Telegram Web Link
👍15398🙏18🥰7🔥4🤔1
በስዊዘርላንድ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመቄዶንያ ለሚገኙ 8500 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሺህ ብር በመሥጠት ሥጦታዋን ስምንት ሚልዮን አምስት መቶ ሺህ አደረሰች:: ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም የድሆች መጠጊያ መሆንዋን ባስመሰከረችበት በዚህ የመቄዶንያ የእርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ ላይወንጌልን በፅንሰ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር አሳይታለች:: “እናንተ የሚበሉትን ሥጧቸው እንጂ ሊሔዱ አያስፈልግም” ብሎ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረውን ቃል የማትረሳዋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ልጆችዋን እጅ እጅ አድርጋ የመቄዶንያን አረጋውያን ጎብኝታለች:: መቄዶንያ 8500 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማንን አቅፎ የያዘና በፍጥነት ወደ ጤናቸው መመለስ የቻሉትን እዚያው ወደ ሥራ እያሠማራ የሚገኝ ውድ ተቅዋም ነው::

ከወራት በፊት በመቄዶንያ አምባሳደር ሆኜ በተሰየምኩበት ወቅት በመቄዶንያ 7000 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን የነበሩ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ የነበረው የመቄዶንያ ቅርጫፍም 44 ነበረ:: አሁን ያሉት የመቄዶንያ ሕሙማንና አረጋውያን 1500 ጨምረው 8500 ሲሆኑ የቅርጫፎቹም ቁጥር 46 ደርሶአል:: እግዚአብሔርበገሐድ እየሠራ ያለበት ይህን ቅዱስ ሥፍራ እባካችሁ መጥታችሁ ጎብኙ::

በዚሁ አጋጣሚ ሙሉ ገቢው ለመቄዶንያ የሚውለውን ባዚልያድ የተሰኘ መጽሐፌን ለተቅዋሙ ማስረከቤ ይታወቃል:: መጽሐፉ አርትዖቱ እየተጠናቀቀ ስለሆነ ይህንን ሙሉ ትኩረቱን ነገረ ምጽዋት ላይ ያደረገ መጽሐፍ ለማሳተም በኅትመቱ ዘርፍ ያላችሁ ወገኖቻችን እንድታነጋግሩን ጥሪ እናቀርባለን::

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የመቄዶንያ ብራንድ አምባሳደር
ግንቦት 28 2017 ዓ.ም.
#share
@diyakonhenokhaile
306🙏38🥰12😱10👍7😍2
‘አቤል አቤል ስለምን ታሳድደኛለህ?’

ዘንድሮ ሐምሌ አምስትን የምንፈስከው በላምና በጊደር ፣ በበግ በፍየል ደም አይደለም፡፡ የዘንድሮ መግደፊያ በዕለቱ የሰማዕትነት ደሙን ባፈሰሰው በታላቁ ሐዋርያ በብርሃነ ዓለም በቅዱስ ጳውሎስ በራሱ ነው፡፡ በዚህ ዓመት ሐምሌ አምስትን የሐዋርያውን ዜና ሕይወት በልተንና ጠጥተን በንባብ ገበታ እንፈስካለን፡፡

ሐምሌ አምስት ገስግሰን ደማስቆ ላይ እንገናኛለን፡፡ ዲያቆን አቤል ካሣሁን ‘በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ [በጳውሎስ ፍቅር] እያሰረ [በሃሳብ] ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ [የሚሆን ‘ቅዱስ ጳውሎስ’ የተሰኘ መጽሐፍን ይጽፍ ዘንድ] ከእርሱ [ከቅዱስ ጳውሎስ] ለመነ’ ተሳክቶለትም የቅዱስ ጳውሎስ የሕይወቱ ብርሃን በብዕሩ ላይ አንጸባረቀ፡፡

በመጽሐፉ እንደሚል የአቤል ደም እንደጮኸበት በሚነገረው በደማስቆ መንገድ የአቤል ብዕር ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸ ነው ፤ በእርግጥም በደማስቆ መንገድ ላይ ታላቅ ወንድሙን ቃየንን የሚከስስ ሳይሆን ታላቅ አባቱን ጳውሎስን የሚያወድስ የአቤል ብዕር ይጮኻል፡፡ መቼም ለሦስት ዓመታት ሙሉ በንባብ አሰሳ ጳውሎስን ሲፈልግ የነበረውን አቤል ቅዱስ ጳውሎስ ቢያገኘው ‘አቤል አቤል ስለምታሳድደኛለህ?’ የሚለው ይመስለኛል፡፡ በእርግጥም የጳውሎስ መገኛው ደማስቆ እንደሆነች የአቤል ደማስቆ ቅዱስ ጳውሎስ ሆኖለታል፡፡
#share
@diyakonhenokhaile
177🥰12👍7🙏5👏1
2/2
ወንድሜ ዲያቆን አቤል ካሣሁን ቅዱስ ጳውሎስ ላይ ንባብና ምርምር ማድረግ ከጀመረ ሦስት ዓመታትን ደፍኖአል፡፡ ጳውሎስ ተጠርቶ ሦስት ዓመት በሱባኤ እንደዘገየ አቤልም ጳውሎስን ጠርቶ ሦስት ዓመት ይማጸነው ዘንድ ግድ ሆነበት፡፡ የብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅር በሚያስቀና መጠን ያደረበት አቤል ስለ እርሱ ማንበብና መጻሕፍትን መመርመር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ከቅዱሱ ሕይወት ጋር በጣም ከመተሳሰሩ የተነሣ ስለ ሐዋርያው ሲያወራ በቅርበት ስለሚያውቀው አብሮ አደጉ የሚያወራ እንዲመስል አድርጎታል፡፡ በሐዋርያው ዙሪያ እጅግ በጣም ደክሞ ያዘጋጀውን ይህንን ብጥር መጽሐፍ ቀደም ብሎ ቢያወጣው እንኳን በቂ የነበረ ቢሆንም በሥራው ካለመርካትና ለጉዳዩ ክብር ከመሥጠት አንጻር ከድኖ ሲያበስለውና እየከፈተ ሲያማስለው ቆይቶአል፡፡

በክርስትና የታሪክ ጥናት ውስጥ እግዚአብሔር ምርጥ ዕቃው አድርጎ ብዙ ድንቅ ሥራውን የገለጠበትን ቅዱስ ጳውሎስን ማወቅ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በማንም ሊተካ የማይችል ጉልሕ ሚና የተጫወተና የቤተ ክርስቲያንን የአገልግሎት ፍኖተ ካርታ ያሰመረ ሐዋርያ ነው፡፡ ‘እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ’ ያለውን ይህንን ሐዋርያ ሕይወት ማወቅም ክርስቶስንም ጭምር ለማወቅ እጅግ አንገብጋቢ ነው፡፡

ይህንን መጽሐፍ ባነበብኩበት ወቅት በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስን በዚህ ልክ ሳላውቀው እንዴት ቆየሁ? ይኼንን ጥቅስ እንዴት በዚህ መንገድ አልተረዳሁትም? የሚያሰኙ እጅግ በርካታ አዳዲስ እውነታዎችን አግኝቼአለሁ:: ልብ የሚነኩና መንፈሳዊ ተመስጦ ውስጥ የሚከትቱ ሃሳቦችና የቃለ እግዚአብሔርን ጣዕም የሚያቀምሱ አገላለጾች እዚህ መጽሐፍ ላይ ዘንበዋል:: ሌላው ቀርቶ የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ የተጻፈውን ልብ የሚያቀልጥ ታሪክና ምሥጢር ያነበበ ሰው በዋናው ባለ ታሪክማ ምን ሊባል ይሆን ብሎ ነፍሱ በሐሴትም በጉጉትም እንድትናጥ የሚያደርግ ነው:: መጽሐፉን በማንበቤ ያገኘሁት ተደሞና መደነቅ ሌላው ሰው አንብቦ ምንኛ ይደሰትበት ይሆን? ብዬ እንድቸኩል አድርጎኛል::

መጽሐፉ ለማዘጋጀት የተደከመበትን ያህል ለማንበብ የሚያደክም መጽሐፍ አይደለም፡፡ በሥነ ጽሑፋዊ ውበቱና በአቀራረብ ግልጽነቱ ፣ በያዛቸው ተጓዳኝ መረጃዎች ሀብታምነቱ ደግሞ እውነትም የአቤል መሥዋዕት ሊባል የሚችል ከቃየናዊ ግዴለሽነት የጸዳ ለርእሱ የሚመጥን ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ ለጥቃቅን እውነታዎች ሳይቀር ተጨንቆ የጻፈበትን ጥልቀት አንባቢ አይቶ የሚፈርደው ሲሆን ለርእሰ ጉዳዩ የሰጠው አክብሮት ደግሞ ‘አቤልም ከንባቡ በኩራትና ከስቡ አቀረበ’ የሚያሰኝ መሥዋዕት በማቅረቡ ‘የራሱን የማይረባ መሥዋዕት አቅርቦ በሥሙር መሥዋዕትህ ከሚቀና ከቃየናዊ ዓይን ይሰውርህ ፤ ‘ወደ ሜዳ እንሒድ’ ባዮችን ይያዝልህ’ የሚያሰኝ ሥራ ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስን በአራት መቶ በላይ ገጾች የሚያስነብበን ይህ ድንቅ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስን ለሚያጠኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ትልቅ ማጣቀሻ ፣ ‘ይሄ ነገር የሐዋርያት ሥራ ትርጓሜ ይሆን እንዴ?’ ሊባል በሚያሰኝ ደረጃ ግብረ ሐዋርያትን አራግፎ የተጠቀመ ፣ ለቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ደግሞ ለአንዳንዶቹ ክፍሎች ትርጓሜ ለአንዳንዶቹ ደግሞ መቅድም መሆን የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ወዳጆች ለጸሐፊው የተጻፈለትን በአበው ትምህርት የተፈተለ መወድስ ለመመረቅ ተዘጋጁ:: ሌሎቻችሁም ይህንን ድንቅ መጽሐፍ አንብባችሁ ከታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ጋር ዳግም በፍቅር እንድትተዋወቁ እጋብዛለሁ፡፡ ‘ማንበብን ለሚወዱት እንደ ጳውሎስም ለተጠሩት ይህንን መጽሐፍ ማንበብ ለበጎ ነው’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 29 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#share
@diyakonhenokhaile
214🙏21👍15🥰9❤‍🔥7
2025/07/12 18:38:33
Back to Top
HTML Embed Code: