Telegram Web Link
#ለአዲሱ አመት 2017በአዲስ አቀራረብ እንቀርባለን
እግዚአብሔር ቢረዳንና ብንኖር
ተከታታይ በሆኑ እና መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች
የቤተክርስቲያን ሥርአት አስተምህሮዎችና በሌሎች ጉዳዮች እንቀርባለን።

እግዚአብሔር ቢረዳን በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች ማገልገል የምትፈልጉ ማለትም ኦሮሚኛ ትግሪኛ እና ሌሎችም በክብር እንቀበላለን ።@Yehuala_zemessiah
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሁን።

#ሐመረ_ኖኅ
@eotchntc
👍6
አንብቤ የወደድኩትና የተባረኩበት


የጴንጤዋ ማርያም

የ ዘጠኝ ወር ልፋት እንዲሁ “አትወልጂም“ በምትል በአንዲት ቃል ሲጠቀለል ምን ይባላል??እድሜ ልኬን ተስዬ ለምኜ ያገኘኋት የማህፀኔ ፍሬ እንደ እፉኚት ከወለድሻት ትገልሻለች መባልስ ምን ማለት ነው??ፈጣሪስ ገና ወጥታ እሹሹሩ ካላልኳት፤ ካላጠባኋት፤ካልሳምኳት፤ካልታቀፍኳት ከገዛ ልጄ ጋር እንዴት ፀብ ውስጥ ይከተኛል???

ለምን ይሄ ሁሉ መከራ በኔ እንደመጣ ባላውቅም እግዚአብሔር ብዬ የለመንኩት አምላክ እንደሌለ ግን አረጋግጫለሁ።  ቢኖርማ ለምን ሰጥቶ ይነሳኛል??ለምን ሰምቶ ዝም ይለኛል??ደግ ከሆነስ ነብሴና ልጄን ሚዛን ላይ አስቀምጦ እንዴት ይተወኛል??ጨካኝ ቢሆን እንጂ....

ሲስ (ባሌ) ጠዋት ዜናውን ከሰማ ጀምሮ ትንፍሽ አላለም።አላማረረም።አላለቀሰም። ግን ደሞ ከኔ በላይ እየታመመ እንዳለ ፊቱ ጥቁር ብሎ በመሀል በመሀል ከፊቱ ባለች ጠባብ መስታወት ያየኛል።ከኋላ የተቀመጥኩት ጎኑ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ሕመሙን እንዳልጨምርበት ብዬ እንጂ ከአጠገቡ ስርቅ አይወድም።ያለወትሮው መኪናዋን ቀስ እያለ ነው ሚነዳት ሆስፒታል እንድንደርስ ሁለታችንም አልፈለግንም።ያላየናት ልጃችንን ገድለን እራሳችንን ለማትረፍ የምንጣጣር ራስ ወዳድ መሆናችን ተሰምቶን ይሁን?...አላቅም። ብቻ ግን የቀጠሯችን ሰዓት ደርሷል ሰዓቱ 9 ሰአት አናቱ ላይ ይላል።ከፊት ደሞ ከእንጦጦ ኪዳነምህረት አስቀዳሽ ምእመናን ቅዳሴ ጨርሰው ከቤተክርስትያኗ እየወጡ መንገዱን ዘግተወታል።ፍዝዝ ብዬ የሚተራመሠውን ሕዝብ እያየሁ የመኪናችን መስታወት በስሱ ሲንኳኳ ብንን ብዬ ዞርኩ።ጭርጭስ ያሉ አሮጊት በመስታወቱ አጮልቀው እያዩኝ የማልሰማውን ነገር እየለፈለፉ ሳይ መስታወቱን ዝቅ አደረኩት

ልጄ እስከ ሽሮሜዳ አድሺኝ እባክሽ እግሬ እምቢ ብሎኝ...

ምንም ሳላወራ በሩን ከፍቼላቸው ተጠጋው። ሲስ ሁኔታውን ከማየት በቀር መልስ አልሰጠም።እማማ መላእክቱን እየጠሩ ይመርቃሉ...

ሚካኤል አለሁ ይበልሽ..እመቤቴ በሰላም ትገላግልሽ...የማህፀንሽን ፍሬ እዪ....ወልደሽ ሳሚ....የጭንቅ አማላጇ ትቅረብሽ....ከለላ ትሁንሽ....ምጥሽን ታቅለው..

እማማ ይተውኝ!!እኔ ለልጅ አልታደልኩም!!ልጄን በማህፀን ገድዬ የቀበርኩ ነኝ!!እማማ ፈጣሪዬ አሳይቶ ነሳኝ(ሳላውቀው የሚታገለኝ እንባ ከአይኔ አምልጦ ጉንጬ ላይ ተንደረደረ።

ውይ ውይ እኔን አፈር ይብላኝ።ይቅር በይኝ ልጄ እኔማ መመረቄ ነው የሆድሽን መች አውቄ? በይ አይዞሽ አታልቅሺ እንዲህ መርቄሽማ ድንግል አታሳፍረኝም ከሆስቢታሉ በፊት አንድዜ ደጇን እርገጩ እሷ መላውን ታውቃለች በሉ እንመለስ...

እማማ እግዜር ይስጦት ግን አይሆንም እኛ በጌታ ነን ሃይማኖታችን አይፈቅድም በምናቀው ተማፅነናል በዛላይ ሰዓቱ ረፍዷል  ትንሽ ከቆየን ሚስቴን አጣታለሁ!!

አይ እንግዲ በጌታ የሆነ በናቱ ቢማፀነው ምን ይከፋል??እሺ በሉኝ.. በተአምሯ  ትደሰታላችሁ  በሱባኤዋ አታሳፍራችሁም ስላችሁ??

እማማ ይውረዱ ሽሮሜዳ ደርሰዋል!!(ሲስ ብስጭት ያለ ይመስላል እንዲህ ሰው አውርቶ አያውቅም።ጴንጤ ብሆን እንኳ እማማ ያመጡትን ሀሳብ ተቀብዬ ለመጨረሻ ጊዜ ልሄድ ፈልጌ ነበር ባምጥ ማርያም ማርያም ይባል የለ?ጨንቆኝ ብሄድ ምን ችግር አለው??በዚህ ሰዓት ማንም ምንም ቢል ልጄን ለማዳን ምንም እሆናለሁ...

ሆስፒታል ደረስን።ነብሴን መርጩ ልጄን የምጥልበት ሰርጀሪ ክፍል ለመግባት እግሬን እየጎተትኩ ሳለሁ ግን እግርና እግሬ መሀል ቀጭን ፈሳሽ እየተንሸራተተ ተሰማኝ።ትንሽ ቆይቶ ሆዴን ሲቆርጠኝ በትንሹ አቃሰትኩኝ።ጩኸቴ ጨመረ።ከዛ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ ከሰርጀሪ ክፍል በአልጋ እየጎተቱኝ ማዋለጃ ክፍል ሲያስገቡኝ፤ብዙ ሴቶች ከበው እየጮኹ ግፊ ግፊ ግፊ እያሉ ሲያበረቱኝ፤ሳቃስት፤ሳለቅስ፤ስወራጭ ማርያም ማርያም ሲባል በደቂቃወች ውስጥ የህፃን ድምፅ ስሰማ ብቻ ትዝ ይለኛል።በእውኔ ይሁን በሕልሜ ታሪክ ተቀይሮ ልጄን ሲያሳቅፉኝ ባለማመን እያየኋቸው የሞት ሞቴን አወራሁ....

እንዴት??እንዴት ሆነ ዶክተር??አትወልጂም ተብዬ??(ዶክተሩ ሚመልሰው ጠፍቶት አይን አይኔን ሲያየኝ በሩ ተከፍቶ ሲስ እየሮጠ ገባ ማን እንደሆነ ባላቅም በእልልታ ታጅቦ ሲቀርበኝ እኛን የመረቁኝ አሮጊት ከስሩ ብቅ ሲሉ አየኋቸው።የእናትነት ፈገግታቸው እያበራ...

አይ አንቺ...አታሳፍሪኝምኮ!!ቀየርሽው አደል!!እሺ አልሺኝ አደል??ሰማሺኝ አደል??አማላጄዋ.. እናቴዋ.. የኔ ገራገር.. እመ ልቤ.. እሰይ እሰይ እሰይ...(እማሆይ ግንባሬን እየሳሙኝ በመሀል እልልታቸውን አቀለጡት

እማማ እንዴት መጡ ግን??

ተአምሯን ላይ ነዋ!!እንደምታደርገው አውቃለሁኮ...አየሽ ዳቤዋን የቀመሰ.. ይጣፍጥ የለ??(እኔና ሲስን አፈራርቀው እያዩን

የምን ዳቤ እማማ? መች ያቀመሱንን??

አይ ልጄ ተው አትዋሽ ከኔ ብትሰውር ከሷ አይሰወርም።ልጄ ስታለቅስብኝ አንተም እንቢ ስትለኝ ከደብሯ  ቆርሼ የያዝኩትን ዳቤ..

አዎ እማ በልቼዋለሁ!!ሲስ ትክክል ናቸው...አንቺ ካለሽ እቺን ድርጊልኝ፤የተሳሉሽ የደረሰላቸው እውነት ከሆነ አሁን ለኔም ድረሺ፤አዋልጂኝ ቅረቢኝ ብዬ እየተሣልኩ እማማ ጥለው የወጡትን ዳቤ በልቻለሁ።ሲስ እሷ ናት የሰማቺኝ ኪዳነምህረት ናት ያዋለደቺኝ(ሳቅና እንባ የቀላቀለ ፊቴን እያየ ሲስ መጥቶ እቅፍ አደረገኝ እማማ እልልታቸውን እያቀለጡት

አየሽ እንዲያው እኛ ተለያየንባት እንጂ "የጰንጤዋ ማርያም የኦርቶዶክስዋ ማርያም ብሎ ነገርኮ የለም"ማርያም እናቴ ብሎ ለጠራት የሁሉ ናት።ለተማፀኗት ለተማመኗት አደለም ላልጠሯት ለማያውቋትም አማላጅነቷን ለማያምንም ትደርሳለች።ለውሻም ትራራለች።አንቺማ ጣድቋን ቆርሰሻል በላኤሰብኮ በስሟ ጥርኝ ውኃ ሰጥቶ ነው የዳነባት።ቆይንጂ ደሞ...እናንተ ቅድም እናት ብሆን አደል አዝናችሁ በመኪና የሸኛችሁኝ??እናንተ ያዘናችሁልኝ ልጇ አምላኳ የሆነ ድንግል ብትጠይቀው እንዴት እምቢ ይላል?ብትማልደው እንዴት ይጨክናል?? ኃጢአታችን ከአምላክ ቢከልለን በማርያም በኩል ግን ይታረቀናል።"ስለ ሔዋን የገነት በር ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን"የተባለውኮ ለዚህ ነው።የተደመደመ ተስፋ በአማላጅነቷ እንደሚለመልም ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሲነግረን እኮ ነው።እየውልሽ እኛ ጎራ ፈጥረን እንጂ እሷኮ ለነውራችን መጋረጃ፤ለእንባችን መሀረብ፤ ለመንገዳችን ስንቅ፤ለቤታችን ውብት፤ለጭንቃችን ደራሽ ናት።እንግዲህ በሉ እኔ ወደቤቴ ልሂድ...

እማማ መች ነው ተመልሰው ሚመጡት??(በስስት እያየኋቸው) እንግዲህማ እናት አትለፋም ልጅ ነው እንጂ ሚመጣው።እዚያው ኪዳነምህረት ደጇ ላይ ብትመጪ እኔንም ወለላዬንም ታገኚናለሽ (ከንፈራቸውን ሸብበው በስሱ ጥርሳቸውን እያሳዩኝ

እማ ማርያምን መጣለሁ!!አልኳቸው። ከልቤ ነው ልጄንም"የማርያም"ብያታለሁ። 

@ewuntegna
@ewuntegna
6👍3
Audio
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ pinned «#ለአዲሱ አመት 2017በአዲስ አቀራረብ እንቀርባለን እግዚአብሔር ቢረዳንና ብንኖር ተከታታይ በሆኑ እና መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የቤተክርስቲያን ሥርአት አስተምህሮዎችና በሌሎች ጉዳዮች እንቀርባለን። እግዚአብሔር ቢረዳን በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች ማገልገል የምትፈልጉ ማለትም ኦሮሚኛ ትግሪኛ እና ሌሎችም በክብር እንቀበላለን ።@Yehuala_zemessiah እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሁን።…»
Audio
#ግሩም
የደብረታቦር መዝሙር
ቀሲስ አሸናፊ
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
#ማቴ_17
ወደረጅም ተራራ ይዟቸው ወጣ
እንኳን አደረሳችሁ
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (Yabsira)
#የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም
ትርጉም


አስተያየትና ለጥያቄ

@yehwi
@eotchntc
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (ኢየሱስ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ)
✞ማርያም አርጋለች✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
✞ማርያም አርጋለች✞

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች

የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
አዝ= = = = =
ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
አዝ= = = = =
የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
አዝ= = = = =
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች

ዘማሪ
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

"በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።"

መዝ ፵፬፥፱
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
👍2
የእመቤታችን_የእርገት_መዝሙሮች(360p)
<unknown>
#በዓለ_እርገታ_ለማርያም

ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም
ቢሾፍቱ ደብረ መጽሔት ቅድስት
ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን
2025/07/08 17:18:14
Back to Top
HTML Embed Code: