Telegram Web Link
የእግዚአብሔር ፍቅር
 
የእግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን የሚከልል፣ ዘላለማዊ የሆነ ፣ ቅድመ ሁኔታዎችን ያላስቀመጠ ነው። ክርስትናችን የተመሠረተው በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ነው። እግዚአብሔር እኛን የወደደበት ፍቅር የክርስትና አዋጅ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ፍጹም በመሆኑ መሙላትና መጉደል አይታይበትም። እግዚአብሔር እንደሚወደኝ ምንም ዓይነት ስሜት አይሰማኝም ልንል እንችላለን። የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያረጋግጥልን ስሜታችን ሳይሆን ቃሉ ነው። እገሌን ለምን ወደድካት ቢባል ሙያዋን አይቼ፣ በጦር ሜዳ አተኳኮሷን ተመልክቼ የሚል ምክንያተኛ አለ። ቅልጥፍናውን፣ ቁመናውን አይቼ ወደድኩት የምትልም አትጠፋም ። የእግዚአብሔር ፍቅር ግን መስፈርት ያላስቀመጠ፣ በራሱ መውደድ ላይ የተመሠረተ ነው። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ህልውና፣ አካል፣ ክብርና ጠባይ አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር ከአካሉና ከህልውናው ጋር ለዘላለም የነበረ ነው። እግዚአብሔር ፍቅርን አልተለማመደም ፣ ፍቅርን አላዳበረም ። እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር ነው። ያለ ፍቅር የኖረበት ዘመን የለም። ፍቅሩ በዘላለም ውስጥ ስላለ ጊዜ ይለውጠዋል የሚል ስጋት የለብንም። ገና ኃጢአተኞች ሳለን፣ ገና ሙታን ሳለን፣ ገና ጠላቶች ሳለን ወደደን ስለሚል ወደፊት ማንነታችንን ሲያውቅ ይሸሸናል የሚል ጥርጣሬ የለብንም። 
ሰዎች የጎደላቸውን የሚሞላላቸው ሰውን ወደድሁ ይላሉ። ዝምተኛው ተናጋሪውን ፣ ሰነፉ ጎበዙን ፣ ፈሪው ደፋሩን ሊወድ ይችላል። ይህ ግን ነገረ ፈጅ ፣ እንደራሴ፣ ጉዳይ ገዳይ እንደ መቅጠር ነው ። እግዚአብሔር የወደደን የጎደለውን ስለምንሞላለት አይደለም። የመላእክት ትጋትም አያሻውም፣ እርሱ የመላእክትም ጠባቂ ነው። ሊሸከሙት አያስፈልገውም ፣ እርሱ ሁሉን የያዘ ነው። ይህን አገኝ ፣ በእገሌ እከብር ብሎ ማንንም አልወደደም። የወደደን ታመን ሳለ ከሆነ ድነው ውለታ ይመልሳሉ ብሎ ይሆናል። የወደደን ግን ሙታን ሳለን ነው። የምንወደውን ሰው እያስታመምን ቆይተን ሲሞት እንሸሸዋለን ፣ በሙት መዝገባችን ያልናቀን ፣ ከመቃብር ሕይወት ያወጣን የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ፍቅርን መግለጥ መሸነፍ ይመስለናል። በአገራችን ጥላቻን በአፍ መግለጥ፣ ፍቅርን በልብ መያዝ እየተለመደ ይመስላል። በተቃራኒው ቢሆን ይሻል ነበር። እግዚአብሔር ግን፡- “በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ” በማለት ለሚወዳት ነፍስ ይናገራል። ኤር. 31 ፡ 3 ። ከሰው ወገን ፍቅርን የሰጠኝ ማንም የለም የሚል ብሶት ካለን የእግዚአብሔር ፍቅር የሚያስፈልገው ለእኛ ነውና አሁን መቀበል ይገባናል። እግዚአብሔር በፍቅሩ ብዙ ነገሮችን ቢያደርግልንም አንድ ልጁን ለቤዛ ዓለም መስጠቱ የፍቅሩ መገለጫ ነው። ዮሐ. 3 ፡ 16። 
በዚህ ዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ፍቅሮች አሉ። አንዱም ፍቅር ከሞት አያድንም። ወዶኛልና አዳነኝ የተባለው ግን ለእግዚአብሔር ፍቅር ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ከዘላለም ሞት ያድናል።

ልዩ ልዩ ፍቅር አለ፡-


1፦ የአባት ፍቅር፡-

የአባት ፍቅር ያገኙ ልጆች ብርታት እንደሚሰማቸው ይናገራሉ። ይህን ፍቅር ያላገኙ ጠንካራ አይደለሁም የሚል ስሜት ይሰማቸው ይሆናል። ከአባት ፍቅር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል። አባት ወልዶ ሊክድ፣ እናት ወልዳ ልትረሳ ትችላለች እግዚአብሔር ግን ታማኖ የማይከዳ ፣ ሲወዱት የማይጠላ ነው። 

2፦ የእናት ፍቅር፡-

በዓለም ላይ የእናት ፍቅር ልዩ ነው። እናት ግን ልጅን ከመወለዱ በፊት ከሞትም በኋላ አታውቀውም። እግዚአብሔር ግን እናታችን ተፈጥሮዋን ሳታካፍለን በፊት ያውቀናል። ከሞት በኋላም አብሮን ይኖራል። የሚሞቱ አባትና እናትን የሰጠን የማይሞተው አባትና እናት እግዚአብሔር ነው። የሥላሴን አባትና እናትነት ዘንግቶ አባት እናት የለኝም የሚል ከንቱ ሰው ነው። 

3፦ የሙሽሮች ፍቅር፡-

ዕለታዊና ትኩስ የሆነው የሙሽሮች ፍቅር ትልቅ ነው ። ይህ ፍቅር ግን ጠባይ ሲገለጥ ይቅር ማለት እያቃተው ፣ ኑሮና ፍቅር አብሮ አይሄድም እያለ ሲዘናጋ ይስተዋላል። እግዚአብሔር ግን ያለ ፍቅር የፈጠረው ቅንጣት ነገር፣ የሚሠራውም ፍንጣሪ ነገር የለውም።

4፦ የወዳጅ ፍቅር፡-

ወዳጅ አብሮን የሚኖር ፣ አዘቅት ስንወርድ እጁን የሚዘረጋልን ፣ ሲያሙን የማያሳማን፣ ስንሞት የተውነውን አደራ የሚወጣ ነው። ወዳጅነት ጥልቅ ቢሆንም የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ይበልጣል። የልብ አውቃ የሆነው ወዳጅ ፣ ሰባት ጊዜ በቀን በድለነው ሰባት ጊዜ ማረኝ ስንለው ይቅር የሚለን ፣ ፍጹመ ምሕረት የሆነው እግዚአብሔር ነው።

5፦ የዘመድ ፍቅር፡-

የሰርግና የልቅሶ ስፖንሰር፣ አብሮ የሚያላቅስና የሚንጎራደድ የዘመድ ፍቅር ነው። የዘመድ ፍቅር ወገንነትን መሠረት ያደረገ ነው። “ትንሽ ሥጋ ከመርፌ ትወጋ” የሚል ነው። የዘመድ ፍቅር የራሱ የሆነ የልብ ሙላት ቢኖረውም የእግዚአብሔር ፍቅር ከዚህ በላይ ነው። ማርጀትና መለወጥ የለበትም።

6፦ የእንስሳት ፍቅር፡-

እንስሳት ፍቅርን ይሰጡናል። ስንመጣ በደስታ ይቀበሉናል። በዚህም ምክንያት እንወዳቸዋለን ፤ አንዳንዴ የማይለወጥ ፍቅርን በመስጠት ከሰው የተሻሉ ናቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ከዚህም በላይ ነው።

7፦ የሕዝብ ፍቅር፡-

ትልቅ ዕዳ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የሕዝብ ፍቅር ነው። ያንን ሕዝብ ላለማስቀየም ከባድ ጥረት ይጠይቃል። የሕዝብ ፍቅር ደስ ያሰኛል። የአንዱ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ከሕዝብ ፍቅር ይበልጣል ፣ ልብን ያሞቃል።

8፦ የንጉሥ ፍቅር፡-

ንጉሥ ሲወደን ደስ ይላል። እርሱን የመሰለ ሰው የለምና ለእኛ ድንቅ ነው፣ እኛን የመሰለ ሰው ግን ብዙ ያውቃልና ለእርሱ ብቸኛ ወዳጅ አይደለንም። የንጉሥ ፍቅር በአንገት ላይ ካራ አስሮ እንደ መቅረብ ነው። ቶሎም እያረጀ ያስቸግራል። ቢሆንም የንጉሥ ፍቅር ልብን ደስ ያሰኛል። እግዚአብሔር ሲወደን ግን ሌላ ሰው እንደሌለ አድርጎ ነው።

9፦ የሕፃናት ፍቅር፡-

ሕፃናት ፍቅራቸው ብርቱ ነው። የሚወዳቸውን ይወዳሉ ፣ ስጦታ ለሚሰጣቸው የተለየ ወንበር ያዘጋጃሉ። እኛም ሕፃንን የምንወደው ቢጠላንም ስለማይጎዳን ነው ። ቢሆንም የሕፃን ፍቅር ደስ ይላል። የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ከሕፃን ንጹሕነት በላይ ቅዱስ ነው።

10፦ የድሃ ፍቅር፡-

ድሃ የሚሰጠው ስለሌለው ራሱን ይሰጠናል። አያስነካንም፣ ሊሞትልን ይቀድማል። አብዛኛው በዓለም ላይ ያለው ወታደር ድሃ ነው፣ ድሃ ታማኝ ነው። ሬሳችንን የሚሸከም ባለጠጋው ወዳጃችን ሳይሆን ድሀው ወገናችን ነው። ከድሃ ፍቅር በላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶልናል። ራሱን ስለ እኛ ደሃ አደረገ የተባለለት የእግዚአብሔር ፍቅር ልዩ ነውና ምስጋና አቅርቡለት።

ለልባችሁ የቀረላችሁን አሳብ እስቲ ግለጡ። እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ!

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
👍3020
ፍቅርን የምትወድ ሁን

“በፍቅር ተመላለሱ” (ኤፌ. 512)

ይህ የሁሉም ነገር መሠረት ነው! ፍቅር ባለበት ቦታ ቁጣ፣ ጩኸት፣ ስድብ የለም፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተወግደዋል፡፡ ጳውሎስ አሳዳጅ ሳለ በእግዚአብሔር ፍቅር ድኗል፡፡ አንተስ ስለምን የእግዚአብሔር ልጅ ሆንክ? ምክንያቱም ይቅር ስለተባልክ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ዋጋው የማይተመን ስጦታ ተቀብለህ፣ እንዴት ለሌሎች አላካፍልም ትላለህ?

ይህን አስብ! ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወንጀሎች ተሸክመህ በእስር ቤት ተጣልክ፤ እናም አንድ ስው ከዚህ አውጥቶ ቤተ መንግሥት አስገባህ። ወይም ሌላ ምሳሌ ለመጠቀም፣ በጠና ታምመህ ለሞት ተቃርበህ ነበርና አንድ ሰው በመድኃኒት አዳነህ። ያን ሰው ከማንም በላይ ከፍ አድርገህ አትመለከተውም? የመድኃኒቱን ስም ስትሰማ እንኳ ደስ አይልህም? ከሥጋ ስቃይ ያዳነንን ከፍ አድርገን የምንወደው ከሆነ፣ ነፍሳችንን የሚያድኑትን መንፈሳዊ ስጦታዎች ምን ያህል እንወዳቸው ይሆን?

ፍቅርን የምትወድ ሁን፤ የዳንከው የእግዚአብሔር ልጅ ባደረገልህ ፍቅር ነውና! ሌላውን የማዳን፣ የመርዳት እድል ካለህስ ይህን ተመሳሳይ መድኃኒት አትሰጠውምን? “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤" እንደተባለው (ማቴ. 6፥14) በዚህ መንገድ አንዳችን የሌላኛችን አበርቺ፣ የሌላኛችን አመስጋኝ መሆናችን የተከበረ እና የለጋስ ልብ ምልክት ይሆንልናል።

ጳውሎስ በመቀጠል “ክርስቶስ ደግሞ እንደ ወደዳችሁ" ይለናል፡፡ እኛ ይቅር ማለት ያቃተን ወዳጆቻችንን ነው፡፡ ክርስቶስ ግን ጠላቶቹን ይቅር ብሏል፡፡ ከጌታችን የተቀበልነው ስጦታ ምንኛ ይበልጣል! ክርስቶስ እንደወደደን መውደድ ከፈለግን ለጠላቶቻችን እንኳን መልካም ማድረግ አለብን፡፡

ጳውሎስ “ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።" በማለት አክሎ ተናግሯል፡፡

ተመልከት… ስለሌሎች መከራ መቀበል ለጠላቶችም ቢሆን ጥሩ መዓዛ ያለው መባ ሲሆን፣ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው፡፡ ለሌሎች ብትሞት በእውነት መስዋእት ትሆናለህ፡፡ እግዚአብሔርን መምሰል ማለት ይህ ነው፡፡ እስከ መሥዋዕት መውደድ፣ በነጻ ይቅር ማለት፤ ክርስቶስ እንደ ተመላለሰ በፍቅር መመላለስ፡:
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
22👍11
#መጻጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት)

በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው "ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም" አለው። "ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ" ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ "የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ" እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ "በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና "በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ" እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡

ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

#የዕለቱ_ምንባቦች
1ኛ. የቅ.ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላ. 5÷1-26
2ኛ. የቅ. ያዕቆብ መልእክት 5÷14-20
3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3÷1-12

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 4ዐ(41)÷3
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።

(እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡) መዝ 4ዐ÷3  የሚለው ይሆናል፡፡

#የዕለቱ_የወንጌል
በዮሐንስ ወንጌል 5፥1-25 ድረስ ያለው ነው፡፡

#ቅዳሴ፦ ቅዳሴ እግዚእ

ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታች ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
👍2213
ተስፋ መቁረጥና ስንፍና

ተስፋ መቁረጥና ስንፍና እጅግ ክፉዎች ናቸውና ከእነዚህ እንራቅ፡፡

“ክፋታቸውስ እንደምን ያለ ነው?” ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- ተስፋ መቁረጥ የወደቀው ሰው እንደ ገና እንዲነሣ አይፈቅድለትም፤ ስንፍናም የቆመው ሰው እንዲወድቅ ያደርጓል፡፡ ስንፍና ገንዘብ ያደረግናቸውን መልካም ነገሮች ከማሳጣቱም በላይ ሊመጡ ካሉ ክፉ ነገሮች እንዳንጠበቅ ያደርገናል፡፡ ስንፍና ከሰማያትም ቢኾን ይጥለናል፤ ቀቢጸ ተስፋም ወደ ክፋት ዐዘቅት እንድንሰጥም ያደርገናል፡፡ በእውነት በቀቢጸ ተስፋ ካልተያዝን ከጽኑ ክፋት መመለስ ይቻለናል፡፡

እነዚህ ኹለቱ ምን ያህል ኃይል እንዳላቸው ይበልጥ ታውቅ ትረዳ ዘንድ ምሳሌ ጠቅሼ ልንገርህን? መልካም! ዲያብሎስ መጀመሪያ ላይ መልካም ነበር፤ ከስንፍናና ከቀቢጸ ተስፋ የተነሣ ግን እንደ ገና የማይነሣ ኾኖ ወደ ክፋት ወደቀ፡፡ ዲያብሎስ ጥንቱ መልካም እንደ ነበረ ሲናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለውን አድምጥ፡- “ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ” (ሉቃ.10፡18)፡፡ መብረቅ የሚለው አገላለጽ ዲያብሎስ ከመውደቁ በፊት ምን ያህል ብሩህ ሕይወት እንደ ነበረውና በምን ያህል ቅጽበት እንደ ወደቀ የሚያመለክት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ተሳዳቢ፣ አሳዳጅና ነውርን የማያውቅ ሰው ነበር (1ኛ ጢሞ.1፡13)፡፡ ነገር ግን ቀናተኛ ስለ ነበርና ተስፋ ስላልቈረጠ ተነሥቶ መላእክትን የሚተካከል ኾነ፡፡ ይሁዳ ሐዋርያ ነበር፤ ነገር ግን በስንፍና ምክንያት ጌታውን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ፈያታዊ ዘየማን ደግሞ እንደዚያ እጅግ ክፉ የነበረ ሰው ቢኾንም ቅሉ ተስፋ ስላልቈረጠ ኹሉንም ቀድሞ ገነት ገባ፡፡ ፈሪሳዊው ሰው ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ስለ ነበር ከምግባር ማማ ላይ ወደቀ፡፡ ቀራጩ ግን ተስፋ ስላልቈረጠ ከፈሪሳዊውም በልጦ ወደ ምግባር ሰገነት ወጣ፡፡

ስለዚህ ይህን ዐውቀን ዘወትር ከስንፍናና ተስፋ ከመቁረጥ እንራቅ!

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
👍2316
ሥራህን ሥራ

ሌሎች ሰዎችን ከማያድን ክርስቲያን በላይ የከፋ ምንም የለም፡፡ አንተ ሰው! ድኻ ነኝ የምትለኝ ለምንድን ነው? ኹለት ዲናር የጣለችዋ ሴት ትፋረድባሃለች፡፡ ከምናምንቴ ቤተሰብ እንደ ተወለድክ የምትነግረኝስ ለምንድን ነው? ሐዋርያትም ምናምንቴዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ታላላቅ መኾን ተችሏቸዋል፡፡ አለመማርህን ሰበብ አድርገህ አትንገረኝ፤ ሐዋርያትም ያልተማሩ ነበሩና፡፡

ባሪያ ብትኾንም እንኳ፣ ስደተኛ ብትኾንም እንኳ ሥራህን መሥራት ይቻልሃል፤ ሌሎችን መርዳት ይቻልሃል፤ ሰዎችን ማዳን ይቻልሃል፥ አናሲሞስም እንደ አንተ ዓይነት ሰው ነበርና (ፊልሞ.1፥10-11)፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ምን ወዳለ ማዕረግ ከፍ እንዳደረገውና ምን ብሎ እንደ ጠራው አድምጥ፡- “በእስራቴ ስለ ወለድሁት፡፡”

ወዳጄ ሆይ! እኔ እንኳን ሕመምተኛ ነኝ ብለህ አትንገረኝ፤ ጢሞቴዎስም እንደ አንተ ዘወትር ይታመም ነበር፡፡

ፍሬ የማያፈሩ ዛፎች እንደ ምን ብርቱዎችና ተወዳጆች፣ ግዙፋንና ሐመልማላውያን እንደዚሁም ረጃጅም እንደ ኾኑ አላየህምን? የፍራፍሬ ቦታ ቢኖረን ግን ፍሬ የሚያፈሩት ሮማንንና ወይራን እንተክላለን እንጂ እነዚህ ፍሬ የማይሰጡንን ዛፎች አንተክልም፡፡ ምክንያቱም እንዲሁ ለዓይን ማረፊያ ለማየት ካልኾነ በስተቀር ሌላ ጥቅም የላቸውምና፡፡

የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚመለከቱ፣ ሌሎች ሰዎችንም የማይረዱ ክርስቲያኖችም እንደ እነዚህ ዛፎች ናቸው፡፡ እንዲያውም ከእነዚህ ዛፎችም የባሱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የሚቆረጡት ለእሳተ ገሃነም ነው፡፡ ዛፎቹ ግን ቢያንስ ቢያንስ ጠረጴዛም ወንበርም ለመሥራት ይጠቅማሉ፡፡ ለቤት መሥሪያ ይጠቅማሉ፡፡ አጥር ቅጥር ኾነው ያገለግላሉ፡፡

እነዚያ አምስቱ ደናግል እንደዚህ ነበሩ (ማቴ.25፥1)፡፡ ርግጥ ነው ንጽህናቸውን የጠበቁ ነበሩ፡፡ ለሚያያቸው ኹሉ ግሩም የኾነ ጠባይ የነበራቸው ነበሩ፡፡ ሥርዓት ያላቸው ነበሩ፡፡ ይህ ኹሉ ግን ምንም አልጠቀማቸውም፡፡ ወደ እሳተ ገሃነም ከመጣ’ል አልታደጋቸውም፤ ዘይት የተባለው ምጽዋት አልነበራቸው’ማ! ክርስቶስን በነዳያን አማካኝነት የማይመግቡትም ዕጣ ፈንታቸው ጽዋ ተርታቸው ይኸው ነው የሰነፎቹ ደናግል ዕጣ!

አንተ ሰው ልብ ብለህ አስተውል! እነዚህ ደናግል በግል ኃጢአታቸው አልተነቀፉም፡፡ በዝሙት ወይም በሐሰት ምስክርነት አልተወቀሱም፡፡ በፍጹም! ይልቁንም የተነቀፉትና የተወቀሱት ሌሎች ሰዎችን ባለመጥቀማቸው ነው፡፡

እንደዚህ ከኾነ ታዲያ ሰዎች ክርስቲያን ተብለው ሊጠሩ የሚችሉት በምን መመዘኛ ነው? እኮ በምን መስፈርት? አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! በሊጥ ውስጥ የተጨመረ እርሾ ሊጡን እንዲቦካ ካላደረገው እንዲሁ እርሾ ተብሎ መጠራት ብቻውን ምን ይረባዋል? ዳግመኛም ወደ እርሱ የቀረቡትን ሰዎች መዓዛው ካልሸተታቸውና ቤቱን ካላወደው በቀር ከርቤ በከርቤነቱ ምን በቁዔት አለው?

ሌሎች ሰዎችን መርዳት አይቻለኝም ብለህ አትንገረኝ፡፡ እንዲያውም ልንገርህ፤ አንተም ስማኝ፡- አንተ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ሌሎች ሰዎችን አለመርዳት የማይቻል ነው፡፡ ዕጣን መዓዛ እንዲኖረው፣ እርሾም ሊጥን እንዲያቦካ ተፈጥሮው እንደ ኾነ ኹሉ፥ አንድ ክርስቲያንም በስም ክርስቲያን ከመባል አልፎ በእውነት ያለ ሐሰት ክርስቲያን ከኾነ ሌሎች ሰዎችን መርዳት መቻሉ፣ ሌሎችን የሚጠቅም ሥራ መሥራቱ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

ስለዚህ አይኾንልኝም፤ አይቻለኝም በማለት እግዚአብሔርን አታማርር፡፡ ፀሐይ ብርሃኗን በእኔ ላይ ማብራት አይቻላትም ካልክ ፀሐይን እየሰደብካት ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያንም ሌሎች ሰዎችን ሊጠቅማቸው አይችልም የምትል ከኾነ እግዚአብሔርን እየሰደብክ [ሎቱ ስብሐትና] ሐሰተኛም እያደረግኸው ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን ሌሎች ሰዎችን ካለመርዳትና ካለመጥቀም ይልቅ ፀሐይ ሙቀትና ብርሃን ባትሰጥ ይቀላል፡፡ እንደዚህ ከሚኾን ብርሃን ወደ ጨለማ መቀየር ይቀላል፡፡

እናስ? እና’ማ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡ የማይቻለው መርዳት አለመቻል ነውና፡፡ አይኾንልኝም እያልክ በከንቱ እግዚአብሔርን አታማርር፡፡

ሕይወታችንን በአግባቡና በሥርዓቱ የምንመራ ከኾነ እነዚህን ነገሮች ኹሉ በቀላሉ ማድረግ ይቻለናል፤ እነዚህ ነገሮች ሊደረጉ ግድ ነው፡፡ በመቅረዝ ላይ የተቀመጠ ሻማ ብርሃኑን መደበቅ እንደማይቻለው ኹሉ ክርስቲያንም የእውነት ክርስቲያን ከኾነ ብርሃኑም መሸሸግ አይቻለውም፡፡ ስለዚህ እውነተኞች ክርስቲያኖች ከኾንን ሌሎች ሰዎችን መርዳት መጥቀምም ችላ አንበል፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
26👍21
#መጋቢት_10

#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል

መጋቢት አስር በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል። መጀመሪያ የፃድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት እሌኒ እጅ ነው።

«እርሷ ለእግዚአብሔር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሀይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው።

ከዚህ በኋላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠበቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእረሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አስጨነቀችው።

በተጨነቀም ጊዜ ለንግስት እሌኒ የጉልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው።

ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግስት እሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ። አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ።

አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኃላ ሶስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት።

ለልጅዋ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መፅሀፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው።

ከዚህም በኃላ ስራአታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በአስራ ሰባት ተፅፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች። ሁለተኛው በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዮ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።

ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው ከኢየሩሳሌም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።

የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እነድ ማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወስዱ የሮም ንጉስ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ እፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።

ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አነፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።

ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉስ ሀርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው።

ይህንንም ንጉስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሰራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ። ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቅፍረውም የከበረ እፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሱና ሰራዊቱም ሰገዱለት።
በልብሰ መንግስቱም አጐናፀፈው ታላቀወ ክብርንም አከበረው እጅግም ደስ አለው ከሰራዊቱ ጋር። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሱ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው፡፡

የመድኃኒታችን የመስቀሉ በረከት ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
26👍11🕊3
  ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው??

👉 ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ለማወቅ አንባቢው መጀመሪያ ዮሐ 1:1 ላይ ስላለው የቃል ምንነት ማወቅ ግድ ይለዋ።
     የዚህን ቃልነት ላወቀ ሌላው ጉዳይ የሚከብደው አይሆንም።

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
  — ዮሐንስ 1፥1

=)በመጀመረያ አለ። መጀመሪያ የሌለው መጀመሪያን ሲናገር።
=)ቃል ነበር አለ።  ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ በኹነት ቃላቸው የሚሆን የወልድን መኖር(ህልውናውን) ሲናገር
=)  ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር አለ። ይሄ መጀመሪያ በሌለው መጀመሪያ ሲኖር ነበር ያልኳችሁ ቃል በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ነበር።  የእግዚአብሔር አብ ጋር ነበር። ሲለን
=) ቃልም እግዚአብሔር ነበር። ይሄ ቃል ለብዙ ኢአማንያን መልስ ነው።።  ይሄ ከአብ ጋር ነበር ያልኳችሁ ቃል የአብ ፍጥረቱ አይደለም እሱ ራሱ  እግዚአብሔር (ፈጣሪ) ነው እንጂ።


“ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።”
  — ዮሐንስ 1፥14

=) ቃል ስጋ ሆነ አለን። ቅድም የነገርዃችሁ ያ ከፈጣሪ ጋር አብሮ ሲኖር የነበረ ቃል። ራሱ እግዚአብሔር (ፈጣሪ) ነው ያልኳችሁ ቃል ስጋን ለበስ ሰውን ሆነ።። ይህ ቃል ስጋ ለበሰ በእኛ ሲያድር ኢየሱስም ተባለ።።

ስለዚህ ኢየሱስ አምላክ ነው ማለት ነው።


ኢየሱስ በስጋዌው ወራት አማላጅ ወይስ ፈራጅ??

👉 ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ከላይ በጥቂቱ አይተናል። ታድያ ይህ አምላክ የሆነ ቃል ስለምን ሰው መሆን አስፈለገው???
   መልሱ አንድ ነው ሊያድነን ነው ለዚህ ምንም አይነት ጥቅስ መጥቀስ አያስፈልገንም። ሁሊችንም ምናምንበት ጉዳይ ነው።   እኛ ሚያድነን እንዴት ነው ከተባለ ከአብ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱም ጋር በመስቀሉ ቤዛነት በደሙ ፈሳሽነት ለማስታረቅ ብለን እኝመልሳለን።

👉 አንዳዶች ከ አብ ጋር ነው እንጂ ከራሱ ጋር አላስታረቀንም ሲሉ ይደመጣሉ። እንዲህ አይነቶችን መናፍቃን ይሄ ቃል ይዋጋቸዋል።

“ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤”
  — 2ኛ ቆሮ 5፥18

👉 ይህም ማለት የስጋዌው ወራት ላይ እያለ ፍፁም ሰውነትቱን በደንብ አረጋግጦልናል።
   ተርቧል ተጠምቷል ታርዟል ተመቷል።  እንደ ለበሰ የስጋው ባህሪ እኛን አስታርቆናል።
የማማለድ አማረኛ ትርጉሙ ማስታረቅ ነው። ይህ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው ወራት አማላጅ ነበር።‼️

ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን አማላጅ ወይስ ፈራጅ

👉 አንዳድ አላስተዋይ ሰዎች ኢየሱስን ቀድሞ በስጋዌው ወራት የፈፀመውን የማማለድ ተግባር አሁንም ሊሰጡት ሲሞክሩ ይታያሉ። ይህ ኢየሱስ ካለማወቅ የሚመጣ ምንፍቅና ነው። እንደነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ ኢየሱስ አሁንም ይራባል አሁንም ይጠማል እንደማለት ነው። ለነዚህ መናፍቃን ይሄ የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ይዋጋቸዋል።


“........ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።”
  — 2ኛ ቆሮ 5፥16

=) ክርስቶስ በሥጋ እንደሆነ ያውቅነው ብንሆን እንኳ አለ። ምንም በሥጋው ሲራብ ሲጠማ ሲያማልድ የምናውቀው የምታውቁት ቢሆንም ሲል
=) ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አይነት ግብር ሥራ አናየውም አናውቀውም ሲለን ነው።

👉 ታዲያ ኢየሱስ ከክርስቶስ ለቤተክርስቲያናችን አማላጅ ነው? ወይስ ፈራጅ??

እንደ ቤተክርስትያናችን አስተምህሮ ኢየሱስ ፈራጅ ነው

ለዚህም ማስረጃችን

“ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።”
  — ዮሐንስ 5፥22-23

ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው አለን። መጀመሪያ የሌለው ሆኖት አይደለም። ወልድ ስጋ ቢለብስ ኋላ የማይፈረድ አይምሰላችሁ ሲል። አንድም ሰጠው አለ
=) አንድን ነገር በቃል ከመናገር በፊት በልብ ማሰብ ይቀድማልና በአብ ልብነት የታሰበች ፍርድ በወልድ ቃልነት ትፈፀማለች ሲል።

=) አብ በአንድ ሰው እንኳ አይፈርድም አለ። ለአብ ፍርድ መፍረድ ተስኖት አይደለም። ኋላ ወልድ አማላጅ የሚሉ አሉና ስለነዚህ ተናገረባቸው። አንድም  አብ በአንዳችንም ላይ አይፈርድም ፍርዱን በወልድ ይፈርብናል። ይፈርድልናል ሲል። ይህን ተናገረ።

በዚህ ቃል መሰረት ወልድ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም።

በመጨረሻም አንድ ነገር እናንሳ እና እናጠቃልላለን።

👉 መጀመሪያ ኢየሱስ አማላጅ የሚሉ ወገኖቻችን በዚህ ወንጌል ሲያፍሩ ሀሳባቸውን ቀየር አርገው።  ኢየሱስ እኮ ፈራጅ ነው ነገር ግን የአለም ፍፃሜ ቀን ነው እስከዛ አማላጅ ነው ሲሉ ይደመጣሉ ነነዚህ አርዮሳዊያን አሁንም ቤተ ክርስትያናችን መልስ ከመስጠት አልቦዘነችም!!!!!!

ማስረጃ ፦

“ወንድሞች ሆይ፥ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ፤ እነሆ፥ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል።”
  — ያዕቆብ 5፥9

=) ወንድሞች ሆይ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በእርሳችሁ አታጉረምርሙ አለ። ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው የተባለለት ፈራጅ እንዳይፈርባችሁ።  እርስ በእርሳችሁ አታጉረምርሙ  አለ። ይሄ ማጉረምረም የሚለው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ትርጓሜው በደል ኋጢያት ትዕብት እብሪት በጥሬው ማጉረምረም የሚለውን ትርጓሚውን ይይዛል።

“ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች።”
  — ዘኍልቁ 11፥1

“በድንኳናችሁም ውስጥ እንዲህ እያላችሁ አጕረመረማችሁ። እግዚአብሔር ስለ ጠላን እንዲያጠፋን በአሞራውያን አጅ አሳልፎ ይሰጠን ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣን።”
  — ዘዳግም 1፥27

ስለዚህ ወንድሞቼ ፈራጁ እንዳይፈርድባችሁ አታጉረምርሙ(በደል አትስሩ)።  ለምን እንዳይፈረድባችሁ!!!!!

የሚፈርድብን ማን ነው ብትሉኝ።  ፍርድን ሁሉ ለወልድ የተሰጠው ፈራጅ።

"..እነሆ፥ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል።”
  — ያዕቆብ 5፥9

ከወዴት አለ " ከደጅ" መቼ አሁን ቆሟል።!!!!!!!!!!!!!

ኢየሱስ በስጋዌ ወራት ከአብ አራሱ ከመንፈስ ቅዱስ ሲያማልድ

አሁን ላይ
ኢየሱስ ተፈፀመ ካለባት ጀምሮ ሲፈርድ  ፈራጅ ሆኖ ይኖራል

🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3012🕊4
"ብዙዎች ቢጾሙም ለእነርሱ መጾም ማለት የጾም ምግብ መብላት ማለት ነው። እነርሱ በጾም ወቅት ለራሳቸው የሚበሏቸውን በጣም ጣፋጭና ገንቢ ምግቦችን ያዘጋጃሉ  አልፎ ተርፎም ውድና የማይገኙ ቅመማ ቅመም ይጨምሩባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የጾም ቅቤ፤ የጾም አይብ፤ የጾም ቸኮላታ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ።  በአጠቃላይ የጾም ምግቦቻችን ብዛትና ዓይነት ከልክ እጅግ ያለፈ ነው።

በዚህም ነብዩ ዳንኤል ስለ ጾም የተናገረውን ይዘነጉታል። "በዚያ ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራ አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱንም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።" (ዳን 10፥2-3) በዚህ አባባሉ ውስጥ "ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም" የሚለው ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ። አንድ ሰው በጾም ወራት በየዕለቱ ጥሩ ጥሩ ምግቦች እየበላና የሚናፍቀውን ምግብ ለሰውነቱ እየሰጠ የሥጋውን ፈቃድ እንዴት ሊቆጣጠር ይችላል? አይችልም።

መንፈሳዊው ሰው የጾም ትክክለኛ ፍቺ ሥጋን በማዋረድ የምግብን ፋላጎት ድል ለማድረግ ካበቃ በኋላ ከቁሳዊው ዓለም በላይ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ያውቃል ። በመሆኑም የጾም ምግቦችን መብላት ብቻ መሆን የለበትም እርሱ በሚጾምበት ጊዜ ግድ የሚለው መታቀብ ነው ። ይህም ማለት የሚመገበው ሙሉ ለሙሉ የጾም ምግብ ቢሆንም ሥጋው ሊያገኛቸው የሚናፍቃቸውን ነገሮች በሙሉ መከልከል ማለት ነው ።

ብዙ ሰዎች የሚጾሙት በልምድ ወይም በፊደል ስለሆነ ምንም የሚጠቀሙት ነገር የለም ። እነዚህ ሰዎች ጾምን መለኮታዊ ዓላማውን በመገንዘብ ስለማይጀምሩት ወደ ጾም መንፈሳዊነት ወይም ስለ ትእዛዙ መንፈሳዊነት ሊገቡ አይችሉም። በመሆኑም ሰውነታቸው ይጹም እንጂ መንፈሳቸው አይጾምም።
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
32👍13
ሆድ አምላክ ይሆናልን?
(ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን)

የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር።

ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው።  እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን።

የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው።

እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው።

ይህ ብቻ አይደለም፤ እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው። 

ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል፦
አንደኛ- አስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም፤
ሁለተኛ- ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው።

እንግዲህ እናስተውል ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል፦
መጀመሪያ- እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ፤
ሁለተኛ- ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ፤
ሦስተኛ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው። 

ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም።

የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን  ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን?

ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ስለ ፍቅር ትጾማለህ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ፤ በፍቅር ብርሃን ደምቀህ ትነሣለህ።

ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር እንጂ። ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህም ለዘለዓለም ትኖራለህ።

እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ፤ ነጋሪት ትጎስማለህ። እንዳትጾም የሚረዱህ የሚመስልህን ጥቅሶችም በመብራት እየፈለግህ ትለኩሳለህ። በጅብ ቆዳ የተለጎመ ከበሮ ሲመቱት 'እንብላው' ብሎ ይጮኻል እንዲሉ አበው፤ የሆድ ጠበቃ የሆኑ የጅብ ስብከት የሚያመሰጥሩ የእንብላው መጽሐፍ ሊቃውንትንም አታጣም።

እናም ወዳጄ ሆይ "እለ ከርሦሙ ያመልኩ" "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" እንደለ ቅዱስ ጳውሎስ (ፊልጵ. ፫፥፲፰ )የምትወደው ሆድህ ጠላት ሆኖ በግራ እንዳያቆምህ በእግዚአብሔር  ፍቅር ሰይፍነት የስስትን ገመድ ቆርጠህ ጥለህ ከምጽዋትና ከተገራ ሰውነት ጋር ጹም!
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
25👍12🕊1
#ደብረ_ዘይት
(የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት)

የዐቢይ ጾም የአምስተኛው ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ደብረዘይት የስሙ ትርጓሜ የዘይት ተራራ ማለት ነው ስያሜ የተሰጠው በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለ ነበር ነው፡፡
እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?›› አሉት (ማቴ. 24፥3፣  ዘካ. 14፥5 ፤ ሐዋ. 1፥11 ፤ 1ኛ ተሰ. 4፥16 ፤ ራዕ. 22፥7)

#አመጣጡስ_እንዴት_ነው?

ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበብ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርሃ መጋቢት ዕለት እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው የሚያውቀው የለም ይባል የለምን? ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን፤ ብዙ የመጋቢት ወር፤ ብዙ የእሑድ ዕለት አለና ለይቶ የሚያውቅ የለም፡፡ ሞት ለማን አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ. 3፥19 በዕለተ ምጽአት ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፏን ነቅለው ደንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደ ብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መለኸት ይነፋል፡፡ 1ኛ መቃ. 9፥8 ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባሕር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም በድን ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛው ነጋሪቱን መቶ (ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት) ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደጉነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡    

ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ.13፥43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያቢሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ቡሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለ ክፉ ሥራቸው (ከኔ ሂዱ) ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ፤ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ ደረት ይደቃሉ እንባቸው ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ለቅሶ የማይጠቅም ሐዘን ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን አይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡    

#ምልክቱስ_ምንድን_ነው? ብለው ጌታን ሲጠይቁ ‹‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳል፤ ረሃብም ቸነፈርም መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ›› አላቸው፡፡ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡

#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ
እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ....
(ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡....)

#የዕለቱ_ምንባባት
1ኛ ተሰሎንቄ 4÷13-ፍጻ፡-
ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡.....

2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡-
አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡.....

ሐዋ. 24÷1-21፡-
በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡..... (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ. 49÷2
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡
ትርጉም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም እይልም፤
እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡

#የዕለቱ_ወንጌል
ማቴ. 24÷1-25፡-
ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡.....”
#የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
👍456
ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ

“እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።”

መዝ፦ 33፥8።

በጣም ደግ የሆኑ ሰዎችን እናውቃለን። ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስላቸው፣ ያንተ እጅ አያጠግብህም በእኔ እጅ ጉረስ እያሉ በላይ በላዩ የሚያበሉ ሰዎች በዙሪያችን አሉ። ሰለጠኑ የሚባሉት እንኳን በሰው እጅ ሊጎርሱ የራሳቸውንም እጅ ማመን አቅቷቸው ምግባቸውን ወደ አፋቸው የሚያደርሱት በማንኪያ፣ በሹካና በቢላዋ ነው። እንብላ ማለትንም እየረሱ ነው። ሁሉንም ነገር ስሌት ውስጥ እየከተቱት ነው። ባልና ሚስትም የየግላቸውን ይከፍሉ ይሆናል እንጂ አንዱ ባንዱ ገንዘብ ማዘዝ አይችልም። በኅብረት ውስጥ ያለ ግለኝነት እንደ መሰልጠን እየታየ ነው። ኅብረቱም አይቅርብኝ ፣ ግለኝነቱም አይቅርብኝ እየተባለ ነው። ቀኑን ሙሉ ጋጋሪ አቁመው እንጀራ የሚያስጋግሩ ፣ የጋገሩትን እንጀራ መንገደኛ በልቶ ካልጨረሰው የሚያዝኑ ፣ እንግዳ መቀበል አገልግሎታቸው የሆኑ ሰዎችን እናውቃለን። ከቤታቸው ደጃፍ አንድ ጎላ ንፍሮ ቀቅለው መንገደኛ ሁሉ ይበላው ዘንድ በየሰንበቱ የሚያስቀምጡ ቸሮችን አይተናል። እያዘከሩ ሰው የሚሰበስቡ ፣ ማኅበራዊነትና መንፈሳዊነት እንዳይጠፋ የሚታገሉ ብዙዎች ናቸው። “እኔ ቤት መጥቶ ሳይበላ ነው የሄደው” በማለት ተቀይመው የሚቀሩ ፣ እንደ እናቱ ባያየኝ ነው ብለው አዝነው የሚጎዱ የዋሃንን በትክክል እናውቃለን። እነዚህ ደጎች ሳይጎድልባቸው እንደ ሰጡ አልፈዋል። ስጡ ላለው አምላክ ታዘዋልና ተሰጥቶአቸዋል። በብዛት ሳይሆን በበረከት መኖር ችለዋል። ዛሬ ብዙ ገንዘብ አለ ፣ በረከት ግን የለም። ለድሀ አንሰጥም ፣ ለማንድንበት መድኃኒት ግን ብዙ እናወጣለን። እግዚአብሔር ስንሰጥ በጤና እንደሚከፍለን አናውቅም። እናውቃለን ብለን ሞኝ ሆንን። የሌሎች የረሀብ ሕመም ሲሰማን የእኛ ሕመም እየተፈወሰ ይመጣል።

ቸሮች በታኞች አይደሉም። ሰውን የሚያሰክር መጠጥ ፣ ሱስ የሚጋብዙ እነዚህ ጥይት የሚመጸውቱ ናቸው። ቸሮች የሚዘሩ ናቸው። ዘሪ መሬቱን ያውቀዋል ፣ ከርሞ ይመለስበታል። ዛሬ ይዘራል ፣ ነገ እዚያው ያጭዳል። ቸሮች አንድን ሰው ካለበት ሁኔታ እልፍ ማድረግ፣ ከግብ ማድረስ ዓላማቸው ነው። ቸር ሰው በበረሃ እንደ ተገኘ ውኃ ነው ፣ ያረካል ። ቸሮች ውስጣቸው ሕያው ነው፣ እንቅስቃሴ ላይ ሲሆን ሊወጣ የሚታገላቸው ኃይል አለ። ራሳቸውን በጣም ስለማያዩት ፣ የሌሎች ጉድለት ስለሚታያቸው ደስተኞች ናቸው። ፍቅር ተግባራዊ ሲሆን ቸር ያደርጋል። ስስታም ፣ ንፉግ ሰው አፍቃሪ አይደለም። እነዚህ ሁሉ ቸሮች ክፉ ቀንን ያለፍንባቸው ፣ ጨለማችን ላይ ብርሃን ያወጁ ናቸው። ያለ ደጎች ድጋፍ እዚህ አልደረስንም። ተቀብለን እንዳልተቀበለ መካድ አይገባንም ። እነዚያን ቸሮች ማመስገን፣ ዛሬ ተራው የእኛ ከሆነ በችግራቸው መርዳት ይገባናል።

ቸሮች የእግዚአብሔርን ጠባይ የተካፈሉ ናቸው። እግዚአብሔርን የሚመስሉ ፣ የሚንሰፈሰፉልን ፣ በረከትን በተርታ የሚያቀርቡልን ፣ ልባቸውም እጃቸውም የተከፈተልን ስጦታዎቻችን ናቸው። እግዚአብሔርን የምናየው በቸሮች ውስጥ ነው። ሰው ቅባትና የውበት ዕቃ ሲሸምት ይውላል ፤ እውነተኛ ውበት ግን ቸርነት ነው። እግዚአብሔር በባሕርይው ቸር ነው። ቸርነቱን በቃላት መግለጥ፣ በእውቀት ማስረዳት አይቻልም። የእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት መንጋጋ ያስመልጣል። ይህን ቸርነት ያልተካፈለ ሰው ፣ እንስሳና እጽዋት የለም። ቸር አንድ ቀን ከሰዎች ብልጠት የተነሣ ቢስ ይሆናል። “ቸር ሲያጠቁት ቢስ ይሆናል” እንዲሉ። እግዚአብሔር ግን እያጠቃነው አሁንም ቸር ነው።

ነቢዩ በመዝሙሩ፡- “እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው” ይላል። እግዚአብሔርን ወደ ቤታችን መጋበዝ ፣ እግዚአብሔርን ተሸክሞ ወደ ሰዎች ቤት መሄድ ተገቢ ነው። መቅመስ ማጣጣም፣ ለመብላት መዘጋጀት፣ መሞከር ፣ መለማመድ ነው። የእግዚአብሔርን ቸርነት መቅመስ አለብን። ቸርነቱን የሚቀምሱ ቸር ይሆናሉ። ቀጥሎ፡- “በእርሱ የሚታመን ምስጉን ነው” አለ። ቸር የማንሆነው ቢጎድልብኝ ብለን ነው። ቸርነት ግን በእግዚአብሔር በመታመን የሚገኝ ነው። ስጡ ላለው ቃል ታዝዤ አይጎድልብኝም ብሎ ማመን ይፈልጋል። እምነት ልምምድ ነው። መቅመስ ፣ ማየት ይገባል። የቸርነት ሕይወት ደስ ያሰኛል። የተቆለፉ ትልልቅ ቤቶች፣ ምግብ እየተበላሸ የሚደፋባቸው የባለጠጋ ሳሎኖች ይህን ቸርነት ቢለማመዱ የሞት ጥላ ይገፈፍላቸዋል። እንዴ በየምሽት በሚሊየን እያወጡ ይጋብዙ የለም ወይ? ቢባል እርሱ ንግድና ጉራ እንጂ ቸርነት አይደለም። ቸርነት የባለጠጎች ዕዳ ሳይሆን ሁሉም የሰው ልጅ የሚለማመደው ሀብት ነው። በእጃችን ማጉረስ ባንችል በእጃችን የቆሸሸውን ምስኪን ማጠብ እንችላለን። የሰውነት ክፍሎቻችን የቸርነት መሣሪያ ናቸው ። ቸርነቱን የምንቀምሰው በጸሎት ነው። የሚለምኑ ይቀበላሉ ፣ ቸርነቱንም ያያሉ።

እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠን ሕይወትን ነው። የሕይወት ዋጋዋ ስንት ነው ? ያኖረን ቸርነቱ ነው። እስትንፋሳችን በአፍንጫችን ላይ የተንጠለጠለች ፣ ለመሄድ የተዘጋጀች ናት። እስትንፋሳችንን በአፍንጫችን ያሳደረልን ፣ ያዋለልን ጌታ ቸር ነው ። ይህን ቸርነቱን ማጣጣም ፣ ማመስገን፣ መመስከር ይገባል። በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ቸር ነው።

እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
👍3016
የ ስራ ማስታወቅያ
•የልብስ ስፌት ባልሞያ
መስፈርት: በሞያው የተሻለ ልምድ ያላት ያለው የሐገር ባህል ልብስ የሰራች ቢሆን ይመረጣል

•ፆታ:   ሴት
•አድራሻ: አቃቂ
•ደሞዝ:  በስምምነት
•ስልክ: 0930923061
3👍1
ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    
39👍19
የ ስራ ማስታወቅያ
•የልብስ ስፌት ባልሞያ
መስፈርት: በሞያው የተሻለ ልምድ ያላት ያለው የሐገር ባህል ልብስ የሰራች ቢሆን ይመረጣል

•ፆታ:   ሴት
•አድራሻ: አቃቂ
•ደሞዝ:  በስምምነት
•ስልክ: 0930923061
👍131
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ?

ሔዋን ከእባብ ጋር ተነጋገረች የሚለውን አምነህ አቡነ አረጋዊ በእባብ ተራራ ወጡ ሲባል ከቀለድህ ፣ ኤልያስን ቁራ መገበው ሲባል ተቀብለህ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቁራውን መገቡት ሲባል ከዘበትህ ፣ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር አደረ ሲባል አምነህ አቡዬ አንበሶች ጋር ነበሩ ሲባል ካጣጣልክ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀበት ቀን ለአንተ የዓለም ፍጻሜ መስሎሃል ማለት ነው::

አንድ አባት 'ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?' ተብለው ሲጠየቁ 'የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ' ብለዋል፡፡ 'አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው' ካልከኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሞአል ማለት ነው? 'እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ' ሲል አብረን አልሰማነውም? (ማቴ. 28፡19)

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
34👍13
ዕለተ ምጽአት

አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ የተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ደጅም እንጸናለን እንጂ። አንተ ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ብለሃልና።

በእለተ ምጽአት አምላክ ሲመጣ ሦስት ጊዜ ታላቅ የሆነ የመለከት መነፋት ይሆናል። ይህ የመለከት ድምጽም ሙታንን ሁሉ የሚያነቃ ነው።

በመጀመሪያው አዋጅ መለከት ሲነፋ በዓለም ዳርቻ ሁሉ የተበተነ የሥጋ ትቢያ ይሰበሰባል። በላይ ያለውና በታች ያለው በባሕር ያለውና በየብስ ያለው በአራዊትም ሆድ ያለው በልዩ ልዩ ሞት ፈጽሞ ያረጀና የጠፋ በምድር ላይ የወደቀ የሥጋ ቅርፍትም ሁሉ ወደ ቀደመ መገናኛው ይሰበሰባል።

በሁለተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ አጥንቶች ከሥጋና ከደም ጋር ይያያዛሉ ያለመንቀሳቀስ ያለመናወጥም እስከ ጊዜው ድረስ ፍጹም በድን ይሆናል።

በሦስተኛው አዋጅ መለከት ሲነፋ ሙታን እንደ ዓይን ጥቅሻ ፈጥነው ይነሳሉ ጻጽቃንና ኃጥአን ክፉም ቢሆን በጎም ቢሆን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሠሩትን ከምድር የተከተላቸውን ሥራቸውን ተሸክመው ይነሣሉ ጻድቃንን በቀኝ ኃጥአንንም በግራህ ታቆማለህ። ለመረጥካቸውም በምሥጋና ቃል ትናገራቸዋለህ እንዲህ ብለህ፥-

እናንተ የአባቴ ቡሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥተ ሰማያት ትወርሱ ዘንድ ወደ እኔ ኑ ብራብ አብልታችሁኛልና፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛልና፣ እንግዳ ብሆን አሳድራችሁኛልና፣ ብታረዝ አልብሳችሁኛልና፣ ብታመም ጎብኝታችሁኛልና፣ ብታሠር መጥታችሁ ጠይቃችሁኛልና በማለት (ማቴ. 25፥34-36) እንደተነገር ሁሉ ዳግመኛም ወደ ግራው ተመልሰህ በወቀሳ ቃል እንዲህ ትላቸዋለህ ብራብ አላበላችሁኝምና፣ ብጠማ አላጠጣችሁኝምና፣ እንግዳ ብሆን አላሳደራችሁኝምና፣ ብራቆት አላለበሳችሁኝምና፣ ብታመም አልጎበኛችሁኝምና፣ ብታሠር አልጠየቃችሁኝምና በማለት (ማቴ 25፥ 42-23) ያን ጊዜ ዓመጽና ሽንገላን ይናገር የነበረ አፍና አንደበት ሁሉ ይዘጋል። ያንጊዜ ኃዘን ይደረጋል፡ የማይጠቅም ኃዘን ነው።  ያንጊዜ ጩኸት ይደረጋል የማይጠቅም ጩኸት ነው። ያንጊዜ ፍጅት ይሆናል የማይጠቅም ፍጅት ነው። ያንጊዜ ለቅሶ ይሆናል የማይጠቅም ለቅሶ ነው። የሚያስደነግጥ የነጐድጓድ ቃል የሚቆርጥና የሚከፍል የሚለይ ብርቱ ብልጭልጭታም ወደእነርሱ ይላካል ይኸውም የኃጥአን ዕድላቸው ነው።

ያን ጊዜም ምድር አደራዋን ትመልሳለች እናትም የሴት ልጅዋን ጩኸት አትሰማም። ያን ጊዜ በሕይወትዋ ዘመን የሰራችው የነፍስ ሥራዋ ይገለጻል።

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ያን ጊዜ ትምረን ዘንድ ይቅርም ትለን ዘንድ በበላነው በቅዱስ ሥጋ በጠጣነው በክቡር ደምህ እንማጸንሃለን። ስለ እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ስለ ሁሉ ቅዱሳን መላእክት ጻድቃን ሰማዕታት ነቢያት ሐዋርያት እንዲሁም ደናግላን መነኮሳት እንማጸንሃለን። አምላክ ሆይ ያን ጊዜ ማረን ራራልንም ይቅርም በለን።
    

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2011
#ገብር_ኄር (የዐቢይ ጾም 6ኛ ሳምንት)

የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፡፡ በዚህ ሳምንት የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብርኄርን የሚያወሳ ነው። ማለትም ስለ ታማኝ አገልጋይ ነው፡፡

የማቴ.25፥14-25 የሚነግረን ይህን ነው፦ “አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው፣ ሁለት መክሊት የሰጠውም አለ፣ አንድ መክሊትም የሰጠው አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ፡፡ ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ፡፡ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ በሻሽ ጠቅልሎ የጌታውን መክሊት ቀበራት፡፡

ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጥቶ ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ አምስት አተረፍኩ አለው፡፡ “ገብርኄር ወምዕመን ዘበሁድ ምዕምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ” “አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ ጌታዬ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሌላ ሁለት አትርፌ አራት አድርጌአለሁ፡፡ “አንተ ታማኝ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ቀርቦ “ጌታዬ አንተ ክፉና ጨካኝ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ እንደሆንክ ስለአወቅሁ መሬቱን ቆፍሬ ቀበርኋት እነኋት መክሊትህ” አለው፡፡ “አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር”፡፡ ኑ የዚህን ሀኬተኛ መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ ኑ ይህን ሰነፍና ሃኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጨምሩት” አለ ማቴ. 25፥14-25፡፡

ባለ ጸጋ የተባለው ጌታ ነው፡፡ መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ ያተረፉት በሚገባ በታማኝነት ያገለገሉ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው መክሊቱን የቀበረው ደግሞ በታማኝነት በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ሲገባው ያላገለገለ ነው፡፡ ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው መጣ ማለት በዕለተ ምጽአት ለሁሉም በአገለገለው አገልግሎት ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ ያሳየናል፡፡ ያገለገሉትን ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አላቸው ማለት ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡ ሰነፎች ደግሞ ጥርስ ማፋጨት ስቃይ ጽኑዕ ጨለማ ባለበት ሲዖል መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ
መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ፡፡

ትርጉም፦ ጌታው በመልካም ሥራ የሚያገኘው በሐብቱ ኹሉ ላይ የሚሾመው፤ የታመነ በጎ አገልጋይ ማን ነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለኾንህ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ይለዋል፡፡

#መልዕክታት
2ኛ ጢሞ.2÷1-15
"ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡" (ተጨማሪ ያንብቡ)

1ኛ ጴጥ.5÷1-11
"እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡" (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ግብረ_ሐዋርያት
የሐዋ.1÷6-8
"እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"

#ምስባክ
መዝ. 39÷8
"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"

ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ

#ወንጌል
ማቴ. 25÷14-30
“መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡” (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ቅዳሴ ➛ ቅዳሴ ባስልዮስ
👍2917
ትዕግስት እና ጽናት

“በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፡፡" (1ኛ ቆሮ. 9፥24)

እዚህ ላይ ጳውሎስ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚያስፈልገውን ትጋት እና ተግሣጽ ለማጉላት የሩጫ ውድድርን እንደምሳሌ ይጠቀማል:: እነዚያ የቆሮንቶስ ሰዎች “በፍጹም እውቀታቸው" በመታበያቸው፣ ያጎደሉትን ነገር በመንገር በዘዴ ይወቅሳቸዋል:: ጳውሎስ ጥረታቸው ከልብ የመነጨ ቢሆንም እንኳ ፍቅር የሌለው ራስን መግዛት የሌለው ከሆነ ያልተሟላ እንደሆነ ይነግራቸዋል::

የክርስትናን ሕይወት ሁሉም ከሚሳተፉበት የሩጫ ውድድር ጋር ያመሳስለዋል፤ ነገር ግን በዚህ ውድድር ሽልማቱን የሚቀበለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህ ንጽጽርም ድነት ለአንድ ሰው ብቻ የተገደበ ወይም ጥቂቶች የሚድኑ መሆናቸውን አያመለክትም:: ይልቁንም ልባዊ ጥረት፣ ተግሣጽ እና ትኩረት የመስጠትን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ያሳያል:: እንደ ሩጫ ውድድሩ ሁሉ፣ ወደዚህ ውድድር ለመግባት ሙሉ በሙሉ መዘጋጀት አለብን፤ ከፊል ጥረት ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የመጨረሻውን መስመር ለመድረስ እና ሽልማቱን ለመውሰድ በቁርጠኝነት እና በዓላማ መሮጥ አለብን፡፡

“እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ” የሚለው የጳውሎስ ማሳሰቢያ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሙሉ መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ እንዳልደረሱ ያመለክታል:: ገና ብዙ ነገርም መስራት ነበረባቸው:: ይህ የክርስቲያን ሕይወትን ቀጣይነት ያለው ቅድስናን የመሻት ጉዞ ነው::

የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፤ እኛ ግን የማይጠፋውን::" (1ኛ ቆሮ. 9፥25)

ለሩጫም ሆነ ለሌሎች ውድድሮች የሚያሠለጥኑ ሰዎች እንደ ሆዳምነት፤ ስካር ወይም ስንፍና ካሉ ነገሮች ይርቃሉ:: ከመጠን ያለፈ ራስን መግዛትንም ያሳያሉ:: ሙሉ ለሙሉም በዝግጅታቸው ላይ ያተኩራሉ፡፡ ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በማስወገድም ጥንካሬያቸውን እና አፈፃፀማቸውን ከፍ ለማድረግ ራሳቸውን ያለማመዳሉ:: በማያምኑበት ጨዋታዎች ውስጥም እንኳ ሯጮች ለሚጠፋው ምድራዊ ሽልማት ሲሉ በጥብቅ ራስን መግዛት ይኖራሉ፡፡

የጳውሎስ ነጥብ ግልጽ ነው፤ አትሌቶች ለሚጠፋ ሽልማት እንዲህ ያለውን ትጋትና ራስን መካድ የሚያሳዩ ከሆነ፣ ክርስቲያኖች የማይጠፋውን የዘላለም ሕይወት አክሊል ለማግኘት ምን ያህል መጣርይኖርባቸዋል? ለክርስቲያናዊ ሕይወት የሚሰጠው ሽልማት ከማንኛውም ምድራዊ ውድድር ከሚገኘው ሽልማት እጅግ የላቀ ነው:: የክርስቲያን “አክሊል" ጊዜያዊ ወይም አካላዊ ሽልማት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ያለ አንድነት እና የተስፋ ቃሉ ፍጻሜ፣ ዘላለማዊ ደስታ ነው::

የክርስትና ሕይወት በሁሉም ነገር ራስን መግዛትን ይጠይቃል:: በአንዱ ኃጢአት ላይ እየተዘፈቅን፣ ከአንዱ ኃጢአት መራቅ ብቻ በቂ አይደለም:: ለምሳሌ፣ አንድ አማኝ በቁጣ ወይም በትዕቢት እየተሸነፈ፡ በስካር ላይ አሸንፌያለሁ ማለት አይችልም:: እንደ ሯጭ ሁሉ አንድ ክርስቲያን በማንኛውም የሕይወት ዘርፍ፣ በአስተሳሰብ፣ በቃል እና በድርጊት ቅድስናን ማሳካት አለበት፡፡

ጳውሎስ ራስን ስለ መግዛት የሰጠው አጽንዖት የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ያላቸውን ቸልተኝነትና 'በእውቀታቸው ላይ ያላቸውን ከመጠን ያለፈ እምነት ይፈታተናል፡፡ እውቀት ብቻውን ሽልማቱን ማግኘትን አያረጋግጥም:: በፍቅር፤ በትህትና እና ራስን በመግዛት መታጀብ አለበት:: ውድድሩ ከፊል ጥረት ወይም ራስን ማመስገን ሳይሆን ስለ ሙሉ ቁርጠኝነት፤ ጽናት እና በመጨረሻው ግብ ላይ ስለማተኮር ነው ፤ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ያለ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡

“ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም!" (1ኛ ቆሮ. 9፥26)

ከላይ እንዳየነው የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ከሯጮች ራስን የመግዛት ጥበብ ጋር በማነፃፀር ምክር ይሰጣቸዋል፣ አሁን ራሱን ወደ ምሳሌው ያቀርባል፡፡ ይህን ለማድረግ ምክንያት የሆነውም በምሳሌነት ሌሎችን መመራት በክርስቲያናዊ ሕይወት አስፈላጊ ስለሆነ ነው::

ጳውሎስ “እንዲሁ አልሮጥም" ሲል፣ ያለ ዓላማ ሳይሆን በአእምሮ'ዬ ግልጽ የሆነ ግብ አስቀምጬ እሮጣለሁ ማለቱ ነው:: ያለ ምክንያት ተግባራቸውን ያደርጉ ከነበሩት ከቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በተለየ የጳውሎስ እያንዳንዱ ድርጊት ሆን ተብሎ የሚደረግና ሌሎችን ማዳን ላይ ያነጣጠረ ነበር፡ ነፃነቱን ቢጠቀምም፣ ከክፉ ለመታቀብ ቢመርጥም ወይም ራሱን ለሌሎች ሲል ቢያዋርድም ሁልጊዜ ግልጽ ዓላማ አለው! እግዚአብሔርን ማክበርና ባልንጀራዎቹን ማነጽ ነው፡፡

ጳውሎስ በመቀጠል እንዲህ አለ! “ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም” ይህ መንፈሳዊ ውጊያው ከጥላ ጋር የሚደረግ ሳይሆን እውነተኛ ጠላት ከሆነው ከሰይጣንና ከኃጢአት ኃይሎች ጋር የሚደረግ ትግል ነው፡፡ በአንጻሩ፣ የቆሮንቶስ ስዎች ጉልበታቸውን ከእውነተኛው ጠላት ጋር በመታገል ከማዋል ይልቅ፤ የራሳቸውን ልዕልና ለማሳየት ያውሉት ነበር፡፡

“ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክኹ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ::" (1ኛ ቆሮ. 9:27)

እዚህ ላይ፣ ጳውሎስ በራሱ ሕይወት ውስጥ ያለውን ከሥጋ ምኞት ጋር የሚደረገውን የማያቋርጥ ትግል አምኗል፤ ይህም ካልታረመ ወደ ኃጢአት ሊመራ ይችላል፡፡ ይህ እንዳይሆን "ሰውነቴን እየገሠጽኩት አስገዛዋለሁ" ይለናል፡፡ ይሁን እንጂ ጳውሎስ አካሌን አደክመዋለሁ ወይም እጠላዋለሁ አላለም:: ይልቁንም ጌታ ባሪያን እንደሚገሥጽ አድርጎ ይገስጸዋል:: ግቡ አካሉን ማድከም ሳይሆን ከኃጢአት ምኞቶች ይልቅ፣ አካሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል ማረጋገጥ ነው፡፡

ጳውሎስ የበቁ ሰዎች ላይ እንኳ ስላለ የቸልተኝነት አደጋ ተናግሯል። ምንም እንኳን ቢሰብክም፣ ቢያስተምርም... ነቀፋ የሌለበት ሕይወት መምራት ካልቻለ አሁንም “ከብቃት ውጪ" ሊሆን እንደሚችል አምኗል:: ይህ የሚያሳስበንም ማንም ከኃጢአት ፈተና ነፃ የሆነ የለም፣ ሌላው ቀርቶ እንደ ጳውሎስ ያለ የበቃ እንኳ ከዚህ ነጻ አይሆንም። ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ነፍሳት ወደ ክርስቶስ አምጥቶ ለወንጌል ብዙ ደክሞ የሠራው ጳውሎስ መውደቅን የሚፈራ ከሆነ፣ እኛ ተራ አማኞች እንዴት አብዝተን ንቁ መሆን የለብንም?

ብዙዎቹ በእምነታቸው ወይም “እውቀታቸው” ብቻ ይኩራሩ ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ ይህን የተሳሳተ አካሄድ አፍርሶታል:: እምነት ብቻውን በቂ አይደለም፤ እርምጃ እና ተግሣጽም ያስፈልጋል:: አዲስ ክርስቲያኖችን ሊጎዳ እንደሚችል እያወቁ በጣዖት ቤተመቅደሶች ውስጥ መብላትን የመሰሉ ግድየለሽ ምግባራቸውም የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ወደ መንፈሳዊ ውድቀት ሊመራቸው እንደሚችል ያስጠነቅቃል:: ለዚህም ነው ጳውሎስ ራሱን እንደ ምሳሌ የተጠቀመው፡፡ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ስኬት ቢኖረውም፣ ራሱን ያለማቋረጥ ይገሥጻል፤ ለቅድስናም ይተጋል፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
27👍9
ስለየተኛው እናመስግን?

“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እኅቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡

እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንኾናለን፡፡”

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍223
ማስታወቂያ

መምህር ይትባረክ ጋሻው ከፍተኛ የባህል ፈውስ መድህኒት አዋቂ እና ቀማሚ  ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦ በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
0917468918
0917468918
1 👉ለመፍትሄ ሀብት
2 👉ለህማም
3 👉ለመስተፋቅር
4 👉ቡዳ ለበላው
5 👉ለገበያ
6 👉የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 👉ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 👉ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 👉ለዓቃቤ ርዕስ
10👉ለመክስት
11 👉ለቀለም(ለትምህርት)
12 👉ሰላቢ የማያስጠጋ
13 👉ለመፍትሔ ስራይ
14 👉ጋኔን ለያዘው ሰው
15 👉ለሁሉ ሠናይ
16 👉ለቁራኛ
17 👉ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 👉ለመድፍነ ፀር
19 👉ሌባ የማያስነካ
20 👉ለበረከት
21 👉ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 👉አፍዝዝ አደንግዝ
23 👉ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 👉ለግርማ ሞገስ
25 👉መርበቡተ ሰለሞን
26 👉ለዓይነ ጥላ
27 👉ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 👉ለሁሉ መስተፋቅር
29 👉ጸሎተ ዕለታት
30 👉ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 👉ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 👉ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 👉ለድምፅ
34 👉ለብልት
35 👉በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ
0917468918
0917468918

      💚💛❤️ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 💚💛❤️
🌼🌻🌼🌻
👉የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
👉ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
👉ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
👉ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
👉ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
👉ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
👉ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
👉ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
👉ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
👉መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
👉ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን  💚💛❤️      
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር እኛ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልኝ ወይም በቴሌግራም መሪጌታ ይትባረክ ጋሻው ብላችሁ ታገኙናላችሁ
ወይም በስልክ ቁጥር ይደውሉልን
0917468918
0917468918
👍5
2025/07/13 18:48:12
Back to Top
HTML Embed Code: