Telegram Web Link
ትዕግስት እና ጽናት

“በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፡፡" (1ኛ ቆሮ. 9፥24)

እዚህ ላይ ጳውሎስ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚያስፈልገውን ትጋት እና ተግሣጽ ለማጉላት የሩጫ ውድድርን እንደምሳሌ ይጠቀማል:: እነዚያ የቆሮንቶስ ሰዎች “በፍጹም እውቀታቸው" በመታበያቸው፣ ያጎደሉትን ነገር በመንገር በዘዴ ይወቅሳቸዋል:: ጳውሎስ ጥረታቸው ከልብ የመነጨ ቢሆንም እንኳ ፍቅር የሌለው ራስን መግዛት የሌለው ከሆነ ያልተሟላ እንደሆነ ይነግራቸዋል::

የክርስትናን ሕይወት ሁሉም ከሚሳተፉበት የሩጫ ውድድር ጋር ያመሳስለዋል፤ ነገር ግን በዚህ ውድድር ሽልማቱን የሚቀበለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህ ንጽጽርም ድነት ለአንድ ሰው ብቻ የተገደበ ወይም ጥቂቶች የሚድኑ መሆናቸውን አያመለክትም:: ይልቁንም ልባዊ ጥረት፣ ተግሣጽ እና ትኩረት የመስጠትን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ያሳያል:: እንደ ሩጫ ውድድሩ ሁሉ፣ ወደዚህ ውድድር ለመግባት ሙሉ በሙሉ መዘጋጀት አለብን፤ ከፊል ጥረት ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የመጨረሻውን መስመር ለመድረስ እና ሽልማቱን ለመውሰድ በቁርጠኝነት እና በዓላማ መሮጥ አለብን፡፡

“እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ” የሚለው የጳውሎስ ማሳሰቢያ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሙሉ መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ እንዳልደረሱ ያመለክታል:: ገና ብዙ ነገርም መስራት ነበረባቸው:: ይህ የክርስቲያን ሕይወትን ቀጣይነት ያለው ቅድስናን የመሻት ጉዞ ነው::

የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፤ እኛ ግን የማይጠፋውን::" (1ኛ ቆሮ. 9፥25)

ለሩጫም ሆነ ለሌሎች ውድድሮች የሚያሠለጥኑ ሰዎች እንደ ሆዳምነት፤ ስካር ወይም ስንፍና ካሉ ነገሮች ይርቃሉ:: ከመጠን ያለፈ ራስን መግዛትንም ያሳያሉ:: ሙሉ ለሙሉም በዝግጅታቸው ላይ ያተኩራሉ፡፡ ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በማስወገድም ጥንካሬያቸውን እና አፈፃፀማቸውን ከፍ ለማድረግ ራሳቸውን ያለማመዳሉ:: በማያምኑበት ጨዋታዎች ውስጥም እንኳ ሯጮች ለሚጠፋው ምድራዊ ሽልማት ሲሉ በጥብቅ ራስን መግዛት ይኖራሉ፡፡

የጳውሎስ ነጥብ ግልጽ ነው፤ አትሌቶች ለሚጠፋ ሽልማት እንዲህ ያለውን ትጋትና ራስን መካድ የሚያሳዩ ከሆነ፣ ክርስቲያኖች የማይጠፋውን የዘላለም ሕይወት አክሊል ለማግኘት ምን ያህል መጣርይኖርባቸዋል? ለክርስቲያናዊ ሕይወት የሚሰጠው ሽልማት ከማንኛውም ምድራዊ ውድድር ከሚገኘው ሽልማት እጅግ የላቀ ነው:: የክርስቲያን “አክሊል" ጊዜያዊ ወይም አካላዊ ሽልማት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ያለ አንድነት እና የተስፋ ቃሉ ፍጻሜ፣ ዘላለማዊ ደስታ ነው::

የክርስትና ሕይወት በሁሉም ነገር ራስን መግዛትን ይጠይቃል:: በአንዱ ኃጢአት ላይ እየተዘፈቅን፣ ከአንዱ ኃጢአት መራቅ ብቻ በቂ አይደለም:: ለምሳሌ፣ አንድ አማኝ በቁጣ ወይም በትዕቢት እየተሸነፈ፡ በስካር ላይ አሸንፌያለሁ ማለት አይችልም:: እንደ ሯጭ ሁሉ አንድ ክርስቲያን በማንኛውም የሕይወት ዘርፍ፣ በአስተሳሰብ፣ በቃል እና በድርጊት ቅድስናን ማሳካት አለበት፡፡

ጳውሎስ ራስን ስለ መግዛት የሰጠው አጽንዖት የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ያላቸውን ቸልተኝነትና 'በእውቀታቸው ላይ ያላቸውን ከመጠን ያለፈ እምነት ይፈታተናል፡፡ እውቀት ብቻውን ሽልማቱን ማግኘትን አያረጋግጥም:: በፍቅር፤ በትህትና እና ራስን በመግዛት መታጀብ አለበት:: ውድድሩ ከፊል ጥረት ወይም ራስን ማመስገን ሳይሆን ስለ ሙሉ ቁርጠኝነት፤ ጽናት እና በመጨረሻው ግብ ላይ ስለማተኮር ነው ፤ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ያለ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡

“ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም!" (1ኛ ቆሮ. 9፥26)

ከላይ እንዳየነው የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ከሯጮች ራስን የመግዛት ጥበብ ጋር በማነፃፀር ምክር ይሰጣቸዋል፣ አሁን ራሱን ወደ ምሳሌው ያቀርባል፡፡ ይህን ለማድረግ ምክንያት የሆነውም በምሳሌነት ሌሎችን መመራት በክርስቲያናዊ ሕይወት አስፈላጊ ስለሆነ ነው::

ጳውሎስ “እንዲሁ አልሮጥም" ሲል፣ ያለ ዓላማ ሳይሆን በአእምሮ'ዬ ግልጽ የሆነ ግብ አስቀምጬ እሮጣለሁ ማለቱ ነው:: ያለ ምክንያት ተግባራቸውን ያደርጉ ከነበሩት ከቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በተለየ የጳውሎስ እያንዳንዱ ድርጊት ሆን ተብሎ የሚደረግና ሌሎችን ማዳን ላይ ያነጣጠረ ነበር፡ ነፃነቱን ቢጠቀምም፣ ከክፉ ለመታቀብ ቢመርጥም ወይም ራሱን ለሌሎች ሲል ቢያዋርድም ሁልጊዜ ግልጽ ዓላማ አለው! እግዚአብሔርን ማክበርና ባልንጀራዎቹን ማነጽ ነው፡፡

ጳውሎስ በመቀጠል እንዲህ አለ! “ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም” ይህ መንፈሳዊ ውጊያው ከጥላ ጋር የሚደረግ ሳይሆን እውነተኛ ጠላት ከሆነው ከሰይጣንና ከኃጢአት ኃይሎች ጋር የሚደረግ ትግል ነው፡፡ በአንጻሩ፣ የቆሮንቶስ ስዎች ጉልበታቸውን ከእውነተኛው ጠላት ጋር በመታገል ከማዋል ይልቅ፤ የራሳቸውን ልዕልና ለማሳየት ያውሉት ነበር፡፡

“ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክኹ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ::" (1ኛ ቆሮ. 9:27)

እዚህ ላይ፣ ጳውሎስ በራሱ ሕይወት ውስጥ ያለውን ከሥጋ ምኞት ጋር የሚደረገውን የማያቋርጥ ትግል አምኗል፤ ይህም ካልታረመ ወደ ኃጢአት ሊመራ ይችላል፡፡ ይህ እንዳይሆን "ሰውነቴን እየገሠጽኩት አስገዛዋለሁ" ይለናል፡፡ ይሁን እንጂ ጳውሎስ አካሌን አደክመዋለሁ ወይም እጠላዋለሁ አላለም:: ይልቁንም ጌታ ባሪያን እንደሚገሥጽ አድርጎ ይገስጸዋል:: ግቡ አካሉን ማድከም ሳይሆን ከኃጢአት ምኞቶች ይልቅ፣ አካሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል ማረጋገጥ ነው፡፡

ጳውሎስ የበቁ ሰዎች ላይ እንኳ ስላለ የቸልተኝነት አደጋ ተናግሯል። ምንም እንኳን ቢሰብክም፣ ቢያስተምርም... ነቀፋ የሌለበት ሕይወት መምራት ካልቻለ አሁንም “ከብቃት ውጪ" ሊሆን እንደሚችል አምኗል:: ይህ የሚያሳስበንም ማንም ከኃጢአት ፈተና ነፃ የሆነ የለም፣ ሌላው ቀርቶ እንደ ጳውሎስ ያለ የበቃ እንኳ ከዚህ ነጻ አይሆንም። ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ነፍሳት ወደ ክርስቶስ አምጥቶ ለወንጌል ብዙ ደክሞ የሠራው ጳውሎስ መውደቅን የሚፈራ ከሆነ፣ እኛ ተራ አማኞች እንዴት አብዝተን ንቁ መሆን የለብንም?

ብዙዎቹ በእምነታቸው ወይም “እውቀታቸው” ብቻ ይኩራሩ ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ ይህን የተሳሳተ አካሄድ አፍርሶታል:: እምነት ብቻውን በቂ አይደለም፤ እርምጃ እና ተግሣጽም ያስፈልጋል:: አዲስ ክርስቲያኖችን ሊጎዳ እንደሚችል እያወቁ በጣዖት ቤተመቅደሶች ውስጥ መብላትን የመሰሉ ግድየለሽ ምግባራቸውም የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ወደ መንፈሳዊ ውድቀት ሊመራቸው እንደሚችል ያስጠነቅቃል:: ለዚህም ነው ጳውሎስ ራሱን እንደ ምሳሌ የተጠቀመው፡፡ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ስኬት ቢኖረውም፣ ራሱን ያለማቋረጥ ይገሥጻል፤ ለቅድስናም ይተጋል፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
27👍9
ስለየተኛው እናመስግን?

“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እኅቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡

እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንኾናለን፡፡”

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍223
ማስታወቂያ

መምህር ይትባረክ ጋሻው ከፍተኛ የባህል ፈውስ መድህኒት አዋቂ እና ቀማሚ  ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦ በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
0917468918
0917468918
1 👉ለመፍትሄ ሀብት
2 👉ለህማም
3 👉ለመስተፋቅር
4 👉ቡዳ ለበላው
5 👉ለገበያ
6 👉የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 👉ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 👉ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 👉ለዓቃቤ ርዕስ
10👉ለመክስት
11 👉ለቀለም(ለትምህርት)
12 👉ሰላቢ የማያስጠጋ
13 👉ለመፍትሔ ስራይ
14 👉ጋኔን ለያዘው ሰው
15 👉ለሁሉ ሠናይ
16 👉ለቁራኛ
17 👉ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 👉ለመድፍነ ፀር
19 👉ሌባ የማያስነካ
20 👉ለበረከት
21 👉ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 👉አፍዝዝ አደንግዝ
23 👉ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 👉ለግርማ ሞገስ
25 👉መርበቡተ ሰለሞን
26 👉ለዓይነ ጥላ
27 👉ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 👉ለሁሉ መስተፋቅር
29 👉ጸሎተ ዕለታት
30 👉ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 👉ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 👉ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 👉ለድምፅ
34 👉ለብልት
35 👉በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ
0917468918
0917468918

      💚💛❤️ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 💚💛❤️
🌼🌻🌼🌻
👉የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
👉ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
👉ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
👉ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
👉ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
👉ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
👉ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
👉ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
👉ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
👉መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
👉ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን  💚💛❤️      
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር እኛ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልኝ ወይም በቴሌግራም መሪጌታ ይትባረክ ጋሻው ብላችሁ ታገኙናላችሁ
ወይም በስልክ ቁጥር ይደውሉልን
0917468918
0917468918
👍5
ቤተሰብና ምጽዋት

ኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ለጸሎት የሚኾን ቤት ከማዘጋጀት በተጨማሪ፥ ምጽዋት ከመስጠት አንጻርም ሊበረቱ ይገባቸዋል፡፡ ቢቻል ቢቻል ድኾችን በየጊዜው የሚመግቡባት አንዲት ቤት ብትኖራቸው መልካም ነው፡፡ ይህቺን ቤትም “የክርስቶስ በዓት” ብለው ሊሰይሟት ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም በድኾቹ አድሮ በዚያች ቤት ውስጥ መጥቶ የሚመገበው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያን ሙዳየ ምጽዋት ሳጥን እንዳለች ኹሉ ክርስቲያኖችም በየቀኑ ምጽዋት የሚያስቀምጡባትና አጠራቅመውም ድኾችን የሚረዱባት ትንሽ “ሙዳየ ምጽዋት” ማዘጋጀት ይገባቸዋል፡፡ ምጽዋት ባለበት ዲያብሎስ የለምና፡፡ በየቀኑ ጸሎት ከመጀመራቸው በፊትም በሙዳየ ምጽዋቷ ውስጥ የዓቅማቸውን ምጽዋት በማስቀመጥ መጀመር አለባቸው፡፡   

ከድኾች በተጨማሪ የኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ቤት ዘወትር ለመነኰሳት ክፍት መኾን አለበት፡፡ ቅዱሳኑ ምድራውያን መላእክት ወደዚያ ቤት ሲገቡ፥ እኩያት አጋንንትም በአንጻሩ እንደ ጢስ ተነው እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉና፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
32👍8❤‍🔥1
#መጋቢት_27

#መድኃኔዓለም (#ጥንተ_ስቅለት)

መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች።

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ) ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ ተደራድሮበት ነበር፡፡
ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡

የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡

ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡

ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡

በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን
👍159
የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡

በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡

‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡

የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡

ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡

የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን!

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2515
​​​​​​​​ኒቆዲሞስ
የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት።


''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። (ዮሐ 3:3-6)

ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር። በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡

ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡

ኒቆዲሞስ ማነው?

፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው《ዮሐ 3-1》
፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው《ዮሐ 3-1》
፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው《ዮሐ 3-10》
፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው 《ዮሐ 7-51》

ኒቆዲሞስ ምን አደረገ?

ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ《ዮሐ 3:1-21)
አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው 《ዮሐ 7-51》
ጌታን ለመገነዝ በቃ《ዮሐ 19-38》

=> ከኒቆዲሞስ ምን እንማር?
አትኅቶ ርእስ ጎደሎን ማወቅ የእውነት ምስክር《ስምዐ ጽድቅ》መሆን ትግሃ ሌሊት እስከ መጨረሻ መጽናት በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡

የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3714🕊1
የሌሊቱ ተማሪ ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በዮሐ. 3÷1 ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ 1÷2) በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው ኒቆዲሞስ “መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርገ የሚችል የለምና።" በማለት ተናገረ።(ዮሐ3፥2) በዚህ ጊዜ ጌታችን የገነት በር ስለሆነው ስለ ምስጢረ ጥምቀት አስፍቶና አምልቶ በምሳሌ ጭምር አስረዳው። "እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” (ዮሐ 3፥3) በማለት መንፈሳዊ እውቀት የጎደለው መሆኑን አሳይቶ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጪ እንደሚሆን አስርግጦ ነገረው።

በዚህም ታላቅ ምስጢርን ሊገልጥለት ወደደ። ይህ አነጋገር ከአይሁድ አለቆች አንዱ ለሆነው ፈሪሳዊ ሰው ከባድ ነበር። ምሥጢሩም ቢጸናበት ጊዜ ጌታን እንዲህ በማለት ጠየቀው “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንደምን ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማሕጸን ተመልሶ ሊገባ ይችላልን?“። (ዮሐ 3፥4) ጌታችንም ለኒቆዲሞስ መልሶ የአዳም ልጆች ሁሉ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ካልተወለዱ (በመንፈስ ቅዱስ መታደስን በሚያሰጥ ጥምቀት ካልተጠመቁ) መንግሥተ ሰማያትን መውረስ እንደማይችሉ ነገረው።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
30👍16🕊1
ምጽዋት ሥርየተ ኃጢአትን ትሰጣለች፡፡ ሞትንም ቢኾን ታርቃለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልጽ አደርግልሃለሁ፡፡

“መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውን ከተደረገ ታሪክ ተነሥቼ እነግርሃለሁና የምነግርህን ነገር አትጠራጠር፡፡

ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፡፡ መልካም ሥራን የሞላባትና ምጽዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታከማች ነበረች፡፡ ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ኹሉ ትሰጣቸው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች፡፡

አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛው ሰዓት ብድራታቸውን እንደሚከፍሉ ተመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኼዱ፡፡ ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስንና ሌላውን ኹሉ አሳዩት፡፡ ከእነርሱ ጋር በሕይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደ ነበረች ነገሩት፡፡ እንደ እናት የምትኾንላቸውን እንደ አጡ አልቅሰው ነገሩት፡፡ ስለ እነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት፡፡ 

የተወደደ ጴጥሮስስ ምን አደረገ? “ኹሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፡፡ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ ‘ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ’ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች፡፡ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች፡፡ እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፡፡ ምእመናንንና መበለቶችንም ጠራ፡፡ ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት”  (ሐዋ.9፥40-41)፡፡

የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርያው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህን? በወዲያኛው ዓለምስ ተወውና በዚህ ዓለምም ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደ ተቀበለች ተገነዘብን? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውንና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን? እርሷ ምግብና ልብስ ሰጠቻቸው፤ እነርሱ ግን ከሞት ወደ ሕይወት እንድትመጣ አደረጓት፡፡ ለመበለቶቹ ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት፡፡ 

እንግዲህ የምጽዋት የመድኃኒትነቷን ኃይል ተመለከትህን? እንግዲያውስ እኛም ይህን መድኃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ፡፡ መድኃኒቱ ይህን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ፡፡ መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይኾን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ፡፡ አንድ ሰው አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቈጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ፡፡ መበለቶች፥ እንደ ጣቢታ ከሞተ ነፍስ ይታደጉን ዘንድ ይህን መድኃኒት ከእነርሱ እንግዛ፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2011
ለምንድን ነው የምንጾመው?

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍348
መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ

መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ የምናገኘው ጥቅም ብዙ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በመውደድ የሚገኘው ርዳታ በእውነት ያለ ሐሰት እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህን በማስመልከተም ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፡- “ወኵሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ - የተጻፈው ኹሉ ለእኛ ምክር ለእኛ እዝናት ሊኾን ተጽፏል” (ሮሜ.15፥4)፤ “ዝንቱ ኵሉ ዘረከቦሙ ለእልክቱ ምሳሌ ተጽሕፈ ለአእምሮ ወለተግሣጽ ዚአነ እለ በድኅረ መዋእል - እነዚያን ያገኛቸው መከራ ኹሉ በኋላ ዘመን ለምንነሣ ለእኛ ምክር እዝናት ሊኾን ተጽፏል” (1ኛ ቆሮ.10፥11)፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የኹሉም ዓይነት መድኃኒቶች ሳጥን ነው፡፡ የትዕቢት ቁስሉ ይሽርለት ዘንድ የሚሻ ሰው በዚህ ሳጥን ውስጥ ጽኑ መድኃኒትን ያገኛል፡፡ ልል ዘሊልነትን ለመጣል፣ ፍቅረ ንዋይን ከእግሩ ሥር ለመርገጥ፣ መከራን ለመናቅ፣ ጥብዓትን ገንዘብ ለማድረግ፣ ትዕግሥትንም ለማግኘት የሚፈልግ ሰው መድኃኒቱን ከዚህ ሳጥን ውስጥ ያገኛል፡፡

በከፍተኛ ሥጋዊ ድኽነት ውስጥ የኖሩትን፣ በጽኑ ሥጋዊ ሕመምም የተሠቃዩትን አይቶና ገድላቸውን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አንብቦ መጽናናትን የማያገኝ ማን ሰው አለ? የመጻጉዕን ታሪክ አንብቦ ጥበብ መንፈሳዊን ገንዘብ የማያደርግ ማን ሰው አለ? ምክንያቱም መጻጉዕ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ሙሉ ሽባ ነበር፡፡ በእያንዳንዷ ዓመት መዳንን ይናፍቅ ነበር፡፡ ይህን ኹሉ ዓመታት በበሽታ ተይዞ እያለ ግን ተስፋ አልቆረጠም ነበር፡፡ ስላለፈው ዓመታት ብቻ ሳይኾን ለወደፊቱም ተስፋ አልቆረጠም ነበር፡፡

እንዲያውም የመከራውን ታላቅነት ተመልከቱ! ተመልከቱና አድንቁ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡- “ልትድን ትወዳለህን?” ባለው ጊዜ፡- “አዎ ጌታ ሆይ! ነገር ግን በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም” ይላልና፡፡

ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር አለ? እኮ ከዚህ በላይ ምን አስጨናቂ ኹኔታ አለ? ለብዙ ዘመናት ሥቃይ ከመታገሡ የተነሣ የተወቀረ ልቡን ተመለከታችሁን? ለብዙ ዓመታት መከራ ከመቀበሉ የተነሣ የልቡ ሁከት እንደ ምን ጸጥ እንዳለለት አያችሁን? ምክንያቱም ከአንደበቱ አንዲት የማጉረምረም ቃል አልወጣችም፡፡ በብዙዎች ዘንድ እንደምንሰማው የተወለደባትን ቀን አልረገመም፡፡ “ይህን ያህል ዓመት ታምሜ እያየኝ፥ እንዴት ልትድን ትወዳለህን ብሎ ይጠይቀኛል?” ብሎ አልተበሳጨም፡፡ “ወደ እኛ የመጣኸው በሕመማችን ላይ ጥዝጣዜ ለመጨመር ነውን? ልትድን ትወዳለህ ወይ ብለህ የምትጠይቀኝስ በእኔ ላይ ለማፌዝ ነውን?” አላለም፡፡ ታዲያ ምን አለ? ተረጋግቶና ከፍ ባለ ትሕትና ኾኖ “አዎን ጌታ ሆይ!”

ተመልከቱ! እያናገረው ያለው እንኳን ማን መኾኑን አያውቅም፡፡ እያናገረው ያለው ሊያድነው ይችል እንደ ኾነና እንዳልኾነ አያውቅም፡፡ ቢኾንም ግን ተረጋግቶ ያለበትን ኹኔታ ነገረው፡፡ ከዚህ በላይ ምንም አልጠየቀውም፡፡ እንዲሁ የሕመሙን ታሪክ ለባለመድኃኒት እንደሚናገር ሰው ኾኖ ነገረው፡፡ ምናልባት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል ብሎ ቢያስብ ነው፡፡ ኢየሱስስ ምን አለው? “ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ኺድ!”

… ስለዚህ ዕለት ዕለት መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ እንደ በሽታችን ዓይነት እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ጽኑ መድኃኒቶችን እናገኛለንና እናንብብ፡፡

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍1917🕊1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

#የዐቢይ_ጾም_ስምንተኛው_እሁድ_ሆሳዕና_ይባላል

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ መልካም በዓል ይሁንልን! ይሁንላችሁ፡፡

#ሆሳህና ማለት......✍️

👉‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው።
👉ሆሳህና ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ጌታ ሆሳህና በአርያም እየተባለ ወደ ቤተ-መቅደስ የገባበት ዕለት መታሰቢያ ነው።
+【ማቴ 21÷12】። ይህ እለትም የመጨረሻው ሳምንት ነው።
+ በዚህ እለትም የሚፈፀመው ሥርዓት አምልኮ ከሌሎቹ ሰንበታት የሰፋና የረዘመ ነው።

+ ከሰርክ ሆሳህና እስከ ትንሳኤ ያለው ሰባት ቀን ሕመማት ይባላል።
+ በእነዚህ ቀኖች ብዙ አዝማድ መባልዕት አይበሉም።
👉 ስግደት፣ በመስገድ የጌታችን መከራና ሞት የሚያስታውሱ መጻሕፍትን፣ በማንበብ፣ አዳም
ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ የኖረበትን ለማሰብ ነዉ፡፡
+ የጨለማና የመከራ ዘመን በማስታወስ መንበረ ታቦቱን ጥቁር ልብስ በማልበስ፣ ጥቁር ልብስ ተክኖ በመልበስ ስረዓቱ ይከናወናል።
+ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
👉 ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናገሮ ነበር። ሲመጣም በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል።
👉 መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ ፣ ምዕራፍ ፱፣ ቁጥር ፲፫ ። የሆሣዕና በዓል የቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።
👉( መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፯ ቁጥር ፳፮) በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብናበማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይታደላል።
👉በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚጠቅሱት የ ቅዱስ ማቴዎስ (ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩፡፲፯)፤ የ ቅዱስ ማርቆስ (ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፩–፲)፣ የ[ቅዱስ ሉቃስ]] (ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፱–፴፰) እና ፤ የ[[ቅዱስ ዮሐንስ] (ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፲፪–፲፭) ወንጌላት ይነበባሉ ።
👉 በሆሣዕና ዕለት ከሌሎች እንስሳት ይለቅ ጌታን ለመሸከም ለክብር የተሸከመችው አህያ ናት።
👉ጌታን የተሸከመችው አህያ ከዚያ በፊት ያላየችውና ያልተደረገላት ክብር ተደርጎላታል። አህያ ከዚህ በፊት ለኛ እህል ተሸክማ ስትሄድ ሂጂ እያልን በዱላ
እንደበድባት ነበር፡ ነውም።
👉 ነገር ግን በሆሣዕና ዕለት እንኳን በዱላ ልትደበደብ ቀርቶ ሰዎች በእርሷ ላይ ለተቀመጠው ጌታ ሲሉ ልብሳቸውን ሁሉ እያነጠፉላት በንጣፍ ላይ ተራምዳለች ።
👉 ኢየሩሳለሌም ሲደርስ ከገጹ ብርሃን የተነሣ ከተማዋ ብርህት ሆነች፡፡ ሕዝቡ የሆነውን ሊያዩ ወጡ፡፡
👉ሕፃናት ፀሐይ ስትሰግድለት መላእክት ከበው ሲያመሰግኑት አይተው በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የሰሌን ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል፡፡

👉 ሆሣዕና ማለት በልዕልና ጸንቶ የሚኖር መድኃኒት ማለት ነው፡፡
#ጾም #ጸሎታችንን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን! አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3329❤‍🔥4
ማስታወቂያ

መምህር ይትባረክ ጋሻው ከፍተኛ የባህል ፈውስ መድህኒት አዋቂ እና ቀማሚ  ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦ በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
0917468918
0917468918
1 👉ለመፍትሄ ሀብት
2 👉ለህማም
3 👉ለመስተፋቅር
4 👉ቡዳ ለበላው
5 👉ለገበያ
6 👉የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 👉ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 👉ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 👉ለዓቃቤ ርዕስ
10👉ለመክስት
11 👉ለቀለም(ለትምህርት)
12 👉ሰላቢ የማያስጠጋ
13 👉ለመፍትሔ ስራይ
14 👉ጋኔን ለያዘው ሰው
15 👉ለሁሉ ሠናይ
16 👉ለቁራኛ
17 👉ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 👉ለመድፍነ ፀር
19 👉ሌባ የማያስነካ
20 👉ለበረከት
21 👉ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 👉አፍዝዝ አደንግዝ
23 👉ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 👉ለግርማ ሞገስ
25 👉መርበቡተ ሰለሞን
26 👉ለዓይነ ጥላ
27 👉ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 👉ለሁሉ መስተፋቅር
29 👉ጸሎተ ዕለታት
30 👉ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 👉ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 👉ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 👉ለድምፅ
34 👉ለብልት
35 👉በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ
0917468918
0917468918

      💚💛❤️ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 💚💛❤️
🌼🌻🌼🌻
👉የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
👉ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
👉ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
👉ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
👉ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
👉ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
👉ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
👉ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
👉ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
👉መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
👉ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን  💚💛❤️      
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር እኛ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልኝ ወይም በቴሌግራም መሪጌታ ይትባረክ ጋሻው ብላችሁ ታገኙናላችሁ
ወይም በስልክ ቁጥር ይደውሉልን
0917468918
0917468918
👍51
ሰሞነ ህማማት ማክሰኞ

 ማክሰኞ (የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል
ይኸውም የሆነበት ምክንያት ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ ሰጠ ጌታችን ፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሐተ ቤተመቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጻሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል ነው፡፡
ጥያቄውም ከምድራውያን ነገስታት ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ስልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ (ማቴ 21፡23-27 ፣ ማር 11፡27-33 ፣ ሉቃ 20፡1-8) ጌታም መልሶ እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፣ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች ከሰማይ? ወይስ ከሰው? አላቸው፤ እነሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፣ ከሰው ብንል ሕዝብ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ከወዴት እነደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፣ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ስልጣን እንደሚያደርግ አጥተውት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡
ጌታ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ እንዲል (ማቴ 16፡7) እንደ ፈሪሳውያን ከክፋት ከጥርጥር መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው፡፡ (ማቴ 21፡28 ፣ ማቴ 25፡46 ፣ ማር 12፡2 ፣ ማር 13፡37 ሉቃ 20፡9 ፣ ሉቃ 21፡38) በዚህ ሳምንት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበት ይገባዋል፡፡
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
36👍17
​​​​​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች እንመልከት

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታችንን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም ይኸውም ቆሎ ዳቦ ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13  ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍258
Forwarded from Ggh
ሕማማት ሐሙስ [ ጸሎተ ሐሙስ ]

"እንበለ ደዌ ወሕማም እንበላ ጻማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሐክሙ ለብርሃነ ትንሳኤ በፍስሐ ወበሰላም"

ይህ ዕለት ብዙ ስያሜዎች አሉት። ከስያሜዎቹ ሁሉ ጎልቶ የሚነገረው ግን ጸሎተ ሐሙስ የሚለው ነው።

1, ጸሎተ ሐሙስ ፡- ጌታችን መከራ ፣ ፈተና በገጠመን ጊዜ ተግተን መጸለይ እንዳለብን ለማስተማር በጌቴሴማኔ ስለ ጸለየ ፤ እንዲሁም ለሐዋርያት ሥርዓተ ጸሎትን ስላስተማረ አንድም "ወደፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ " ብሎ ስላዘዘን ዕለቱ ይህን ስያሜ አግኝቷል።

2. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ፡- ጌታችን በዚህ ዕለት "ይህ የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት ነው" ብሎ ሥጋ ወደሙን ስለሰጣቸው እንድም በእንስሳት ደም ይፈጸም የነበረውን መሥዋዕተ ኦሪትን አሳልፎ አዲሱን መሥዋዕት ሥጋ ወደሙን ስለሰጠን ይህን ስያሜ አግኝቷል።

3, የነጻነት ሐሙስ ፡- የሰው ልጅ ከዲያቢሎስ ባርነት ተላቆ ነጻነት የተረጋገጠበት ብሉይ ኪዳን አልፎ አዲስ ኪዳን የተተካበት በመሆኑ አንድም "ከእንግዲህ ወዲህ ባሪዎች አልላችሁም ልጆች ግን እላችዋለሁ "ብሏልና የነጻነት ሐሙስ ትባላለች። /ማቴ 26÷17-19/ ፣ /ማር 14÷12-16/ ፣ /ዮሐ 15÷15/

4. ኅጽበተ ሐሙስ ፡- በዚህ ዕለት ጌታችን ትህትናን ለማስተማር ራሱን ዝቅ አድርጎ የሐዋርያቱን እግር ስላጠበ ዕለቱ ይህን ስያሜ አግኝቷል። እባቶቻችን እንዳስተማሩን እግራቸውን መታጠባቸውም ጥምቀት ሆኖላቸዋ።

5, የምስጢር ቀን ፡- ጌታችን ኅብስቱንና ወይኑን ባርኮ ፣ ቀድሶና ለውጦ "ይህ በዕለተ አርብ ስለ ዓለም ቤዛ የሚቆረሰው ሥጋዪና የሚፈሰው ደሜ ነው ብሉ ጠጡ" በማለት ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን እንዱን ምስጢረ ቁርባንን የፈጸመበት (የመሰረተበት) ዕለት በመሆኑ የምስጢር ቀን ይባላል። በዛሬ ቀን ከሌሎቹ ቀኖች በተለየ መልኩ ቅዳሴ ይኖራል የተዘጋጁ ክርስቲያኖች ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ።

የዕለቱ ምስባክና ወንጌል


📖 አንድ ሰዓት መዝ 54÷21 ፣ 12
= ሉቃ 22÷1-
14
📖 ሦስት ሰዓት መዝ 93÷21
= ማቴ 26÷17-
19
📖 ስድስት ሰዓት መዝ 30÷13
= ማር 14÷12-
16
📖 ዘጠኝ ሰዓት መዝ 22÷1-2
= ሉቃ 22÷7-
13



ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍279🕊1
ቀዳም ሥዑር

"በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና። ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ። ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን" /ማቴ. ፳፯፥፷፪-፷፫/
ከስቅለት ማግሥት የምትመጣው ቅዳሜ በሥጋው የሞተው ጌታችን በመቃብር ያረፈበት ዕለት ነው። ይህች ዕለት በተለያዩ ስያሜዎች ትጠራለች።

1. ቀዳም ሥዑር

ይህች ዕለት ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ሥዑር /የተሻረች/ ተብላለች። ቅዳሜ ጠዋት፣ ምእመናኑና ካህናቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፤ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም "በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ፤ ትንሣኤውን ገለጸ፤ የምሥራች" እየተባለ ይዘመራል። ካህናቱም የተባረከ ቀጤማ ለምዕመናን ያድላሉ። ቀጤማ የሚበቅለው በወንዝ ዳርና በረግረጋማ ቦታዎች ነው። ክረምት ሲሆን ውኃ ሲሞላ በውኃ ትዋጣለች ፣ የተፈጥሮ መልኳ ጠፍቶ ቢጫ ትሆናለች አልፎም ተርፎ ትበሰብሳለች ፤ ክረምት አልፎ ውኃ እየጎደለ ሲሔድ ደግሞ ትለመልማለች።

ካህናትም ለምለም ቄጤማ ማደላቸው ክርስቶስ ስለ እኛ በመስቀል ተሰቅሎ በመሞቱ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በሙሉ በሰው ልጅ ላይ የተፈረደበት መርገምና ሞት መወገዱ ፣ አንድም ቄጤማ በውኃ ሙላት ምክንያት የተነጠቀውን አረንጓዴነት ውኃ ሲጎድል መልሶ እንደሚያገኝ ሁሉ የሰው ልጅም በክርስቶስ መከራና ሞት ወደ ቀድሞው ክብሩ መመለሱን ለማብሠር ነው።

2, ለምለም ቅዳሜ

ካህናትና ዲያቆናት ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜ ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል እየመቱ ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምዕመናንም ይህንን ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ያስሩታል። ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት ለማያስታውስ የሚደረግ ነው፡፡ 

በብሉይ ኪዳን ምድር በጥፋት ውሃ በተጥለቀለቀች ጊዜ የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ፣ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡

3. ቅዱስ ቅዳሜ

ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል። ዕለቱ በሲዖል ለነበሩት ነፍሳት የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በሰንበት ዕለት የግልም ሆነ የአዋጅ ጾም በፍጹም አይጾምም። ነገር ግን በዚህች ቅዳሜ ይህ ሥርዓት ይሻራል ይጾማልም። ስለዚህ የተሻረችው ቅዳሜ ተባለች። በዚህ ዕለት የሚጾምበት ምክንያት እናቱ እናታችን ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታን ሞት አይተው እስከ ትንሳኤው ምግብን አልቀመሱም ነበር። ይህን መሠረት በማድረግ ሁላችን ከቻልን ከሐሙስ ምሽት ጀምሮ እናከፍላለን ይህ ከከበደን ደግሞ አርብ ማታ ተመግበን ቅዳሜን ቀኑን ሙሉ ውለን እስከ ሌሊቱ 9:00 ሰዓት እናከፍላለን እንጾማለን።



ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍2716🕊5
“ተነሥቶአል በዚህ ፣ የለም” ማር. 16፡6 ።

እንኳን ለ2017 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ !

“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም ፤”

ትርጓሜ፡-

“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ።
ዲያብሎስን አሰረው ፤ አዳምን ነጻ አወጣው ።
ሰላም ! ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ።” /ኦርቶዶክሳዊ አዋጅ/

. . .

በዓለም ላይ አንድ መቃብር ብቻ ባዶ ነው ። በጠባቆች የሚጠበቁ ብዙ መቃብሮች አሉ ። መቃብሩ እየተጠበቀ ግን ከተማውን የሞላ አንድ ብቻ ነው ። ተነሥተው ሕያው የሆኑ ሰዎችን አናውቅም ፣ ዳግም ሞት ላይዘው የተነሣውን ጌታ ግን እናውቃለን ። መግነዙን ቢያልፍ ፣ የተዘጋውን ቋጥኝ አያልፍም ፤ ቋጥኙን ቢያልፍ ወታደሮችን አያልፍም ፤ ወታደሮችን ቢያልፍ ገንዘብ የሚያስለፈልፋቸውን እውነትን ሐሰት የሚሉትን ማለፍ አይችልም ተብሎ ሳለ ምድርን የሞላው አንድ ብቻ ነው ። የሥጋውያንና የረቂቃንን ምክር ፣ የሲኦልና የሮማ ቤተ መንግሥትን ትብብር ፣ የቤተ ክህነትና የቤተ መንግሥትን ሽርክና ፣ የሊቀ ካህናትና የንጉሠ ነገሥትን ፊርማ አሸንፎ ልብን ግዛቱ ያደረገ አንድ ብቻ ነው ። እርሱም ከሞት የተነሣው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

እንደ እርሱ ሞት ያስገረመ ፣ እንደ እርሱ ትንሣኤ ያስደመመ የለም ። የማይሞተው ሲሞት “የምትወዱት አልቅሱለት” ተባለ ፣ በራሱ ኃይልና ሥልጣን ሲነሣ “ክብርና በረከት ይገባዋል” ተባለ ። መቃብሮች ሁሉ አጽሞች እንዳይሰረቁ ይጠበቁ ይሆናል ፣ እንዳይነሣ የሚጠበቅ መቃብር ግን የለም ።ክርስቶስ ግን እንዳይነሣ መቃብሩ ዘብ ቆመበት ፤ ከወዳጆቹ ይልቅ መነሣቱ በጠላቶቹ የታመነ ነበር ። ጠላቶቹ መሞቱንና መነሣቱን  ቢያምኑም አልዳኑም ። ለመዳን ከእርሱ ጋር መሞትና መነሣት ያስፈልጋልና ። ገደልነው ብለው ደስ ይላቸዋል ፣ ወዲያው እነሣለሁ ብሏል እያሉ መረበሽ እንቅልፍ ይነሣቸዋል ። የማያስተኛ ሟች ፣ የማይያዝ የትንሣኤ ጌታ ነው ። መቅደስ እያከበሩ መቅደስ ሰውነቱን አፈረሱ ፣ የሦስት ቀን ድልን ፈቀደላቸው ። ያዘኑ ወዳጆቹ ይደሰቱ ዘንድ ፣ የተደሰቱ ጠላቶቹ ያፍሩ ዘንድ ክርስቶስ ተነሣ ። የእስራኤልን መነሣት ተስፋ እያደረጉ የሚያነሣትን ገደሉት ። እንደ አቅማቸው ከእንቅልፍ እየተነሡ እንደ አቅሙ ከሞት እንደሚነሣ ዘነጉ ። የኃጢአት አውራው ዝንጋዔ ነው ። አይቶ እንዳላየ መሆን ነውና ።

ወትሮም እነርሱ በመቅደስ ሆነው እርሱ በመንደር ሲያስተምር አላፈሩም ። ከመቅደስ ሳይሆን ከከተማው አውጥተው ሰቀሉት ። ዛሬም ክርስቶስ በደጅ ነው ፣ መቅደሱ በሰቃዮች ሲሞላ ክርስቶስ በደጅ ይኖራል ። በመቅደስ በአሮናዊ ሥልጣን ፣ በደጅ በሮማውያን ሥልጣን ከምድረ ገጽ ይጥፋ ብለው ተነሡ ። ከመቅደስ ቢያባርሩት መቅደሱ ፈረሰ ፣ ከከተማ ቢያባርሩት ኢየሩሳሌም ተደመሰሰች ። ከዓለም ቢያባርሩት ዓለም ምጥ ያዘው ። እውቀቱ ወደ አለማወቅ ተለወጠ ። የመግደል እውቀት የማዳን እውቀት መሆን አቃተው ። እርሱ ግን ሰማይ ቤቱ ፣ ምድር ግዛቱ ፣ ምእመን ርስቱ ነው ።

ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እንደ ቆየና ሕያው እንደ ነበረ ክርስቶስም በሙታን መንደር ሙታንን እየፈለገ ሕያው ነበር ። ዮናስን የጣሉ እንደ ሞተ ያውቃሉ ፣ የጣሉት ሳያዩት ንስሐ የገቡ አዩት ። ክርስቶስም ያረዱት ሳይበሉት ፣ ኃጢአተኛ ነን ያሉ ጠገቡት ። ዮናስ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ነነዌ በንስሐ ድምፅ መጣ ፣ ጌታም ወደ ነነዌ ዓለም “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያሉ ወደሚሄዱት ደቀ መዛሙርት መጣ ። ከትንሣኤ በኋላ ቂምና መተዛዘብ የለም ፣ ለካደው ጴጥሮስ ቅድሚያ ተገለጠ ፣ አፍሮ እንዳይጠፋበት ። ለማናፍረው እያፈረ ስንት ዘመን አባበለን ። የሸሹትን ደቀ መዛሙርት ሳይታዘብ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ ። እርሱ “የሰውን ድካም ያውቀዋልና” ። ሞት ፍቅሩን አልገደለበትም ። እኛ ጭረት ፣ ትንሽ ቍስል ፍቅራችንን ገድላብን ይኸው ተስፋ ቢስነት ያሰቃየናል ። ለይቅርታ ካልተነሣን ሳንነሣ እንቅር ። መነሣት ብቻ በቂ አይደለም ፣ ለምንድነው የተነሣነው ማለት ያስፈልጋል ። ጌታ ለይቅርታ ፣ ብዙዎች ለበቀል ተነሡ ።

ክርስቶስ ጊዜ ሰጥቶት አልተነሣም ፣ በራሱ ኃይል ተነሣ ። በእግዚአብሔር መንግሥት ጊዜ የሚባል ቸር የለም ፣ ሁሉን የሚያደላድል የመለኮት እጅ ነው ። ሰዎች ማደሪያ ከልክለውት በደብረ ዘይት ጫካ ያድር የነበረው ምድር ግን ለሦስት ቀን ሸሸገችው ። ገጣሚው፡-

“ሞት ይቅር ይላሉ ፣
ሞት ቢቀር አልወድም ፤
አፈሩም ድንጋዩም ከሰው ፊት አይከብድም” ያለው ለዚህ ነው ።

እርሱ በሥጋ ሞተ ፣ በመለኮቱ ግን ሕያው ነው ። ሰንበትን በመቃብር አከበረ ። የሕይወት ሰንበታችን ነውና ልናከብረው እንደሚገባን አስተማረን ። መነሣቱን አይሁድም ይጠብቃሉ ጦር ይዘው ፣ ቅድስት እናቱም ትጠብቃለች ምስጋና ይዛ ። አጠባበቃችን እንጂ መጠበቃችን ዋጋ አይሰጠውም ። እግዚአብሔር ወራጁን ትቶ ምንጩን ያያል ። ሰው ግብዝ ነውና ወራጁን እያየ ያብዳል ። የእግዚአብሔር ልጅን መቃብር ከሦስት ቀን በላይ አልቻለውም ። በፈቃዱ ሞተ ፣ ተቀበረ ። ጠባቂዎቹ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብቻ እንዲጠብቁ ታዘዙ ። በአይሁድ ልማድ ሦስተኛው ቀን ሞት እርግጥ የሚሆንበት ነው ። ጌታችን ግን ሞት እርግጥ በሚሆንበት ቀን ትንሣኤውን እርግጥ አደረገ ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት አፍረው ወደ ገሊላ ይመለሱ ነበር ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት ተነሣ በማለታቸው ወንጀለኛ ተብለው መከሰስ ሳይሆን አበዱ ተብለው መታከም ይኖርባቸው ነበር ። የሚከሰስም ጤነኛ ነውና ።

የምታምኑት እስኪ እልል በሉለት ። ምንድነው ዝምታው ? ስለ ሞት እያወራችሁ ስለ ሕያው ጌታ ምነው ዝም አላችሁ ? ጌታ ሆይ ተነሥተሃል አምናለሁ ። አይሁድ በጥፊ የመቱትን ጉንጭህን እስመው ዘንድ ወዴት አገኘዋለሁ ? ከበው ርኩስ ምራቃቸውን የተፉብህ ከብቦ የሚያስጨንቀንን በትንሣኤህ ጉልበት በትነው ።

ጸሎት

ቅድስት ሞትህን ቡርክት ትንሣኤህን አምናለሁ ፣ እባክህ ጽድቄን ይቅር በለው ። ፎቶ የሚያነሣ ይዤ እመጸውታለሁ ፣ መልክ ቀራጭ አቁሜ ስግደት እሰግዳለሁ ። ለዝና ደግ ነኝ ፣ ለወሬ ሰጪ ነኝ ። ዛሬ ኃጢአቴን ሳይሆን ጽድቄን ይቅር በለው ። ክፉ መስሎ የሚከፋውን ሁሉ ይጠላዋል ፣ ደግ መስሎ መክፋትን አንተ ትጠላዋለህ ። እባክህን ግብዝነት ያሸተተውን ይህን ሁሉ ሬሣ አንሣው ። አደራህን ብቻህን እንዳትነሣ የሞተ ወገንህን ይዘህ ተነሣ ። ታርደህ በጽዮን ለቆምከው በግ ምስጋና አቀርባለሁ ። በማይፈጸም ዘመን ለዘላለሙ አሜን::
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍3211
💖        🍒        💖

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡


✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
💛
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
💛
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡:

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍469
🎼ዘፈን ለምን ይከለከላል ⁉️

➭ ዘፋኝነት የተከለከለበትን ምክንያት በግድ ማወቅ አለብኝ ለምን ትላለህ?

➨ ምክንያቱን ማወቅህ አያፀድቅህም አለማወቅህም አያስኮንንህም፡፡ ነገር ግን ዘፋኝ ብትሆን ትጠየቅበታለህ፡፡ ባትዘፍን ደግሞ ታዛዥ ተብለህ በእግዚአብሔር ዘንድ ትመሰገነበታለህ፡፡ ስለዚህ የሚመለከትህን ለምን አታደርግም?

➣ . . . ዘፈን ለምን እንደተከለከለ መዘርዘሩ ምስጢሩን እንደሚያጠበው መገለጹ ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ይሕ እንዳለ ሆኖ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት የዘፈንን ጎጂ ገጽታ ማሳየት ይገባል፡፡

ሀ. ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡

➣ ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13፥21 አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን ተረዳ፡፡
ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል ‹‹ . . . እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› የዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለውን አጋንንትን ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጎራ መሰለፋቸው ነው፡፡

➾ ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቅ አይንህ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለህ መርምር፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛውም እንደሆነ ማስተዋል ሞክር፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተህ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ባለውቃቤዎችስ ሲደነፉ ተመልክተህ አታውቅምን? የባለ ውቃቤዎች ድንፋታ ደግሞ ቁርጥ እዋኽ፣ እዋኽ እየተባለ የሚዘፈነውን ባህላዊ ዘፈን ይመስላል፡፡ ፍከራው ቀረርቶውና በየብሄረሰብ የምትመለከተውን ዘፈንና ጭፈራ ብትመረምር ከዚህ የቀረበ መመሳሰል አታጣበትም፡፡ ቅዱስ ሐዊ እንደተናገረው ‹‹ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ›› ነውና፡፡

➨ አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ የዘፈንና የጭፈራ ዓይነት ሁሉ ምንጮች ናቸውና፡፡ ከዚህ በኋላ የእኔ ስጋት ዘፋኞች እና ጨፋሪዎች አዳዲስ የዘፈን እና ጭፈራ መንገድ ለመኮረጅ ሲሉ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ፍለጋ በየፀበል ስፍራው መዞር እንዳይጀምሩ ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች የሚሹት ገንዘብንና ዝናን ብቻ እንጂ ሃይማኖት እና ምግባርን አይደለምና፡፡

➲ ለ. ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡

⚠️ ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዘመናችን የሐጢያት ተግባራት በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ አንበሳ ምግቡ ሥጋ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንበሳ ሳር እንዲበላ ማድረግ እንደማያቻል ሁሉ ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡

➼ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ስለ ተግባረ እድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ህግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሰሩ ይገባል፡፡
እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጨዋታ፣ በእግር አንደማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር፡፡ ይሕ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደስራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል፡፡

➲ ሐ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሀጥያት ነው፡፡

➣ ገላ 5፡21 ስለዚህ ዘፈን መዝፈን በመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ይከለከላል፡፡ ክርስትያኖች በመንፈሳዊ ሀሳብ መመላለስ እንጂ እንደ ዘፈን ያለውን ስጋዊ ስራ መስራት የለባቸውም፡፡ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ተብሏልና፡፡ ገላ 5:21

➲ መ. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡

➣ ሐመር መጽሔት ይህን ሲያስረዳ ‹‹ዛሬ የአለም ሕዝብ የሚያዘወትረውን ዘፈን ሐዋርያት በትምህርታቸው ደጋግመውና አጥብቀው ተቃውመውታል ይላል

በእርግጥም ሐዋርያት በዲድስቅልያ ‹‹አትኩኑ ዘፋንያነ››፤ ‹‹ዘፋኝ አትሁኑ›› ብለዋል፡፡ ዲድስ አን7
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ብሏል፡፡ ሮሜ 13፡13 ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ " በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡" ይለናል 1ኛ ጴጥ 4፡3

➣ በላይኛው አንቀጽ በሰፈረው የሮም ክታቡ ቅዱስ ጳውሎስ ዘፋኝነትን ከዝሙትና ከስካር ጋር አስተካክሎ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ጴጥ 2፡13-15

➭ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑትንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ መመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ2፡13-15
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ ‹‹ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል፡፡›› ይለናል፡፡ መጽ ሐዊ አን50

➨ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ !"ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ" በማለት ይማፀናል (ተግ ዘዮሐ አፈ 28)

⚠️ ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ፀንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን፡፡ መጽ ሐዊ አን 12 ይህ የሐዊ ቃል ሐዋርያው "የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› ማለት በምን ይለያያሉለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
👍4522
2025/07/09 15:29:02
Back to Top
HTML Embed Code: