዲያቆኑ ሐዋርያውን ጠቅሰ “ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል” 1 ቆሮ. 11:30 ከዚያም : “ሥጋና ደሙ ተራ እንጀራና ወይን ብቻ ከሆነ እንዴት ሳይገባቸው ተቀብለው የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ቻሉ?” ብሎ ጠየቀ::
አዝናኙ ውይይት እንደቀጠለ ነው:: ሰውዬው ጥያቄውን መመለስ ትቶ Unworthy ማለት worthy ያልሆነ ነው ብሎ ቃሉን አብራራ:: ቀጠለና ጉዳዩን ከማይገናኘው የሴት ጠጉር አለመሸፈን ጋር አገናኘው:: (ሲጀመር ጠጉር ስላልሸፈነች የሞተች የለችም እየተወራ ያለው ቆርበው ስለሞቱ ሰዎች ነው) አልበቃው ብሎ ስለ sex godess ስለ me too movement ዘባረቀ:: መልስ ስታጣ የምታውቀውን ሁሉ ልትዘባርቅ እንደምትችል ያሳያል::

ዲያቆኑን ማባበልም ጀመረ “የአንተን ሃሳብ የሚያራምዱ ሰዎችን ከልቤ አከብራለሁ:: እውነት እውነት እላችሁዋለሁ የሚለውን ይዘው ይህ እውነተኛ ሥጋው ነው የሚሉት ከልብ አከብራለሁ” አለ:: አክባሪ ይሥጥልን ግን እኛ ይሄን ጥቅስ እንደማስረጃ አላነሣንም:: ዲያቆኑ እዚያው ቆሞ “ለተራ እንጀራ ሰው እንዴት ይሞታል?” ብሎ የጠየቀውን ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ትቶ ከዚህ በፊት ሌሎች ሰዎች ያነሡትን weak argument እየጠቀሰ እንዲህ በለኝና ልርታህ ብሎ ተለማመጠ:: (ተው ባልወልድህም አባትህ እሆናለሁ is in my head)

ከዚያ ደግሞ በmystical change የሚያምነውን ኦርቶዶክሳዊ በግድ transubstantiationን ካላመንክልኝና እርሱን ለመቃወም ያጠራቀምኩትን መከራከሪያ አንተ ላይ ልጠቀመው ይል ጀመር::

ቀጥሎ የተነሣው ድኅነት ሒደት ነው የሚለው ሃሳብ ነው:: ይሄን ጊዜ ፓስተሩ ከቁርባን ርእስ እርፍ ያለ መስሎት ፈነደቀ::
“It is now becoming a salvation issue” እያለ ሲቅበጠበጥ አሁን ገና ተመቻቸህልኝ ብሎ ደስ እንዳለው ያስታውቅ ነበር:: ምሕረቱ “ድናችኋል ብቻ ሳይሆን ትድናላችሁም ይላል” ብሎ የድህነትን ሒደታዊነት አብራራ::


ይህን ጊዜ ሌላው ፓስተር ጸጋ አላስቻለውምና ገባ

ፓስተር ጸጋ “ በጸጋው ድናችኋል” ይላል አለና ዘሎ ገባ::

ድኅነት synergetic ስለሆነ የጸጋው energy የእኛን ትብብር ይሻ የለም ወይ? አለና ምሕረቱ “መዳናችሁን ፈጽሙ”ን ጠቀሰ:: አብርሃምም ልጁን የመሠዋቱን ሥራ አነሣ:: እነርሱ ግን “work out your salvation” የሚለው ቃል ውስጥ “work” የሚል ቃል ሲሰሙ ደስታቸውን መሸከም አልቻሉም:: ቃሉን ጳውሎስየተናገረው መሆኑም አላሳሰባቸውም::

ሥራን ለማጣጣል የቀኙን ወንበዴ ጠቀሱ:: ተቸንክሮ ምን ሊሠራ ይችላል አለ:: (Though the thief on the cross was nailed, he still worked on his salvation. He confessed his sin, saying that he was worthy of the cross. He taught his companion to fear God, and he professed the purity of Christ and the coming of His kingdom)

እግዚአብሔር ባልሠጠው መክሊት አይጠይቅምና circumstantial ነው አለ:: ሊሞት አልጋ ላይ ስላለ ሰው አለመጠመቅ አላወራሁም ብሎ ሞገተ::
@diyakonhenokhaile
ከዚህ በኋላ ያለው ውይይት ዲያቆን ምሕረትን በግድ ካቶሊክ ካልሆንክ የሚል ንትርክ ነው:: inflability of the councils, vatican 1 2 3 etc

“የቅዱስ ቁርባን ደምን የሰጠው ከእጁ እየፈሰሰ ነበር” የሚል ያላልነውን በሉ የሚል ቃልም በጌታ እንደመዘበት እያለው ተናገረ:: It is not right to ridicule Christ for the sake of argument.
@diyakonhenokhaile

አራት መቶ ዓመት አልፎ ሃሳቡን የAugstine ሊያደርግበት ሲጥር ምሕረት ውይይቱን ወደ አግናጥዮስ ዘመን መለሰው:: የመጨረሻው ጥያቄያቸው

Who is the ultimate authority? የሚል ነበር::
ሲመስለኝ ከዲያቆን ምሕረት የጠበቁት መልስ “The Bible” የሚል ነበር:: እርሱን ካለ “If the Bible is the ultimate authority, where does it say that the first Christians believed it is the actual body and blood?” ብለው ሊዘጉትና መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፈው እውነት በላይ ያንን እውነት ሰዎች እንዲህ ተረድተውት ነበር እንዲል ጠይቀው ውይይቱን ሊዘጉ ነበር::

ምሕረት የለሹ ዲያቆን ግን Bible በማለት ፈንታ Bibleን በቀኖና የወሰነችውን The Body of Christ ይዞ የሙጥኝ አለ:: የእናቱን የቤተ ክርስቲያንን ቀሚስ ይዞ ድርቅ ሲል

Good to meet you brother አሉና ጨበጡት በአማርኛ ሲተረጎም
“አንተን ብሎ ምሕረት መዓት ሆንክብን እንጂ” እንደማለት ነው::

My beloved brother, Deacon Mihret, may God bless you. We saw ‘Berekete Estifanos’ in you. May God guide your path

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 3 2017 ዓ.ም.
#share #share
@diyakonhenokhaile
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የሚያዩኝ ሁሉ ይላገዱብኛል፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ በእግዚአብሔር ተማመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ቢወድደውስ ያድነው” መዝ. 68:7

“የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበር” ማቴ. 27:39

#share
@diyakonhenokhaile
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/30 16:44:51
Back to Top
HTML Embed Code: