Telegram Web Link
#የቃሉን_ወተት

ማቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥
⁸ ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።
⁹ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።
¹⁰ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
¹¹ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
¹² ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።
¹³ እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።
¹⁴-¹⁵ እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።
¹⁶ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
¹⁷-¹⁸ ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።
🔴__የአርምሞ_እናት__ዲ_ዘለዓለም_ታከለ__ዘጎላ_____New_EP_Yiheg_Fetsame____Ye_a…
<unknown>
#የዕለቱ_ጣዕም
የአርምሞ እናት
ዘማሪ ዘለዓለም ታከለ
#የሚማልደው
ክፍል ፩
ሰላም ውድ ክርስቲያኖች በመጀመሪያ "ምልጃ" የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ምን እንደሆነ እንመለከታለን።
ምልጃ ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ እንደተገለጸው
መሠረታዊ ትርጉሙ አንዱ ስለሌላው መጸለይ ማለት ነው።
ይህም በክርስትና ኅብረት ውስጥ ያለ ምዕመን አንዱ ስለአንዱ በምልጃ መለመን ወይንም መጸለይ እንዳለበት የሚያመለክት ነው።

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥6
አንድም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኙ ሰዎች ለኀጢአተኞች ይቅርታ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሰጣቸው የሚደረግ ጸሎት ነው። ልክ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ለ እስራኤል ዘስጋ ምልጃን እንዳቀረበ

ዘኍልቁ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ግብፃውያን ይሰማሉ፤ ይህን ሕዝብ ከመካከላቸው በኃይልህ አውጥተኸዋልና፤
¹⁴ ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።
¹⁵ ይህን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው ብትገድል ዝናህን የሰሙ አሕዛብ፦
¹⁶ እግዚአብሔር ይህን ሕዝብ ወደ ማለላቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና በምድረ በዳ ገደላቸው ብለው ይናገራሉ።
¹⁷-¹⁸ አሁንም፥ እባክህ፦ እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን።
¹⁹ ይህን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ካወጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው፥ እባክህ፥ እንደ ምሕረትህ ብዛት የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር በል።
²⁰ እግዚአብሔርም አለ፦ እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤

#በሌላ በኩል ምልጃ ስለ ሰዎች ስለ መኳንንት ስለ ነገስታት የሚቀርብ ነው።
ይህም ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው።

1ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።
³-⁴ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።

#ምልጃ የሚለው ሀሳብ ለመንፈስ
ቅዱስ ተሰጥቶ ሲነገር ለምዕመናን ኃይልን እውቀትን ጥበብን በመስጠት እንዴት እንዲጸልዩ አለማወቃቸውን በነሱ ቦታ ተገብቶ ያስታውቃቸዋል።

“እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”
— ሮሜ 8፥26


ይቀጥላል ......
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የቃሉን_ወተት

ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
¹⁸ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
¹⁹ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
²⁰ ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤
²¹ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።
²² ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
²³ እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
²⁴ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?
²⁵ የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን።
_የደማስቆ_ምርኮኛ_ነኝ_____Yedemasko_Merkogna_Negn__ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ(128k)
<unknown>
#የዕለቱ_ጣዕም
ዘማሪ ቴወድሮስ ዮሴፍ
#የቃሉን_ወተት

ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
² በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።
³-⁴ ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።
⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
⁷ ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
⁸ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።
⁹ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።
¹⁰ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
ኑ_በእግዚአብሔር_ደስ_ይበለን___ፈለገ_ዮርዳኖስ_ሚዲያ(360p)(1)
<unknown>
#የዕለቱ_ጣዕም
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
@eotchntc
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት(ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ))
#እንኳን_ለቅድስት_አርሴማ
በዓል በሰላም አደረሳችሁ
@eotchntc
Forwarded from Quality button
የጌታችንን ትንሳኤ የተጠራጠረው ሐዋርያ ማነው?
#የቃሉን_ወተት

ፊልጵስዩስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
⁸ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤
⁹ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
_ያዳነኝን_አውቀዋለሁ_____Yadanegnen_Awkewalehu___ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ(128k)
<unknown>
#የዕለቱ_ጣዕም
ያዳነኝን አውቀዋለሁ
ዘማሪ ቴወድሮስ ዮሴፍ
@eotchntc
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#የሚማልደው ክፍል ፩ ሰላም ውድ ክርስቲያኖች በመጀመሪያ "ምልጃ" የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ምን እንደሆነ እንመለከታለን። ምልጃ ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ እንደተገለጸው መሠረታዊ ትርጉሙ አንዱ ስለሌላው መጸለይ ማለት ነው። ይህም በክርስትና ኅብረት ውስጥ ያለ ምዕመን አንዱ ስለአንዱ በምልጃ መለመን ወይንም መጸለይ እንዳለበት የሚያመለክት ነው። “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ…
#የሚማልደው
ክፍል ፪
ምልጃ በመጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ያህል ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ይገኛል።
ምልጃ የሚለው ሀሳብ በሌላ በኩል ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሲነገርለት ወይም ሲቀጸልለት እንመለከታለን። ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክብር ለሱ ይሁንና መደበኛ አማላጅ ነው የምንል አይደለም። ወይም ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ እንደዛ ብሎ አይነግረንም።
ታዲያ በቀጥታ አማላጅ ነው የማንል ከሆነ እነዚህ የተጠቀሱት ሀሳቦች ለምን ተጠቀሱ

1.ምንም እንኳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ (Almighty God)ቢሆንም ፍጹም ሰው መሆኑን ለአማኞች(ለክርስቲያኖች )ለመግለጽ
ፍጹም ሰው በመሆኑ ደግሞ ደካማ የሆነውን የሰውን ስጋ በመልበሱ ደግሞ
ስጋ የሚሰራውን ሁሉ ከኃጢአት በቀር አድርጓል።ጸሎትን(ልመናንም) ማቅረብ ጭምር
እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”
— ዕብራውያን 5፥7

2. ለምዕመናን የጌታችንን የኢየሱስን አርአያና ምሳሌነት ለማሳየት
ይህም የጌታችንን ትህትና እና ፍቅርን
በጉልህ ለመግለጽ
ምዕመናን ደስ ባላቸው በጨነቃቸው በከፋቸው አሊያም በሚፈሩበት በሚጨነቁበት ወቅት ወደ አምላክ ልመናን እና ጸሎትን ወይም ምልጃን ያቀርቡ ዘንድ ለማስተማር ነው።

ይቀጥላል
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 46
ምዕራፍ 8 :2-9
@eotchntc
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 47
ምዕራፍ 8 :9-12
@eotchntc
#የቃሉን_ወተት

1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
¹⁰ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
¹¹ ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤
¹² ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
🛑ረድተሃልና____ዘማሪ_ዲያቆን_ዘላለም_ታከለ_ዘጎላ_(128k)
<unknown>
#የዕለቱ_ጣዕም
ረድተሃልና
ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም
Audio
በቃልና በኑሮ ሆነሃል ምስክር
እንደ ፀሀይ አበራ በእግዚአብሔር ሀገር..
ገብረመንፈስቅዱስ በረከታቸው ይደርብን
🙏🙏🙏🙏🙏
2025/07/06 18:15:37
Back to Top
HTML Embed Code: