Telegram Web Link
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ!

ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡

ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

("ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ - ገፅ 86)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
21👍11
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ!

ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡

ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

("ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ - ገፅ 86)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍1910
#ሕፃናትና_እኛ_ስንነፃፀር

እስኪ ንገረኝ ! ሕፃናት ቤት እንሥራ ብለው የሚጫወቱት ጨዋታና እኛ በዚህ ዓለም የሚያማምሩ ቤቶችን ስንሠራ ልዩነታችን ምንድን ነው? ሕፃናት እራት እናሰናዳ ብለው በሚጫወቱት ጨዋታና እኛ በምናዘጋጀው ጣፋጭ ማዕድ ልዩነቱ ምንድን ነው? ምንም ምን ልዩነት የለውም፡፡ እንዲያውም እኛ እንደዚህ በማድረጋችን በእኛ ላይ የሚያመጣው ከፍ ያለ ቅጣት (ኵነኔ) አለው፤ [የሕፃናቱ ግን የለውም፡፡] ይህን የምናደርገው ነገር ፍጹም የጎስቋላነት ተግባር እንደ ኾነ ያልተገነዘብነው እንደ ኾነም ይህ ምንም አያስደንቅም፡፡ ገና እስከ አሁን ድረስ ዐዋቂ ሰዎች አልኾንንምና፡፡ ያን ጊዜ ግን ዐዋቂዎች ስንኾን ግን [ረብ ጥቅም የለውም እንጂ] አሁን የምናደርገው ተግባር ኹሉ የሕፃን ሥራ እንደ ኾነ እናውቃለንና፡፡

ሕፃናት እያለን ስናደርጋቸው የነበሩት ተግባራት ዐዋቂዎች ስንኾን እንንቃቸዋለንና፡፡ ሕፃናት እያለን ግን እነዚህን ልናገኛቸው ብለን አስበን የምንጨነቅባቸው የነበሩ ናቸው፡፡ ሕፃናት ኾነን ገልና ሸክላ ስንሰበስብና ካብ ስንከምር ረጃጅም አጥሮችን ከሚሠሩ ሰዎች እንደማንተናነስ አድርገን እናስብ ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚያ ያቆምናቸው የድንጋይ ክምሮች ወዲያውና እዚያው ፈራርሰው የሚወድቁ ነበሩ፤ ጸንተው ቢቆሙም እንኳን የሚሰጡን ረብ አልነበረም፡፡ አሁንም እኛ በዚህ ዓለም የምንሠራቸው የሚያማምሩ ቤቶች ያው እንደ እነዚህ የሕፃንነታችን ጊዜ ካቦች ናቸው፡፡ አሁን የምንሠራቸው ቤቶች ሀገሩ በሰማይ የኾነውን ሰው ተቀብለው ማኖር የሚቻላቸው አይደሉምና፤ እነርሱ ተቀብለው ማኖር አለመቻላቸው ብቻም ሳይኾን በላይ በሰማይ ሀገሩ የኾነ ሰውም በእነዚህ ቤቶች መኖርን የሚሻ አይደለምና፡፡ ሕፃናት የከመሩአቸው ካቦች እኛ በእግራችን ነካ ብናደርጋቸው የሚፈራርሱ ናቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ በመንፈስ ልዑል የኾነ ሰውም እነዚህን እኛ የምንደነቅባቸው ቤቶች የሚመለከታቸው እንደዚህ ነው፡፡ ሕፃናቱ ቤት ብለው የከመሩአቸው ካቦች በእግራችን ነካ ብናደርግባቸውና ብናፈርስባቸው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ ተመልክተን [የማያስለቅስ ያስለቅሳቸዋል ብለን] እኛ እንደምንስቅ ኹሉ፥ እነዚህ በመንፈስ ልዑላን የኾኑ ሰዎችም እኛ በእነዚህ ቤቶች መፍረስ ስንተክዝ ተመልክተው [በማያሳያዝን ያዝናሉ በማያስተክዝም ይተክዛሉ ብለው] ይስቃሉ፡፡ እንዲያውም መሳቅ ብቻም ሳይኾን ያለቅሳሉ፡፡ ምክንያቱም፡-

[አንደኛ] ርኅሩኀን ናቸው፤

[ኹለተኛ ደግሞ] እኛ ከእነዚህ ቤቶች ጋር ይህን ያህል በመጣበቃችን ምክንያት የሚመጣብን ጉዳት ብዙ የብዙም ብዙ እንደ ኾነ ያውቃሉና ያለቅሳሉ፡፡

ስለዚህ ዐዋቂዎች እንኹን፡፡ እስከ መቼ ድረስ ነው በምድር ላይ የምንንፏቀቀው? እስከ መቼ ድረስ ነው በድንጋዮችና በምድራዊ መኖሪያ ቤቶች ራሳችንን የምናስታብየው? እስከ መቼ ድረስ ነው ዕቃ ዕቃ የምንጫወተው?

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን 23፥10)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍219
"እውነተኛ ክርስቲያን አባቱ ክርስቶስን ይመስላል፡፡ ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሰደባል እንጂ አይሳደብም፡፡ የጠፉትን ፍለጋ ይደክማል እንጂ ይባስ ብሎ አይገፈትርም፡፡ በወንድሙ ውድቀት ያለቅሳል እንጂ አይደሰትም፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን አባቱ ሌላ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና በጊዜውም ያለ ጊዜውም ሊሆን ይገባል፡፡ ባገኘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ባጣንም ጊዜ፤ ባለጤና በሆንን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በታመምንም ጊዜ፤ ሲሳካልን ብቻ ሳይሆን ባልተሳካልንም ጊዜ ማመስገን መለማመድ አለብን፡፡ የምስጋናችን ምንጭ የሁኔታዎች መለዋወጥ ሳይሆን ስለ አምላካችን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ስንለማመድ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልናል፤ እንደ አባታችን ኢዮብ የዲያብሎስን አፍ እንዘጋለን፡፡

ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋላችሁን?” እንኪያስ "በዘፈን የደነቆረን ጀሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፡፡ ሴትን በመመኘት የታወረው ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አድርጉት፡፡ በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፡፡ ወደ ኃጢአት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አድርጉት፡፡ ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፈር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፡፡ ከተአምራት ሁሉ የበለጠ ተአምር ይሄ ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
35👍23❤‍🔥2
ወንድሞቼ "እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡

ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡ እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2410
አምላክ ልቧ ቆንጆ የሆነችውን ሴት እንዲሰጥህ አምላክህን ለምን። ያንተ የሆነችውን ሴት አምላክ እስኪሰጥህ ትዕግስት ይኑርህ ልብህ ያርፈባትን ውደድ አፍቅር አይንህ እዛም እዚህም አይቀላውጥ በቁንጅና፣ በተክለ ሰውነት እና ባለባበስ አትማርክ  ሴት ልጅ ባለባበሷ እና በመልኳ አይትህ አትናቅ ቆንጆ ስታማርጥ ያንተ የሆነችውንና ህይወትህን የምታጣፍጥህልህን ሴት እንዳታጣ። ለማፈቀር ወይም ለመፈቀር ሰው መሆን በቂ ስለሆነ።

የሰው አስቀያሚ የለውም የአስተሳስብ እንጂ፡፡ ቆንጆ አይደለችም፣ አለባበሷ ይደብራል፣ አቋሟ አያምርም አትበል ቀርበህ የውስጧን ውበት ሳታይ በላይ ውበቷ አታጣጥላት ለተርዳው ሰው እና በሳል ለሆነ ሰው ከላይ ውበት ይልቅ የውስጥ ውበት ሚዛን ይደፍልና። ስለዚህ ላንተ ከተመቸችህ ምንም ትሁን የአንተን ህይወት አንተ እንጂ ሌላ ሰው አይኖርልህም ለራስህ ብለህ ኑር ለራስህ ብለህ አስተውል ለሰው ብለህ ምንም ነገር አታድርግ ለህሊናህ እንጂ።

ቆንጆ አግብቼ የእከሌ ሚስት ቆንጆ ናት ወዘተ እንዲባልልህ ሳይሆን ለህይወትህ የምትመችህን የምትስማማህን ሀሳብህን የምትርዳህ እና ከልብ የምታፈቅርህን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን ልብህ ያያትን አግባ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
40👍13
#ጠቃሚ_ምክር_ከቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ባልንጀራህን ልትገሥጽ ብትፈልግ፣ ልትመክር ብትሻ፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ልታደርግ ብትፈቅድ ይህን ያለ ቍጣና ከስሜታዊነት ወጥተህ አድርገው፡፡ የሚገሥጽ፣ የሚመክር ሰው ባለ መድኃኒ ት ነውና፡፡ ነገር ግን ለራሱ ባለ መድኃኒትን የሚሻ ከኾነ ሌላውን ሰው እንደ ምን መፈወስ ይቻለዋል? ራሱ ቁስለኛ ኾኖ ሳለ ሌላውን ለመፈወስ ከመኼዱ በፊት የራሱን ቁስል የማያሽረው ለምንድን ነው? ባለ መድኃኒት ሌላ ሰውን ለማዳን በሚኼድበት መጀመሪያ የራሱን እጅ ያቆስላልን? የሌላውን ዐይን ለማዳን የሚኼድ ባለ መድኃኒት አስቀድሞ የራሱን ዐይን ያሳውራልን? እንዲህ ከማድርግ እግዚአብሔር ይጠብ ቀን፡፡

ስለዚህ አንተ ሰው! ሌላውን ከመገሠጽህና ከመምከርህ በፊት የራስህ ዐይኖች አጥርተው የሚያዩና ንጹሃን ይኹኑ፡፡ ሕሊናህን አታቆሽሸው፡፡ እንዲህ ከኾነ ግን ሌላውን ማንጻት እንደ ምን ይቻልሃል? በቍጣ ውስጥ መኾንና ከቍጣ ንጹህ መኾን የሚሰጡት ውስጣዊ ሰላም በጭራሽ የሚነጻጸር አይደለም፡፡ እንዲህ ከኾነ ታዲያ ሰላም የሚሰጥህን ጌታ [ነፍስህን] አስቀድመህ ከዙፋኑ ላይ ጥለህና ከጭቃው ጋር ለውሰኸው ስታበቃ፡ ከእርሱ እርዳታን የምትሻው እንዴት ብለህ ነው? ዳኞች የዳኝነት ሥራቸውን ሊያከናውኑ ሲፈልጉ አስቀድመው ካባቸውን ደርው ከፍርድ ዙፋናቸው ላይ እንደሚቀመጡ አላየህንምን? አንተም ነፍስህን የዳኝነት ልብስን አልብሰሃት በተገቢው ቦታዋ ልታስቀምጣት ይገባሃል፡፡ እርሱም የማስተዋል ልብስ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 62-63)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍286
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ይረዳው?

ይህን ጽሑፍ አንድ ወንድሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብን በተመለከተ ለጠየቀኝ ጥያቄ የሰጠሁት መልስ ነው፡፡ (በመ/ር ሽመልስ መርጊያ)

ውድ ወንድሜ ሆይ እርግጥ ነው መጽሐፍ ቅዱስን ወዲያው ለመረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ ምዕራፍ ውስጥ ብዙ በይዘታቸው የተለያዩ መልእክቶች ስለሚተላለፉ ነው፡፡ ይህ የአንድ መንፈሳዊ መጽሐፍ ጠባይ ነው፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ዓይነት አጻጻፍ በጥንት ቅዱሳን አባቶች መጻሕፍት ላይ ይገኛል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አንድ ዛፍ ነው፡፡ ግንዱ አንድ ሲሆን ብዙ ቅርንጫፎችና እጅግ ብዙ ቅጠሎች ያሉት ሲሆን ፍሬው ግን ምንም በቁጥር አንዱ ቅርንጫፍ ከአንዱ ቅርንጫፍ ይበልጥ የሚያፈራ ቢሆንም አንድ ነው፡፡ ይህን ላስረዳህ፡፡ ግንዱ አንድ እግዚአብሔር ነው፡፡ ወይም ሥሩ እግዚአብሔር አብ ነው ግንዱ ክርስቶስ ነው ለዛፉ ሕይወት የሚሆነውና ፍሬ እንዲሰጥ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

ቅርንጫፎቹ እኛ ነን ቅጠሎቹም ፍሬ እንድናፈራባቸው የተሰጡን ጸጋዎች ናቸው፡፡ ሌላም አለ የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል ከአንድ ጉዳይ ይነሣና ከተነሣበት ጭብት ጋር ፈጽሞ የተለየ ሃሳብን ምናልባትም ብዙ ሃሳቦችን አንስቶ ሊሆን ይችላል ከዚያ በኋላ ወደ ተነሣበት ርእሰ ጉዳይ ይመለሳል፤ ግንዱን ግን አይለቅም፡፡

ይህን የአንድ የዛፍን ባሕርይ በመመልከት መረዳት ትችላለህ፡፡ አንድ ዛፍ ምንም እጅግ ቅርንጫፎች ቢኖሩት ከግንዱ የተቀበለውን ከተጠቀመ በኋላ በምላሹ ለግንዱ የሚያደርሰው የራሱ የሆነ ሥርዐት አለው፡፡ ተመልከት ወዳጄ፡-ዛፉ ከግንዱ ምግቡን የሚያዘጋጅበትን ውኃና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ሲያገኝ ከባቢ አየሩንና ፀሐይን በቅጠሉ ወደ ግንዱ በማድረስ ምግቡን ያዘጋጃል፡፡ ይህንን ሲፈጽም ከግንዱ ያገኘውንም በአንድነት በመጠቀም ነው እንጂ ከፀሐይና ከከባቢ አየሩ ያገኘውን ብቻ በመጠቀም አይደለም፡፡ ስለዚህ ግንዱ ይህ ቅርንጫፍ ፍሬ እንዲያፈራ ያደርገዋል፡፡ ቅርንጫፉ እርሱ የሚፈጽመው የራሱ የሆነ ሚና ቢኖረውም ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርገው ግንዱ ነው፡፡

ስለዚህ የዚህ ሒደት ተጠቃሚ ለመሆን ከፈለግህ ዛፉን በትክክል ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ያም ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ከሀ - ፐ ማለትም ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ዮሐንስ ድረስ አንብበህ መጨረስ አለብህ፡፡ ያለበለዚያ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት አትችልም፡፡ አንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንብበህ ሌላውን መተው ማለት ሥሩን አውቀህ ግንዱንና ቅርንጫፉን አለማወቅ ወይም ግንዱን አውቀህ ሥሩንና ቅርንጫፉን ብሎም ቅጠሉንና ፍሬውን አለማወቅ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተሰነካክለህ እንዳትወድቅ አይታደገህም፡፡

ለኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አስኳሉና መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ግንዱ ያላደረገ የትኛውም ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፕሮግራም አውጥተህ መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ ለሙሉ ቢያንስ በዓመት ሦስቴ መላልሰህ ልታነበው ይገባሃል፡፡ ያለበለዚያ እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ልትቆም አትችልም፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ አሳቦችንም መረዳት የምትችለው ከዚያ በኋላ ነው፡፡ 

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
20👍13
ተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ከማሳዘን ውጪ ምንም ይኹን ምን [አንፍራ፡፡] ሠለስቱ ደቂቅ የሚንበለበል እሳት በፊታቸው ቢያዩም ናቁት፤ ኃጢአትንም ብቻ ፈሩ፡፡ በእሳቱ ቢቃጠሉ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር እንደሌለ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባይገኝባቸው ግን እጅግ የከፋ ጉስቁልና እንደሚያገኛቸው ያውቃሉና፡፡ ምንም ሳንቀጣ ብንቀርም እንኳን እጅግ ትልቁ ቅጣት ግን ኃጢአት መሥራት ነው፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም ያህል ቅጣት ቢያገኘንም እጅግ ትልቁ ክብርና ጸጥታ ግን በተጋድሎና በምግባር ሕይወት መኖር ነው፡፡

እግዚአብሔር ራሱ፡- “በደላችሁ በእናንተና በእኔ መካከል አልለየችምን?” ብሎ እንደ ተናገረ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል (ኢሳ.59፡2)፡፡ ቅጣት ግን “እግዚኦ አምላክነ ሰላመ ሀበነ እስመ ኵሎ ወሀብከነ - አቤቱ አምላካችን ኹሉን ሰጥተኸናልና ሰላምን ስጠን” እንደ ተባለ ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል (ኢሳ.26፡12)፡፡

እንበልና አንድ ሰው ቁስል ወጣበት፡፡ የሚያስፈራው የትኛው ነው - የሚሰፋው ቁስል ወይስ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ቢላ? ብረቱ ወይስ እጅግ እየባሰበት ያለው ቁስል? ኃጢአት የሚሰፋ ቁስል (Gangrene) ነው፤ ቅጣት ደግሞ የቀዶ ጥገናው ሐኪም ቢላ ነው፡፡ ያልፈረጠ የሚሰፋ ቁስል ያለው ሰው ሕመሙ እንዳለበትና ለወደፊቱም የማያፈርጠው ከኾነ ሥቃዩ እየባሰበት እንደሚኼድ ኹሉ፥ ቅጣት ያላገኘው ኃጢአተኛ ሰውም ከሰዎች ኹሉ ይልቅ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፤ ለወደፊቱ ጭራሽ ቅጣትና መከራ የማያገኘው ከኾነ ደግሞ ከአሁኑ ይልቅ እጅግ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፡፡ የጣፊያ ወይም የሆድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ መብል ቢበሉ፣ ቀዝቃዛ መጠጦችን ቢጠጡ፣ የተለያዩ ዓይነት ጣፋጭና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው መብሎችንም ቢወስዱ ይህ ድሎት ሕመማቸው እንደሚጨምረውና እንደ ሕክምናው ሕግ ራሳቸውን ከመብሉም ከመጠጡም በመጠኑ ቢወስዱ ግን የመዳን ተስፋ ሊኖራቸው እንደሚችል ኹሉ፥ በክፋት ዓዘቅት የሚኖሩ ሰዎችም ቅጣት ካገኛቸው በጎ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከክፋታቸው ጋር አብረው ዝንጋዔንና ድሎትን የሚጨምሩበት ከኾነ ግን ሆዳቸውን ከሚያማቸው ሰዎች በላይ እጅግ ጐስቋሎች ሰዎች ናቸው - ደዌ ዘነፍስ ከደዌ ዘሥጋ ይልቅ የከፋ ነውና፡፡ ተመሳሳይ ኃጢአት እያላቸው አንዳንዶቹ በማጣትና በብዙ ሕመም ሲሠቃዩ፣ ሌሎቹ ግን እስኪበቃቸው ድረስ እየጠጡና እየተስገበገቡ የሚበሉ እየተመቻቸውም በደስታ የሚኖሩ ሰዎችን ብትመለከት እነዚያ መከራ የሚቀበሉት የተሻሉ እንደ ኾኑ አስተውል፡፡ በእነዚህ መከራዎች የተወገደላቸው የፈንጠዝያ ሕይወት እሳት ብቻ ሳይኾን ሊመጣ ወዳለው ፍርድና አስፈሪ ዙፋን ሲኼዱም ከቀላል ዕረፍት ጋር አይደለምና፤ ስለኾነም እዚያ ሲኼዱ ከኃጢአታቸው የሚበዛውን በዚህ ዓለም ባገኛቸው ሥቃይ አስወግደው ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍257
እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
41👍21
የነነዌ ሰዎችና እኛ

ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? ("ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡

ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡

እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡

የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡

(በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2319🕊2
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡

ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍228🕊1
በከንቱ እንዳንደክም መጾም እንደሚገባን እንጹም

በመጾም እየደከምን ሳለ የጾም አክሊልን ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበርና፤ ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የኼደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነውና (ሉቃ.18፡12)፡፡ ቀራጩ ደግሞ በአንጻሩ አልጾመም ነበር፤ ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው፡፡ ይህም የኾነበት ምክንያት [ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ በመፃዒ ሕይወቱም ጾም አላሻውም ለማለት ሳይኾን ከተአምኖ ኃጣውእ ጋር] ሌሎች ግብራት ካልተከተሏት በቀር ጾም ረብ ጥቅም እንደሌላት [እና ትሕትና የጾም አጣማጅ መኾኑን/ የምትሠምረው ከትሕትና ጋር መኾኑን] እንድታውቅ ነው፡፡

የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል (ዮና.3፡10)፡፡ እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም (ኢሳ.58፡3-7፣ 1ኛ ቆሮ.9፡26)፡፡ ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለባቸው ለማያውቁ ሰዎች የጾም ጉዳቱ ትልቅ ነውና በጥርጣሬ እንዳንኼድ፣ እንዲሁ አየርን እንዳንደልቅ፣ እንዲሁ ከጨለማ ጋር እንዳንጋደል፥ ይህን የምናከናውንባቸውን ሕጎች ልንማር ያስፈልገናል፡፡

ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
17👍15🕊2❤‍🔥1
በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም፥ ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
14👍12
"#ይቅርታ" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ከሠራተኞችህ አንዱ ከአንተ መቶ ቅንጣት ወርቆችን ተበደረ እንበል፡፡ ሌላ ሰው ደግሞ ከዚህ ሠራተኛህ የተበደረው ጥቂት ብር ነበረው፡፡ ከዚህ ሠራተኛህ የተበደረው ያ ሰውም ወደ አንተ መጥቶ ቸርነትን እንድታደርግለት ለመነህ፡፡ አንተም ሠራተኛህን ጠርተህ፡- “የዚህን ሰው ዕዳ ተውለት፤ ከእኔ ከተበደርከው ዕዳህም እቀንስልሃለሁ” ብትለውና ይህ ሠራተኛህ ከዚያ በኋላ በዚያ ሰው ላይ ቢጨክንና ቢከፋ ይህን ሠራተኛ ከእጅህ ሊያድነው የሚችል ሰው አለን? እጅግ እንደ ነቀፈህ አድርገህ ቆጥረህ ብዙ ግርፋትን አትገርፈውምን? [እንዲህ ብታደርግ] እጅግ ፍትሐዊ ነው፡፡ እግዚአብሔርም የሚያደርገው እንደዚህ ነው፤ በዚያች ዕለተ ምጽአት ላይ እንዲህ ይልሃልና፡- “አንተ ክፉና ተንኰለኛ ባሪያ ያንን ሰው ይቅር ብትለው ይቅርታው የአንተ ነበርን? ለእርሱ እንድታደርግለት የታዘዝከው ከእኔ የተበደርከውን ነበር፡፡ ያልኩህ ‘ዕዳዉን ብትተውለት እኔም እተውልሃለሁ’ ነው፡፡ በእውነት እንዲህ ይህን ኹኔታ ጨምሬ ባልነግርህም እንኳን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ዕዳዉን ትተውለት ዘንድ በተገባህ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ወዳጅ ኾኜ ውለታን ጠየቅሁህ እንጂ እንደ ጌታ አላዘዝኩህም፡፡ የጠየቅሁህ የእኔ ከኾነው ነው፤ ይህን ካደረግህም እጅግ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን እንደምሰጥህ ቃል ገብቼልህ ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ልትሻሻል አልቻልክም፡፡”

ከዚህም በላይ ሰዎች እንደዚህ ሲያደርጉ የሚቀንሱት የዕዳ መጠን ሠራተኞቻቸው ላበደሩአቸው ሌሎች ሰዎች የቀነሱትን ያህል ነው፡፡ ለምሳሌ እንበልና አንድ ሠራተኛ ከአሠሪው መቶ ቅንጣት ወርቅን ይበደራል፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ከዚህ ሠራተኛ ዐሥር ቅንጣት ይበደራል፡፡ ሠራተኛው ዐሥር ቅንጣት ላበደረው ብድሩን ቢተዉለት አሠሪው ግን መቶ ቅንጣቱን አይተውለትም፤ የሚተውለት ዐሥር ቅንጣቱን ብቻ ነው፤ ሌላዉን እንዲመልስለት ይፈልጋል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ አንተ ለባልንጀራህ ጥቂቱን ስትተውለት እግዚአብሔር ደግሞ ዕዳህን ኹሉ ይተውልሃል፡፡ ይህስ [መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ] የት ይገኛል? [ጌታችን] ስለ ጸሎት ባስተማረው ትምህርት ውስጥ አለ፡፡ “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና” እንዲል (ማቴ.6፡14)፡፡ በ“መቶ ዲናር” እና በ“እልፍ መክሊት” መካከል ያለው ልዩነት ያህል ለሰው ይቅር የምንለው ዕዳና ከእግዚአብሔር ይቅር የሚባልልን ዕዳም አይነጻጸርም (ማቴ.18፡24፣28)!

እንግዲህ መቶ ዲናርን ዕዳ ይቅር ብሎ እልፍ መክሊትን የሚቀበል ኾኖ ሳለ ይህቺን ጥቂት ዕዳስ እንኳን ይቅር ሳይል ጸሎቱን በራሱ ላይ የሚያደርስ ይህ ሰው የማይገባው ቅጣት እንደ ምን ያለ ቅጣት ነው? ምክንያቱም “እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን” ብለህ እየጸለይክ ሳለ አንተ ግን ከዚያ በኋላ ይቅር የማትል ከኾነ እግዚአብሔር ምሕረቱን ወይም ቸርነቱን ኹሉ እንዲያርቅብህ ካልኾነ በቀር ሌላ ምንም እየለመንከው አይደለም፡፡ “እኔ ይቅር በለኝ ብቻ ነው እንጂ የበደሉኝን ይቅር እንደምል በደሌን ይቅር በለኝ ብዬ አልጸልይም” የሚል ሰው ደግሞ አለ፡፡ ታዲያ ይኼ ምንድን ነው? አንተ እንዲህ ብለህ ባትጸልይም እግዚአብሔር ግን እንዲህ አያደርግም፤ ይቅር የሚልህ አንተ ይቅር ስትል ነው፡፡ ይህም ከዚያ በኋላ እንዲህ ብሎ ግልጽ አድርጎታል፡- “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማዩ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም” (ማቴ.6፡15)፡፡ ስለዚህ ጸሎቱን ሙሉ ባትደግመው ወይም ዕለት ዕለት እንደዚያ ብለህ ስትጸልይ ፈርተህ ከባልንጀራህ ጋር እንድትታረቅ ብሎ እንድትጸልው ባዘዘህ መንገድ ሳይኾን ቈርጠህ ብትደግመው እንኳን ደገኛ መንገድ ነው ብለህ አታስብ፡፡

“ብዙ ጊዜ ለምኜዋለሁ፤ ተማጽኜዋለሁ፤ ማልጄዋለሁ፤ ሊታረቀኝ ግን አልቻለም” ብለህ አትንገረኝ፡፡ እስክትታረቀው ድረስ በፍጹም አታቁም፡፡ ጌታችን ሲናገር፡- “መባህን ትተህ ኺድ፤ ወንድምህንም ለምነው” አይደለምና፡፡ ያለው፡- “ኺድ፤ ታረቅ” ነው (ማቴ.5፡24)፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ለምነኸው ቢኾንም እስክታሳምነው ድረስ ግን ይህን ማድረግህን አታቋርጥ፡፡ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት ይለምነናል፤ እኛ ግን አንሰማውም፡፡ ኾኖም [አልሰሙኝም ብሎ] መለመኑን አላቋረጠም፡፡ ታዲያ አንተ ባልንጀራህን ለመለመን ትታጀራለህን? እንዲህ የምታደርግ ከኾነስ ልትድን የምትችለው እንዴት ነው?

የይቅርታ ልብ ይስጠን።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍1715
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ስለ_ቤተክርስቲያን

"አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ ትበልጣለች ቢል አልተሳሳተም፡፡ የኖኅ መርከብ እንስሳትን ወደ ውስጥዋ ብታስገባም እንስሳት አድርጋ ጠበቀቻቸው እንጂ አልለወጠቻቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን እንስሳትን ትቀበላለች፤ ትለውጣቸውማለች፡፡ ለምሳሌ ወደ ኖኅ መርከብ ቁራ ገባ፤ የወጣውም ግን ቁራ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ገባ፤ የወጣውም ግን ያው ተኵላ ኾኖ ነው፡፡ እዚህ ቤተ ክርስቲያን ግን አንድ ሰው እንደ ቁራ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ ርግብ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ በግ ኾኖ ነው፡፡ እንደ እባብ ኾኖ ቢመጣ የሚወጣው እንደ ጠቦት በግ ኾኖ ነው፡፡ ተፈጥሮው ወደዚያ ስለሚለወጥ ግን አይደለም፤ ክፋቱ ስለሚርቅለት እንጂ፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ንስሐና ምጽዋት)

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

"ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ ኃጢአትህንም አርቃት፡፡ በአደባባይ የምትወድቀው ቊጥሩ ከምትነሣው ጋር እኩል ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ በደል ኃጢአት የምትሠራውን ያህልም ፍጹም ተስፋ ሳትቈርጥ ንስሐ ግባ፡፡ ኹለተኛ ብትበድል ኹለተኛ ንስሐ ግባ፡፡ በስንፍና ተይዘህ በፍጹም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለኝም አትበል፡፡ በእርግና ዘመን ብትኾንና ብትበድልም እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡ እዚህ ስትመጣ ካህናት [“እግዚአብሔር ይፍታሕ” ብለው] ከኃጢአት እስራት ፈትተው ይቅርታ ይሰጡሃል እንጂ “ለምን በደልህ?” ብለው አይፈርዱብህምና፡፡ ስለዚህ፡- “አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ ኃጢአትህም ይቀርልሃል (መዝ.50፡4)፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍235
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በ፲፩ ኛው በዓለ ሢመታቸው ያስተላለፉት መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ክቡራንና ክቡራት በሙሉ፤
ፈተናዎች ቢበዙብንም ምሕረቱን ከኛ ያላራቀ እግዚአብሔር እንኳን ለዐሥራ አንደኛው በዓለ ሢመተ ክህነት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

‹‹ወይእዜኒ ተመየጡ ኀቤየ ወአነሂ እትመየጠክሙ፡- ‹‹አሁንም ወደኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደናንተ እመለሳለሁ›› (ዘካ. ፩-፫)
ቅዱስ መጽሐፍ ታላቁ የዓለማችን መጽሐፍ ነው፤ በዕድሜም በብዛትም በዓለም ውስጥ የሚተካከለው የለም፤ ቅዱስ መጽሐፍ በዓለም ውስጥ በብዙ ቋንቋ የተተረጐመና ብዙ አንባቢና ተከታይ ያለው ብቸኛው የዓለማችን ታላቅ መጽሐፍ ነው፡፡

የቅዱስ መጽሐፍ ይዘት በጥቅሉ ሲታይ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው ያለውና የሚኖረው ግንኙነትን የሚገልጽ ነው፤ የግንኙነቱ ሁናቴ ሲታይ ደግሞ ቀጥ ያለ ሳይሆን ብዙ ፈተና ያስተናገደ ጐርባጣና ጠመዝማዛ እንደሆነ በግልጽ ያመለክታል፤ በረጅሙ ግንኙነት እግዚአብሔር ፍጡሩን እየተከታተለ በምሕረትና በፍቅር ሲጐበኝ አንዳንዴ ደግሞ ሲቀጣም ሲገሥጽም ይታያል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ሰዎች የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው እንደ ቃሉ ለመኖር ሲጣጣሩ፣ ነገር ግን በአብዛኛው እንዳልተሳካላቸው፣ በዚህም ጉዳታቸው እየከፋ እንደሄደ እናስተውላለን፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር ሰውን ለመመለስ መጣራቱን አቋርጦ እንደማያውቅ ተጽፎአል፡፡ ‹‹አሁንም ወደኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደእናንተ እመለሳለሁ›› የሚለው ጥሪውም ይህንን ያስረዳል፡፡ ጥቅሱን በትክክል ስናጤነው ሰዎች ከእግዚአብሔር የመኮብለል ዝንባሌያቸው ያየለ እንደሆነ፣ በአንጻሩ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥሪ የማያቋርጥ እንደሆነ የሚያስረግጥ ነው፤ ቀድሞም ሆነ ዛሬ የምናየው ሐቅም ይኸው ነው፤

ከዚህ አንጻር በዘመናችን ያለው ሁኔታም ስንመለከት ከበፊቱ ብዙም የተሻለ ሆኖ አናገኘውም፤ ይልቁንም በጣም የተዛባና ለእግዚአብሔር ቁጣ የተጋለጠ ሆኖ እናየዋለን፤ ያለንበት ዘመን ለእግዚአብሔር ክብርን የነሣ፤ ከፍቅርና ከአንድነት የራቀ፣ ራስ ወዳድነትና በቃኝ አለማለትን የወረረው፤ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ የተዋጠ ትውልድ የታየበት ዘመን ነው፡፡ የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን፣ ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ፣ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረ ሰብ ጤናማ ህላዌ ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ ይህን አደገኛ አዝማሚያ በማስተዋል ካልታረመ ሂዶ ሂዶ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማስከተሉ አይቀርምና እንደ እግዚአብሔር ጥሪ ወደእሱ ብንመለስ ይሻላል፡፡

•ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች፡-

እኛ የሃይማኖት አባቶችም አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቈራጥነት ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን አስተምረነው የማይመለስ ከሆነ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ እኛ ባለማስተማራችን የሚጎዳ ትውልድ ካለ ግን እኛ የደሙ ተጠያቂዎች መሆናችንን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጾአልና ነው፤ የኛ ኃላፊነት እስከዚህ ድረስ ከባድ መሆኑን ባንዘነጋውም እንደዓለሙ በልዩ ልዩ ደካማ አስተሳሰቦችና ተግባራት እየተሰናከልን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ውሉ አድሮአል፡፡

ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል፤ ባናጨበጭብም ዝምታን መርጠናል፤ ነገር ግን ኃላፊነቱን የተረከብነው ጥፋት ሲፈጸም ዝም ብሎ ለማየት አልነበረም፤ ከዓለሙ ጋር አብሮ ለማጨብጨብ ወይም አድማቂ ለመሆንም አልነበረም፡፡ ከቅዱስ ወንጌሉ መሠረተ ሐሳብ ፍንክች ሳንል የእውነት፣ የፍትሕ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የዕርቅ፣ የይቅርታ፣ የአንድነትና የስምምነት ጠበቃ መሆናችንን ማሳየት ነበረብን፡፡ ሰውን ሁሉ በእኩልነት በመቀበልና የሁሉም እኩል አባቶች መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ይገባን ነበር፤ የተዛባውን በማረም ትውልዱን ለማዳን ያደረግነው ጥረት የሚያረካ እንዳልሆነ ታዛቢው ሁሉ አይቶብናል፡፡ያም በመሆኑ ሁኔታው እኛንም ቤተ ክርስቲያንንም ለፈተና ለመዳረግ እየዳዳ ነው፤ በመሆኑም በዚህ ክሥተት የእግዚብሔር ቁጣ የለበትም ለማለት አንደፍርም፤ በዓለሙ ብልሹ አሰራርም ተሳታፊ ከመሆን አላመለጥንም፡፡ክሱ፣ አቤቱታው፣ ሰውን ከሥራ እያፈናቀሉ ፍትሕ ማዛባቱ፣ በደምብ ተለማምደነዋል፤ ደመወዛችሁ ይብቃችሁ የሚለውን አምላካዊ መርሕ ዘንግተን የዚህ ዓለም ንዋይ እያሸነፈን ነው፤ ግን ዓለምን ልናሸንፍ እንጂ በዓለም ልንሸነፍ አልተጠራንም፤
በዚህ ምክንያት የብዙ ምእመናን ልብ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ምክንያት እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል፤ በዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣ በእኛና በሕዝባችን በሀገራችንና በዓለማችን እንዳይገለጥ እነሆ አሁንም ቃሉ ተመለሱ እያለ ነውና እንመለስ፤ እየተዛባ ያለው ሁሉ መስተካከል ይችላል፤ በሃይማኖት የማይቻል ነገር እንዳለ የሚያስብ ካለ ሃይማኖት የሌለው እሱ ነው፡፤

•ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች፡-
እኛ የሃይማኖት አባቶች ከሌላ የምንዋሰው ንግግርና አስተምህሮ የለንም፤ ዐሠርቱ ቃላትን ማክበርና መተግበር ማስተማርና ማሥረጽ በቂያችን ነው፡፡ ምክንያቱም ከዐሠርቱ ቃላት የበለጠ ሌላ ሕግ በዓለም ስለሌለ ማለት ነው፤ ቢኖርም ከሱ የተኮረጀ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ የኛ አስተምህሮ አትግደል እንጂ ግደል ሊሆን አይችልም፤ የኛ ተግሣጽ አትስረቅ፣ አትዋሽ፣ የሌላውን አትመኝ፣ አታመንዝር የሚል እንጂ በተመሳሳይ የፆታ ጋብቻ ወደ ነውረ ኃጢአት ተሠማራ የሚል ትምህርት መቼውም ቢሆን ከቶ ሊኖረን አይችልም፡፡

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጭ ከዘመኑ የወሬ ሱሰኛ መሣሪያን እየተበደርን ከቅዱስ ወንጌሉ ጋር የሚጣረስ ንግግርና አስተምህሮ ማስተላለፍ ለምን አስፈለገ? ይህ ለኛ ኃሣር እንጂ ክብር ሊያስገኝልን አይችልም፤ ከእንደዚህ ያለ ድርጊትም መራቅ አለብን፤ የኛ ደንበኛና ዘላለማዊ ፖለቲካ ቅዱስ ወንጌል ነው፤ ዘላለማዊውን ትተን ጊዜያዊውን፣ መለኮታዊውን ትተን ሰዋዊውን አንከተል፡፡ ይህ ለኛ የሞራል ዝቅጠት ያስከትልብናል፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርም ከኛ የሚጠብቁት ትክክለኛውን ቃለ ቅዱስ ወንጌል ማስተማር ነው፤ ለዓለሙ ፖለቲካ ግን የራሱ ባለቤቶች አሉለት፡፡ እኛ በፖለቲከኞች ላይ ያለን ሥልጣንና መብት ማስተማርና መምከር ነው፤ ያም ሆኖ አንዱን በመደገፍ ሌላውን በመንቀፍ ሳይሆን ሁሉም እኩል ልጆቻችን መሆናቸውን አውቀን በፍቅር በመመልከት ነው፡፡ ሲጋጩብንም የማስታረቅና የማቀራረብ፤ የመምከርና የማሳመን እንጂ ወደ አንዱ ተለጥፎ ሌላውን ዘልፎ መናገር የቆምንለት ቅዱስ ወንጌል አይፈቅድልንም፡፡

ፓለቲከኞችም ባልዋሉበትና ባልተፈቀደላቸው፣ ሌላው ቀርቶ የተቋቋሙበት ሕገ መንግሥቱ እንኳ የማይፈቅድላቸውን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገቡ የግል ፍላጎትና ዓላማ ለማስፈጸም መሞከር ፍጹም ስሕተት ነው፤ ተቀባይነትም የለውም፤ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው ለፖለቲከኞቹም አይበጅም፡፡ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ በጋራ ጉዳዮች ላይ በፍቅርና በመከባበር ተመካክሮና ተግባብቶ መስራት ያሻል፤ በዚህ መንፈስ ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ተናበው ቢሰሩ በሀገር ላይ ሰላም ይሰፍናል፣ ልማት ይፋጠናል፣ ዕድገት ይመዘገባል፤ ስለዚህም በዚህ ዙሪያ ሁላችንም ከምር ልናስብበት ይገባል።

•ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች፡-
👍215
በዛሬው ዕለት እያከበርነው ያለ በዓለ ሢመተ ክህነት ዓላማው የተሰጠንን ተልእኮ በማሰብ ለተሻለ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የመነቃቃትና የመነሣሣት መንፈስ ለመፍጠር ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙንን ፈተናዎች በመለየት፣ በቀጣዩ እንዳይደገሙ ነቅተንና ተግተን መስራት ያስፈልጋል፡፡ ባለፉት ዓመታት እጅግ በጣም አስቀያሚ ነገሮችና ፈተናዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ተከሥተዋል፤ አሁንም አልቆሙም፡፡

በየአካባቢው መብቱ ተነፍጎ በቀየው እንዳይኖር በልዩ ልዩ ምክንያት እየተፈናቀለ ያለውን ሕዝባችን ለማጽናናትና ለመደገፍ በአንድነት መቆም ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን የመንከባከብ የመጠበቅና ዕንባቸውን በማበስ ፍትሕንና ርትዕን የማንገሥ ኃላፊነት አለባት፤ ይህንን ኃላፊነት በአስተውሎት ልትወጣው ይገባል፡፡

በመሆኑም መጪው ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያለው ውጣ ውረድ በማስተካከል መልክ የምታስይዝበት፣ የተፈናቀሉ ልጆችዋን የምታጽናናበትና የምታግዝበት እንዲሁም ለፈተና የተጋለጡ ልጆቻችን ሁሉ የዜግነት፣ የሃይማኖትና የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ሰላም ፍቅር፣ ፍትሕ፣ አንድነት በሀገር እንዲነግሥ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ ሕዝቡን የሚያገለግልበት ዓመት እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በርትተን መሥራት አለብን፡፡ ይህንን ብናደርግ በእውነትም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰናል ማለት ነው፤ እኛ ከተመለስን እሱም ወደኛ መመለሱ አይጠረጠርም፤ ስለዚህ አሁንም ወደ እሱ እንመለስ፡፡

#በመጨረሻም
በሀገራችን ላይ ይልቁንም በቤተክርስቲያናችን ላይ ያለው ድባብ እጅግ በጣም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ለማንኛችንም ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ካህናትና ምእመናን በሃይማኖት ጸንተው እንዲቆሙ በቤተክርስቲያናችን ላይ እጃቸውን እየዘረጉ የሚገኙ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ጠላታቸው አይደለችምና እጃቸውን እንዲያነሡ፣ መንግሥትም ለቤተክርስቲያን የሕግ ከለላና ጥበቃ እንዲያደርግ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👍168
+ ትዳርና ሩካቤ +

ሩካቤ በባልና በሚስት መካከል መሳሳብን ይጨምራል፡፡ በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን አንድም በክርስቶስና በክርስቲያን ነፍስ መካከል ላለው አንድነትም ምሳሌ ነው፡፡ ይህ የሚኾነው ግን ክርስቲያኖች በትዳራቸው ውስጥም ቢኾን ራስን መግዛት ሲከናወን ነው፡፡ ባልና ሚስት፥ ፍቅራቸው በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ወዳለው ዓይነት ፍቅር ለማደግ መጣር አለባቸው፡፡
ምንም እንኳን ሩካቤ ማድረጉ ጤናማና የተፈቀደ ቢኾንም በሐዲስ ኪዳን ካለው የጋብቻ ዓላማ ውጭ ግን መኾን የለበትም፡፡ ራስን ሳይገዙ እንዲሁ ከልክ በላይ የሚያደርጉት ከኾነ ዝሙት ይኾናልና፡፡ ትዳሩ መንፈሳዊ ተግባራትን የሚያስበልጥ፣ አግባብ ባለው መልክም ሩካቤ የሚፈጸምበት ከኾነ ግን ባለ ትዳሮቹ በመንግሥተ ሰማያት ቀዳሚያን ናቸው፡፡ መኝታው ንጹህ የሚኾነው ራስን በመግዛት ሲፈጸምና በተፈቀደው ትዳር ውስጥ ሲኾን ነው፡፡ በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ላለው “መንፈሳዊ አንድነት” አምሳል መኾን የሚችለውም እንደዚህ ሲኾን ነው፡፡ ይህን ለመለማመድም ባልና ሚስት ምረረ ገሃነምን ቢያስቡ መልካም ነው፡፡ ዳግመኛም ራሳቸውን መግዛት ይችሉ ዘንድ ባልና ሚስት በስምምነት የሚፈጽሙት “የሩካቤ ጾም” ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ነገር ግን ተስማምተው ካልኾነ በቀር አንዳቸው አንዳቸውን በመከልከል ሊያደርጉት አይገባም፡፡ ሊቁ ይህን ይበልጥ ግልጽ ሲያደርግልን እንዲህ ይላል፡- “ጌታችን ክርስቶስ በቅዱስ ጳውሎስ አድሮ አንዱ አንዱን ሊከለክለው እንደማይገባ አስተምሯል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ግን እነርሱ ስላልፈለጉ ብቻና እንዲህ በማድረጋቸው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙ መስሏቸው ከገዛ ባሎቻቸው ጋር ሩካቤን ለማድረግ ፈቃደኛ አይኾኑም፡፡ ባሎቻቸውንም ወደ ዝሙትና ተስፋ ወደ መቁረጥ ይገፋፉአቸዋል፡፡” ስለዚህ፡- “በስምምነት ካልኾነ በቀር አንዱ አንዱን ሊከለክል አይገባውም፡፡ ‘ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነው?’ ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- ‘ባል ራሱን መከልከል ካልፈለገ በቀር፥ ሚስቱ [በግድ] ልትከለክለው አይገባትም፡፡ ሚስትም ራሷን መከልከል ካልፈለገች በቀር፥ ባሏ [ያለፈቃዷ] ሊከለክላት አይገባውም፡፡ ለምን? ታላላቅ ክፋቶች ወደ ትዳር ውስጥ ዘልቀው የገቡትና አድገውም ትዳሩን ያፈራረሱት በዚህ ዓይነት መከልከል ምክንያት የመጡ ናቸውና፡፡ መጀመሪያውኑ ከሩካቤ ለመታቀብ ባለመስማማትና አንዱ አንዱን በመከልከሉ ምክንያት ዝሙት፣ ሴሰኝነትና የቤተሰብ መበታተን ወደ ትዳር ውስጥ ገብተዋልና፡፡ አንቺ ሴት እስኪ ንገሪኝ! [አንዳንድ] ወንዶች ሚስቶች እያሏቸው እንኳን ዝሙት የሚፈጽሙ ከኾነ፥ ጭራሽ ሚስቶቻቸው የሚከለክሏቸው ከኾነ’ማ እንደ ምን ያለ ኃጢአት ይፈጽሙ ይኾን?”

በመኾኑም በስምምነት የማይደረግ ነገር የአንዳቸው ድካም ለትዳሩ ፈተና እንደ ኾነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለጊዜው ከሩካቤ መታቀባቸው በመፈቃቀድ የማያደርጉት ከኾነ በመካከላቸው ጠብ፣ ቊጣ፣ ግጭትና መቃቃር መናናቅም እንዲመጣ ያደርጓልና፡፡ ከዚህም የተነሣ በሰላምና በመደማመጥ መወያየትና መግባባት ከመካከላቸው ይጠፋልና፡፡ እነዚህ ከመካከላቸው ጠፍተው ሳለ የሚፈጽሟቸው በጎ ምግባራትም ረብ የለሽ ይኾኑባቸዋል፤ ፍቅር ቀድሞ ከመካከላቸው ጠፍቷልና፡፡ እንዲህም በመኾኑ ሊቁ፡- “ፍቅር ከጠፋ ታዲያ መጾማቸውና መታገሣቸው ኹሉ፥ ምን የሚያመጣላቸው ጥቅም አለ?” ይላል፡፡

እዚህ ላይ ሊጠቀስ የሚገባው ነገር፥ ባልና ሚስት ልጅ መውለድ የማይችሉ ቢኾኑም እንኳን ሩካቤ ሊያደርጉ እንደሚገባቸው ነው፡፡ ሊቁ እንደ ነገረን የጋብቻ ተቀዳሚ ዓላማ ጽድቅን መፈጸም እንጂ ልጅ መውለድ ብቻ አይደለምና፡፡ ስለዚህ ኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ልጅ ባይወልዱ (መካን ቢኾኑም) እንኳን፥ አንደኛ ከኃጢአት እንዲጠበቁ ስለሚያደርጋቸው፣ ኹለተኛ አንድነታቸውን ጽኑዕ ስለሚያደርገው፥ ራሳቸውን ገዝተው ካልኾነ በቀር “ልጅ ካልወለድን” ብለው ሩካቤን ማድረግ እንደ ነውር ሊመለከቱት አይገባም፡፡ ዳግመኛም መካን ቢኾኑም እንኳ መፋታት አይገባም፡፡ ልጅ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለምና (ዘፍ.30፡2)፡፡

(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3634❤‍🔥2
#ምን_ይጠቅምሃል?

ከእግዚአብሔር ባልሆነ ክብር መክበርን ለምን ትሻለህ? ክብርን ፍለጋ ከቆላ ወደ ደጋ፣ ከደጋ ወደ ቆላ ትወጣ ትወርዳለህ ለመሆኑ ክብር ከወዴት ናት ያለችው? ክብር እኮ ባለክንፉ መልአክ ክንፍ ስላለው የማያገኛት፤ እጅና እግር የሌለው ቶማስ ክንፍ ይቅርና እጅና እግር እንኳን ሳይኖረው የሚያገኛት ስጦታ ናት።

ዝጉሃዊ ባሕታዊ ከደጅ ሳይወጣ በበዓት ተከትቶ በሩን ዘግቶ የሚያገኛት ከሰማይ እንጅ ከምድር ያልሆነች ናት። ከእግዚአብሔር እንጅ ከሰው አይደለችም።

ክብርን መሬት ለመሬት አገር ላገር እየዞርህ መፈለግህን ተው። ሰው በተሰበሰበበት ሕዝብ በበዛበት ዐደባባይ ተገኝቼ ካልተናገርሁም አትበል። እንደዚህ ባሉ ቦታዎች ያገኘኸውን ክብር ከአንድ ቀን በኋላ አታገኘውም። ቅዱስ ጳውሎስ ከበርናባስ ጋር በሊቃኦንያ ከተሞች በሰበከ ጊዜ ሕዝቡ ተገረሙበት በሊቃኦንያም ቋንቋ አማልክት በሰው አምሳል መጡልን አሉ።
ነገር ግን በበነጋው ጳውሎስን የሞተ እስኪመስላቸው ድረስ በድንጋይ ወገሩት።

ትናንት ዕጣን ሊያጥኑለት መሥዋዕት ሊያቀርቡለት ለነበረው ሰው ድንጋይ ያነሡበታል ብለህ ታስባለህ? ሰዎች ያመጡልህን ክብር መልሶ ለመውሰድ ጊዜ አይፈጅባቸውም። እግዚአብሔር ግን ከሰጠህ አይወስድብህም። ሰዎች ስላልሰጡህ ክብር ማዘንህ በፊትህ መጥቆር ይታወቅብሃል፤ ነገር ግን ያ ክብር ከእግዚአብሔር ካልሆነ ምን ይጠቅምሃል?
ከእግዚአብሔር በሆነ ጊዜ ደግሞ አንዳች ነገር ሳይቀንሱ ያመጡልሃል።

የደብረ ጽሙናው አባ ሲኖዳ በሕይወት ሳሉ በገዳማቸው ዙሪያ ከሚኖሩ ሰዎች ክብርን አልተቀበሉም ነበር። እንዲያውም ይባስ ብሎ ከገዳማቸው አሳደዷቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር ክብራቸውን ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ገለጠው። ያሳደዷቸው ሰዎች በሕይወት ባያገኟቸውም አፅማቸው ባረፈበት ቦታ ሂደው ይቅርታ ጠየቋቸው። በሕይወት ሳሉ ማንም አልተከተላቸውም በባዶ እግራቸው ከገዳሙ ወጡ። ክብራቸው ሲገለጥ ግን በፈረስ በበቅሎ አፅማቸውን ጭነው አመጧቸው።

የክብር ቀን አለ፤ ዛሬ ይሁን ብለህ አታስቸግር።
የመገለጥ ጊዜ አለ፤ አሁን ግለጠኝ ብለህ ፈጣሪህን አትለምን። የምትከበርበት አገር አለህ ያለ ቦታህ መጥተህ አክብሩኝ አትበል። አብርሃምን ያከበረው በካራን ሳይሆን በከነዓን መሆኑን አስብ። ያለ ሀገርህ በባዕድ ምድር ክብረ ሥጋን ክብረ ነፍስን ቢሰጥህ ምን ይጠቅምሃል? ክብር ደስታን የሚሰጠው በግብፅ ሳይሆን በከነዓን ሲሆን ነው። ዮሴፍ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከነዓንን አለመርሳቱን አስብ። ግብጽ በሰጠችው ክብር ራሱን አላስታበየም። ይልቁንም ራሱን እንደ ፈላሲ ቆጠረ እንጅ። በሚሞትበትም ጊዜ አጥንቶቹ ሳይቀር በግብጽ እንዳይቀሩ ለልጆቹ አሳሰባቸው።

ሰማያዊ ሀገር አለህ። በዚያ የተዘጋጀልህን ክብርም ታውቃለህ። የግብጹን ተወው። አገርህ ስትገባ አሁን ያማረህን ክብር ትወርሰዋለህ።

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2922
2025/07/08 15:31:29
Back to Top
HTML Embed Code: