Telegram Web Link
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ pinned «#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ምእራፍ 9 ክፍል 57 መግቢያ:-በዚህ ምእራፍ ውስጥ ከ ቁጥር 1-6 ቅዱሱ ሐዋርያ ጳውሎስ ለወገኖቹ እስራኤል ስለመጸለዩ ከ ቁጥር 7-13 ብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ስለመነገሩ ከ ቁጥር 14-24እግዚአብሔር በምህረትም ሆነ በመዓት ላይ ስልጣን ያለው መሆኑን ከቁጥር 25-26አሕዛብ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመባላቸው ከ ቁጥር 25-33 ከእስራኤል ብዙዎች ኦንደማይጸድቁ ስለመነገሩ ሮሜ 9…»
ጰራቅሊጦስ

መንፈስቅዱስ(παράκλητος)

ጰራቅሊጦስ  ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የአንዱ አምላክ  እግዚአብሔር  ሦስተኛው አካል(person )ነው።
መንፈስቅዱስ በባህሪው መንጽዔ(የሚያጸና)  እና መንጽሒ(የሚያነጻ) ሲሆን ለእግዚአብሔር  ሥላሴ እስትንፋሳቸው ነው። እግዚአብሔር  መንፈስቅዱስ አንድም ከሳቴ ምስጢር  ወይንም  ምስጢር ገላጭ በመባል ይጠራል።
መንፈስቅዱስ  የእግዚአብሔር  እስትንፋስ (ህይወት )ነው። በአብና በወልድ ውስጥ ህልው ሆኖ ይኖራል።
Holly sprit is  also called  peraclitos and
he is the third person of the one the Almighty  God
መንፈስቅዱስ  ኀያል እግዚአብሔር በመሆኑ የእግዚአብሔር  ነገር መመርመር የሚችል  ብቸኛ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ብዙ መጠሪያዎች አሉት ከነዚህም መካከል
፩.መንጽሒ (የሚያነጻ)ሲሆን  ሰዎችን ከኀጢአት  ጠብቆ የሚያነጻ  ብሎም  ሰዎች በኀጢአት ከ ወደቁ በኋላ ንስሐ ሲገቡ በልባቸው ታትሞ ይቅር በማለት ያነጻቸዋል።
፪.መጽንዒ(የሚያጸና) በሁኔታዎች  በችግሮችና   በተግዳሮቶች ውስጥ  ሰዎችን አጽንቶ እግዚአብሔርን እንዳይክዱና በምልአት እንዲገልጡት  የሚረዳቸው ነው።
፫.ከሳቴ ምስጢር(ምስጢርን የሚገልጥ)
ከእግዚአብሔር  የሆነውን ምስጢር  እውቀት  እንደ ፈቃደ እግዚአብሔር   ይገልጣል። ሰዎችም በዚህ መንፈስ ተነሳስተው  ትንቢትን ይናገራሉ።
፬.ናዛዚ(የሚያረጋጋ) የሚያጽናና ነው
“እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።”
  — ዮሐንስ 16፥7
፭.መስተስርይ (ይቅር ባይ)ፍጹም አምላክ  በመሆኑ ኀጢአትን  ሁሉ ይቅር ይላል።
በዓለ  ጰራቅሊጦስ  የተለያዩ አይነት  ስያሜዎች  አሉት እነርሱም
በዓለ  ጰራቅሊጦስ
በዓለ ጰንጠቆስጤ (50ቀን)
በዓለ ሀምሳ
በዓለ ሰዊት(የአይሁድ  በዓል የነበረ)በዚያን እለት የሚከበር
መንፈስቅዱስ  በሐዋርያት  መካከል ጌታ ኢየሱስ  ካረገ ከ 10ቀን በኋላ  በመካከላቸው  በእሳትና  በነፋስ  አምሳል  ተገለጠ። የመንግስትን ወንጌል እንዲያስፋፉ 72 ቋንቋዎች ተገለጡላቸው። በዕለቱም በ ረድኤት ወ በ ኀይለ መንፈስ ቅዱስ  በመክበራቸው በስብከት 3000 ምዕመናንን ለጌታ ጨምረዋል።
መንፈስቅዱስ  አንድ የህይወት  ምንጭ ሲሆን የተለያየ  ጸጋ ለሰዎች ይሰጣል ።
ሐዋርያት  በዚህ ቅዱስ መንፈስ ከከበሩ በኋላ ወደ ጾም  ገቡ  አለምንም በወንጌል ማጥለቅለቅ ጀምረው እስከ ፍጸሜያቸው ድረስ አድርገውታል።
እግዚአብሔር  መንፈስቅዱስ  በቤተክርስቲያን  ውስጥ ያለ የነበረ የሚኖረውም እርሱ ከአብና ከ ወልድ ጋር  እርሱ  ነው።
ክብርና አምልኮ ውዳሴ ከምድር እስከ አርያም  ድረስ ለእርሱ ለመንፈስቅዱስ

ይሁን።

አሜን

ዲያቆን የኋላሸት

ባህርዳር


2015 ዓ.ም
Glory to the Hollysprit

እንኳን አደረሰን
Audio
ዘማሪ ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ
#ሐዋርያት_ተባበሩ
እንኳን አደረሳችሁ
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ
ከ 3 ዓመት በፊት በባህርዳር ጽርሐ ጽዮን መንፈስቅዱስና እመቤታችን
ቤተክርስቲያን
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (ኢየሱስ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ)
መንፈስቅዱስ እና አሰራሩ በክርስቲያን ኅብረት ውስጥ ምን ይመስላል?
መንፈስ ቅዱስ (holy sprit) በቤተክርስቲያን(ኤክሌሲያ) ውስጥ የሚሰራው ትልቁ ኀይል እርሱ ነው። በዘመነ ሐዋርያት ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን አጋዥ መከታ አድርገው ክርስትናን በአለም ዙሪያ ሰብከዋል። ሐዋርያት ወደአገልግሎት ገና ከመግባታቸው በፊት መንፈስቅዱስን ተቀብለዋል ከተቀበሉም በኋላ ፍሩሀን፣ድንጉጻን፣ የነበሩት እጅግ ጽቡዐን(የጸኑ)እና የተጉ ሆነዋል።(ሐዋ 2:1-47) በቅድስት ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስን አሰራር ስንመለከት በጉልህ የምንመለከተው የቅዱስ እስጢፋኖስን ጉዳይ ነው።ቅዱስ እስጢፋኖስ በአይሁድ
መካከል የጸና ሆኖ የመሰከረው መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ መንፈስቅዱሳ አድሮ ነው።
•ምንም እንኳን አይሁድ እስጢፋኖስን ገድለው ክርስትናን ሊያጠፉ ቢያስቡም የክርስትያን ማኅበር አንድ ላይ በመሆን ለስብከት ተሰማርተዋል።(ሐዋ 8) •በዚህ የተቀደሰ ኅብረት ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አብራ ነበረች ክብር ይግባትና።
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ምእራፍ 9 ክፍል 57 መግቢያ:-በዚህ ምእራፍ ውስጥ ከ ቁጥር 1-6 ቅዱሱ ሐዋርያ ጳውሎስ ለወገኖቹ እስራኤል ስለመጸለዩ ከ ቁጥር 7-13 ብሉይ ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ስለመነገሩ ከ ቁጥር 14-24እግዚአብሔር በምህረትም ሆነ በመዓት ላይ ስልጣን ያለው መሆኑን ከቁጥር 25-26አሕዛብ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመባላቸው ከ ቁጥር 25-33 ከእስራኤል ብዙዎች ኦንደማይጸድቁ ስለመነገሩ ሮሜ 9…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 58
ሮሜ 9:5
አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።
አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና
አባቶች በስጋ ከእስራኤል መሆናቸውን ለማመልከት አባቶች ለእነርሱ ናቸውና አለ።
ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥
ጌታችን ከእስራኤል መወለዱን ሲያመለክት ነው።
እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።
ከእስራኤል በስጋ የተወለደው ኢየሱስ በክርስቶስ የባህርይ አምላክ ወይም ጌታ መሆኑን ጌትነቱ ደግሞ የዘላለም መሆኑን አስረግጦ ለእስራኤል ተናገረ።አይሁድ የጌታችንን የባህርይ አምላክነት አላመኑም ነበርና በግልጽ ነገራቸው።
ሮሜ 9:6
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም። እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም።
የእግዚአብሔር ቃል እብለትና ውሸት የሌለበት የማይሻር መሆኑን ያመለክታል።
እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤
በስጋ ከእስራኤል የተወለዱ ሁሉ እስራኤላውያን አለመሆናቸውን ተናገረ ይህም የሆነው እስራኤል ማለት ህዝበ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ሁሉም እስራኤላዊ በእግዚአብሔር ባለማመኑ እስራኤላዊ እንደማይባሉ ይህ የተወደደ ቅዱስ ሐዋርያ ነገረን።......ይቀጥላል

@eotchntc
“በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”
  — ራእይ 12፥7
ሰኔ ሚካኤል
የሰኔ ሚካኤል በዓለ ንግስ በቢሾፍቱ ከተማ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

12/10/2017 ዓ.ም

@eotchntc
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
አስደናቂ ተአምር ያለባት እና በአህዛብ የተከበበችዉ በቂልጦዋ ሎዛ ማርያም
ሰኔ 21ን ከጓደኞቼ ጋር በዛ አከበርን
ይሄን video ለማየት
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VnnnRBTXaoQ?si=Ib1aPotJjENZUDp0
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
🚨ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
Forwarded from 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg
ሐዋርያዊ መልሶች በቴሌግራም🥰

❤️ ለኦርቶዶክሳውያን ምርጥ ቻናል ነዉ
join በማለት ቤተሰብ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።የመፀሃፍ ቅዱስ ጥናት፣ዶግማ ኤና ቀኖና እና ብዙብዙ ትምህሮችን ያገኙበታል᎓᎓
2025/07/03 14:39:25
Back to Top
HTML Embed Code: