Telegram Web Link
Well come /channel ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
የውበት ጀርባው

ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ
ያበባ  ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ
ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ  ስትበሳ
የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ
የዋጠችው ህመም፤  ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ?  
ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ
ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ
ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ስእል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ 
ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ ፤ 👍


|በዕውቀቱ ስዪም| @Ethio_Art
@Daves_Art
🇪🇹ጦብያው🇪🇹
ጦብያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምህ ሰልስ
ያባትክን አደራ መልስ....❤️
@Ethio_Art
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251707601574
ወይም @DaveidArt ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!


ተጨማሪ ስዕሎችን ለመመልከት ከታች ባለው Link ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@Daves_Art 🤏
2024/06/01 02:54:09
Back to Top
HTML Embed Code: