Telegram Web Link
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” ማቴ.10÷16

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን!

አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
#ልንናደድ_የሚገባን_ማን_ላይ_ነው?

ብዙ ኃጢአቶችንና ወንጀሎችን የሠራ አንድ ሰው ለሠራው ኃጢአትና ወንጀል ሳይቀጣ ሲቀር አይተን ብዙዎቻችን እንበሳጫለን፡፡ ያ ሰው እንዲጠየቅና እንዲቀጣ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይኾን ከቀረ ግን ቅር እንሰኛለን፤ እንናደዳለን፡፡

እንዲህ የምንኾነው ግን የገዛ ራሳችንን ግብር ስለማንመለከት ነው፡፡ መበሳጨትና መናደድ ቅርም መሰኘት የሚገባን በገዛ ራሳችን ላይ ነውና፡፡ እያንዳንዳችን ለራሳችን እንዲህ ብለን ልንጠይቅ ይገባናል፦ "በሌሎች ሰዎች ላይ ስንት በደል ፈጸምሁ? ለዚህ በደሌስ ስንቴ ሳልቀጣ ቀረሁ?"

በራሳችን ላይ ብዙ ምሳሌዎችን እንደምናገኝ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህን ማወቃችን ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ የተቆጣነው ቁጣና የተበሳጨነው ብስጭት እንደ ጢስ ተኖ እንደ ትቢያ በንኖ እንዲጠፋ ያደርጓል፡፡ ከዚህም በላይ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር እንድናዞር ስለ በደልነውም በደል ይቅርታንና ቸርነትን እንድንለምን ያደርገናል፡፡

እንዲያውም እኛ በበደልነው በደልና ሌሎች ሰዎች በሠሩት ኃጢአት ልዩነቱን እናስተውለው ይኾናል፡፡ ምናልባት የእኛ በደል የተሰወረና ለሌሎች ሰዎች የማይታይ ሕቡዕ ይኾናል፤ በአንጻሩ ደግሞ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የሚታይ ይኾናል፡፡

ታዲያ በዚህ ኹኔታ የእኛ በደል ንኡስ፥ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት ግን ዐቢይ እንደ ኾነ ልናስብ ይገባናልን? በጭራሽ! ምክንያቱም በስውር የሚሠ'ራና ሌላ ሰው የማያየው በደል ብዙውን ጊዜ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ስርቆትንና ቀማኛነትን የመሳሰሉ በግልጽ የሚታዩ ኃጢአቶች ኃጢአት መኾናቸው በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ መታወቃቸው ብቻም ሳይኾን በቀላሉ ንስሐ ሊገባባቸውና ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ውሸትን፣ ሐሜትንና በስውር ማታለልን የመሳሰሉ በስዉር የሚሠሩ በደሎች ግን በደል መኾናቸውን ለማወቅም ስለ እነዚህ ንስሐ ገብቶ ለማስወገድም እጅግ ክቡዳን ናቸው፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ፡፡ ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡
#ይቅር_በለኝ ...

የምህረት ባለቤት፣ የይቅርታ ምንጩ፣ የርህራሄ ባህሩ፣ የአዛኝነት ልኩ፣ የተቀባይነት ሚዛኑ እግዚአብሔር ሆይ ምህረትህ ጥላ ይሁነኝ። አንተን በመበደል መትጋቴን ይቅር በል። አንተን በማሳዘን መዝለቄን እኔም ጠልቼዋለሁና ምህረት አድርግልኝ።

አንተን አውቄ እንዴት እንዲህ እኖራለሁ? የአንተ ልጅ መሆኔ በግብሬ እንዲገልጥ አቅም ሁነኝ። የኔ ጌታ እኔ ምንም አቅም እንደሌለኝ ገብቶኛል አቅሜ አንተ ሁን። በራሴ ስጋ ስለለበስኩኝ ይህም ስጋ የኃጢአት ዝንባሌ በውስጡ በመኖሩ ከስጋዬ ጋር ትግል ገጥሜ አንተን እንዳላሳዝንህ ደግፈኝ። አንተን የሚያከብር የአንተ ጸጋ ይብዛልኝ።

ስጋ ለእግዚአብሔር ህግ መገዛት ተስኖታል ተብሎ በቃልህ እንደተጻፈው በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ተገዝቼልህ ስጋዬ ደግሞ እንዲታዘዝህ እርዳኝ። ሁሌ ለነፍሴ ማድላት እንዲሆንልኝና ስጋዬን መጎሰም የምችልበት አቅም የምትሰጠኝ ጌታዬ ጸጋህን በውስጤ አፍስስልኝ።

ለቁጥር ለሚታክቱ ጊዜያት በአንተ ላይ መሸፈቴን አውቀዋለሁ፣ ብዙ ማጥፋቴን እና መበደሌን ተረድቻለሁ። ይቅር እንድትለኝ በፊትህ ቀርቢያለሁኝና የማይነጥፍ የምህረት ባለቤት እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለኝ። 

አንተን በድዬ ደስ ቢለኝ ምን ይርባኛል? አንተ በእኔ ተከፍተህ እኔ በድሎት ነኝ ብል ምንስ ይጠቅመኛል? ለአንተ ጀርባ ሰጥቼህ ፊቴ ለሌላው ቢገለጥ ትርፌ ምንድን ነው? ምን ይጠቅመኛል አንተ ካሳዘንኩኝ? ምንስ ይረበኛል ፍቃድህን አልፌ በፍቃዴ ብራመድ? ምንስ እረብ አገኛለሁ ከምትጠቅመኝ ከአንተ ሸሽቼ የስጋ መሻቴን ብከተል? ..... ምንም ምንም አልጠቀምም። ምንም ....

ልለይ እስኪ ከማይረባኝ አልሂድ በቃ ትላንት በሄድኩበት ጎዳና። በሰጠኸኝ በአዲሱ ቀን እኔም አዲስ ሆኜ መኖር እንድችል በጸጋህ ደግፈኝ። ትላንቴን ይቅር ልትል ታማኝ የሆንከው አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ በማይበጠስ የምህረት ሰንሰለት አጥረህ የምታኖረኝ አንተ ነህና ዛሬዬን በምክርህ እንድኖር ምህረትህን አብዛልኝ።

አድርጌው የማዝንበት ነገር አንተን አያከብርምና ክብርህ በሌለበት ህይወት ውስጥ እንዳልገኝ እግሮቼን እና ሃሳቤን ጠብቅ።  የማላዝንበት ነገር በማድረግ እንድኖር እና ልክ ላልሆነ ነገር ተሰልፌ ልክ እንደሆንኩኝ እንዳይሰማኝ ማስተዋልን አድለኝ።

ከላይ ስታይ መንፈሳዊ ውስጤ ሲታይ አለማዊ አልሁን፣ ሰዎች ሲያዩኝ ጥሩ ነገሬ አንተ ስታየኝ ግን መጥፎ ሆኜ አልገኝ፣ በአደባባይ መልካም በጓዳዬ መጥፎ አልሁን፣  ከጸጋህ የተነሳ አንተን በመምሰል ልምምድ ውስጥ አሳድገኝ። 

“እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥6
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
#ምክር_ዘቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

እስኪ ንገሩኝ! ከእናንተ መካከል ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አንዲት ምዕራፍ ወይም ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥቂት [በቃልህ] ድገም ቢባል ይህን ማድረግ የሚችል ማን ነው? አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ግን ይኼ ብቻ አይደለም፡፡ ከመንፈሳዊ ነገሮች አንጻር እንደዚህ አእምሮ የጎደላችሁ ኾናችሁ ሳለ ዲያብሎሳዊ በኾኑ ነገሮች ላይ ግን እሳት የላሳችሁ ናችሁ፡፡ እንዲህም በመኾናችሁ አንድ ሰው መጥቶ ዲያብሎሳዊ ዘፈኖችንና የዝሙት ሙዚቃዎችን ንገሩኝ ቢላችሁ፥ ከእናንተ መካከል እነዚህን በትክክል የሚያውቁና ደስ ተሰኝተው የሚደግሙአቸው ብዙ ሰዎችን ያገኛል፡፡

ለምንድን ነው እንደዚህ የምትኾኑት? ከእናንተ መካከል “እኔ መነኰሴ አይደለሁም፡፡ ሚስት አለችኝ፡፡ ልጆች አሉኝ፡፡ የቤተሰብ መሪ ነኝ” የሚል ምክንያት የሚያቀርብ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ለምን እንደዚህ ትላላችሁ? ብዙዎችን ያጠፋው “ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ለመነኰሳት ብቻ ነው” የሚለው አመለካከታችሁ ነው፡፡ ከመነኰሳቱ ይልቅ ይበልጥ ማንበብ ያለባችሁ ግን እናንተ ናችሁ፡፡ ይበልጥ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በዓለም የሚኖሩና ዕለት ዕለትም ቁስል የሚያገኛቸው ሰዎች ናቸውና፡፡ ስለዚህ ካለማንበባችሁም በላይ “የእኛ ማንበብ ትርፍ ነገር ነው” ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ የዲያብሎስ አሳብ ነው፡፡ ወይስ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ “ይህም ኹሉ እኛን ሊገሥጸን ተጻፈ” ያለውን አላደመጣችሁምን? (1ኛ ቆሮ.10፡11)፡፡

አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! ወንጌልን በእጅህ ለመያዝ ብትፈልግ አስቀድመህ እጅህን ትታጠባለህ፡፡ ታዲያ በወንጌሉ ውስጥ ያለውን ቃለ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ እጅግ አስፈላጊ እንደ ኾነ አታስብምን? ብዙ ነገሮች ምስቅልቅላቸው የወጣው በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ጥቅሙ እንደ ምን የበዛ እንደ ኾነ ማወቅ የምትሻ ከኾነ መዝሙረ ዳዊትን ስትሰማና የአጋንንትን ዘፈን ስታደምጥ ምን እንደምትኾን፣ ቤተ ክርስቲያን ስትኾንና ቤተ ተውኔት ስትቀመጥ እንዴት እንደምታስብ ራስህን መርምር፡፡ ያን ጊዜ በነፍስህ ላይ የሚስተዋለው ልዩነት እንደ ምን ታላቅ እንደ ኾነ ትገነዘባለህ፡፡ ነፍስህ አንዲት ብትኾንም ቅሉ እዚያ ስትኾንና እዚህ ስትኾን በአኳኋንዋ እንዴት እንደምትለያይ ታስተውላለህ፡፡ ይኸውም የተወደደ ጳውሎስ፡- “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” እንዳለው ማለት ነው (1ኛ ቆሮ.15፡33)፡፡ ስለዚህ ዘወትር ከመንፈስ ቅዱስ የኾኑ መዝሙራትን ልንሻ ይገባናል፡፡ ግዕዛን ከሌላቸው ፍጥረታት ያለን ብልጫ ይህ ነውና፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
መጠላትህን አትጥላው!

አሉታዊ ሰው ከመልካም ስራ ውስጥ እንከን ማውጣት ይችልበታል፤ ሰበብ የሚቀናው ሰው ስለሆነውም ስላልሆነውም ጉዳይ ምክንያት ከመደርደር ወደኋላ አይልም። የማይተው ልማድ ሁሌም ሲያሰናክለን ይኖራል፤ ውስጣችን የኖረው አመለካከት ዘወትር ከመንገዳችን እየቀደመ ሲያሰናክለን ይገኛል። ወዶ ሳይሆን ልማድ ስለሆነበት ብቻ ሰውን የሚያማ ሰው አለ፤ ፈልጎት ሳይሆን አብሮት ስላደገ ብቻ ዘወትር በመቃወም እድሜውን የሚፈጅ አለ።
ነገር ግን አንዳንዴ ተቃውሞ የፍቅርን በር ይከፍታል፤ በጭፍኑ መተቸት፣ ያለምክንያት መጠላት ማንነታችን ግልፅ እንድናወጣ ያግዘናል። ጭፍን ጥላቻ ወዳጆቻችን ይበልጥ እንዲወዱንና እንዲያከብሩን ያደርገናል።

አዎ! ጀግናዬ..! መቼ እንደሚጠቅምህ አታውቅምና መጠላትህን አትጥላው፤ በመገፋትህ አትናደድ፤ ባልሆንከው ስም በመጠራትህ አትበሳጭ፤ በመጨቆንህ አትማረር፤ በኑሮ ውድነቱ አታለቃቅስ። አንዳንድ ሁኔታዎች ብቸኛው አማራጭ  መቀየርና ማደግ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ተገንዘብ። ወደውም ይሁን ሳይወዱ፣ መርጠውም ይሁን ሳይመርጡ የለውጥንና የእድገትን መንገድ መጀመር ደግሞ ዋነኛው የህይወት ስኬት ነው።  ጠላቶችህ ሲጥሉህ ወዳጆችህ አብዝተው ከፍ ያደርጉሃል፤ ተቃዋሚዎችህ ስምህን ሲያብጠለጥሉ ፈላጊዎችህ ከእነርሱ በላይ በፍቅር ደጋግመው ያነሱሃል። አንዳንድ ጫና የፍቅር በር ሲሆን፣ አንዳንድ ፍቅር ደግሞ የውድቀት መንገድ ነው። አርቆ ተመልካች በቃላት አይሰናከልም፤ ስራውን ከልቡ የሚሰራ በፍፁም በኮሽታ አይደነግጥም፤ ስራውንም አያቆምም።

አዎ! ፍቅርን የሚጠሩ ጥላቻዎች አሉ፤ ለአዲስ መንገድ የሚያመቻቹ እንቅፋቶች አሉ፤ ወደፊትን የሚያስተካክሉ የአሁን ችግሮች አሉ። ክፉ ሰዎች ክፉታቸው እንደሚጠቅም አያውቁም፤ ከዳተኞችም ክህደታቸው ትርፍ እንዳለው አይረዱም። እንዴት? የክፋትን አስጠሊነትና አላስፈላጊነት የክፉዎችን ተግባር ብቻ በመመልከት ስለምንረዳ፤ የክህደትን መሪርነት ከዳተኞች በሚያስከትሉት ሃዘን፣ ለቅሶና ተስፋ የማያስቆረጥ ስሜት ስለምንገነዘብ። መጥፎ ሰው የመሆንን አላስፈላጊነት መጥፎ ሰዎችን ከማየት ውጪ ምንም ሊያሳውቀን አይችልም፤ የውሸትን አስከፊነት ዋሾ ከሆኑ ሰዎች በቀር ማንም ሊያስተምረን አይችልም። ዘረኝነትን ለመጠየፍ የዘረኛውን ተግባር መመልከት በቂ ነው። የተማሩትን የሚኖሩ፣ ያስተዋሉትን በተግባር የሚገልፁ፣ የህይወት ትምህርትን ከእያንዳንዱ የህይወት አጋጣሚዎቻቸው የሚወስዱ ሰዎች ደግሞ በተወራባቸው ወሬ የሚደነግጡ፣ በአሉባልታ የሚሸበሩና ስራቸውን የሚያቆሙ ሳይሆን ይበልጥ ትኩረታቸውን እራሳቸውና ምርጫቸው ላይ በማድረግ በአሸናፊነትና በበለጠ ድል አድራጊነት ወደፊት መጓዛቸውን የሚቀጥሉ ናቸው።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-

#ሲጸልይ_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡

#ሲያመሰግን_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

#ሲመጸውት_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

#ቅዱሳት_መጻሕፍትን_ሲያነብ_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
#ጾመ_ፍልሰታን_ለምን_እንፆማለን?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

🔴👉ፆመ ፍልሰታ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ተብሎ ተወስኖ ይጾማል።

#ፍልሰታ :- ፈለገ፣ ተሰደደ (ተገለጠ) ፣ መከፈት፣ መገለጥ፣ ከሚለው የግእዝ ስውር ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሳኤ ያመለክታል።

🔵👉የጾሙ ዋና ምክንያት ሐዋሪያት የእመቤታችንን የእረፍቷን ነገር አስመልክተው የጾሙት ፆም ነው።

🔴👉ታሪኩን በአጭሩ እንዲህ እንመለከታለን :-

🔵👉እመቤታችን በጥር እሁድ በ21 ቀን አረፋለች ። ሐዋሪያት በአጎበር አድረገው ወደ ጌቴሴማኔ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል። ዛሬ ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ስለዚህ አስክሬኗን በእሳት እናቃጥላለን ብለው ተነሱ።

🔷👉ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሯን ጨበጠው መልአኩ ሁለት እጁን ቆረጠው፣ እጁ ከአጎበሩ ተንጠጥሎ ቀረ ከዚህ በኃላ መላዕክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረዋታል።

🔴👉በ8 ወሩ በነሐሴ ሐዋርያት አስከሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎት እና በምህላ እሑድ ሥጋዋን ቀብረዋታል። ማስከኞ ተነስታለች። ከመትንሳኤ ወልድ/ እንደ ልጇ ትንሳኤ ያሰኘው ይህ ነው፡፡ በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይም ከ12 ቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ አልነበረም።

🔵👉ቅዱስ ቶማስም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት፣ ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ/ ከሚጓዝበት የደመና ጉዞ ላይም ለመውደቅ ወደደ ተበጠበጠ፣ ቀድሞ የልጇን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ፣ አይዞህ አትዘን ወንድሞችህ ሐዋርያት ትንሳኤዬን ዕረገቴን አላዩም አንተ አይተሀል ፣ ተነሳች አረገች ብለህ ንገራቸው ብላ ምልክት ይሆነው ዘንድ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው።

🔴👉 ከዚህ በኃላ ቶማስ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው አግኝተን ቀበርናት አሉት፣
ሞት በጥር በነሐሴ መቃበር ተው ይሄ ነገር አይመስለኝም አላቸው።

🔷👉 ቅዱስ ጴጥሮስም አንተማ ልማድህ ነው ፣ አንተ ብቻ ተጠራጥር አትቀርም አንተ እየተጠረጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው።

🔴👉እርሱም የያዘውን ያውቃልና ፀጥ ብሎ ይሰማቸዋል። ከዚህ በኃላ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፈተው አጣት፣ ደንግጦ ቆመ፤  አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሰታለች፣ አረጋለች አላቸው  የያዘውን ሰበን ሰጥቶአቸው ለበረከት ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተበታትነዋል።

🔶👉 በዚህ ምክንያት በአመቱ ቶማስ ትንሳኤሽን፣ ዕረገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ቅዱሳን ሐዋሪያት ነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ  ሱባኤ በጀመሩ በ14 ተኛው ቀን  ትኩስ በድን አድርጎ ሰጣቸው ከቀበሯትም በኃላ በነሐሴ 16 ቀን በክብር ተነስታለች።

🔵👉 በዚህ ቀን ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሶ እመቤታችንም ከልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህቺ ጊዜ ትፆማለች።

  🔵 እኛም ከእናታችን ከቅድስት ኪዳነ ምህረት በሱባኤውና በፆሙ ስንጠነክር የእሷ አማላጀነት የልጇ የመድሐኔዓለም ቸረነት ከመከራ ስጋና ከመከራ ነፍስ አድኖ ለንሰሀ ጥሪ እንደሚያበቃንና ቅዱስ ስጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንደሚፈቅድልን አምነን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባናል ።
፨፨፨ ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
​​​​የጾም ሥርዓቱና ጥቅሙ

‹‹መላው ሕዋሳታችን ካልጾሙ የምግብና መጠጥ ጾም ብቻ ዋጋ የለውም። መጽሐፉም  የሚለው ‹ወደ አፍ  የሚገባ ሰውን አያረክስም፤  ከአፍ  የሚወጣ እንጂ› ነው። ስለዚህ ዐይን ፣ ጆሮ፣ እግርና እጅ የመሳሰሉት የስሜት ሕዋሳታችን መጾም አለባቸው፡፡

ከምግብና መጠጥ ይልቅ የሚበልጡት እነዚህ ናቸው፡፡ ከምግብና መጠጥ  የምንቆጠበው በራሱ ኃጢአት ስለኾነ ሳይኾን ምግብና መጠጥ ሥጋን አጥግቦ በገደል ስለሚጥል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ስለሚጎትት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡

ስንጾምም  ከሐሜት፣ ከአሉባልታ፣  ከዝሙትና  በሐሰት  ከመመስከር፣ ወዘተ መቆጠብ አለብን::

የጾም መሠረቱ ሃይማኖት ነው፡፡ በሃይማኖት የተነሣ ለተወሰኑ ጊዜያት ከምግብና ከመጠጥ የምንከለከልበት ኹኔታ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ጾም ይህ ብቻ አይደለም፤ ሁለት ዓይነት መስመር አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአጽዋማት ወቅት ከምግበ ሥጋና ከኃጢአት ትከለክላለች፡፡

ከኃጢአት ዅልጊዜም እንከላከላለን፡፡ ከምግብ የምንከለከለው ምግብ ኃጢአት ስለኾነ ሳይኾን ከሃይማኖት የተነሣ ነው፡፡ ምግብ በልተን ፈቃደ ሥጋችንን ከምናደልብ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሥጋችንን ጎስመን ያለ ምግብና ያለ መጠጥ እግዚአብሔርን እያመሰገንን የምንኖርበትን ሰማያዊና ዘለዓለማዊ ሕይወት የምናስብብት መንገድ ነው፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡-

"ንጽሕት" ስንል፡-
ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር፣ ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት፡፡ "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ" ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል፡፡ (ተአምረ ማርያም)

"ጽንዕት" ስንል:-
ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት ቅዱስ ያሬድ "ወትረ ድንግል ማርያም" ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ)

"ክብርት" ስንል፡-
ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው እመቤታችንን ግን የምናከብራት "የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና፡፡

"ልዩ" ስንል፡-
ከእርሷ በቀር እናት ሆና ድንግል እመቤት ሆና አገልጋይ የሆነች በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና፡፡

በዚህም እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ እንላታለን፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin0
ወደ እኔ ና ሳበኝም

           በህይወታችን አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል? ሁሉ ነገር የሚደራረብባችሁ ዙሪያው ጨላማ የሚሆንባችሁ መከራው ሁሉ የሚከብዳችሁ ሸክም ሁሉ የሚጸናባችሁ ጊዜ አለ አይደል? ልክ እሱ ጊዜ ላይ ሆኜ በጣም ስጨነቅ ለአንድ ወዳጄን አማከርኩት እርሱም ይህን ጥቅስ ጠቅሶ ሊያጽናናኝ ሞከረ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማቴ 11፥28 ውስጤ በጥያቄ ተወጠረ ደካማ መሆኔን ተርድቶ ሸክሜ መክበዱን አውቆ ሳለ እንዴት ወደእኔ አይመጣም? እንዴት ወደ እኔ ና ይለኛል? በእኔ ደካማነት ያውም ሸክሜ ከብዶ  እንዴት እርሱ ድረስ ችዬ እሄዳለሁ? የሚል ጥያቄ ውስጤን ይንጠው ጀመረ።

            ጌታዬ ሆይ አንተ ወደ እኔ ና አቅሜን ታውቀው አይደል፤ አንተ ጋር እንዴት እደርሳለሁ? ሸክሜንስ ታውቀው አይደል እንዴት እችለዋለሁ? እኔ ግን እንደ ጴጥሮስ በማዕበል ውስጥ ሆኜ "ጌታ ሆይ አድነኝ" ስል እጣራለሁ። ጴጥሮስን እጁን ስበህ የማዕበሉን ሸክም አቅልለህ እንዳወጣኸው እኔንም ሸክሜን አቅልለህ ወደ አንተ ሳበኝ። ጌታዬ ሆይ ሳበኝ ሸክሜንም አራግፍልኝ ያኔ ሸክሜ ቀሏልና ከአንተ ኋላ እሮጣለሁ። ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነውና ስምህን በላዬ ላይ አፍስልኝ ደናግል በወደዱህ መውደድም ልውደድህ። ጌታዬ ሆይ ሰሎሞን በመኃልየ መኃልዩ "ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።" እንዳለ እንደደናግሉ ያለ ፍቅር በእኔ ልብ የለም። የተገዛውላቸውና  የማደርጋቸው ሥጋዊ ምኞቶቼ ሸክም ሆነው ከብደውኝ ወደ አንተ መድረስ አልቻልኩምና ሸክሜን አራግፈህ ሳበኝ በእራሴ ወደአንተ መምጣት አይቻለኝምና።

             ጌታዬና መድኃኒቴ ሆይ ማቴዎስን ከቀራጭነቱ ሸክም አላቀህ ተከተለኝ እንዳልከው እኔንም ሸክሜ አላቀህ ተከተለኝ በለኝ። ወደቤቴ ግባና እንደዘኪዮስ ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኗል የሚል ቃልን አሰማኝ። ይህን ለማድረግ ዛፍ ላይ መውጣት ካለብኝም እንደ ዘኪዮስ ምድራዊ በሆነ በሾላ ዛፍ ላይ ያይደለ ሥሮቿ በምድር ቅርንጯፋ በሰማይ የሆነችውን ዛፍ/ሀረግ/ እናትህን እርሷን ተጠግቼ በእርሷ አማላጅነትም ተንጠላጥዬ አንተን ለማየት ተስፋ አደርጋለሁና ጌታዬ ሆይ ወደ እኔ ና ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልም በለኝ።

         ይህን እያሰብኩ ወደተነሳሁበት ጥቅስ ኀሊናዬ መለሰኝ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማለቱ ለካ የሚያሳየው ቅርብ መሆኑን ነው። ኑ ማለቱም እንዳግዛችሁ ፍቀዱልኝ ሲል ነው ለካ! ጌታዬ ሆይ አንተ በሁሉ የሞላህ አይደለህ የትም ብሔድ አንተ ከእኔ ጋር ነህ ስለዚህ ጌታ ሆይ አድነኝ ሳበኝም ሸክሜንም አራግፈህ አሳርፈኝ። ይኸው ፍቃዴን ሰጥቼሀለሁ ጌታዬ ሆይ አሳርፈኝ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
#ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ

እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ።

በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ።

የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ።

በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ።

እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን።
#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
ይህ መልዕክት የአብዛኛዎቻችንን ችግር የሚፈታ ስለሆነ በአጽንኦት ይነበብ

ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ እንዲሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች” እንዳለው እግዚአብሔርን የመጠማታችንን ልኬት ለመጸለይ ባለን ጉጉት እናውቀዋለን። የምንወዳቸውን ስናስብ ምን ይሰማናል?
የሚናፍቁንን ሰዎች በስልክ ስናወራስ ደስታችን ምን ያህል ነው በእውነቱ በቀን የስንት ብር የሞባይል ካርድ እንሞላለን ምንስ ያህል ሰዓት ከምንወዳቸው ጋር እናወራለን__እንዲህ የናፈቅነውን ሰው በአካል ስናገኝስ ምን ያህል ደስ ይለናል?
እግዚአብሔርን ማናገር ማዋራት ማዋየት ጸሎት ይባላል፡፡

እግዚአብሔር በየዕለቱ ሊያዋራን ይፈልጋል:: በየደቂቃው እርሱ ያንኳኳል አስቡት በደንብ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ እኛ ምን ያህል ክፉዎችና በደለኞች እንደሆንን እያወቀ እንኳን ሊያናግረን ይፈልጋል፡፡ እና ልታናግረው አትፈልግም?

ጸልዬ እኮ አላውቅም !

ቤተክርስቲያን ሄጄ ስሳለም ካልሆነ በቀር በግሌ ምንም ጸሎት አድርጌ አላውቅም ትለኝ ይሆናል፡፡ አንተ እግዚአብሔርን አናግረኸው አታውቅ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ስንት ጊዜ አናግሮሀል ስንትስ ጊዜ ሳታውቀው ሰምተኸዋል። ይሄ አያሳስብህ፤ አንተ ሄደህ የእግዚአብሔርን በር አታንኳኳም። እርሱ በርህን ያንኳኳልና አስገባው፡፡ በጣም ቀላል ጸሎት እነግርሀለሁ…በጣም ቀላል።

ሥራዬ እና ያለኝ ጊዜ የተጣበበ ነው ለመጸለይ ጊዜ አጣለሁ::

ይገባኛል ጭንቀትህ...ጸሎት ሥራ አይደለም፡፡ የምትደሰትበት እግዚአብሔርን የምታወራበት እንደ አባት የምታማክርበት ያንተና የእግዚአብሔር ሰዓት ብቻ ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ለእግዚአብሔር አንድ ደቂቃ አታጣም፡፡ አንድ ደቂቃ ደግሞ ከሰጠኸው ከቤተክርስቲያን ተወዳጅ ጸሎቶች አንዱን የአንድ ደቂቃ ጸሎት አስተምርሀለሁ፡፡ በጣም ቀላል ኦርቶዶክሳዊ ጸሎት እነግርሀለሁ አንድ መስመር ብቻ የሆነ ጸሎት "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ማረኝ" (ኪርያላይሶን)

"አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ ምህረት የባህርይህ ነውና እኔን ደካማውን ኃጥእ ልጅህን ማረኝ፡፡ በእኔ የሚሆን አንዳች ነገር የለምና በምህረትህ ይሁን ፍቅር ነህና ማረኝ".....  ይህንን ጸሎት ለመጸለይ አንድ ደቂቃ በቂ ነው፡፡ እስቲ ከዚህ ጀምር ይህንን ጸሎት ቀስ እያልን እንደጋግመው ቃላቱን በተረጋጋ ልብ አንድ በአንድ እያስተዋላችሁ የነገርኳችሁን በልባችሁ አመላልሱት፡፡ በሐዋርያቱ ብዛት አስራ ሁለት ጊዜ እየደጋገማችሁ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ማረኝ" ብላችሁ ጀምሩ፡፡

መቼ እና የት እንጸልይ ?

ዛሬ ጀምሩት ማታ ከመተኛታችሁ በፊት አባታችንን እግዚአብሔርን አናግራችሁት ተኙ ጠዋት ስትነሱም አስታውሳችሁ አናግሩት፡፡

ዛሬ ያንተ ቀን ይሁን፡፡ በሥራ በጣም ከተጨናነቅህ እረፍትን እንዲሰጥህ ሥራህ ቦታ ጸልየው ትምህርትህ ላይ ሆነህ አስበው አንዷን ደቂቃ ስታገኛት ወደ እረፍትህ መጀመሪያ ናት እግዚአብሔርን አናግረው፡፡ ታክሲ ውስጥ መንገድ ላይ አንዷን ደቂቃ ባገኘሀት ቁጥር አባትህን አውራበት፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
​​ነሃሴ_7
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ቁጽረታ (ጽንሰታ)ለማርያም

ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል።

ስለ
ምን ነው_ቢሉ :- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው። አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ።

"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ።" - "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው።"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)

ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል።

የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር።

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር። ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ። እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም።

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው። አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች። "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች።

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ። ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ። በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ።

እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች። ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ።

በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች።
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" - "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ። (ቅዳሴ ማርያም)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(John Chrysostom. C.349-407) Archbishop of Constantinople
=====================================
ቅዱስ ዮሐንስ በዘመኑ ለተነሱት መናፍቃን የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና እውነታውን አስረግጦ አስተምሮአል። መናፍቃን "ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከ ምትወልድ አላወቃትም የሚለውን "ማቴ1፣25። ተብሎ ስለተጻፈ ድንግል ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር በትዳር ኖራለች ብለው ለተነሱበት የተሳሳተ ሃሳብ ሲመልስ፣እስከ የሚለው ሃረግ ወይም ቃል " ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከምትወልድ አላወቃትም ማለት አንድም ወንድ እንደማታውቅ አንድም እስከ የሚለው ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው ፤ በመሆኑም ጌታን እስከምትወልድ የምትወልደው መድኃኔዓለምን እንደሆነ አላወቀም፣ የድኅነት ምክንያት ሆና እንደተመረጠች አያውቅም ነበር፣ በሉቃስ ወንጌል ላይም ማርያም ነገርን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ስለነበር ከቅዱሳን የከበረች ከመላዕክትም የበለጠች እንደነበር አያውቅም ነበር ። በሌላው ጌታን በፀነሰች ጊዜ ገጽዋ ይለዋወጥ ነበር ይህንንም ሲያይ ዮሴፍ ጻድቅም ስለነበር ሳይገልጣት ተዋት።

 ሌላው መናፍቃኑ ያነሱ የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ " የጌታ ወንድሞች ተብሎ በማቴ12፣46-50፤ ማር3፣31-35 ፤ሉቃ 8 ፣19-21 ላይ የተመዘገበውን ፅንሰ ሃሳብ በመያዝ ማርያም ሌላ ልጆች አሉዋት ከዮሴፍ የተወለዱ ለሚሉትም ዮሐንስ አፈወርቅ መልስ ሲሰጥ ፤ በመስቀሉ እግር ሥር የከናወነውን ምስጢር አራቆ በመተርጎም እንዲህ አስተምሯል
ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ መናፍቃን እንደሚሉት ከዮሴፍ ጋር በሚስትነት ኖረች ካሉ። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በመስቀል ላይ ሆኖ በዕለተ አርብ ከመስቀል ሥር ለነበረችው እናቱ እነሆ ልጅሽ አላት ፣ ልጆች አሏት ካሉ ለምን በመስቀል ሥር አልተገኙም ፣ ለሚወደው ደቀ መዝሙርስ ለምን በአደራነት ሰጠው ወደ ቤቱስ እንዲወስዳት ያዘዘው ብቸኛ ስለነበረች አይደለም እንዴ ይህንን ልብ ብለን እናስተውል በማለት አስተምሯል።በሌላው ለምን ወንድሞቹ ተባሉ የሚል ጥያቄ ከተነሳ በመንፈሳዊ ሕይወት አንድ ኅብረት ያላቸው ወንድማማች ስለሚባሉ፤ በሌላው ዮሴፍ ከቀድሞ ትዳሩ ባለቤቱ የወለዳቸውና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው ያደጉ የዮሴፍ ልጆችም ነበሩና ፤ከምንም በላይ ግን ዮሴፍን በምስጢር የድንግል ማርያም እጮኛ ጠባቂ እንዳደረገ የምስጢረ ሥጋዌንም ነገር ያለጊዜው ላለመግለጥ ምስጢር ለማድረግ ነው ። አበው እንስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና።
ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ ድንግል ናት። ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ ድኅረ ፀኒስ ድንግል። እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከመውለዷም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም በትንቢት እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ሕዝቅኤል (በምዕራፍ 44 ቁጥርም 1-4) ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል። ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐዬ ፅድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና (ዮሐ1፣5) ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃልዬ መኃልይ መዝሙሩ "እህቴ ሙሽራዬ ሆይ የተዘጋ ገነት የታተመ ፈሳሽ ነሽ" በማለት ስለዘላለማዊ ድንግልናዋ ጽፏል።(መኃ4፣12)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
በድያለሁ ይቅር በለኝ የሚለውን ሰው እግዚአብሔር ይቅር እንደሚል

የማይበድል ሰው የለምና … ኃጢአት ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፉም አድርገናል ብለው ቢለምኑህ፥  … ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በማደሪያህ በሰማይ ስማ፥ ፍርድንም አድርግላቸው፤ አንተንም የበደሉህን ሕዝብህን ይቅር በል። አሁንም፥ አምላኬ ሆይ፥ በዚህ ስፍራ ወደሚሆነው ጸሎት ዓይኖችህ የተገለጡ፥ ጆሮችህም የሚያደምጡ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ።

2ዜና 6÷36-40

ማብራሪያ

ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተንበርክኮና እጁን ዘርግቶ የጸለየው ጸሎት ነው፡፡ አምላኩ እግዚአብሔር የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን እንዲሰማው ይማጸናል፡፡ 

የሰሎሞን ጸሎት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይቅርታን እንዲሰጥ ነው፡፡ ጸሎቱ የቀረበው እርሱ በማይኖርበት ዘመን ( በአካለ ሥጋ በማይኖርበት ጊዜ) እስራኤል ቢበድሉት ይቅር እንዲላቸው ነው፡፡ ሰሎሞን  የእስራኤል ልጆችን በጸሎቱ ለእግዚአብሔር አሳልፎ የሚሰጥበት ነው፡፡

እስራኤል እግዚአብሔርን ስለ በደሉ በጠላት ፊት ድል ተመትተው ወደ እርሱ ቢመለሱ፥ ስምሙንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት በፊቱ ቢጸልዩና ቢለምኑት እንዲሰማቸው ፣የሕዝቡንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር እንዲል ልመና ያቀርባል፡፡ ቁ 24ና 25

እግዚአብሔርን ስለ በደሉ ሰማያት በተዘጉ ጊዜ ዝናብም ባልዘነበ ጊዜ፥ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስሙንም ቢያከብሩ፥ ባስጨነቃቸውም ጊዜ ከኃጢአታቸው ቢመለሱ እንዲሰማቸውና ይቅር እንዲል እንዲሁም ዝናብን እንዲሰጣቸው ይማጸናል። የሰሎሞን ልመና የማይበድል ሰው የለምና  በድለናል ብለው ፊትህ ከቀረቡ ጸሎታቸውን ስማ ፤ ይቅር በላቸው ነው፡፡

ለሰሎሞን ጸሎት እግዚአብሔር ምላሽ ሲሰጥ እናያለን፡፡

እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው፡- ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ … በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈግሉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ። 2ዜና 7÷12-14

የእግዚአብሔር ምላሽ ሰው: -  በድያለሁ ይቅር በለኝ ብሎ ቢጸልይ እንደሚሰማውና ኃጢአቱን ይቅር እንደሚለው ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት እንደዚህ አይነት አምላክ ነው፤ በድለነው ክፉ የምንለውን ነገር ቢያመጣብን ሰውነታችንን አዋርደን ስንጸልይና ፊቱን ስንፈልግ የሚሰማ አምላክ ነው፡፡

ስለ እስራኤል ልጆች የጸለየው ንጉሥ ሰሎሞን በስተ መጨረሻ ግን የማይበድል ሰው የለምና እንዳለው እርሱም እግዚአብሔርን በመበደል አሳዘነ፡፡ የአሕዛብን ሴቶች በማግባቱ ጣኦትን አመለከ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ተገልጦ ተቆጣው፡፡ ቸር አምላክ ነውና ፈጽሞ ግን አልተለየውም፡፡ 2ነገ 11÷1-13

በእርግጥም እግዚአብሔርን ከአዳም ጀምሮ አሁን እስካለነው ድረስ ያልበደለ የለም፡፡ ይቅር ባይ አምላክ ግን በየዘመኑ ለነበሩት ሰዎች ይቅርታ ሲሰጥ ኖሮአል፡፡ ከእኛም ይቅርታውን አላራቀም፤ ቸር አምላክ በድለነው ይቅር በለን ብለን ከለመንነው የለመንነውንም አይነሳንም፡፡

እግዚአብሔር በስሙ የተጠራነውን ሕዝብ እንዲሁ እንደዋዛ የሚተው አምላክ አይደለም፡፡ የቆሸሸውን ልብሳችንን በማጠብ ደጋግመን እንደምንለብስ አንዘንጋ፡፡ ቆሸሸ ብለን ደህናውን ልብስ አንጥልም፡፡ እንደዚሁም ስለበደልን አንጣልም፡፡ ይቅር በለን በማለታችን ቸሩ አምላካችን ይቅርታውን ሰጥቶን በቤቱ እንድንኖር ያደርገናል፡፡

እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና፤ ሃሌ ሉያ

ቸርነቱ ለዘላለም ነውና፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
"#አሻጋሪዎች"

ሰባኪው በአንድ ቤተክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር
ያስተምራል። በየእለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ (ይማራሉ)። ከእነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ መሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው።

#አንድ_ቀን_ግን_እንዲህ_ሆነ
ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።” የሚለውን ማቴ. 17፥20 ያለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል ጠቅሶ ሰው በእምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳና የዕለቱን ስብከት አጠናቀቀ።

መሻገሪያ በሌለው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ። ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዚአብሔር አምናለሁ እግዚአብሔርም ይህን ለእኔ ማድረግ አይሳነውም" በማለት በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም የሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ ቤቱ ግባ።

ሚስቱም በመደንገጥ "ቤተክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ "ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው" ብላ "በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" በማለት ባለቤቷን ተማጸነች።

በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ ትምህርቱን ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄዶ፥ "ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው። በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን" ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ #እናሻግራለን እንጂ #አንሻገርም!" ሲል መለሰለት።

እኛስ የምንናገረውንና የምናዳምጠውን፣ የምናስተምረውንና የምንማረውን፣ የምንሰብከውንና የምንሰብከውን እየኖርን ነውን?

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
​​​​​​ሰንበት
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡

ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡

ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-

👉 እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
👉 ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
👉 ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
👉 የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት
👉 ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
👉 የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡

ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚትማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)

በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)
ከሰንበት ረድኤት በረከት ይካፍለን!
ሌሎች እህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ክብረ መንግሥቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሳችሁ !

“ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን”

ሌላኛው (ወንጌላዊ) “ከስምንት ቀን በኋላ”   ይላል ። ይህም ከማቴዎስ ጋር በደንብ ይስማማል እንጂ አይጋጭም ። ሉቃስ የተናገረበትንና ይዟቸው የወጣበትን ቀን ሲገልጽ ማቴዎስ ግን በመሐል ያሉትን ቀኖች ብቻ ይገልጻል። ነገር ግን ልብ በሉ እጸልይላችኋለሁም የማቴዎስን መልካምነት ተመልከቱ ፤ እርሱ ሳይመረጥ የተመረጡትን አልሸሸጋቸውም ። ዮሐንስም ብዙ ጊዜ በልበ ቀናነት የጴጥሮስን እንግዳ ምስጋናዎች በመመዝገብ እንዲህ ያደርጋል ። የእነኚህ ቅዱሳን ሰዎች አገልግሎት በሁሉም ቦታ ከቅንዓትና ከከንቱ ውዳሴ የጸዳ ነው ።

“ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው ። በፊታቸውም ተለወጠ ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ ። እነሆም ፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው ።” 

እነዚህን ብቻ ከእርሱ ጋር የወሰደው ስለ ምንድር ነው ? ምክንያቱም እነዚህ (ሦስቱ ሐዋርያት) ከሌሎቹ ስለሚበልጡ ነው ። ጴጥሮስ ብልጫውን (ጌታን) እጅግ በመውደድ ፣ ዮሐንስ ደግሞ በእርሱ (በጌታ) እጅግ አብልጦ በመወደድ አሳይተዋል ። ያዕቆብ ከወንድሙ (ከዮሐንስ) ጋር ጽዋውን መጠጣት እንችላለን ብሎ በመመለሱ  ፣ በመልሱ ብቻ ሳይሆን በሥራውም ነው ። ይህም ሌሎች ሥራዎችን በመሥራትና ያለውን በመፈጸም ነው ። እርሱ ቅን የነበረ ቢሆንም ለአይሁዳውያን ግን የሚያስጨንቅና የሚያሳዝን ነበር ። ሄሮድስ ራሱ ያዕቆብን በሰይፍ ያስገደለው አይሁዳውያንን ደስ ለማሰኘትና ታላቅ የሆነ ውለታ እንደ ዋለላቸው በማሰብ ነው ።

ነገር ግን ለምንድር ነው ወዲያውኑ ወደ ተራራ ያላወጣቸው ? (ይህንንም ያደረገው) ሌሎቹን ደቀ መዛሙርት ከሰብአዊ ድካም ለመጠበቅ ነው ። ለዚህም ሲል ከእርሱ ጋር ወደ ተራራ የሚወጡትን ደቀ መዛሙርት ስም በግልጽ አልተናገረም ። ምክንያቱም (ስማቸውን ቢጠራ ኖሮ) የተቀሩት እርሱን ለመከተልና የክብሩን ነጸብራቅ ለመመልከት አብዝተው ስለሚፈልጉ እንደ ተረሱ ይሰማቸው ነበር ።

ለምን ታዲያ አስቀድሞ ተናገረ ?   አስቀድሞ በመናገሩ ታላቅ የሆነውን እውነት ለመያዝ ዝግጁ እንዲሆኑና በጊዜውም በነበረው ጥልቅ ስሜት ተሞልተው ፍጽም ንቁ በሆነ አእምሮአቸው እንዲገኙ ነው ።

ሙሴና ኤልያስን ለምንድር ነው ያመጣው ? ብዙ ምክንያቶችን ልናቀርብ እንችላለን ፦ የመጀመሪያው አንዳንዶች ኤልያስ ሌሎች ኤርምያስ አልያም ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ ነው ይሉ ነበርና የነቢያት አለቃ የሆነውን (ኤልያስን) በማምጣት በአገልጋይና በጌታ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲመለከቱ አስቦ ነው ። በዚህም ጴጥሮስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ለሚለው ምስክርነት የተሰጠው ምስጋና ትክክለኛነት ተገልጿል ።

ሆኖም ግን ከዚህ በተጨማሪ አንድ ሰው ሌላ ምክንያቶችንም መጥቀስ ይችላል፦ ሰዎች ክርስቶስ ሕግን ተላልፏል ፣ የራሱ ያልሆነውን የአብን ክብር ለራሱ አድርጓል ፣ የእግዚአብሔርንም ስም ያጠፋል ብለው ከሰውት ነበር ። እንዲህም አሉት፡- “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም”   በሌላም ስፍራ አይሁድ ይህንን ተናገሩ፡- “ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም ፤ ስለ ስድብ ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት ።”   (ክርስቶስ ግን) እነዚህ ሁሉ ክሶች ከቅናት እንደ መጡ ፣ በአንዱም እንኳን ተጠያቂ እንዳልሆነ ፣ ጠባይና ተግባሩም ሕጉን እንዳልተቃረነ ፣ አልያም ራሱን ከአባቱ ጋር እኩል አድርጎ መጥራቱ የራሱ ያልሆነን ክብር ለራሱ መስጠት እንዳልሆነ ለማሳየት በዚህ ረገድ ምስክር የሚሆኑትን ጠራቸው ። የሕጉን መፍረስ ሙሴ ችላ አይልምና ፣ ለሚተላለፈው ፣ ሕጉን የተቀበለው ሙሴ ጠላት ክብር አይሰጥምና ሙሴን ጠራው ። ልክ እንደዚሁ ኤልያስም በበኩሉ ለእግዚአብሔር ክብር ቀናተኛ ነበር ። እርሱም የእግዚአብሔርን ጠላት ፣ በሐሰትም ራሱን እግዚአብሔር ብሎ የሚጠራ ራሱን ከአብ ጋር የሚያስተካክልን ሰው አያደምጥም አይታገሥም (ነበርና ኤልያስንም ጠራው)። ደብረ ታቦር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደ ሰበከው !

የጸባዖት ብርሀን በጓዳችን ይግባ !
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
​​​​#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin
2025/07/06 23:26:17
Back to Top
HTML Embed Code: