Telegram Web Link
እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡

#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍144
በዚህ ዓለም ሳለን የእኛ ማዕረግ የሚወሰነው እንደ እድሜያችን እንደ ተሰጥኦአችን ወይም እንደ ችሎታችን ነው።
በዘላለማዊው ሕይወት ግን ማዕረጋችን የሚወሰነው እግዚአብሔርን የበለጠ በምታውቅ ልብ ነው። ምናልባት ብዙዎች የተናቁ የተጠሉና ችላ የተባሉት እነዚያ ተሰጥኦ ወይም ሥልጣን ያላቸውን ሊበልጧቸው ይችላሉ።
ስለዚህ ታናናሽ የተባሉትን በሙሉ እንዳትንቁ ይሁን። እግዚአብሔር ኢያሪኮን ለማዳን በወደደ ጊዜ የመረጠው ጋለሞታዋን ረዓብን ነበር። ከዚህ የተነሳ ረዓብ በጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ ከተጠቀሱት የእግዚአብሔር ሰዎች መካከል አንዷ ሆና እንድትቆጠር ሆኗል። /ማቴ 1፥1 ጀምሮ/ ያለፈው ሕይወቷ ስለ ተረሳና ቅድስት ስለ ሆነች ለሚያስታውሳት ሁሉ ሕያው ምሳሌ ወይም አርአያ ሆናለች።


እግዚአብሔር ጋለሞታዋንና አጋንንት የነበሩባትን ሴት ምን ያህል እንደተከባከባት ስትመለከት ልትደነቅ ትችላለህ። እርሱ እንዲህ ያለውን እንክብካቤ ለተናቁት ለተጠሉትና ምንም ዓይነት ነገር አይገባቸውም ለተባሉት ሁሉ ያደርጋል። /1ኛ ቆሮ 1፥27-28/

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍20🕊4
የወልድ ፍቅር!!
(ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ)

ባሕርይውን ዝቅ ብሎ የታየው ከሁላችንም በላይ ከዘመናት ሁሉ አስቀድሞ የነበረው ነው፤ ይህ ሰው የሆነው ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ የሚኖረው ነው፡፡ የሆነው ሁሉ በእርሱ የተደረገ ነበር፤ የሆነው ሁሉ የተደረገው በምክንያት ነበር፡፡ ያለ ምክንያት የተደረገ አንዳችም ነገር የለም፡፡ እርሱም ለሰው ልጆች ዘላለማዊ ዋስትና ሲባል የተደረገ ነው፡፡ እርሱ ከመጀመርያው ያለ ምክንያት ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር ሀልዎትስ ምን ምክንያት ይኖረዋል! ነገር ግን በምክንያት እርሱም የሰው ልጅን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ሥጋ ለብሶ ሰው ሆነ፤ የተፈጸመውም የእኛ ድኅነት ነው፡፡ ያዋረድነውን እግዚአብሔርነቱን፣ የናቅነውን መንግሥቱን፣ ያቃለልነውን ወገኖቹ ሊያደርገን ስለዚህ የእኛ ባሕርይን ነሣ፡፡ ሥጋ ዝቅ ያለ ሲሆን እግዚአብሔርን ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም የሰው ልጅ ሆነ፡፡በሥጋ ከድንግል ተወለደ፡፡
አስቀድሞ ግን ከባሕርይ አባቱ ከዘላለም የተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፡፡ ከሴት ተወለደ፤ ነገር ግን ድንግል ነበረች፡፡
የመጀመርያው ሰው ሁለተኛው መለኰት ነው፤ ሁለት ባሕርያት ያሉት አይደለም፡፡ በፍጹም ተዋሕዶ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነ እንጂ፡፡ ሰው እንደ መሆኑ አባት የለውም፤ አምላክ እንደ መሆኑ እናት የለውም፡፡ በማሕጸነ ድንግል ተወሰነ፤ በነብያቱ አፍ አምላክነቱ ተመሰከረለት፡፡ ነቢያቱ ብቻ የመሰከሩ አይደለም፤ አብም የምወደው ልጄ ነው አለ፤ እርሱም አባቴ ነው አለ እንጂ፡፡
ሰው እንደ መሆኑ በጨርቅ ተጠቀለለ፤ አምላክ እንደ መሆኑ የተገነዘበትን ጨርቅ ጥሎት ተነሣ፡፡ በበረት ላይ ተኛ፤ መላእክቱ ግን አመሰገኑት፡፡ ወደ ግብጽ ተሰደደ፤ በዚያ የነበሩትን የሐሰት አማልክተ ግብጽን ግን እንዲሰደዱ አደረገ፡፡ በአይሁድ አለቆች ዘንድ ደም ግባት አልነበረውም፤ በዳዊት ዘንድ ግን ውበቱ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው፡፡ …እንደ ሰው ተጠመቀ፤ ኃጢአትን ይቅር የሚል ግን እርሱ ነው፡፡…ተራበ፤ ፍጥረትን የሚመግብ ግን እርሱ ነው፡፡ …ደከመ፤ ደካሞችን ከሸክማቸው የሚያሳርፍ ግን እርሱ ነው፡፡ ደክሞት አንቀላፋ፤ እስራኤልን የሚጠብቅና የማይተኛው አምላክ ግን እርሱ ነው፡፡ ግብርን ለቄሳር ከፈለ፤… ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤን የተቀበለ ግን እርሱ ነው፡፡ ሳምራውያን ጋኔን አለብህ አሉት፤ እርሱ ግን አጋንንትን
ያወጣል፡፡… አይሁድ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ፤ ነገር ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡ ጸለየ፤ ጸሎትንና ምልጃን የሚቀበል ግን እርሱ ነው፡፡ አለቀሰ፤ የሰዎችን እንባ የሚያብስ ግን እርሱ ነው፡፡ እጅግ ርካሽ በሆነ በሰላሳ ድራም ተሸጠ፤ ዓለምን እጅግ ውድ በሆነ ደሙ የገዛ ግን እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ እውነተኛው የበጎች እረኛ ግን እርሱ ነው፡፡ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ አፉን አልከፈተም፤ ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ግን እርሱ ነው፡፡ ወንጀለኞችን ይፈውስ ዘንድ ከወንጀለኞች ጋራ ተሰቀለ፡፡ ሞተ፤ ሕይወትን የሚሰጥ ግን እርሱ ነው፡፡ ወደ ሲዖል ወረደ፤ ነገር ግን ነፍሳትን ይዞ ወጣ፡፡ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በታላቅ ምስጋና ይመጣል፡፡

አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበን፡፡ አሜን!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍28❤‍🔥61
እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና_ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡

#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍168
#ንስሓ_የማያድነው_ኀጢአት

ከእግዚአብሔር ምህረት ቸርነት። ከእመቤታችን በስተቀር ከሰው ኀጢአት አይታጣም።

የዘመናችን የአጥማቅያን ቡድን አድናቂዎች እና ተከታዮች ሳያውቁት እና ሳይመስላቸው አምልኮተ ሰብእ እየፈጸሙ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ንስሓ የሌለው ኀጢአት ነው። ንስሓ የማያስተሰርየው በደል ኑሮ አይደለም፦ የጻድቅ ተከታይ ስለሆነ ጻድቃንን ይዘነጋል የእሱ ጻድቅ ከፊቱ ያለው አያ እንተና ብቻ ነው።

የፈዋሽ ተከታይ ስለሆነ ፈውሰ ነፍስ አያስፈልገውምና። ለፈውስ ደጅ የሚጠናው አቶ እንተናን ነው። የቅዱስ አጥማቂ ቸከታይ ስለሆነ ቅድስና አያስፈልውምና። የካህን ፊት እንዳያይ መተተኞች ጠንቋዮች እያሉ የልብ ጆሮውን ይዘጉበታል። ንስሓቸውን የጨረሱ ፈዋሾች ተከታይ ስለሆነ እነሱን በማገልገል ጊዜውን ያባክናል።

በፍርሀት ልቡናው እንዲርድ ጋኔን ወረረህ አሠረህ ተበተበህ እያሉ መውጫ ቀዳዳ ያሳጡታል። ሳያውቀው ያመልካቸዋል። ምክንያቱም እነሱ ከሌሉ በሕይወት የማይኖር ይመስለዋል። የዛር አድናቂ የልብ ተመጻዳቂ ያደርጉታል። ጻድቅ ሲባል አቶ እንተና ነው ትዝ የሚለው።
የማያድን ለንስሓ የማያበቃ ተከታይነት ይሄ አይደለምን??

አሁን አሁን ክፍት የሥራ ፈጠራ መንገዶች አራት ናቸው፦
#ባህታዊነት#አጥማቂነት#ሰባኪነት#ዘማሪነት ናቸው።

#ማንም ተነሥቶ ስማ ወገን ዓለም ሊናድ ነው ከበረሃ የመጣ መልእክት ነው... ካለ ባህታዊ እንተና ይሆናል። እውነተኛ ነው? ከየትኛው በረሀ? ከየትኛው ገዳም ማለት የለም መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

#ማንም ተነሥቶ ውጣ ልቀቅ ምናምን ቅብጥርጥር ካለ አጥማቂ እንተና ይሆናል። በዛር ነው? በእግዚአብሔር? መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

#ማንም ተነሥቶ ጎርነን ባለ ድምጽ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ...ካለ ሰባኪ እንተና ይሆናል። ተምሯል?አልተማረም? መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

#ማንም ተነሥቶ ያላንተ ለኔ፣ ካመድ ያነሣኸኝ...ካለ ዘማሪ እንተና ይሆናል። ሦስቱን የዜማ ልኮች ጠብቋል?አልጠበቀም? መከተል ነው እንጂ ማን ያጣራዋል።

አያችሁ? በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ ሆነና ይነዱን ጀመር። ሰውን የእውር አፍጣጭ የጨለማ ገልማጭ አደረጉት።
ለንስሓ የማያበቃ በደል ይሄ አይደለ?

(#መምህር ገብረ መድኅን እንየው)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍233
380ካሬ ዲጂታል ካርታ ያለዎ ለመኖሪያ ለስራ የሚሆን
አድራሻ ኮተቤ ኮሌጅ
ዋጋ 85,000,000
ድርድር አለው

የወር ገቢ 80,000 በላይ
ውስጡ ጂ+3 ፎቅ እና ጂ+1 ሰርቪስ ያለው

ፈጥነው ይደውሉ

📞 0943166027
📞 0914243082
በቴሌግራም @business_251 ያናግሩን
👍9😢4🕊1
🌿❤️ አቡነ አረጋዊ ታሪክ ባጭሩ 🌿❤️

አረጋዊ ማለት ያረጀ፣የሸመገለ ፣ አዋቂ ትልቅ ሰው ማለት ነው:: አባታችን ይህ ስም የተሰጣቸው ገና ልጅ እያሉ ነበር ለምን ይሆን?
🌿❤️ አባታችን አቡነ አረጋዊ ከተሰሐቱ ቅዱሳን (ከሮምና ኤሽያ ከመጡት ከ9 ቅዱሳን አባቶች
አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበር፡፡ እናታቸው ንገሰተ እደና ትባላለች፡፡
የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ይባል ነበር፡፡ የሚካኤል ማለት ነው ፡ ጥበብ መንፈሳዊ ሲማሩ
🌿❤️ አድገው ወደ እሰክድርያ ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ
እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውነ አውቀው መዓርገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
የንጉስ ልጅ መባልን የንጉስ አልጋ ወራሽነትን ሸሽተው የሞቀ ቤተ ሰቦቻቸውነ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው
🌿❤️ በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አበምኔቱም ወደዚህች የሕይወት መንገድ ስለመራህን
ብፁህ አረጋዊ መባል ይገባሃል ፡ ብለው የበሰለ አስተሳሰባቸውን መሠረት አድርገው ገና አንድ ፍሬ ህፃን እያሉ አረጋዊ ተብለው ተጠሩ፡፡
🌿❤️ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ
🌿❤️ በአራተኛ መዐረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል። በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት
ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ሲያስተምሩ የሀገራችንን ዜና ሰምተው ለመምጣት
በ480 ዓ.ም መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በክነፉ
🌿❤️ ተሸክሞ አክሱ አድርሷቸዋል፡፡ ተመልሶ ሄደው ስለ ኢትዮጵያ ቅድስት ሀገር
መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው
ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱ ሁሉ ጓዛቸውን ጠቅልለው
በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ
🌿❤️ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ራሳቸውን ዘጠኝ ሆነው
መጥተዋል፡፡ለቅዱሳኑ መምጣት ዋነኛው ምክንያት ንጉስ አልሜዳ ያነሳውን የምንታዌ(የሁለት በህሪ)ትምህርት በመቃወማቸው የደረሰባቸውን የነገስታት ጫና ለመከላከል ሲሉ ነው፡፡ የአባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀመዝሙራቸውን ማትያስን
🌿❤️ አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሱ፡፡
ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ
ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ
አድሮ በመዝሙር 90/91፡11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ
መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው
ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ
ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡
ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው
አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት
በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ
ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ቅዱሳን መላእክት ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላች ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላ
ግን ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት
🌿❤️ ተሰብስበውላቸዋል፡፡ ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ
ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ
መንግስቴን አወርሰሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ
አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ
ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም
ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው
🌿❤️ ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ
እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል፡፡

በረከታቸው፣ ቃልኪዳናቸው፣ አማላጅነታቸው
በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ ፀንቶ ይደር .......አሜን።

ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3317
#ከጠላት_ፈተናዎች_ተጠንቀቅ!

ዲያቢሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ ብቻ የተደረገ ቁጣና ጠላትነት አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርም ጠላት ነውና በእኛ ላይ ሚደርሰው መከራ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ተቃውሞ ነው። ዲያቢሎስ እግዚአብሔርን ማጥቃት ባለመቻሉ ፍጥረታቱን በማታለልና ከእርሱ ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ቅጣት እንዲገቡ በማድረግ ሊበቀለው ይጥራል፡፡

የተወደድኸው ሆይ! ይህንን ነገር አስተውል! ዲያቢሎስን ስትቃወመውና ስትዋጋው ክፉን ነገር ከእናንተ እያራቅህ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየተዋጋህ ነው፡፡ ስለዚህም የክፉውን ዲያቢሎስ ዲያቢሎስ ማማለያና መደለያ በመቀበል እግዚአብሔርን ከማሳዘን ይልቅ ፈተናውን በጽናት ስትታገል በውጊያው ላይ ብትሞት ይሻልሃል፡፡

ለአፍታም ቢሆን ብቻህ እየተዋጋ እንዳለህ አድርገህ አታስብ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ ድል መንሣትን ይሰጥሃል፡፡ "አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቆጣው? በልቡ:: አይመራመረኝም ይላልና፡፡" (መዝ ፲ ፥ ፲፪ -፲፫) ጥሩርና ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።›› (መዝ. ፴፭፥፪-፫)

"አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ፡፡ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።" (ኢሳ. ፫፥፩-፪)

በነፍሳችን ላይ ደካማነትን እስካላየ ድረስ ሰይጣን አያጠቃንም፡፡ ጎበዝ አዳኝ ወፎችን ለማደን እንደሚያደርገው ዲያቢሎስም ወጥመዱን ለማስገባት ሁልጊዜ ከእኛ ላይ ቀዳዳን ይፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜም ይዋጋናል፣ ይሸነግለናል በምኞቶቻችንም እየገባ ያገኘናል፡፡

አዳምን በሔዋን፣ ሶምሶንን በምወድደው ደሊላ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በእንግዶች ሴቶች ፍቅር፣ የአስቆሮቱ ይሁዳንም በገንዘብ ፍቅር እንደጣላቸው አላየህም፡፡ ስለዚህ እንደ ጎበዝ ሐኪም ሁን፣ ጉድለትህንና ሕመምህንም አክም፤ ኩራትህን በትሕትናና በየዋህነት ድል አድርገው፣ የትዕቢት በሽታህንም አንተነትህን በመናቅ ፈውሰው፡፡ በተአምራትና በታላቅ ነገሮችም ከመመካት ተጠበቅ ምክንያቱም ዲያቢሎስ ራሱ በብርሃን መልአክ መመስል ይችላል፡፡ በስብ ውስጥ መርዙን ሊከት፣ በማጥመጃው ዘንግ ውስጥም የመደለያ ጣፋጭ ምግብን ሊያደርግና መልካምና ጠቃሚ ነገር ይከተላል ብለህ እንድታምን ሊያታልልህ ይችላል፡፡ አንተ ግን ፈጽሞ አትታለል፣ በከንቱም አትነዳ፡፡ ይልቅስ ከዲያቢሎስ ጥቃት ትጠበቅ ዘንድ ሁሉን ነገር አስተውልና መርምር፡፡

ይሁዳ ጌታውን አልከዳምን? ኢዮአብስ ወዳጅና የሚታመን ሰው መስሎ አሜሳይን አልገደለውምን? (፪ነገ. ፳ ፥ ፱)

በእግዚአብሔር ታመን! ከመሪ በላይ አጥብቀህ ያዘው፤ ሁሉን ነገር ወደ እርሱ አምጣው፡፡ ድጋፍህና መጠጊያህ አድርገው፤ እርሱ ሁለንተናህ አድርገው።

(#ሊቀ_ዲያቆናት_ሀቢብ_ጊዮርጊስና_ሥራዎቹ ገጽ 43-45 - Deacon Henok Haile)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍214
በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!

እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው።

በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው።

በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችኋል።

እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል።

በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍227❤‍🔥2
።።።።።።ጥቅምት 17።።።።።።
ሊቀ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
ጥቅምት ፲፯ (17) ሊቀ ዲያቆን ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ማዕረገ ዲቁናን በ ሐዋርያቱ እጅ በ አንብሮተ እድ የተሾመበት እለት ነው እንኳን አደረሳችሁ ።

አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው፦ የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን። ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤

እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።

በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም_በኋላ_እጃቸውን_ጫኑባቸው።
የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።

እስጢፋኖስም_ጸጋንና_ኃይልን_ተሞልቶ_በሕዝቡ_መካከል_ድንቅንና_ታላቅ_ምልክትን_ያደርግ_ነበር።

( የሐዋ 5 ፥ 2 - 8 )

የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን


ግራኝን ከእነ ሰራዊቱ ያሳደደው የቅዱስ እስጢፋኖስ ሰራዊት!

ግራኝ የተባለው አሕዛባዊ ዓመፀኛ በተነሣና በክርስቲያኖች ላይ ጦርነትን በዐወጀ ጊዜ በየአውራጃውና በየመንደሩ ፍጅትና ሁከት ሆነ።

ግራኝም የረከሰች ሃይማኖታቸውን ያልተቀበለውን ኹሉ እንዲገድሉ ለሰራዊቱም ኹሉ ትእዛዝ ሰጠ። ብዙዎች ክርስቲያኖችም በግፍ በጭካኔ በሰይፍ ተገደሉ። በእሳትም የተቃጠሉ አሉ፤ በመጋዝ የተሰነጠቁ አለ፤ ወደጥልቅ ጉድጓድ ተጥለው የሞቱ አሉ፤ ከየመንደራቸውም ወጥተው ወደተራራዎችና ዋሻዎች የተሰደዱ አሉ። ጠንበላ በምትባል የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት አውራጃም የግራኝ ሰራዊቶች ደርሰው ይኽችን የጠንበላን አውራጃ ከበቧት። የሀገሪቱም ሰዎች ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሰማዕቱን ይማጸኑት ጀመር። የግራኝም የወታደሮች አለቃ ለመሸመቅ አስቦ ወደ አንድ ዋሻ ሲገባ ዋሻው በተአምር ተደርምሶ ገደለው፣ በውስጡም ቀበረው። ርጉም ግራኝም እሳት ይዞ ጠንበላ አውራጃ የምትገኘውን የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን ሊያቃጥላት ቀረበ። ነገር ግን ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤቱን እንዲያቃጥል አልፈቀደለትምና ሊያቃጥላት አልቻለም። ይልቁንም በቅዱስ እስጢፋኖስ ትእዛዝ በቤተ ክርስቲያኑ ጠፈር ላይ የነበሩ ንቦች ተነሥተው ከነሰራዊቱ እስከሩቅ አውራጃ ድረስ አሳደዱት። ግራኝም ከነሰራዊቱ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ፈጥኖ ሸሸ። የጠንበላ ሀገር ሰዎችም ከግራኝ ያዳናቸውን የቅዱስ እስጢፋኖስን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

ሊቀ ዲያቆናት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዘመኑ ግራኞች ሀገራችንን ይታደግልን።
✞ ✞ ✞

ዳግመኛም ሊቀ ዲያቆናት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአንድ አሕዛብ ላይ ያደረገው ተኣምር ይኽ ነው፡- ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከአሕዛብ ወገን የኾነ አንድ ሰው "የክርስቲያኖች አምላካቸው ምን ያደርገኛል?" ብሎ ታበየ። "ክርስቲያኖች ወደሚያምኑበት የጠበል ሥፍራ ብገባስ መግባቴን ያውቅ ዘንድ ማን ይቻለዋል?" ብሎ እግዚአብሔርን ተፈታተነ። ይኽንንም ብሎ ክርስቲያን መስሎ ወደ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ መካነ ጠበል በድፍረት ገባ።

ይኽም ደፋር አሕዛብ ወደ ጠበሉ በድፍረትና በመታበይ በገባ ጊዜ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ ተገልጦ ይዞ ያንፈራግጠው ወደታችና ወደላይ ያንከባልለው ጀመር። ያም ሰው በታላቅ ቃል "የክርስቲያኖች ወዳጅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ! እባክህ እዘንልኝ፣ እንደዚህ መድፈርን አልደግምም፣ በአምላክህ እግዚአብሔር ስም እምላለሁ። ከእንግዲህም ክርስቲያን እሆን ዘንድ እጠመቃለሁ...." እያለ ጮኸ። በዚያ የነበሩ ካህናትም ይነግራቸው ዘንድ ሲጠይቁት እርሱም አንድ ቀይ ሰው ተገልጦ በምድር ላይ ጥሎ እንደገሠፀውና እንደቀጣው ከነገራቸው በኋላ "ከእንግዲህስ ሳልጠመቅ ያሳለፍኩት ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል" አላቸው። እንዲያጠምቁትም ጠየቃቸው። እነርሱም አስተምረው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቁት። እርሱም ጽኑ ክርስቲያን ኾኖ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግል ሆነ።

የሊቀ ዲያቆናት የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን።

(ምንጭ፦ ሞረትና ጅሩ ወረዳ የሚገኘው ጠንበላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ያሳተመው ገድለ ቅዱስ እስጢፋኖስ)

ጽሑፍ ከገድላት አንደበት ገጽ የተወሰደ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍414🕊2
አባ ዮሐንስ ሐጺር ትምህርቶች

የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን መንገድ ይዘጋል ፣ የእህሉንም መግቢያ ይይዛል። ያንጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ ይጠማሉ። በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ። የነፍስን ፆር ለማሸነፍም በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ይገባል። አንድ ሰው በጾምና በረኃብ ከጸና የነፍሱ ጠላቶች ይዳከማሉ።

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

እኔ በትልቅ ዋርካ ሥር የተቀመጠንና አራዊት ሊጣሉት የመጣን ሰው እመስላለሁ። ሊቋቋማቸው እንደማይችል ከተረዳ ሸሽቶ ወደ ዛፉ በመውጣት ነፍሱን ያድናል። በእኔም የተፈጸመው ይኼው ነው። በበዓቴ ተቀምጬ ክፉ ሐሳቦች ሊቃወሙኝ ሲመጡ ፣ ልቋቋማቸው እንደማልችል ባወቅኹ ጊዜ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ሸሽቼ እመሸጋለሁ። በዚያም ከጠላቶቼ ፍላፃ እድናለሁ።

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

መለወጥ የምትፈልግ ነፍስ በተመለከተ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ በአንዲት ከተማ ውስጥ ብዙ ወዳጆች የነበሯት አንዲት አመንዝራ ሴት ነበረች። ከገዥዎቹ አንዱ ቀረባትና "መልካም ሴት ለመሆን ቃል ግቢልኝና አገባሻለሁ" አላት። እርሷም ቃል ገባችለትና ተጋቡ። ወደ ቤቱም ወሰዳት። የቀድሞ አፍቃሪዎቿ ያቺን ሴት ፈለጓት። እርስ በእርሳቸውም "ያ ልዑል ወደ ቤቱ ወስዷታል ፤ ወደ ቤቱ ብንሄድ ይቀጣናል። ነገር ግን በጓሮ በኩል እንሂድ ፣ ለእርሷም እናፏጭላት፥ የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ከድርሱ ወርዳ ወደኛ ትመጣለች፤ በዚህም ያለ ችግር እናገኛታለን" ተባባሉ። ወደ ቤቷም ጓሮ ተጉዘው ያፏጩ ጀመር። እርሷ ግን የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ጆሮዎቿን ደፈነች። ወደ ውስጣዊው እልፍኝም ገባች። በሩንም ጥርቅም አድርጋ ዘጋች። ይህች ሴት የእኛ ነፍስ ምሳሌ ናት። ወዳጆቿ የተባሉም ፈተናዎቿ ናቸው፣ ገዥ የተባለውም ክርስቶስ ነው፣ እልፍኝ የተባለውም ዘለዓለማዊው ቤት ነው። እነዚህም የሚያፏጩት ክፉዎች አጋንንት ናቸው፣ ነገር ግን ነፍስ ሁልጊዜም በክርስቶስ አምባነት ትሸሸጋለች።

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

አባ ዮሐንስ ልቡናው ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረ ምድራዊ ነገሮችን ይዘነጋ ነበር። አንድ ቀን አንድ ወንድም ቅርጫት ሊወስድ ወደ አባ ዮሐንስ በአት መጣ። አባ ዮሐንስም ምን ፈልጎ እንደሆነ ጠየቀው። ያም ወንድም "ቅርጫት ፈልጌ ነው" አለው። አባ ዮሐንስ ወደ በኣቱ ተመለሰና ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው አመራ። ጥቂት ቆይቶ ያ ወንድም አንኳኳ አባ ዮሐንስም ወጥቶ "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" ሲል መለሰለት። ተመልሶ ወደ በኣቱ ሲገባ ልቡናው በሰማያዊ ነገር ስለተመሰጠ ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው እንደገና ገባ። ለሦስተኛ ጊዜ ያ ወንድም ሲያንኳኳ አባ ዮሐንስ ተመልሶ መጣና "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" አለና መለሰለት። አባ ዮሐንስም እጁን ይዞ እየጎተተ ወደ በኣቱ አስገባውና "ቅርጫት ከፈለግህ ያዝና ሂድ፣ በእውነቱ እንዲህ ላሉት ነገሮች እኔ ጊዜ የለኝም" አለው።

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር በኣት መጣና ሥራውን እያየ ያመሰግነው ጀመር። አባ ዮሐንስ ዝም አለውና ገመድ መሥራቱን ቀጠለ። እንግዳውም እንደገና ወሬውን ቀጠለ ፣ አባ ዮሐንስም ጸጥ አለው። ለሦስተኛ ጊዜ እንግዳው ወሬ ሲያበዛ "አንተ ወደ በኣቴ በመግባትህ እግዚአብሔር ወጥቶ ሄደ" ብሎ ተናገረው።

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ "የብሕትውናን ኑሮ በከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበረ። ያ ሰው በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና ባለዝናም ነበር። አንድ አረጋዊ አባት ከማረፉ በፊት ያንን ሰው ሊያየው እንደሚፈለግ ለዚያ ሰው ጥሪ ደረሰው። ያም ሰው በቀን ከተጓዝኩ ሰዎች ስለሚከተሉኝ ለኔ የተለየ ክብር ይሰጡኛል ብሎ አሰበ። ስለዚህም በሌሊት ሰው ሳያየው ለመጓዝ ወሰነ። በመሸ ጊዜም አሁን ማንም አያየኝም ብሎ ተነሣና ጉዞ ጀመረ። ነገር ግን ሁለት መላእክት ታዝዘው ፣ መብራት ይዘው መንገዱን ይመሩት ነበር። ይህንን የተመለከቱ የከተማው ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ ፣ መላ ከተማው ያንን የመላእክት ብርሃን እያየ ከኃላ ተከተለው። ከክብር በሸሸ ቁጥር የበለጠ ክብርን አገኘ። በዚህም "ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል ፤ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ከፍ ይላል።" የሚለው የወንጌል ቃል ተፈጸመ (ሉቃ. ፲፬፥፲፩)።

የአበው በረከት ይደርብን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
13👍13❤‍🔥9
2025/07/13 22:21:36
Back to Top
HTML Embed Code: