Telegram Web Link
የጥቁር አዝሙድ 32 ዘረፍ ብዙ የጤና ሲሳዮች

1ኛ. ለእርጋታ
አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡
እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡
አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡
የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡

2ኛ. ለሳልና ለአስም
በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡

3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ
አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡

4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡

5ኛ. ለኩላሊ ትጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው)
ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡
ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ ልዩነቱን በጉልህ ያገኙታል፡፡

7ኛ. ከበሽታ ሁሉ ለመጠበቅ
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር አዋሕዶ ያለማቋረጥ ጧት ጧት መውሰድ በሕይወት ዘመንዎ ሙሉ ጤነኛና የሐኪም እርዳታ የማያሻው ሰው ይወጣዎታል፡፡

8ኛ. በጭንና ጭን መካከል የቆዳ መቆጣት ሲያጋጥም
በቅድሚያ አካባቢውን በውኃና በሳሙና በሚገባ ማጠብ፣ ቀጥሎ በሚገባ ማድረቅና በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማታ ቀብቶ ማደርና ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይህንኑ መፈጸም፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ውጤቱን ያዩታል፡፡

9ኛ. ለልብና ለደም ሥሮች ሕመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት ይረዳል፡፡

10ኛ. ለለምጽና ለመሳሰሉት
ተጠቂውን የሰውነት ክፍል በቱፋሕ (ፖም) ወይም አፕል ኮምጣጤ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለ15 ቀናት መቀባት፡፡

11ኛ. ለቁርጥማት ፣ ሮማቲዝምና የጀርባ ሕመም
የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት፡፡

12ኛ. ለራስምታት
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

13ኛ. ለጨጓራና ለአሲድ
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ በሽታው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡

14ኛ. ለራስ ማዞርና ለጆሮ ሕመም
አንድ ጠብታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጆሮ ውስጥ መጨመር በሻይ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት፡፡

15ኛ. ለቆዳ መቀረፍ
በዚህ አይነቱ ሕመም የተጠቃው የአካል ክፍል በጥቁር አዝሙድ ዘይት መቀባት ሕመሙ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መቀጠል፡፡

16ኛ. ለቡግር
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት የሰሊጥ ዘይትና አንድ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት ጨምሮ በአንድነት መለወስ ማታ ማታ ተቀብቶ ማደርና ጠዋት ለብ ባለ ውኃና በሳሙና መታጠብ፡፡

17ኛ. ለስብራት አፋጣኝ ጥገና
የምስርና የሽንኩርት ሾርባ፣ ቅቅል እንቁላል፣ አንድ ትልቅ ማንኪያ የደቀቀ ጥቁር አዝሙድ በአንድነት ቀላቅሎ ቢያንስ አንድ ቀን ወስዶ በቀጣዩ ቀን አርፎ እንደገና በሁለተኛው ቀን መውሰድ፤ ስብራቱ የዘመናዊ ሕክምና በጀሶ ከታሰረ በኋላ በአቅራቢያ ያለውን አካል በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማሸት፤ እስሩ ከተፈታ በኋላ ደግሞ ለብ ባለ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በየቀኑ ማሸት ነው፡፡

18ኛ. ለጠባሳና ለመሳሰሉት
አንድ እፍኝ ጥቁር አዝሙድ በሚገባ ማፍላት የተጎዳውን አካል ማጠብና ለሩብ ሰዓት በተዘጋጀው ፍል ጥቁር አዝሙድ ውስጥ መንከር፡፡ አካሉን ማንቀሳቀስ፡፡ ሳይሸፈን አድካሚ እንቅስቃሴ ሳያደርጉ መቆየት፡፡ ከመኝታ በፊት በየቀኑ ይህን መደጋገም፡፡

19ኛ. ለደም ብዛት
ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ቢወስዱ ምንኛ ጥሩ ነበር፡፡

20ኛ. ለኩላሊት ኢንፌክሽን
የጥቁር አዝሙድ ዱቄት በወይራ ዘይት ለውሶ ሕመም በሚሰማበት ቦታ መለጠፍ፤ በተጨማሪም አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፣ ከዚያ በኋላ ኢንፌክሽኑ ይወገዳል፡፡

21ኛ. ለሐሞት ከረጢት
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ ሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት፡፡
ፊትዎ ቅላት እስኪያሳይና ችግሩ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መፈጸም፡፡ በየዕለቱ በባዶ ሆድ አንድ ሲኒ የወይራ ዘይት መጠጣት አይርሱ፡፡

22ኛ. ለልብና ለደም ዝውውር ችግር
የልብ ሕመምተኛ ሰው በማናቸውም ወቅት እንደ ምግብም፣ እንደመጠጥም እንደአስፈላጊነቱ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

23ኛ. ለትውከት
ጥቁር አዝሙድ ከቅርንፉድ ጋር በደንብ ማፍላት ማጣፈጫዎች ሳይጨምሩ በቀን ሦስት ጊዜ መጠጣት፡፡
ሁለተኛ ዙር መጠጣት አያስፈልግም፡፡

24ኛ. ለቃርና ለመሳሰሉት
የተወሰኑ የጥቁር አዝሙድ ቅባት ጠብታዎች በአንድ ኩባያ ትኩስ ወተት ውስጥ ጨምሮ በማር አጣፍጦ መጠጣት፡፡
የቃር ስሜትዎ እንዳልነበር ሆኖ ይጠፋል፡፡ በእንግሊዘኛ (Lettuce) የተሰኘውን ተክል በብዛት መብላትንም አይዘንጉ፡፡

25ኛ. ለዓይን በሽታ
በጥቁር አዝሙድ ዘይት በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የሰውነት አካል ከመኝታ በፊት ማሸት በማናቸውም ትኩስ መጠጥ ውስጥ አልያም የሥራ ሥር ጭማቂ እንደ ካሮት የመሳሰሉት ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡

26ኛ. የምግብ ፍላጎትን ለማሳደግ
ከምግብ በፊት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ቅመሙን በጥርሶችዎ ማድቀቅ፣ ከዚያም ጥቂት ኮምጣጤ ጠብታዎች የተቀላቀለበት አንድ ስኒ ቀዝቃዛ ውኃ ያወራርዱት፡፡

27ኛ. ለቅማልና ለቅጫም
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት በኮምጣጤ ለውሶ ለመታሻ በሚያገለግል መልኩ ማዘጋጀት ፀጉርን ተላጭቶ መቀባት አሊያም ቆዳው ድረስ ዘልቆ እንዲገባ ማድረግና ለሩብ ሰዓት ለፀሐይ ማጋለጥ፡፡ ከአምስት ሰዓታት በኋላ መታጠብ፡፡
ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንኑ ደጋግሞ መፈጸም፡፡

28ኛ. ለጥርስ፣ለቶንስልና ለጉሮሮ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና ለጉሮሮ ችግር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት፡፡
29ኛ. ከደም ላይ ኮሊስትሮን (ስብን) ለማስወገድ
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት አንድ ማንኪያ የእኸሊ ቅጠል ከአንድ ስኒ ንጹሕ ማር ጋር ለውሶ በባዶ ሆድ መብላት፡፡

30ኛ. ለሽንት መታቀብ ችግር
ከእምብርት በታች ያለውን የሰውነት አካል በጥቁር አዝሙድ ቅባት ከመኝታ በፊት ማሸት፡፡
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በአንድ ኩባያ ውኃ አፍልቶ በማር አጣፍጦ ከመኝታ በፊት በእለቱ መጠጣት፡፡

31ኛ. ፊት ላይ እንደ ቡጉር ክብ ሆኖ ለሚወጣ አተርን ያክል ጠጣር ነገር (WATER)
በሽታ በሽታው የሰፈረበትን አካባቢ በረጅላ (Purslane) ተክል በሚገባ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት 15 ቀናት መቀባት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት መጠጣት፡፡

32ኛ. ለሚያስነጥስ
ከባሕር ዛፍ የተጨመቀ ዘይት 40% ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር ደባልቆ በሁለቱም አፍንጫ በቀን ሦስት አራት ጊዜ ጠብታ ማድረግ ነው።
የቶንሲል ህመምን በቤት ውስጥ ለማከም የሚረዱ ዘዴዎች

ውድ ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ የፌስቡክ ተከታታዮች እንዴት አመሻችሁ? በተደጋጋሚ የቶንሲል ህመም ያጋጥመናል የምንወስደወን መድሀኒት ለማገዝና ቶሎ ለማገገም የሚረዱ ቀላል ዘዴዎችን እነሆ!!!

ቶንሲል በጉሮሮ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሁለት እጢዎች ሲሆኑ፥ የተለያዩ ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ወደ ሰውነታችን ዘልቀው እንዳይገቡ ይከላከላሉ።

የሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅም የሚያሳድጉ ነጭ የደም ህዋሳትንም ያመርታሉ።እነዚህ እጢዎች ሲመረዙ ቶንሲላይተስ የተሰኘ በተለምዶ ቶንሲል ብለን የምንጠራው ህመም ይከሰታል።

በባክቴሪያ አልያም ቫይረስ ኢንፌክሽን የሚከሰተው የቶንሲል ህመም፥ የቶንሲል እጢዎችን የማሳበጥና ጉሮሮን የመከርከምልክቶች አለው።ህመሙ አንዳንድ ጊዜም መተንፈስ አለማስቻልን ሊያስከትል ሁሉ ይችላል።

የቶንሲል ህመምን የተለያዩ መድሃኒቶችን በመውሰድ መዳን የሚቻል ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ በሚዘጋጁ ነገሮች በቀላሉ ማከም እንደሚቻል ይታወቃል።
 ውሃ ውስጥ ጨው ጨምሮ አፍን መጉመጥመጥ፣ አፍ እና ጉሮሮን ከጎጂ ተህዋስያን ማፅዳት ፡፡
 የፍራፍሬ ጭማቂዎችን ከሶስት እስከ አምስት ቀናት መውሰድ በሽታ የመከላከል አቅምን በማሳደግ የትኛውንም መመረዝ (ኢንፌክሽን) ለመዋጋት ያግዛል።
 ማርን ከውሃ ጋር ደባልቆ መጠጣት ፡፡
 ሎሚ መምጠጥ ወይም ከሻይ ጋር መጠታት ፡፡
 ዝንጅብል
 ዝንጅብል ጨምቀን /ቀጥቅጦ ማፍላት እና ማር ጨምሮ መጠጣት ፡፡
 ዝንጅብልን ሻይ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትም ሌላኛው አማራጭ ነው።
 ሙቅ ውሀ መታጠን፡፡
 በቂ ፈሳሽ መጠጣት፡፡
በኢትዮጵያ ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ

ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ ዛሬ እንደገለፁት በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች መያዛቸው ተናግረዋል፡፡

በአንድ ቀን ውስጥ ከ1000 በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፍት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመሩ የሚያሳየው ሶስተኛው የኮቪድ 19 መረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋልል፡
እርጎ በመጠጣት የምናገኛቸው የጤና ጥቅሞች

1. እርጎ በጠቃሚ ንጥረ ነገር የበለፀገ ነው፡- በካልስየም የበለፀገ ሲሆን ሰውነታችን ከሚያስፈልገው የእለታዊ ካልስየም ፍላጎት(Need) ውስጥ 49 በመቶ የሚሆነውን ካልስየም ከአንድ ኩባያ እርጎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህም የጥርሳችንንና የአጥንታችንን ጥንካሬ አስተማማኝ በማደረግ ጤንነታቸውን ይጠብቃል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ ቫይታሚን ቢ፣ፎስፈረስ፣ማግኒዜየም እና ቫይታሚን ዲ አለው፡፡ በዚህም የልብ በሽታን፣የደም ግፊትንና ድባቴን የመሳሰሉ የጤና ችግሮችን ይከላከላል፡፡

2. ከፍተኛ የፕሮቲን ንጥረ ነገር ስለያዘ ለሰውነት ግንባታና ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ በተጨማሪም የምግብ ፍላጎትን (Appetite) በመቀነስ የሰውነት ክብደታችንን ለመቆጣጠር ይረዳናል፡፡

3. የሆድ መንፋት፣ የአይነምድር ድርቀትና ተቅማጥን በማስወገድ ጤናማ የሆነ የምግብ ሥርዓተ ልመት (Boost digestive health) እንዲኖር ያደርጋል፡፡

4. የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጠናክራል፡፡ በተለይ በየዕለቱ እርጎ የሚጠቀሙ ሰዎች በበሽታ የመጠቃት እድላቸው ከማይጠቀሙት ጋር ሲነፃፅር በእጅጉ የቀነሰ ነው፡፡

5. እረጎ የአጥምት መሳሳትን ይካላከላል፡፡እርጎ በቫይታሚንና በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ ለአጥንት ጤና ወሳኝ ነው፡፡ በየእለቱ ከተመገቡ ደግሞ ከዕድሜ መግፋት ጋር የሚከሰተውን የአጥምት መሳሳት ይከላከላሉ፡፡

6. የደም ቅባትና የደም ግፊትን በመቀነስ አርጎ ለልብ ጤና ተስማሚ መሆኑን ይነገርለታል፡፡

7. የአለርጂ (ያለመስማማት) ምልክቶችን ይቀንሳል፡፡ ከውጭ አካባቢ ከወቅት ጋር ተያይዞ በሰውነታችን ላይ የሚያጋጥሙ የአለርጂ( የአለመስማማት) ምልክቶችን አንድ ኩባያ እርጎ በየዕለቱ በመጠጣት መቀነስ ይቻላል፡፡ አለርጂው የቆዳ፣የአፍንጫ፣ የጀሮ ወይም ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሊሆን ይችላል፡፡

8. እርጎ በጉንፋንና በኢንፍሎይንዛ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል፡፡ እርጎ በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማችንን በማሳደግ በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ቲ-ሴልስ (ቲ- ሕዋሳት) ኢንፌክሽኖችን እንዲዋጉ ያጠነክራቸዋል፡፡

9. የእርሾ ኢንፌክሽንን (yeast infection) ለመከላከል ይረዳል፡- ፀረ-ተዋህሲያን (antibiotic) መድኃኒት በተደጋጋሚ ጊዜ መወሰድ ለእርሾ ኢንፌክሽን ያጋልጣል፡፡ ስለዚህም በእርጎ ውስጥ ያለው ባክቴሪያ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የፒኤች ደረጃ ሚዛናዊ በማድረግ በእርሾ ምክንያት የሚመጣውን የኢንፌክሽን ሕመምና ምቾት ማጣት ይከላከላል፡፡

10. ከፍተኛ የደም ግፊት ይቀንሳል፡- በቅርብ ጊዜ በተደረጉ ጥናቶች እርጎ በየዕለቱ መጠጣት ከፍተኛ የደም ግፊትን በጥሩ ሁኔታ መቀነሱ ተረጋግጧል፡፡
በየዕለቱ ስለምንበላው ጤፍ ያልተነገሩ ጥቅሞች

በርግጥ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ስለጤፍ ማስተዋወቅ ለቀባሪው እንደማርዳት ያህል ይቆጠራል፡፡

ይሁንና አገራችን ለዓለም ካበረከተቻቻው ድንቅ የእህል ዘሮች ውስጥ ስለጤፍ ጠቀሜታ ሳይንስን መሠረት አድርጎ መናገር ደግሞ ሌላ የጥናት መረጃዎችን ዋቤ ማደርግ ይጠይቃል፡፡

ስለሆነም ከታዋቂው organicfacts.net ያገኘነውን 10ሩን አስደናቂ የጤፍ የጤና ጥቅሞችን እናካፍላችሁ፡፡

1. እድገትን ያፋጥናል፡- ለሰውነታች ጠቃሚ የሆኑ 8 አይነት የአሚኖአሲድ የፕሮቲን ንጥረነገሮችን ይዟል፡፡

2. ሴሊያክ የተባለውን በሽታ ይከላከላል፡፡ ግሉቲን ስንዴና በገብስ በመሳሳሉት እህል አይነቶች ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ይህም ትንሹ አንጀት ለብግነት የሚዳርገውን ሴሊያክ የተሰኘውን በሽታ የሚያባብሱ ሲሆን ጤፍ ግን ከዚህ የፕሮቲን አይነት ነፃ ነው፡፡

3. የአጥምታችንን ጤና ይጠብቃል፡፡ በውስጡ የያዘው በቂ ካልሲየም ለዚህ ደጀን ነው፡፡

4. ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅም እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም ካሉ የያዘው ቫይታሚን ሲ በሽታን በመከላከል ረገድ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን በማጠናክር ረገድ ወሳኝ በመሆኑ ነው፡፡

5. የደም ዝውውርን ይጨምራል፡፡ ብዙዎቻችን አንደምናውቀው ጤፍ በብረት ማዕድን የበለፀገ ነው፡፡ ስለሆነም የደም ማነስ ላለባቸው ሰዎች በተለይ ቀዩ ጤፍ በብዛት እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ የደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች መድከም፣ራስ ማዞር፣ የጡንቻ መዛልና የራስ ምታት የሚያጠቃቸው ሲሆን ከችግሩ ለመለቀቀቅ ጤፍ አብዝተው እንዲመገቡ ይመከራል፡፡

6. የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል፡- ኢንሱሊን ቀስ ብሎ ወደ ደም ቧንቧ እንዲፈስ ይረዳል፡፡

7. በወር አባባ ጊዜ ለሚከሰት ሕመምና ችግር መፍትሔ ይሰጣል፡፡ጤፍ በውስጡ ፀረ- ማቃጠል ባህሪያትና የወር አበባን ሕመም የሚያስታግስ ኤጀንትም አለው፡፡

8. የምግብ መፈጨት ጤናማነትን ይጨምራል፡፡ በውስጡ የያዘው ፋይበር የአንጀት እንቅስቃሴን ጥራትን በመጨመር የሆድ መነፋትና ጭብጠትን እንዲሁም ድርቀት ያስወግዳል፡፡

9. በሰወነታችን ውስጥ የኃይል ምርትን ያግዛል፡፡ በውስጡ የያዘው ከፍተኛ መጠን የኮፐር ማዕድን ይህን ተግባር በበቂ ሁኔታ ይወጣል፡፡

10. ጤናማ ልብ እንዲኖረን ይረዳል፡- ዝቅተኛ የሶድየም መጠን ስላላው የደም ግፊት መጠንን በመቀነስ ፣ልብ ድካም እና ስትሮክን በመሳሰሉ በሽታዎች እንዳንጠቃ ይረዳናል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን
የቀዝቃዛ ሻወር 5 ታምራዊ ጥቅሞች

ስለ ቀዝቃዛ ሻወር ጥቅም ከመዳሰሳችን በፊት አንድ ቀላል እውነታ እናስቀምጥ፡፡ ሙቅ ሻወር መሠረታዊ ፍላጐት ሳይሆን ለመዝናኛነት እና ቅንጦት የምንጠቀምበት ነው፡፡ በአብዛኛው የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በቅርብ በሚያገኙት ውሃ ውስጥ ሻወር ይወስዳሉ፡፡ በሃይቅ ውስጥ ዋኝተው የሚያውቁ ከሆነ በቀላሉ ሊያስታውሱ የሚችሉት ነገር የውሃውን ቅዝቃዜ ነው፡፡ግሪኮች በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለህዝብ አገልግሎት የሚውል የሙቅ ሻወር አገልግሎትን ፈጠሩ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ አብዛኛዎቹ ግሪካዊያን ካለው የጤና ጥቅም አንፃር ቀዝቃዛ ሻወርን ነበር የመረጡት፡፡ ጥቅሞቹን ማንበብ ይጀምሩ፡፡

ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በኋላ ቶሎ እንድናገግም ያረዳል!!

አትሌቶች ከባድ ልምምድ ካደረጉ በኋላ የሚያጋትማቸውን ድካምና ህመም ለመቀነስ በበረዶ ውሃ ሻወር ይወስዳሉ/ይዘፈዘፋሉ እኛ ግን ያን ያህል እርቀት መጓዝ አይጠበቅብንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ጥቅም ለማግኝት ከልምምድ በኋላ ቀዝቃዛ ሻወር መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

ስብን (ፋት) ለማቅለጥ!!

ሁለት የስብ አይነቶች በሰውነታችን ውስጥ ይገኛሉ ነጭ ስብ እና ቡናማ ስብ፡፡ ነጩን ስብ እንደ መጥፎ ሰው እንቁጠረው ቡናማውን ደግሞ እንደ ጥሩ ሰው፡፡ ነጩ ስብ ሁላችንም የምናውቀው የሰውነታችን ስብ ሲሆን ሁላችንም ለማጥፋት የምታገለው ነው፡፡ ሰውነታችን ከሚፈልገው በላይ የሆነ ከፍተኛ ካሎሪ በምንወስድበት ጊዜ በሃይል(Energy) መልክ እንዲጠፋ ማድረግ ይሳነናል/ያቅተናል በሃይል/ጉልበት መልክ ካልተወገደ/ካልጠፋ ግን ይህ ነጭ ስብ በታችኛው ጀርባችን፣ አንገት፣ ከዳሌ ከፍ ብሎ ባለው የመካከለኛው ሰውነት ክፍል እና ከጉልበታችን ከፍ ብሎ ባለው የእግር ክፍል ላይ ይከማቻል፡፡ቡናማ ስብ ጥሩ ሰው ሲሆን የሚሰጠን ጥቅም ለሰውነታችን ሙቀት መፍጠር ነው፡፡ በከባድ ቅዝቃዜ ወቅት እነዚህ ቡናማ ስቦች ይነሳሱና ካሎሪን በማቅለጥ የሰውነታችን ሙቀት እንዲጨምር ያደርጋሉ ይህም የሰውነት ክብደትን በመቀነስ ይረጋናል፡፡

የደም ዝውውርና በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል!!

ስብን ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር እንዴት እንደሚረዳን ከላይ ተመልክተናል ሰውነታችን ስብን ለማቃጠል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የበሽታ መከላከያ ስርዓታችንን ያነሳሳል ይህም ቫይረስን የሚዋጉነጭ የደም ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋቸዋል የእነዚህ ሴሎች መመረት በህመም የመጠቃት እድላችን እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ ቀዝቃዛ ሻወር አጠቃላይ የደም ዝውውርን ይጨምራል ይህም የደም ቧንቧዎች እንዳይጠነክሩ እና የደም ግፊት ያስወግዳል፡፡

የሚስብ ፀጉር እና ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል!!

በሰውነታችን ላይ ያለውን ብጉር ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ ሙቅ ውሃ ቆዳን ያደርቃል ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክልና ቀዳዳዎችን በመዝጋት በቆሻሻ ከመደፈን ይከላከላል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ የሚያንፀባርቅና በጣም የሚስብ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክሎችን በመዝጋት ቆሻሻ በራስ ቅላችን ላይ እንዳይከማች ይረዳል፡፡

ደስተኛ እና ፈጣን እንድንሆን ያደርጋል!!

ጠዋት ከአልጋ ላይ ሲወርዱ ደብርዎትና ተጫጭኖዎት የሚይነሳ ማነው? ይህ ሁሉም ሰው የሚያጋጥመው ነገር ይመስለኛል ነገር ግን ጠዋት ወደ ስራ ከመሄድዎ በፊት ገና ከአልጋዎ እንደወረዱ ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ፡፡ ቀዘቃዛ ውሃ በሰውነትዎ ላይ በሚፈስበት ጊዜ ለቅዝቃዜው ምላሽ በጥልቀት ይተነፍሳሉ(ይህ ሰውነትዎ ኦክስጂን አወሳሰዳችን በመጨመር ሰውነታችን ራሱን ለማሞቅ የሚያደርገው ሙከራ ነው፡፡የልብ ምትዎ ይጨምራል የዚህ ውጤት ደም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን እንዲዳረስ በማድረግ ጉልበት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
#ምግብ #እና #የወሲብ #ግንኙነት!



👉👉 #ወሲብና ምግብን ምን ያገናኛቸዋል? ብለው ይጠይቁ ይሆናል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት አመጋገባችን እና የወሲብ ሕይወታችን ቀጥተኛ ትስስር አላቸው። ደስታ የሚፈጥር ንጥረ ነገር ያላቸው ምግቦች ጤናማ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋሉ። ከነዚህ ምግቦች ጥቂቱን እነሆ ፡-

👉👉 #ቸኮሌት

🔺 #ቸኮሌት ፊኒሌትያላሚን የሚባል ንጥረ ነገር አለው። ንጥረ ነገሩ የፍቅር ግንኙነት ሲጀመር ደስ የሚል ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል። ቸኮሌት ውስጥ ትራይፕቶፋን የተባለ አሚኖ አሲድ ይገኛል። ይህም ሰውነት ውስጥ ደስታ የሚያመነጭ ሴሮቶኒን የሚባል ንጥረ ነገር እንዲዘዋወር ይረዳል። ትራይፕቶፋን ከእንቁላል፣ ከለውዝ፣ ከሶያ ምርቶችም ሊገኝ ይችላል። ቸኮሌትና የወሲብ ሕይወት መካከል ግንኙነት አለ መባል የጀመረው ከ16ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ነው።

👉👉 #ቃርያ#ሚጥሚጣ

🔺 #ካፕሳይሲን የሚባለው ንጥረ ነገር ቃርያ፣ ሚጥሚጣ በመሰሉ የሚያቃጥሉ ምግቦች ውስጥ ይገኛል። ሰዎች ደስታ ሲሰማቸው የሚመነጨው ኢንዶርፊን ሆርሞን እንዲዘዋወር ቃርያና ሚጥሚጣ ያግዛሉ። በተጨማሪም የደም ዝውውርን ያፋጥናል። የሰውነት የሙቀት መጠንና የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምርም ይረዳል። እነዚህ በወሲብ ወቅት ሰውነታችን ላይ የሚስተዋሉ ለውጦች ናቸው።

👉👉 #ፍራፍሬዎች

🔺 #ጥናቶች እንደሚያሳዩት የብልት አለመነሳት ችግር ያለባቸው ወንዶች ፍላቮኖይድ የተባለ ኬሚካል የያዙ ምግቦች እንዲመገቡ ይመከራል። ለምሳሌ ብሉቤሪ የተባለ የእንጆሪ ዝርያ፣ ብርቱካንና ሎሚም ችግሩን ይቀርፋሉ። የተለያዩ ፍራፍሬዎችን መመገብ የብልት አለመነሳት ችግርን 14% ይቀንሳል። ከአትክልት፣ ፍራፍሬዎች፣ የወይራ ዘይትና ለውዝ በተጨማሪ የሜዲትራኒያን አካባቢ ምግቦች የብልት አለመነሳት ችግርን እንደሚቀርፉም ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ቼሪ፣ ብላክቤሪ የተባለው የእንጆሪ አይነት፣ የወይን ፍሬ እና ቀይ ጥቅል ጎመን አንቶካይኒን የያዙ ምግቦች ናቸው።


🔺 #ሲጠቃለል የወሲብ ሕይወትን እንደሚያሻሽሉ የሚነገርላቸው አፍሮዲሲያክ( የወሲብ ፍላጎት ጨመሪ) የተባሉ ምግቦችን ለውጦቻቸው በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል። አንደኛው የወሲብ ፍላጎት፣ ሁለተኛው ወሲብ የመፈጸም ብቃትና ሦስተኛው ከወሲብ የሚገኝ ሀሴት ናቸው። በእርግጥ ተመራማሪዎች እነዚህን ውጤቶች መለካት አልቻሉም። እንዲያውም እስካሁን በእርግጠኛነት መናገር የቻሉት አፍሮዲሲያክ የቆዩ ፍራፍሬዎችን ሽታ ነው።

🔺 #ዶ/ር ክሪችማን የተባሉ የተባሉ የሥነ ተዋልዶ ጤና ተመራማሪ እያንዳንዱ ሰው የተሻለ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረኝ ረድቶኛል የሚለውን ምግብ እንዲያዘወትር ይመክራሉ። አብዛኞቹ አፍሮዲሲያክ የሚባሉ ምግቦች ጤናማ ምግቦች ናቸው። ወሲብ የተሻለ እንዲሆን ይረዳሉ የሚባሉ ነገር ግን ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን አለመጠቀም ይመከራል።

👉👉 #አልኮል #ወሲብን #የተሻለ #ያደርጋል?


🔺 አልኮል የወሲብ ተነሳሽነትን ቢጨምርም፤ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚደረግበት ወቅት ተጽዕኖ ሊያሳድርም ይችላል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ከመጠን በላይ መጠጣት የወሲብ ፍላጎትን ይቀንሳል። የአልኮል ሽታ ስለሚረብሽም የወሲብ ሕይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
🔺 አንዳንዴ የወሲብ ፍላጎት አናሳ ሲሆን ከጤና ችግር ጋር ሊያያዝ ስለሚችል ሀኪም ማማከር ይመከራል፡፡


👉👉 #የወሲብ ሂደት ላይ ተጽእኖ ከሚያመጡ ችግሮች መሃከል የሆርሞን ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው። ሆኖም ለዚህ ችግር አመጋገባችን የሚስገኘው ለውጥም ቀላል የሚባል አይደለም ፡፡
Nurse
#mekedonia_charity_organization
#health_care
#nursing
#nurse
Addis Ababa
Diploma in Nursing from recognized health institute with progressive working experience as a nurse & having professional working license
Quanitity Required: 6
Minimum Years Of Experience: #5_years
Deadline: October 20, 2021
How To Apply: Interested applicants should bring their credential; original & copies of non-returnable application letter, CV, educational transcripts, experience letter & other supporting documents in person at Mekedonia Charity Organization, to the Human Resource Administration Office. For further information, contact Tel. 0914083714 / 0919410022
Forwarded from Dr Million B
Trigeminal neuralgia /የፊት ነርቭ ህመም
trigeminal neuralgia የፊት ነርቭ ህመም በአለማችን ላይ በጥቂት ሰዎች ላይ የሚፈጠር የነርቭ ህመም ሲሆን የ5 አምስተኛውን ነርቭ ወይም/cranial nerve V እያልን የምንጠራውን ነርቭ ያጠቃል።
ይህ ህመም የፊትን ክፍል የላይኛውን / ግንባር ጋር ያለውን የፊት ክፍል/ ወይም የፍት የማህለኛውን ክፍል /አለዛ የአይን በታች፣ጉንጭ፣እንዲሁም የላይኛውን ከንፈር ውይም የፊታችን የታችኛውን ክፍል /የታችኛው መንጋጋ ያለበትን የፊት ክፍል ያጠቃል።
ምክንያቶቹ ምንድናቸው?
ምክንያቱ በውል ባይታወቅም በብዛት
መካከለኛ እድሜ ላይ ያሉ ሴቶችን ያጠቃል
ጥርስ ከተነቀለ ውይም ፊት ላይ አደጋ ከደረሰ ተከትሎ ይከሰታል
እንዲሁም ጭንቅላት ውስጥ እጢ ካለ እንደ አመላካች ሊሆን ይችላል።እንዲሁን multiple sclerosis የተሰኘ የነርቭ ስርአት ህመም ሊስከትለው ይችላል በተጨማሪም አንጎል ውስጥ ይህ ነርቭና የደም ስር ተጠጋግተው ሲገኙ ህመም ሊከሰት ይችላል ። ብዙ ሰዎች ህመሙ ከጥርስ ችግር ብለው ስለሚያስብ ህመሙ በተከሰተበት በኩል ያሉትን ጥርስ በመደዳ ማስነቀል ችግሩ Trigeminal neuralgia እንደሆን አመላካች ነው ።እንዲሁም በጥርስ ሀኪሞች ችግሩን በቀላሉ ከጥርስ ህመም ለመለየት ስለሚቸገሩ ታማሚው ብዙ ጥርስ ሊያስነቅል ይችላል
የህመሙ ምልክቶች
በድንገት የሚከሰት ከባድ የፊት ህመም ንዝረት ያለው፣ ንጥረት ያለው ለጥቂት ሰከንድ ወይም ደቂቃ የሚቆይ ሲሆን በግዜ ሂደት የህመሙ ደረጃ እየጨመረ እንዲሁም ህመሙ ቶሎ ቶሎ መምጣት ይጀምራል።
ህመሙ ለሊት የሚይከሰት ሲሆን ጥዋትና ምሽት በብዛት ሊከሰት ይችላል
ህመሙ አንደኛውን የፊት ክፍል ብቻ በማጥቃት ይታወቃል እንዲህም የታችኛውን የፊት ክፍል በይበልጥ የሚያጠቃ ሲሆን የመሀከለኛውን የፊት ክፍል በሁለተኛነት ደረጃ ያጠቃል የላይኛው የፊት ክፍል ላይ አልፎ አልፎ ይከሰትል።
ታማሚው ማድረግ የለለባቸው ነገሮች ምንድናቸው?
ታማሚው ችግሩ ከታወቀለት የሚከተለቱን ነገሮች ማድረግ የለበትም የሚያደርግ ከሆነ ህመሙን ያስነሳል ውይም ያባብሳል።
ፂም መላጨት
ቅዝቃዜ /አየር ወይም ውሀ
በእጅ በድንገት መንካት
በድንገት ልብስ ፊት ከነካ
መታከም ይችላል?
ህመሙ በግዜ ከታወቀና ከታከመ መዳን ይችላል ።
በግዜ መታወቁ ህክምናው ቀላል እንዲሆና በመጀመሪያ በመድሀኒት ህክምና ይድናል።የመድሀኒት ህክምናው ለረጅም ግዜ የሚሰጥ ሲሆን በቂ የክትትል ግዜና ህመሙ እንዳይመልስ ያድርጋል። ህመሙ በመድሀኒት ካልዳነ የቀዶ ህክምና ሌላው አማራጭ ህክምና ነው
ህክምናው በማን ይሰጣል
ህክምናው በፊት፣በመንጋጋ፣በእፍ እና በጥርስ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም ይሰጣል።
2025/07/04 15:14:41
Back to Top
HTML Embed Code: