የዓለም ዜና፤ የሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜና
--154 የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በእሥር ላይ መሆናቸውን ቅድሚያ ለሰብዓዊነት ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት አስታወቀ።
--የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን ዛሬ አስታወቀ።
--በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ ግድብ ተንዶ በትንሹ 42 ሰዎች ሞቱ። በኬንያ ሰሞኑን የዘነበዉ ከባድ ዝናብ በተለይ መዲና ናይሮቢ ላይ በርካቶችን አፈናቅሏል።
--የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ የዶቼ ቬሌን ራድዮ ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎችን እና ጋዜጦችን ማገዱ አስታወቀ። ወታደራዊዉ ጁንታ ይህን ያደረገዉ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሂዉማን ራይትስ ዎች ያወጣዉን መግለጫ ለምን ዘገባችሁ በሚል ነዉ።

--የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት ሲያበቃ፤ ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር በጋዛ ጉዳይ ላይ ለመምከር በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ መግባታቸዉ ተዘገበ።
ዝርዝሩን ያድምጡ!
https://p.dw.com/p/4fJoV
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በሁለት ወራት ገደማ የመጨረሻውን ሥምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል
ከ 26 ደቂቃዎች በፊትከ 26 ደቂቃዎች በፊት
ለሶማሌላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። https://p.dw.com/p/4fJoS
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ጎርፍ ያጠፋው ህይወት
አዲስ አበባ ዉስጥ ባለፈዉ ዕሁድ ከእኩለ ለሌት ጀምሮ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ ጎርፉ በትንሽ ግምት 13 ሰዎች ወሰደ።አንዳድ የዓይን ምስክሮች የሟቾቹ ቁጥር 14 ነዉ ይላሉ።ከጎርፍ አደጋው የተረፉ እንዳሉት ጎርፉ ድንገት የደረሰዉ ጎርፍ የወሰዳቸዉ ሰዎች ሰዎች ጎዳና ላይ የሚያድሩ ችግረኞች ነበሩ።የዓይን ምስክሮቹ እንዳሉት በተኙበት ከአጠገባቸዉ በጎርፍ ከተወሰዱት ሰዎች እስካሁን የተገኘዉ የ8ቱ አስከሬን ብቻ ነዉ።(የቪዲዮ ዘገባ በስዩም ጌቱ)
DW Amharic የሚያዝያ 23 ቀን 2016 የዓለም ዜና የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያውያን የቪዛ አሰጣጥ ሒደት እንዲጠብቅ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያጤን ኢትዮጵያ ጠየቀች። የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንቶች 6 ሚሊዮን ዶላር ለማጭበርበር የተደረገ ሙከራ ማክሸፉን አስታወቀ። ከ7 ሚሊዮን በላይ ደቡብ ሱዳናውያን የምግብ ዋስትና እጦት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተመድ አስጠነቀቀ። እስራኤል በጋዛ ወደምትገኘው ራፋ ያቀደችውን ወታደራዊ ዘመቻ አሜሪካ አሁንም እንደምትቃወም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገለጹ። ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የማረከቻቸውን የምራባውያን የጦር መሣሪያዎች፣ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች እና ወታደራዊ ሠነዶች በሞስኮ ለዕይታ አቀረበች። https://p.dw.com/p/4fP3o?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
"አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ" የመብት ጥሰቶች

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሰቡሲሬ ወረዳ ሞቶ ቀበሌ ሚያዚያ 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም 14 የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን እንዲሁም በምዕራብ አርሲ ዞን ታጣቂዎች በሰዎች ላይ ግድያ፣ እገታ እና የአካል ጉዳት መፈፀማቸውን ገልጾ፤ 5 ሰዎች በዚሁ ዞን በታጣቂዎች መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታውቋል። https://p.dw.com/p/4fOfE?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የትግራይ ተፈናቃዮች መመለስ

በአማራ ክልል በኩል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የተመሰረቱ ሕገወጥ አስተዳደሮቹ ፈርሰው ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው የሚመለሱበት ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር፣ አዳዲስ ሰፋሪዎች ከያዙት ቦታ ሊወጡ ከፌደራሉ መንግስት ጋር በነበረ ውይይት መግባባት ላይ መደረሱ ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናግሯል። https://p.dw.com/p/4fOsk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የባህላዊ እሴቶች ሚና ለሰላም

"ሃሳባችንን እንደ ኋላ ቀር የማየት አባዜ ሰፍኗል፡፡ ትውልዱ ጋር አውቃለሁ ባይነት ከፋ፡፡ ይህ ደግሞ አይሆንም፡፡ አሁንም ላለው ችግር እኛ የምንለው ተቀባይነት አጣ እንጂ ከመናገር ሀሳብ ከመስጠት ታቅበን አናውቅም” https://p.dw.com/p/4fNtv?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
በአማራ ክልል የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 2.5 ሚሊዮን ማሻቀቡ

መንግስት አጠቃላይ በአማራ ክልል በችግር ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች በየወሩ ከ2 .2ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግም የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡ https://p.dw.com/p/4fOPp?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
ኢትዮጵያውያን ቲክቶከሮች ስለቲክ ቶክ መታገድ ምን ይላሉ?
ፀሀይ ጫኔ

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ቲክ ቶክ ከቻይናው ኩባንያ ባይትዳንስ እጅ እስካልወጣ ድረስ በሀገሪቱ ውስጥ እገዳ ለመጣል የሚያስችል ረቂቅ ህግ ያለፈው ቅዳሜ አጽድቋል።ያ ለመሆኑ ቲክ ቶክ ቢታገድ በይዘት ፈጣሪዎች እና በተጠቃሚዎች ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? https://p.dw.com/p/4fM0x?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች

ኤኮኖሚኢትዮጵያ
Eshete Bekeleከ
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ንብረት የሆነው ዱባይ ወርልድ ኩባንያ የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት አቅደዋል። ለዚህም የወደብ አጠቃቀም እና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ሥምምነት በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት። ሥምምቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ባለሥልጣን ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። https://p.dw.com/p/4fP5U?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
2024/05/02 09:07:54
Back to Top
HTML Embed Code: