ለኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ገዳም መሬቱ ሲገዛ የተበደርነውን 6 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል የተዘጋጀ ኘሮግራም።
በቀጥታ -Live
👉🏽ከሳን ሙጉዌል ካሊፎርኒያ አሜሪካ👈
👉🏽ገዳሙ ሲገዛ የቀረውን የገንዘብ ዕዳ ከፍለን እንጨርስ!
በረከታችሁን ውሰዱ : ትልቁ ገዳም በሳን ሙጉዌል ካሊፎርኒያ 🇺🇸 አሜሪካ !!! Call Donate your support !!!https://www.youtube.com/live/cpukCNzzxe0?feature=share

Youtube
- YouTube
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
❤54👍52🥰11
+ የሚካኤል ክንፉ +
ቅዱሳን መላዕክት፣ ጻድቃን ሰማዕታት ብዙ ጊዜ ሲዖልን በምልጃቸው በርብረው ሰይጣንን ጉድ ቢሰሩትም የቅዱስ ሚካኤል ግን ይለያል። በእርግጥ ሲዖልን በርብሮ ነፍሳትን በማውጣት እመቤታችንን የሚተካከላት የለም፤ ምክንያቱም በወለደችው በአንድ ልጇ ሲዖልን ባዶ አስቀርታበት ሰይጣንን ጉድ ሰርታው ነበር። ለዚህም ነው ከፍጥረት ሁሉ አስበልጦ ሰይጣን እመቤታችንን የሚጠላት። ከእመቤታችን ቀጥሎ ግን ነፍሳትን ከሲዖል በምልጃው በርብሮ በማውጣት ቅዱስ ሚካኤልን የሚተካከል ያለ አይመስለኝም። አንድ ሰው ወፍጮ ቤት ገብቶ የወፍጮ ብናኝ ሳይነካው መውጣት እንደማይችል ሁሉ ቅዱስ ሚካኤልም ለየሆነ ጉዳይ ሲዖል ደረስ ብሎ ሲወጣ በክንፉ ነፍሳትን ሳይዝ መውጣት አይችልበትም።
ገና ሲነበብ አጋንንትን በሚያርደው በድርሳነ ሚካኤል ጥቅምት ንባብ ላይ እንዲህ ያለ ውብ ተዓምር ተጽፎልናል። "ከደቂቀ አዳም ወገን ሰውነቱ በኃጢአት የረከሰ አንድ ሰው ነበረ፤ ያ ሰውም ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ከተንኮልና ከክፋት በስተቀር አንዳችም በጎ ሥራ ሰርቶ አያውቅም። ነገር ግን አንድ ዓላማ ብቻ ነበረው፤ ይኸውም በየወሩ ቅዱስ ሚካኤልን በዓል ማክበር፣ ዝክሩን እየዘከረ ለነዳያን ማብላት ማጠጣት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ያ ሰው ሞተና አጋንንት ይህች ነፍስ የኛ ናት በማለት ሲደነፉ ሚካኤል ግን የኔ ናት እያለ ይከራከር ነበር።
እንዲህም የኔ ናት፣ የኔ ናት በመባባል ከጌታ ዙፋን ፊት ስለቀረቡ ጌታ አራት አማራጭ ነገሮች አቀረበላቸው። ይህም፦ ሚካኤል ወስዶ ይደብቀው፣ እናንተ ግን ፈልጋችሁ ብታገኙት ውሰዱት፤ ወይም እናንተ ወስዳችሁ ሸሽጉትና ሚካኤል ፈልጎ ካገኘው ይውሰደው፤ ከእነዚህ አንዳቸውን ምረጡ አላቸው። እነርሱ ግን ሚካኤል ወስዶ ከመንበረ መለኮት ቢሸሽገው ምን ለማድረግ እንችላለን እያሉ በሃሳብ ጭንቅ ተዋጡ። ከብዙ የሃሳብ መለዋወጥ በኋላም እኛ እንሸሽገዋለን ብለው ያን ሰው ዕመቀ ዕመቃት አውርደው የገሃነመ እሳት አዝዋሪት ባለበት ጥልቅ ባሕር ውስጥ ደበቁትና እንግዲህ ሚካኤል ፈልጎ ያግኘው ተባባሉ።
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል እነዚያን አጋንንት ከዚህ ቦታ አካባቢ ዘወር በሉ አላቸውና ወደ ሲዖል ገብቶ መፈለግና መበርበር ጀመረ፤ ነገር ግን የሚፈልገውን አላገኘም ነበረ። ነገር ግን ፈልጎ ሲወጣ በአንድ ክንፉ ፯ ዕልፍ ነፍሳት አወጣ፤ በሁለተኛውም ክንፉ እንዲሁ አወጣ፣ በሦስተኛውም አወጣ፣ በመደጋገምም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነፍሳትን አወጣ፤ ሆኖም ሊያገኘው አልቻለም። በዚህ ሰው ምክንያት ያወጣቸው ነፍሳት ቁጥራቸው 7540 ደረሰ፤ ከነዚህም ውስጥ ያልተጠመቁ አረመኔዎች ይገኙባቸው ነበር። ያን ጊዜ የሰማይ መላዕክት ሁሉ ይህስ እጅግ በጣም አስደናቂ ነገር ነው አሉ።"
ከዚህ ውብ ታሪክ የምንማረው ነገር ቢኖር ቅዱስ ሚካኤልን ይሁን ማንኛውንም ቅዱስ መዘከር በፍርድ ቀን ጠበቃ ማቆም ማለት ነው፤ ስለ እኛ ነፍስ ከአጋንንት ጋር ይከራከሩልናልና። የሚገርመው ደግሞ በዚያ ኃጥእ ሰው ቅዱስ ሚካኤልን መዘከር ምክንያት ብዙ ሺህ ነፍሳት ምሕረትን አገኙ። እኛም የፈለገ ኃጢአተኛ ብንሆን ቅዱሳንን መዘከራችን ከእኛ አልፎ የብዙ ነፍሳት መዳኛቸው ሊሆን ይችላልና ቅዱሳንን ከመዘከር መባዘን አይገባንም።

❤118👍44😍8🤩5🙏4🎉2💯2👏1
በአንድ ወቅትም እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" ብሎ የሚያስተምረው የአምላኳ ልጅ ናትና ለጠላቷ ለሰይጣን ይቅር እንዲባል መማለድ ጀመረች። "ሰይጣንን ማርልኝ" ብላ አምላኳን በጸሎት ጠየቀች። ቅዱሳን መላዕክት ኃጢአት እንዲሰሩ ትህትናቸው እንደማይፈቅድላቸው ሁሉ ሰይጣንም ንስሐ ይገባ ዘንድ ትዕቢቱ አይፈቅድለትም እንጂ እኛን ይቅር ያለ አምላክ ሰይጣንንም ቢመለስ ይቅር እንደሚለው የታመነ ነውና ሂጂና ራስሽ ተይቂው ተባለች። ከቅዱስ ሚካኤልም ጋር ሆና የንስሐን ስብከት ለሰይጣን ልትሰብክ ወደ ሲዖል ገሰገሰች። ሰይጣን ግን እንኳን ጥያቄዋን ተቀብሎ ይቅርታ ሊጠይቅና ንስሐ ሊገባ ይቅርና እርሷንም በሲዖል ለማስቀረት ይታገል ጀመረ። በዚህ ጊዜም ነበረ ቅዱስ ሚካኤል እርሷን ነጥቆ ከሲዖል ይዟት የወጣው፤ ነገር ግን እንደለመደው 10 ሺህ ነፍሳትን በክንፉ ከሲዖል አውጥቶ ሰይጣንን ጉድ ሰርቶታል።
በቅጽል ስሙ "ሺህ በክንፉ ሺህ በአክናፉ" ብለን የምንጠራው ወዳጃችን ገናናው መልዓክ ቅዱስ ሚካኤልን በመልክዕ ጸሎቱም እንዲህ ብለን ለክንፉ ምስጋናን እናቀርባለን :-
"ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ። ከመ ሠርቀ ፀሐይ ሥነ ጸዳሉ። ኦ መልአክ ጊዜ ተፈኖከ ዘእምላዕሉ። ይትፌሥሑ በምጽአትከ እለ ውስተ ሲዖል ኵሉ፤ መጻእከኑ መጻእከኑ ሚካኤል ይብሉ።
ሚካኤል ሆይ እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችህ ሰላም እላለሁ። የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ሆይ ከላይ ከሰማይ ተልከህ በምትመጣበት ጊዜ ፤ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሁሉ ሚካኤል ሆይ መጣህልን፣ ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"
ከዘማሪውም ጋር አብረን እንዘምራለን።!!...
"ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ያሳደገኝ መልዓክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው"
አሁንም ዘወትር ከእኛ የማይለየው መልዓክ በክንፈ ረድኤቱ ጠብቆ፣ በአማላጅነቱ ከልሎን ከሲዖል እሳት ያድነን። አሜን!!
..........................................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ (ክንፈ ሚካኤል)
ግንቦት 28/2015 ዓ.ም
ጅማ፣ ኢትዮጵያ

🙏125❤72👍49🥰5💯2
ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን? አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን? የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ የማይሰማው ይመስላችኋል? እንዴት አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
❤237🥰79😭66👍44😢35🙏23🤩4🎉1
"የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም" መዝ. 51:17
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
❤148👍25🥰15
ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ
የአምላክ ሰው መሆንና ተወልዶ የማደጉ ዜና ሲነገር ሁልጊዜም የሚዘነጋ ክብሩ ግን ከብዙ ቅዱሳን ክብር የሚበልጥ አንድ ታላቅ ሰው ዛሬ በልቡናዬ ውል አለ፡፡ መቼም ከፀሐይ አጠገብ ያለ ኮከብ በፀሐይ ብርሃን ምክንያት መሸፈኑ አይቀርምና በተወለደው የጽድቅ ፀሐይ ፣ የሰላም ንጉሥ በልደቱ ደስታ ተውጠን ፣ በገብርኤል ብሥራት ፣ በድንግል ምስጋና ፣ በመላእክት ዝማሬ ተስበን የዘነጋነውን ፣ ድምቀት ሳያንሰው የተሸፈነውን ኮከብ የቅዱስ ዮሴፍን ነገር ባሰብኩኝ ጊዜ ክብሩን ለመናገር ልቡናዬ ተጨነቀ፡፡
በቅድስናው እያመንን ፣ ውለታውንም እያወቅን የምንዘነጋውን ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች የድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለማቃለል ስሙን በክፉ ማስረጃነት ሲያነሱብን ከእነርሱ ሸሸን ብለን ሳናውቅ ከበረከቱ የሸሸነውን ጻድቅ ዛሬ ልዘክረው ብል ልቤ በጥፋተኝነት ስሜት ተጨነቀብኝ፡፡
ስለ እርሱ ብዙ ያልዘመርንበትን ፣ ብዙ ያልተቀኘንበትን ዘመን ሳስብ ‘ላዕከ ማርያም ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ስለረሳንህ ቀኛችን ትርሳን ፣ ስላላሰብንህም ምላሳችን ከትናጋችን ይጣበቅ’ ብዬ ይቅርታውን ለመለመን ተመኘሁ፡፡
ቅዱስ ዮሴፍን ማን ብለን እንጥራው? እርሱ እንደሆን እንደ አብርሃም ዘመዶቹን የተወ አማኝ ፣ እንደ ይስሐቅ የታዘዘውን ብቻ ያደረገ ትሑት ፣ እንደ ያዕቆብ በእምነት ግብጽ የወረደ ስደተኛ ነውና እርሱን ለመግለፅ እንደምን ያለ ቋንቋ እንጠቀም ይሆን?
እስቲ ንገሩኝ? ‘መልካሙን እረኛ’ ክርስቶስን የጠበቀውን እረኛ ቅዱስ ዮሴፍን ከቶ በምን ቃል እንገልጸዋለን? የአብን ልጅ ያሳደገውን (ሐፃኔ ወልደ አብ) ቅዱስ ዮሴፍን በምን ቅኔ እናወድሰው?
ሕዝቅኤል ያያትን የእስራኤል አምላክ ገብቶባት ለዘላለም የተዘጋችውን ደጅ የጠበቀውን ታማኝ ዘብ ፤ ‘ከበሩ ደጀ ሰላም መንገድ በዚያ ይገባል በዚያም ይወጣል’ ተብሎ የተነገረለትን የተዘጋችው በር ደጀ ጠኚ ፣ ከታላቅዋ ተራራ ከድንግል ማርያም ያለ ሰው እጅ ድንጋይ ተፈንቅሎ ሲወርድ ቆሞ የተመለከተውን የሐዲስ ኪዳኑን ዳንኤል ከቶ እንዴት ባለ ቃል እንገልጸዋለን?
በቤተ ልሔም ግርግም ውስጥ በላምና አህያ መካከል የተኛውን ሕፃን የተመለከተውንና እንደ ነቢዩ ዕንባቆም
‘በማዕከለ ክልዔ እንስሳ ርኢኩከ’ /በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ/ ሊል የሚቻለውን የቅዱስ ዮሴፍን ክብር በምን አቅማችን እንግለጸው?
ወደ ግብጽ ወርዶ ለወገኖቹና ለዓለም ሁሉ ምግብን እንዳቆየው የብሉይ ኪዳኑ ዮሴፍ ወደ ግብጽ በመከራ ተሰድዶ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስን ለሁላችን ላቆየልን ጻድቅ እንዴት ያለ የምስጋና ቃል እናዋጣ?

Telegram
ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
Henok Haile
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==

❤123👍64😍16🙏15
የደብረ ታቦር ማግሥት ሽራፊ ሃሳቦች
ጌታ በታቦር ተራራ ላይ ጴጥሮስና ሙሴን እንዳገናኛቸው ሳስብ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳንን አገልግሎት ልዩነት ጎልቶ ታየኝ::
ጴጥሮስም ሙሴም ከባሕር የተመረጡ ናቸው:: ሙሴ እኅቱ በቅርጫት ጥላው ከወንዝ መካከል ተገኝቶ ሕዝብን ነፃ ሊያወጣ ተጠራ:: ጴጥሮስ ደግሞ ቤተሰቦቹ ለሥራ ጀልባ ላይ ትተውት ጌታው ከጀልባ ላይ ዓለምን በወንጌል ነፃ እንዲያወጣ ጠራው::
ጴጥሮስ ዓሣን ከማጥመድ ሰውን ወደ ማጥመድ የተጠራ ነበር:: ስለዚህ በጴጥሮስ ሕይወት ዓሣ ወደ ሰው ተለውጦአል:: ሙሴ ደግሞ ሰውን ወደ ዓሣ የሚለውጥ አገልጋይ ነበረ:: መቼ ካላችሁኝ ከባሕር ጨምሮ ያሰጠማቸውና እንደ ዓሣ በባሕር የቀሩት ፈርዖንና ሠራዊቱ ናቸው::
ጳውሎስ "የሞት አገልግሎት" ያላት ኦሪት ሰውን እንደ ዓሣ ወደ ባሕር ትጨምራለች ወንጌል ግን ሰውን እንደ ዓሣ ከዓለም ባሕር ታወጣለች::
እግዚአብሔር ሙሴን ባሕር ከፍሎ እንዲራመድ አስቻለው:: ጴጥሮስን ግን በባሕሩ ላይ እንዲራመድ አስቻለው:: ኦሪት ባሕርን ከፍላ ታሻግራለች:: ወንጌል ግን ባሕርን እንደ መሬት ታስረግጥሃለች::
በወንጌል ያመነው ጴጥሮስ ለዓመታት ዓሣ ባጠመደበት ባሕር ላይ በእግሮቹ ተራመደ:: እኛንም ጌታ እንደ ጴጥሮስ በባሕር ላይ ሊያራምደን ይቻለው ነበር:: ችግሩ እኛ አምነን እሺ ብለን ከጀልባው አንወርድም:: በባሕር ለመራመድ ደግሞ ከጀልባ መውረድ ያስፈልጋል::
ሙሴን ጌታ ድንኳን ሥራ ብሎት ነበር ጴጥሮስን ግን ልሥራ ሲል ከለከለው:: ኦሪት አላፊ ናትና ድንኳን ሥራልኝ ትላለች:: የዘላለም ወንጌል አገልጋይ ግን ድንኳን መስፋት አያስፈልገውም::
ጌታ የሐዲስ ኪዳኑን ሙሴ ጴጥሮስን "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህ?" ብሎ ሦስቴ እንደጠየቀውና ጴጥሮስ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ እንዳለ ሳስብ ጥያቄውን ለጌታ መልሼ ማቅረብ ብችል ምን ይለኝ ይሆን? ብዬ አሰብሁ::
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ ትወደኛለህ?
ብዬ ብጠይቀው ለእኔ የሚመልሰው ይሄንን ነው::
ልጄ ሆይ እንደምወድህ አንተ አታውቅም::
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 15 2015
ዚጊቲ አርባ ምንጭ
@diyakonhenokhaile

❤110👍45👏7🎉6🥰4😍1
+ አልቆም ያለ ደም +
"በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ" ሉቃ. 8:44
ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።
ደምዋ ፈስሶ አያልቅም ወይ? ዓሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ? እንዴት ያለ ሕመም ነው?! ሰው በክፉ ሽታዋ እስኪርቃት ድረስ የማይቆም ደም::
ባለ መድኃኒቶች ሊያቆሙት ያልቻሉትን የደም ጎርፍ የናዝሬቱ ባለ መድኃኒት በቀሚሱ ብቻ አቆመው:: በልብሱ ጫፍ ብቻ::
ሳያያት ሳይነካት እጁን ሳይጭንባት በልብሱ ጫፍ ብቻ የደምዋን ዝናብ እንዲያባራ አደረገው:: የሕመምዋን ማዕበል ገሠጸው::
በልብሱ ጫፍ ብቻ የሚፈውስ ሐኪም እንዴት ያለ ነው? ቀጠሮ ሳይሠጥህ ሳያናግርህ ቀና ብሎ ሳያይህ ስትነካው ብቻ የምትድንበት ከሆነ እርሱ መድኃኒት የሚያዝ ሐኪም ሳይሆን ራሱ መድኃኒት ነው:: የልብሱን ጫፍ የነካ ከዳነ ሥጋውን የበሉ ደሙን የጠጡማ ምንኛ ይድኑ ይሆን?
ሊፈውሳት አስቦ አልነበረም የዐሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ከሞት ሊያስነሣ መንገድ ሲሔድ ግን እግረ መንገዱን የዓሥራ ሁለት ዓመት የቁም ሙትዋን ፈወሳት::
መድኃኔዓለም እንዲህ ነው:: ወደ በሽተኛው ሳይሔድ በቃሉ ብቻ ተናግሮ ይፈውሳል ፤ በሽተኛው ቤት ገብቶ በአልጋው ላይ ይፈውሳል:: ሊፈውስ ሲሔድም ይፈውሳል:: እናም የሴቲቱ አልቆም ያለ ደም በልብሱ ጫፍ ብቻ ቀጥ አለ::
ጌታዬ ሆይ የእኔንስ ደም የምታቆመው መቼ ነው?
ምን ደም ፈስሶህ ያውቃል ካልከኝ ኃጢአት የሚባል ደም ሲፈሰኝ አይታይህም? አንተስ በቃልህ "ኃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች" ብለህ የለ? እንደ ደም የቀላው የእኔ ኃጢአት ነው:: ይኸው ሲፈስ ከሴቲቱ በላይ ቆየ::
ላቆመው ብል አልቆም አለኝ:: ያላሰርኩበት ጨርቅ ፣ ያልሞከርኩት ቅባት ፣ ያልሔድኩበት ባለ መድኃኒት የለም:: ገንዘቤን ከሰርኩ እንጂ ኃጢአቴ ግን መቆም አልቻለም:: እንዲያውም መጠኑ እየጨመረ ነው:: ባሕር ሆኖ ሊያስጥመኝ የደረሰ የኃጢአት ደም ከብቦኛል::
ለእኔ የሚሆን የቀሚስ ጫፍ ታጣ ይሆን? እኔ እንደ ሴቲቱ ታላቅ እምነት የለኝም ቀሚስህ ግን አሁንም ኃይል አለው:: ልትፈውሰኝ ና አልልህም ስታልፍ ግን ልዳስስህና ልዳን:: ጉዞህን ሳላሰናክል ሰው ሳይሰማ በልብስህ ጫፍ ብቻ ደሜን አቁምልኝ::
እባክህን ደሜ ሳይቆም ሌላ ዓመት አልሻገር::
እኔ ኃጢአቴን "ያለፈው ዘመን ይበቃል" ማለት ቢያቅተኝም አንተ ግን ይበቃሃል በልልኝ::
በእምነት ማጣት የታጠፈውን እጄን ወደ ልብስህ ጫፍ ዘርጋልኝ:: እኔ ማቆም ያልቻልኩትን የበደል ደም ጸጥ አድርገህ "አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ ወጥቶአል" በል:: እነጴጥሮስም ይደነቁ እኔም በሰላም ልሒድ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 2015 ዓ.ም.

❤82👍31😭16🙏7🥰6🎉2
ወታደሮቹ ረዣዥም ስለታማ የሆኑ ብዙ እሾኾችን በጥንቃቄ ጎንጉነው በጌታችን ራስ ላይ አቀዳጁት፡፡ ‹‹የሕይወትን ራስ በራሱ ላይ የእሾኽ ዘውድ ደፉበት›› እሾኹ ወደ ራሱ ዘልቆ ሲገባ ‹‹ከራሱ ቊስሎች ደም እንደ ውኃ በዝቶ ፈሰሰ ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ፤ ሰውነቱም ሁሉ በደም ተጠመቀ››
የእሾኽ አክሊሉ እስከ መጨረሻው ከጌታችን ራስ ላይ አለመውለቁን የምንረዳው ጲላጦስ ‹ሰውዬው ይኸው› (ecce homo) ብሎ በፊታቸው ባቆመባት በመጨረሻዋ ሰዓት እንኳን ጌታችን የእሾኽ አክሊል ደፍቶ በማየታችን ነው፡፡ (ዮሐ. ፲፱፥፭)
እንደ ወንጌሉ ገለጻ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራውን የጌታችን ልብሱን በአንገቱ ሲያወጡና ሲያጠልቁ የእሾኽ አክሊሉን ማንሣታቸውና መልሰው ማቀዳጀታቸውንም መዘንጋት የለብንም ፤ እሾኹን እየነቀሉ በሚሰኩበት ጊዜ ሁሉ ጌታችን ጽኑ ሥቃይ ተሰቃይቷል፡፡
ቅዳሴያችን እንዲህ ይላል ፡-
‹‹ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት ፤
ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፡
ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው ከፊቱ የሚሠወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ እጁን አንሥቶ መታው፡፡
የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡
ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው?
ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው?
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው?›› (ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ፶፪)
ጌታችን የደፋው የእሾኽ አክሊል ከወታደሮቹ ጭካኔ ባሻገር የሚያሳየን ታላቅ ነገር አለ፡፡ የሰው ልጅ ከገነት በተባረረ ጊዜ ‹‹ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን ፤ እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብሃለች›› ተብሎ ተረግሞ ነበር፡፡ (ዘፍ. ፫፥፲፰) ይህ በእርግማን የበቀለ እሾኽ በዕለተ ዓርብ ተጎንጉኖ የጌታችን ዘውድ ሆነ፡፡94 ጌታችን በዚያች ዕለት የደፋው አክሊል የእኛን ኃጢአት ነበር፡፡
ወዳጄ ሆይ! ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን ራስ ላይ እሾኽ እንዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም፡፡ ሆኖም አንተም እሾኽ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሠራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ፡፡ በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን ራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው፡፡ ስለ መተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል፡፡
እየዘበቱ በፊቱ ከሰገዱ በኋላ ማታ ሲደርስበት እንደነበረው ዓይነት በተመሳሳይ ንቀት በፊቱ ላይ ተፉበት፡፡ በአዳም ፊት ላይ የሕይወትን መንፈስ እፍ ባለው አምላክ በፊቱ ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፡፡96
በመትፋት ብቻ አላበቁም ፤ በእጁ ያስያዙትን መቃ ተቀብለው በደረቀው እንጨት ራሱን መቱት፡፡ የእሾኽ አክሊል የተደፋበትን ራሱን መቱት ማለት እሾኹን ወደ ራሱ እንደ ሚስማር እየመቱ እንዲገባ አደረጉ ማለት መሆኑንና ምን ያህል ሥቃይ እንደሚያስከትል እናስተውል፡፡ የሕይወትን ራስ ፣ የማዕዘንን ራስ ፣ የቤተ ክርስቲያንን ራስ ፣ ለአለቅነትና ለሥልጣን ሁሉ ራስ የሆነ የክርስቶስን ራሱን መቱት፡፡
‹‹የከበረ ራሱን በመቃ በመቱት ጊዜ መላእክት ተንቀጠቀጡ! ጌታችን ከኃጢአተኞች ምን ያህል ድፍረትና ንቀትን ተቀበለ? አላዋቂው የሰው ልጅስ በጌታ ፊት ላይ እንዴት ሊተፋበት ደፈረ? ይህ ሁሉ የሆነው ስለ ኃጢአቱ ሊተፋበት ይገባው በነበረው በሰው ልጅ ፈንታ ነው›› ይላል ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 27 2016 ዓ.ም.
ከሕማማት ገጾች የተቆረሰ

❤38👍24😭17🙏10❤🔥2
#ሩፋኤል_ይቅር_በለኝ
አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ
ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ
ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ
ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 3 2012 ዓ ም
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ
ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ
ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ
ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 3 2012 ዓ ም
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
Telegram
ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
Henok Haile
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
👍78😢51❤43🙏16🥰3
+ አምናለሁ እና አላምንም +
ልጁ የታመመበት አባት ነው:: ጌታን "ቢቻልህስ ልጄን ፈውስልኝ" አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው፡፡
ይህን ጊዜ ሰውዬው “ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው፡ አለ" ማር, 9:24
የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል "አምናለሁ አለማመኔን እርዳው
ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም?
ያምናል እንዳንል "አለማመኔን" ይላል ፤ አያምንም እንዳንል "አምናለሁ" ይላል:: የቸገረ ነገር ነው? ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን ''አምናለሁ አለማመኔን እርዳው" የሚለውን ቃል እየደጋገምኩት ቀረሁ::
እያመኑ አለማመን እንዴት ያለ ነው? ብዬ መላልሼ ሳጤነው ግን ሰውዬው የእኔኑ ድክመት እየተናገረ እንደሆነ ገባኝ::
አምናለሁ እላለሁ:: በእርግጥም በፈጣሪ መኖር አምናለሁ:: ሁሉን እንደሚችልም አምናለሁ::
ግን ደግሞ በእርሱ ታምኜ አላውቅምና በሥራዬ እክደዋለሁ:: ኑሮዬ "በሥራቸው ይክዱታል" ከተባሉት የሚመደብ ነው:: (ቲቶ 1:16) አቅዋሜ የማመን ኑሮዬ ያለማመን ነውና አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ብል ለእኔ የሚገባ ጸሎት ነው::
ወረደ ተወለደ ተጠመቀ ተሰቀለ ሞተ ተነሣ ዐረገ ብዬ አምናለሁ:: በትሕትና መውረድን ፣ በንስሓ መወለድን ፣ በታናሽ እጅ ዝቅ ብሎ ጽድቅን መፈጸምን ፣ መከራን በትዕግሥት መቀበልን ፣ ከመከራ ሞት ወዲያ ተነሥቶ በክብር ከፍ ማለትን ግን እኔ ሕይወት ላይ አላውቀውም:: የምተርከው ክርስቶስ እንጂ የሚተረክ ክርስትና የለኝም:: ስለዚህ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው በልኬ የተሰፋ ጸሎት ነው::
መች በዚህ ያበቃል::
እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው::
@diyakonhenokhaile
ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢአት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳው:: ከምግብ እጾማለሁ ከኃጢአት ግን አልጾምም:: ሥጋ መብላት ትቼ የሰው ሥጋ በሐሜት የምበላ ነኝና እጾማለሁ አለመጾሜን እርዳሁ እላለሁ::
እጸልያለሁ አለመጸለዬን:: ቆሜ የማደርሰው ጸሎትስ አለኝ:: ግን ልቤ ሠላሳ ቦታ ደርሶ ይመለሳል:: የምጸልየው ማናገር የማልፈልገውን ሰው በግድ የማናግር ያህል የግብር ይውጣ እንጂ ነፍሴ እርሱን ሽታ አይደለምና እጸልያለሁ አለመጸለዬን እርዳው እላለሁ::
እሰግዳለሁ አለመስገዴን እርዳውስ? ላቤ እስኪወርድ ሰግጄ አውቃለሁ:: ልቤ ግን አንዴ አልሰገደም::
ጌታ ሆይ እመጸውታለሁ አለመመጽወቴን እርዳው:: እዘምራለሁ አለመዘመሬን እርዳው:: አስቀድሳለሁ አለማስቀደሴን እርዳው:: እማራለሁ አለመማሬን እርዳው:: ሆኜ ያልሆንሁትን አድርጌ ያላደርግሁትን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና እርዳኝ::
▫️@diyakonhenokhaile
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጳጉሜን 3 2015 ዓ.ም

❤147👍61🙏22🥰17😢10🤩2😍2