Telegram Web Link
“በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”
  — ራእይ 12፥7
ቅዱስ ሚካኤል
#የገና_ጾም
ጾመ ነብያት
የጌታችንን የኢየሱስን መወለድ በኃይልና በጉጉት በመጠበቅ ነቢያት የጾሙት ታላቅ ጾም
እንኳን አደረሰን
#ከሌለህበት_አታኑረኝ

የኔ አባት ጌታ ሆይ ሁልጊዜም  አንተን ማግኘት ፣በአባትነትህ ፍቅር መጎብኘት፣ በአንተ ጥላነት መጠለል፣ በቸርነትህ ከነፍስም ሆነ ከስጋ ውጣ ውረድ መገላገል፣ ብቻ  ሰላምን የሚያድለውን ያንተን ድምጽ መስማት ሁልጊዜም ይናፍቀኛል።

አባ ብቸኝነት፣ ካንተ ይልቅ የሚባል ህይወት እንዴት ይጨንቃል።
ካለመገኘትህ መኖር ፣ ካላንተ መጓዝ ለካ በድቅድቅ ጨለማ የመጓዝን አስፈሪነት ያስንቃል።

ካለስምህ ለካ ማዕረጌ ሁሉ ባዶ  እውቀቴ ጎደሎ የማይጠቅም ሞኝነት ነው።
እና  የኔ አባት ጌታ ኢየሱስ ሆይ በምህረትህ ብዛት በልቤ ጓዳ ተመላለስ
ቃልህን ሰምቼ የምኖር እና የማደርገው እሆን ዘንድ ቅዱስ መንፈስህን አድለኝ።
የመዳኒቴ አምላክ ሆይ  አንተነትህ  በማይነገርበት  አደባባይ አታቁመኝ

አንተ ከሌለህበት  የስም አጠራሬ ይኖር ዘንድ አትተወኝ።
ይልቁኑ አንተ ካለህ ረሀቡ ጥጋብ  ድቅድቁ ብርሀን  ገደሉ ሜዳ መከራው ደስታ ፈተናው የክብር ይሆንልኛል።

የኔ አባት  አኪያዬ  ጌታ መድኀኒአለም
አንተ ካለህ ሲኦል እንኳን ገነት ይሆናል።
ስለዚህ ባርከኝና ከእቅፍህ አግባኝ።

ዘመኔን ቀድሰው።
ባንተ ቤት በእቅፍህ ያልቅ ዘንድ ይሁን
አሜን

ዲያቆን  የኋላሸት ይኸነው
የካቲት 5/2016
ባህርዳር
#እሰይ_እልልል

ዘማሪ ሐዋዝ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተመልሷል
ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት(ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ))
#እናታችን_ጽዮን_መቼም_አንረሳሽም

በምልዐትና በስፋት እንድናከብርሽ ፈጽሞ ያከበረሽ መድሐኒአለም ይፍቀድልን

🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የህዳር_ጽዮን_በዓል
በቢሾፍቱ ከተማ
ደብረ ገነት ቃጅማ ጊዮርጊስ እና ማርያም ቤተክርስቲያን
21/3/2017 ዓ.ም
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#2017
ያላመኑ በሙሉ
ከ ኢየሱስ ህብረት የጎደሉ
ወደ ቤተክርስቲያን የሚጨመሩበት
ዓመት ያድርግልን
#የቃሉን_ወተት

- ገላትያ 6
1: ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
2: ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ።
3: አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።
4: ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤
ኢትዮጵያን የአረብ ሊግ አባል የማድረግ እንቅስቃሴ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዕድገት ፋይዳ የሌለው በአንጻሩ ግን ጎጂ የሆነ እንቅስቃሴ ነው። ሊጉ ሃይማኖታዊ እንጂ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዓላማ የሌለው ከንቱ ስብስብ ነው። የሊጉ አባል ሀገራት ምን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አገኙ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ምንም የሚል ነው። በፖለቲካውም ረገድ አባል ሀገራቱን ከመበታተን አልታደገም። ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ሶርያ፣ የመን፣ ሊብያ እና ኢራቅ አባላት በመሆናቸው ምን አተረፉ? በሊጉ ስር የተጠለሉት የእርዳታ ድርጅቶች በብዙ ሀገራት ይንቀሳቀሳሉ። መስጊዶችንና መድረሳዎችን ከማስገንባት የዘለለ ለሰው ልጆች የሚጠቅም ምን የረባ የልማት ሥራ ሠርተው ያውቃሉ? አባላቱን ለመቀላቀል በመንግሥት እየተሰጠ ያለው ሰበብ የግብፅን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያስችላል የሚል ነው። ነገር ግን አዋጭነቱ ምን ያህል ነው? ጉዳቶቹስ ታስበውባቸዋል ወይ? ብሎ መጠየቅ አስተዋይነት ነው። ግብፅ ከምዕራባውያን የምትቀበላቸውን አጀንዳዎች በአረብ ሀገራት ላይ የምትጭነው በዚህ ሊግ አማካይነት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ሌሎቹ ሀገራት የሊጉ አባላት መሆናቸው የግብፅ ተገዢ ካደረጋቸው አባል መሆን ኢትዮጵያን ሰተት አድርጎ የግብፅ ብብት ስር የሚከት እርምጃ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለ? የግብፅን ጫና ለመቋቋም አዋጭ የሆነው መንገድ ሌሎች ሀገራትን ጠቅልሎ የግብፅ ተገዢ ያደረገ ማሕበር ውስጥ መግባት ሳይሆን የውስጥ አንድነት ማስጠበቅና በኢኮኖሚም ሆነ በፖለቲካ ረገድ የሀገራችንን ፍላጎት ከሚጋሩ ሀገራት ጋር የጋራ ሕብረት መፍጠር ነው። ግብፅ ሁል ጊዜ እኛን አጀንዳ አድርጋ በሊጉ ስብሰባዎች ላይ ማቅረቧ ሊጉን ለመቀላቀል በቂ ሰበብ አይሆንም። የግብፅን ክስና ሀሜት መስማት ካስፈለገ የግድ አባል መሆን አይጠበቅም። ሕንድን የመሳሰሉት ሀገራት በታዛቢነት እንደሚገኙት ሁሉ ታዛቢ ሆኖ መቅረብ ይቻላል። አረቦችና የአረብ ባሕል እንዳላቸው የሚያስቡ ሀገራት የፈጠሩት ማሕበር አባል መሆን አረባዊ ላልሆነችና አብዛኛው ሕዝብ ክርስቲያን ለሆነባት ሀገር ጠቃሚ አይደለም። ይሁን ከተባለም መዘዙ ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ውሳኔ እንጂ የጥቂት ፖለቲከኞችና የጥቂት ሙስሊም መሪዎች ውሳኔ ሊሆን አይገባውም።
#ጌታ_እኮ_ነው

በዚህ በሚደንቅ ንግግር ውስጥ የጌታን ጣፋጭነት የሐዋርያትን ለጌታ ያላቸውን የላቀ ፍቅር እናይበታለን።
ጌታን ሲያዩ ከፊታቸው ባህር ወይ ገደል የፈለገው ነገር ቢኖር ጉዳያቸው አልሆነም። ምክንያቱም በሁሉ ላይ ስልጣን ያለው አምላክ መሆኑን ያውቁ ኖሯል።

ጌታ እኮ ነው እንድንል ጌታ ኢየሱስ የልቦናችንን መስኮት ይክፈትልን

- ዮሐንስ 21:
7: ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን፦ “ጌታ እኮ ነው፡” አለው። ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበረና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ራሱን ጣለ።

#የቃሉን_ወተት
@eotchntc
ህዳር 30/2017 ዓ.ም
ቢሾፍቱ (ደብረዘይት )
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
ስንክሳር_ታሕሳስ ፫(3).aac
5.9 MB
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (የኋላሸት)
#የቃሉን_ወተት

2ኛ ጴጥሮስ 1:20
ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤
21: ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።
#የቃሉን_ወተት

- ኢሳይያስ 49:15
በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።
2025/07/06 04:33:07
Back to Top
HTML Embed Code: