Telegram Web Link
"በኮከብ ተመርተው ሕፃኑን ከእናቱ ጋር አዩት"

"ጌታ ሆይ ለእኔ የሚሆን አንድ ኮከብ አጥተህ ይሆን? ወደ አንተ የሚመልሰኝ በልቤ እንድሰግድልህ የሚያደርገኝ ኮከብ ለእኔ ለምን አትልክም? ቁጥር ከሌላቸው ከዋክብት አንዱን ለእኔ ብታዝዝ ምናለ?" ብዬ ልጸልይ ጀመርሁና መልሼ ሳስበው አላይ ብዬ እንጂ ብዙ ከዋክብት ወደ እግዚአብሔር ሊመሩኝ እንደሞከሩ ትዝ አለኝ::

ወዳጄ ሆይ ወደ ጌታ የማይመሩህን ኮከቦች ስታይ እንደ እኔ ጊዜህን አታጥፋ:: ሰብአ ሰገልን የሚያንከራትት ወደ ጌታ ይመራናል ብለህ ስትጠብቀው ዓለምን እያዞረ የሚያስጎበኝ ስንት ደንባራ ኮከብ አለ መሰለህ!

ጌታን የሚያሳይ ኮከብ ታዲያ የቱ ነው? ካልከኝ "ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ" ተብሎ የተነገረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዳን. 12:3) የአጥቢያ ኮከብ የተባሉ መላእክቱ ፣ ለጨለማው ዓለምብርሃን ሆነው መንገድ የሚያመለክቱ ኮከብ ብሩሕ የተባሉ ብሩሃን ከዋክብት እነቅዱስ ጊዮርጊስ ናቸው:: በከዋክብት የተመሩ ሰብዓ ሰገል ጌታን እንዳገኙት የእግዚአብሔር ቅዱሳን ወደ እርሱ ያደርሱናል::

" ወደ ማርያም ከመጡት፥ ኢየሱስም ያደረገውን ካዩት ከአይሁድ ብዙዎች በርሱ አመኑ  " .ዮሐ 11:45

@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
259👍41🙏27🥰24👏12
የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ (ርእስ)

የአእላፋት ዝማሬን ዕውን ለማድረግ ላለፉት ሦስት ወራት እንቅልፍ ያጡ ፣ የታመሙ ፣ ልባቸው በስድብና በሽሙጥ ንግግር የቆሰለ ፣ በረዣዥም ስብሰባዎችና የጉልበት ሥራዎች የዛሉ ፣ ዝግጅቱን በዚህ ደረጃ ከፍ እንዲል ሰዎችን አሳምኖ ገንዘብ በማሰባሰብ የተንከራተቱ ፣ መዝሙር ለማስቀረጽ ሥራ ትተው በስቱድዮ የዋሉ ፣ ሦስት ጊዜ revise የተደረገውን Stage design የሠሩ ፣ በመሐረነ አብ ጸሎት በየአድባራቱ ደጅ የጠኑ ፣ ተነግሮ የማያልቅ ድካም የደከሙ ትሑታንና ታዛዦች የሆኑ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የቦርድና የሥራ አስፈጻሚ አባላት ፣ የጃን ያሬድ ኅብረ ዝማሬ መዘምራን ፣ የጃን አጋፋሪ event organizing ቡድንና በሥሩ የተቋቋሙ 15 ቡድኖች ፣ የጃን አግናጥዮስ የሕፃናትና አዳጊዎች project አባላት ፣ የጃን እስጢፋኖስ ዲያቆናት ፣ የጃንደረባው ሚድያ እሳት የላሱ የካሜራና ኤዲቲንግ የግራፊክስ ባለሙያዎችና የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ ወጣቶች የአእላፋት ዝማሬን እውን ለማድረግ የከፈሉት መሥዋዕትነት እጅግ ብዙ ነው::

ለዚህ አገልግሎት ምስጋና የሚገባው ዕንባና ተማጽኖአችንን ያልናቀ ልዑል እግዚአብሔር ነው::

ዓለም ዘመኑ ጥሩ አይደለም ብላ ስካሩን ጭፈራውን ፈንጠዝያውን ግድያውን አላቆመችም:: እኛም ስብሐተ እግዚአብሔር የወቅቱን ሁኔታ እያየች የማታስታጉል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደመሆናችን ሲከፋን የምንተወው ደስ ሲለን የምንቀጥለው መዝሙር የለም ብለው ለጸሎተ ምሕላና ለአእላፋት ዝማሬ የተሠጡ ወጣቶች ብዙ ናቸው:: "አርምሞ ጽርዓት በሌለበት ምስጋና ሳናቋርጥ ዘወትር እናመሰግንሃለን:: ይኸውም ሊቃነ መላእክት የሚያመሰግኑህ ምስጋና ነው" (ጸሎተ ኪዳን)

ምግብ ቤት ገብተን ጥሩ ስንበላ አስተናጋጁን እናመሰግናለን:: ቲፕ እንሠጠዋለን:: ማዕድ ቤት ውስጥ እሳት የበላቸውን ሼፎችና ተባባሪ ሠራተኞች ግን አናያቸውም:: የአእላፋት ዝማሬንም በተመለከተ ሊመሰገን የሚገባው እንቅልፉን የሠዋ ብዙ ወጣት ከጀርባ አለና አስተናጋጁን ለቀቅ አድርጋችሁ ሼፎቹ ላይ አተኩሩ:: ከዚያ ውጪ ግን ከታመነበት ተአምር መሥራት የሚችለውን ቅን 1/21ኛውን ጃን ያሬድ ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በጸሎት በገንዘብ በሃሳብ ደግፉ::

@janderebaw_media

@diyakonhenokhaile
302👍57🙏47👏19😍14
374👍41🙏32🔥18❤‍🔥15🥰11💯7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም ለኪ ለኖኅ ሐመሩ

#share

@diyakonhenokhaile
445👍68🥰52🙏46❤‍🔥24💯17👏13🎉7
አንዳንድ ሰዎች 'እግዚአብሔር ሰይጣንን ባይፈጥረው ኖሮ እኮ

ይኼ ሁሉ ችግር አይፈጠርም ነበር' ብለው በራሳቸው ድምዳሜ ይተክዛሉ፡፡ ሰይጣንን የፈጠረው ግን እግዚአብሔር አይደለም፡፡

'ሆይ ጉድ ታዲያ ማን ፈጠረው ልትል ነው?' ካልከኝ ሰይጣንን የፈጠረውማ ራሱ ሰይጣን ነው፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረው ሰማልያል ወይም ሳጥናኤል የተባለ እጅግ የተዋበ ሊጋርድ የተቀባ ኪሩብ ፣ ብሩህ መልእክተኛ የአጥቢያ ኮከብ የሆነ መልአክን ነበር፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረው በዔድን ገነት የነበረ ፣ የከበረ ዕንቊ ልብሱ የሆነለት ፣ በእግዚአብሔር ተራራ የሚኖር አለቃን ነበረ፡፡

'ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ' ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር የፈጠረው እጅግ የተዋበ በቅድስና የተሸለመ መልአክን እንጂ ሰይጣንን አልነበረም፡፡ ሕዝ. ፳፰፥፲፭

(የብርሃን እናት ገጽ 47)

የብርሃን እናት 9ኛ ዕትም አሁን በገበያ ላይ ነው::

▫️@diyakonhenokhaile

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
301👍92👏13❤‍🔥9
187👍30😍13🥰12😢12
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ?

ሔዋን ከእባብ ጋር ተነጋገረች የሚለውን አምነህ አቡነ አረጋዊ በእባብ ተራራ ወጡ ሲባል ከቀለድህ ፣ ኤልያስን ቁራ መገበው ሲባል ተቀብለህ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቁራውን መገቡት ሲባል ከዘበትህ ፣ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር አደረ ሲባል አምነህ አቡዬ አንበሶች ጋር ነበሩ ሲባል ካጣጣልክ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀበት ቀን ለአንተ የዓለም ፍጻሜ መስሎሃል ማለት ነው::

አንድ አባት 'ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?' ተብለው ሲጠየቁ 'የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ' ብለዋል፡፡ 'አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው' ካልከኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሞአል ማለት ነው? 'እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ' ሲል አብረን አልሰማነውም? (ማቴ. 28፡19)


@diyakonhenokhaile
200👍59🙏17👏15🥰5🎉4
"ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፥ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ" መሣ. 14:14

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
156👍45🥰14🙏8
"ክርስቲያን ልትሆን ብትወድ አንዳንዴ እንደ ጣዖታት አንዳንዴ እንደ ኪሩቤል ሁን::
ለክፉ ነገር ሲሆን "ዓይን እያላቸው የማያዩ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ" ጣዖታትን ምሰል:: ለመልካም ነገር ግን "ዓይኖቻቸው ብዙ የሆኑ ኪሩቤልን ምሰል" ቅዱስ አባ ሲሶይ

▫️@diyakonhenokhaile

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
228🙏51👍45🥰10💯9
ክርስቶስን ያመንነው ለምድራዊ ነገር ብቻ ከሆነ ምስኪኖች ነን:: ሌላ ዓለም ባይኖርም ለክርስቶስ ብሎ መከራን መታገሥ ሞኝነት በሆነ ነበር::

ቆላስይስ 3:2፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም፡፡ (በሰማይ የሃሉ ልብክሙ - ልባችሁ በሰማይ ይሁን)

እወ የሃሉ በሰማይ ልብነ በእንተ ስምከ አጽንዓነ ወረስየነ ድልዋነ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ ወአምላክነ

አዎን ልባችን በሰማይ ይሁን! ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ስምህ አጽናን ልባችን በሰማይ እንዲሆን የተገባን አድርገን

▫️@diyakonhenokhaile

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
129👍27🥰13🙏13👏8😍3
ከዐሠርቱ ትእዛዛት ውስጥ የሚገርመኝ እውነታ ሁሉም ትእዛዝ የተነገሩት በነጠላ ለአንድ ሰው መሆኑ ነው፡፡ 'አድርግ አድርግ ፣ አታድርግ አታድርግ'! ሙሴ ዓሠርቱን ትእዛዛት ይዞ የወረደው በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩት ለእስራኤላውያን ቢሆንም ትእዛዛቱ ግን አታምልኩ ፣ አትስረቁ ፣ በሐሰት አትማሉ ወዘተ የሚል አልነበረም፡፡ ዐሥሩም በነጠላ አድርግና አታድርግ በሚሉ ትእዛዝና ሕግ የተሞሉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለው ሃሳብ እንዲህ ነው፡፡

መስረቅ ሲያምርህ 'ሀገሩ ሁሉ እየሰረቀ ነው እኔ ብቻዬን ምን ለውጥ አመጣለሁ? ጊዜው የሌብነት ነው!' ብለህ አትጽናና፡፡ እግዚአብሔር 'አትስረቅ' እንጂ አትስረቁ አላለም፡፡ ሀገሩ ሁሉ ይስረቅ አንተ ግን 'አትስረቅ' የታዘዝከው ለብቻህ ነው ፤ የሚጠይቅህም ለብቻህ ነው፡፡ ማመንዘር በእኔ አልተጀመረ የማያመነዝር ማን አለ? ብለህ ለኃጢአትህ ማኅበርተኞች አታፈላልግ፡፡ 'አታመንዝር' ያለው ለአንተ ለብቻህ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር ያለውም ላንተ ነው፡፡ 'የሥራው ጸባይ ነው፡፡ ሥራዬ መዋሸት ይጠይቃል' ብለህ ሐሰትህን የኑሮ መግፊያ ስልት አታድርገው፡፡ ብዙዎች በሐሰት ቢመሰክሩ አንተ ግን አትመስክር፡፡ ሁሉም መስክሮ እኔ ብቀር ምን ለውጥ ያመጣል? ብለህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ 'ብዙ ናቸው ብለህ ከክፉዎች ጋር አትተባበር' ፈጣሪህ ያዘዘህ ለብቻህ ነው፡፡ የጋራ ኩነኔና የጋራ ጽድቅ የለም፡፡

ጌታ እንዲህ ይላል ፦

'እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ' ራእ. 22፡12

▫️@diyakonhenokhaile

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
228👍83🙏17👏15🥰9
ፈርዖን ሕፃናትን አስገድሎ በጣለበት የባሕር ውኃ ሰምጦ ሞተ::

ጎልያድም ብዙዎችን በገደለበት በገዛ ሰይፉ ተቀላ::

ያዕቆብ ኤሳውን ባታለለበት የበግ ደም በልጆቹ ተታለለ::

ሐማም መርዶክዮስን ለማስገደል ባስቆመው እንጨት ራሱ ተሰቀለበት::

በሌላው ላይ የሚደረግ ክፋትና ወጥመድ ተመልሶ እንዲመጣ ሰማይ ቤትን አይጠብቅም:: እግዚአብሔር በምድር ለሚሠራ ግፍ በምድርም ይመልሳል:: ለዚህም ነው "ለሌላው ሰው የምትቆፍረውን ጉድጓድ ብዙ አርቀህ አትቆፍረው አንተም ልትገባበት ትችላለህና" የሚባለው::

"ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና "
ገላ 6:7

▫️@diyakonhenokhaile

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
228👍82🥰19🙏6👏5😭3
ዛሬ ወደ ግዮን ሆቴል ጎራ ብዬ ሐመረ ብርሃን ያዘጋጀውን ዐውደ ርእይ ተመልክቼ ነበር:: በእርግጥ ልጆቹ የአዋቂ ሥራ መሥራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል:: እንዲህ እንዳመረሩ ግን ያየሁት አሁን ነው:: ዐውደ ርእዩ ሳይዘጋ ብትሔዱና ብትጎበኙ ብዙ ታተርፋላችሁ:: የብራና ጽሑፍና ሥዕል የአንጥረኞች ጥበብ የድጉሰት ውበት ሁሉንም ታያላችሁ:: በብራና ላይ የመጻፍ ዕድልም ጭምር ይገጥማችኋል:: ካለፈ የሚቆጭ ይህንን እድል ተረባርበው ይጠቀሙ::

▫️@diyakonhenokhaile

https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
206👍63🥰13🙏2
የማይገባው ተሸላሚ

ቄሱ ሲናዝዙ "ኩኑ ፍቱሐነ ወንጹሐነ ይረስየኒ ወይሬሲክሙ ድልዋነ ለመንግሥተ ሰማያት" "የተፈታችሁ ንጹሐን ሁኑ እኔንም እናንተንም ለመንግሥተ ሰማያት የተገባን ያደርገን ዘንድ" ብለው ጣታችንን ዐሥራ ሁለት ጊዜ በእግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ሲያስቆጥሩን ለወትሮ ያላሰብሁት ነገር ታሰበኝ::

"እኔንም እናንተንም ለመንግሥተ ሰማያት የተገባን ያደርገን ዘንድ" የሚለው ቃል!

መንግሥተ ሰማያትን መውረስ መቼም ከእኛ መካከል የማይፈልግ ሰው የለም:: ለመንግሥተ ሰማያት ግን የተገባን ነን ወይ?

እውነት አሁን ጌታ ቢመጣና ሁሉንም በደላችንን ትቶ ሁላችንንም በቀኙ

አቁሞ መንግሥቴን ውረሱ ቢለንና ወደ መንግሥቱ ብንገባስ? ለመንግሥተ ሰማያት የሚሆን ማንነት አለን ይሆን? ከእኛ መካከል ለመንግሥተ ሰማያት የተገባ ማን ነው?

ጌታ ሆይ እንኳን ለመንግሥትህ በምድር ላለችው ቤትህ የሚገባ ማንነት እንደሌለኝ ሳስብ "መንግሥትህ ትምጣ" ማለት አስፈራኝ::

"በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው" በተባለላት ቤትህ እንኩዋን እንደሚገባኝ መመላለስ ላልቻልሁት ለእኔ መንግሥትህን እንዴት ልመኝ? 1 ጢሞ. 3:15

" አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?” ብሎ ዳዊት ቢጠይቅ የመለህለት ውስጥ ራሴን አጣሁት:: መዝ. 15:1 ስለዚህ ለመንግሥትህ የሚሆን ማንነት ማጣቴ አሳፈረኝ::

የሰርግ ልብስ ሳልለብስ ወደ ሰርግ ቤትህ የገባሁ ብሆንስ? በመላእክት ማኅበር መካከል ዕርቃኔን ብቆምስ? እውነት የኔን ጠባይ ወደ መንግሥትህ ይዤው ልገባ ይቻል ይሆን? በመንግሥትህ ለእኔ ዓይነቱ ሰው የሚሆን ቦታ አለህ ይሆን? እርግጥ ነው በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ብለሃል:: ለእኔ ዓይነቱ ቁስለኛ የሚሆን ቤትስ ይኖርህ ይሆን? ግዴለም ከደጁም ቢሆን አስገባኝ::

ያስተማሩ የሐዋርያት ማኅበር ፣ ድል የነሡ ሰማዕታት ማኅበር ፣ ቡሩካን የሆኑ የጻድቃን ማኅበር በዚያ እንዳለ አውቃለሁ:: ወደ መንግሥትህ ብገባ የእኔ ምድብ ወዴት ይሆን? ይቅር የተባሉ ሰዎች ማኅበር የለህ ይሆን? ምሕረትህ የበዛላቸው ሰዎች ማኅበር ፣ እንደ ቸርነትህ ብዛት የተማሩ ፣ እንደ ይቅርታህ ብዛት መተላለፋቸው የተደመሰሰላቸው ሰዎች ማኅበር የለህ ይሆን? ክርስቲያን ተብዬ ልጠራ ያልተገባኝ እኔን በቸርነትህ ለመንግሥትህ ዜግነት የተገባሁ አድርገኝ::

#share

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 2016 ዓ.ም.

@diyakonhenokhaile
👍228143🙏74😭58❤‍🔥9😍6🥰5
2025/07/13 14:19:59
Back to Top
HTML Embed Code: