Telegram Web Link
እውነተኛ ክብርን ማግኘት ትፈልጋለህን? ክብርን ናቅ፤ ያን ጊዜም ትከብራለህ፡፡ ለምን እንደ ናቡከደነፆር ታስባለህ? እርሱ ክብርን መጨመር በፈለገ ጊዜ ከዕንጨትና ከድንጋይ የራሱን ምስል ሐውልት አቁሞአልና፤ ሕይወት በሌለው በዚህ ግዑዝ ነገር ሕይወት ላለው ለእርሱ ክብር የሚጨምርለት መስሎት ነበርና፡፡ [ነገር ግን ክብር ሳይኾን ውርደት አገኘው፡፡] እንግዲህ የስንፍናውን መጠን አለፍነት ታያለህን? እከብርበታለሁ ብሎ ባቆመው ነገር እንዴት የገዛ ራሱን እንደ ዘለፈበት ትመለከታለህን? በራሱና በገዛ ነፍሱ ንጽህና ሳይኾን ሕይወት በሌለው ነገር ላይ መደገፉ፣ በዚያ ረዳትነትም ክብርን ማግኘት ፈልጎ ሐውልቱን ማቆሙ፥ ከዚህ በላይ ምን ሞኝነት አለ? ራሱን ለማክበር ብሎ የገዛ ሕይወቱን እንደ ማስተካከል፥ በዕንጨት ላይ ዕንጨት እንደ መጨመር ያለ ምን ሞኝነት አለ? ይህ ማለት “አንድ ሰው ፈሊጥ ያውቃል የሚባለው ሰው በመኾኑ ሳይኾን የቤቱ ምንጣፍ ያማረ ስለ ኾነ፣ የቤቱ ደረጃም የተወደደ ስለ ኾነ ነው” እንደ ማለት ይቈጠራል፡፡ በእኛ ዘንድ በእኛ ዘመን ናቡከደነፆርን የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እርሱ ሐውልት እንዳቆመ አንዳንዶችም ስለ ለበሱት ልብስ፣ ስለ ገነቡት ቤት፣ ስላላቸው ፈረስ፣ ገንዘብ ስላደረጉት ሠረገላ፣ ወይም ስለ ቤታቸው አሠራር ክብር የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡

ከሰውነት አፍአ ወጥተው ይህን በመሰለ መጠን አለፍ ዕብደት ይያዛሉ፡፡ የራሳቸውን ሕይወት እንደ ማስተካከል ቁሳዊ ነገርን በመሰብሰብ ክብርን ይፈልጋሉ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስ ወንጌል፣ 4:20 በተረጎመበት ድርሳኑ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍173
“በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡ እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡ በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡ ‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡”

“ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡ ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡ ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክትን እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡ አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡ ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ via ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2913❤‍🔥1
“ልጆቼ! ሰዎች ክፋትን እየሠሩ ብትመለከትዋቸው በፍጹም አትጥሏቸው፡፡ ሰው ክፋቱ እንጂ እርሱ ራሱ አይጠላምና፡፡ የሐሰት ትምህርቱ እንጂ እርሱ ራሱ አይጠላምና፡፡ ምክንያቱም እርሱ ራሱ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ እጅግ መልካም ፍጥረት ነው፡፡ ክፉ ሥራው ግን ከዲያብሎስ ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሥራና የዲያብሎስ ሥራ ለይተን እንወቅ፤ እንረዳ፤ ከዚያም ማቀላቀልን እንተዋለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወገኖቹ አይሁድ ክርስቶስን እንዳንገላቱት፣ እንደዘበቱበት፣ እንዳሳደዱት፣ እልፍ ወትእልፊት ጸያፍ ነገርም እንደተናገሩበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ግን እንዲህ በማድረጋቸው ጠላቸው? በፍጹም! እንዳውም ስለ እነርሱ ይረገም ዘንድ ይጸልይ ነበር /ሮሜ.9፥3/፡፡ ነቢዩ ሕዝቅኤል እነዚህ ሰዎች በነቢያት ደም የሰከሩ መኾናቸውን ጠንቅቆ ቢያውቅም ይጸልይላቸው ነበር /ሕዝ.9፥8/፡፡ ሙሴ እነዚህ ሰዎች ኃጢአት እንደ ሠሩ ቢያውቅም ስለ እነርሱ ከሕይወት መጽሐፍ ይደመሰስ ዘንድ ይለምን ነበር /ዘጸ.32፥32/፡፡ ለምን? ሰዎቹ መዳን የሚገባቸው /ሮሜ.10፥1/ ደግሞም በሥላሴ አምሳል የተፈጠሩ እጅግ ግሩማን ናቸውና የሥላሴ ፍጥረት አይጠላም፤ ክፉ ሥራቸው ግን ከክፉው (ከዲያብሎስ) ነውና ይጠሉታል፡፡

ልጆቼ! አንድ የጤና ባለሙያ ታማሚውን ጠልቶ ፊቱ የሚያዞርበት ከኾነ፣ ታማሚውም ሐኪሙን አታሳዩኝ እያለ ከጠላው እንደምን ከበሽታው መዳን ይቻለዋል? እኛስ ክፉ የሚሠሩትን የምንጠላቸው ከኾነ እንደምን ከክፉ ሥራቸው ልናወጣቸው እንችላለን?

ልጆቼ! እንግዲያውስ በክፉ በሽታ የተያዘውን ወንድማችን ከበሽታው እንዲፈወስ ልንረዳው ይገባናል እንጂ ጤነኞች የምንኾን እኛ ሌላ በሽታ የምንጨምርበት ልንኾን አይገባንም፡፡ ከበሽታው ምንም የማይፈወስ ቢኾን እንኳ ከእኛ የሚጠበቀውን ኹሉ በማድረግ እስከ መጨረሻው ልንጥርለት ይገባናል፡፡ እስኪ ይሁዳን አስታውሱት! የታመመው ሊድን በማይችል በሽታ ነበር፡፡ ግን መፈወስ የማይችል ነው ብሎ ክርስቶስ ተወው? በፍጹም! እስከ መጨረሻይቱ ደቂቃ ታገሠው፤ ደግሞም እንዲመለስ ይገስጸው ነበር እንጂ፡፡ እኛም ይህን ከአባታችን ልንማር ይገባናል፡፡ ክፋትን የሚሠሩ ሰዎች ስናይ ፈጥነን አንተዋቸው፡፡ የሚቻለንን ኹሉ እናድርግላቸው እንጂ፡፡ ባይመለሱ እንኳ ሽልማታችን አይቀርብንም፡፡ ይህም ብቻ ሳይኾን ክፋትን የሚሠራት እኁ በእኛ እንዲደነቅ እናደርገዋለን፡፡ ምክንያቱም እንዲህ በክፋት የሰከሩ ሰዎች ተአምራትን አድርገን፣ ሙትን አስነሥተን ከምናሳያቸው ይልቅ በትኅትናችን፣ በጨዋነታችን፣ በትዕግሥታችን እጅግ ይማረካሉና፡፡ አንድ ሙት ማስነሣት ምን ይደንቃል? ዓለም ኹሉ በከመ ቅጽበት ይነሣ የለምን?

ሰዎች ከፍቅር በላይ በምንም መንገድ ከክፋታቸው ልንመልሳቸው አንችልም፡፡ ፍቅር ሰዎችን ከአውሬነታቸው መልሳ ሰዎች እንዲኾኑ የታደርግ ታላቅ መምህርት ናት፡፡ እንግዲያውስ ብዝሕ ያላቸውን በረከቶች በእኛ ላይ እንዲጐርፉ፣ ደግሞም መቼም የማይገማና የማይበላሽ ፍሬአቸውን በጊዜው እንድንበላ የግብረገብነት ኹሉ ራስ የምትኾንን ፍቅር በልባችን ውሳጤ እንትከላት፡፡
ይህን እንድናደርግ ሰውን በመውደዱ ሰው የኾነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(የቅዱስ ጳውሎስ መልእክትን 1ቆሮ 13፡1-7 በተረጎመበት ድርሳኑ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
15👍13❤‍🔥2🕊1
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

ጸሎት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምታደርስ ቀጭኗ ጎዳና ናት፡፡ ከኃጢአት በመራቅ የሚቀርብ ጸሎት ፍጹም የሆነ ሥራን ይሰራል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እኖርክ በእግዚአብሔር ስም ለጸሎት የምትቆም ከሆነ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ ህሊናህም ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡ በጸሎት ተመስጠህ ልብህን ወደ እግዚአብሔር አንሳ፡፡

አጠገብህ ስሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠኸው ቁጥር ነው፡፡ ጥላቻ በልቦናህ ነግሶ ከሆነ የዳቢሎስ እርዳታ እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡

የተንኮል ቃልን አትናገር፤ ለባልንጀራህ ጉድጓድ አትቆፍር፤ ወደ አመንዝራም ሴት አትመልከት የፊቷም ደምግባት አያጥምድህ፡፡ በእርሷ መረብ እንዳትጠመድ ከአንደበቷ ከሚፈልቁት ጣፋጭ ቃሎች ተከልከል፡፡ ከእርሷ ፈጽሞ ሽሽ፡፡

በሰዎች ውድቀት አትደሰት፡፡ በደለኛ እንዳትሆን ጠላትህ ክፉ ሲደርስበት አይተህ ደስ አይበልህ፡፡ ጠላትህ በኃጢአት ተሰነካክሎ ብታይ ስለ እርሱ እዘንለት አልቅስለት፡፡ እጆችህን ለሥራ አትጋቸው፤ ከንቱ ንግግር አትውደድ ለነፍስና ለሥጋ ብሩህነት በሥራ መጠመድን ውደድ፡፡

(ምንጭ፡- ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም፣ በመ/ር ሽመልስ መርጊያ፣ ገጽ 65-66)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍157
#ጻድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት (ነሐሴ ፳፬ - እረፍቱ)

ነሐሴ ፳፬ በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ #ሐዲስ_ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ #አባታችን_ተክለሃይማኖት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖሩ።

በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ። የሀገር መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል። ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶች ያደርጋቸዋል።

በዚያም ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ።

ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት ባያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደመኳንንቶቹ ሁሉ ላከ።

እግዚእ ኀረያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞራሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት። ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድን ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ።

የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዙእ ኀረያ እንደሆነች አገኛት እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው የዜናው መሰማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው።

ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ይህ ቅዱሱ ተፀንሶ በታኀሣሦ ወር በሃያ አራት ተወለደ በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ ቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸውና ከጐረቤቶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው።

ለክርስትና ጥምቀትም በአስገቡት ጊዜ ፍሥሓ ጽዮን ብለው ሰየሙት። ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመነፈስ ቅዱስ ጸና።

ከዚህም በሗላ ዲቁና ይሾመው ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት በዚያንም ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ነበር። ወደ ጳጳሱም በአደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት። የዲቁና ሹመትንም ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።

ጐልማሳ በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ። ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ የሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክነፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳጄ አትፍራ እንግዲህ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኀፀን መርጬ አከብሬሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኩሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘብን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርኩዙን ይዞ በሌሊት ወጣ።

ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሔዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ። ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ ለጣፆት የሚሠውበትን ሁሉ ሻረ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንት እስከሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ።

ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሔዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው እርሱ ግን በደኀና ይመለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሠቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትንም ጦር ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው።

ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር።

ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኀነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስን በማመን ያጸናቸዋል።

ከዚህ በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ በገድል ተጸምዶ ወደሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደባሪያ ሲያገለግል ኖረ በአንድነት የሚኖሩ መነኰሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር።

በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በሗላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደሚኖር ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔዶ ከእርሱም የምንኲስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሔዶ ለአቡነ አረጋዊ አራተኛ ከሆነ ከአባ ዮሐኒ ዘንድ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ። ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ።

በዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ ከዚያም ግራርያ ወደ ሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበረ ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው።

ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኲሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስበርሳቸውም አይተዋወቁም እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ሰለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እነደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም።

በዚህም በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በሗላው በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ። በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣ ኖረ።

ይቀጥላል....

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍239🕊1
መምህር ዘበነ ለማ
#ጻድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት (ነሐሴ ፳፬ - እረፍቱ) ነሐሴ ፳፬ በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ #ሐዲስ_ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ #አባታችን_ተክለሃይማኖት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ…
የቀጠለ....


ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።

አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ።

በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ተክለሃይማኖት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍1511
"እኔ ከእርሱ [ከባልንጀራዬ] ጋር ምንም ግንኙነት የለኝምና የሚል ደካማ መልስም አትስጠኝ፡፡ ምንም ግንኙነት የሌለን ከዲያብሎስ ጋር ብቻ ነው፡፡ ከሰዎች ኹሉ ጋር ግን በጣም ብዙ የምንጋራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም አንድ ዓይነት ባሕርይ (ሰው መኾንን) አለን፤ እኛ በምንኖርባት ምድር ይኖራሉ፤ እኛ የምንበላውን ምግብ ይበላሉ፤ አንድ ጌታ አለን፤ እኛ የተቀበልነውን ሕግ ተቀብለዋል፤ እኛ ወደ ተጠራነው መንግሥትም ተጠርተዋል፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም አንበል፡፡ እንዲህ ብሎ መናገር ሰይጣናዊ ንግግር ነውና፡፡ ዲያብሎሳዊና ኢ-ሰብአዊነት ነውና፡፡ ስለዚህ ለወንድማችን ያለንን ጥንቃቄ እናሳይ እንጂ እንደዚህ ዓይነት ቃላትን አንናገር፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍1410
#አንጨነቅ

በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡

ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
     🔸 @Z_TEWODROS

✍️Comment @Channel_admin09
15👍10🕊2
"ሥጋ በዝሙት እንደሚረክስ ኹሉ፥ ነፍስም በሰይጣናዊ አሳቦች፣ በእኩይ ሃይማኖትና በእኩይ ግብር ትረክሳለች፡፡ አንድ ሰው "በሥጋ ድንግል ነኝ" ቢል፥ ነገር ግን በወንድሙ የሚቀና ከኾነ እርሱ ድንግል አይደለም፡፡ ከቅናት ጋር ሩካቤ ስለ ፈጸመ ድንግልናውን አጥቷል፡፡ ውዳሴ ከንቱን የሚወድድም እርሱ ድንግል አይደለም፡፡ የቅናት ስሜት ክብረ ድንግልናውን አሳጥቶታል፡፡ ስሜት ወደ ውሳጤው ዘልቆ ገብቶ የነፍሱን ድንግልና አፍርሶበታልና። ወንድሙን የሚጠላም እርሱ ድንግል ከመኾን በላይ ነፍሰ ገዳይ ነው። በአጠቃላይ እያንዳንዱ ሰው በተገዛለት ክፉ ስሜት ድንግልናውን ያጣል። ስለዚሁ ምክንያትም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ኹሉ መቀላቀሎችን አራቀ የነፍሳችን ጸር የኾኑ ማናቸውንም አሳቦች ወደን ፈቅደን ባለመቀበል ደናግል እንድንኾን አዘዘን።

እንግዲህ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ልንናገረው የሚገባን ምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ምሕረት ልንቀበል የምንችለው እንዴት ነው? ልንድን የምንችለውስ እንዴት ነው? ጸሎትንና የጸሎት ፍሬዎች የኾኑትን እነርሱም ትሕትናንና የውሃትን ዘወትር ለራሳችን እንያዝ ብዬ እነግራችኋለሁ። እርሱ “ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ" ብሎአልና (ማቴ.11፥29)። ክቡር ዳዊትም፦- “የተሰበረን መንፈስ ለእግዚአብሔር ሠዋ፤ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም” ብሎአል (መዝ.50፥17)። እግዚአብሔር ከተሰበረ፣ ትሑት ከኾነና ከሚያመስግን ልብ በላይ አጥብቆ የሚወድደው የለምና።

ስለዚህ ወንድሜ! አንተም ያላሰብከውና የሚያናውጽ መከራ ቢገጥምህ መጠጊያ ይኾኑህ ዘንድ ሰዎችን እንዳትመለከት፤ ዘላቂና ቋሚ ያይደለ እርዳታን እንዳትፈልግ ተጠንቀቅ። ይልቅ ኹሉንም ናቃቸው፤ በአሳብህም መድኃኒተ ነፍሳት ወደ ኾነው ወደ እግዚአብሔር ተፋጠን። ልባችንን መጠገን (መፈወስ) የሚቻለው ልባችንን ብቻውን የሠራ (የፈጠረ) እና ግብራችንን ኹሉ የሚያውቅ እርሱ ብቻ ነውና (መዝ.32፥15)። ወደ ሕሊናችን ጓዳ መግባት፣ አሳባችንን መመርመር ልባችንንም ማጽናናት ሥልጣን (ኃይል) ያለው አርሱ ብቻ ነውና። እርሱ ልባችንን ካላጽናና ሰዎች ኹሉ የሚያደርጉልን ነገር ትርፍና ረብ የለሽ ነውና። እግዚአብሔር ሲያጽናናንና ሲያረጋጋን ግን እንደ ገና ሰዎች ቍጥር በሌለው መከራ ቢያውኩንም በፍጹም እኛን መጉዳት አይቻላቸውም፤ እርሱ ልባችንን ጽኑዕ ሲያደርግ ማንም እኛን ለማነዋወጽ ኃይል የለውምና።"

(ንስሓ እና ምጽዋት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 73-74 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
9👍6
#ከጠላት_ፈተናዎች_ተጠንቀቅ

ዲያቢሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ ብቻ የተደረገ ቁጣና ጠላትነት አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርም ጠላት ነውና በእኛ ላይ ሚደርሰው መከራ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ተቃውሞ ነው። ዲያቢሎስ እግዚአብሔርን ማጥቃት ባለመቻሉ ፍጥረታቱን በማታለልና ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ቅጣት እንዲገቡ በማድረግ ሊበቀለው ይጥራል።

የተወደድኸው ሆይ! ይህንን ነገር አስተውል! ዲያቢሎስን ስትቃወመውና ስትዋጋው ክፉን ነገር ከእናንተ እያራቅህ ብቻ አይደለም ፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየተዋጋህ ነው፡

ስለዚህም የክፉውን ዲያቢሎስ ማማለያና መደለያ በመቀበል እግዚአብሔርን ከማሳዘን ይልቅ ፈተናውን በጽናት ስትታገል በውጊያው ላይ ብትሞት ይሻልሃል፡

ለአፍታም ቢሆን ለብቻህ እየተዋጋህ እንደሆነ አድርገህ አታስብ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ ድል መንሣትን ይሰጥሃል። "አቤቱ አምላክ ሆይ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ። ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቈጣው? በልቡ አይመራመረኝም ይላልና።” (መዝ. ፲ ፥፲፪፣፲፫ ) "ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ። ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።" (መዝ. ፴፭፥፪-፫)

"አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ እስራኤልም የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙሀም፥ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። (ኢሳ. ፵፫፥ ፩-፪)

በነፍሳችን ላይ ደካማነትን እስካላየ ድረስ ስይጣን አያጠቃንም፡፡ ጎበዝ አዳኝ ወፎችን ለማደን እንደሚያደርገው ዲያቢሎስም ወጥመዱን ለማስገባት ሁልጊዜ ከእኛ ላይ ቀዳዳን ይፈልጋል። ብዙ ጊዜም ይይዋጋናል፣ ይሸነግለናል፣ በምኞቶቻችንም እየገባ ያገኘናል።

አዳምን በሔዋን፣ ሶምሶንን በምወድደው ደሊላ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በእንግዶች ሴቶች ፍቅር፣ የአስቆሮቱ ይሁዳንም በገንዘብ ፍቅር እንደጣላቸው አላየህም? ስለዚህ እንደ ጎበዝ ሐኪም ሁን፣ ጉድለትህንና ሕመምህንም አክም፣ ኩራትህን በትሕትናና በየዋህነት ድል አድርገው፣ የትዕቢት በሽታህንም አንተነትህን በመናቅ ፈውሰው። በተአምራትና በታላቅ ነገሮችም ከመመካት ተጠበቅ፤ ምክንያቱም ዲያቢሎስ ራሱ በብርሃን መልአክ መመሰል ይችላል። በስብ ውስጥ መርዙን ሊከት፣ በማጥመጃው ዘንግ ውስጥም የመደለያ ጣፋጭ ምግብን ሊያደርግና መልካምና ጠቃሚ ነገር ይከተላል ብለህ እንድታምን ሊያታልልህ ይችላል። አንተ ግን ፈጽሞ አትታለል፣ በከንቱም አትነዳ። ይልቅስ ከዲያቢሎስ ጥቃት ትጠበቅ ዘንድ ሁሉን ነገር አስተውልና መርምር።

ይሁዳ ጌታውን አልከዳምን? ኢዮአብስ ወዳጅና የሚታመን ሰው መስሎ አሜሳይን አልገደለውምን? (፪ነገሥ. ፳፥፱) በእግዚአብሔር ታመን! ከመሪ በላይ አጥብቀህ ያዘው፤ ሁሉን ነገር ወደ እርሱ አምጣው፡፡ ድጋፍህና መጠጊያህ አድርገው፤ እርሱን ሁለንተናህ አድርገው፡፡

#ሊቀ_ዲያቆናት_ሀቢብ_ጊዮርጊስና_ስራዎቹ ገጽ 43-45
Deacon Henok Haile

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍83😢1
#ጳጉሜን

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡

ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ ጳጉሜን ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃች ትለያለች፡፡ ጳጉሜን በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ በዘመነ ሉቃስ ማብቂያ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 15 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡

የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
10👍3
#ጳጉሜን

ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ  “ሄፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መሆኑን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተነግሯል፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ (ምንጭ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፱፻፭)፡፡ ምዕራባዊያኑ ጳጉሜን  ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል፡፡ እኛ ግን የወር ተጨማሪ አድርገናታል፡፡ በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ትባል እንጂ ሊቃውንት ግን ተረፍ ይሏታል፡፡ ጳጒሜን የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደሆነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመሆኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ ይውላል፡፡

የጳጉሜን ወር ‹‹የምሕረት ወር›› ስለመባሏ፡-
ኢትዮጵያ በዓለም ብቸኛዋ የ፲፫ ወራት ጸጋ ባለቤት ስትሆን የጳጉሜን ወርም በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምሕረት ወር ተብሎ ይታመናል። በተለይም  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ጸሎት የሚያደርግበት ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበት የምሕረት ወር መሆኑን ታስተምራለች፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት ምእመናኑ በጳጉሜን ጸበል በመጠመቅ ድኅነት በማግኘታቸው የምሕረት ወር መሆኑን ምእመናን ያብራራሉ፡፡

የጳጉሜን ወር በጸሎት በንስሓ ተወስነን ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርባት ድልድይ ናት፡፡ ከዚህም የተነሳ  እግዚአብሔር የፈቀደላቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጸሎት በመጸለይ ጸበል በመጠመቅ ያስቧታል፡፡  በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው ሲሆን መሠረት የሚደረገውም ጾመ ዮዲት ነው፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ ይህን መሠረት አድርገው ሕዝቡ ሳይቀር “ጳጉሜን ዕድሜ ትሰጠናለች፤ በኋላም ታድነናለች” ብለው ጾም ይጾሙባታል፡፡ (ምንጭ-ቅዱስ መልከ ጸዴቅ ድርሳን)፤ በሀገራችንም ንግሥት ዘውዲቱ እና ምኒልክ የጾም ሥርዐት ይፈጽሙባት ነበር፡፡ ሌሎችም ሽማግሌዎችና ባልቴቶች አክብረው ይጾሙባታል፡፡ የጳጉሜንን አቆጣጠር አንዱ ከቀን ጋራ ሲደርገው፣ ሌለኛው ደግሞ ከወር ጋራ ቢያደርገውም በሁሉም አቆጣጠር ውስጥ ሕያዊት ሆና መገኘቷ የታወቀ ነው፡፡

የዐውደ ዓመት መሸጋገሪያ ናት፡፡
ይህም ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ መሸጋገሪያ ናት፡፡ ጳጉሜን የዓመቱ መጨረሻ ወር ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜ አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ ናት፡፡ ስለሆነም አዲሱ ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የልማት፣ የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆንልን በጾምና በጸሎት ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ነገረ ምጽ አት የሚታሰብባት ናት፡፡
የጳጉሜን ወር የነገረ ምጽአት የሚታሰብባት ስትሆን ምጽአት ማለት የጌታን መምጣት የሚያስረዳ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የጌታን ምጽአት በዓመት ሁለት ጊዜ ታስታውሳለች፤ ይኸውም በጳጉሜን ወርና በጌታ ጾም እኩሌታ (በደብረ ዘይት) ነው። ቅዱስ ዳዊት ”እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነዳል፤” እንዲል፤(መዝሙረ ዳዊት ፵፱ ፣ ፪-፬)፡፡  ይህ ስለ ነገረ ምጽአት ያስረዳል፡፡

ይህም ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገሪያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፣ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፣ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ናትና ነው፡፡ ጳጉሜን የክረምቱ ማብቂያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም በመጨረሻው ዘመን መከራ የሚበዛበት የዚህ ዓለም ማብቂያ ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜን አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ጻድቃን አዲሲቷን ምድር (መንግሥተ ሰማያትን) ለመውረስ ተዘጋጅተው “ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን የእግዚአብሔር መንግሥት ውረሱ” የሚባሉባት ቀን ናት፡፡ የጌታ አመጣጥ ሳይታሰብ ነውና በተሰጠን ጸጋ ቅዱስ አምላካችንን እያመሰገንን ተዘጋጅተን እንድንጠብቀው  የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን፤ ቀጣዩ ዘመንም ቃሉን ፈጽመን መልካም ፍሬ የምናፈራበት ዓመት ይሁንልን፤ አሜን !!!
(ማኅበረ ቅዱሳን)
(ይቀላቀሉ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍155
[ጳጉሜን 3 በዓሉ የሚከበርለት የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ታሪክ]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::

ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡

ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡

አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ ስለነዚኽ መላእክት ፡-

“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ
መካነ ትጉሃን ዐጸዱ ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ”

(ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ (ባሕርዩ) በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ) ይላል

ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤ ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡-

“ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” እንዲል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)።

ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)።

እነዚኽ ከሰራዊተ ሩፋኤል የወጡ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል።

“ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡

ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ
★ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው የሩፋኤል ሰራዊት ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡

ይኽ መልአክ ሩፋኤል ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይኽ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይኽ ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ፋንድያ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “አይቴ ውእቱ ምጽዋትከ ወጽድቅከ” (በጐነትኽ ምጽዋትኽ ያዳነኽ ወዴት ነው?) በማለት በተናገረችው ጊዜ ዐዝኖ ሞትን ተመኘ (ጦቢ ፪፥፲፬)፡፡

ያን ጊዜ መልአኩ ሩፋኤል ባሎቿ ስለሞቱባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ለማዳን ተልኮ በመምጣት አስቀድሞ በርሷ ላይ ዐድሮ ባሎቿን ይገድልባት የነበረውን ጋኔን አስወጥቶላት የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፤ በዚኽም “ፈታሔ ማሕፀን” ተብሏል "ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማሕፀኖሙ አንተ" እንዲለው፡፡

በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት “አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምነ ሰብዐቱ ቅዱሳን መላእክት” (ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ) ብሏቸው ተሰውሯል (ጦቢ ፲፪፥፲፭)፡፡

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
[የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ይደርብን]

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
     🔸 @Z_TEWODROS

✍️Comment @Channel_admin09
👍131🕊1
በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደበረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ፥ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም!

“እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለ ኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ፥ ፈጽመው ሊወገዱ እንደማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም፥ ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍11❤‍🔥61
ተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ከማሳዘን ውጪ ምንም ይኹን ምን [አንፍራ፡፡] ሠለስቱ ደቂቅ የሚንበለበል እሳት በፊታቸው ቢያዩም ናቁት፤ ኃጢአትንም ብቻ ፈሩ፡፡ በእሳቱ ቢቃጠሉ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር እንደሌለ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባይገኝባቸው ግን እጅግ የከፋ ጉስቁልና እንደሚያገኛቸው ያውቃሉና፡፡ ምንም ሳንቀጣ ብንቀርም እንኳን እጅግ ትልቁ ቅጣት ግን ኃጢአት መሥራት ነው፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም ያህል ቅጣት ቢያገኘንም እጅግ ትልቁ ክብርና ጸጥታ ግን በተጋድሎና በምግባር ሕይወት መኖር ነው፡፡

እግዚአብሔር ራሱ፡- “በደላችሁ በእናንተና በእኔ መካከል አልለየችምን?” ብሎ እንደ ተናገረ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል (ኢሳ.59፡2)፡፡ ቅጣት ግን “እግዚኦ አምላክነ ሰላመ ሀበነ እስመ ኵሎ ወሀብከነ - አቤቱ አምላካችን ኹሉን ሰጥተኸናልና ሰላምን ስጠን” እንደ ተባለ ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል (ኢሳ.26፡12)፡፡

እንበልና አንድ ሰው ቁስል ወጣበት፡፡ የሚያስፈራው የትኛው ነው - የሚሰፋው ቁስል ወይስ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ቢላ? ብረቱ ወይስ እጅግ እየባሰበት ያለው ቁስል? ኃጢአት የሚሰፋ ቁስል (Gangrene) ነው፤ ቅጣት ደግሞ የቀዶ ጥገናው ሐኪም ቢላ ነው፡፡ ያልፈረጠ የሚሰፋ ቁስል ያለው ሰው ሕመሙ እንዳለበትና ለወደፊቱም የማያፈርጠው ከኾነ ሥቃዩ እየባሰበት እንደሚኼድ ኹሉ፥ ቅጣት ያላገኘው ኃጢአተኛ ሰውም ከሰዎች ኹሉ ይልቅ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፤ ለወደፊቱ ጭራሽ ቅጣትና መከራ የማያገኘው ከኾነ ደግሞ ከአሁኑ ይልቅ እጅግ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፡፡ የጣፊያ ወይም የሆድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ መብል ቢበሉ፣ ቀዝቃዛ መጠጦችን ቢጠጡ፣ የተለያዩ ዓይነት ጣፋጭና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው መብሎችንም ቢወስዱ ይህ ድሎት ሕመማቸው እንደሚጨምረውና እንደ ሕክምናው ሕግ ራሳቸውን ከመብሉም ከመጠጡም በመጠኑ ቢወስዱ ግን የመዳን ተስፋ ሊኖራቸው እንደሚችል ኹሉ፥ በክፋት ዓዘቅት የሚኖሩ ሰዎችም ቅጣት ካገኛቸው በጎ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከክፋታቸው ጋር አብረው ዝንጋዔንና ድሎትን የሚጨምሩበት ከኾነ ግን ሆዳቸውን ከሚያማቸው ሰዎች በላይ እጅግ ጐስቋሎች ሰዎች ናቸው - ደዌ ዘነፍስ ከደዌ ዘሥጋ ይልቅ የከፋ ነውና፡፡ ተመሳሳይ ኃጢአት እያላቸው አንዳንዶቹ በማጣትና በብዙ ሕመም ሲሠቃዩ፣ ሌሎቹ ግን እስኪበቃቸው ድረስ እየጠጡና እየተስገበገቡ የሚበሉ እየተመቻቸውም በደስታ የሚኖሩ ሰዎችን ብትመለከት እነዚያ መከራ የሚቀበሉት የተሻሉ እንደ ኾኑ አስተውል፡፡ በእነዚህ መከራዎች የተወገደላቸው የፈንጠዝያ ሕይወት እሳት ብቻ ሳይኾን ሊመጣ ወዳለው ፍርድና አስፈሪ ዙፋን ሲኼዱም ከቀላል ዕረፍት ጋር አይደለምና፤ ስለኾነም እዚያ ሲኼዱ ከኃጢአታቸው የሚበዛውን በዚህ ዓለም ባገኛቸው ሥቃይ አስወግደው ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍19🕊21
መስከረም 1 - ርዕሰ አውደ ዓመት

በግዕዝ አውደ ዓመት ይባላል - ርዕሰ አውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ አውደ ዓመት ተባለ። በአማርኛ ደግሞ እንቁጣጣሽ፣ የዘመን መለወጫ ወይም ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል፡፡ የዘመን መለወጫ የሚለው ግልፅ ስለሆነ ሁለቱን ስያሜዎች ለየብቻ እንመልከታቸው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ የተሰየመው በነቢዩ ዘካሪያስ ልጅ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንጂ በሐዋርያው/ ወንጌላዊው ዮሐንስ አለመሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በብሉይና አዲስ ኪዳን መካከል የነበረ እና "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ የኖረ፣ በመጨረሻም በሔሮድስ ትዕዛዝ ራሱን የተቆረጠ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡

በዚህም ምክንያት የቤተክርስቲያን አባቶች የበዓላትን ስርአት ሲሰሩ፣ ይህ በዓል ለመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ መታሰቢያ እንዲሆንና በእሱ ስምም እንዲጠራ በመወሰናቸው ነው፡፡

ዕንቁጣጣሽ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉና ተራ በተራ እንያቸው፡፡

አንደኛው በኖህ እና በልጆቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን፡፡ ሴም፣ ካምና ያፌት ሶስቱ የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ኖህ አህጉራትን ለሶስቱ ልጆች አከፋፍሎ ሲሰጥ ለካም አፍሪካ ደረሰው፡፡ ካም ወደ አፍሪካ የገባው እና መጀመሪያ የረገጠው ኢትዮጵያን ሲሆን ወሩም ምድሪቱ በአደይ አበባ ያሸበረቀችበት የመስከረም ወር ነበር፡፡ በምድሪቱ ውበት በመደመሙና ይህ ዕጣም ለእሱ ስለደረሰው ተደስቶ “ዕንቁ ዕጣ ወጣልኝ” አለ፡፡ እንግዲህ እንቁጣጣሽ ለሚለው ቃል አንዱ የየት መጣ ሀሳብ /Etymology/ እንዲህ የሚል ነው፡፡

ሁለተኛው ምድሪቱ በአደይ ፈክታ ሲመለከት “ዕንቁ ዕፅ አወጣሽ” ከሚል ነው እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ የመጣ የሚል ነው፡፡

በዚህኛው አካሄድ “ዕንቁ” ከኦይስተር ቅርፊት /pearl/ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ድቡልቡል፤ ጠንካራ አንጸባራቂ፤ ነጭ ውድ ጌጥ/ ለጌጥነት የሚያገለግል ነገር/ ሲሆን “ዕፅ” ደግሞ በግዕዝ የአማርኛው “ተክል” አቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክሉን መልክ ከዕንቁ ጋር በማነጻጸር የምድሪቱን ውበት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡፡

ሶስተኛው ደግሞ የቀዳማዊ ምኒሊክ እናት ንግስት ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሄደችበት ጊዜ ንጉሱ “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ” ብሎ መስጠቱን መሰረት አድርጎ የሚነሳ ሃሳብ ሲሆን ወሩም ወርሃ መስከረም ነበር።

#ቀሲስ_ንዋይ_ካሳሁን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍216
“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” መዝ 65፥11

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን እንደ ኃጥአታችን ያይደለ እንደቸርነቱ የንስሃ ጊዜ የፍሬ ጊዜ ሰጥቶናልና እናመሰግነው ዘንድ ይገባናል፡፡ ምስጋናችንም ይህን የተወዳጅ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል በመተግበር እንግለፅ፡፡

“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌ 4፥22

መልካም አዲስ አመት!
🌻🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌻
👍4115🕊2❤‍🔥1
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡

ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍113
መስከረም 2፡ ምትረተ ርዕሱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

“ለአንተ ልትሆን ዘንድ አልተፈቀደም” (ማቴ.14፥4፣ ማር. 6፥18)

የጌታ መንገድ ጠራጊ፣ ሐዋርያ፣ ካህን፣ ነቢይ፣ መምህረ ንስሐ፣ ሰማዕት እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድምህ ሚስት ለአንተ እንድትሆን አልተፈቀደም ቢለው ወደ ወህኒ በጷጉሜን 2 ቀን አስገባው።

በመስከረም 2 ቀንም ሄሮድስ የልደት በዓሉን ሲያከበር የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት የነበረችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅ (ወለተ ሄሮድያዳ) በዘፈኗ አስደሰተችው። የፈለገችውንም ስጦታ እንደሚሰጣት ቃል ገባላት እርሷም ከእናቷ ተማክራ የኦሪትና የሐዲስ ኪዳን ድልድዩን የቅዱስ ዮሐንስን አንገት እንዲሰጣት ጠየቀች።

ሄሮድስ ምንም እንኳን ገዳሚዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ እንደሆነ ቢያውቅምና እርሱን ቢገድለው ሕዝቡ ሁሉ ቅዱስ ዮሐንስ ሰባኬ ወንጌልና ባሕታዊን ይከተሉት ስለነበር ለጊዜውም ቢሆን ቢጨነቅና ቢፈራም የኋላ ኋላ ግን የእርሱን ክብርና ቃል አስበልጦ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን አንገት አስቆርጦ ሰጣት።

በድነ ሥጋውን ግን ቅዱሳን ሐዋርያት በክብር ቀብረውታል። (ማቴ.14፥1-12፣ ማር.6፥14-30) ራሱ ግን ከእነ ሄሮድያዳ እጅ አምልጣ ለ15 ዓመታት ያህል አስተምራለች። በዚህም ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ራሱ የተቆረጠበት ዕለት ስለሆነ በልዩ ሁኔታ ታስበዋለች።

የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓላት
መስከረም 26፡ በዓለ ጽንሰቱ
ሰኔ 30፡ በዓለ ልደቱ
መስከረም 2፡ ራሱ የተቆረጠበት
መስከረም 15፡ ነፍሱ ከራሱ የወጣችበት
የካቲት 30፡ ራሱ የተገኘችበት
ሰኔ 2፡ ራሱ በኤልሳዕ መቃብር የተቀበረበት
መስከረም 1፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ

የመጥምቀ መለኮት ረድኤት በረከቱን ያሳድርብን። የዓመት ሰው ይበለን። አሜን።

የመስከረም 2 ዓመታዊ በዓላት:
ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
ቅዱስ ዳስያ ሰማዕት
ቅዱስ ዲዲሞስ ሰማዕት
ቅድስት መሪና

የመስከረም 2 ወርኃዊ በዓላት:
ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት)
ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
ቅዱስ አቤል ጻድቅ
ቅዱስ አባ ጳዎሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
አባ ሕርያቆስ ዘሀገረ ብሕንሳ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

ምንጭ: የመስከረም 2 ቀን ስንክሳር
መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍184🕊1
#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

#ተወዳጆች_ሆይ! አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

#ልብ_በሉ! ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

#ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን? እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍178
2025/07/14 21:47:17
Back to Top
HTML Embed Code: