Telegram Web Link
📮የቁርኣን ምክር 1⃣

💥(„...ከሰዎች ውስጥም ብዙዎች ያለ እውቀትና ማስረጃ በዝንባሌ፣ በስሜትና በግምት ብቻ ሰዎችን ያጠማሉ፤ ጌታህ ወሰን አላፊዎች እነማን እንደሆኑ ያውቃል። <እርሱም ወሰን አላፊዎችን አይወድም>„)
ከአል-አንዓም አንቀጽ 119 የተወሰደ።

💥ወሰን ከማለፍም ይሁን፣ ከወሰን አላፊዎችና በግምትና በስሜት ከሚነዱ ሰዎች እንድንጠነቀቅ ቁርኣን ይመክረናል!

💥በስሜት ከመመራትና ጠሞ ከማጥመም አላህ ይጠብቀን።
📮የቁርኣን ምክር 2⃣

💥(„...ሰዎችን ሊያጠም ያለ እውቀት አላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጥፍ ሰው የበለጠ በዳይ ማን አለ?! አላህ በደለኛ ሰዎችን ቀናውን መንገድ አይመራቸውም።„)
ከሱረቱል-አንዓም አንቀጽ 144 የተወሰደ።

💥ውሸትን በራሱ እንድንጠነቀቅና ይበልጥ ደግሞ ያለ በቂና ትክክለኛ እውቀት ዲን ላይ በመናገር (ሐላል..ሐራም በማለት) አላህና መልእክተኛው ላይ መዋሸትና መቅጠፍን እንድንርቅ ቁርኣን አጥብቆ ይመክረናል!

መመለስ አሻፈረኝ ብለን ያለ እውቀት እየተመራንና እየመራን ከቀጠልን ከራሳችን አልፎ ሰዎችንም መበደላችን አይቀርም።
አላህ ደግሞ በደለኛን በዱኒያ ወደ ሐቅ ጎዳና፣ በኣኺረህ ደግሞ ወደ ጀነት መንገድ አይመራውም!
ስለዚህ አላህ ቀናውን መንገድ እንዲመራንና እንዲያስተካክለን ቀድመን እኛ እሱ ከከለከለን ነገሮች መከልከል ይገባናል።

💥ከበደልና አላህ ላይም ይሁን ሰዎች ላይ ከመዋሸት አላህ እራሱ ይጠብቀን!።
📮የቁርኣን ምክር 3⃣

💥ሙእሚኖች ጀነት ሲገቡ፤ („...የጀነትን መንገድና ጀነት ለመግባትም ያበቃንን መልካም ስራ ለመስራት ለመራን ጌታችን አላህ ምስጋናና ውዳሴ ይገባው!
አላህ ባይመራን ኖሮ አንመራም ነበር፣ የጌታችን መልእክተኞችም እውነትን ይዘው ነበር ወደኛ የመጡት።„ ይላሉ! "ይህች ትሰሩት በነበረው መልካም ስራችሁ ምክንያት የታደላችኋት/ በምሪት የተሰጠቻችሁ ጀነት ናት" ይባላሉ።)
ከሱረቱል-አዕራፍ አንቀጽ 43 የተወሰደ መልእክት።

💥ጀነት የሚገባው -በአላህ ፍቃድ- በስራ እንደሆነና ለውዷ ጀነት ውድ ጊዜአችንን በመስጠት የተለያዩ መልካም ስራዎችን በብዛት መስራት እንዳለብንና በስራችን ከመደነቅ ታቅበን ለመልካም ስራዎች ሁሉ ያበቃንና የመራንን አላህን ማመስገን እንደሚገባን ቁርኣን ይመክረናል።

💥የዱኒያ ባለስልጣን አንድን ሰው ቢወደው ወይም ቢያደንቀው ነገ ትቶት የሚሞትን ወይም የሚፈርስን ምድራዊ ቤት ነው የሚሰጠው!
አላህ ግን ባሪያውን ሲወደው መሞትና መሰደድ የሌለባትንና መቼም የማትፈርሰዋን ጀነት ነው የሚያድለው!።

ذَٰلِكَ فَضْلُ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ.

نسأل الله من فضله!
📮የቁርኣን ምክር 4⃣

💥(„ምድርን አላህ አስተካክሎና ለነዋሪዎች የምትመች፣ የሚያስፈልጋቸውንም ነገር በሙሉ የያዘች አድርጎ ከፈጠራት በኋላ በምትሰሩት ወንጀል ምክንያት አታበላሿት።
አላህንም በፍርሃትና በተስፋ መካከል ሆናችሁ ተገዙት/ለምኑት፣ የአላህ እዝነትና ችሮታ እምነትና ስራዎቻቸውን ከሚያሳምሩ ሰዎች ቅርብ ነው።„)
ከሱረቱል-አዕራፍ አንቀጽ 56የተወሰደ መልእክት

💥ወንጀል ምድርን፣ የሰዎችን ስነ-ምግባርና ስራ፣ ያበላሻል።
የብስም ይሁን ባህር ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች በሙሉ ምክንያታቸው የሰው ልጆች ወንጀልና ጥፋት እንደሆነና፣
💥ሰዎች ምድር ላይ ሲኖሩ በሁሉም ነገር አላህን ከፈሩ፤ ምድር እንደምታምር፣ የሰዎች ሲሳይ እንደሚሰፋ፣ ስራና ስነ-ምግባራቸውም እንደሚስተካከልና ዓለም ላይ ሰላም እንደሚሰፍን ቁርኣን ይነግረናል።

ወደ ቁርኣን እንመለስ!
📮የቁርኣን ምክር 5⃣

[{የአላህን ብርሃን ማን ችሎ ያጠፋል?!}]

💥(„የአላህን ብርሃን/ ኢስላምን በአፎቻቸው/ በንግግራቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህ ደግሞ ከሃዲያን ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን/ዲኑን መሙላትን እንጂ ሌላን አይፈልግም። አጋሪዎች/ ከሃዲያን ቢጠሉም፣ አላህ ኢስላምን ከሃይማኖቶች ሁሉ የበላይ ያደርግ ዘንድ፤ መልዕክተኛውን "ሙሐመድን صلى الله عليه وسلم
ትክክለኛና ጠቃሚ እውቀት እና ትክክለኛ እምነትና ስራ ላይ የተመሰረተን ሃይማኖት/ኢስላምን አሲዞ ልኳቸዋል„)
ከሱረቱ-አት'ተውባህ አንቀጽ 32እና 33የተወሰደ መልእክት።

💥ኢስላምን ለማጥፋትና የኢስላምን ነቢይ ለማጠልሽት የሚደረግ ሙከራ በሙሉ ትርፉ ድካምና እራስን መጉዳት ብቻና ብቻ ነው።

💥እነሱ ኢስላምን ለማጥፋት ይጥራሉ፣ አላህ ደግሞ ዲኑን ሙሉና የበላይ ማድረግ እንጂ ሌላን አይፈልግም አይፈቅድምም! አላህ አሸናፊና የሻውን ሰሪ ነው። ነገሮች በሙሉ በርሱ ቁጥጥር ስር ናቸው! ድከም ያለው ዝም ብሎ ይደክማል!። በከንቱ እየለፉ በአፍ ከመለፍለለፍና ከመቅጠፍ፣ በእጅም ከመሳልና ከመፃፍ የዘለለ ኢስላምና ነቢዩ ላይ የሚያደርሱት ምንም ዓይነት ጉዳት አይኖርም።
የጸሃይን ብርሃን ሙሉ በሙሉ መጋርድ ወይም ማስወገድ የሚችል ማንም እንደሌለው ሁሉ የኢስላምን ብርሃን ማጥፋት የሚችል አይኖርም!።

ሙእሚኖች ይህን አውቀው ይጽናኑ፣ ከሃዲያንም ተስፋ ይቁረጡ!

💥ከአንቀጹ እንደምንረዳው፣ ኢስላም የበላይ የሚሆነው "በትክክለኛና ጠቃሚ እውቀት፣ በመልካም ስራና ስነ-ምግባሮች ነውና እነዚህ ነገሮች ላይ እንበረታ"

ወደ ቁርኣን እንመለስ!
📮የቁርኣን ምክር 6⃣

💥(„አፈሩ መልካምና ጥሩ የሆነ ሀገር ምርቱ በአላህ ፈቃድ ያማረ ሆኖ ይወጣል/ይበቅላል፤ መጥፎ መሬት ደግሞ ምርቱ ደካማና የማይጠቅም ይሆናል...„)
ከሱረቱል-አዕራፍ አንቀጽ 58 የተወሰደ መልእክት።

💥ይህ የሙእሚንና የካፊር፣ ልቡ በኢማን የተስተካከለና ልቡ ያልተስተካከለ ሰው ምሳሌ ነው።

💥በቁርኣንና በዲን ህግጋት መጠቀም የሚችለው ቀድሞ ልቡን ያስተካከለና እውነትን ለመቀበል ልቡን ክፍት ያደረገ ሰው ነው።

ዝናብ ለምና ቀድሞ የተዘጋጀ/የታረሰ መሬት ላይ ካላረፈ በስተቀር እንደ ማይጠቅመው ሁሉ ለኢማንና መልካም ስራ እራሱን ላላዘጋጀ ሰው የቁርኣንና የሐዲሥ ምክሮች ምንም አይጠቅሙም።

💥ልሙጥና ደረቅ ድንጋይ ላይ የሚፈስ ዝናብ/ውኃ ወደ ውስጡ መግባት እንደ ማይችለው ሁሉ አላህን በማመጽና ኣኺራን በመርሳት ልቡ የደረቀ ሰውም የቁርኣን ምክሮች ወደ ልቡ አይዘልቁም።

ከቆሻሻዎችና ከስሜት የጠራ ንጹህ ልብ፤
ቁርኣንን መቅራትና ማድመጥ አይጠግብም፣ ከርሱ ውጪም ለታመመና ለተራበ ልቡ መድሐኒትና ምግብ አይሻም።

ልባችንን ዘውትር እንፈትሸው፣ ከቆሸሸም በቁርኣን እናጽዳው!

ልብ ከተስተካከለ በትንሽ መልካም ስራ ጀነት መግባት ይቻላል።
ልብ ካልተስተካከለ ግን የስራ መብዛት ብዙም ዋጋ አይኖረውም።

ወደ ቁርኣን እንመለስ!
📮የቁርኣን ምክር 7⃣

💥አላህ ቁርኣንን ሲገልጸው እንዲህ ብሏል፣ („ይህ መጽሐፍ ከአላህ ለመሆኑን ምንም ጥርጥር የለበትም እርሱም አላህን ለሚፈሩ መሪ ነው„) ሱረቱል-በቀራህ 2 ።

💥ቁርኣን ለሰው ልጆች በሙሉ የሁለቱንም ዓለም ህይወት የሚያስተካክልና ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመራ መጽሐፍ ነው።

💥ቁርኣን በመሰረቱ ምንም እንኳ ለመላው የሰው ልጅ መመሪያ ቢሆንም ሰበብ ያላደረሱና አላህን የማይፈሩ ግን ቁርኣን ሊመራቸውና ሊያስተካክላቸው አይችልም።
ለዚህም ነው፣ < َهُدى لِلْمُتَّقِيْن> ያለው።

💥ቁርኣንን እየቀራንና እየሰማን የማንገሰጸውና የማንለወጠውም ውስጣችን ላይ የአላህ ፍራቻ በመጥፋቱ ወይም በመቀነሱ ምክንያት ነው።
ልብ ላይ ትንሽም ቢሆን "ተቅዋ/የአላህ ፍራቻ" ካለ ቁርኣን ያሳድገዋል፣ አካላትም ለመልካም ስራ ይነሳሳሉ፣ ከወንጀልም ይታቀባሉ።
ልብ ሲደርቅና አላህን ሲረሳ ግን ቁርኣን መስማቱም ይሁን ማንበቡ ልሙጥ ድንጋይ ላይ ውኋ እንደ ማፍሰስና ብረትን በብረት እንደ መምታት ይሆናል።
💥ይህ በእንዲህ እንዳለ ቁርኣን የሚያስተካክለው የሰዎችን የኣኺራህ ህይወት ብቻ ሳይሆን በሚገባ ካጠናነውና ከተከተልነው የዱኒያ ህይወትንም ጭምር የሚያስተካክል መሪ መጽሐፍ ነው።

ቁርኣንን የቀራና የተረዳ ሰው ቤትኛውም ዘመንና ሀገር ቢኖር ኋላ ቀርና ሞኝ አይሆንም!።
ምክንያቱም አላህ- <هُدى لِلْمُتَّقِيْن> "አላህን ለሚፈሩ መሪ ነው" ሲል፤ መሪነቱን በምንም አልገደበውም።
ይህ ደግሞ "ቁርኣን ለሰው ልጆች በሚያስፈልጉ ነገሮች ላይ በሙሉ አማኞችን ወደ ትክክለኛው ጎዳና የሚመራና ለስኬት የሚያበቃ መሪ መሆኑን ነው የሚያሳየው"
ለዚህም ነው፣ "ልጅህን ቁራኣን አስተምረው ቁርኣን ደግሞ ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል" የተባለው።

አለምስ ቢሆን የተቀየረችውና ህይወትን ያቀለሉ ግኝቶች የተገኙት ቁርኣን ከወረደ በኋላ አይደል?!
ከቁርኣን መውረዱና ከነቢዩ ሙሐመድ* መላክ በፊት ስልጣኔ የሚባል ነገር ነበረ?!
ብዙ የሳይንስ ምርምር ውጤቶችስ ቢሆን ቁርኣን ቀድሞ ገልጿቸው የለ?!

"ታዲያ ወዴት ትሄዳላችሁ?! ቁርኣን ለሁሉም የሰው ልጆች መገሰጫና መማሪያ እንጂ ሌላ አይደለም"

ወደ ቁርኣን እንመለስ!
ጥርጣሬ ቢያይልብህ እንኳ የማይገባውን ሰው ያለ አግባብ ከመወንጀል ይልቅ ምናልባት የሚገባውን በዝምታ ማለፍ እንደሚቀልና ይህም አጉል የዋህነት ሳይሆን ተገቢ ጥንቃቄ መሆኑን አውቀህ አንደበትህን ቆጥብ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«በአዛን ውስጥ ያሉ አስደናቂ ተአምራት»
አዛን የተዋቀረበት የቃላት ብዛት
« አላሁ አክበር ከሚለው መጀመሪያ እስከ ላ ኢላሀ ኢለሏህ» እስከሚለው መጨረሻ የቃላት ብዛት 50 ናቸው።
ቁርአን 6:160 እንደሚነግረን
በአንድ በጎ ተግባር አላህ የሰው ልጅ አስር ሀሰና ይሰጠዋል።
በአምስት አውቃት ሰላት ስንሰግድ የአምሳ ሶላት ያህል እንደ የምናገኘው የሀሰናት መጠን ጋር ቃላቶቹ ጋር እኩል ናቸው።
ሌላም ልቀጥል የአረበኛ ፊደላት ብዛታቸው 28 ናቸው ።
ከነዚህ ውስጥ አስገራሚው ነገር አዛን የሚባልባቸው ፊደላት ብዛት 17 ናቸው ።
ከታች ፊደላትን ቁጠሩ እስኪ
ا ل ه ك ب ر ش د ن م ح س و ي ع ص ف
እነዚህ 17 ፊደላት በቀን ውስጥ ከምንፈፅመው ረከአ ጋር እኩል ናቸው።
ሱብሀነላህ ጥራት ይገባህ ጌታየ!
ይቀጥላል ፣
አንድ አመት አስራ ሁለት ወር ነው ቁርአንን ይህን ያረጋግጥልናል አል_ተውባህ 36 ኛው አንቀፅ ላይ ይናገራል።
እዚህ ላይ ምን ያስገርማል ካላችሁ የአዛን ንግግሮች 12 አረፍተ ነገር ናቸው ።
الله اكبر الله اكبر1
الله اكبر الله اكبر2
اشهد ان لا اله الا الله3
اشهد ان لا اله الا الله 4
اشهد ان محمد رسول الله 5
اشهد ان محمد رسول الله 6
حى على الصلاة7
حى على الصلاة8
حى على الفلاح9
حى على الفلاح10
الله اكبرالله اكبر11
لا اله الا الله12
12 አረፈተ ነገር ብቻ መሆናቸው ሳይሆን የአዛን ድምፅ በነዚህ ወሮች ለደቂቃዎች ለሰከንድ ጥሪው በአለም አይቁያረጥም።
በቅርቡ ሳይንስ ይህን አረጋግጡዋል ።
በመሆኑም ምድራችን ዙሪያዋ 360° ሲሆን እያንዳንዱ ዲግሪ ማሐል የ4 ደቂቃ ልዩነት ቢኖርም አዛን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ሳይቋረጥ መሰማቱ እጅግ አስገራሚ ነው።
የአንድ እለት 24 ሰዓት ማለት ምድር በምድር ወገብ 360 ድግሪ አንዴ የምትዞረበት ጊዜ ማለት ነዉ፡፡
በቅድሚያ ድግሪ ማለት የምድር ወራጅ መስመር እና ገዳሚ መስመር የሚገናኙበት ነጥብ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ የምድር ወራጅ መስመር እና ገዳሚ መስመር የሚገናኙበት 4 የተለዩ ነጥቦች አላቸዉ፡
በያአንዳንድ ዲግሪ ርቀት መካከል የ4 ደቂቃ ልዩነት አዛን ይደረጋል ይህም 360° × 4 ደቂቃ= 1440 ደቂቃ = 24 ሳአት ይሆናል ። ሱብሃነላህ
የመጨረሻው የአዛን ቃላት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው አረፍተ ነገርም የፊደሎቹ ብዛት 12 ነው።
ሙሐመድ ረሱሉላለህ የሚለውም የፊደል ብዛት እንዲሁ 12 ነው።
ሱብሀአነላህ
ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ "ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ማለት ነው፣
እነዚህ ቃላቶች الله ከሚለው ሶስት ፊደሎች ብቻ የተዋቀሩ ናቸው ።
لا إله إلا الله
«ማንኛውም እዚህ ዩንቨርስ ያለ አካል የራሱን ስም የተፃፈበትን ፊደላት በመጠቀም ስለማንነቱ መልሶ በነዚያው ፊደላት ለሌላው መግለፅ የሚችል ከአላህ በቀር ወይም ከዚህ ከላኢላኢለላህ ከሚለው ቃላት በቀር ሌላ ቃላት የለም ወደፊትም መፍጠር አይቻልም ።
እንቀጥል ሌላ ተአምር
አዛን አላህ አክበር ብሎ «አላህ»ብሎ በአላህ ስም ይጀምራል ላኢላሀኢለላህ ብሎ በ «አላህ» ስም አዛኑ ያልቃል ። አዛን ላይ የሚደጋገመሙ ብዙ ቃላቶች አላህ የሚለው ነው።
በብዛት የተደጋገሙ ቃላቶችችም እነዚህ የአላህ ስም የተገለፀባቸው ቃላቶች ናቸው ።
አዛን ውስጥ ብዛት ያለው ቃል አላህ የሚለው አስር አንድ ግዜ ተጠቅሱዋል።
11 ቁጥር በባህሪው እኩል መካፈል የሚችለው ለአንድ ብቻ እና ብቻ ነው ።
ሱብሀነላህ
በአዛን ውስጥ አሊፍ የሚለው ፊደል 47 ጊዜ ተጠቅሱዋል ።
ላም የሚለው ፊደል 45 ግዜ ይነሳል ።
ሀ የሚለው ፊደል 20 ግዜ ተጠቅሱዋል የነዚህ ፊደላት ድምር = 112 ፊደላት ናቸው።
አስገራሚው ነገር ይህ ቁጥር የአላህ ስም ከሱረቱል ፋቲሀ እስከ ሱረቱል ኢኽላስ ባለው ምዕራፍ መካከል ተገልፁዋል ግን በመጨረሻዎቹ ፈለቅ እና ናስ በሚባሉ ሁሉት ሱራዎች ላይ የአላህ ስም የለም ።
ሱብሀነ አላህ
አዛን በአመት ከ1800 ግዜ በላይ እንሰማለን ይህ ሁሉ ተአምር እንደያዘ አስተውለን ይሆን?
ምንም አማራጭ የለንም አልሀምዱሊላህ አላ ኒእመተል አዛን አልሀምዱሊላህ አላኒዕመተል ኢስላም ከማለት ውጭ አላህ ታላቅ ነው።
ኢስላምን ተረድተው ከሚያስረዱት አድርገን ።
«የሆነ ሰው እንደተመቸው አይቶ በድሎህ ሳለ፤ ከሆነ ጊዜ በኋላ አንተ እርሱን ለመበደል ሙሉ አቅም ካገኘህ ፥ ከምትበቀለው ይልቅ ይቅር ብለህ ብታልፈው የበለጠ እርካታ ታገኛለህ።»
#አኽላቃችን

የሰዎች አኽላቅ ይበልጥ ቁልጭ ብሎ የሚታየው በችግር ጊዜ ነው።
በሰላምና ሁሉም ነገር በፈለጉት አቅጣጫ እየሄደ ባለበት ወቅት ላይ ሁሉም ሰው አመለ-ሸጋና አኽላቀ- ሙሉእ ነው።
አኽላቅ ትልቅ የዲን አካል እንደመሆኑ፤ ሰላትና መሰል ዒባዳዎች ላይ በሁሉም ሁኔታዎች ላይ እንደምንጸናው ሁሉ መልካም አኽላቅና ኢስላማዊ አደቦች ላይም ሁሌም እንጽና።

ችግር፣ ንዴትና ሰዎች እኛን መበደላቸው ከሙስሊም የማይጠበቅ የወረደ አኽላቅ እንዲኖረን አያድርገን።

ትክክለኛ ሙስሊም ጦር ሜዳ ላይ እንኳ ሆኖ ኢስላም ያዘዘውን አጠቃላይ አኽላቅና አደብ አይለቅም!

የተነካ ወይም የተጎዳ በመሰለው ቁጥር ከሚገባው በላይ ጸባዩ የሚለዋወጥ፣ ስሜቱን መቆጣጠር የሚሳነውና የሚናገረውን የማያውቅ ሙስሊም፤
{"ትክክለኛ የአላህ ባሮች (የጀነት እጩዎች) በቁጣ ጊዜ ንዴታቸውን ዋጥ የሚያደርጉ ናቸው"} የሚለውን የአላህን ቃል ሊያስታውስና ሊረጋጋ ይገባዋል።

ሁሌም አብሮን የሚኖር መልካም አኽላቅ አላህ ያድለን።
#አላህ_ጀነት_ውስጥ_ለአማኞች_ያዘጋጀላቸው_ጸጋዎች

#ሐዲሥ 372/ 1880

ጃቢር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "የጀነት ሰዎች ይበላሉ፤ ይጠጣሉ። ግና አይጸዳዱም፣ አይናፈጡም፣ አይሸኑም። ምግባቸው እንደሚስክ የሚያውድ ሽታ ባለው ግሳት መልክ ከአካላቸው ይወገዳል። የአላህን ክብርና ልቅና መግለጽን የመተንፈስ ያህል ይማራሉ።" (ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የጀነት ሰዎች የተዘጋጀላቸው እጅግ የሚያጓጓና የተሟላ ፀጋ።
2/ የጀነት ምግብ እጅግ ጥሩ እና ንጹሕ ከመሆኑ የተነሳ ከአካል ተርፎ በዓይነ ምድር፣ በሽንትና በንፍጥ መልክ የሚወገድ ነገር የለም። ሁሉም ለአካል ይስማማል። ሁሉም የሚያውድና የሚማርክ ሽታ ይሆናል።
3/ የጀነት ሰዎች አላህን በማውሳት (በዚክር) ይደሰታሉ። ዚክር የመተንፈስ ያህል ይቀላቸዋል። ይዋሐዳቸዋል።

አላህ ሆይ! እዝነትህ የሆነችውን ጀነትን ወፍቀን አሚን
ቴሌግራም/ telegram/
https://www.tg-me.com/eslamic_center
#ሐያቱ_ሷሐባ #አቡ_ዑበይዳህ__ኢብኑ #አል_ጀራሕ (ረ.ዐ) #ክፍል_1

“ማንኛውም ኡምማ (ሕዝብ) የራሱ አሚን (ታማኝ) አለው። የዚህ ኡምማ አሚን አቡ ዑበይዳህ ነው።” (ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ))

ግርማ ሞገስ ያለው፣ ረጂም እና በመጠኑ ሰውነቱ ሞላ ያለ ሰው ነበር። ብሩህ የሆነ ገጽታን የተላበሰ ሲሆን እሱን መመልከት የሚያስደስትና ከእሱ መዋልም መንፈስን የሚያድስ እንደነበር ተነግሮለታል። ጠባየ ሸጋ፣ አንደበተ ርቱዕ፣ ትዕግስተኛና ፍፁም ዓይን አፋርም ነበር። የነቢዩ (ﷺ) ኮምዩኒቲ (ማኅበረሰብ) ታማኝ ወይም “አሚን” በመባል ይታወቃል። ሙሉ ስሙ ዓሚር ኢብኑ ዐብደላህ አል ጀራሕ ነው። አቡ ዑበይዳህ በመባል ነው ይበልጥ የሚታወቀው። የነቢዩ (ﷺ) ባልደረባ (ሶሐባ) የነበሩ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) በአንድ ወቅት ስለ አቡ ዑበይዳህ ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር፦

“በቁረይሽ ጎሣ ውስጥ ሦስት ሰዎች አሉ፤ እነዚህ በግልጽነታቸውና በመልካም ጠባያቸው ከሌላው ሰው የተለየ የሚያደርጋቸው አያሌ ምግባር ነበራቸው። እውነትን እንጂ የማይናገሩ፣ በሚያዋሯቸውም ጊዜ ለነቀፌታና ለትችት የማይቸኩሉ ሰዎች ነበሩ። እነርሱም፦ “አቡበክር አስ ሲዲቅ፣ ዑሥማን ኢብኑ ዐፍፋን እና አቡ ዑበይዳህ ኢብኑ አል ጀራሕ (ረ.ዐ) ናቸው።”

አቡ ዑበይዳህ (ረ.ዐ) ኢስላምን በቅድሚያ ከተበቀበሉት ሙስሊሞች መካከል አንዱ ነበር። ኢስላምን የተቀበለው አቡበክር (ረ.ዐ) ከተቀበሉ ከአንድ ቀን በኋላ ነበር። ለመስለሙ ምክንያት የሆኑትም አቡበክር (ረ.ዐ) ናቸው። አቡበክር (ረ.ዐ) አቡ ዑበይዳን፣ ዐብዱረሕማን ኢብኑ አውፍን፣ ዑሥማን ኢብኑ መዕዙንን እና አርቀም ኢብኑ አቡ አርቀምን ወደ ነቢዩ (ﷺ) በመውሰድ “ሸሃዳ” እንዲይዙ አደረጉ። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች የኢስላም የመጀመሪያ ልጆች ናቸው።

አቡ ዑበይዳህ (ረ.ዐ) በእነዚህ አስከፊ ወቅቶች ማለትም ሙስሊሞች በመካ ውስጥ ባሳለፉት የመከራና የሥቃይ ጊዜያት የነበረና ኢስላም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የገጠመውን ዕድል የተጋፈጠ ነው። ከቀደምት ሙስሊሞች ጋር አብሮ ተሰዷል ነገር ግን በገጠሟቸው ፈተናዎችና መከራዎች ሁሉ በአላህ እና በመልዕክተኛው ያለው እምነት የማያወላውልና የማይበገር መሆኑን አስመስክሯል። በተለይም በበድር ዘመቻ ላይ ያሳየው ተጋድሎ ታላቁን ሥፍራ ይይዛል።

አቡ ዑበይዳህ (ረ.ዐ) ለሙስሊሙ ጦር ግንባር ቀደም ተዋጊ በመሆኑ በጠላት ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ከፍተኛ ነበር። የቁረይሽ ፈረሰኞችም አቡ ዑበይዳህን በጣም ይጠነቀቁት፣ ይሸሹት፣ እና ፊት ለፊትም መጋፈጥን ይፈሩ ነበር። ነገር ግን አንድ አቡ ዑበይዳህን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ የሚከታተለውና አደጋ ሊያደርስበት የሚሞክር ሰው ነበር። አቡ ዑበይዳህ ግን ሰውየው ጋር ላለመግጠም ጥረት ያደርጋል።

ሰውየውም ቅኝቱን ቀጠለ። አቡ ዑበይዳህም ይህን ሰው ላለመገናኘት ሞከረ። ነገር ግን ይኸው ባላንጣ መንገዱን ዘጋበት፡፡ ፊት ለፊት ተፋጠጡ። አሁን አቡ ዑበይዳህ ራሱን ሊገታና ጊዜም ሊወስድ አልፈለገም። በሰውየው ጭንቅላት ላይ ከባድ በትር አሳረፈበት። ሰውየውም መሬት ላይ ተዘረረ ፤ በቅጽበት ሕይወቱ አለፈች፡፡

ሟቹ ማን ይሆን? አዎ የአቡ ዑበይዳህ (ረ.ዐ) አባት ነበር። የአንድ ፈጣሪ ሥርዓተ አምልኮን ለማንገሥና በብዙ አማክልት ማመንን ለማጥፋት በተደረገ ዘመቻ አባቱን በመግደሉ አይቆጭም። በዚሁ አጋጣሚ አቡ ዑበይዳህ የገደለው አባቱን ሳይሆን በአባቱ ውስጥ ያለውን የብዙ አማልክት እምነትና ሃይማኖት ነው።

ይህን ክስተት በሚመለከት ነበር አላህ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ ያወረደው፦

لَّا تَجِدُ قَوْمًۭا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْءَاخِرِ يُوَآدُّونَ مَنْ حَآدَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَوْ كَانُوٓا۟ ءَابَآءَهُمْ أَوْ أَبْنَآءَهُمْ أَوْ إِخْوَ ٰنَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُو۟لَـٰٓئِكَ كَتَبَ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلْإِيمَـٰنَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍۢ مِّنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّـٰتٍۢ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَـٰرُ خَـٰلِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ ۚ أُو۟لَـٰٓئِكَ حِزْبُ ٱللَّهِ ۚ أَلَآ إِنَّ حِزْبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ ﴿٢٢﴾

“በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፡፡ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል፡፡ ከእርሱም ወደዋል፡፡ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡“
(አል ሙጃደላህ፡ 22)

አቡ ዑበይዳህ (ረ.ዐ) በአባቱ ላይ የወሰደው እርምጃ ያልታሰበና ያልተጠበቀም አልነበረም። በአላህ ከፍተኛ እምነት ያለው፣ ለኢስላም ቀናኢ የሆነ እንዲሁም ለነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ኡምማህ (ሕዝብ) የነበረው ትኩረት ከፍተኛ ሶሐባ በመሆኑ ነው።

ሙሐመድ ኢብኑ ጀዕፈር (ረ.ዐ) እንዳወሩት ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

በአንድ ወቅት አንድ የክርስቲያን ልዑካን ቡድን ወደ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይመጣል “አቡልቃሲም ሆይ! (ነቢዩን ማለታቸው ነው) በመካከላችን በሀብትና በንብረት ክፍፍል ምክንያት ስምምነት ላይ ልንደርስ አልቻልንምና እርስዎ የሚያምኑበትን ሰው በመሃከላችን እንዲፈርድ ቢልኩልን ፤ እኛ በእናንተ ሙስሊም ሕዝቦች ላይ ከፍተኛ ክብርና እምነት አለንና መፍትሔውን ከእርሶ እንጠብቃለን” አሏቸው።

ነቢዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) “ወደ ማታ ላይ ተመልሳችሁ እንድትመጡ ጠንካራና ታማኝ የሆነን ሰው እሰጣችሁና ይዛችሁ ትሄዳላችሁ።” አሏቸው።

ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ) የነቢዩን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መልስ ከሰሙ በኋላ የተከሰተውን ሁኔታ ራሳቸው ይተርኩልናል፦ “ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚፈልጉትን ሰው መስፈርቱን አሟላለሁ በሚል ዝሁር ወቅት ላይ ቀደም ብዬ በመግባት ከነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አጠገብ ተቀመጥኩ። ነቢዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስግደታቸውን እንደ ጨረሱ ወደቀኝና ግራ በመዞር ተመለከቱ፤ እኔም እንዲመለከቱኝ ከፍ ከፍ ማለት ጀመርኩ። ነገር ግን አሁንም መመልከታቸውን ቀጠሉ። ትኩረታቸውን ወደ አቡ ዑበይዳህ ኢብኑ አል ጀራሕ አደረጉ። ጠሩትና ‘ከእነዚህ ሰዎች ጋር ሂድ፤ ያልተስማሙበትም ጉዳይ አለና በትክክልና በእውነት ዳኛቸው።” አሉት፡፡ አቡ ዑበይዳህም ከሰዎቹ ጋር ቀጠሮ ያዘ።”

አቡ ዑበይዳህ (ረ.ዐ) ታማኝ ብቻም አልነበሩም። በተሰጣቸው ማንኛውም የኃላፊነት ሥራ ሁሉ ጠንካራ እና አይበገሬ መሆናቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች አስመስክሯል።

ኢንሻአላህ ክፍል 2 ይቀጥላል

telegram/
https://www.tg-me.com/eslamic_center
#ባለሥልጣናት_ለሕዝባቸው #ቅንና_ታማኝ፣ #አዛኝና_ገራገር #እንዲሆኑ_ስለማዘዝና #እንዳያታልሏቸው፣ #እንዳይጨቁኗቸው፥ #ጥቅማቸውን #ችላ_እንዳይሉ #ስለማስጠንቀቅ
#ሐዲሥ 78 / 656

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “በኒ ኢስራኢሎች ገዥዎቻቸው ነቢያት ነበሩ። አንዱ ነቢይ ሲሞት ወዲያውኑ ሌላ ነቢይ ይተካ ነበር። ከኔ በኋላ ግን ነቢይ የለም። የሚኖሩት ኸሊፋዎች ናቸው። ግና በቁጥር በርካታ ናቸው።” (ሶሐቦቹም)፦ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?” በማለት ጠየቋቸው። “መጀመሪያ የፈፀማችሁትን ቃልኪዳን ሙሉ። የነርሱን መብት ደግሞ (ሳታጓድሉ) ስሟቸው። የናንተን መብት ከአላህ ጠይቁ። አላህ በሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ይጠይቃቸዋልና።” አሉ። (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

➥ ኢስራኢል የሚባለው የዕቁብ ሲሆን፥ ልጆቻቸው የአይሁድ ጎሣዎች ናቸው። ኢስራኢል እብራይስጥኛ ስም ነው። ትርጉሙም የአላህ ባሪያ ማለት ነው።
➥ “በመጀመሪያው የፈፀማችሁትን ቃልኪዳን ሙሉ” ማለት ከነርሱ ጎን ተሰለፉ፣ ታዘዟቸው፣ ከነርሱ _ ያለ ሕግ አግባብ _ ያፈነገጠውን ወገን ደግሞ ተፋለሙ ማለት ነው።
➥ የሰው ልጅ ምንጊዜም ቅኑን መንገድ የሚያሳየው፥ ጉዳዩን የሚፈጽምለትና የሚያስተናብርለት፥ ግፍን የሚከላከልለት ነቢይ ወይም እርሱን የሚተካ አካል ያስፈልገዋል። ከነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) በኋላ ሌላ ነቢይ አይመጣም። ምትኮቻቸው ግን ይኖራሉ። ኹለፋእ ሐቅ ላይ እስከፀኑ ድረስ እነርሱን መታዘዝና መደገፍ ግዴታ ይሆናል።
➥ ኅብረተሰቡም መሪዎችን ጥቅሙን እንዲያስከብሩ የመጠየቅ መብት አለው።
➥ ሙስሊሙ ኡምማ በአንድ የኸሊፋ ሥርዓት መተዳደር እንዳለበት ይህ ሐዲሥ ይጠቁማል። ከሥርዓቱ ያፈነገጡትን መፋለምና አደብ ማስያገዛትም ይጠበቅበታል።
➥ ነቢዩ (ﷺ) በዚህ ሐዲስ ትንቢት ተናግረዋል። የተናገሩትም ዝንፍ ሳይል እንዳሉት ሆኗል።
#በሌሎች_መታወክንና_መጎዳትን_ስለመሸከም

አላህ እንዲህ ብሏል፦
“ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)። አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል።” (አል ዒምራን 3፡ 134)

#ሐዲሥ 76 / 648

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ ሰው መልዕክተኛውን (ﷺ)፦ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የቅርብ ዘመዶች አሉኝ። ስቀጥላቸው ይቆርጡኛል። መልካም ስውልላቸው ክፉ ይውሉብኛል፥ እኔ እታገሳቸዋለሁ። እነርሱ ግን አይረዱኝም።” አላቸው። “እንደምትለው ከሆንክ ትኩስ አመድ እያጎረስካቸው ነው። በዚህ ባሕሪ እስከፀናህ ድረስ ከአላህ ዘንድ የሆነ ረዳት ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል” አሉት፡፡ (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

⇛ ታጋሽነት ትልቅ ባሕሪ ነው። ከአላህ ዘንድ ደረጃን ያስገኛል።
⇛ “ትኩስ አመድ ማጉረስ” ማለት እየጎዳሃቸው ነው ለማለት ነው። ምክንያቱም ለእነርሱ መልካም ሲውል እነርሱ ክፉ ሲመልሱለት ወንጀል ይከናነባሉ።
⇛ ክፉ ለሠራ መልካም መመለስ ከታጋሽነትም በላይ የሆነ ባሕሪ ነው። በሸሪዓው ይበረታታል። ተቀናቃኙ ወገን ጥፋቱን አስተውሎ እንዲመለስም ያደርገዋል። ካልሆነ ግን ከአላህ ርቆ ሊቀር ይችላል።
2024/05/12 16:30:42
Back to Top
HTML Embed Code: