እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በአል አደረሳችሁ!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
❤45👍26🕊1
ባስልዮስ ሆይ! ንገረኝ...
በዚህ ዓለም የሥራ መስክ ገበሬ መርከብ ለመንዳት የማይነሣው፣ ወይም ወታደሩ የግብርናን ሥራ የማይሠራው፣ ወይም ሙያው መርከብ ነጂ የኾነ ሰው ጦር እንዲመራ እልፍ ጊዜ ቢጎተትም እንኳ እሺ የማይለው ለምንድን ነው? እያንዳንዱ ያለችሎታው ቢሰማራ የሚከተለውን አደጋ አስቀድሞ ስለሚያይ አይደለምን? ታዲያ ጥፋቱ ቁሳቁስና ንብረት በሚኾንበት ኹኔታ አስቀድመን ብዙ የምናስብና ግፊትና ግዴታን የማንቀበል ኾነን ሳለ፥ ክህነትን እንዴት እንደሚይዙትና እንደሚያገለግሉበት ለማያውቁ ቅጣቱ ዘለዓለማዊ በኾነበት ኹኔታ ግን ያለብዙ ማሰብና ማሰላሰል እንዲሁ በዘፈቀደ ወደዚህ ዓይነት ታላቅ አደጋ ውስጥ ዘለን እንገባለንን? የሌሎች ሰዎች ግፊትስ ምክንያት ሊኾነን ይችላልን? አንድ ቀን ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ በርትዕ የኾነው እግዚአብሔር ይጠይቀናል፡፡ ይህ ሰበብም አያድነንም፡፡ ከምድራዊ ነገሮች ይልቅ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ይበልጥ ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናልና፡፡ በትንንሽ ነገሮች ላይ ጠንቃቆች ስንኾን እንታያለንና፡፡ እስኪ ንገረኝ! አንድ ሰው የቤት ሥራ ሙያ ሳይኖረው ብትሠራልን ስንለው እሺ ብሎ ቢመጣና ከዚያ በኋላ ግን ዕንጨቱንና ድንጋዩን ቢያበላሽና የሠራው ነገር ወዲያውኑ ተበታትኖ ቢወድቅ በራሱ ፈልጎ አለመምጣቱና በሌሎች ግፊት ሥራውን መጀመሩ በቂ ምክንያት ሊኾነው ይችላልን? በጭራሽ! የሌሎችን ግፊትና ጥሪ አልቀበልም ማለት ነበረበትና በርግጥም ተጠያቂ ነው፡፡
ታዲያ እንዲህ ዕንጨትና ድንጋይ ለሚያበላሽ ሰው በጥፋቱ ከመጠየቅና ከመቀጣት ለመዳን ምንም ምክንያት ከሌለው፥ ነፍሳትን የሚያጠፋ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በግድየለሽነት የሚያንጽ ሰው’ማ እንዴት? የሌሎች ግፊትና ማስገደድ በቂ ምክንያት ይኾነኛል ብሎ ሊያስብ ይችላልን? እንዲህ ብሎ ማሰብስ ሞኝነት አይደለምን?
ፈቃደኛ ያልኾነን ሰው ማንም ሊያስገድደው እንደማይችል ለማሳየት ብዬ ሐተታ መስጠት አያስፈልገኝም፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት እንደ ተናገርኩት ይህ ፈቃደኛ ያልኾነ ሰው እጅግ ተጭነዉትና ግድ ብለዉት ሌሎች ብዙ መንገዶችንም ተጠቅመው ወደዚህ ኃላፊነት አመጡት እንበል፡፡ ታዲያ ይህ ከቅጣት ሊታደገው ይችላልን? እማልድሃለሁ፤ በፍጹም ራሳችንን አናታልል! ሕፃናት ሳይቀሩ በቀላሉ በሚያውቁት ነገር ላይ እንደማናውቅ ኾነን አናስመስል፡፡ እንደማናውቅ ማስመሰላችን በዚያች ዕለት ላይ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም አይጠቅመንምና፡፡
(በእንተ ክህነት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ 4፥2
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው)

👍27❤2
#ደብተራ_ማለት፦
(በመምህር ገብረ መድኅን)
1ኛ፦ ደብተራ 'ብርሃን' ማለት ነው፦ እግዚአብሔር በብርሃን ድንኳን ሊቀ ነቢያት ሙሴን በአምሳለ ንጉሥ ተገልጾ በብርሃን ድንኳን በሰባት የእሳት መጋረጃ 22ቱን ሥነ ፍጥረት በልቡናው ሥሎ ቃል በቃል 570 ጊዜ አነጋግሮታል፤ የደብተራ ልጅ ማለት የብርሃን ልጅ ማለት ነው። ወይም ሰማያዊ ወልደ ሰማያዊ ማለት ነው።
2ኛ፦ ደብተራ 'ኦሪት' ናት ባስልኤል ኤልያብን ያህል ጠበብት ሙሴን ያህል ነቢይ አሮንን ያህል ካህን አሥነስቶ ያሳነጻት ናት። ታቦተ ሕጉ ያለባት አምልኮቱ የሚመሠከርባት ሕጉ የሚነገርባት ድንኳን ደብተራ ኦሪት ትባላለች፤ የደብተራ ልጅ ማለት የሕግ ልጅ የመቅደስ አገልጋይ ማለት ነው። ሕገ ኦሪትን ያወቀ እንደሙሴ እንደ አሮን ያለ ማለት ነው።
3ኛ፦ ደብተራ 'ድንግል ማርያም' ናት በአምሳላዊት ድንኳን በረድኤት ይገለጽ የነበረው እግዚአብሔር በንጽሕና በቅድስና በታነጸች በአማናዊት ደብተራ በእመቤታችን ማህጸን በኩነት ተገልጿልና ደብተራ ትባላለች። የደብተራ ልጅ ማለትም የድንግል ማርያም የቃል ኪዳን ልጅ ማለት ነው። እንደ ጴጥሮስ እንደ ጳውሎስ መሆን ነዋ!
4ኛ፦ ደብተራ መስቀል መድኅነ ዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል መሠዊያ ነውና ደብተራ ተብሏል ሕያው ደመ መለኮት የነጠበበት ቅዱስ መስቀል የከበረ ደብተራ ነው፦ የደብተራ ልጅ ማለትም የመስቀል ልጅ ማለት ነው።ወይም መስቀለኛ መስቀላዊ ማለት ነው።
5ኛ፦ደብተራ ርዕሱ ድንኳን ይባላል በዘር በሩካቤ ያይደለ እንበለ ዘር እንበለ ሩካቤ የተወለደ የመድኅን አካሉ ደብተራ ተብሏል ሠዋዒ ተሠዋዒ ተወካፌ መሥዋዕት ነውና እንደ ብሉይ ሊቀ ካህናት ከአፍአ ወደውስጥ ደመ በግዕን ይዞ ለሥርኤት ወደ ደብተራ ኦሪት አልገባም ራሱን በደብተራ ርዕሱ አቀረበ እንጂ፦የደብተራ ልጅ ማለትም የክርስቶስ ልጅ ማለት ነው።በክርስቶስ የሚያምን የክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።
6ኛ፦ደብተራ ቤተ ክርስቲያን፦ ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡባት መቅደሰ ወንጌል ደብተራ ተብላለች አገልጋዮቿም ካህናተ ደብተራ ይባላሉ፤ የደብተራ ልጅ ማለትም የመቅደስ አገልጋይ ቅዳሴውን የሚቀድስ፣ ቅኔውን የሚቀኝ፣ ድጓውን የሚያዜም፣ ዝማሜውን የሚዘም ብራናውን የራመመ ቀለሙን የቀመመ ማለት ነው። የረቀቀ የተራቀቀ ምጡቅ መርጌታ ማለትኮ ነው!ከደብተራ ሙያ አንዱን ሳያውቁ መንቀፍ ወፍ ነዳሽ ጉም አፋሽ መሆን ነው።
ለደብተራነት መዐርግ መድረስ ጭንቅ ነው እንጂ ልጅ መሆንስ ቢሹትም አይገኝ።
ደብተራ እያሉ መተንኮስ በይፋ ክርስትናን እና ክርስቲያኖችን በመጥላት የሚደረግ ሥሁት ድንቁርና ነው። ጠንቋይን ለተከበረው ደብተራ መስጠት አይቻልም ጨለማ ከብርሃን ጋር ኅብረት የለውምና። የሀገር በቀል የዕውቀት ሀሳቦችን የደብተራ ዕውቀት ነው አንቀበልም አንሰማም ማለት ግን ኦርጂናል የጣሊያን አእምሮ ነው። ደብተራ ዶክተሮች ሳይኖሩ ዶክተር ነበር። በተውሶ ጭፍን ግልበጣ የተሠራ አእምሮ እውነትን ካልተጠላት የተማረ አይመስለውም ማለት ነው። ከውሸተኛ ተንኮለኛ ቁም ነገር አገኛለሁ ከማለት ዑቅያኖስ ሜዳ ሁኖ እህል ይዘራበታል ማለት ይቀላል። ወይም ሰሜን ተራራ ደልዳላ ሜዳ ይሆናል ማለት ይሻላል።
(በመምህር ገብረ መድኅን እንየው)

👍26❤6😢1
ብስራተ ገብርኤል (ታህሳስ 22)
“ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ”
ታህሳስ 22 በዛሬው ቀን ዓለም ለመዳን የቅድስት ድንግል ማርያምን ይሁንታን የፈለገበት ቀን ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከምንም በላይ የሰውን ነጻ ፈቃድ ስለሚያከብር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲልከው ፈቃዱዋን ይጠይቃት ዘንድ ነበር፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት መሰላችሁ “እነሆ በደጅህ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል” (ራእ.3፡20) እንዳለው ዓይነት ነው፡፡ ነገር ግን በይዘቱ የቅድስት እናታችን ይሁንታ በጣም የተለየ ነው፡፡ ስለዚህም የዓለም መዳን በእርሱዋ ይሁንታ ላይ ነውና እግዚአብሔር በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በኩል የቅድስት ድንግል ማርያምን ፈቃድ ጠየቀ፡፡
ለእርሱዋም በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አንደበት እግዚአብሔር ቃል ለሰው ልጆች መዳን ከእርሱዋ ተፀንሶ ለመወለድ ፈቃዱ እንደሆነ፣ እርሱዋንም የዘለዓለም እናቱና የሰው ልጆችን ፍጹም የመውደዱ ምልክት ሊያደርጋት እንደወደደ አበሰራት፡፡ ቅድስት እናታችንም ፍጹም ትወደውና ታመልከው የነበረው እግዚአብሔር ከእርሱዋ ተወልዶ ዓለምን ለማዳን መፍቀዱን ስትሰማ በፍጹም ደስታ ተሞልታ ግሩም በሆነ ትሕትና “ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ”(እንደቃልህ ይደረግልኝ) በማለት ዓለምን እፎይ አሰኘቻት፡፡ እስከዛች ጊዜ ድረስ ዓለም በጭንቀት ተውጣ የእርሱዋን መልስ በጉጉት ትጠባበቅ ነበርና፡፡
የቅድስት እናታችን የይሁንታ ቃል በተሰማ ጊዜ በሲኦል ያሉ ቅዱሳት ነፍሳት በደስታ ቦረቁ፡፡ በአካለ ሥጋ የነበሩ ነቢያትና ቅዱሳን እንደ እምቦሳ በደስታ ዘለሉ፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልም በደስታ ተውጦ ለመላእክት ጉባኤ “በቅድስት ድንግል ማርያም የይሁንታ ቃል ምክንያት ዓለም ዳነች” ብሎ የምስራች አላቸው፡፡
ነቢዩ ሕዝቅኤል “በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ” (ሕዝ.1÷26) ብሎ እንደገለጠው እግዚአብሔር አምላክ ለመላእክት በሰው ምሳሌ ተገልጦ ይታያቸው ነበር እንጂ እርሱን ገጽ በገጽ ለመመልከት አልበቁም ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ገብርኤል የፅንሰቱን ነገር ለመላእክት በነገራቸው ጊዜ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ቃል ሰው በመሆን በአካል ሊያዩት እንደተቃረቡ ተረድተው ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማያውቅ ታላቅ የሆነ የደስታ ዝማሬ ዘመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ደስታቸው ድርብ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ደስታቸው የሰው ልጆች መዳን ሲሆን ሁለተኛው ግን አምላካቸውን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ለማየት በመብቃታቸው ነበር፡፡
“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ!!

👍13❤4❤🔥1
#ታኅሣሥ_24
#አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
ታኅሣሥ ሃያ አራት በዚህች ዕለት ጌታችን በቃሉ ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደታቸው ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡
ቅዱሳን አባቶቻችን እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና እነ አቡነ ዜና ማርቆስ ሌሎቹም እነ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ አኖሪዮስ(ትልቁ)፣ አቡነ ገላውዲዮስ፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋርና አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል የትውልዳቸው መሠረት ኢያሱ ለሌዋውያን ክፍል ትሆን ዘንድ ከለያት ከኢየሩሳሌም ነው፡፡ ስማቸውን የጠቀስኳቸው እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን የወንድማማቾች ልጆች ሲሆኑ ከአዳም ጀምሮ 61ኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ይኸውም እንዴት ነው ቢሉ ትውልዱ ከአዳም ጀምሮ በካህኑ አሮን በኩል የሆነውና የሌዋዊያን ሊቀ ካህን የነበረው የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ከታቦተ ጽዮንና ከብዙ ሌዋዊያን ካህናት ጋር ሊቀ ካህን ሆኖ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አክሱም ተቀምጦ ኖረ፡፡ የኦሪትንም ሕግ እየዞረ ለኢትዮጵያ ሰዎች አስተማረ፡፡ ትውልዱም በአብርሃ ወአጽብሓና በአባ ሰላማ ዘመን እስከነበረው እንበረም የሚባለው ጻድቅ ድረስ ደረሰ፡፡ የእንበረምም ትውልድ ደገኛው ሕይወት ብነ በጽዮን ድረስ ደረሰ፡፡ ሕይወት ብነ በጽዮንም የደማስቆ ምድር ከሚሏት ከወለቃ ሀገር የመኮንን ልጅ የሆነችውን ወለተ ሳውልን አግብቶ አበይድላን ወለደ፡፡ አበ ይድላም በንጉሡ ድልዓዥን ዘመነ መንግሥት ለ150 ካህናት አለቃ ሆኖ በወለቃ ሀገር የክርስቶስን የወንጌል ሕግ እያስተማረ ብዙዎችን አጠመቀ፡፡ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ እያስተማረ መጥቶ በሸዋ ምድር ተቀመጠ፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳነጸ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትንም ያደርግ ነበር፡፡ ‹‹በሸዋ ጽላልሽ ተቀምጦ ሲያስተምርም በአንዲት ቀን እስከ ሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ ያጠምቅ ነበር›› በማለት ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይመሰክርለታል፡፡
አበይድላ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር ከሸዋ ጽላልሽ ምድረ ዞረሬ ሚስት አግቶ ሀበነ እግዚእን ወለደ፤ ሀበነ እግዚእም በኩረ ጽዮንን ወለደ፤ በኩረ ጽዮንም ሕዝበ ቀድስን ወለደ፤ እርሱም ነገደ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ሕዝበ ቀድስም ብርሃነ መስቀልን ወለደ፤ እርሱም ዐቃቢነ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ብርሃነ መስቀልም ሕይወት ብነን ወለደ፤ እርሱም ሴትን ወለደ፡፡ ሴትም ወረደ ምሕረትን ወለደ፡፡ ወረደ ምሕረትም ዘካርያስን ወለደ፡፡ ዘካርያስም የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የሆኑ 6 ወንድማማች ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም እንድርያስ፣ አርከሌድስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ፣ ቀሲስ ዮሐንስና ቀሲስ ዮናስ ናቸው፡፡ እንድርያስም ሳሙኤል ዘወገግን ወለደ፤ አርከሌድስም ሕፃን ሞዐን ወለደ፤ ዘርዐ አብርሃምም ታላቁን አኖርዮስን ወለደ፤ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብም ተክለ ሃይማኖትን ወለደ፤ ቀሲስ ዮሐንስም ዜና ማርቆስን ወለደ፣ ቀሲስ ዮናስ ደግሞ የፈጠጋሩን ማትያስንና ገላውዲዮስን ወለዳቸው፡፡ ገላውዲዮስም የመሐግሉ ቀውስጦስን ወለደ፡፡ እነዚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናታቸውም በኩል እንዲሁ በዝምድና የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ማቴዎስ የተባለው ደገኛ ክርስቲያን የሸዋ ገዥ የነበረ ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ መድኃኒነ እግዚእንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ ሶስቱ ሴቶች ልጆችም እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ እኅትማማቾችም ደጋጎቹን አባቶቻችንን ወለዱልን፡፡ እምነ ጽዮን የእነ ዜና ማርቆስን እናት ማርያም ዘመዳንና ወለደች፡፡ ትቤ ጽዮንም ሕፃን ሞዐን ወለደች፡፡ ክርስቶስ ዘመዳ ደግሞ ታላቁን አኖሬዎስን ወለደች፡፡ የፈጠጋሩ ገዥ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ የተክለ ሃይማኖትን እናት እግዚእ ኀረያን ወይም በሌላ ስሟ ሣራን ወለደ፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ15 እና በ22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቀል፡፡
ከዕለታት በአንዱ ቀን አባታችን ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ዱር ሄደው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ታያቸው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹እንደዚህ ባለ ገናንነት የማይህ ጌታዬ ማነህ?›› ባሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ዘወትር የምጠብቅህ ካንተ የማልለይ እናትህንና አባትህንም ስላንተ ከውኃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኳቸው እኔ ሚካኤል ነኝ፡፡ ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው›› አላቸው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል ይህን ሲነግራቸው ጌታችን በሥጋ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደነበር ሆኖ መልከ መልካም ጎልማሳ መስሎ ታያቸው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ እንዴት ሰነበትክ? ቸር አለህን?›› አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ‹‹ጌታዬ ሆይ አንተ ማነህ?›› ብለው ሲጠይቁት ጌታችንም ‹‹እኔ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ነኝ፤ በናትህ ማኅፀን ፈጥሬህ ያከበርኩህ እኔ ነኝ፡፡ በተወለድክ በሦስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ታመሰግነኝ ዘንድ የምስጋና ሀብት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ በርሃብ ዘመን በቤት የሚያሻው ምግብ ሁሉ ቅቤው፣ የስንዴው ዱቄት በእናት በአባትህ ቤት ይመላ ዘንድ በእጅህ ሀብተ በረከት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ ያንን ሰው አንተን በተጣላ ጊዜ በነፋስ አውታር የሰቀለኩት በመዓት ጨንገር የገረፍኩት እኔ ነኝ፡፡ ውኃ ጠምቶህ በለመንከኝ ጊዜ ከደረቅ መሬት የጣፈጠ ውኃ ያመነጨሁልህ እኔ ነኝ፡፡ ከልጅነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ተአምራት እያደረግሁ በአንተ እጅ የታመሙትን ያዳንኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ወደፊትም አደርግልሃለሁ›› አላቸው፡፡ ይህንን ብሎ በእጆቹ ባረካቸውና ‹‹ንሣእ መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ የሹመትን ሀብት አሳደረባቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሁን፤ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሁን፤ አንተን የሰማ እኔን መስማቱ ነው፤ የላከኝ አባቴንም መስማቱ ነው፡፡ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ ማለቱ ነው፡፡ የላከኝ አባቴንም እንቢ ማለቱ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ቀድሞ ለሐዋርያት ሰጥቻቸው ነበር፡፡ ከሐዋርያትም ሹመትን የተቀበለ ጳጳሱ ትሾምና ትሽር፣ ትተክልና

👍13❤3
ትነቅል ዘንድ ሥልጣንን ሰጠህ፡፡ ይህንንም ያደረኩልህ የጳጳሱን ቃል በመናቅ አይደለም፡፡ የፍቅሬን ጽናት ባንተ እገልጽ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ሐዋርያት ወዳልደረሱበት ሕዝብ በመምህርነት እልክህ ዘንድ በሚካኤል ቃል አዲስ ስም አወጣሁልህ፡፡ አንተም በማናቸውም ሥራ ከእነርሱ አታንስም፣ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁና፡፡ ሰውን ሁሉ በእኔ ስም እያስተማርክ ታሳምን ዘንድ፣ ሚካኤልም ባሰብከው ሥራ ሁሉ ረዳት ይሁንህ፣ ሁል ጊዜ ካንተ አይለይም፤ በምትሄድበትም ጎዳና ሁሉ እርሱ መሪ ይሁንህ፤ እኔም ባለ ዘመንህ ሁሉ አልለይህም›› ካላቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ዐረገ፡፡
ብፁዕ አባታችንም እጅ ነሥተው ‹‹ለእኔ ለኀጥኡ የማይገባኝ ሲሆን ይህን ሁሉ ጸጋ የጠኸኝ ስምህ በሰማይ በምድር የተመሰገነ ይሁን›› አሉ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ሀብተ ኃይልን የተመሉ ሆኑ፡፡ ወደቤታቸው ተመልሰው ያላቸውን ሀብት ንብረት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥተው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ›› ብለው ቤታቸውን እንደተከፈተ ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ፔጅ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS

👍15❤1
#ሁላችንም_እንችላለን! (ልብ ብለው ያንብቡት)
ስኬት ለተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የተለገሰች ስጦታ ሳትሆን ለሁላችንም ያለአድልዎ የተበረከተችልን ነች። ስኬት በቴሌቪዥን መስኮት ለሚታዩት፣ በመጽሄት የፊት ገጽ ላይ ለሚወጡት፣ በራዲዮ ለሚደመጡት፣ በጋዜጣ ለሚሞገሱ ታዋቂ ሰዎች ብቻ ሳትሆን የሁሉም ነች። እነዚህ ሰዎች ይህንን እድል ያገኙት ከእድል ወይም በተለየ ምርጫ ሳይሆን ጠንክረው በመስራታቸውና ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀማቸው ነው።
ዛሬ ላለመስራታችን ላለመለወጣችን ላለማደጋችን ምክንያት የሆኑብንን ሁሉ ከላያችን ላይ አራግፈን ወደ ፊት የምንጓዝበትን ምክንያታዊ ሀሳቦችን አዝለን እንሩጥ! በዙሪያችን ያሉ አሉታዊ ሀሳቦችን መንቅረን በአዎንታዊ ሀሳቦች ራሳችንን እንክበበውና በኩራት ህይወታችንን ወደ ተሻለው እንምራው። በጎ ባልሆኑ ሀሳቦች የተከበበውን ማንነታችንን በአሸናፊነት ውሀ እንጠበውና ውስጣችን ንጹህ ሆኖ የማይቻለውን እንቻል።ምክንያቱም ከማንችልበት አንድ ምክንያት ይልቅ የምንችልበት ቢሊዮን ምክንያቶች ስላሉን! እስኪ እርስዎ የተሸነፉበትን፣ የተሰቃዩበትን፣ የተቸገሩበትን፣ የተዘለፉበትን፣ የተናቁበትን፣የተባረሩበትን፣ ያጡበትን ሳይሆን በህይወትዎ ውስጥ ያሉ ያላስተዋሏቸውን ብዙ በጎ ጎኖችን ይቁጠሩ።
ከብዙ አስቀያሚ ጎኑ ይልቅ አንዱ መልካም ነገር ላይ ያተኩሩ። የህይወትዎን በጎ ጎን መቁጠር ሲጀምሩ ከሚያስቡት በላይ ህይወትዎ በመልካም አገሮች እንደተከበበች ያያሉ! ያኔ እውነትም "እችላለሁ" የምችልበት ቢልዮን ምክንያትም አለኝ" ይላሉ። አሸናፊም ይሆናሉ።
(fb ላይ የተገኘ እና በድጋሚ የተለጠፈ)

👍17❤2
Forwarded from ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ (Yared)
ታኅሣሥ 27 በቦሌ መድኃኔዓለም ከቀኑ 09:30 ለአእላፋት ዝማሬ እንገናኝ::
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
🔸 @Z_TEWODROS
✍️Comment @Channel_admin09
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
🔸 @Z_TEWODROS
✍️Comment @Channel_admin09
👍12❤7❤🔥1
ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ልደተ ክርስቶስ እንዲህ አለ፦
ጌታ ሆይ ቅድስት እናትህ ድንግል ሳለች አንተን ፀንሳ በመውለድ እናትነትን ገንዘቧ አደረገች፤ ድንግል ሆና ሳለች ከጡቶቿ ወተት ፈሰሰ፤ ድንግል ከሆነች መሬት ንጹሕ ምንጭ እንዲፈልቅ፤ እንዲሁ ድንግል ከሆነችው እናትህ ጡቶች ወተት ፈለቀ፡፡ እርሱዋ አንተን ብትሸከምህ አንተ ጽንዕ ሰጥተሃት ነው፤ በተራብክ ጊዜ አንተን ከጡቶቹዋ ትመግብህ ዘንድ፣ ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ተራራ የመሰለህ አንተን አንደ ሕፃናት ታቀፈችህ፤ በፈቃድህ የተጠማህ አንተን በእጆቹዋ በፍቅር ትዳብስህ ዘንድ፤ የምህረት እሳት የሆንኽ አንተ ክንዶቿን መለኮታዊው እሳት እንዳይቃጥላቸው ጠበቅኻቸው፡፡
ጌታ ሆይ እናትህ ግሩም የሆኑ ተአምራት የተፈጸሙባት መካን ናት። ወደ እርሱዋ የሁሉ ጌታ የሆነው ገባ፤ የአገልጋዩን አርአያ ነስቶ ተወለደ። የእግዚአብሔር ቃሉ የሆነ እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ዝምተኛ ሆኖ ተወለደ። ነጎድጓድ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጭምት ሆኖ ተወለደ። እረኛ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ በግ ሆኖ በመወለድ በአባግዕ ቋንቋ ተናገረ፡፡
ጌታ ሆይ የእናትህ ማኅፀን ከተፈጥሯዊው ሥርዓት በተቃራኒው ፈጸመ፤ ሁሉን ያከናወነ በባለጸግነቱ ወደ እርሷ ገባ፤ ደሃ ሆኖ ተወለደ። ከሁሉ በክብር የሚልቀው እርሱ ወደ እርሷ ገባ፤ ትሑት ሆኖ ተወለደ። በክብሩ ገናና የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ የባሪያውን መልክ ይዞ ተወለደ። ብርቱ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው ሕፃን ሆኖ በማኅፀን ተገኘ። ፍጥረትን ሁሉ የሚመግበው መራብንና መጠማትን ገንዘቡ አደረገ፤ (አጣጣመ) ሁሉን በበረከቱ የሚያለብሰውና የሚያስጌጠው እርሱ ራቁቱን ተወለደ።
እኛን ለማዳን ሲል የእኛን ተፈጥሮ ገንዘቡ ላደረገ ለእርሱ ክብር ምስጋና ይሁን።
መልካም በዓለ ልደት

❤28👍11🕊2
የተርሴስ እና የደሴቶች ነገስታት ስጦታን ያመጣሉ:
የዐረብ እና ሳባ ነገስታት እጅ መንሻ ያቀርባሉ:
ነገስታትም ሁሉ ይሰግዱለታል።
እንኳን ለጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
የዐረብ እና ሳባ ነገስታት እጅ መንሻ ያቀርባሉ:
ነገስታትም ሁሉ ይሰግዱለታል።
እንኳን ለጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma
✍️Comment @Channel_admin09
❤15👍7
ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ያገኘነው ምንድን ነው?
ዳግም ልደት
በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል።
ሰላም
በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ ነውና።
ብርሃን
“በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።” ኢሳ 9፥2። ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ የነበረው አዳም ወደሚደነቀው ብርሃን የተሸጋገረው በክርስቶስ ልደት ነው። እኛም በልደቱ ያገኘነውን የጽድቅ ብርሃን ጠብቀን ለመኖር (ብርሃነ ወንጌልን) ፈጽመን ከኃጢአት ርቀን በጽድቅ ሥራ ተወስነን ብርሃን ሆነን ልንኖር ይገባል።
ነጻነት
“በነጻነት እንኖር ዘንድ ክርስቶስ ነጻ አወጣን። ከእንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገና በባርነት ቀንበር አትያዙ”። ገላ 5፥1። የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በነጻነት እያመሰገነ ይኖር ዘንድ ተፈጥሯልና። ኃጢአት በመሥራት የዲያብሎስ ባርያ ሳንሆን በተሰጠን ነጻነት በመጠቀም የጽድቅ አገልጋዮች ሆነን ልንመላለስ ይገባል።
ይቅርታ
በአዳም በደል ምክንያት ከአብራኩ የተከፈሉ በሙሉ በደለኛ ሆነው የነበሩበትን ዘመን ለውጦ አዳምንና የልጅ ልጆቹን በደል ደምስሶ ፍቅርን ይመሰርት ዘንድ ጌታ ተወለደ። በምድርና በሰማይ ላሉት ፍቅርን መሠረተ። እርሱ የሰው ልጆችን በደል ሳይቆጥር ሁሉን ይቅር እንዳለ ክርስቲያንም የበደሉትን ሁሉ ይቅር ይል ዘንድ የፈጣሪው ትዕዛዝ ነውና ዘወትር ሊፈጽማት የምትገባ ከእግዚአብሔር ጸጋ የምታስደምር የልደቱን ብርሃን ለማየት እንደበቁ በዚህም ደስ እንደተሰኙ እንደ ቅዱሳን መላእክት ለእውነተኛ ምስጋና የምታደርስ የጽድቅ መሠረት የበረከት በር ናት። ማቴ 18፥21-23፣ ማቴ 5፥23-25። መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ የሚለው አምላካዊ ቃል ይቅርታ የክርስትና ሕይወት መመሪያ መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልንፈጽማት ይገባል።
ፍቅር
ፍቅር ሰሃቦ ለወልድ ኃያል እም መንበሩ ወአብጽሖ እስከለሞት /ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው።/ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅን በደል ሳይቆጥር በዙፋኑ ሆኖ ምሬሃለሁ ማለት ሲችል ፍቅሩን ይገለጽ ዘንድ በከብቶች በረት ተወለደ። እውነተኛ ፍቅሩ ለክርስትናችን መሠረት ለጽድቃችን ፋና እንደሆነ መጻሕፍት ያረጋግጣሉ።
እንግዲህ በልደቱ ያገኘነውን ሰላም፣ ነጻነት፣ ይቅርታ፣ ብርሃንና ፍቅር ዋጋ የተከፈለበት ጸጋ የወረስንበት በመሆኑ ዘወትር በድንቅ ፍቅሩ የሚታደገን አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ እስከ መጨረሻው ድረስ ጸንተን እንድንኖር ክብራችንንና ጸጋችንን አስተውለን ከኃጢአት ርቀን በንሰሐ ታጥበን እራሳችንን ለክርስቶስ የተወደደ መስዋዕት አድርገን እንድናቀርብ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አይለየን። አሜን።

👍13🕊3❤1
#ሰብአ_ሰገል_ወርቅ_ዕጣንና_ከርቤ_የመገበራቸው_ምስጢር፡-
የጌታችንን ልደት በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው የመገበራቸው (አምሐ አድርገው የመስጠታቸው) ምስጢር እንደምንድን ነው ቢሉ፡-
#ወርቅ፡-
ወርቅ መገበራቸው ይኸን የምንገብርላቸው ነገሥታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ነህ፤ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወርቅ ጽሩይ ነው፤ ጽሩየ ባሕርይ ነህ ሲሉ፤ እንዲሁም በአንተ ያመኑ ምዕመናንም ጽሩያነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው ሲሉ። አንድም ወርቅ የሃይማኖት ምሳሌ ነው። የሃይማኖት ጽሩይነቱና ግብዝነቱ የሚታወቅ መከራ ሲቀበሉበት ነውና።
#ዕጣን፡-
ዕጣን መገበራቸው ይህንን የምናጥናቸው ጣዖታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ። አንድም ዕጣን ምዑዝ ነው፤ አንተም በባሕርይ ምዑዝ ነህ ሲሉ እንዲሁ ደግሞ በአንተም የሚያምኑ ምእመናንን ምዑዛነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው ሲሉ። አንድም ዕጣን የተስፋ ምሳሌ ነው። ዕጣን ከሩቅ እንዲሸት ተስፋ ያልያዙትን እንደያዙት ያላዩትን እንዳዩት ታደርጋለችና።
#ከርቤ፡-
ከርቤ መገበራቸው ምንም ቀድሞ ያልተፈጠርህ በኋላም የማታልፍ ብትሆንም በሰውነትህ መራራ ሞትን ትቀበላለህ ሲሉ፤ አንድም ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል፤ የተለየውን አንድ ያደርጋል። አንተም ከማኅበረ መላእክት የተለየ አዳምን አንድ ታደርገዋለህ፤ ጽንዓ ነፍስ ሰጥተህ ታጸናዋለህ ሲሉ። አንድም በዕለተ ዓርብ ያቀምሱታልና ከርቤ አመጡለት። ከርቤ የምዕመናን ምሳሌ ነው። በፍቅር አንድ ይሆናሉና። ከርቤ የፍቅር ምሳሌ ነው። ከርቤ አንድ እንዲያደርግ ፤ ፍቅርም አንድ ታደርጋለችና።
በአጠቃላይ ሰብአ ሰገል ወርቅ፣ እጣን ከርቤ የገበሩለት ሃይማኖት፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ገንዘቦችህ ናቸው ሲሉ ነው። በሌላ መልኩ ወርቅ ለመንግሥቱ፣ ዕጣን ለመለኮቱ፣ ከርቤ ለሞቱ ምሳሌ ናቸው።

👍20❤6
#ጌታ_ስለተወለደባት_ምሽት_ቅዱስ_ኤፍሬም_አንዲህ_አለ፦
"ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡
ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን፤ ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!
ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን።
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት።
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት።
የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው።
ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!
ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ።

❤17👍9🕊3
#የጌታ_ልደት_በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡
መፅሃፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡
እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡

👍23❤6😢2🕊1
ድንግል ማርያም ሕፃኑን እያባበለች በመደነቅ ቃል ነደደች
እንዲህ ስትል
"ድንግሊቱን እጸንስ ዘንድ የሰጠኝ ማን ነው?
ይህንን አንድ ሲሆን የበዛ ፣ ታናሽ ሲሆን ታላቅ የሆነ ፣ ከእኔ ጋር ሲሆን በሁሉ የሞላ ሕፃን የሠጠኝ ማን ነው?
....
በእኔ [ማኅጸን] ውስጥ እያለህ ከእኔም ውጪ በሁሉ ቦታ ነበርህ ፣ በወለድሁህ ጊዜም ረቂቅ አምላክነትነህም ከእኔ ውስጥ አልወጣም። በእኔ ውስጥ ነህ ፣ ከእኔም ውጪ ነህ! ይህ ነገር ለእኔ ለእናትህን ያስደነቀኛል።
የሚታየው ሰውነህን በፊቴ ባየሁ ጊዜ የማይታየው አምላክነትህን በሕሊናዬ አየዋለሁ። ቅዱስ ሆይ በሚታየው ሰውነትህ ውስጥ አዳምን አየዋለሁ ፣ በማይታየው መለኮትህ ውስጥ ደግሞ በአንተ ሕልው ሆኖ የሚኖረውን እግዚአብሔር አብን አየዋለሁ።
አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?
ምን ብሎ እንደሚጠራህ አንደበቴ አያውቅም። አእላፋት ስሞች ለአንተ አይበቁህም ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን የሰው ልጅ ነህና ፣ የዳዊት ልጅ ስትሆን የማርያም ልጅ ነህና!
ልጄ ሆይ ከእኔ ጋር ሆነህ ሳለ ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በመሆንህ አልቀናም። ለሚያምንብህ አምላክ ነህ ፣ ለሚያገለግልህ ጌታ ነህ ፣ ለሚወድህም ሁሉን ያንተ ታደርገው ዘንድ ወንድም ነህ!"
የአንደበቶች ሁሉ ጌታን አንደበት እንደሌለው ያደረገው ምን ይሆን? ልጄ ሆይ አንተን በድንግልና መፅነሴን ክፉ ሰዎች እየዘለፉ ነው።
ቅዱስ ሆይ ለእናትህ አንደበት ሁነኝ ፣ አንተን ከማን እንደፀነስሁህ ይረዱ ዘንድ ተአምርህን አሳይ።
ሁሉን የምትወድደው ሆይ ስለ አንተ ብዬ የተጠላሁ ሆንሁ ፣ ለሰው ልጆች መሸሸጊያ የሆንህ አንተን በመፅነሴ መከራን ተቀበልሁ።
አቤቱ በዮናስ ላይ እንደተቆጣ ባሕር በእናትህ ላይ ተቆጥቷል።
ሔሮድስ የተባለ ማዕበል የባሕርን ጌታ ሊይዝህ ፈልጓል። የእናትህ ፈጣሪዋ ሆይ ወዴት እንደምሸሽ ንገረኝ"
(ቅዱስ ኤፍሬም)

❤30👍11❤🔥2
ጾሙስ አበቃ.....?
(#በአባ_ገብረ_ኪዳን)
ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!
አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?
የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!
ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ!
የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!

👍21❤16❤🔥3
#ሰው_ሆይ!
በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።
እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)
ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?
(ከአቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ)

👍29❤15
#ጥር_7
#በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ
ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::
#ሕንጻ_ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::
ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::
ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::
መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::
ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::
ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::
#ቅዳሴ_ቤት
ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::
ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::
ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::
ከበዓሉ በረከት ይክፈለን
(#ስንክሳር_ዘተዋሕዶ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

❤24👍18🕊2😢1
ገሃድ ምንድን ነው?
ገሃድ መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና፡ አንድም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡ (ማቴ 3፡13-17)
ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም በዓለ ጥምቀት ከመዋሉ አንድ ቀን ቀድሞ ማለትም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሃድ ጾም ነው ማለት ነው!

👍38❤12