Telegram Web Link
በዚህ ምድር ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር ካልተዛመድን በሰማያት ልንዛመደው አንችልም፤ የመንግሥቱ ጣዕም ያለው በዚህ ነውና። ከእግዚአብሔር ጋር  ያለው ዝምድና እዚህ ምድር ላይ ይጀምራል። ይህም እንደ እግዚአብሔር እንደ ራሱ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ።" ምሳ 23፥26 በሚለው ጥያቄ ይጀምራል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ልብን አንጽቶ በፍቅር ከሞላው በኋላ በዚያ ራሱን ያሳድራል። ወንጌል "የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና።"ሉቃ 17፥21 ብሎ እንደሚናገር ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ማረጋገጫ ይሆናል።

ስለዚህ የሰማያትን መንግሥት ከማግኝት በፊት ሰው በውስጡ ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ማግኝት መቻል አለበት። ይህ ይሁን እንጂ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያገኝ የሚችለው እንዴት ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ኅብረት ሊያገኝ የሚችለውስ እንዴት ነው? ሁል ጊዜ ከእርሱ ጋር የሚሆነውስ እንዴት ነው? በዚህ ዙሪያ የምሰጣችሁ ምክር ምንጊዜም ቢሆን በእርሱ እንድትጠመዱ ሲሆን ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ስለ እርሱ ሥራና ስለ ራሱ በማንበብ የሚከናወን ይሆናል።

ከቅዱሳኑ ጋር ስላለው ዝምድና ስለ ድንቅ ባሕርያቱና በማንኛዎቹም አጋጣሚዎች ውስጥ ስላለው ስለ እርሱ እጅ አንብቡ። በዚህ ጊዜ ልባችሁ በእርሱ ፍቅር ይንቀሳቀሳል። በማንኛውም ጊዜ ውስጥም ከእርሱ ጋር ይገናኝ ዘንድ ዝግጁ ነው ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
27
ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!!

የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17

ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።

ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።

#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
14
Forwarded from መምህር ዘበነ ለማ (Yared)
ማስታወቂያ

መምህር ይትባረክ ጋሻው ከፍተኛ የባህል ፈውስ መድህኒት አዋቂ እና ቀማሚ  ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦ በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
0917468918
0917468918
1 👉ለመፍትሄ ሀብት
2 👉ለህማም
3 👉ለመስተፋቅር
4 👉ቡዳ ለበላው
5 👉ለገበያ
6 👉የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 👉ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 👉ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 👉ለዓቃቤ ርዕስ
10👉ለመክስት
11 👉ለቀለም(ለትምህርት)
12 👉ሰላቢ የማያስጠጋ
13 👉ለመፍትሔ ስራይ
14 👉ጋኔን ለያዘው ሰው
15 👉ለሁሉ ሠናይ
16 👉ለቁራኛ
17 👉ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 👉ለመድፍነ ፀር
19 👉ሌባ የማያስነካ
20 👉ለበረከት
21 👉ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 👉አፍዝዝ አደንግዝ
23 👉ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 👉ለግርማ ሞገስ
25 👉መርበቡተ ሰለሞን
26 👉ለዓይነ ጥላ
27 👉ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 👉ለሁሉ መስተፋቅር
29 👉ጸሎተ ዕለታት
30 👉ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 👉ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 👉ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 👉ለድምፅ
34 👉ለብልት
35 👉በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ
0917468918
0917468918

      💚💛❤️ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 💚💛❤️
🌼🌻🌼🌻
👉የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
👉ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
👉ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
👉ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
👉ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
👉ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
👉ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
👉ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
👉ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
👉መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
👉ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን  💚💛❤️      
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር እኛ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልኝ ወይም በቴሌግራም መሪጌታ ይትባረክ ጋሻው ብላችሁ ታገኙናላችሁ
ወይም በስልክ ቁጥር ይደውሉልን
0917468918
0917468918
2
#ቅዱስ_ጳውሎስ_ወቅዱስ_ጴጥሮስ

ሐምሌ አምስት በዚህች ዕለት ስለክርስቶስ የተገፋ፣ ስለክርስቶስ የተወገረ፣ ስለክርስቶስ የተሰደደ፣ ስለክርስቶስ የታሰረ፣ ስለክርስቶስ ከዓለም ሃሳብና መሻቷ የተለየ፣ ስለክርስቶስ ራሱን የለየ፣ ስለክርስቶስ ምእመናን ያነፀ፣ ስለክርስቶስ መልካምን መልእክት የጻፈ #ቅዱስ_ጳውሎስ በሰማዕትነት ዐረፈ። ነገር ግን በስጋ አረፈ እንጂ በመንፈስ ህያው ነው፤ የፅድቅን አክሊል ተቀበለ፣ ከክርስቶስ ጋር መኖርን እንደናፈቀ አገኛት። ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን ማኅበር ተቀላቀለ። ከመላእክት ምስጋና ተጋራ በስጋ ሕይወቱ ከእውቀት ከፍሎ እንዳወቀ በሰማያዊው ኑሮ በእጅጉ የበለጠ እውቀትን ተቸረ። በማይጠወልግ፣ በማይደርቅ፣ በማይዝል፣ ፍሬያማም በሆነ ክርስቶስ ግንድነት ላይ ቅርንጫፍ ሆኖ ተሰርቷልና በስጋ ኑሮው በድካም ዝለት ጠውልጎ እንደነበረ የሚጠወልግ አይደለም፤ በማስተማር ብዛት ጉሮሮው እንደደረቀ አሁን የሚደርቅ አይደለም፤ በብርቱ ክንድ ላይ በምቾት አለና የሚዝልም አይደለም፤ ክፉወች ሮማውያን ግን ቅዱስ ጳውሎስን ገደልን አሉ። አይሁድም እፎይ ጳውሎስ ሞተ አሉ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የናፈቀው ክርስቶስ ጋር ሊኖር ወደዘላለማዊው ሕይወት ሄደ።

ራሱን ሕያው መስዋእት አድርጎ በክርስቶስ ፊት እንደ ንጹህ መገበሪያ አድርጎ እንደ ጧፍ በሮማ አደባባይ ነደደ። አይሁድ በቅዱስ ጳውሎስ መሞት ድል ያደረጉ ይመስላቸዋል ነገር ግን የፅድቅን አክሊል በራሱ ላይ አድርጎ ከፀሐይ ይልቅ እያበራ በሰማይ ሆኖ ቅዱስ ጳውሎስ አለ። በማይደርቅ ግንድ ላይ የተተከለ ቅዱስ ጳውሎስ ፍሬ በሙላት የያዘ የለመለመ ቅርንጫፍ ሆኖ አለ፣ በቅድስና በተዋበ የክርስቶስ አካል መካከል መልካም ብልት ሆኖ አለ፡፡

አይሁድ ግን ቅዱስ ጳውሎስን ገደልን አሉ በሰይፍ አንገቱን ቆርጠው በስጋ ገድለውታልና አላዋቂ አይሁድ ከሮማውያን ጋር አብረው ጳውሎስን ገደልን አሉ፤ እርሱ ግን ከአፈር በተበጀ ስጋ ሞት ቢሞት በእግዚአብሔር እስትንፋስ ስለተሰጠች ነፍስ ሕያው ነው፡፡

ዳግመኛም በዚህች ዕለት በብርሃኑ ብርሃንን በጨውነቱ መጣፈጥን በመድኃኒቱ ፈውስን የሰጣቸው ተወዳጅ የሐዋርያት አለቃ #ቅዱስ_ጴጥሮስን አይሁድ ቁልቁል ሊሰቅሉት ወደ ሮም አደባባይ ከወዳጁ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር አጣደፉት፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን በትምህርቱ ብርሃን ጨለማቸውን ገፎላቸው፣ በእምነት መድኃኒት ሙታናቸውን አንስቶላቸው፣ ጎባጣቸውን አንቅቶላቸው፣ አንካሳወቻቸውን አፅንቶላቸው፣ ክፉ ጠላት ዲያቢሎስንም አባሮላቸው ነበር፤ አይሁድ ግን ከወዳጃቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ይልቅ ጠላቶቻቸውን ሮማውያን ጋር አብረው አንድም ከወዳጃቸው ከክርስቶስ ይልቅ ከጠላታቸው ዲያቢሎስ ጋር አብረው ቅዱስ ጴጥሮስን እንደጌታውና መምህሩ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ዘቅዝቀው ሊሰቅሉት ወደሮም አደባባይ አፋጠኑት የማይጠፋውን ፋና ሊያጠፉ፡ የማይደበዝዘውን ብርሃን ሊያደበዝዙ፡ የማይሞት የክርስቶስን ልጅ ሊገድሉ በገሃነም ደጆች የማትናወጥ ክርስትናን ሊያናውጡ አይሁዳውያን
የክርስቲያኖች ዋና ያሉትን ቅዱስ ጴጥሮስን በብዙ ስቃይ አንገላቱት። ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የስጋ ሞቱ ዕረፍቱ እንደሆነ እጅግ አስቀድሞ አውቆ ነበር፤ የአይሁድ ማሰቃየት ወደክርስቶስ የፀጋ ግምጃ ቤት እንደሚያደርሰውም አውቆ ነበር፤ የአይሁድ መጨከን ወደክርስቶስ አማናዊ ፍቅር
እንደሚመራው አውቆ ነበር። “ገደልንህ” አሉት እርሱ ግን “ወደዘላለማዊ ህይወት ክርስቶስ ገፋችሁኝ” አላቸው። “ክርስቲያኖችን ጨረስን” አሉት እርሱ ግን “የእኛ ሞት የክርስቲያኖች ዘር ነው” አላቸው። “አንተ ርጉም” አሉት እርሱ ግን “የክርስቶስ ምህረት በእናንተ ላይ ይሁን” ሲል በፍቅር ጸለየላቸው፡፡

እነሆ አባቶቻችን እነሆ ዋኖቻችን በክፋት በአንዳች እንኳን የሚከሰሱበት ምክንያት አልተገኘም በቀማኝነትም ማንም እነሱን ሊከስ የሚችል የለም ነገር ግን የሚሰድቧቸውን መረቁ፣ ለሚያሳድዷቸው ጸለዩ፣ ለተራቡት ምግብን ለተጠሙት መጠጥን አቀበሉ፣ ድሆችን ተንከባከቡ፣ ድውዮችን ፈወሱ፣ የጨለማን ክፋት በፍቅር ብርሃን አረከሱ፣ የዲያቢሎስ ጭካኔ በክርስቶስ ርህራሄ ሰበሩ፡፡

እነሆ አባቶቻችን አስቀድመው ክርስቶስን አይተው ነበርና ክርስቶስን በትምህርቱ በተአምራቱ በሞቱም መሰሉት፡፡

የከበረች በረከታቸው ከእኛ ጋር ትሁን። አሜን!!!

እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስና ለቅዱስ ጳውሎስ ዓመታዊ መታሰቢያ እለት አደረሰን፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
11
2025/07/12 12:45:32
Back to Top
HTML Embed Code: