Telegram Web Link
Forwarded from Gech
የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ መልእክት

"በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።”  (ማር 1፥9 )

አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ የመወለዱና በዚህ ምድር ሠላሳ ሦስት ዓመት የመኖሩ ዋና ዓላማ ሰውን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ለማዳን ነው። በመወለዱም አምላክነቱን ሳይለቅ የሰውን ባሕርይ ባሕርይው አድርጓልና ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም እንደሰውነቱ እየታዘዘ እንደ አምላክነቱ ታምራት እየሠራ በየጥቂቱ አደገ። "ልኅቀ ከመ ሕፃን እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝማድኢሁ ወለይእቲ እሙ ድንግል"  ዕድሜው ሠላሳ ሲሞላ የተነገረው ትንቢት፣ የተቆጠረው ሱባዔ ይፈጸም ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ "ነስሑ ወእመኑ እስመ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት" እያለ የሚሰብከውን ዮሐንስን በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲያጠምቀው ጠየቀው።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ግን አስቀድሞ በነበረው ትምህርቱ "ከእኔ በኋላ የሚመጣውን የእግሩን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ ነው" እያለ እንዳስተማረ ጌታችን ወደ እሱ ቀርቦ አጥምቀኝ ቢለውም "አነ እፈቅድ እምኀቤከ እጠመቅ" በማለት ደቀ መዝሙር በመምህሩ ይጠመቃል እንጂ እንዴት መምህር በደቀመዝሙሩ ይጠመቃል ሲል ራሱን ዝቅ በማድረግ ከለከለው። ጌታችን ግን መልሶ፦ "አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።" ያን ጊዜም ቅዱስ ዮሐንስ ሊያጠምቀው ፈቀደለት (ማቴ3፥15)። ጌታችንም በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ጥር ፲፩ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት በሠላሳ ዓመቱ ተጠመቀ። ቀዳማዊ አባቱ አብ በደመና ሆኖ "ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር- የምወደው ልጄ ይህ ነው" አለ። መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረደ። አንድነት ሦስትነትም ተገለጠ።

በዮርዳኖስ መጠመቁ እንደ እንግድዓ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የሆነ አይደለም። በብሉይ ኪዳን አባታችን አብርሃም በኮሎዶጎሞር ድል ቀንቶት ሲመለስ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ካህኑ መልከጼዴቅን አግኝቶት ነበር። ካህኑ መልከጼዴቅም ኅብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ በማለት ተቀብሎታል። በኋላ ዘመን እስራኤልም ወደ ተስፋይቱ ምድር የገቡት ይህን የዮርዳኖስ ወንዝ ተሻግረው ነበር። ነቢዩ ኤልያስም ወደ ተዘጋጀችለት ብሔረ ሕያዋን ያረገው ዮርዳኖስን ወንዝ በመጎናጸፊያው ከፍሎ ተሻግሮ ነው ።

እነዚህና ሌሎች በብሉይ ኪዳን የተደረጉ ነገሮች በሐዲስ ኪዳን ስለሚሆነው የጥምቀቱ ነገር ከሩቅ ማሳያዎች ነበሩ። አብርሃም የምእመናን፣ ኅብሰተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ የጠበቀው ካህኑ መልከጼዴቅ ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን እንካችሁ ብሎ የሰጠን የክርስቶስ፣ ዮርዳኖስ ደግሞ የጥምቀት ምሳሌዎች ናቸው። እስራኤልም ከባርነት ተላቀው ሲወጡ የተስፋይቱን ምድር ከነዓንን ያገኟት ዮርዳኖስን ተሻግረው መሆኑ የሐዲስ ኪዳን ምእመናን በጥምቀት በኩል የክርስቶስ አካል ሆነው ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያዩ የመሆናቸው ምሥጢር ነበር። ከዚህም ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት "ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገባ ድኅሬሁ" በማለት ዮርዳኖስ አምላክን ለማጥመቅ የተመረጠ ወንዝ ስለመሆኑ ትንቢት ተናግሮለታል። ጌታችን የተጠመቀበት ቦታም ዮር እና ዳኖስ የሚባሉ ወንዞች በሚገናኛቸው ላይ ነው። ሕዝብና አሕዛብ ተጠምቀው አንድ ሆነው በአንድ መጠሪያ ክርስቲያኖች ተብለው የሚጠሩ ናቸውና።በዚህም መለያየት ጠፍቷል።

ውድ ልጆቻችን፦ የጌታችን ወደዚህ ምድር መምጣትና መጠመቅ ብዙ ትምህርትና ተአምራት የታየበት ነው። ዋና ዓላማው አዳምን በተንኮል አሳስቶ ከልጅነት ጸጋ ያጎደለውን ጠላት ዲያብሎስን ድል ነሥቶ ወደ ቀደመው የልጅነት ጸጋው መመለስና አዳምና ልጆቹ ድል የሚነሡበትን መንገድ ማሳየት ነው። ሰይጣን ድል ከተነሣባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ የጌታችን ጥምቀት ነው። የአዳም የዕዳ ደብዳቤ የተደመሰሰው በጥምቀቱ ነውና። በሌላም በኩል ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሔዶ ትሕትናን አስተምሮናል። ወደ ዮሐንስ ሔዶ መጠመቁም ነገሥታትም ቢሆኑ ምእመናንም ቢሆኑ ወደ ካህን ሔደው እንዲጠመቁ ሥርዓት ሲሠራ ነው። ባዕለጸጋ እና ድሃ እኩል በሚያገኙት በውኃ መጠመቁም ጥምቀት የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ ናትና መንግሥተ ሰማያት በገንዘብ ብዛት የማትገዛ ለሁሉም የተሰጠች መሆኗን ሲያሳይ ነው።

በጥምቀቱ ትሕትናን ገንዘብ ብታደርጉ ታላቅነትን ታገኛላችሁ ሲል አስተምሮናልና ትሑት ልቡናን ገንዘብ ማድረግ ይገባል። ይህንም የትሕትና መምህር አምላካችን በትሕትና ወደ ዮሐንስ ተጉዞ አሳይቶናል። በጥምቀቱ መለያየት የጠፋበት ነው። ሕዝብና አሕዛብ መባባል አሁን የለምና። "አንተም እንዲሁ አድርግ..." እያለ በወንጌል የሚያስተምረን አምላክ እኛም ከመካከላችን መለያየትን አርቀን ፍቅርን አንድነትን አጽንተን መኖር ይገባል። መልከ ጼዴቅ ለአብርሃም ኅብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት ይዞ መታየቱም ከጥምቀት ባሻገር ምእመናን እንዲቆርቡ ማስተማሩ ነውና ከሁሉም በላይ ይህን በዓል ስታከብሩ በዓላቶቻችን መጽደቂያ እንጂ መመጻደቂያ እንዳይሆን በምግብና መጠጥ ብቻ ሳንይሆን ክቡር ሥጋውና ደሙን በመቀበል፤ ከዘፈንና ከዳንኪራ ርቃችሁ በመዝሙርና በምስጋና እንድታከብሩ እናሳስባችኋለን።

በመጨረሻም የተወደዳችሁ ውድ ልጆቻችን ኾይ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልን አሁን ዓለማችንም አገራችንም ሰላም ያጣችበት ዘመን ላይ ነንና የአዳምን በደል ይቅር ብሎ የዕዳ ደብዳቤውን አጥፍቶ እውነተኛ ሰላሙን የመለሰለት የሰላም አምላክ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ሰላምን ለአገራችን ይሰጥልን ዘንድ ወደ አምላካችን እንድትጸልዩ አሳስባችኋለሁ። መልካም በዓል!!

       አባ ፊልጶስ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (የኋላሸት(ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ))
“ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤”
  — 1ኛ ጴጥሮስ 3፥21
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (የኋላሸት)
ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
² ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
³ የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።
⁴ ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
⁵ እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
⁶ አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
⁷ ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
⁸ አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
⁹ አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦
¹⁰ ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
¹¹ ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (የኋላሸት)
Forwarded from ሐመረ ኖኅ(የኖኅ መርከብ) (የኋላሸት)
ቃና_ዘገሊላkana_zegelila_የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_መዝሙር360p.mp4
6.3 MB
Track 8
Unknown Artist
ገ/ዮሐንስ "የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም"
የዮሐንስ ወንጌል ትርጉም

ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።

11.“የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።”

¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
ዮሐንስ ወንጌላዊ ስለጌታችን እውነተኛ ብርሃንነት በሰፊው ከመሰከረ እና ይህም ብርሃን አወጣጡ ከዘለዓለም የነበረ እንደገናም ወደ ዓለም የመጣ መሆኑን በግልጽ ነገረን።

ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም

ዓለም እና መላዋ የተፈጠሩት ቃል በተባለው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው እግዚአብሔር ወልድ የተፈጠሩ መሆኑን እንረዳ ዘንድ ይህንን ጻፈልን።
ይህም ሲባል የሰውን ልጅ ጨምሮ መልካም ነገር ያደሮግ ዘንድ በክርስቶስ ተፈጥሯል።

“እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”
— ኤፌሶን 2፥10
በምድር ላይ ያሉት ሁሉ በእርሱ ኀይል ስልጣን ገዢነትና አለቅነት ተከውነዋል።

“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት
በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”
— ቆላስይስ 1፥15-16

ዓለሙም አላወቀውም ማለቱ የሰው ልጆች በተለየ እስራኤል ዘስጋ ጌታችን ከእመቤታችን ስጋን ነስቶ በመዋዕለ ስጋዌው በምድር እየተመላለሰ ትምህርትን ሲያስተምርና ድዊን ሲፈውስ እርሱ እግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አለመረዳታቸውን ይነግርባቸዋል።

ማር ዮሐንስ የተባለ የቤተክርስቲያን ሊቅ እንዲህ ይላል
"ይህንም ስለሰነፎች ሰዎች ይናገራል። ፍላጎታቸው ምድራዊ የሆነ ሰዎች ጌታችንን አላወቁትም። የጽድቅ ሰዎች ግን ሰው በሆነ ጊዜ አውቀውታል። ይላል።

11.“የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።”


በስጋ ወደ ሚዛመዱት ወደ እስራኤል ዘስጋ መምጣቱንና እስራኤል ዘ ስጋ ግን ሊቀበሉት አለመቻላቸውን ነገረን።
ጌታችን ከእስራኤል ዘስጋ ከነገደ ይሁዳ የተወለደ ፍጹም ሰው የሆነ ፍጹም አምላክ ነውና

“እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።”
— ማቴዎስ 2፥5-6
የዘር ሀረጉን ስንመለከት ወደ ይሁዳ ነገድ መሆኑን እንረዳለን።

“የፋሬስ ልጅ፥ የይሁዳ ልጅ፥ የያዕቆብ ልጅ፥ የይስሐቅ ልጅ፥ የአብርሃም ልጅ፥ የታራ ልጅ፥”
— ሉቃስ 3፥34

የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።”

የገዛ ወገኖቹ ያለው እስራዔል ዘስጋን ነው።
ጌታን ወደ አምስት ገበያ ህዝብ እንደተከተለው የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ህዝብ አንዳንዱ ህብስት አበርክቶ ማብላቱን አይተው ለሆዳቸው፣ ድዊ እንደሚፈውስ ሰምተው ከህመማቸው ለመዳን፣ ውበቱን ለማየትና እንደ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ሀሳብ ደግሞ ከትምህርቱ ከቃሉ
ከአፉ ስህተትን ለመልቀም መሆኑን ይናገራሉ። ነገር ግን ጥቂቶች 120 ቤተሰብ ብቻ ጌታን በፍጹም ልባቸው አምነው ወደው ተቀበሉት በዚህም ምክንያት ዮሐንስ አልተቀበሉትም አለ

ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
¹³ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።


ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤


ለተቀበሉት ሁሉ ግን ማለቱ 120ው ስለመቀበላቸው ራሱንም ጭምር ጠቅልሎ ነው

ይቀጥላል
የዝርወተ አጽሙ ለጊዮርጊስ በዓል
በባህርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አስተርእዮ/_ephiphany

“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥9

በገሃድ መታየት ወይንም መገለጥን የምናወሳበት እለት
ይህ እለት ሁለት አይነት ድርብ በዓል የሚከበርበት ነው

1.የጌታችን በትህትና መገለጥ በኀይልና በክብር ይነገርበታል።

2.የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እረፍት በዓል በድምቀት ተከብሮ ይውላል።

መገለጡ ደግም ኀጢአት የሆነውን ዓመጽን ለማጥፋት ነው።

1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።
⁵ እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


የጌታችን መገለጥ በትህትና የሆነና በሥጋ ማርያም የተከወነ ነው።
በመገለጡም በሰዎች ዘንድ ህያው የታወቀ
በመላእክት ዘንድ የታየ ሆነ።

“እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16

1 Timothy 3 ግዕ - 1 ጢሞቴዎስ
16: አማን ዐቢይ እስመ ምክሩ ለዝንቱ ጽድቅ፦
ዝኬ ዘአስተርአየ በሥጋ፣
ሰብእ ወጸድቀ በመንፈስ፣
ወአስተርአዮሙ ለመላእክት፣
ወሰበክዎ ውስተ አሕዛብ፣
ወተአመነ ውስተ ዓለም፣
ወዐርገ በስብሐት።

ጌታ በመገለጡ ምክንያት ካለመታዘዛችንና ከመውደቃችን ነጻ አደረገን

ቲቶ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
⁴ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥
⁵ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤

መገለጡም ይሁዳ ከተባለው ነገድ ነው።

“ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም።”
— ዕብራውያን 7፥14

የተገለጠው ደግሞ ህይወት የሆነ ነው።
ህይወትነቱ ደግሞ የዘላለም ነው።

“ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥2

ሁለተኛው ደግሞ በዓለ እረፍታ ለቅድስት ድንግል ማርያምን የምናስብበት
ይሆናል።
2024/06/02 18:31:23
Back to Top
HTML Embed Code: