Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Fuulli Facebook Gadaa Media Network yeroof ugguramee waan jiruuf, karaa YouTube fi Twitter (X) nu hordofaa!
https://www.facebook.com/share/p/1HQJiC5Zie/?mibextid=wwXIfr


የረጆ ሚዲያ አዲስ አቅጣጫ!
======
የሶማሊ ክልል አመራር ብልሹነትና እና የፌዴራል መንግሥት ዝምታ ለምን?
__________________
ከዛሬ በኋላ ረጆ ሚዲያ ስለ ሙስጠፌ አግቸር የምትጽፈው አይኖርም፤ ካለም ጥቂት ይሆናል፡፡ ይልቁንም ትኩረቷን በፌዴራል መንግሥት በተለይም በኦህዴድ ብልጽግና ባለሥልጣናት እና በቡችሎቻቸው ላይ ታደርጋለች!!!
========
የኦህዴድ ብልጽግና ባለስልጣናት ርካሽና ወራዳ ገመናቸውን በአደባባይ በማስጣት የተደበቁበትን ጭምብል (ማስክ) በማስወለቅ ህዝቡ ከነዝህ ቆሻሾች ማር መጠበቅ እንደሌለበት አጥብቃ ትሰራለች!!!
========
መግቢያ፦
ረጆ ሚዲያ ትኩረቷን በሶማሊ ክልል ላይ በማድረግ ላለፉት ዓመታት የፕሬዝዳንት ሙስጠፌ አግቸርን ኢ-ፍትሃዊነት፣ ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሁም በእርሳቸው እና በቤተሰባቸው የሚፈጸመውን የኮንትሮባንድ ንግድ በስፋት ስታጋልጥ ቆይታለች። በተጨማሪም፣ ሙስጠፌ አግቸር የአእምሮ በሽተኛ እና ክልሉን ለመምራት ብቁ እንዳልሆኑ፣ ይህም በሚሰሯቸው ስራዎች ማለትም የጎሳ ግጭቶች መባባስ (በተለይም በአፋር እና ሶማሊ ክልል መካከል)፣ በክልሉ ልማት አለመኖር፣ እና በድንበር አካባቢ ከሀገር በሚወጣው ዶላር ምክንያት በተለየ ሁኔታ የኑሮ ውድነት ተባብሶ ህዝቡ ወደ ባሰ ድህነት መውረዱን ደጋግማ ጽፋለች።

የፌዴራል መንግሥት ዝምታ እና የተጠያቂነት ጥያቄዎች

የፌዴራል መንግሥት ይህን ጉዳይ በሚገባ ያውቀዋል። የፌዴራል ባለሥልጣናት ስለ ሶማሊ አመራሮች ሲናገሩ “ፌዴራል የተቀመጡት የሶማሊ አመራሮች ፈሪዎችና ሆዳሞች” እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ህዝቡም በነርሱ ላይ ተስፋ ከቆረጠ ቆይቷል፡፡

እዚህ ላይ የረጆ ሚዲያ ጥያቄ ግልጽ ነው፦ የአዕምሮ በሽተኛ መሆኑን ካወቃችሁ፣ ለምን 8 ሚሊዮን ህዝብን እንዲመራ ፈቀዳችሁለት? የአዕምሮ በሽተኛ መሆኑን በፊት ካላወቃችሁ፣ ባወቃችሁ ጊዜ አልረፈደምና ለምን አልቀየራችሁትም? (በነገራችን ላይ ፕሬዝዳንቶችን መቀየር ያለበት በክልሉ ፓርላማ ቢሆንም፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈቀደውን ስለሚያደርግ ነው)።

ረጆ ሚድያ አሁን የተገነዘበችው አንድ እውነታ ቢኖር ሙስጠፌ አግቸርን ስልጣን ላይ ያመጣውም የሚያስወግደውም የሶማሊ ህዝብ እንዳልሆነ ነው። ረጆ ሚዲያ የአዕምሮ በሽተኛ ፣ ሙሰኛ፣ ዘራፊ ብላ ብትጮህ ሰሚ እንደሌላት እርግጥ ነው። በፌዴራል ያሉ የኦህዴድ ብልጽግና ባለሥልጣናት እና ሌሎችም ባለሥልጣናት የሚፈልጉት ለዚህ ደሀ ህዝብ ከተበጀተው በጀት ላይ ሙስጠፌ አግቸር ምን ያህሉን እንደሚያካፍላቸው ማስላት ነው። ህዝቡ ሞተ፣ ተቸገረ፣ ልማት ኖረ አልኖረ፣ ክልሉ በሙስና ተወሯል የሚለው የህዝቡ እሮሮ ለነሱ ለነፍስያቸው የሐሴት ሙዚቃ ነው። ይህን በሰሙ ቁጥር ሙስጠፌ አግቸር ጋር ደውለው “ይህ ችግር ስላለ እንድንከላከልልህ ዘንድ ገንዘብ ፈሰስ አድርግ” ይሉታል፤ እርሱም ያደርጋል። ሙስጠፌ አግቸር በአጭሩ የኦህዴድ ብልጽግና cash cow ነው፤ ያልቡታል፡፡ ይህ መውጫ የሌለው የክፋት አዙሪት (vicious cycle) ነው። በተጨማሪም ክልሉ እርስ በርሱ እንድጋጭና ሁልጊዜ ውስጣዊ ችግሮች እንድኖርበት ፌዴራሉ ይፈልጋል፡፡ አዲስ አበባን የማይነካና የአብይን ስልጣን ላይ ችግር የማያመጣ እስከሆነ ድረስ ክልሉ ቢወድም ፌዴራሉ ይበልጥ እንድቀጣጠል ተጨማሪ ነዳጅ ያቀብላል እንጂ ለማብረድ እጁን አያነሳም፡፡ አውቆን የተኛን ፌዴራልን ረጆ ሚድያ መቀስቀስ አትችልም!

ስለዝህ አዲስ የትኩረትና የትግል አቅጣጫ መቀየስ የግድ ብሏል፡፡

የረጆ ሚዲያ ቀጣይ ትኩረት እና ዓላማዎች

ስለዚህ፣ ከዛሬ በኋላ ረጆ ሚዲያ ስለ ሙስጠፌ አግቸር የምትጽፈው አይኖርም፡፡ ካለም ጥቂት ይሆናል፤ እርሱም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና አዲስ መረጃ ሲኖር ይሆናል። ይልቁንም ትኩረቷን በፌዴራል መንግሥት በተለይም በኦህዴድ ብልጽግና ባለሥልጣናት እና በቡችሎቻቸው ላይ ታደርጋለች። ይህን የምታደርግበት ዋነኛ ምክንያቷ የእነዚህን ግለሰቦች አስነዋሪ ተግባራት ለህዝቡ በመግለጽ አመራር ላይ ያሉት ሰዎች የኢትዮጵያን ህዝብ የመምራት ሞራል እንደሌላቸው ማሳየት ትፈልጋለች። በሥነ-ምግባር ከተበላሹ ዋልጌዎች መልካም ነገር መጠበቅ ከዝንብ ማር መጠበቅ መሆኑን በማመን ገመናቸውን በአደባባይ በማስጣት የተደበቁበትን ጭምብል (ማስክ) ታወልቀዋለች።
ይህን ማድረጓ ምን ይጠቅማል?

* የሀገር ደህንነት ማስጠበቅ: አገራችን ኢትዮጵያ ነው። ሌላ አገር የለንም። በአገር ደረጃ እየደረሰ ያለው ጥፋት፣ ጦርነት (በአማራ፣ ኦሮሚያ እንዲሁም ትግራይ ክልል) ከኛ የራቀ ቢመስልም ነገ ሁላችንንም መንካቱ ስለማይቀር ከነዚህ ሆዳሞች አገር መዳን አለበት።

* ሙስናን መግታት: ምስጢራቸው ወደ አደባባይ ከወጣ፣ ቢያንስ የሶማሊ ክልል ወይም ሌላ ክልል ላይ ሄደው የሞራል የበላይነት ማሳየት አይችሉም። ስለዚህ ለእነርሱ የሚሰጠው ገንዘብ ይቀንሳል።

* የህዝብ ንቃት መፍጠር: የብልጽግና ፓርቲ ስብስቦች እይታቸው ከፍ ሲል ኮሪደር ልማት ዝቅ ሲል ደግሞ መኝታ ቤት መዳራት መሆኑን በማስረጃ በማቅረብ ህዝቡ እነርሱን መታገል እንዳለበት በማነሳሳት፣ ቢያንስ እየሰሩ ያሉትን ነገሮች መልሰው እንዲያጤኑት እድል ለመስጠትና ህዝቡ ነገን እንዲኖር ለማድረግ ነው።

የህዝብ ተጠያቂነት እና ጥሪ*

ስለዚህ፣ እዚህ ገጻችን ላይ ገመናቸውን የምናወጣቸው ሰዎች ግለሰቦች እንዳልሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። እነዚህ በመንግሥት ሥልጣን የተሰጣቸው የህዝብ አገልጋዮች ናቸው። ህዝቡ ደግሞ ስለነርሱ የማወቅ መብት አለው። የህዝብ ሥልጣን እስከያዙ ድረስ ምንም የግል (private) የሚባል ሕይወት የላቸውም። ረጆ ሚድያ ያደረጉትን እያንዳንዱን ወንጀል አደባባይ ላይ ለማስጣት እንደምትሠራ በታላቅ አክብሮት ለገጻችን ተከታዮች ልታሳውቅ ትወዳለች። የሶማሊንና ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳስለቀሱት ሁሉ ባገኙት ገንዘብ ፍስሐ እንደማያገኙ ሊያውቁት ይገባል። ረጆ ሚዲያም ሙስጠፌ አግቸር ላይ የምትጽፈው በመንግሥት የሚታወቅ በመሆኑና ሚስጢር ባለመሆኑ ምንም እርምጃ የሚወሰድበት ስላልሆነ መተዋችን ሊታወቅ ይገባል።ቢያንስ ሙስጠፌ ብጩ ቢሆንም አብይን እንደማይወደው ስለምናውቅ ያስማማናል፡፡

ረጆ ሚድያ የሚትፈልገው የብልጽግና ፍትህ ሳይሆን፣ ብልጽግናን በህዝቡ አይን ወራዳና ዋልጌ መሆኑን በማስረጃ በማቅረብ ቅቡልነቱን ማሳጣት ዋነኛ አጀንዳዋ ነው። በዚህ ጉዞዋ ወቅት ስለ ብልጽግና ባለሥልጣናት የምታውቁትን መረጃዎች በማጋራት፣ በጋራ ይህን አስከፊ ስርዓት እንድትታገሉት ጥሪ ታቀርባለች!

ረጆ ሚዲያ
https://www.facebook.com/share/p/15CATyYRok/?mibextid=wwXIfr

አቶ ዛዲግ አብረሃ: የስልጣን ስግብግብነትና ማንነትን የመቀያየር ጥበብ
=======
ዛሬ የዛዲግን ማስክ እንገፈዋለን፡፡ የዛዲግን ብዙ መልኮች፣ ስለሱ ማንነትና ተግባር በጥቂቱ በመናገር ብልጽግና ውስጥ ያለው ስብስብ ብልሹና ወራዳ መሆኑን ለማሳየት እንሞክራለን፡፡
---------

የዛዲግ አመጣጥና የልጅነት ጊዜ

አቶ ዛዲግ አብረሃ ትውልዱ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከምትገኘው ስሔታ (ሐውዜን) አካባቢ ነው። በተለምዶ "አብረሃ ሓኪም" እየተባሉ የሚጠሩት አባቱ፣ በአንድ በኩል የኢሠፓ አባል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የጤና ባለሙያ ነበሩ። በስራ ምድብ ምክንያት በ1970 ዓ.ም አካባቢ ከሓውዜን ለቀው አላማጣ መኖር ጀመሩ። በመሆኑም የአቶ ዛዲግ ቤተሰብም ሆኑ ራሱ ዛዲግ ስልጣን ለማግኘት ሲሉ እንደሚያወሩት ወለየ ሊሆኑ ቀርቶ፣ ወደ ራያ የሄዱትም በአባታቸው የስራ ምድብ ምክንያት ነበር።

ከቅርብ የሚያውቁት ሰዎች እንደሚመሰክሩት፣ ዛዲግ ከልጅነቱ ጀምሮ የመታየት ፍላጎት ነበረው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የስልጣን ጥማት አሳደረበት። በ1997 EC በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የቅንጅት አስተባባሪ እንደነበርም ይነገራል። በ1999 EC ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ ሲመረቅ፣ ቅንጅትም ተበታትኖ ስለነበር ሊረዳው አልቻለም። በዚህም ምክንያት እስከ 2001 EC ድረስ ስራ አጥ ሆኖ በአዲስ አበባ ኖሯል።

የፖለቲካው ዓለም ገበያና የስልጣን ሽኩቻ
ዛዲግ ኢህአዴግ እያለ ብዙ መልክ ነበረው፡፡ ሁለት ሰዎችን አምሳያ አድርጎ እንደ ጣዖት ይከተል ነበር፡፡ መለስና በረከትን ስማቸውን ማንሳት የሚያሾም ይመስለው ነበር፡፡ በኃላ ላይ ኃይለማርያምና ደመቀን እንደ እየሱስ መከተል ጀመረ፡፡ አሁን ያለበትን ብዙ ሰው ያውቀዋል፡፡ ዛዲግም ብልጽግና ሲመጣለት ቀድሞ በመቀላቀል አደግዳጊነቱን በስራ ያሳየ ሰው ነው፡፡ ለዚህም የማሽቃበጥ ስራው እናቱን ሁሉ በራያነት ስም ለአብይ ኩታ እንድታቀርብለት አድርጓል፡፡ "የራያ እናቶች አብይን ሸለሙ" የሚል ዜናም በብሄራዊ ቴሌቪዥን እንዲሰራለት አድርጓል::

የስልጣን አነፍናፊው አቶ ዛዲግ በዚህ መሃል በሰው አማላጅነት ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር ተገናኘ። አቶ በረከትም የብአዴን አባል አደረጉት። የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ሆነው በተመደቡበት ወቅት ደግሞ ዛዲግን ምክትላቸው አድርገው ሾሙት።

ከ2005 EC ወዲህ የበረከት ስምዖን ባንዲራ ከኢህአዴግ የወረደበት ዘመን እንደነበር የተረዳው ዛዲግ፣ አቶ በረከትንና ብአዴንን በአንድ ላይ ከዳ። "እኔ ትግራዋይ ነኝ፤ የብአዴን አባል የሆንኩት ሳልፈልግ በበረከት ሴራና ጫና ነው፤ ስለዚህ ከብአዴን ለቅቄአለሁ፤ የህወሓት አባል አድርጉኝ" ብሎ ማመልከቻ ጻፈ። ህወሓቶችም ተቀበሉት። የአዲስ አበባው የህወሓት ጽህፈት ቤት ዛዲግን የተቀበለው በተራ አባልነት ነበር።

ሆኖም አቶ ዛዲግ አሁንም የአቋራጭ ስልጣን ይፈልግ ስለነበር፣ "ከፍተኛ አመራር ካልሆንኩኝ" ብሎ "ያዙኝ ልቀቁኝ" አለ። አማላጆች እንደ ጉድ ተላኩ። ይህም ከባድ የጭቅጭቅ ምክንያት ሆነ። በአማላጆች ብዛት እስከ ሚኒስትር ማዕረግ የደረሰው ዛዲግ፣ በየቀኑ የሚፈልጋቸውን ወዳጆች እየቀያየረ "Reading is my hobby. Just reading, reading! my role model is Meles Zenawi" እስከ ማለት ደረሰ። "ጫማም በአጎቴ ከአውስትራሊያ ነው የማስልከው" እያለም ይናገር እንደነበር ተገልጿል።

የህወሓት ጉባኤ ውድቀትና የከሃዲነት ጉዞ

በዚሁ ሁኔታ እየተሞዳሞደ፣ በወሬ እንጂ በስራ የማይታወቀው አቶ ዛዲግ አብረሃ በ13ኛው የህወሓት ጉባኤ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመመረጥ ከፍተኛ እምነት ይዞ ነበር ወደ ጉባኤው የገባው። ሆኖም ግን ዛዲግ ቅጥፈቱ ተጋለጠና አልቀናውም። ለማዕከላዊ ኮሚቴ እጩነት ቢጠቆምም፣ በአሁኑ ወቅት የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑና በደንብ የሚያውቁት አንድ ጓድ፣ ዛዲግ "ከፍተኛ የሆነ ስልጣን ጥማት አለብህ፣ ለዚሁ ሲባልም የመታየት እንቅስቃሴ ነው የምታደርገው። ግለኝነትም ያጠቃሃል፤ ወገንተኝነትም የለህም። የተለያዩ ሰዎችን በማማለድ ካልሆነ በቀር በመደበኛ የድርጅቱ አሰራር ስልጣን ተሰጥቶህ አያውቅም፤ ስለዚህ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አትመጥንም" ብሎ ተቃወመው። ጉባኤተኛውም ይህንን የተቃውሞ ድምጽ ተጨማሪ አስተያየቶችን ተቀብሎ የአቶ ዛዲግ እጩነት ውድቅ አደረገ።

በዚሁ ሁኔታ የተናደደው አቶ ዛዲግ ጉባኤውን አቋርጦ ሄደ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ፀረ ህወሓትና ፀረ ትግራይ ህዝብ እንቅስቃሴ ጀመረ። እንደገናም ከዳ!

የግል ሕይወት ውጣ ውረድና "ቁጭራ ሰፈር አዳሪነት"

ዛዲግ ሁለት ክፉ ጠባዮች አሉት ይባላል፡- ሴሰኝነት እና ሱሰኝነት።

የመጀመሪያ ሚስቱ የህግ ባለሙያ ስትሆን እየባለገባት ተቸገረች፡፡ ስካሩንና ሱሱን ችላው ነበር፡፡ ሴሰኝነቱን ግን መቋቋም አልቻለች፡፡ ፈታችው፡፡ ዛዲግም ልጆቹን ችላ አላቸው፡፡ ሚስቱ ለልጆቹ ቀለብ አልቆርጥ ሲላት ወደ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ በመሄድ ችግሯን ተነፈሰች፡፡ ጋዜጠኞቹም መረጃውን balance ለማድረግ ዛዲግ ጋር ይደውላሉ፡፡ እርሱም ተዉት ይህን ጉዳይ ማውጣት አትችሉም ብሎ ያስፈራራቸዋል፡፡ ጋዜጠኞቹም የመጣው ይምጣ በማለት መረጃውን ይጽፋሉ ከዚያም ለህትመት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ይወስዳሉ፡፡ በነጋታው ጋዜጣው ሲወጣ የዛዲግን ታሪክ የያዘው ገጽ ነጭ ሆኖ ይወጣል፡፡ ለካ ሰውዬው ስልጣኑን ተጠቅሞ አስጠፍቶት አድሯል፡፡

ዛዲግ አብዮታዊ ነኝ በሚልም የመለስ ዜናዊ ልጅን ካላገባሁ አለ፡፡ ሽማግሌም ላከ፡፡ ይሁን እንጂ ከቀድሞ ሚስቱ የወለዳቸው ልጆቹን ደብቆ ነበር፡፡ ሲደረስበት ከመለስ ልጅ እንዲርቅ ተደረገ፡፡አንዳንዶች "በሽታ ያመጣብኛል" ብላ ግንኙነቷን እንዳቋረጠችው ይናገራሉ፡፡
የቀድሞ ሚስቶቹን ከፈታ በኃላ ወደ ሽባባው ቤተሰብ ተጠጋ፡፡ ስሌቱ አማራ ነኝና ተቀበሉኝ ይኸው አማራም አግብቻለሁ ለማለት ነበር፡፡ ዛዲግ የዘነጋው ነገር ግን የሽባባው ቤተሰብ የአገው ብሄረሰብ አባል መሆናቸውን ነው፡፡ ወዲያውኑ የአዴፓ ሰዎች ዛዲግ አማራ አይደለም የተጋባውም ከአማራ አይደለም ያሉበት ምክንያትም ይኸው ነው፡፡ አሁን ደግሞ የአያቱን የበርሄን ስም ሽሮ “ሻረው” ሆኛለሁ ብሏል፡፡ ይሄም አማራ የመሆን ፍላጎቱ አካል ነው፡፡ አሁንም የብልግና ዓመሉ አልተው አለው፡፡ የሚስቱን ቤተሰቦች ሳይቀር ማማገጥ ጀመረ፡፡ እህቷንም አጫወታት፡፡ ይህም ትዳሩ አሁን ላይ አልዘልቅ አለ፡፡ ተበተነ፡፡

አስገራሚ ባህሪያትና የፓርቲ ለውጥ

ዛዲግ አስገራሚና አስቂኝ ባህሪያት እንዳሉት ይነገራል። ሲሰክር የቦታ ምርጫ እንደሌለው እና ገንዘብ የለውም እንዳይባል ክልሎችን ይቀፍላል። በተለይ የሶማሊ ክልል አመራሮች በራሳቸው ላይ እምነት ስለሌላቸው የክልሉን በጀት ለዛዲግ ክፍት አድርገውለታል፡፡ "ቁጭራ ሰፈሮችን" (ዶሮ ማነቂያ፣ ሰባተኛ) እየጎበኘ፣ "የታጠነ ያልታጠነ" እያለ ያማርጣል፣ ከዚያም እዚያው ጠጥቶ ይተኛል።

አንዳንድ ጊዜም የዱባይ ነጋዴ ሴቶችን እያፈላለገ፣ እቃዎቻቸውን ኤርፖርት ድረስ ሄዶ በስልጣኑ እንደሚያስወጣላቸው ከዚያም "ወደ አልጋ" እንደሚሄድ ይነገራል። ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ የራሱን የተከበረ የጋብቻ አልጋውንም ጭምር ሌላ ሴት አምጥቶ ማጫወቱ ነው።

የብልጽግና "አይዶሎጎች" እና ተለዋዋጭ ማንነት
እንደ ዛዲግ ያሉ ሰዎች ናቸው እንግዲህ ለብልጽግና ፓርቲ "idologue" ነኝ ብለው ፂማቸውን አሳድገው ምሁር የሚጫወቱት ተብሏል። "ከእነዚህ አይነቱ ወራዳ እንዴት ማር ሊገኝ ይችላል?" የሚለው ጥያቄም ይነሳል።የሚገርመው ደግሞ ብልጽግና በሀገር አቀፍ ባደረጋቸው ሁለት ትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ዛዲግ ጥናቱን እንዲያቀርብ ተደርጎ ነበር፡፡ በዝያ ስብሰባ የተሳተፉ የብልጽግና ሰዎች በአንድ ድምጽ ይህን ሰው መልሳችሁ አታምጡብን ቢሉም ጠቅላዩ ግን ዛዲግን ተዉት በማለት እንክብካቤ ሲያደርጉለት ተስተውሏል፡፡

አንዱ ዩትበር "ዛዲግ ስልጣን ካሳዩት አይደለም ብሄሩ ፆታው ይቀይራል፡፡ ስልጣን ከ50% በላይ ለሴቶች ይሰጣል ቢባል ሴት ነኝ ብሎ ይቀርባል" በማለት፣ ዛዲግ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም የማንነት ለውጥ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን መናገሩን እዝህ ላይ መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡

ህዝቡ ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ብልጽግና የሰበሰባቸው ሰዎች ብልሹ ኢህአዴግ እንኳ በአቅሙ "አይመጥኑም" ብሎ የጣላቸውን ግለሰቦች መሆናቸውን ስናይ አገር አደጋ ላይ መውደቁ እርግጥ ይሆናል፡፡

ለዝህ ነው ብልጽግ ና የውዳቂዎች ስብስብ ነው የሚባለው፡፡ ሀሳባቸው ከኮሪደር ልማትና ከትዳር ህይወታቸው ውጭ ከመልከስከስ በቀር የሚያስቡት የአገር ልማት የለም፡፡ እንደ ዛዲግ ያሉት "አይዶሎጎች" ይዞ ሌላ ቢያስብ ኖሮ ያስገርም ነበር፡፡ የሚበላውን ያጣውን ህዝብ "ቪዥን" የሚባል አዲስ ምግብ በምናብ እየመገቡት ይገኛል፡፡
2025/07/12 04:49:17
Back to Top
HTML Embed Code: