በሆነ ጊዜ ኖሀ የሚባል አንድ ባለጠጋ ነበረ።እናም እድሜ
ለሰጠው ፈጣሪ ግዜ አይሰጥም ነበረ።በዛን ወቅት አላዛር የሚባል በጣም የተቸገረ ሰው
ነበረ።በጣም ተቸግሮ የሚበላው
የሚቀምሰው ነገር አልነበረውም።እናም በጣም ቆሳስሎም ነበረ።እናም ቁስሎቹንም ውሾች ይልሱት ነበር።እርሱም ወደ ባለጸጋው ቤት ፊትለፊቱ ቆሞ እርሱ የሚበላውን እየተመኘ ምራቁን ይውጥ ነበረ።ከእለታት አንድ ቀን ሞት አይቀርምና ባለጸጋው ሰውዬ ሞተ።ወደ ሲኦልም ገባ ከዛም አብረሀም አብረሀም እባክህን ከዚህ ቦታ አድነኝ እኔኮ የአላዛር ጎረቤት ነኝ አለ።አብረሀምም የዛኔ አርሱ ተርቦ ከበርህ ጀጅ ሲቆም አብልተከዋል ወይ? አለው።አንተ የመሬት ላይ የነበረክ ሞልቶ የነበረው ሀብት እዚህ አይጠቅምህም አንተ እዛ ዋጋህን ጨምረህ እዚህ ከስሮበሀል።ደግሞም የሁለት አለም ሰው መሆን አይቻልም አለው።ከዛም ናሀም እንደዚህ አለወ እሺ አንድ ነገር ብቻ አርግልኝ አለው።አብረሀምም ምንድነው? ብሎ ጠየቀው።ኖሀም ቢያንስ ምድር ያሉኝን ወንድሞችን እዚህ እንዳይመጡ አንድ ሰው አስነስተህ በደምብ አስተምርልኝ።ምክኒያቱም እነርሱ ስራቸው ከባንኮኒ ወደ ሌላ ባንኮኒ ከሌላ ሴት ወደ ሌላ ሴት ነው ስራቸው።እናም ወደዚህ እንዳመጡ አርጋቸው እባክህን አለው።





ግን በአሁኑ ጊዜ ቢሆን እውነት እንደዚህ እናደርጋል ወይ?
እኛ ብንሆን ሰው ከሞት ተነስቶ ሊያስተምር መጣ ቢባል እውነት የሚያስተምረውን እንሰማለን ወይስ ላይክና ኮሜንት ለማግኘት እንሮጣለን? እራሳችንን እንጠይቅ እንፈትሽ።ንሰሀ እንግባ እንቁረብ ከአላስፈላጊ ነገሮች እንራቅ


ሼር በማድረግ ያላወቁትን እንድናሳውቅ እለምንሀቹሀለው እባካችሁን።
✞ ለስንቱ እንጀራ ሆንክ

ለስንቱ እንጀራ ሆንክ ለስንቱ መጠጥ (2)
ኢየሱስ ስምህ ሲጣፍጥ


የበላነው በለስ ገድሎን ሰለነበር
የሕይወት እንጀራን ስንናፍቅ ነበር
ከሰማያት ወርደህ ታርደህ የበላንህ
ኢየሱስ ክርስቶስ ይጣፍጣል ስምህ

አዝ__________

የሕይወት ውሃ ምንጭ ከሆድህ ይፈልቃል
ሰማርያ ወርዶ ውሃ ማን ይቀዳል
በልብ እየፈሰስክ ነፍስ የምታረካ
ቅዳልን ኢየሱስ ጔዳችንን እንካ

አዝ__________

ከያዕቆብ ጉድጔድ ለዘመናት ጠጣን
አመታት አለፉ እጅግ እየጠማን
አይደለም ለእንስራ ለልብ የምትደርስ
የወይኑ ዘለላ በነፍሳችን ፍሰስ

አዝ__________

በሲና የነበርክ የጉዟችን አለት
በረሃው ቀዝቅዞ ረክተን አለፍንበት
ከጥልቅ እንደሚፈልቅ ከአለቱ ላይ ጠጣን
ስምህ እርካታ ነው ከእንግዲህ ላይጠማን

አዝ__________

ሳምሪት ታመኝበት መቅጃ አትጠይቂው
ጉድጔዱም ጥልቅ ነው ብለሽ አትንገሪው
የሕይወትሽ ውሃ መፍሰሻ ነው እርሱ
ለልብ የሚቀዳ እርሱ ነው ንጉሱ

ለስንቱ እንጀራ ሆንክ ለስንቱ መጠጥ x2
ኢየሱስ ስምህ ሲጣፍጥ

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
@eotcbete
@eotcbete
@eotcbete
በአንድ ወቀት አንድ በጣም ወፍራም,እሮብና አርብ የማያውቅ
ፈጣሪውን የማያመሰግን ሰው ነበረ።እናም ይህ ሰው ከምግብ ውጪ ምንም ነገር አያውቅም ነበር።እናም ይህ ሰው በሆነ ግዜ ላይ የሆነ ጉድጓድ ውስጥ ብዙ ወርቅ ያገኛል።እናም ማውጣት አልቻለም።ምን እንደሚያደርግ እያሰበ እያለ የሆነ ልጅ በጎኑ ሲያልፍ አየ።ከዛን ልጁን ጠራውና እዚህ ጉድጓድ ውስጥ ገብተህ ወርቁን አውጣና 300 ብር እሰጥሀለው አለው።ከዛን ልጁ 300 ብር ብዙ ስለነበረ እንደዚ አለ።አሁን ለስላሳ እገዛለሁ አለ።ከዛ ቆይ አባቴን ጠርቼው ልምጣ አለ።ሰውዬውም ለምን? አለ።ልጁም ምክኒያቱም አንተ እኔ ከከበድኩህ ትለቀኛለክ አባቴ ግን አይለከኝም።



የተረዳችሁትን comment ላይ አስቀምጡ


share share
••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
@eotcbete
@eotcbete
@eotcbete
#የታላቋ_ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያናችንን
#ሕግና_ሥርዓት_አክብረን_እናስከብር
⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።⛪️


⛪️፩. #በቅዳሴ_ጊዜ_ያሉ_ሥርዓቶች
🔔 “አሐዱ አብ” ሳይባል በሰዓት መድረስ፤
🔔 “በሰላም ግቡ” ሳይባል አለመውጣት፤
🔔 የግል የጸሎት መጽሐፍ አለማንበብ፤
🔔 በቅዳሴ ጊዜ ከቦታ ቦታ አለመዘዋወር፤
🔔 የግል ሰላምታ፣ ወሬና ስልክ አለማውራት፤
🔔 የቤተ ክርስቲያን ቦታን የግል አለማድረግ፤
🔔 መቅደስ ውስጥ ለልጆች ምንም ዓይነት ምግብ መስጠት አይቻልም፤ ከቅዱስ ቊርባን በኃላ ዘቢብ (በቍርባን ቀን ከደረቀ ዘቢብ በውኀና በጽዋ እየታሸ ለቈራቢዮች የሚሰጠው የክርስቶስ
ደም ዘቢብ ይባላል) ብቻ ይፈቀዳል።

⛪️፪. #የቅዳሴ_ጠበል_ሥርዓት
🔔 የቅዳሴ ጠበል ይዞ አለመውጣት፤
🔔 በቅዳሴ ጠበል ፊትን አለመዳበስ እንዲሁም  እንዳይፈስ መጠንቀቅ፤

⛪️፫. #የአለባበስ_ሥርዓት
🔔 ሕፃናት ልጆችን ክርስቲያናዊ አለባበስ ማልበስ
🔔 ሴት ልጅ ረጅም ቀሚስና ነጠላ ትልበስ
🔔 ሴት ልጅ ፀጉርዋን በነጭ ሻሽ ትሸፍን፤ ሱሪም አትልበስ
🔔 ወንድ ልጅ አግባብ ያለው ሱሪ፣ ነጠላና እጀ ሙሉ የሆነ ልብስ ያድርግ
🔔 ማንኛችንም ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ ሜካፕ፦ ዊግ፣ ጥፍር ቀለም፣ ሊፒስቲክና ሌሎችንም ነገሮች አለመጠቀም
👉“ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው።” ዘዳ. ፳፪፥፭
👉“ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን? ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት” ፩ኛ ቆሮ. ፲፩፥፲፫-፲፬

⛪️፬. የካህናትን፣ የወንዶችንና የሴቶችን መግቢያ በር መለየት፤

⛪️፭. ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር ስንል፦
🔔 ጫማችንንና ካልሲያችንን ከግቢ በር ማውለቅ (በፌስታል መያዝ)
🔔 የቤተ ክርስቲያናችንን ልዩ መዓዛ ለመጠበቅ መጥፎ የሰውነት ጠረንን ማጥፋት (የግል ንጽሕናን መጠበቅ)
“የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ” ዘፀ. ፫፥፭

⛪️፮. ሴት ልጅ ጠበል በቅዳት እና መዝጋት መክፈት፤ እምነት ቆፍሮ ማውጣት ስለማትችል ወንዶችን ትጠይቅ፤

⛪️፯. ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ፣ ከእመቤታችን አማላጅነት፣ ከቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ ከጻድቃን ሰማዕታት እንዲሁም ከቅዱሳን አባቶቻችን በረከት እንድናገኝ፤ ቤተ ክርስቲያን እንዳንሄድ እንቅፋት ከሚሆንብን ነገሮች፤ ከቡና፣ ጫት፣ ሲጋራ፣ ስጋር፣ ሀሜት፣ ዝሙት፣ ሙስና፣ በሀሰት ከመመስከር እንዲሁም ከማንኛውም መጥፎ ነገሮች ራስን ማራቅ ይገባናል።
“የእግዚአብሔርን እና የአጋንንትን ጽዋ አንድ አድርጋችሁ መጠጣት አትችሉም።” ፩ኛ ቆሮ. ፲፥፳፩

••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
@eotcbete
@eotcbete
@eotcbete
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
በፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ታላላቅ መመህራንና ዘማርያን ተጋብዘው ከ20-22 በተዘጋጀው ጉባኤ እንድትሳተፉ ቤተክርስቲያናችን ጥሪ ታቀርባለች እንዲሁም በነገው እለት ማለትም መስከረም 21 / 2014 አ.ም የእመቤታችን ንግስ ስለሆነ እንዳትቀሩ እያልን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን

አድራሻ አስኮ ብርጭቆ ሰፈር
ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን💛💚
2024/05/12 14:26:17
Back to Top
HTML Embed Code: