Telegram Web Link
Forwarded from Ggh
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ተነሥቶአል በዚህ ፣ የለም” ማር. 16፡6 ።

እንኳን ለ2017 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ !

“ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም
ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም ፤”

ትርጓሜ፡-

“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ።
ዲያብሎስን አሰረው ፤ አዳምን ነጻ አወጣው ።
ሰላም ! ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ።” /ኦርቶዶክሳዊ አዋጅ/

. . .

በዓለም ላይ አንድ መቃብር ብቻ ባዶ ነው ። በጠባቆች የሚጠበቁ ብዙ መቃብሮች አሉ ። መቃብሩ እየተጠበቀ ግን ከተማውን የሞላ አንድ ብቻ ነው ። ተነሥተው ሕያው የሆኑ ሰዎችን አናውቅም ፣ ዳግም ሞት ላይዘው የተነሣውን ጌታ ግን እናውቃለን ። መግነዙን ቢያልፍ ፣ የተዘጋውን ቋጥኝ አያልፍም ፤ ቋጥኙን ቢያልፍ ወታደሮችን አያልፍም ፤ ወታደሮችን ቢያልፍ ገንዘብ የሚያስለፈልፋቸውን እውነትን ሐሰት የሚሉትን ማለፍ አይችልም ተብሎ ሳለ ምድርን የሞላው አንድ ብቻ ነው ። የሥጋውያንና የረቂቃንን ምክር ፣ የሲኦልና የሮማ ቤተ መንግሥትን ትብብር ፣ የቤተ ክህነትና የቤተ መንግሥትን ሽርክና ፣ የሊቀ ካህናትና የንጉሠ ነገሥትን ፊርማ አሸንፎ ልብን ግዛቱ ያደረገ አንድ ብቻ ነው ። እርሱም ከሞት የተነሣው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

እንደ እርሱ ሞት ያስገረመ ፣ እንደ እርሱ ትንሣኤ ያስደመመ የለም ። የማይሞተው ሲሞት “የምትወዱት አልቅሱለት” ተባለ ፣ በራሱ ኃይልና ሥልጣን ሲነሣ “ክብርና በረከት ይገባዋል” ተባለ ። መቃብሮች ሁሉ አጽሞች እንዳይሰረቁ ይጠበቁ ይሆናል ፣ እንዳይነሣ የሚጠበቅ መቃብር ግን የለም ።ክርስቶስ ግን እንዳይነሣ መቃብሩ ዘብ ቆመበት ፤ ከወዳጆቹ ይልቅ መነሣቱ በጠላቶቹ የታመነ ነበር ። ጠላቶቹ መሞቱንና መነሣቱን  ቢያምኑም አልዳኑም ። ለመዳን ከእርሱ ጋር መሞትና መነሣት ያስፈልጋልና ። ገደልነው ብለው ደስ ይላቸዋል ፣ ወዲያው እነሣለሁ ብሏል እያሉ መረበሽ እንቅልፍ ይነሣቸዋል ። የማያስተኛ ሟች ፣ የማይያዝ የትንሣኤ ጌታ ነው ። መቅደስ እያከበሩ መቅደስ ሰውነቱን አፈረሱ ፣ የሦስት ቀን ድልን ፈቀደላቸው ። ያዘኑ ወዳጆቹ ይደሰቱ ዘንድ ፣ የተደሰቱ ጠላቶቹ ያፍሩ ዘንድ ክርስቶስ ተነሣ ። የእስራኤልን መነሣት ተስፋ እያደረጉ የሚያነሣትን ገደሉት ። እንደ አቅማቸው ከእንቅልፍ እየተነሡ እንደ አቅሙ ከሞት እንደሚነሣ ዘነጉ ። የኃጢአት አውራው ዝንጋዔ ነው ። አይቶ እንዳላየ መሆን ነውና ።

ወትሮም እነርሱ በመቅደስ ሆነው እርሱ በመንደር ሲያስተምር አላፈሩም ። ከመቅደስ ሳይሆን ከከተማው አውጥተው ሰቀሉት ። ዛሬም ክርስቶስ በደጅ ነው ፣ መቅደሱ በሰቃዮች ሲሞላ ክርስቶስ በደጅ ይኖራል ። በመቅደስ በአሮናዊ ሥልጣን ፣ በደጅ በሮማውያን ሥልጣን ከምድረ ገጽ ይጥፋ ብለው ተነሡ ። ከመቅደስ ቢያባርሩት መቅደሱ ፈረሰ ፣ ከከተማ ቢያባርሩት ኢየሩሳሌም ተደመሰሰች ። ከዓለም ቢያባርሩት ዓለም ምጥ ያዘው ። እውቀቱ ወደ አለማወቅ ተለወጠ ። የመግደል እውቀት የማዳን እውቀት መሆን አቃተው ። እርሱ ግን ሰማይ ቤቱ ፣ ምድር ግዛቱ ፣ ምእመን ርስቱ ነው ።

ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እንደ ቆየና ሕያው እንደ ነበረ ክርስቶስም በሙታን መንደር ሙታንን እየፈለገ ሕያው ነበር ። ዮናስን የጣሉ እንደ ሞተ ያውቃሉ ፣ የጣሉት ሳያዩት ንስሐ የገቡ አዩት ። ክርስቶስም ያረዱት ሳይበሉት ፣ ኃጢአተኛ ነን ያሉ ጠገቡት ። ዮናስ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ነነዌ በንስሐ ድምፅ መጣ ፣ ጌታም ወደ ነነዌ ዓለም “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያሉ ወደሚሄዱት ደቀ መዛሙርት መጣ ። ከትንሣኤ በኋላ ቂምና መተዛዘብ የለም ፣ ለካደው ጴጥሮስ ቅድሚያ ተገለጠ ፣ አፍሮ እንዳይጠፋበት ። ለማናፍረው እያፈረ ስንት ዘመን አባበለን ። የሸሹትን ደቀ መዛሙርት ሳይታዘብ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ ። እርሱ “የሰውን ድካም ያውቀዋልና” ። ሞት ፍቅሩን አልገደለበትም ። እኛ ጭረት ፣ ትንሽ ቍስል ፍቅራችንን ገድላብን ይኸው ተስፋ ቢስነት ያሰቃየናል ። ለይቅርታ ካልተነሣን ሳንነሣ እንቅር ። መነሣት ብቻ በቂ አይደለም ፣ ለምንድነው የተነሣነው ማለት ያስፈልጋል ። ጌታ ለይቅርታ ፣ ብዙዎች ለበቀል ተነሡ ።

ክርስቶስ ጊዜ ሰጥቶት አልተነሣም ፣ በራሱ ኃይል ተነሣ ። በእግዚአብሔር መንግሥት ጊዜ የሚባል ቸር የለም ፣ ሁሉን የሚያደላድል የመለኮት እጅ ነው ። ሰዎች ማደሪያ ከልክለውት በደብረ ዘይት ጫካ ያድር የነበረው ምድር ግን ለሦስት ቀን ሸሸገችው ። ገጣሚው፡-

“ሞት ይቅር ይላሉ ፣
ሞት ቢቀር አልወድም ፤
አፈሩም ድንጋዩም ከሰው ፊት አይከብድም” ያለው ለዚህ ነው ።

እርሱ በሥጋ ሞተ ፣ በመለኮቱ ግን ሕያው ነው ። ሰንበትን በመቃብር አከበረ ። የሕይወት ሰንበታችን ነውና ልናከብረው እንደሚገባን አስተማረን ። መነሣቱን አይሁድም ይጠብቃሉ ጦር ይዘው ፣ ቅድስት እናቱም ትጠብቃለች ምስጋና ይዛ ። አጠባበቃችን እንጂ መጠበቃችን ዋጋ አይሰጠውም ። እግዚአብሔር ወራጁን ትቶ ምንጩን ያያል ። ሰው ግብዝ ነውና ወራጁን እያየ ያብዳል ። የእግዚአብሔር ልጅን መቃብር ከሦስት ቀን በላይ አልቻለውም ። በፈቃዱ ሞተ ፣ ተቀበረ ። ጠባቂዎቹ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብቻ እንዲጠብቁ ታዘዙ ። በአይሁድ ልማድ ሦስተኛው ቀን ሞት እርግጥ የሚሆንበት ነው ። ጌታችን ግን ሞት እርግጥ በሚሆንበት ቀን ትንሣኤውን እርግጥ አደረገ ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት አፍረው ወደ ገሊላ ይመለሱ ነበር ። እርሱ ባይነሣ ኑሮ ሐዋርያት ተነሣ በማለታቸው ወንጀለኛ ተብለው መከሰስ ሳይሆን አበዱ ተብለው መታከም ይኖርባቸው ነበር ። የሚከሰስም ጤነኛ ነውና ።

የምታምኑት እስኪ እልል በሉለት ። ምንድነው ዝምታው ? ስለ ሞት እያወራችሁ ስለ ሕያው ጌታ ምነው ዝም አላችሁ ? ጌታ ሆይ ተነሥተሃል አምናለሁ ። አይሁድ በጥፊ የመቱትን ጉንጭህን እስመው ዘንድ ወዴት አገኘዋለሁ ? ከበው ርኩስ ምራቃቸውን የተፉብህ ከብቦ የሚያስጨንቀንን በትንሣኤህ ጉልበት በትነው ።

ጸሎት

ቅድስት ሞትህን ቡርክት ትንሣኤህን አምናለሁ ፣ እባክህ ጽድቄን ይቅር በለው ። ፎቶ የሚያነሣ ይዤ እመጸውታለሁ ፣ መልክ ቀራጭ አቁሜ ስግደት እሰግዳለሁ ። ለዝና ደግ ነኝ ፣ ለወሬ ሰጪ ነኝ ። ዛሬ ኃጢአቴን ሳይሆን ጽድቄን ይቅር በለው ። ክፉ መስሎ የሚከፋውን ሁሉ ይጠላዋል ፣ ደግ መስሎ መክፋትን አንተ ትጠላዋለህ ። እባክህን ግብዝነት ያሸተተውን ይህን ሁሉ ሬሣ አንሣው ። አደራህን ብቻህን እንዳትነሣ የሞተ ወገንህን ይዘህ ተነሣ ። ታርደህ በጽዮን ለቆምከው በግ ምስጋና አቀርባለሁ ። በማይፈጸም ዘመን ለዘላለሙ አሜን::
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
💖        🍒        💖

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡


✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-
💛
ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
💛
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
💛
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡:

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
🎼ዘፈን ለምን ይከለከላል ⁉️

➭ ዘፋኝነት የተከለከለበትን ምክንያት በግድ ማወቅ አለብኝ ለምን ትላለህ?

➨ ምክንያቱን ማወቅህ አያፀድቅህም አለማወቅህም አያስኮንንህም፡፡ ነገር ግን ዘፋኝ ብትሆን ትጠየቅበታለህ፡፡ ባትዘፍን ደግሞ ታዛዥ ተብለህ በእግዚአብሔር ዘንድ ትመሰገነበታለህ፡፡ ስለዚህ የሚመለከትህን ለምን አታደርግም?

➣ . . . ዘፈን ለምን እንደተከለከለ መዘርዘሩ ምስጢሩን እንደሚያጠበው መገለጹ ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ይሕ እንዳለ ሆኖ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት የዘፈንን ጎጂ ገጽታ ማሳየት ይገባል፡፡

ሀ. ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡

➣ ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13፥21 አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን ተረዳ፡፡
ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል ‹‹ . . . እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› የዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለውን አጋንንትን ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጎራ መሰለፋቸው ነው፡፡

➾ ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቅ አይንህ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለህ መርምር፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛውም እንደሆነ ማስተዋል ሞክር፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተህ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ባለውቃቤዎችስ ሲደነፉ ተመልክተህ አታውቅምን? የባለ ውቃቤዎች ድንፋታ ደግሞ ቁርጥ እዋኽ፣ እዋኽ እየተባለ የሚዘፈነውን ባህላዊ ዘፈን ይመስላል፡፡ ፍከራው ቀረርቶውና በየብሄረሰብ የምትመለከተውን ዘፈንና ጭፈራ ብትመረምር ከዚህ የቀረበ መመሳሰል አታጣበትም፡፡ ቅዱስ ሐዊ እንደተናገረው ‹‹ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ›› ነውና፡፡

➨ አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ የዘፈንና የጭፈራ ዓይነት ሁሉ ምንጮች ናቸውና፡፡ ከዚህ በኋላ የእኔ ስጋት ዘፋኞች እና ጨፋሪዎች አዳዲስ የዘፈን እና ጭፈራ መንገድ ለመኮረጅ ሲሉ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ፍለጋ በየፀበል ስፍራው መዞር እንዳይጀምሩ ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች የሚሹት ገንዘብንና ዝናን ብቻ እንጂ ሃይማኖት እና ምግባርን አይደለምና፡፡

➲ ለ. ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡

⚠️ ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዘመናችን የሐጢያት ተግባራት በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ አንበሳ ምግቡ ሥጋ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንበሳ ሳር እንዲበላ ማድረግ እንደማያቻል ሁሉ ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡

➼ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ስለ ተግባረ እድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ህግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሰሩ ይገባል፡፡
እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጨዋታ፣ በእግር አንደማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር፡፡ ይሕ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደስራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል፡፡

➲ ሐ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሀጥያት ነው፡፡

➣ ገላ 5፡21 ስለዚህ ዘፈን መዝፈን በመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ይከለከላል፡፡ ክርስትያኖች በመንፈሳዊ ሀሳብ መመላለስ እንጂ እንደ ዘፈን ያለውን ስጋዊ ስራ መስራት የለባቸውም፡፡ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ተብሏልና፡፡ ገላ 5:21

➲ መ. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡

➣ ሐመር መጽሔት ይህን ሲያስረዳ ‹‹ዛሬ የአለም ሕዝብ የሚያዘወትረውን ዘፈን ሐዋርያት በትምህርታቸው ደጋግመውና አጥብቀው ተቃውመውታል ይላል

በእርግጥም ሐዋርያት በዲድስቅልያ ‹‹አትኩኑ ዘፋንያነ››፤ ‹‹ዘፋኝ አትሁኑ›› ብለዋል፡፡ ዲድስ አን7
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ብሏል፡፡ ሮሜ 13፡13 ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ " በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡" ይለናል 1ኛ ጴጥ 4፡3

➣ በላይኛው አንቀጽ በሰፈረው የሮም ክታቡ ቅዱስ ጳውሎስ ዘፋኝነትን ከዝሙትና ከስካር ጋር አስተካክሎ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ጴጥ 2፡13-15

➭ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑትንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ መመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ2፡13-15
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ ‹‹ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል፡፡›› ይለናል፡፡ መጽ ሐዊ አን50

➨ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ !"ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ" በማለት ይማፀናል (ተግ ዘዮሐ አፈ 28)

⚠️ ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ፀንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን፡፡ መጽ ሐዊ አን 12 ይህ የሐዊ ቃል ሐዋርያው "የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› ማለት በምን ይለያያሉለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ማግባትን ለምትሹ !

"ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው ? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን ? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው ፤ እንዲህ ያለውን ፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው ፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት"  ፩ኛ ቆሮ.፯፥፪

"ከድህነት ይወጣ ትወጣ ዘንድ " ነው የሚለውን? ወይስ " ሀብት ለማግኘት ሲባል " ነው የሚለውን ? አይደለም ! ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው ፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ ልጆቼ ! እማልዳችኋለሁ ፦ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው ፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

አባቶች ሆይ ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት ፦ ሀብትን አላየም ፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም ፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም ፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

እናቶች ሆይ ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡ እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ ! ይስሐቅን ምሰሉት ፦ ዘፈንን ፣ ዳንኪራን ፣ ሳቅና ስላቅን ፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን ፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ ፣ ዝሙት ፣ ቅናት ፣ ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም ፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር ፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን ፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም ፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት ፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
🕊 እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🕊

የሰባት ዓመት ተጋድሎ በጥቂቱ !

1, በብረት አልጋ ፣ በምስማር ጫማ ስቃይ ደርሶበት ቅዱስ ሚካኤል ደርሶለት ከአሰቃዮቹ ነጥሎ ወስዶ አዳነው።

2, ሆዱን ዘርግፈው ፣ አንሉን አፍርሰው ፣ አጥንቱን አቃጥለው ፣ ሥጋው ተበጣጥሶ ከመሬት ተበትኖ ጌታችን ተገልጦ ፈወሰው።

3, እጆቹን አስረው ገዳይ መርዝ አጠጡት ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን መርዙ ላይ በአገጩ አማትቦ ስለነበር ምንም አልሆነም።

4, የብረት ጥርስ ያለው ወፍጮ ውስጥ ከተው በጣጠሱት አርቀውም ቀበሩት ነገር ግን ሳይቆይ ከሞት ተነሳ።

5, በመጋዝ ሁለት ቦታ ከአናቱ ቁልቁል ሰውነቱን ከፍለውት አርባ ክንድ ቆፍረው ቀበሩት ፣ በላዩም ዘጠኝ ክንድ አፈር ቆልለውበት ዘወር ሲሉ ከተቀበረበት ብድግ ብሎ ተነሳ።

6, በአንዲት ደሀ መበለት ሴት ቤት ውስጥ ከቋሚ ምሰሶ ጋር አሰሩት በዚህም ጊዜ ደረቁ እንጨት ለመለመ ፣ ቅጠልም አውጥቶ ዋርካ ሆነና ለቤቱ ጥላ ሆኖ አገለገለ።

7, ሥጋውን ፈጭተው ፣ አቃጥለው አመዱን በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ በተኑት ሲመለሱም ድምጽ ሰምተው ዞር ሲሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ እነሱ እየተጣራ ሲመጣ አዩት። እርሱንም ከማሰቃየትና ከመግደል ተሸነፍን ሲሉ እጅ ሰጡ ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ።

የሰማዕቱ ምልጃ አይለየን !

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
የእውነተኛ ወዳጅ ምክር !

“ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።” [መጽሐፈ ምሳሌ 1÷5]
"እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መሆኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡" በእርግጥ ሁላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሰራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ሆነን ንስሐ ሳንገባም ለማለፍ እንጥራለን ፣ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ደግሞ ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን ታዲያ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

እስኪ ራስህን መርምር ! ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ፣ ጓደኛህ ኃጢአት ሰርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ትክክል እንዳልሆነ እንዲያውቅ ታደርግ ይሆን? ምናልባት እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ጓደኛህ አለ አግባብ ሊቈጣህ ፣ ምን አገባህም ሊልህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትሆነው?

አየህ ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊሆን የሚገባውን መምረጥ አለበት። ስንቆጣው ቁጣችንን ታግሶ የሚጸና ብቻ ሳይሆን እኛም ስናጠፋ የሚያርመን ሊሆን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልሆነ ጓደኝነታችን ጥቅም አይኖረውም ፤ ጓደኞዬ ነው ማለትም ከንቱ ነው። ነገር ግን ልናውቀው የሚገባን አንድ ነገር አለ ! ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው ፣ በሰው ፊት ልናዋርደው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ሁልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መሆን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ሁልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሳ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልሆነ እንዲያውቅ ማድረግም አለብን ምክንያቱም እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? +

ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት::

"ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39

ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ::

"ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ::
ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20)

እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም?
ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?  "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥  በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ  "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር::

የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን?  ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን?

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ::

"ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም::

ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦  ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13)

ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ::

ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ:: 

አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር::

የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
አስር ጊዜ ተወለጅ


        በመልካም ምግባራቸው የታወቁ በአሸናፊነታቸው የተመሰከረላቸው ሰዎች ሲገኙ በተለምዶ 'እንደርሱ ዓይነቱስ አሥርም ቢወለድ አይቆጭም' ይባላል። ለመልካምነታችው መገለጫ ምቹ ጊዜና ቦታ የሚፈልጉ ሰዎች መልካም ተብለው አስር ጊዜ በተወለዱ የሚስብል ከሆነ ለመልካምነቷ ምንም እንከን የማይወጣላት ነውር ነቀፋ የሌለባት መልካምነት መገለጫዋ ከመሆን አልፎ መጠሪያዋ የሆነ መልካሚቱ ተብላ የምትጠራዋ እመቤታችንማ ምንያህል ጊዜ  እንድትወለድ እንመኝ ይሆን? ለአሸናፊነታቸው የጊዜ ገደብ ያለባቸው አሸናፊነታቸውም በድኩማን ላይ ብቻ የሆኑትን አስር ጊዜ በተወለዱ ካልን ለአሸናፊነቷ ወደር የሌላት አሸፊውን እግዚአብሔርን እንኳን በንጽህናዋና በቅድስናዋ አሸንፋ በማኀጸኗ እንዲያድር  ያደረገች ድንግል ማርያምን ስንት ጊዜ ተወለጅ እንል ይሆን? በእውነት አንቺ አንድ ጊዜ ተወልደሽ ዘመንን መለወጥ  መርገምን ማስወገድ ነውርን ማራቅ ነቀፌታን ማስወገድ ብርሃንን መዝራት ከቻልሽ አስር ጊዜ ብትወለጂልን ኖሮማ ምን ይሆን ነበር?      
      
         ድንግል ሆይ ልጅሽ ወዳጅሽ ጌታ በጥር 21 እልፍ አእላፍት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣው ባለሽ ጊዜ "ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኀጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን?" አልሽው፤ ጌታም በሲኦል ያሉ ነፍሳትን አሳይቶሽ "እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል።" ሲልሽ አንቺም ፍቅርን በተሞላ ቃል "ልጄ ሆይ ለእነዚህማ አይደለም አንዴ ሰባት ጊዜ እሞትላቸዋለሁ።" አልሽው። መወለድሽ በኃጢአት ቁር ተቆራምደን በበደል ጨለማ ተደናበርን ለነበር ለእኛ የጽድቅ ጸሐይ የመውጫ ሠማያችን የተዘረጋበት ነውና አስር ጊዜ ተወለጅልን። ልደትሽ ማለት በመካከላችሁ አድር ዘንድ መቅደሴን ስሩልኝ ያለው አምላክ በራሱ እጅ የሠራሽ መቅደሱ የተገለጥሽበት ዕለት ስንናፍቅሽ ኖረን ያረፍንብሽ እረፍታችን ከአምላክ የታረቅንብሽ የእርቅ ዘመናችን መድኀኒቱ የተያዘብሽ ሙዳያችን ከርሐባችን የምንጠግብሽ መሶባችን ለጥም ጊዜ የንጹህ ውሃ መገኛ ምንጫችን አንቺ የተገለጥሽበት ነው። የሠውነት ክብራችን የተመለሰው በአንቺው መወለድ ነውና የባሕሪያችን መመኪያ ሆይ አስር ጊዜ ተወለጅልን።

         ያ ባህታዊ ድንግል ሆይ ከበዓላቶችሽ ሁሉ የቱን ትወጃለሽ ሲልሽ በዓላቶችሽን ሁሉ እንደምትወጅ ከሁሉም  ግን የልደትሽን በዓል አብልጠሽ እንደምትወጂ በተናገርሽ ጊዜ ምክንያቱን ስትናገሪ ከጠባብ ወደ ሰፊ ከጨለማ ወደ ብርሃን የመጣሁበት ነውና በዚሁም ላይ እናትና አባቴ ልጅ አጥተው ከመሥዋዕት ተከልክለው ሲኖሩ ነቀፌታቸው የተወገደበት ነውና ስትይ ተናግረሻል። በእውነት ግን ድንግል ሆይ በአንቺ ልደት ከጠባቡ ወደሰፊው ከጨለማ ወደ ብርሃን የተሸጋገርነው እኛው ነንና ስለእኛ ስትይ አስር ጊዜ ተወለጅ። በአንቺ መወለድ ለጊዜው መካን ተብለው ተንቀው ተገፍተው ይኖሩ የነበሩት ቅዱሳን ወላጆችሽ  ሐናና ኢያቄም ነቀፌታቸው ይወገድ እንጂ ፍጻሜው ግን በልደትሽ የተወገደው የእኛው ነውርና ነቀፌታ ነውና ከፍቅራችን ጽናት የተነሳ አስር ጊዜ ተወለጅ ብለን ብንናገርም አንቺ አንደ ጽኑህ መድሀኒት  ልደትሽም ፍፁም ነውና አንድ ጊዜ መወለድሽ ለዓለም መዳን ምክንያት በቂ ሆኖልና አስር ጊዜ መወለድ አያሻሽም።

       ድንግል ሆይ በእኛ ልብ ግን አስር ጊዜ ብቻ ያይደለ ዘወትር ተወለጅ፤ በየጊዜውና በየሰዓቱ ሁሉ ፍቅርሽ በልቦናችን ይወለድ። በእኛ ዘንድ ያለው ነውርና ነቀፌታ ይወገድልን ዘንድ ጨለማ ከተባለ ኃጢአት ብርሃን ወደተባለ ጽድቅ እንሻገር ዘንድ በእኛ ዘንድ የተከማቸው የኃጢአት ክምር ይቃጠልና ይጠፋ ዘንድ በበደል ቁር መቆራመዳችን ይበቃ ዘንድ ዘወትር የፍቅርሽ እሳት በልባችን ውስጥ ይወለድ። ድንግል ሆይ ፍቅርሽ በእኛ ውስጥ መወለድ ብቻ ያይደለ ዘወትር በጥቂቱ በልባችን ይደግ ይስፋ ፍቅርሽ እረፍት ያሳጣን ዘወትርም አንቺን ለማመስገን ያንቃን ለውዳሴሽም ያትጋን ዘወትርም የመወለድሽን ዜና እያሰብን እንደሰት  የሰውነት ክብራችን የተመለሰው ዳግመኛም ወደ ገነት የገባንብሽ በራችን  አንቺው ነሽና ሰው እንሆን ዘንድ ዘወትር አንቺን ማመስገንን ከልባችንና ከአፋችን አትነጥይብን።

  ድንግል ሆይ ለድኀነታችን መሠረት ለሆነው ልደትሽ ምስጋናን እናቀርባለን።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
መኳንንት በሮቹን ክፈቱ 

             ከጌታችን ቅዱሳት ስዕላት መካከል እጅግ ሳያቸው ከሚያስደንቁኝና  ትህትናውን  ቸርነቱን  ታማኝነቱን እረኛነቱን ይልቁኑ ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት ፍቅሩን አጉልተው ከሚያሳዩኝ መካከል  የሠማይና የምድር ንጉስ ሆኖ ሳለ የእኛን የባርያዎቹን ያውም ታማኝ ያልሆነውን አመጸኞቹን ባርያዎች ፍለጋ ወደንና ፈቅደን የዘጋነውን ደጅ ሲያንኳኳ የሚያሳየው ምስለ ስዕል ሁሌም ይደንቀኛል።

           በዮሐንስ ራዕይ እንዲህ የሚል ቃል አለ "እንሆ፥በደጅ ቆሜ አንኳኳለኹ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ወደ ርሱ እገባለኹ።"/ራዕ3፥20/ ታዲያ  ስታንኳኳ ኑረህ ያልተከፈቱ እንደኔ ልብ ያሉትንም ዛሬም እያንኳኳህ ነው? እየሰማሁህ የዘጋሁብህን የኔን ደጅ ስታንኳኳ አትዝልም? እንደዛች በመኃልየ መኃልይ ምዕራፍ 5 ላይ እንዳለችው ሙሽራ የምታንኳኳውን የልቤን ደጅ ላለመክፈት "ቀሚሴን አወለቅኹ እንዴት እለብሰዋለኹ፧እግሬን ታጠብኹ እንዴት አሳድፈዋለኹ።" ዓይነት የምደረድረው ውሃ የማያነሳ ምክንያት አላሰለቸህም ዛሬም በደጄ ቆመህ እያንኳኳህ ነው?ምኔስ ነው በደጄ እንድትቆም ያደረገህ ደጄ እንኳን ውብና የሚስብ አይደለም አጥሬ ድኩም የኮሽም አጥር ነው ምኔስ ሳበህና እስከዛሬ ከበራፌ አቆመህ? የቤቴንም ውስጡን ታቀዋለህ ማረፊያ እንኳን የሌለው በቆሻሻ የተሞላ ነው። ታዲያ ስለምን ያለመሰልቸት እስከዛሬ በደጄ ቆምክ? የማንኳኳትህን ድምጽ ከመልመዴ የተነሳ የተለመደና ትኩረቴን የማይስበው ድምጽ ሆኖ ማንኳኳትህን እንኳን ዘንግቼዋለሁ።አንተ ግን መረሳትህ እንኳን ሳያስጨንቅህ በደጄ ቆመሀል። ዛሬ ግን በዚህ ምስልህ መስኮትነት አሻግሬ ወደራሴ ደጅ ብመለከት ለካ እስከ ዛሬ ደጄን እያንኳኳህ ነው?

            እንዲህ ያለህ ንጉስ ከየት ይገኛል? ያለ መሰልቸት የአመጸኛ ባርያውን ደጅ በፍቅር የሚያንኳኳ ንጉስ እንደምን ያለ ነው? ለዘመናት ሲያንኳኳ መልስ ባለማግኘቱ ያልተሰላቸ ይህን ንጉስ ፍቅሩ እንደምን ይደንቅ? እናንተ መኳንንቶች በሩን ክፈቱ። በራሴ ላይ ያነገስኳችሁ መኳንንት የዓለም ፍቅር ከንቱ ምኞት የኃጢአቴና የበደሌ ክምር የሀሰት መኳንንት ሁላችሁ የያዛችሁትን  የልቤን ደጅ ልቀቁትና  በደጅ ለዘመናት ሳይሰለች ሲያንኳኳ ለነበረው "የክብር ንጉስ በሩን ክፈቱ የክብርም ንጉስ ይግባ። ይህ የክቡር ንጉስ ማን ነው? እርሱም እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል እግዚአብሔር ነው።"/መዝ 24፥8/ብርቱ ሲሆን የእኔን የአቅመቢሱን ቤት ደጅ ይጠናል ኃያል ሲሆን እኔን ደካማውን ይማጸናል። ንጉስ ሲሆን ከእኔ ከባርያው ደጅ ለዘመናት ያለመሰልቸት ቁሞ ያንኳኳል።

      ይህን ያህል ፍቅር እንደምን ያለ ነው? ይህን ያህል ትህትናስ ምን ድንቅ ነው? ፍቅር ንጉሱን ከዙፋኑ አወረደህ ከእኔ ባሪያህ ደጅም አቆመህ። የወጋህን እሾክ በፍቅር የምትንከባከብ የሰቀለህን ችንካር በፍቅር የምትጠራ አንተ ቸርነትህ ብዙ ነው። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ነፍሴ አንተን ተጠምታለችና በበራፌ ቀዳዳ በኩል እጅህን አሾልከህ አውለብልብልኝ የከፈልክልኝን ፍቅርህና ውለታህንም አስታውሼ አንጀቴ ስለ አንተ ይታወክ ደጄንም ለመክፈት ያብቃኝ። የቤቴንም ጨለማ በብርሃንህ አስወግደው። ጌታዬና ንጉሴ ሆይ አንተ ብርቱና ኃያል አይደልህ? ያለ አንተም የልቤን የሚያውቅ የለምና፤ ስንፍናዬን ስለምታውቅ በከሃሊነትህና በኃይልህ ከፍተህ ግባ።
  እናንተ መኳንንቶች በሩን ክፈቱ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​​​🔻 አንድ ምዕመን ንስሐ ከገባ በኋላ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል ማድረግ አለበት።

1, የተቀበለውን ቀኖና በትክክል መፈጸም

ቀኖና የግሪክ ቃል ሲሆን መለኪያ ማለት ነው። ካህኑ ለበደለው ምዕመን እንደ ሃይማኖቱ ጽናት ፣ እንደ አእምሮው ስፋት ፤ የሠራውን በደል መጥኖ ቀኖና ከሰጠው በኋላ እንደታዘዘው መፈጸም አለበት። የነነዌ ሰዎች ፣ ት. ዮና 3 ፥1 ። ንጉሡ ህዝቅያስ ፣ ኢሳ 38 ፥ 1 ። ቅዱስ ጴጥሮስ ሉቃ 22 ፥ 54 ። እና ሌሎችም ይቅርታን ያገኙት ፤ በበደላቸው ተጸጽተው በማልቀሳቸውና ንስሃ በመግባታቸው ነው።

በንስሐ ወቅት ፡መሬት ላይ መተኛት ምግብ መቀነስ ፣ ከዓለማዊ ነገሮችና ለመንፈሳዊ ሕይወት ከማይመቹ ጓደኞች መራቅ ያስፈልጋል። በንስሐ ጊዜ እንዳናደርግ ከታዘዝነው ነገር ራሳችንን በመግዛት መቆጠብ አለብን ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ወደ ድኅነት ከጠራን በኋላ እንደገና ተመልሰን ወደተውነው ድካማችን መመለስ የለብንም። የጊዜውን ሳይሆን የመጨረሻውን ማሰብ አለብን። 2 ጢሞ 4 ፥10 ። መዝ 6፥6 ።

2, በደላችን በንስሐ እንደሚሰረይልን ማመን

ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው በደላችንን ለመደምሰስ ስለሆነ ከበደላችን ሊያነጻን የታመነ አምላክ ነው። ከሠራነው ብዙ ኃጢአት አንጻር የሚሰጠን ቀኖና ትንሽ መስሎ ቢታየንም። ማሰብ ያለብን የራሳችንን በደል ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቸርነት ነው።

ከእኛ በደል የእግዚአብሔር የቸርነት ሥራው እጅግ ይበልጣልና የታዘዝነውን ፈጽመን የቀረውን እንደቸርነትህ ማለት ይገባል። “የታዘዛችሁትን ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ” ተብለናልና ። ሉቃ 17 ፥ 10።

3, በሥጋውና በደሙ መታተም (መቁረብ)

አንድ የተራበ ሰው እጁን ስለታጠበ ብቻ አይጠግብም። የግድ ምግብ መብላት አለበት። ንስሐ ማለት መታጠብ ፣ ከእድፍ (ከኃጢአት) መንጻት ማለት ሲሆን ፤ ድኅነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት የሚሰጠውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል ነው። ዮሐ 6፥33።

ብዙዎቹ መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ (ለሽማግሌ ብቻ) አድርገው ስለሚቆጥሩት ለመቀበል ሲዘጋጁ አይታዩም። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል ። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና ።

4, ሁሌም ለንስሐ መዘጋጀት

ንስሐ ከገባንና ከቆርብን በኋላ እንደገና በኃጢአት ልንወድቅ እንችላለን። አምለካችን “ለምን ንስሐ አልገባህም እንጅ ለምን ኃጢአት ሠራህ? አይልምና” ሁለተኛ ስንበድል ሀፍረት ሳይሰማንና ከኃጢአት መላቀቅ ካልቻልሁ በየጊዜው የንስሐ አባቴን ከማስቸግር አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል በማለት ፡ ሁሉንም እርግፍ አድርገን እንድተወው ፡ ክፉ ሀሳብ በአምሯችን ሊፈታተነን ይችላል።

ነገር ግን ከንስሐ በኋላ እንደ መላእክት በቅድስና ብቻ እንኖራለን ማለት ሳይሆን “ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ፤ ሰባት ጊዜ ይነሳል” ምሳ 24፥ 16 ። እንደተባለ ፡ አምላካችን ብንወድቅ ሊያነሳን ፤ ብንጠፋ ሊፈልገን ፤ ብንርቅ ሊያቀርበን ፤ በኃጢአት ብንረክስ ሊቀድሰን (እንደ ባዘቶ ሊያጠራን) የታመነ አምላክ ስለሆነ ተስፋ ሳንቆርጥ ፤ በኃጢአታችን ሳንደበቅ ፤ ዘወትር ለንስሓ መዘጋጀት አለብን። ኢሳ 1 ፥ 18 ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል::  ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ  ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ:: 

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር። ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ ቀን ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህች ዕለት ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል  የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ከቁስልህ የምትፈወስበት ጊዜ እንደደረሰ ዕወቅ:: ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ከንስሓ በቀር መፍትሔ የለውም:: እንደ ሕዝቅያስ አሁኑኑ ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የግዮን ወንዝ
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
    “ከእግዲህስ. . .  ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ"

       ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ሲመርጥ ስምኦን የተባለ ጴጥሮስን አሳ ለማጥመድ ሌሊቱን ሙሉ ደክሞ አንዳችም ሳያገኝ ከባህሩዳር ከወንድሞቹ ጋር መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር፤ የ55 ዓመቱ አረጋዊ የዮና ልጅ ስምኦን በተስፋ መቁረጥ ተቀምጦ ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ ቀርቦ በታንኳው ካስተማረ በኋላ ጀልባውን ፈቀቅ አንዲያደርግ የዮና ልጅ ስምኦንን ጠየቀው፤ ስምኦንም በትህትና እንደታዘዘው አደረገ ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ለፍቶ አንዳች ያላገኘው አሁን በታዘዘው መሰረት መረቡን ሲጥል ለመጎተትና ስበው ለማውጣት እስኪቸገሩ ድረስ መረቦቻቸው ለመቁጠር በሚያዳግቱ አሳዎች ብዛት ተሞላ። የዮና ልጅ ስምኦንም እጅግ ደነገጠ ይህ ሰው ዘመኔን ሁሉ የማውቀውን አሳ ማጥመድ ሌሊቱን ሁሉ ስደክም ባድርም አንዳች ሳላገኝ የዕድሜዬን አጋማሽ የሚሆን እርሱ አንዳፍታ መጥቶ በዚህ ሰፊ ባህር ላይ አሳ የት እንደሚገኝ ካወቀ በእኔ ልብ ያለው ኃጢአት አይሰወረውም አለ።

        ስምኦን ጴጥሮስም እንዲህ አለው "ጌታ ሆይ ከእኔ ራቅ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ።“ ይህን ትሁት ተነሳሒ ተመልከቱት በፍጹም ጸጸት ሆኖ ኃጢአቱን ለሐዲስ ኪዳኑ ሊቀ ካህኑ ይናዘዛል። ካህን ተመልክቶ ንስሐ ሳይገባ እድሉን ማሳለፍ አልፈለገምና ኃጢአተኛነቱን ተናዘዘ። ወደ አገልገሎት ከመሰማራት በፊት ንስሐ ይቅድማልና ኃጥአቱን በካህናት አለቃ በክርስቶስ ፊት አስቀመጠ፤ ጌታም ንስሐውን ተቀብሎ ዘመኑን ሙሉ ሲደክም የኖረበትን አሳ አጥማጅነቱን ይበቃካል ብሎ እንዲህ አለው፦ "ከእንግዲህስ አሳን አታጠምድም ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ" የዮና ልጅ ስምኦንም አሳ በማጥመድ መንከራተት ደክሞታልና እሺ ብሎ ሰው አጥማጅነትን ለመማር ጌታን ተከተለ። ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ያህል ሰው አጥማጅነትን ለመማር ጌታውና መምህሩ ባደረበት እያደረ በዋለበት እየዋለ አንዴም እየወደቀ አንዴም እየተነሳ የትምህርቱ የመጨረሻ ቀን ላይ ደረሱ። በዚህ የመጨረሻ ቀን ታላቅ ፈተና ቢገጥመው መምህሩን ሊቀ ካህኑንና ጌታውን አላውቀውም ብሎ ካደ።

        ሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስም አላቀውም ብሎ አልቀረም የጌታውን የፍቅርና የምህረት ገጽ ተመልክቶ ራሱን በንስሐ ባህር ነክሮ ኃጥአቱን በእንባው አጠባት። ከዚህ ፈተና በኋላ ይህ አላውቅህም ብሎ የካደው ጴጥሮስም የመምህሩና የጌታውን ገጽ ቢናፍቅም አላውቅህም ብሏልና ፈርሃት ግን በልቡ አለ። መምህሩ አስቀድሞ እንደተናገረው ሞቶ ወደ መቃብር ከወረደ በሦስተኛው እለት ሞትን ድል አደርጎ ከተነሳ በኋላ ሁለት ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ በተዘጋ ቤት ገብቶ ተግልጦላቸዋል። ከጌታችን ትንሳኤ በኋላ ሁለት ጊዜ ለሐዋርያቱ ከተገለጠ በኋላ ጴጥሮስና ሌሎች ስድስት ሐዋርያት አሳ ለማጥመድ ወደ ጥብርያዶስ ባህር ሔዱ። ጴጥሮስ ለ3ዓመታት ወደ ተወዉ አሳ ማጥመድ ቢመለስም ከድካም ውጪ አንዳች ሊያገኝ ግን አልተቻለውም። በዚህ ጊዜ ጌታችን ተገለጠላቸውና አንዳች የሚበላ አላችሁን አላቸው። ዮሐንስም ወደ ጴጥሮስ ጆሮ ጠጋ ብሎ ጌታ እኮ ነው አለው። ጴጥሮስም ወደ ባህሩ ዘሎ ገባ።

      ከእግዲህስ አሳን አታጠምድም ሰውን ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ የተባለው ጴጥሮስ ወደ ተከለከለው አሳ አጥማጅነት ተመልሶ ተገኘ። ወዳጄ እንደ ጴጥሮስ ወደ ተውከው የተመለስክበት ነገር የለምን? እንደውሻ ወደ ትፋታችን የተመለስንበት ነገር የለምን? ላንሰራው ምለን የሰራነው ኃጢአት በአበ ነፍሳችን ዳግመኛ እንዳትመለስበት ተብለን የተገሰጽንበት ግን አሁንም እዛው የተገኘንበት የለምን? ከእንግዲህስ ወደ በደል ገደል ወደኃጢአት ጫካ አትውረድ ወደ ጽድቅ ማማ ወደብርሃንም ተራራ ከፍ በል እንጂ ተብለህ ተመልሰህ ግን ወርደህ የተገኘህበት የለምን? አለሁ እንጂ ግን ምን ላድርግ እንዴትስ ልውጣ ካልክ ጴጥሮስ ራሱን ወደ ባህር እንደወረወረ ራስህን በንስሐ ባህር ላይ ጣል። ከዚያማ ጌታ እንዲህ ይልሃል ልጄ ሆይ ትወደኛልህን? መልስ ምን ይሆን? አዎ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ! ብለህ ከመለስክ ጌታህ እንዲህ ይልሃል በጎቼን ጠብቅ። የፍቅር ብዛት የኃጢአትን ሸክም ያቀላልና።


       ከእግዲህ አሳን አታጥምድ አንተ ለክርስቶስ ሰውን ስታጠምድ እርሱ ለአንተና በዙሪያህ ላሉ ሁሉ የሚበቃ አሳን እርሱ ይሰጥሃልና።
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
እንደ በሽተኛ ሁን

መልካም ክርስቲያን የሚባለው እንደ በሽተኛ ሰው ሆኖ የሚኖር ነው። ምክንያቱም በሽተኛ ያገኘውን ፣ ያቀረቡለትን ሁሉ አይመገብም። ክርስቲያንም ያየው ነገር ሁሉ ሊያምረውና ሊያጓጓው አይገባም። ምግብም ቢሆን ተገኘ ብሎም ማግበስበስ የለበትም። ምግብ ፈተና ያመጣበታል ሕዋሳቱን ያንቀሳቅስበታል ፣ ሥጋዊ ምኞቱን ያነሳሳበታልና በመጠኑ ሊኖር ይገባል። በመንገድ ሲጓዝም ቢሆን አስተውሎ ፣ ረጋ ብሎ ነው እንጅ አይዋከብም።

በሽተኛ ብዙ አያወራም። ክርስቲያንም ብዙ ማውራት መለፍለፍ የለበትም። በሽተኛ ድምፁ ከፍ ያለ ነገር ሁሉ ስለሚረብሸው ይጸየፋል። በሽተኛ አይበሳጭም ትእግስተኛ ነው ጉልበትም ቢሆን አይጠቀምም ይልቁን ጉልበቴ እግዚአብሔር ነው ይላል። ማንም ቢናገረው ዝም ብሎ ያሳልፋል። ክርስቲያንም እንደዚህ በሽተኛ ሊሆን ይገባዋል።

ምናልባት በሽተኛው ስላልቻለ ሊሆን ይችላል ዝም የሚለው ክርስቲያን ግን ጉልበት እያለው እየቻለ እንኳ እንደ ደካማ ሊሆን ይገባዋል። ክፉ ሲናገሩት መመለስ እንደማይችል ሰው መሆን አለበት። ስለዚህ መልካም ክርስቲያን ለመሆን ከፈለግን እንደ በሽተኛ ሰው እንኑር።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
+ ያደረግሽው ምንድር ነው? +

አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንዲህ አለ :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ::

ከዚያ በኁዋላ ግን እግዚአብሔር ለሔዋን :- ለምን ዛፉን ብላ ብለሽ ሠጠሽው? አላላትም:: "ያደረግሽው ምንድነው" ብቻ አላት::

እርሱ በሰዎች አስተያየት አይፈርድም:: ሌላው ስለ አንተ የሚለውን ትቶ አንተን ለብቻህ ይጠይቅሃል:: የሰዎችን ግምገማ አይሰማም:: እንደ ሃናንያ "ኸረ ጌታ ሆይ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ነበረኮ" ቢሉትም ቸል ብሎ ምርጥ ዕቃው ያደርግሃል:: በድንጋይ ልትወገር ይገባታል ሲሉት ክሱን ትቶ ከሳሾቹን ሊከስስ መሬት ላይ ይጽፋል::
ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጻፉ ጣቶቹ ዘማዊትዋን ሴት ነጻ ሊያወጣ አፈር ይጭራል::

ሰው ጨካኝ ፈራጅ እንደሆነ ያውቃልና በአዳም አስተያየት ሔዋን ላይ አይፈርድም:: "ያደረግሽው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃት::

እግዚአብሔር ዛሬም ነፍሳችንን ይጠይቃታል::

ያደረግሽው ምንድር ነው? የአዳምን ክስ ሰምቻለሁ! ሰዎች ስለ አንቺ የሚሉትን አዳምጫለሁ:: አንቺ ግን ንገሪኝ:: ግራውን ሰምቼ አልፈርድም:: ምናልባት ቀኙን ብሰማ ይሻላል የሚል ርኅሩኅ አምላክ ነው::
እኛ የምንፈርድባቸው ሰዎች ሁሉ ቢጠየቁ የሚናገሩት የየራሳቸው የታሪክ ማዕዘን (side of the story) አላቸው::
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሰምቶ አልፈረደም ሔዋንን ጠርቶ ጠየቃት
"ያደረግሽው ምንድር ነው?"
ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
     🔸 @Z_TEWODROS

✍️Comment @Channel_admin09
Forwarded from Ggh
​​የተሠጠህን ቁጠር

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው:: የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም:: ዕባብ ደግሞ የሰይጣን አንደበት ነበረ::

ሰይጣን እንዲህ አላት :- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው። ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ:: ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ።

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቶአት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች።

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል።

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን:: ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ:: ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ:: አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ።

ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​የተሠጠህን ቁጠር

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው:: የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም:: ዕባብ ደግሞ የሰይጣን አንደበት ነበረ::

ሰይጣን እንዲህ አላት :- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው። ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ:: ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ።

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቶአት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች።

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል።

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን:: ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ:: ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ:: አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ።

ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ  አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ረቢ ወዴት ትኖራለህ

ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት::

"ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39

ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ::

"ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ::
ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20)

እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም?
ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?
"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?  "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥  በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ  "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር::

የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23)

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን?  ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን?

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ::

"ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም::

ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦  ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13)

ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ::

ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ:: 

አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር::

የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን::

ረቢ ወዴት ትኖራለህ?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
2025/06/29 16:35:23
Back to Top
HTML Embed Code: