ይህንን ታሪክ የጻፍኩት 2012 ላይ ነበር:: ይህንን ታሪክ አንብበው በግንቦት ልደታ ዕለት ተስለው የወለዱ እናቶች በየዓመቱ ይጽፉልኛል:: አንዳንዶቹም ሳገኛቸው ይነግሩኛል:: ዓለምን በእጁ የያዘውን ጌታ በእቅፍዋ የያዘች እመብርሃን የወላጆችዋን የመካንነት ሕመም ለሚታመሙ ሁሉ በአማላጅነትዋ “ልጅ እኮ የላቸውም” ብላ ለምና ብዙ ውኃ ቤቶችን በልጅ ወይን ሞልታለች:: “ይሁንልኝ” ብላ አምላክን በእርስዋ እንዲያድርግ ነፃ ፈቃድዋን ለሰጠች ድንግል “ይሁንላቸው” ብላ በጸሎትዋ በመካኖች ማሕፀን ልጅ ማሳደር ከተሞላችው ጸጋ አንጻር ጥቂት ነገር ነው::

ይህንን የግንቦት ልደታ ተአምር በእኔ ብዕር ሲመሰከር ቆይቶ እንዳልነበር ጊዜው ደርሶ ባለ ታሪክዋ ነፃነት የእናቲቱን ምልጃ የልጅዋን ቸርነት በራስዋ አንደበት እንዲህ መስክራለች::

ፍቅርን እንደ ሸማ የለበሱት የቩርዝቡርግ ምእመናን አሁን የቅዱስ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ለመግዛት ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም እየታገሉ ነው:: መላው ዓለም ተረባርቦ ካገዛቸው በቅርቡ እውን ያደርጉታል:: በቩርዝቡርግ ግን ግንቦት ልደታ ከዝክር አልፎ ንግሥ እንደሚሆንና የልደታ ለማርያም ክብረ በዓል እንደሚከበርና መላው አውሮፓ ለግንቦት ልደታ ወደ ቩርዝቡርግ እንደሚጎርፍ ተስፋ አደርጋለሁ::

Meine lieben Brüder und Schwestern in Würzburg, ich wünsche Ihnen ein gesegnetes Fest der Geburt Mariens. Ich hoffe, Sie bald wiederzusehen. Möge Gott Ihnen helfen, das Kirchenbauprojekt abzuschließen.
https://youtu.be/HkXps7PbIKM?si=MS1y88vOuyNxhdlL
ሙሉ ቃለ መጠይቁን እንድትሰሙት እጋብዛለሁ::
"ሱሪዬን የበቃው ሰው ይለብሰዋል ብለህ አትጨነቅ" የሚል ብሂል አለ:: አንዳንዴ ከሁኔታዎች በላይ የእኛ ሕሊና የሚፈጥረው ምስል የከፋ ነው:: ከምጡ በላይ ምጡን እያሰብን የምናምጠው ምጥ ይበረታል:: የማታውን ጨለማ በመፍራት ብሩህ ቀናችንን እናጨልማለን::

"ጌታ ቅርብ ነው:: በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ፊልጵ. 4:6
Photography #mykeysjourney

#share
@diyakonhenokhaile
የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን - የቤተክርስቲያን ታሪክ | The History of The Church part 1

https://youtu.be/Y1lmGKLFMQQ?si=RKRU5ODk_CPB2JSv

#share
@diyakonhenokhaile
ግብፃውያን ጳጳሳት በኢትዮጵያ | Coptic Metropolitans in Ethiopia | Ethiopian Church History 2

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ1600 ዓመታት በእስክንድርያ መንበር ጥላ ሥር ትተዳደር ነበር:: በእነዚያ ዓመታት የመጡት ግብፃውያን ጳጳሳት ቆይታ ምን ይመስል እንደነበር በዚህ ትምህርት በሰፊው ተዳስሶአል::

https://youtu.be/MZml82waOp4?si=vKkQZt006yBBqZcd

#share
@diyakonhenokhaile
+ ሁለት ነበርን +

ገነት ውስጥ ሆነን ስናምፅ ባንተ ላይ
ያንተን መንግሥት ሽተን ዙፋንህን ስናይ
ዕፀ በለስ በልተን ካንተ ስንጣላ
ሁለት ነበርን እንጂ አልነበረም ሌላ

ሁለት የአፈር ሥራ ሁለት ወንጀለኛ
ዘር ልተካ ሳይል ሳይበዛ አመፀኛ
እዚያው ብትመልሰው ከመጣበት አፈር
ማን ይጠይቅሃል ከፍቅርህ በስተቀር?

ሁለት ጆንያ አፈር መልሰህ ከመሬት
ሌላ ሰው ብትሠራ ሌላ አዲስ ፍጥረት
የማያምፅ አዳም ታዛዥዋን ሔዋኒት
ደግመህ ብትፈጥር ላንተ ምን አለበት?

ሸክላህን አክብረህ ሲሰበር ያልጣልከው ሲያምጽብህ አይተህ በአየር ያልበተንከው
ከቶ ለምን ይሆን ዘሩን ያበዛኸው
እስኪገርፍህ ድረስ ጉልበት የሰጠኸው

ጠላትክን መግበህ እንዲህ የወዷድከው
ምድርን ሙላ ብለህ በሁሉ ያነገስከው
ምራቁን የተፋው በአንተ ላይ ጨክኖ
ማጥፋት ስትችል ነው ገና ሁለት ሆኖ

ማን ነበር ከልካይህ ፈጥረህ እንዳታጠፋ ምሕረትህ ነው እንጂ በዓለም የሰፋ
ቸርነትህ እንጂ ምድሪቱን የሞላ
አንተን የሚያስቆም ከቶ የለም ሌላ

“ሔት፡፡ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና" ሰቆ ኤር. 3:22

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 23 2017 ዓ.ም.
#share
@diyakonhenokhaile
በቀይ አበቦች መስክ ላይ መመላለስ እንዴት መንፈስን ያድሳል? እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የእናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጉልበት ስመው ሲሞሸሩ ማየት እንዴት ደስ ያሰኛል? ሰማንያ ስምንት ወጣቶች በሥጋ ወደሙ ከብረው በመላእክት ታጅበው በዝማሬ ባሕር ሲዋኙ ማየት እንደምን ያለ ደስታ ነው? ከእነዚህ አርባ አራት ሙሽሮች የሚወለደውን አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ማየትስ እንዴት ያጓጓል? ልጆቻችን በእናንተ መታዘዝ ኮርተናል:: ሰይጣን የሚዋጋውን የቤተሰብ ቤተ መቅደስ ስትገነቡ የዓይን ምስክሮች ስለሆንን ደስ ይለናል:: እልፍ ሁኑ! እናንተን ለመዳር ወገባቸውን የታጠቁ እጅግ የሚወዷችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ወጣቶች ሁሉ የእናንተን ደስታ አይተው ነፍስ አልቀረላቸውም! ትዳራችሁን እንደ ሰርጋችሁ ያማረ ያድርግልን!
#share
@diyakonhenokhaile
በስዊዘርላንድ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመቄዶንያ ለሚገኙ 8500 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሺህ ብር በመሥጠት ሥጦታዋን ስምንት ሚልዮን አምስት መቶ ሺህ አደረሰች:: ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም የድሆች መጠጊያ መሆንዋን ባስመሰከረችበት በዚህ የመቄዶንያ የእርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ ላይወንጌልን በፅንሰ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር አሳይታለች:: “እናንተ የሚበሉትን ሥጧቸው እንጂ ሊሔዱ አያስፈልግም” ብሎ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረውን ቃል የማትረሳዋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ልጆችዋን እጅ እጅ አድርጋ የመቄዶንያን አረጋውያን ጎብኝታለች:: መቄዶንያ 8500 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማንን አቅፎ የያዘና በፍጥነት ወደ ጤናቸው መመለስ የቻሉትን እዚያው ወደ ሥራ እያሠማራ የሚገኝ ውድ ተቅዋም ነው::

ከወራት በፊት በመቄዶንያ አምባሳደር ሆኜ በተሰየምኩበት ወቅት በመቄዶንያ 7000 አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን የነበሩ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ የነበረው የመቄዶንያ ቅርጫፍም 44 ነበረ:: አሁን ያሉት የመቄዶንያ ሕሙማንና አረጋውያን 1500 ጨምረው 8500 ሲሆኑ የቅርጫፎቹም ቁጥር 46 ደርሶአል:: እግዚአብሔርበገሐድ እየሠራ ያለበት ይህን ቅዱስ ሥፍራ እባካችሁ መጥታችሁ ጎብኙ::

በዚሁ አጋጣሚ ሙሉ ገቢው ለመቄዶንያ የሚውለውን ባዚልያድ የተሰኘ መጽሐፌን ለተቅዋሙ ማስረከቤ ይታወቃል:: መጽሐፉ አርትዖቱ እየተጠናቀቀ ስለሆነ ይህንን ሙሉ ትኩረቱን ነገረ ምጽዋት ላይ ያደረገ መጽሐፍ ለማሳተም በኅትመቱ ዘርፍ ያላችሁ ወገኖቻችን እንድታነጋግሩን ጥሪ እናቀርባለን::

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የመቄዶንያ ብራንድ አምባሳደር
ግንቦት 28 2017 ዓ.ም.
#share
@diyakonhenokhaile
2025/06/27 03:34:49
Back to Top
HTML Embed Code: