Telegram Web Link
በአንቺ ዘንድ ያለው ደስታ ከኤልሳቤጥ ደስታ የሚበልጥ ሲሆን የምሥራቹን ሳትንቂ ደስታዋን ልትካፈይ ወደ እርስዋ የገሰገስሽው እመቤታችን ሆይ አንቺ የደረሰብሽ ኀዘን ከኀዘናችን እጅግ ቢበልጥም ፣

አንቺ ያሳለፍሽው ስደት ከስደታችን እጅግ ቢልቅም ፣ ዐርብ ዕለት ያለቀስሽው ልቅሶሽ ከልቅሶአችን ብዙ እጥፍ ቢሆንም የምናዝነውና መከራን የምንታገሠው በአቅማችን ነውና ኀዘናችንን ለመካፈል ወደ እኛም ከመምጣት እንዳትቀሪ፡፡

እርግጥ ነው እኛ እንደ ኤልሳቤጥ ለአንቺ የሚሰግድ ፅንስ በሆዳችን የለም፡፡ በእኛ ዘንድ የተፀነሰው 'ለፀነሱ ወዮላቸው' 'ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች' ተብሎ የተነገረለት የኃጢአት ፅንስ ነው፡፡ እንደ ኤልሳቤጥ በደስታ የሚያስጮኸን ሳይሆን በኀዘን የሚውጠን የበደል ፅንስ ይዘናልና ድንግል ሆይ እኛን ለመርዳት ፍጠኚ፡፡ በሆዳችን የያዝነውን የኃጢአት ፅንስ ነቢዩ ዳዊት እንደተመኘው በሆድሽ ውስጥ በያዝሽው ዓለት ላይ እስክንፈጠፍጠውና ዕረፍት እስክናገኝ ድረስ ጓጉተናልና ወደ ኤልሳቤጥ እንደመጣሽ ወደ እኛም ነዪ፡፡

በተራራማው ሀገር በአስቸጋሪ መንገድ ወደ ኤልሳቤጥ የገሰገስሽው እመቤታችን ሆይ ወደ እኛ ነይ ስንልሽም መንገዱ እንደማይመችሽ እናውቃለን፡፡ 'ተራራው ዝቅ ይበል' ተብሎ የተነገረለት ተራራማው ልባችን በትዕቢት ተራሮች ስለተሞላ ከይሁዳ ተራሮች በላይ ወደ እኛ መምጣት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሉቃ. ፫፥፫ ድንጋይ ብቻ የሆነው ጭንጫው ልባችን ለመንገደኛ የማይመች እንደሆነ እናውቃለን፡፡

የኃጢአት ወኃ ገብ የሆነው ሕሊናችንም አቋርጠሽ ለመምጣት የሚያስቸግር የበደል ጭቃ የሚበዛው መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሆኖም ወደ ተራራ ልባችን ፣ ወደ ጭቃው ሕይወታችን እንድትመጪ እንሻለንና ከአባቶቻችን ጋር 'ንዒ ኀቤየ' 'ንዒ ርግብየ' ከእናቶቻችን ጋር 'ነይ ነይ እምዬ ማርያም' ማለትን አናቆምም፡፡

ልባችን ምንስ ዓይነት ተራራ ቢሆን ላንቺ ምንሽ ነው? 'ይህን ተራራ ወደዚያ ሒድ' የምትይበት የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት 'ካመንሽው ብፅዕት' ዘንድ ይጠፋልን?

እንደ ዘሩባቤል 'ታላቁ ተራራ ሆይ አንተ ምንድርን ነህ? በማርያም ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ' የምትዪበት የልዑል ኃይል በሆድሽ አይደለምን? ሕይወታችን ምንም

እንኳን ቢጨቀይም አንቺ እንደሆንሽ ከነ ልጅሽ በሚሸት በረት ውስጥ እንኳን ለመምጣት አልተጸየፍሽም:: ሕይወታችን እንደ እንስሳ ቢሆንብሽ እንኳን ልጅሽን ከእንስሳት መካከል ለማስተኛት ፈቃድሽ አልነበረምን? ወደ እኛ መምጣትሸን ተስፋ እያደረግን ቅዱሳኑ ሁሉ 'ወደ እኔ ነይ' 'ወደ እኛ ነይ' ብለው የደረሱልሽን ዜማ እያደረስን መምጣትሽን እንጠባበቃለን፡፡
🙏🙏

▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
235👍47🙏35🤩6👏3🥰2
65👏7👍6🙏6🎉1
"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው" ዕብ.

13:7

A blessed meeting With His Grace Abune Fanuel, Archbishop of Washington DC Diocese. A great reunion With My beloved Spritual Father and Mentor Kesis Hibret Yeshitla, With Our Mezmur Legend, Liqë Mezemiran Yilma Hailu, With the pioneer of dogmatic books Melake

Ariyam Birhanu Gobena

#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
190👍41🙏26🥰12👏9🔥2
2025/07/10 01:49:00
Back to Top
HTML Embed Code: